#ህወሃትን ለማዳን ገደል ከምትገቡ እሱን ግደሉና ንሰሃ ግቡ!Seyoum Teshome

#ህወሃትን ለማዳን ገደል ከምትገቡ እሱን ግደሉና ንሰሃ ግቡ!=====================================
ከ1993ቱ የህወሃት መከፋፈል በኋላ አቶ #መለስ_ዜናዊ መላ-ቅጡ ጠፍቷቸው ነበር፡፡ ከዚያ ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር #ዝጉብኝ ክፍል ገብተው “ምን ይሻለናል? እንዴት ከዚህ ጉድ መውጣት ይቻለናል?” በማለት መከሩ፡፡ አቶ በረከት’ሻ “ድርጅታችን ኢህአዴግ ሀገሪቱን የመምራት ስልጣኑን በህዝብ ፍቃድና ምርጫ ላይ የተመሠረተ ማድረግ አለበት” የሚል ምክር ሰጡ፡፡ አቶ መለስም ” ዳይ… በረከት የተግባር ዕቅዱን አዘጋጅ” አሉና ከዝጉብኝ ክፍል ወጡ፡፡ አቶ በረከት እዚያው ቆዩና የ1997ቱን ምርጫ ዕቅድ አዘጋጁ፡፡ ምርጫው እየቀረበ ሲሄድ በረከትና መለስ አፍንጫቸውን አላባቸው፡፡ የምርጫው ዕለት የኢትዮጲያ ህዝብ በአፍ-ጢማቸው ደፋቸው፡፡ የምርጫው እለት ማታ ከተደፉበት ተነስተው የምርጫ ኮሮጆ ሲገለብጡ አደሩ፡፡ ሁለቱ መላጣዎች በፈጣጣው ምርጫውን አጭበረበሩ፡፡ የኢትዮጲያ አምላክ ነገረ-ስራቸውን ተመለከተና የሁለቱንም ጤና አንጨበረረው፡፡ በረከትም ተንጨብርሮ በሼሁ (ምፅ) እርዳት ደ/አፍሪካ ሄዶ ታክሞ ዳነ፡፡ መለስ ዜናዊ ሊታከም በሄደበት ደየመ (“ሙት ወቃሽ” መሆን ጥሩ አይደለም)፡፡ ድርጅታቸው #ኢህአዴግ ደግሞ እንዳይሞት-እንዳይድን ሆኖ ታመመ፡፡ ግማሹ ኢህአዴግ እንደ አቶ በረከት “የአዕምሮ መታወክ ነው” ይላል፡፡ ሌላው አይ እንደ አቶ መለስ “በበታችነትና እብሪት የተሞላ የፍርሃት ደዌ ተጠናውቶት ነው” ይላል፡፡ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ኢህአዴግ እንደ እብድ የሚያደርገውን ነገር አያውቅም ነበር፡፡ በመጀሪያ በ2001 ዓ.ም “ፀረ-ሽብር” የተባለ የፍርሃት መድሃኒት #ከአሜሪካ አስልኮ አስገዛና እሱን መውሰድ ጀመረ፡፡ ይህ መድሃኒት በቀጣዩ አመት 2002 99.6% አይንና ጆሮው ተደፈነ፡፡ የተለየ ሃሳብና አስተያየት በሰማ ቁጥር ድንጋይ እያነሳ መወርወር ጀመረ፡፡ በዚያ ላይ፣ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ፥ የሚዲያ አዋጅ፥ የበጎ አድራጎት ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ፥ …ወዘተ የሚባሉ መድሃኒቶች ሰወስድ በሽታው እየባሰበት ሄደ፡፡ በመጨረሻ በ2007 100% መስማትና ማየት ተሳነው!! ይሄው ከዚያ በኋላ የእውር-ድንብሩን ይሄዳል፡፡ ይሄዳል አያይም፣ ቢጠሩት አይሰማም፡፡ ብቻውን ይሄዳል፣ ማንም አብሮት የለም፡፡ ብቻውን ያወራል ማንም አይሰማውም፡፡ በ2008 #ቄሮ የሚባል “የባህል መድሃኒት” አዋቂ ተጠርቶ መጣና #ኦህዴድ የሚባለው የኢህአዴግ ክፍል ጆሮውን ቆረጠው፣ የአይን ግርዶሹን ያለማደንዘዥ በስለት ገፈፈው፡፡ የኦህዴድ አይንና ጆሮ ሲከፈት #የብአዴን አይን ጭላንጭል ማየት ጀመረ፡፡ የህወሃትና ደህዴን አይን ታውሮ እና ጆሮ ደንቁሮ ደንቆሮ ቀረ፡፡ እና እንዳልኳችሁ ኦህዴድ የአይን ሞራው በጩቤ ሲገፈፍለት ከገደል አፋፍ ላይ እንደ መንጠልጠሉን ተመለከተ፡፡ የህዝቡ ጩኸት ጆሮ ያደነቁራል፡፡ ከዚያ ጅብ እንዳየ አህያ ሽምጥ ጋለበ፡፡ ብአዴን ኦህዴድን ተከትሎ መጋለብ ጀመረ፡፡ ህወሃትና ዴህዴን ግን በነበሩበት የገደል አፋፍ ፈፍ ላይ ተንጠልጠለዋል፡፡ ኦህዴድና ብአዴን ከገደሉ አፋፍ ለመራቅ እያናፉ ሲገልቡ ከህወሃት ጋር የተሳሰሩበት “እትብት” ጠልፎ ጣላቸው፡፡ አሁን ያላቸው አማራጭ ሁለት ነው፦ ከህወሃት ጋር ያላቸውን እትብት በጥሶ መጣል ወይም ከህወሃት ጋር ተያይዞ ከገደል መግባት፡፡ ህወሃትና ደኢዴን እንደው ቢጠሯቸው አይሰሙም፣ ቢወጏቸው አያዩም፤ ቢስቧቸው አይመጡም፣ ቢለቋቸው ገደል ከመግባት አይድኑም፡፡ ስለዚህ ኦህዴድና ብአዴን ያላቸው አማራጭ ህወሃትን ገድሎ መዳን ወይም እሱን ለማድን አጉል ሲታትሩ አብሮ መውደቅ! እንደ እኔ “የማይድን በሽተኛ ለማዳን ከመሞት እሱን ገድሎ ንሰሃ መግባት!” ይሻላል፡፡ ስለዚህ #ኦህዴድና_ብአዴን ህወሃትን ለማዳን ገደል ከምትገቡ እሱን ግደሉትና ንሰሃ ግቡ!

የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደማይቻል ኢህአዴግ አስታወቀ

በስብሰባ ተወጥሮ የከረመው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ በቡድንም ሆነ በተናጠል መንቀሳቀስ እንደሚከለከል አስታወቀ፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አገዛዙ ስልጣን እንዲለቅ የሚጠይቁ የቡድንም ሆነ የተናጠል እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት፤ በቀጣይ ቡድናዊም ሆነ ተናጠላዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደሚከለከል ፓርቲው ይፋ አድርጓል፡፡ ፓርቲው ስብሰባውን ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በስብሰባው መሐል፣ ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ከዚህ በፊት ተሰምተው የማይታወቁ የመፍትኤ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፤ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ መጠናቀቁን ተከትሎ የወጣው መግለጫ ግን፣ ዜጎች በቡድንም ሆነ በተናጠል እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይችሉ ያስጠነቅቃል፡፡

ይህ ማስጠንቀቂያ፤ ዜጎች በጋራ ወይም በቡድን የሚያደርጓቸውን የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ጭምር እንደሚያካትት ታውቋል፡፡ ፓርቲው፣ አድሮ ቃሪያ ከመሆን ውጭ የመለወጥ አቅምም ሆነ ፍላጎት እንደሌለው ከመግለጫው መረዳታቸውን የገለጹ ታዛቢዎች፤ በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ለመከልከል፣ ፓርቲው አስራ ስምንት ቀናት ሙሉ በር ዘግቶ ስብሰባ ማካሄዱ እንዳሳዘናቸውም ታዛቢዎቹ አክለዋል፡፡

የድርጅቱ መግለጫ ይቀጥልና፣ በድርጅታችን ውስጥ የበላይም ሆነ የበታች ፓርቲ የለም ይላል፡፡ ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 21 ቀን 2010 ሲያካሂድ በሰነበተው ስብሰባ ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ በኢህአዴግ ውስጥ የበላይነት ያለው ወይም የበታች ሆኖ የሚኖር ፓርቲ የለም ብሏል፡፡ የድርጅቱ መግለጫ፣ የስርዓት ለውጥ ከተደረገበት ከ1983 ጀምሮ እስከ ዛሬ የዘለቀውን የህወሓት የበላይነት አስተባብሏል፡፡ የአንድ ሀገር ወሳኝ የስልጣን ቦታዎች የሆኑትን መከላከያ፣ ደህንነት እና ሌሎች የጸጥታ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የያዘው ህወሓት ቢሆንም፣ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ ግን ይህን የበላይነት ማስተባበሉን የፖለቲካ ተንታኞች አልተቀበሉትም፡፡

ድርጅቱ ባወጣው በዚሁ መግለጫ ላይ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን የነካካ ቢሆንም፤ አብዛኛው የመግለጫው ክፍል ግን ከዚህ ቀደም ድርጅቱ ከተናገራቸው አባባሎች ተመዘው የመጡ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን እያካሄደ ባለበት ሰዓት በመሐል ባወጣው መግለጫ ላይ፣ በሀገሪቱ ለተፈጠሩ ፖለቲካዊ ቀውሶች እና ግጭቶች ተጠያቂው እኔ ነኝ ብሎ ነበር፡፡ ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ዛሬ የወጣው መግለጫ፣ አዲስ ነገር ያልታየበት እና ፓርቲው ራሱን ጥፋተኛ አስመስሎ ለሌላ የሰልጣን ዘመን መሰናዳቱን የሚያሳብቅ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ፖለቲካዊ ቀውስ ‹‹ጊዚያዊ›› ሲል አሳጥሮ ጠርቶታል፡፡ ሆኖም ህዝብ ሲጠይቅ የቆየው የፖለቲካ ለውጥ፣ የአጭር ጊዜ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ ሲንከባለል የመጣ መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡

‹‹ኢህአዴግ አገራችንን ከመበታተን ቋፍ አውጥቶ አዲስ አይነት ዴሞክራሲያዊ አንድነትና የእኩልነት ትስስር በመገንባት ረጅም ርቀት ተጉዟል፡፡›› ሲል በራሱ መግለጫ ራሱን ያሞካሸው ፓርቲው፤ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ለመገንባት ብዙ ስራዎች መሰራታቸውንም በመግለጫው አትቷል፡፡ በተከተለው ፖለቲካዊ አካሄድ፣ ለዘመናት አንድ ሆነው በኖሩ ህዝቦች መካከል ጥርጣሬ እና አለመተማመን የፈጠረው ኢህአዴግ፣ ሀገራችንን ከመበታተን ቋፍ ታድጊያታለሁ ማለቱ እንዳስገረማቸው፣ የድርጅቱን መግለጫ የተከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በመግለጫው አንደኛው ክፍል፣ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ለመገንባት ደፋ ቀና ሲል መክረሙን ይናገርና፤ ‹‹ብሄረሰባዊና አገራዊ ማንነትን አስተሳስሮ በመገንባት በኩል የታየውን ጉድለት በአፋጣኝና በአስተማማኝ መንገድ መፍታት እንደሚኖርብን ታምኖበታል፡፡›› በማለት በፖለቲካዊ ሴራዉ ምክንያት በአንድ ሀገር ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን መለያየት ለመጥቀስ እንደሞከረ ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ላይ የተለያዩ ጉዳዮችን የጠቃቀሰ ቢሆንም፤ ባጠቃላይ ግን ምንም አዲስ ነገር ያልታየበት፣ ፓርቲው ስልጣን የመልቀቅም ሆነ ራሱን የመለወጥ ፍላቶት እንደሌለው ያረጋገጠ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ገልጸዋል፡፡ ተንታኞቹ አክለውም፤ መግለጫው በርዝመቱም ሆነ በተደጋጋሚ በተገለጹት ቃላቱ አሰልቺ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

BBN Daily News December 30, 2017

ሀተታ ዘ-ህወሀት (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Ethiopia, TPLF officials

እንኳን ተነቦ፡ ገጹን ለመቁጠር የሚያደክመውን፡ በዝባዝንኬ የታጨቀውን፡ በፍሬከርሲኪ ወሬዎች የተጠቀጠቀውን፡ እንደቢንቢ ጆሮ ላይ በሚጮሁ ቃላት የተሞላውን፡ የህወሀትን ሃተታ በኢህአዴግ በኩል ወጥቶ አየሁት። አንብቤ ለመጨረስ ስንት ጊዜ አልጋ ላይ ወጣሁ፡ ስንት ጊዜ ወንበር ቀየርኩ፡ እንዴት ይሰለቻል?! መቼም እንዲህ ዓይነት ኋላቀርና ዘመኑን የማይመጥን ድርጅት የጫነብን ፈጣሪ ምን ሀጢያት ብንሰራ ይሆን? ከመርዘሙ መንዛዛቱ።

