የህወኣት አርማጌዶን – መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር)

“በደንብ መዝነቡ አይቀርም”። አለ ትኩር ብሎ እየተመለከተኝ።  በዚህ ሁኔታ ሳየዉና ሳዳምጠዉ ሁሌም ዉስጤ ይደነግጣል። ብዙ ጊዜ ትንቢት ከሚመስለዉ ምልከታዉ ጋር የሚያስፈራና እልፎ አልፎም የሚያሳዝነዉ ሳቤላዊ  የንግግር ቃናዉ በቀላሉ ትኩረት ይስባል። ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ “ነጎድጓዱ በአራቱም አቅጣጫ እየተሰማ ነዉ። ንፋሱም ተራዉን ሳይጠብቅ እዚህም እዚያም ሽዉ እያለ ነዉ። ሰዉና እንሰሳቱም አምሳያቸዉን እየፈለጉና እነርሱን ከሚመስላቸዉ ጋር በመጠጋት  ሊመጣ ያለዉን ዉሽንፍር በጋራ ለመጋፍጥ ወዲህ ወዲያ ሲሉ እየታየ ነዉ። መጪዉ ማህበልና ጎርፍ የስንቱን ሕይወት እንደሚያጠፋ ማወቅና መገመት ቢያስቸግርም በርካታ እናቶች ግን በልጆቻቸዉ በድን ላይ ተቀምጠዉ ደግመዉ ደጋግመዉ እንዲያለቅሱ የተፈረደባቸዉ ይመስላል። ብዙ ስቃይና መከራም ይሆናል” አለ ሰለሞን በሁለት ጣቶቹ ግንባሩን በስሱ እያሻሸ።

ምንም ነገር ተናግሬ ላቋርጠዉ ስላልፈለኩ በዝምታ ዓይን ዓይኑን መመልከቴን ቀጠልኩ። እሱም አሳቤ የገባዉ ይመስል ንግግሩን ቀጠለ “የሚያስፈራ ዘመን ነው። እናት የልጇን ሬሳ መቅበር አትችልም፤ አባትም ለሚስትና ለልጆቹ መከታ መሆን ላይችል አቅም ያጣል፤ ባልንጀሮችም እንደባላንጣ ይተያያሉ፤ ሕፃን አዛዉንቱ የሚሰማቸዉ ላይኖር የስቃይ ጣራቸዉን ያሰማሉ። መጪዉ ዘመን አስፈሪ ነዉ። ትዉልዱ ከማያዉቁት መልሃክ የሚያዉቁት ሴይጣን ከሚለዉ ብሄል ርቆ ብዙ ተጉዟል። በለዉጥ እርግዝናና ምጥ ዉስጥ ባለ ትዉልድ ዙሪያ እርኩስ መንፈስ የሕፃኑን ጉሮሮ ሊደፍን አቆብቁቧል። ስለዚህ ትዉልዱም ነክሶ የማያኝከውን አዉሬ ሊጋፈጠዉ ተዘጋጅቷል።” አለ

