ሀተታ ዘ-ህወሀት (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Ethiopia, TPLF officials

እንኳን ተነቦ፡ ገጹን ለመቁጠር የሚያደክመውን፡ በዝባዝንኬ የታጨቀውን፡ በፍሬከርሲኪ ወሬዎች የተጠቀጠቀውን፡ እንደቢንቢ ጆሮ ላይ በሚጮሁ ቃላት የተሞላውን፡ የህወሀትን ሃተታ በኢህአዴግ በኩል ወጥቶ አየሁት። አንብቤ ለመጨረስ ስንት ጊዜ አልጋ ላይ ወጣሁ፡ ስንት ጊዜ ወንበር ቀየርኩ፡ እንዴት ይሰለቻል?! መቼም እንዲህ ዓይነት ኋላቀርና ዘመኑን የማይመጥን ድርጅት የጫነብን ፈጣሪ ምን ሀጢያት ብንሰራ ይሆን? ከመርዘሙ መንዛዛቱ።

የህዝብን ቁጣ ይበልጥ የሚያቀጣጥል በመሆኑ ግን ወደድኩት። በባዶ ተስፋና ልምምጥ የተወሰኑ ወገኖችን ሊያዘናጋ የሚችል መግለጫ ያወጣል ብዬ ገምቼ ነበር። ጭራሽ ዕድሜውን የሚያሳጥር፡ በተጀመረው ህዝባዊ አመጽ ላይ ቤንዚን የሚያርከፈክፍ ሀተታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ህወሀት መንደር በዚህ በመጨረሻው ሰዓት እንኳን የሚያስብ አንድ ሰው መጥፋቱ የሚያስገርም ነው።

ሀተታ ዘ-ህወሀት በአጭሩ ስድስት ዋና ዋና መልዕክቶችን ማስተላለፍ ፈልጓል።

1ኛ- ቢደክመንም፡ ብናጠፋም፡ ብንበሰብስም፡ ብንገለማም፡ ብንዘርፍም፡ ብንባልግም፡ ስልጣን ግን አንለቅም።
2ኛ- የትግራይ የበላይነት የለም ያልናቸሁን ተቀበሉን። ሁላችንም እኩል ነን ተብሎ ተጽፏል። የመሬቱን ዕውነት ተዉትና የተጻፈውን ብቻ ተቀበሉ።
3ኛ- እኛ ያልፈቀድነው ጋብቻ፡ እኛ ያልቀባነው ግንኙነት መርህ አልባ: የተወገዘ፡ የተረገመ መሆኑን አውቃችሁ ተጠንቀቁ
4ኛ- ከስልጣን በታች ባሉት በማንኛውም ጉዳዮች ላይ ልንወያይ ይቻላል። መወያየት ጥሩ ነው። ስልጣኗን መመኘት ግን ያስቀስፋል።
5ኛ- የእኛን ጉዞ ሊያደናቅፉ ከውስጣችን የተነሱት ላይ በቅርቡ እርምጃ ይወሰዳል። ይመነጠራሉ። ይጠራረጋሉ።
6ኛ- ከእንግዲህ ከመንገዳችን ላይ እንቅፋት የሚሆን፡ የሚያሰናክል ነገር ካለ አንታገስም።

የሀተታው ጭማቂ ከዚህ አያልፍም። ህወሀት ተጃጅሏል። ነዳጅ በተነከረ የሳር ጎጆ ቤት ውስጥ ሆኖ ክብሪት እየጫረ ይጫወታል። የመሳሪያ አፈሙዝ ላይ ቁጭ ብሎ ይፎክራል። ይሸልላል።

በአጭሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሀት የጠበቀው ነገር የለም። ሀተታው ጉዳዩ አይደለም። ኳሷ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች፡ በቄሮዎችና ፋኖዎች እግር ስር እንጂ በህወሀት አይደለችም። በህግ የተፈቀደ አመጽ የለም። የህወሀትን ዕውቅና የሚጠብቅ ተቃውሞ አይኖርም። ትግሉ ይቀጥላል። መዳረሻው ግልጽ ነው። ከህወሀት አገዛዝ ነጻ የሆነ የኢትዮጵያ ምድር ለኢትዮጵያውያን ዕውን ይሆናል። ሀተታው የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ይህ እንደሚሆን ደግሞ አልጠራጠርም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s