የህዝብን ቁጣ ይበልጥ የሚያቀጣጥል በመሆኑ ግን ወደድኩት። በባዶ ተስፋና ልምምጥ የተወሰኑ ወገኖችን ሊያዘናጋ የሚችል መግለጫ ያወጣል ብዬ ገምቼ ነበር። ጭራሽ ዕድሜውን የሚያሳጥር፡ በተጀመረው ህዝባዊ አመጽ ላይ ቤንዚን የሚያርከፈክፍ ሀተታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ህወሀት መንደር በዚህ በመጨረሻው ሰዓት እንኳን የሚያስብ አንድ ሰው መጥፋቱ የሚያስገርም ነው።

ሀተታ ዘ-ህወሀት በአጭሩ ስድስት ዋና ዋና መልዕክቶችን ማስተላለፍ ፈልጓል።

1ኛ- ቢደክመንም፡ ብናጠፋም፡ ብንበሰብስም፡ ብንገለማም፡ ብንዘርፍም፡ ብንባልግም፡ ስልጣን ግን አንለቅም።
2ኛ- የትግራይ የበላይነት የለም ያልናቸሁን ተቀበሉን። ሁላችንም እኩል ነን ተብሎ ተጽፏል። የመሬቱን ዕውነት ተዉትና የተጻፈውን ብቻ ተቀበሉ።
3ኛ- እኛ ያልፈቀድነው ጋብቻ፡ እኛ ያልቀባነው ግንኙነት መርህ አልባ: የተወገዘ፡ የተረገመ መሆኑን አውቃችሁ ተጠንቀቁ
4ኛ- ከስልጣን በታች ባሉት በማንኛውም ጉዳዮች ላይ ልንወያይ ይቻላል። መወያየት ጥሩ ነው። ስልጣኗን መመኘት ግን ያስቀስፋል።
5ኛ- የእኛን ጉዞ ሊያደናቅፉ ከውስጣችን የተነሱት ላይ በቅርቡ እርምጃ ይወሰዳል። ይመነጠራሉ። ይጠራረጋሉ።
6ኛ- ከእንግዲህ ከመንገዳችን ላይ እንቅፋት የሚሆን፡ የሚያሰናክል ነገር ካለ አንታገስም።

የሀተታው ጭማቂ ከዚህ አያልፍም። ህወሀት ተጃጅሏል። ነዳጅ በተነከረ የሳር ጎጆ ቤት ውስጥ ሆኖ ክብሪት እየጫረ ይጫወታል። የመሳሪያ አፈሙዝ ላይ ቁጭ ብሎ ይፎክራል። ይሸልላል።

በአጭሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሀት የጠበቀው ነገር የለም። ሀተታው ጉዳዩ አይደለም። ኳሷ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች፡ በቄሮዎችና ፋኖዎች እግር ስር እንጂ በህወሀት አይደለችም። በህግ የተፈቀደ አመጽ የለም። የህወሀትን ዕውቅና የሚጠብቅ ተቃውሞ አይኖርም። ትግሉ ይቀጥላል። መዳረሻው ግልጽ ነው። ከህወሀት አገዛዝ ነጻ የሆነ የኢትዮጵያ ምድር ለኢትዮጵያውያን ዕውን ይሆናል። ሀተታው የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ይህ እንደሚሆን ደግሞ አልጠራጠርም።

የቻይና ድራጎኖችና የወያኔ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ዘረፋ!!! – ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም


ኢት-ኢኮኖሚ ET-ECONOMY
‹‹የቻይና ድራጎኖችና የወያኔ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ዘረፋ!!!›› ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

አቶ አርዓያ ግርማይ
በኢትዩጵያ የትራንስፖርት መገናኛ አውታሮች፣በኢትዮጵያ ውስጥ 780 ሽህ መኪኖች ይገኛሉ ይህ ማለት ለ100 ሚሊዮን ህዝብ ከመቶ ሰዎች አንድ ሰው መኪና አለው እንደማለት ነው፡፡ ትራንስፖርት መገናኛ አውታሮች ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱት የየብስ ተሸከርካሪ መንገድ፣የምድር ባቡር፣የዓየር መንገድና የውሃ ላይ መንገድ ናቸው፡፡ በኢትዩጵያ በ1983 ዓ/ም የነበረው አጠቃላይ የመንገድ ርዝመት 18,081 ኪሎ ሜትር፣ በ1997 ዓ/ም ወደ 26,550 ኪ/ሜ፣ በ2000 ዓ/ም ወደ 48793 ኪ/ሜ ሲያድግ፣ በ2007 እንደ ኢትዩጵያ አቆጣጠር 105,000 ኪሎ ሜትር ደርሶል፡፡ የትራንስፖርት ዘርፉ ልማት ከአንዱ የሃገራችን አካባቢ ወደ ሌላኛው አካባቢ በአራቱም ማዕዘናት ያለውን በማገናኘት የሚደገገውን የሰዎች እንቅስቃሴ፣የግብርና ምርቶችና የፋብሪካዎች ሸቀጣሸቀጦች ከገጠር ወደ ከተማ፣ ከከተማ ወደ ገጠሪቱ ሃገራችን ለማዳረስ ነው፡፡ በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ወደ ውጭ ለመላክና ወደ ሀገር የሚገቡ የተለያዩ የኢንደስትሪ ሸቀጣ ሸቀጦችን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች፤ በተሸለ ፍጥነትና ተመጣጣኝ ዋጋ ለማዳረስ ዘርፉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ በመንገድ ልማት ቀደም ሲል ዜጎች የመኪና መንገድ ለመድረስ በአማካኝ 10 ሰዓት ሲወስድበሰቸው ነበረው ወደ አንድ ሰዓት ተኩል ለማውረድ ተችሎል፡፡ በዘመነ ዓለም አቀፋዊ ትብብርና ትስስር ዘመን፣የተባበሪት መንግስታት፣ የአለም ባንክና ሌሎች ባንኮች፣ በበለፀጉ ሃገራቶች እርዳታና ብድር በብዙ ቢሊዩን ዶላር የሚገመት ለታዳጊ አገራቶች ተሰጥቶል፡፡ ደሃ ሃገራቶች በትራንስፖርት መገናኛ አውታሮች አማካኝነት በየብስ ተሸከርካሪ መንገድ፣በምድር ባቡር፣በዓየር መንገድና የውሃ ላይ መንገድ አህጉራዊና ክልላዊ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ለማድረግ የታቀደ ግሎባላይዤሽን ፀበል ሆኖ ለአፍሪካ፣ላቲን አሜሪካና ኤሽያ ደሃ ሃገራቶች ውስጥ የፍጥነት መንገዶችና የቀለበት መንገዶች፣ ዘመናዊ የባቡር መሰረተ ልማት፣ የአውሮጵላን ማረፍያዎችና ወደቦች እየተገነቡ እንደሆነ ጥናቶች ይገልፃሉ፡፡በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከ2010/11 እስከ 2014/15 የሚከናወኑት ውስጥ፤