አሁንም መልስ አልሰጠሁትም። ይልቁንም እያስፈራዉ ያለዉ ነገር እኔንም ያስፈራኝ ጀመር።

ሰለሞንም መናገሩን ቀጠለ “እየመጣ ባለ ዉሽንፍር ዉስጥ አብሮ ሊመጣ የሚችል እንግዳ መልሃክ ብቻ ሳይሆን ሴይጣንም ቢሆን እንኳ ይህ ሕዝብ ሊቀበለዉ የተዘጋጀ ይመስላል። ቤት የሕግዚሃብሔር መባሉ ሊቀር ተቃርቧል። አስፈሪ ዘመን ነዉ። ቤተ ክርስትያን በዲያቢሎስ ሰንሰለት ተጠፍራ አርማጌዶንን የምትናፍቅ ሆናለች። የልጆቹን እንባ ከማበስ ይልቅ ቤተ መቅደስ ሆዳቸዉ ቀንድ በሆነባቸዉ ጋኔኖች ተሞልታለች። የሕግዚሃብሔር መንፈስ የታሰረ ይመስል እርኩስ መንፈስ በየቦታዉ መልከስከስ ብቻ ሳይሆን ለመጨረሻዉ አርማጌዶን ዝግጅት ዘጠኝ ቀዳዳ መጫሚያዉን  እየወለወለ ይገኛል። ይህም ሆኖ ተዓምራት በዝቷል። አላዛር ብቻዉን ላይሆን ሌሎችም ከሞት ተነስተዋል የሚል የጠንቋይ ወሬ በከተማይቱ ይሰማል። መንፈስ ከራሱ ጋር አይጣላምና ሴሰኞችና ቀማኞች የከተማይቱን ቤተ መቅደስ ይፈነጬበታል። በልጇ ሬሳ ላይ ተቀምጣ በምታነባ ሴት መንደር ብዙ ቅዱሳንና ነቢያት እንደ ባሕር አሳ ተበራክተዋል። የቆሰለዉን አዉሬ መገሰፅን ባይፈቅዱም ትንቢትን አብዝተዋል ” አለና ሽቅብ በደመና የጠቆረዉን ጨፍጋጋ ሰማይ ከተመለከተ በሃላ “ጉድጓድ የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅትርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች” ሲል  ሁሌም እየደጋገመ የሚለዉን የመክብብን ቅዱስ ቃል አነበነበ።

እኔም ከንግግሩ በላይ የፊቱ ገፅታ ላይ እያነበብኩ ያለሁት ሐዘን የበለጠ አስፈራኝ። ያኔ ልጅ ሆኜ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በፍቃዱ ተክለማርያም ኪናዊ አንደበት የሰማሁትን የቴዎድሮስ የሚያስፈራ ድልና ሽንፈት፡ ማግኘችትና ማጣት እርግማንና ንዴት  እንዲሁም የሞት አፋፍ ጣርና ቁጭት ስሰማ የፈራሁትን ያህል ፈራሁ።

ተስፋ ባጣ ምድረ በዳ
የአንድ ዕምነት ይሆናል ዕዳ
እናም ትንፋሼ አለሆነሽም …..ሆኜብሽ መራር መካሪ
እሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ።
እዉነት ላንቺ መች ተስፋ ናት ጉስቁል ልሳንሽን ነክሳሽ
ክንድሽን ካዛለ ቅርስሽ መጠላለፍ ሲሆን ዕጣሽ…

አዎን! በልጅነቴ የፈራሁትን ያህል አሁንም ምራቅ ዉጬ በሰሎሞን ቁጭት ፈራሁ። ጀግንነትን ሰዉ በማዳን ሳይሆን የንፁሐንን ሬሳ ብዛት አልያም ምርኮኛን በማዋረድ  በሚተረጉሙ መዓይማን እርኩስ መንፈስ ሕዝቤ መከበቡ ሲታወቀኝ ንግግሩ ይበልጥ አስፈራኝ።  በዚህች ሰዓት በጣር የሚቃትተዉ የህወኣት እርኩስ መንፈስ የመጨረሻዉን መርዙን ሊተፋ በአዲስ አበባና መቀሌ እየተወራጨ መሆኑም አሳሰበኝ ።  በቅርቡ ‘ጥቂት መስዋህትነት መክፈል ይኖርብናል’ ያለው  ደብረ ‘ሴይጣን’ ያኔ አዉዜን ላይ በቅርቡም ሶማሌና ኦሮሚያ ላይ ያደረገዉን አይነት የንፁሐን ደም ማፍሰስ መዘጋጀቱን ሳስብ በአጭሩ ሊቀጭ የተዘጋጀዉ የሕፃን አዛዉንቱ መንፈስ ጩኸት ዳግም ከመቅደላ የሚሰማ መሰለኝ።

መልመጥመጡ መሽቆጥቆጡ መስሎሽ ድንገት የሚያዋጣሽ
የእኔ እዉነት ሆነብሽ እዳሽ።
ወራሪም ፈጣሪን ላያቅ
የጣለዉም በስሏል እንጂ ወድቋል ብሎ ግፉ ላያልቅ
መች ትተርፊያለሽ ኢትዮጲያ ህዋስሽ አብሮኝ ካልሰራ….
አንገትሽ ብቻ መቅደላ አፋፍ ወጥታ ብታበራ
የቀረዉ ሰራ አካላትሽ በየጥሻዉ ተዘርሮ
ካባት በወረሽዉ ንፍገት ነፍዞ ደንዝዞ ተቀብሮ…..በአጉል ወጌሻ ታጅሎ
እኔን ለጥንባሳ ጥሎ…

ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ “ቢሆንም ተስፋ ይታየኛል። መሪዉን ለጥንባሳ የመጣያዉ ጊዜ አብቅቷል። ይህንንም ጥንባሳዉም ተረድቶታል። በመሆኑም መጪዉ አርማጌዶን ይሆናል ። ሁላችንም ማወቅ ያለብን እዉነት ደግሞ በመጨረሻ ሁልጊዜ አሸናፊ የሚሆነዉ የተቀደሰ መንፈስ ነዉ። ያ ባይሆን ኖር የሰዉ ልጅ ፍጥረት ከንቱ ይሆን ነበር። አርማጌዶንም የዚህ ዕውነት ምሳሌና መገለጫ ነዉ። ጥያቄ መሆን ያለበት ግን የእያንዳንዳችን ዉሳኔ ነዉ። ወደድንም ጠላንም ዉስጣችን ካለ መንፈስ ተመሳሳይ መንፈስ ጋር እናብራለን። ስለዚህ እራሳችንን እንመረምር ።” አለና በድንገት እጄን ይዞ  ” ዛሬ ሰኞ ነዉ። ሕሁድም ትንሳኤ ይሆናል ። በዕለተ ዓርብ ግን ስቃይና መከራ ይከፋል።

ኦጋዴንና የሀገር አንድነት ሥጋቶች   (ከዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ)

ምዕራፍ አንድ

የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ አዲስ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመሸጋገር ትግሉን ባጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት አገር ውስጥ ያለውን ክፍተት፣ ሁከትና የመንግስትን መዳከም በዓይነ ቁራኛ የሚከታተሉ የውጭ ጠላቶች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አንድነታችንን ለማደፍረስ በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ በመግባት የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈፀም የሚሞክሩ ብዙዎች አሉ፡፡ እነዚህንም ሁኔታዎች መከታተልና ጥንቃቄ ማድረግ ለውጡን የሚያራምዱ ድርጅቶችና ግለሰቦች ኃላፊነት ነው፡፡ እኔና የመሳሰሉ በተሞክሮና በእድሜ የበለፀጉ ደግሞ ከምናየው፣ ከምናነበውና ከምናጠናው ተነስተን ይህቺን ኢትዮጵያን የሚረከበው አዲስ ትውልድ ካለፈው ስተት እንዲማር ይቺ የኢትዮጵያ ምድር ለራሳቸው ባልኖሩ፣ ኢትዮጵያን አስቀድመው ካለፉ ጀግኖች አባቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን ደምና አጥንት የከበረች መሆኑን ዘወትር አስታውሰው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ ጥበብና ጥንቃቄ እንዳይጐድላቸው ማሳሰብ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ከውጪ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን መረዳት የሚቻለው በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ባለው የጂኦ ፖለቲካ አሰላለፍና ክልል ውስጥ ነው፡፡ (የአገር ደህንነት ጥያቄዎች፣ “ያሉና የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሥጋቶች” በሚል ርዕስ ክህደት በደም መሬት በሚለው መጽሀፌ ላይ ዘርዝሬ አለሁኝ)፡፡

