ትንንሾቹን ሳይሆን ትልቁን ማየት l በቶማስ ሰብስቤ


በወቅታዊ የሀገራችን ፖለቲካ በሚፈጠር ትንንሽ ለውጦችና አካሄዶች መመልከት ዘላቂና ተፈላጊ ለውጥ አያመጣም።ኢትዮጵያ የምትሻው ትልቅ ለውጥ ሆኖ ሳለት በትንሹ መዳከር የውድቀት ብቻ ሳይሆን የሀገር ክህደትም ነው።በትንሽ የሚታዮ ለውጦችና አካሄዶች መስመጥ ኢትዮጵያን አለማወቅ ነው።

ምንም የህግ የበላይነት በሌለበት ሀገር በህግ የበላይነት ባለመኖሩ ስለተፈጠሩ ክፍተቶች ማውራት ሳይሆን የህግ የበላይነት የሚዘረጋ ስርዓት ማፍጠር ተገቢ ነው ፤ ሰው ሀሳቡን እንዳይሰጥ ያደረገው ስርዓት ማስታመም የሀሳብ ነፃነት እንዳይመጣ መስራት ነው።በተለይ በአሁን ጊዜ የሀሳብ ነፃነት በስርዓት ለውጥ የሚረጋገጥ ነው ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ያጎራቸው የፀረ ሽብር ህግ እንዳይመለስ ማጥፋት ነው እንጂ ትንንሾቹን ንፅሃን ፖለቲከኞችና ግለሰቦችን እስር አይቶ መጮህ ዋጋ ብዙ አይደለም።የትኛውም የህዝብ ጩህት የታሰሩትን ቢያስለቅቅ የሸብር ህጉ ካልተነሳ በስተቀር የተለቀቁት እንደማይመለሱና ሌሎች እንደማይገቡ ዋስትና የለንም።ለዚህም ነው ትልቁን ካልጣልን አይነተኛ ለውጥ የለም።

በብሄር ማነንት የሚመራ ዘረኝነት ሰርዓትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ህውሃት ና ኢህአዴግን ወደ መጡበት ደደቢት መመለስ እንጂ ዘረኛ ስርዓት ማስታመም መፍትሄ የአለውም።

ይህ ብቻ ሳይሆን አንዳንዶች በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የአባላቱን መለያየት ማለትም የለማና ገዱ ከህወሃት የበላይነት ለመላቀቀ እያደረጉት ያለውን ጥረት እንደ ለውጥ ጫፍና የለማና ገዱ አካሄድን እያጨበጨቡና እያሽቃበጡ ሲያወድሱ ስታይ ይህ ውዳሴ ጤናማ ብቻ ሳይሆን እንዚህ ሰዎች ምንም እንደሚቃወሙና ምን እንደሚፈልጉ አያቁም እንዴ ያስብላል! አይደለም ከፍተኛ ባለስልጣን ሆኖ ተራ የኢህአዴግ ድርጅት አባል ፓርቲው እንዲወድቅ አይሰራም ፤ ቢሰራም አይሳካለትም።

በኢህአዴግ ውስጥ ያለ የትኛውም ባለስልጣን የፈለገ ቢንጠራራ ፣የፈለገ የግል ክህሎትና የላቀ አስተሳሰብ ቢኖረው ሰርዓቱ አያራምደውም።ኢህአዴግ በግለስብ የሚለወጥ ዝቅጠት ላይ ሳይሆን በህዝብ እምቢታ የሚለወጥ ስርዓት ነው።ስርዓቱ የመጠቀ ምሁራንን አደድቦ የሚያስቀምጥና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ድርጅታዊ አስተሳስብ ያሰረው ነው።ስለዚህም እንደፈለገ የሚወራጭ ግለስብ ቢፈጠር የፖለቲካ ፍጆታ እንጂ አይነተኛ ለውጥ አያመጣም።ይበልጥ ገዱና ለማን ማሞካሸትና አይዞን ስትሉ ኢህአዴግ በመልሶ ማጥቃት ስልት ተቃዋሚውን በራሱ ግለስቦች ፍቅር እያሰረ ነው።ኢህአዴግ በህዝብ የሚወድቅ ተራ ድርጅት ነው።

ከትንሽ ልማት ብዙውን ጥፋት ማየት ፣ ከትንሾች ታሳሪዎች አሳሪውን ማጥፋት ፣ ከመጠነኛ ፍርህ ወደ አይነተኛ ፍትህ ፣ ከመሰል ምርጫ ነፃ ምርጫ ፣ የሀሳብ ነፃነት ከታገዱት ከአጋቹ ጋር መለያየት።

ዘረኝነት የጠላ ዘረኛው ስርዓት አባረው።ሀገርህ ስትካድ ከከፋ ከጅውን ልኩን አሳየው።በሰው እንጂ በዘር አልጠራም ካልክ ስርዓቱን በቃ በለው።የዛኔ ነው ደስታም ያለው።

ራስህን ነፃ መውጣት ለሁሉም መልስ አለው።አንተ ወይም አንቺ ነፃ ውጣ።ሀሳብን በነፃነት ለመናገር ነፃ ነን።የመጀመሪያው ትልቅ ስራ ከዘረኛው ኢህአዴግ ስርዓትና አስተሳሰብ ነፃ መውጣ ነው።ምን አይነት ትንንሽ ለውጦች ትልቁን ችግርህ አይሸፍንህ።ትንንሽ ለውጦች ጊዜያዊ ናቸው።ትኩረታች ዘላቂያዊ ከሆነ ትልቁ ጥያቄዎች እንፍታ።ከዚህ ውጪ መንገድ የለም።ትልቁ ጥያቄ ሀገር ፣ነፃነት፣ እኩልነት ፣ፍትሃዊነትና ዲሞክራሲ ነው።ይህ ደሞ በኢህአዴግ ውድቀት በሃላ ህዝብ የሚፈጥረው ስርዓት ንው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s