Road transport;- International highways also link Addis Ababa and other cities and towns with neighboring countries such as Kenya, Djibouti, Eritrea, Somalia, South Sudan and Sudan. In 2012/13, the total road network, excluding community roads, reached 52,227 km, out of which 37.3 percent are Federal roads and the remaining 62.7 percent are rural roads with annual growth rate of 10.7 percent. Based on the classification of the road network, about 19,500kms are in the Federal network, asphalt road constituted 37 percent and gravel road 63 percent. All-weather rural road grew by 14 percent per annum constituting 32,727 km of the total road network in 2012/13. In line with the five year Growth and Transformation Plan (GTP), the Government has targeted to increase the total road network to 64,500 km in 2014/15.

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ግርማይ በ2009ዓ/ም የበጀት ዓመት በ32 ቢሊዩን ብር ወጪ 69 አዲስ የመንገድ ግንባታ ኮንትራክቶችን ለመገንባት ዕቅድ አውጥተው በጨረታ ሥራው የተሰጣቸው ተቆራጮች፡፡ ከዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሃገሪቱን ኦኮኖሚ በአንድ አገር ማለትም በሃገረ ቻይና መዳፍ ውስጥ መግባታችንና የአንበሣውን ድርሻ መቀራመቶ ሃገሪቱን በወለድ አግድ የማስያዝ ያህል ይቆጠራል፡፡ ቀሪውም የወያኔ ግብረ-አበሮች የመንገድ ኮንትራት ተቆራጮች ድርሻ ድርሻቸውን በአቶ አርዓያ ግርማይ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለናሙና ያህል፣ የፕሮጀክቱን ስም፣ ክልል፣ የሚሠራው መንገድ በኪሎ ሜትርና የፕሮጀክቱ ወጪ በመመልከት ለመንገድ ኮንትራክተር ድርጅቶች ሠጥተዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ የአንበሳው ድርሻ 70 በመቶ የቻይና መንግሥት ቀሪውን የወያኔ ድርጅቶችና አጫፋሪዎቻቸው እንደተቀራመቱት በመረዳት አንብበው ይፍረዱ፡፡

{1} ቻይና ሬል ዌይ ሰቨንዝ ግሩፕ ጋምቤላ ክልል ኮንትራት አንድ አበቦ 76 ኪ/ሜ መንገድ 960.1 ሚሊዩን ብር
{2} ቻይና ሬል ዌይ ቁ.3፣ ቤንሻንጉል ክልል ፓዊ መገንጠያ ጉባ 69 ኪ/ሜ መንገድ 893.0 ሚሊዩን ብር
{3} የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንያ፣ ሶማሌ ክልል የጨሪቲ-ጎሮበክስ-ጉራዳሞል 90 ኪ/ሜ መንገድ 1.3 ቢሊዩን ብር
{4} የቻይና ውይ ኢንተርናሽናል፣በአፋር ክልል የአፍዴራ-አረብቲ 79 ኪ/ሜ መንገድ 1.36 ቢሊዩን ብር
{5} ቻይና ሬል ዌይ ቁጥር 3፣ ኦሮሚያ ክልል የኢተያ-ሮቤ-ሌሩ 75.6 ኪ/ሜ መንገድ 1.32 ቢሊዩን ብር
{6} ቻይና ሬል ዌይ ቁጥር 3፣ ደቡብ ክልል የጭኮ-ይርጋ ጨፌ 60 ኪ/ሜ መንገድ 889 ሚሊዩን ብር
{7} ቻይና ሬል ዌይ ቁጥር 3 ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ የሙከጡሪ-ኮከብ መስክ 55.4 ኪ/ሜ መንገድ 768.6ሚሊዩን ብር እና ቻያና ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ)1.06 ቢሊዩን ብር
{8} የቻይና ውይ ኢንተርናሽናል ኃ/የ/የ/ማህበር፣ ከየደዬ-ጪራ-ናንሰቦ 73.35 ኪ/ሜ መንገድ 1.68 ቢሊዩን ብር
{9} ቻያና ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ)፣ ቃሊቲ-ቂሊንጦ ኪ/ሜ ያልተገለፀ በ4.7 ቢሊዩን ብር
{10} ሲጂሲኦሲ ግሩፕ፣ኦሮሚያ ክልል መነቤኛ- ሻምቡ ኪ/ሜ መንገድ ያልተገለፀ በ4.58 ቢሊዩን ብር
{11} የቻይና ሬል ዌይ ሰበን ግሩፕ ከሶዶ እስከ ድንቄ 86 ኪሎ ሜትር መንገድ 1.05 ቢሊዮን ብር
{12} የቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን፣የመልካ ጀብዱ ድሬዳዋ ኢንዱስትሪል ፓርክ 7.5 ኪ/ሜትር መንገድ በ298 ሚሊዮን ዶላር ሥራ ተበርክቶላቸዋል፡፡ በአጠቃላይ የቻይና የመንገድ ሥራ ካንፓኒዎች 20 ቢሊዮን 859 ሚሊዮን መንገድ ስራ በኢትዮጵያ ውስጥ በማግኘት የአንበሣውን ድርሻ አግኝተዋል፡፡ ቀሪውን ደግሞ የወያኔ ድርጅቶች ተቀራምተውታል፡፡
{13} ሰናን ኮንስትራክሽን፣ ቤንሻንጉል ክልል የአሶሳ-ደለቲ-ባኒዳ 36 ኪ/ሜ መንገድ 227.4 ሚሊዩን ብር
{14} የንኮማድ ደቡብ ክልል ከሳይ- ማጂ 29 ኪ/ሜ መንገድ 773 ሚሊዩን ብር
{15} ድሪባ ደፈርሻ ጠቅላላ ሥራ ተቆራጭ፣ አማራ ክልል ደብረ ማርቆስ 4.9 ኪ/ሜ መንገድ 212.1 ሚሊዩን ብር
{16} የሩስያ ኢንቨስትስትሮይ ፕሮኤክት፣ ደቡብ ክልል የጭዳ ሶዶ ኪ/ሜ መንገድ ያልተገለፀ 1.17 ቢሊዩን ብር
{17} ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን፣ኦሮሚያ ክልል የግንጪ-ካቺሌ-ጩሊቲ 59 ኪ/ሜ መንገድ 887.7 ሚሊዩን ብር
{18} ማክሮ ጄኔራል ኮንትራክተር፣ ሶማሌ ክልል የፊቅ ሐመሮ ኢሚ 81 ኪ/ሜ መንገድ 819.1 ሚሊዩን ብር
{19} ዩቴክ፣ ኦሮሚያ ክልል ከባሌ-ፊቅ(ሁለታ ሦስት) 57 ኪ/ሜ መንገድ 852.0 ሚሊዩን ብር
{20} መከላከያ ኮንስትራክሽን፣ አፋር ክልል ኤርታሌ-አህመድ ኤላ 54.8 ኪ/ሜ መንገድ 1.7 ቢሊዩን ብር
{21}እንይ ኮንስትራክሽን፣ቤንሻንጉል ክልል የአሶሳ-ዳለቲ 69 ኪ/ሜ መንገድ 731.5 ሚሊዩን ብር
{22} ፉል ጄኔራል ኮንትራክተር፣ሃረሪ ክልል ከባቢሌ-ፊቅናየሂድ-ያሎን 39.8 ኪ/ሜ መንገድ 513.9 ሚሊዩን ብር
{23} ሲጂሲኦሲ ግሩፕ፣ኦሮሚያ ክልል ከፊንጫ-መነቤኛ- ሻምቡ 65.5 ኪ/ሜ መንገድ 999.3ሚሊዩን ብር
{24} ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን፣ የዓለም ከተማ-ደጎሎ ኮንት 85 ኪ/ሜ መንገድ 1.28 ቢሊዩን ብር
{25} ስንሻይን ኮንስትራክሽን፣ ከደጎሎ-ከላላ ኮንት 71 ኪ/ሜ መንገድ 1.29 ቢሊዩን ብር
{26} ዘልዑል ዮሃንስና ባኮራ ትሬዲንግ ወልዲያ እስከ መቐለ 5.3 ኪሎ ሜትር መንገድ 749.9 ሚሊዮን ብር