በአሁኑ ወቅት አዲስ መነጋገሪያ ርዕስ እንዲሆን የማቀርበው የኦጋዴንን ሁኔታ ነው፡፡

ዛሬ በሱማሌና በኦሮሞ ክልል የተፈጠረው ግጭትና የተፈፀመው ጭፍጨፋ የወያኔ ሴራ መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ተገልጿል፡፡ የወያኔ መንግስት ኃላፊነቱን በሚገባ ባለመወጣቱ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ሁኔታውን አመቻችቷል፡፡ ይህም የተደረገው በዕቅድ አንጂ በድንገት የተፈፀመ አይደለም፡፡ ይህ ሴራ የተሸረበው ህዝቦችን እርስ በርስ በማጋጨት የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም ሲሆን ይህ የሚያስከትለው የርስ በርስ ጥላቻንና ፍጥጫ የሶማሌ ክልል ቀስ በቀስ ከኢትዮጵያ ለመራቅና፣ ለመነጠል ምክንያት ሆኖት ለመገንጠል ሁኔታውን ያመቻቻል፡፡ ይህ አሁን ከሚታየው በስተጀርባ ያለው ሴራ ነው ብዬ አምናለሁኝ፡፡ የረዥም ጊዜ ዕቅድ ያላቸው የኦጋዴን ተገንጣይ ቡድኖች በህዝቦች መሐከል ያለውን ግጭት ለረዥም ጊዜ ዓላማቸው ይፈልጉታል፡፡ የወያኔ መንግስት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ህዝቡን ሲያጋጭ በዚያው መጠን የሶማሌ ተገንጣይ ጦረኞች የራሳቸውን ሀይል ለማጠንከርና ኦጋዴን ሶማሌ ያልሆነውን ሁሉ ከክልሉ አስወጥተው ኦጋዴን የኦጋዴኖች ብቻ አድርገው የመገንጠሉን እንቅስቃሴ ወደ አዲስ ምዕራፍ  ያሸጋግሩታል::: የኦጋዴንን ጥያቄም ዓለም አቀፋዊ(Internationalize) ለማድረግ  ይጥራሉ:: ይኸም የሚሆነው በመንግሥት በኩል በሚወሰዱ አክራሪ(Excessive) እርምጃዎች ወይንም ደግሞ በሕዝቦች መሀከል ያለውን ግጭት ለብዙ ሕይወት ማለፍና እንዲሁም መሰደድ ምክንያቶች ሲሆኑ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ አጀንዳ የሌላቸው አገሮች ጣልቃ ይገባሉ፣ በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካ አንድነት እንዲሁም በሌሎች ኢንተርናሽናል ድርጅቶች ውይይት ያስከፍታል፣ መግለጫዎች ያወጣሉ፣ ውሳኔም ያሰጣሉ:: ይህንን ኦብነግ ይፈልገዋል:: ሁኔታዎችንም ወደዚያ ይገፉሉ፡፡ ጉዳዩ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ጉዳይ ይሆናል፡፡ የተገንጣዮች ስትራቴጂ ይህን ይመስላል፡፡ የኦጋዴን ጉዳይ እንደ ሌሎች የኢትዮጵያውያን ጥያቄ የኢትዮጵያ ጉዳይ ሆኖ መቆየት አለበት፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው የወያኔ መንግሥት ሲወገድና የሕዝቡን አንድነት የሚያረጋግጡ፣ ዋስትናም የሚሆኑ ፖሊሲዎች ሲቀየሱና ህዝቡ የተባበረ አቋም ይዞ ለአንድነቱ  ሲታገል ነው:: ሁልጊዜ ማዕከላዊ መንግስት ሲዳከም ነው ጠላቶቻችን ጥንካሬ የሚያገኙት፡፡

ከዚህ በላይ በዘረዘርኳቸው ምክንያቶች በኦጋዴን ስለሚደረገው እንቅስቃሴና ስለኦጋዴን ኢትዮጵያዊነት ሕዝቡ እንዲነጋገርበት በጉዳዩ የበለጠ ዕውቀት እንዲኖረውና ጥንቃቄ እንዲያደርግ በሁለት ምዕራፍ የተከፈለ ጽሁፍ አቅርቤ አለሁኝ፡፡