‹‹የኢትዩጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2010ዓ/ም በጀት ዓመት 45 ቢሊዮን ብር በጀት ከመንግስት የተመደበለት ሲሆን፣ በዓመቱ የ69 አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመፈራረም እቅድ ይዞል፡፡ እንደ አቶ አርዓያ ግርማ እስካሁን የ19 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቁ 19 ፕሮጀክቶች ተፈርመዋል፡፡››1

‹‹(አገር በቀል ኮንትራክተሮች የነገሡበት የ5.6 ቢሊዩን ብር የመንገድ ግንባታ ስምምነቶች) በሚል ርዕስ የቀረበ ዘገባ መሰረት የኢትዩጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ግርማይ ጋር ሰባት የመንገድ ፕሮጀክቶች ኮንትራክተሮች ተፈራርመዋል፡፡

ሱር ኮንስትራክሽን፡-የኢፈርት ድርጅት ሲሆን፣ የሁለቱን የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ጨረታ አሸናፊ ሲሆን ስራ አስኪያጁ አቶ ታደሰ የማነ ሱር ኮንስትራክሽን ከሰባቱ ፕሮጀክቶች ሁለቱን ከ3.3 ቢሊዩን ብር በላይ ያገኘው በአማራ ክልል ከሶሮቃ-አብረሃጂራ-አብደራፊ(92 ኪ/ሜ በ1.43 ቢሊዩን ብር) እና ከአይከል-ዘ-ፋን-አንገርብ(69 ኪ/ሜ በ1.95 ቢሊዩን ብር) ድረስ ያለውን መንገድ ለመገንባት ነው፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣በአማራ ክልል ውስት ሚያልፈውን የበለስ-መካነ ብርሃን 39ኪ/ሜ መንገድ(1.01ቢሊዩን ብር)ና በአፋር ክልል የሚገነባውን የአዋሽ ሚሌ(ኮንትራት አራት)74 ኪ/ሜ (በ381.8 ሚሊዩን ብር) ያለውን መንገድ ለመገንባት ነው፡፡

ሱር ኮንስትራክሽንና የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት የአንበሳውን ድርሻ 4.691800000 ቢሊዩን ብር ተቀራምተዋል፡፡ ሃገር በቀል ነው ክልል በቀል!!! የማንን ክልል መንገድ ለመስራት ጠባቦች ገንቢ ሆነው ለመዝረፍ በጨረታ ስም አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ!!! ትንሽ አታፍሩም፡፡ሌላው ክልል ምንም የተማረ ባለሙያና የመንገድ ኮንትራክተሮች የሉትም ማለት ነው!!!

ቀሪዎቹ የኢትዩጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከአዋሽ-ሚሌ (ኮንትራት ሦስት) 75 ኪ/ሜ በ440 ሚሊዩን ብር፣ማርካን ትሬዲንግ ከአዲስ አበባ-ሞጆ-መቂ 131ኪ/ሜ መንገድ ጥገና በ 210.31 ሚሊዩን ብርና ዩናታን አብይ ጠቅላላ ተቆራጭ ደግሞ የመቂ-ሻሸመኔ-ሃዋሳ መንገድ 146 ኪ/ሜ መንገድ በ 197.1 ሚሊን ብር ለመገንባት ኮንትራት ፈርመዋል፡፡››2

የትግራይ ምሁራን ሊገነዘቡት የሚገባ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ኢኮኖሚ ዋነኛ ኃብቶች በየትኞቹ ክልሎች እንደሚገኙ ህወኃት/ኢህአዴግ ካሰራጨው የዲያስፖራ ድረ-ገፅ በመረዳት የትግራይ ህዝብ ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ትግል እንዲቀላቀል የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባችሁ!!! በኢትዩጵያ የመንገድ ሥራ በአመዛኙ በውጪ አገር በሚገኝ ብድር የሚገነቡ መሆናቸውና ያለበቂ ጥናቶችና ቁጥጥር የሚሠሩ የለብ ለብ ሥራ የሚዘረፉ ናቸው፡፡ “The economic relationship between China and Ethiopia has become stronger through both Chinese direct investment and trade in Ethiopia since the early 2000s. The sum of Chinese contracts in road construction, electricity and telecommunication sectors show a surge in Chinese foreign direct investment in the last few years. Dozens of Chinese firms are currently engaged in the construction of roads throughout the country, managing nearly 70 percent of the roadwork in Ethiopia.”3
ቻይና ሬል ዌይ ሰቨንዝ ግሩፕ የተባለው የቻይና ኩባንያ አሁን ውል ከፈፀመበት የግንባታ ሥራ ሌላ አራት ፕሮጀክቶች ከ3.5 ቢሊዩን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ቻይና ሬል ዌይ ሁለት መንገድ ፕሮጀክቶችን ይዞ እየሰራ ሲሆን፣ ሁለቱ ፕሮጀክቶች ከ2.7 ቢሊዩን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡

ለአዲስ አበባ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት፣‹‹ከቻይና ኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም ባንክ) 230 ሚሊዩን ዶላር ተገኘ በሚል ርዕስ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተረጋግጦል፡፡ በመረጃው መሠረት ለአዲስአበባ የመንገድ ግንባታ ፖሮጀክት 274.1 ሚሊዩን ዶላር የመንገድ ፕሮጀክት ወጪ ከቻይና (ኤግዚም ባንክ) 230 ሚሊዩን ዶላር ብድር ለሰባት ዓመታት የዕፎይታ ጊዜን ጨምሮ በ20 ዓመታት ውስጥ የሚከፈል ሁለት በመቶ ወለድና ጥቅም ላይ ባልዋለ ገንዘብ ላይ በዓመት 0.25 በመቶ የግዴታ ክፍያና ባንኩ ብድሩን ለሚያስተዳድርበት ደግሞ 0.25 በመቶ የክፍያ ግዴታን ይጥላል፡፡››4

ከቃሊቲ የቀለበት መንገድ አደባባይ እስከ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ እና ቃሊቲ- በቡልቡላ እስከ ቂሊንቶ አደባባይ ላለው መንገድ ፕሮጀክቶች የተገኘው ብድር 102.7 ሚሊዩን ዶላር ሲሆን ዓላማው ከቃሊቲ የቀለበት መንገድ አደባባይ እስከ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ ላለው መንገድና ከቃሊቲ የቀለበት መንገድ በቡልቡላ እስከ ቂሊንቶ አደባባይ፣ ላለው መንገድ የሚውል ነው፡፡ የመንገዱ አጠቃላይ ወጪ አራት ቢሊዩን ብር ቢሆንም ከቻይና የተገነው ብድር 50 በመቶ ሚሸፍን ሲሆን ብድሩን ለመመለስ የአምስት ዓመት የችሮታ ጊዜናን ጨምሮ 20 ዓመታት መፈቀድን፣እንዲሁም በዓመት 2.6 በመቶ ወለድና ብድሩን ለማስተዳደር ለባንኩ 0.50 በመቶና በተመሳሳይ 0.50 በመቶ ጥቅም ላይ ባልዋለው ብድር ላይ የከፈልበታል፡፡ የብድር ስምምነት በተለይም የመንገድ ግንባታውን አስመልክቶ መንግስት ኮንትራቱን የሚሰጠው ለቻይና ኩባንያ እንደሆነ፣ብንኩ በቅድሚያ ሳያውቀው ከቻይና ኩባንያ ጋር ውል ማቆረጥም ሆነ የውል ስምምነቱን ማሻሻል እንደማይችል በስምምነቱ ተጠቅሶል፡፡
ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ከዚህ በፊት የተሰጡት ሥራዎች ዝርዝር ውስጥ ደግሞ ፣ድሬዳዋ ደዋሌና የድሬዳዋ ሐረር የመንገድ ፕሮጀክት፣ የማይፀብሪ ዲማ- ዲማ ፍየል ውሃ የመንገድ ፕሮጀክት፣ የሐረር ባይፓስ የመንገድ ፕሮጀክት፣ በጎንደር የአዘዞ-ጎርጎራ መንገድ ፕሮጀክት፣ ከመሐል ሜዳ ዓለም ከተማ የመንገድ ፕሮጀክት ይገኙበታል፡፡ ማክሮ ጄኔራል ኮንትራክተር ከአዳባ አንጋቱ የሚዘልቀውን የመንገድ ፕሮጀክት በ1.24 ቢሊዩን ብር በማሸነፍ ሥራውን ተረክቦ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ገምሹ በየነ ከሃገር ጠፍተዋል፣ኮንስትራክሽን ድርጅታቸው፣ የኢሌሌ ሆቴልና የብዙ ድርጅቶች ባለሃብት በሙስና የተገኘ ኃብት ዛሬ ማን እንደሚቆጣጠረው አይታወቅም የሙስናላ የሌብነት ክስ የአንድ ሰሞን የወያኔ ፋሽን ግዜ አልፎበታል ማንም በዚህ የሚታለል የለም፡፡ ህዝቡ ‹የዓሣ ግማቱ ከአናቱ!!!› ብሎል ለሥርዓት ለውጥ መታገልና የወያኔን መንግሥት ማስወገድ ብቻ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኖል፡፡

1) የመኪና የአስፋልት መንገድ ግንባታ፣ለሁሉም የአየር ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ 71,000 ሽህ ኪሎ ሜትር የአዲስ መንገዶች ግንባታ በየክፍለ ከተሞቹ መገንባትና ከአዲስአበባ አዳማ ስምንት መሄጃና መመለሻ ያላቸው መንገዶች በ6 ቢሊዩን ብር ወጭ የሚገነባ ዘመናዊ መንገድ በተለይ ለውጭና ገቢ ንግድ መተላለፍያነት የሚያገለግል ዘመናዊ መንገድ ግንባታ ያጠቃልላል፡፡ በ2007 እኢአ በጀት 178.6 ቢሊዩን ብር የፀደቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 29 ቢሊዩን ብር ለመንገዶች ግንባታ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ከአዲስ አበባ አዳማ (ናዝሬት) የተገነባው 84.1 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይህ የፍጥነት መንገድ ስፋቱ 31 ሜትር ሲሆን፣ በአንድ ጉዜ በቀኝና በግራ በኩል ስድስት ተሸከርካሪዎችን የማስተላለፍ አቅም አለው፡፡አጠቃላይ የግንባታው ወጪ 11.2 ቢሊዩን ብር መሆኑን፣ከዚህ ውስጥ 57 በመቶው የተሸፈነው ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር ሲሆን ፣ቀሪው 43 በመቶ ደግሞ በኢትዬጵያ መንግስት መሸፈኑ በምረቃው ወቅት ተገልፆል፡፡የመንገዱ ግንባታ ያከናወነው የቻይና ኮሙኒኬሽን ካምፓኒ () የተሰኘ የኮንስትራክሽን ድርጅት ሲሆን፤የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ ቤጂንግ ኤክስፕሬስ ዌይ ሱፐርቪዝን የተባለው አማካሪ ድርጅት አከናውኖል፡፡ በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ የግንባታው ወጭ 6 ቢሊዩን ነበር የተባለው ምን አይነት እቅድ ይሆን የሃገሪቱ ሹማምንቶች የሚያወጡት በእጥፍ ያህል ልዩነት እንዴት ሊኖረው ቻለ፤

ከሞጆ-ሓዋሳ ድረስ የሚገነባው የፍጥነት መንገድ በአንድ ጊዜ አራት ተሸከርካሪዎችን እንደሚያስተናግድና የግንባታ ወጭውም 349 ሚሊዩን 480 ሽህ ዶላር መሆኑን ሰነዱ የገልጻል፡፡ ሞጆ -ሐዋሳ መንገድ 201 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው፣ግንባታው በሁለት ዙር ተከፍሎ የሚገነባ ነው፡፡ የመጀመሪያው ዙር ግንባታ ከሞጆ- ዝዋይ በራሱ በሁለት ተከፍሎ የሚገነባ መሆኑን ለፓርላማ የቀረበው ፣የብድር ማፅደቂያው አዋጅ አባሪ ሰነድ ያብራራል፡፡ የመጀመሪያው ዙር መጀመሪያ ምዕራፍ ከሞጆ- መቂ ሲሆን፣ለዚህ ግንባታ ማስፈፀሚያ የሚውል 128 ሚሊዩን 460 ሽህ ዶላር በዚህ አመት ከአፍሪካ ልማት ባንክ መገኘቱን ሰነዱ ይገልፃል፡፡ ቀሪው መቂ-ዝዋይ መንገድ ግንባታ ደግሞ የኮርያ ኤክስፖርት ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ 100 ሚሊዩን ዶላር መፈረሙን የአዋጁ አባሪ ይገልፃል፡፡
በ2007 እኢአ በጀት አመት ሶስት መንገዶችን ለመገንባት 6 ቢሊዩን 37 ሚሊዩን ብር ወጭ ስምምነት የተፈራረሙት አንደኛው፣ቻይና ሬል ዌይ ሰባተኛ ግሩፕ ሊሚትድ የተረከበው ፕሮጀክት በደቡብ ክልል የሚገኘውን የኦሞ ወንዝ-ተርጫ መንገድ ግንባታን ሲሆን 83.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው የግንባታ ወጭውም 1 ቢሊዩን 67 ሚሊዩን ብር መሆኑ ተገልፆል፡፡ ሁለተኛው ቻይና ፈርስት ሃይ ዌይ ኢንጂነሪንግ ኮ ሊሚትድ የተባለ ሲሆን በአማራ ክልል የቢልባላ-ሰቆጣ መንገድ ፕሮጀክት ሲሆን መንገዱ 98.7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው የግንባታው ወጭ 2 ቢሊዩን 40 ሚሊዩን ብር መሆኑ ተገልፆል፡፡ ሦስተኛው ደግሞ የህወሃት መንግስታዊ ዘርፍ ለሆነው በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ለተዋቀረው መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሆን በአፋር ክልል የሚገኘውን ከዲቸቶ-ጋላፊ መገንጠያ ኤሊዳር-በልሆ ድረስ ያለውን 80.5 ኪሎ ሜትር መንገድ የግንባታ ወጭ 2 ቢሊዩን 66 ሚሊዩን ብር እንደሆነ የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሔ ተገልፆል፡፡

ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች የሚገኙ ከተሞች በ2015 እኤአ የመንገድ ትስስር 25 በመቶ እንዲደርስ በሚሊንየም ልማት ጎል ተወስኖል፡፡ ሆኖም የአዲስ አባበአ ከተማ አጠቃላይ የመንገድ ኔትወርክ ባለፈው ኣመት ከነበረበት 15.64 በመቶ ወደ 17.5 በመቶ መድረሱን የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቆል፡፡በ2006 ዓ/ም 521 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ሲገነባ ከዚህ ውስጥ 176 ኪ/ሜ አስፋልት፣ 145 ኪ/ሜ የጠጠር፣የኮብልስቶን 202 ኪ/ሜ መሆኑ ተገልፆል፡፡ በዚህም መሠረት አጠቃላይ ከተማዋ መንገድ ትስስር በ2005 ዓ/ም ከነበረበት 4,148 ኪሎ ሜትር ወደ 4,671 ኪ/ሜ በያድግም የተባለው ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡ ለዚህም ዋና ምክንያት የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን በ2006 ዓ/ም 10.3 ቢሊዩን ብር በጀት ጠይቆ የተፈቀደለት 3.8 ቢሊዩን ብር ብቻ ነበር፡፡

World Bank provides 6.2 bln.birr loan:-The ministry of finance and economic development and the world bank signed an agreement providing for 6.2 billion birr loan to finance the 258 kms Nekemte- bure road upgrading project and assist in Ethiopia road authority institutional capacity building.Since the launching of the program, the bank has provided 1.70 billion USD for upgrading and expansion of 3,725 kms of road network which constitutes about six percent of the country’s classified road network.

ለቻይናዎች ጭፍራ፣ለሱዳን ቡችላ
አይገዛም ህዝቡ፣ከዛሬ በኃላ
ለአንባገነን መንግሥት፣ህዝቡን ላልወከለ
አይገዛም ህዝቡ ሳለ እየታገለ!!!
ለዘረኛ መንግሥት፣ህዝቡን ለከፈለ
አይገዛም ጦቢያው፣ሳለ እየታገለ!!!
አይገዛም! አይገዛም! አይገዛም!

ምንጭ
{1} ሪፖርተር ጋዜጣ ታህሣስ 18 ቀን 2010
{2} በሪፖርትር ጋዜጣ፣ግንቦት 21ቀን 2008ዓ/ም
{3} Ethiopia is on a path to become Africa’s China in more ways than one, /by Dee Abdella
{4} ታህሣሥ 9 ቀን 2009 ዓ/ም ሪፖተር ጋዜጣ

ትንንሾቹን ሳይሆን ትልቁን ማየት l በቶማስ ሰብስቤ


በወቅታዊ የሀገራችን ፖለቲካ በሚፈጠር ትንንሽ ለውጦችና አካሄዶች መመልከት ዘላቂና ተፈላጊ ለውጥ አያመጣም።ኢትዮጵያ የምትሻው ትልቅ ለውጥ ሆኖ ሳለት በትንሹ መዳከር የውድቀት ብቻ ሳይሆን የሀገር ክህደትም ነው።በትንሽ የሚታዮ ለውጦችና አካሄዶች መስመጥ ኢትዮጵያን አለማወቅ ነው።