በኦጋዴን በኩል ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሏል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ወታደራዊ አካዳሚ እጩ መኮንን ሆኜ ሶስት ዓመት በቆየሁበት ጊዜ ወታደራዊ ስትራቴጂና ፖለቲካ ስንማር ዋና መለማመጃችን የካራማራ (ጅጅጋ) በር ነበር፡፡ ካራማራ ዋና የጠላት መተላለፊያ በር ስለሆነች ይቺን በር መጠበቅና መከላከል በዚያ አቅጣጫ ለሚመጣ ጥቃት ወሳኝ ነበር፡፡ ሶስተኛ ክፍለጦር በጀግናው ሜጀር ጀነራል አማን አንዶም ወይንም(ኮዳው ትራሱ) ሥር በነበረበት ጊዜ ብዙ ይወራለት ስለነበርና በተደጋጋሚ ጦሩንና አሰላለፉን በትምህርት መልክ ጐብኝቻለሁ፡፡ ከዚም በኋላ በአብዮት ወቅት የእድገት በህብረት አዝማች በነበርኩበት ጊዜ የዘመቻ ቦታ ለመምረጥና በኋላም ዘማቾችን ለማየት በኦጋዴን ብዙ ተጉዣለሁ፡፡ የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኃላፊ በነበርኩበት ጊዜ የዕለት ዕርዳታና የመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክቶችን ለመከታተል በተለይም ደግሞ አርብቶ አደሩን የኡጋዴን ህዝብ በዋቢ ሸበሌ ሸለቆ(ጎዴ) ለማስፈር በተደረገው ሙከራ ኃላፊ ሆኜ በኦጋዴን ብዙ ተንቀሳቅሻለሁ፡፡

የውጪ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር(ቋሚ ተጠሪ) በነበርኩበት ጊዜ የኡጋዴንና የሱማሌን ሁኔታ በጥልቀት ለማወቅ እድል ሰጥቶኛል፡፡ በተለይም 1969 ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ ሁኔታዎችን በኃላፊነት በቅርብ ተከታትያለሁ፡፡ የተከፈለውን ከባድ መስዋዕትነት መስክሬ አለሁኝ፡፡ ሶቭየት ህብረት ኢትዮጵያንና ሶማሊያንም ይዛ ለመቆየት ባደረገችው የፖለቲካ ሙከራ ወቅት ሞስኮና አዲስ አበባ በከፍተኛ ደረጃ በተደረጉት ውይይቶች ውስጥ ተሳትፌአለሁ፡፡ በተባበሩት መንግስታት በቀድሞ ሶቭየት ህብረት በገለልተኛ አገሮች መንግስታት በአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ በአውሮፓ፣ በኢስያና በደቡብ አሜሪካ አገሮች የኢትዮጵያን አቋም ለማስረዳትና ድጋፍ ለማግኘት ተዘዋውሬአለሁ፡፡ አሁንም ከአገሬ ከወጣሁኝ በኋላ በአፍሪካ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት በተፈጠረባቸው አገሮች ሁሉ ተዘዋውሬ ሰርቻለሁኝ፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዚሁ ርዕስ ላይ በአንድ የምርምር ኢንስቲትዩት በመስራት የአፍሪካን ሁኔታ በቅርብ ተከታትያለሁኝ፡፡

 

ለነበረኝ ኃላፊነቴ እንዲረዳኝ ስለኡጋዴን ብዙ ያስተማሩኝ በጣም የማከብራቸው ሁለት ሰዎች ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያምና ፊት አውራሪ ደምሴ ተፊራ ነበሩ፡፡ በጊዜው ምክር ፍለጋ እየሄድኩ ያገኘሁት ዕውቀት ብዙ ነው፡፡ ለመንግስትም የአቋም መግለጫ እንዲረዳ ፕሮፌሰር መስፍን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፃፉት መጽሐፍ(The Problem Child of Africa Somalia) እና የአገር አስተዳደር ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ፊታውራሪ ደምሴ ተፈራ ከሰፊ ልምዳቸው ከጻፉት መጽሐፍ ተነስቼ ብዙ ንግግርና ውይይት ለማድረግ ችያለሁ፡፡ እነዚህ ሁለት አርበኞች ለሀገር አንድነት ባላቸው ተቆርቋሪነት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በማማከር መንግስት በዲፕሎማሲና በወታደራዊ ጉዳይ ትክክለኛ ፖሊሲ እንዲወስድ አድርገዋል፡፡ በሁለተኛው ምዕራፍ የማቀርበው ብዙ ሐሳብ እነሱ ካስተማሩኝና ይህንንም ተመርኩዤ ካደረኳቸው ንግግሮች የተወሰደ ነው፡፡(ክህደት በደም መሬት በሚለው መጽሐፌ ውስጥ በዝርዝር ቀርቧል)፡፡