ምንም የህግ የበላይነት በሌለበት ሀገር በህግ የበላይነት ባለመኖሩ ስለተፈጠሩ ክፍተቶች ማውራት ሳይሆን የህግ የበላይነት የሚዘረጋ ስርዓት ማፍጠር ተገቢ ነው ፤ ሰው ሀሳቡን እንዳይሰጥ ያደረገው ስርዓት ማስታመም የሀሳብ ነፃነት እንዳይመጣ መስራት ነው።በተለይ በአሁን ጊዜ የሀሳብ ነፃነት በስርዓት ለውጥ የሚረጋገጥ ነው ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ያጎራቸው የፀረ ሽብር ህግ እንዳይመለስ ማጥፋት ነው እንጂ ትንንሾቹን ንፅሃን ፖለቲከኞችና ግለሰቦችን እስር አይቶ መጮህ ዋጋ ብዙ አይደለም።የትኛውም የህዝብ ጩህት የታሰሩትን ቢያስለቅቅ የሸብር ህጉ ካልተነሳ በስተቀር የተለቀቁት እንደማይመለሱና ሌሎች እንደማይገቡ ዋስትና የለንም።ለዚህም ነው ትልቁን ካልጣልን አይነተኛ ለውጥ የለም።

በብሄር ማነንት የሚመራ ዘረኝነት ሰርዓትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ህውሃት ና ኢህአዴግን ወደ መጡበት ደደቢት መመለስ እንጂ ዘረኛ ስርዓት ማስታመም መፍትሄ የአለውም።

ይህ ብቻ ሳይሆን አንዳንዶች በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የአባላቱን መለያየት ማለትም የለማና ገዱ ከህወሃት የበላይነት ለመላቀቀ እያደረጉት ያለውን ጥረት እንደ ለውጥ ጫፍና የለማና ገዱ አካሄድን እያጨበጨቡና እያሽቃበጡ ሲያወድሱ ስታይ ይህ ውዳሴ ጤናማ ብቻ ሳይሆን እንዚህ ሰዎች ምንም እንደሚቃወሙና ምን እንደሚፈልጉ አያቁም እንዴ ያስብላል! አይደለም ከፍተኛ ባለስልጣን ሆኖ ተራ የኢህአዴግ ድርጅት አባል ፓርቲው እንዲወድቅ አይሰራም ፤ ቢሰራም አይሳካለትም።

በኢህአዴግ ውስጥ ያለ የትኛውም ባለስልጣን የፈለገ ቢንጠራራ ፣የፈለገ የግል ክህሎትና የላቀ አስተሳሰብ ቢኖረው ሰርዓቱ አያራምደውም።ኢህአዴግ በግለስብ የሚለወጥ ዝቅጠት ላይ ሳይሆን በህዝብ እምቢታ የሚለወጥ ስርዓት ነው።ስርዓቱ የመጠቀ ምሁራንን አደድቦ የሚያስቀምጥና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ድርጅታዊ አስተሳስብ ያሰረው ነው።ስለዚህም እንደፈለገ የሚወራጭ ግለስብ ቢፈጠር የፖለቲካ ፍጆታ እንጂ አይነተኛ ለውጥ አያመጣም።ይበልጥ ገዱና ለማን ማሞካሸትና አይዞን ስትሉ ኢህአዴግ በመልሶ ማጥቃት ስልት ተቃዋሚውን በራሱ ግለስቦች ፍቅር እያሰረ ነው።ኢህአዴግ በህዝብ የሚወድቅ ተራ ድርጅት ነው።

ከትንሽ ልማት ብዙውን ጥፋት ማየት ፣ ከትንሾች ታሳሪዎች አሳሪውን ማጥፋት ፣ ከመጠነኛ ፍርህ ወደ አይነተኛ ፍትህ ፣ ከመሰል ምርጫ ነፃ ምርጫ ፣ የሀሳብ ነፃነት ከታገዱት ከአጋቹ ጋር መለያየት።

ዘረኝነት የጠላ ዘረኛው ስርዓት አባረው።ሀገርህ ስትካድ ከከፋ ከጅውን ልኩን አሳየው።በሰው እንጂ በዘር አልጠራም ካልክ ስርዓቱን በቃ በለው።የዛኔ ነው ደስታም ያለው።

ራስህን ነፃ መውጣት ለሁሉም መልስ አለው።አንተ ወይም አንቺ ነፃ ውጣ።ሀሳብን በነፃነት ለመናገር ነፃ ነን።የመጀመሪያው ትልቅ ስራ ከዘረኛው ኢህአዴግ ስርዓትና አስተሳሰብ ነፃ መውጣ ነው።ምን አይነት ትንንሽ ለውጦች ትልቁን ችግርህ አይሸፍንህ።ትንንሽ ለውጦች ጊዜያዊ ናቸው።ትኩረታች ዘላቂያዊ ከሆነ ትልቁ ጥያቄዎች እንፍታ።ከዚህ ውጪ መንገድ የለም።ትልቁ ጥያቄ ሀገር ፣ነፃነት፣ እኩልነት ፣ፍትሃዊነትና ዲሞክራሲ ነው።ይህ ደሞ በኢህአዴግ ውድቀት በሃላ ህዝብ የሚፈጥረው ስርዓት ንው።

ትንቢት እና ትዕቢት – ከተማ ዋቅጅራ

Sponsored by Revcontent
If You Own a Computer You Must Try This Game
Vikings: War of Clans

ሕወሃት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም ተባለ

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 20/2010)

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሕገ መንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ እንደማይቀር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ።

ዶክተር ነጋሶ እንዳሉት ኢሕአዴግ እንደ ፓርቲ የመቀጠልና ሀገር የማስተዳደር ሕልሙ በማክተም ላይ ነው።

የኢትዮጵያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ወቅታዊውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።

እናም ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት ሕዝብ ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ ባለመስጠቱ ሀገሪቱ አደጋ ላይ ወድቃለች ።

ገዥው ፓርቲም ባሉበት ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች የተነሳ ሀገር ማስተዳደር አቅቶታል ነው ያሉት።

ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ ቢልም ያለውን በተግባር መተርጎም እንዳቃተውም ዶክተር ነጋሶ ገልጸዋል።

የሕዝብ ጥያቄዎችን በአግባቡ አለመመለሳቸውም አሁን በሀገሪቱ ያለውን ችግር ለማባባስ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

እንደ ዶክተር ነጋሶ ገለጻ የሕዝብን ጥያቄ መፍታት ባለመቻሉም ኢሕአዴግ በሕገመንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀሬ ይሆናል።

እርሳቸው እንደሚሉት ኢሕአዴግ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ያለውን ችግር ብቻውን ሊፈታው አይችልም።

እናም በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመምከር ምላሽ መስጠጥ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ይላሉ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን ማድረግ ካልቻለ ኢሕአዴግ እንደ አንድ ፓርቲ የመቀጠልና ሀገር የማስተዳደር ሕልሙ ጨርሶ ያከትማል።