አፍሪካ ቀንድ

ዛሬ አፍሪካ ቀንድ ብዙ ሀይሎች የንግድ፣ የስትራቴጂና የሴኩሪቱ ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚተራመሱባት አካባቢ ሆናለች፡፡ ዛሬ የአፍሪካ ቀንድ በአለም ውስጥ ካሉት ማናቸው ሴኩሪቲ ዞን የበለጠ የሚሊቴሪ እንቅስቃሴዎች የሚታዩባት አካባቢ ሆናለች፡፡ (The most complex militarized security zone in the world) ጅቡቲ ውስጥ ቀድሞ የፈረንሳይ ጦር ሰፈር የነበረው ካምፕ ለሙኒየር(Camp Lemonnier) ታድሶ፣ ተስፋፍቶ የአሜሪካን ጦር ሰፈር ሆኗል፡፡ ጅቡቲ የአሜሪካን አፍሪካ ኮማንድ (Africom) አፍሪካ ውስጥ የቋሚና የተንቀሳቃሽ ኃይሎች መምሪያ ሆናለች፡፡(የአፍሪኮም ዋና መምሪያ የሚገኘው አውሮፓ ነው)፡፡ የፈረንሳይ ጦርም ቁጥሩ ጨምሮ ተጠናክሮ ጅቡቲ ይገኛል፡፡ ቻይና ከአገሩ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ሰፈር በጅቡቲ አቋቁማለች፡፡ ሳውዲአረቢያም በኤርትራና በጅቡቲ የጦር ሰፈር እየመሰረተች ነው ይባላል፡፡ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬት(UAE) በሶማሌ ላንድና አሰብ ላይ ጦር ሰፈር ከአቋቋሙ ሰንበት አለ፡፡ ጃፓን በበኩሏ በሚሊተሪ ኢንዱስትሪና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኋላ ራሷን አግልላ መኖሯ ይታወሳል፡፡ ዛሬ ጃፓን ጅቡቲ ላይ የጦር ሰፈር እየመሰረተች ነው፡፡ ሩሲያ በበኩሏ በሱዳን የጦር ሰፈር ለመመስረት በስምምነት ላይ ደርሳለች፡፡ ደቡብ ሱዳን በምዕራቡ የዓለም የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ስለተደረገባት ከግብጽ ጋር አዲስ ሚሊተሪ ግንኙነት (Alliance) መሥርታለች፡፡

የአፍሪካ ቀንድ የብዙ ኃይሎች የጥቅም መናህሪያ እየሆነች በመጣች ቁጥር የነዚሁ ሀይሎች ተጽዕኖ የእያንዳንዱን ሀገር የፖለቲካ ሁኔታ የመንግስታት ፖሊሲና ሴኩሪቲ ይቀርፃል፡፡ የነዚህ ኃያላን ሀገሮች ብሔራዊ ጥቅም እርስ በእርስም ሆነ ከአፍሪካ ቀንድ መንግስታት ፖሊሲ ጋር የሚጋጭባቸው ብዙ ሁኔታዎችም አሉ፡፡ ኢትዮጵያን ነጥለን ስንመለከት ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ያላት ግንኙነትና ያላት ፖሊሲ እነዚሁ ሀያላን አገሮች ከሚያራምዱት አጀንዳ ጋር የሚጋጩበት ሁኔታዎች ብዙ አሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለው የፖለቲካ ቀውስ ሰላማዊ ሽግግር ውስጥ በአስቸኳይ ካልተገባ እንደ ሲሪያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ የራሷ ያልሆነ(PROXY) ጦርነትና፣ ትርምስ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል በጣም ግልፅ ነው፡፡

 

በወያኔ ማበረታታት ያንሠራራው ቀድሞ “የምዕራብ ሶማሌ ነፃነት ግንባር” ተብሎ የሚታወቀው ንቅናቄ ዛሬ ደግሞ “የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ንቅናቄ” በቀይ ባሕር፣ በሱዳንና በግብፅ (ዓባይ) ካለው ሥጋት ጋር ተጣምሮ መታየት ያለበት ነው፡፡ ችግሩ የነበረ፣ ያለና በወያኔ ፖሊሲ እየተባባሰ የመጣ፣ የሀገሪቱን ሕልውና የሚፈታተን አደጋ ነው፡፡ ስለዚህም የኦጋዴን ሁኔታ ከመፈንዳቱ በፊት ሁሉም አውቆ ነቅቶ መጠበቅ አለበት፡፡

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያ ከጣሊያን ወረራ ነፃ ወጥታ ሕልውናዋን የተሟላ ለማድረግ ሦስት ዐበይት ሥራዎች መሠራት ነበረባቸው እነዚህም የንጉሠ ነገሥቱን ማዕካላዊ አገዛዝ ማጠናከር ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ ማስመለስ፣ በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ እየተንከባለለ የመጣውን “ታላቋን ሶማሊያ” የመገንባት ፖሊሲና እንቅስቃሴ መቋቋም ነበሩ፡፡ እነዚህ ሦስት ሥጋቶች የኢትዮጵያን የመከላከያ ኃይል መስፋፋት አስገደዱ፡፡ ሌላውን ለጊዜው ትተን የሶማሊያን ሥጋት በአጭሩ እንመረምራለን፡

በኢጣሊያ ሶማሌ ላንድና በኢትዮጵያ በኩል የድንበር ጥያቄ የለም፡፡ እ.ኤ.አ በ1897 እና በ1908 ውል መሠረት ድንበሩ ተከልሏል፡፡ ጣሊያን በዚህ ውል ባለመደሰቷ ግን ኢትዮጵያን ለመውረር ሁልጊዜ ምክንያት ትፈልግ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው እ.ኤ.አ በ1934 የወልወል ግጭት የተደረገው ከ2ኛ ዓለም ጦርነት በኋላ የጣሊያን ሶማሌላንድ እንደገና በጣሊያን እጅ ወደቀች፡፡ ድንበሩ በሕግ የተከለለ ቢሆንም ምልክቶች ስላልተደረጉበት በየጊዜው በጣሊያንና በኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል በኋላም ሶማሊያ ነፃ ከወጣችበር ጊዜ ጀምሮ በሶማሌ መንግሥትና በኢትየጵያ መንግሥት መካከል ለነበረው የማያቋርጥ ግጭት ምክንያት ሆኗል፡፡

ከእንግሊዝ ሶማሌላንድ ጋር ያለው ድንበር በሕግ የተከለለ ምልክትም የተደረገበት ስለሆነ በዚያ አቅጣጫ የድንበር ጥያቄ አልነበረም፡፡ ይህም ሆኖ እንግሊዞች እ.ኤ.አ በ1946 የጠነሰሱት ታሏቋ ሶማሊያን የመገንባት ዓላማ በሶማሊያ መንግሥት ዋና የውጭ ፖሊሲና ሕዝቡም እንደ ሃይማኖት ይዞት የሚገባ እምነት ሆኖ ይሰበክ ጀመር፡፡ ስለዚህም ሶማሊያ ነፃ ስትወጣ የተመሰረተው መንግሥት ይህንኑ ዓላማ የሕገ-መንግሥቱ ዋና አንቀጽ አድርጎ አወጀ፡፡ በዚህም መሠረት አምስቱን የሶማሌ ሕዝብ የሰፈረባቸውን ቦታዎች (ጅቡቲ፣ ኦጋዴን፣ ሰሜን ኬንያ(NFD)፣ የእንግሊዝን ሶማሌላንድና የጣሊያንን ሶማሌንድ) አንድ ለማድረግ ትግሉ ተጀመረ፡፡ ለእዚህም ዓላማ እንዲያመች በደቡብ ኢትዮጵያ “የኦሮሞ ነፃ አውጪ” ግንባር፣ በደቡብ ምሥራቅ የምዕራብ ሶማሌ ንቅናቄ፣ በባሌ በኩል በዋቆ ጉቱ የሚመራ ንቅናቄ ተደራጅቶ ከኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅቶች ጋር ግንባር በመፍጠር በኢትዮጵያ ውስጥ ሽብር መፍጠር ተጀመረ፡፡ ሽብሩ እየተስፋፋ በሄደ ቁጥር የኢትዮጵያ ወታደራዊ ድርጅት እያደገ እየተጠናከረ፣ በቁጥርም፣ በሥልጠናና በመሣሪያ ዓይነት ዘመናዊ እየሆነ መጣ፡፡ በ1984 ነሐሴ ወር የምዕራብ ሶማሌ ንቅናቄ በኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር(ONLF)ተተካ፡፡

 

የሶማሌ መንግሥትና የኦጋዴን ጥያቄ

ሶማሊያ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ በሕገ መንግሥቷ የተንፀባረቀው(አንቀጽ 6) ታላቋ ሶማሊያን የመመሥረት ዓላማ በእያንዳንዱ አብዛኛው የሶማሌ ኤሊት ስነ ልቦና ውስጥ የተተከለ ሕልም ነው፡፡ ምንም እንኳን እ.ኤ.አ. በ2012 ዓ.ም. የወጣው አዲሱ ሕገ መንግሥት ይህንን አንቀፅ ባይጨምርም የሶማሊያ ባንዲራ አሁንም ያው ነው፡፡ ባንዲራው አስምት ጫፍ ያሉት ኮከብ ሲሆን እነዚህም የሚያመለክቱት አምስቱ የሶማሌ ታናጋሪ ሕዝቦች የሚኖሩበትን ነው፡፡ የኦጋዴን ሶማሌዎች ግን ኢትዮጵያዊነታቸውን አጥብቀው የያዙ፣ ከሌሎች ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ለኢትዮጵያ አንድነት ብዙ የተዋጉ፣ የታገሉ መስዋዕትነት የከፈሉ ከኢትዮጵያ ያልተለዩ ታሪክ ያላቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡ የሶማሌ መንግሥት በአጐራባች አገሮች የሚኖሩ ሶማሌ ተናጋሪዎችን በሞላ በአንድ ሶማሊያ ውስጥ ማጠቃለል ያላት ፖሊሲ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ውዝግብ ፈጥፎአል፡፡ እነዚሁ አምስት ቦታዎች የሰሜን ዲስትሪክት ፍሮንቲየር(Northern District Frontire) በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ የእንግሊዝ ሶማሌ ላንድ፣(Somali land) ኦጋዴንና፣ አሁን ሶማሊያ የሚባለው አገር ቀድሞ የጣሊያን ሶማሌ ላንድ ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡ የሶማሌ መንግሥታት ይህን ሕልማቸውን በሕግ ዕውን ለማድረግ ስለማይችሉ የነፃነት ነቅናቂዎች በማቋቋም የኢትዮጵያንም፣ የኬንያንም ፀጥታ ሲያናጉ ኖረዋል፡፡ ጅቡቲ ነፃ በወጣችበት ጊዜ በ1979 እ.አ.አ. ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከባድ የዲፕሎማቲክ ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያም ሶማሊያም በጅቡቲ ላይ የይገባኛል መብቶቻቸውን አቅርበው በመጨረሻ ላይ አስታራቂ ሆኖ የተገኘው ነፃ የሆነች ጅቡቲን መመሥረት ሆኖ ተገኘ፡፡ ሆኖም ሶማሊያ የመጀመሪያውን የግልፅ ጦርነት የከፈተችው በኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡ ይህም የሆነው በዚያድ ባሬ አገዛዝ ነበር፡፡ በ1968 ዓ.ም. በምዕራብ ሶማሊያ የነፃነት ንቅናቄ(WSLF) ስም ሶማሊያ ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ የምዕራብ ሶማሊያ የነፃነት ግንባርና ተቀጥያው የኦጋዴን ብሔራዊ የነፃነት ግንባር(ONLF) ያቋቋመው የሶማሌ መንግሥት ነው፡፡ የሁለቱም ዓላማ አንድ ነው፡፡ የዚያድ ባሬ መንግሥት በምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጪ ግንባርና በኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ስም ኦጋዴንን ወሮ ሠራዊቱ ጅጅጋን ይዞ፣ ድሬዳዋና ሐረር በቀረበበት ጊዜ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፈተና ላይ ወድቃ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጀው የሶሻሊስት ፖሊሲ ምክንያቶች ጦር መሣሪያ ከአሜሪካ ማምጣት በማቆሙና፣ የሶቭየት ዩኒየን ከሶማሌ ጋር ቀደም ያለ ግንኙነት ስለነበረው መሣሪያ በሚፈለገው ሁኔታ መገኘት ባለመቻሉ የሶማሊያ ጦር ገፍቶ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባት ቻለ፡፡ በወቅቱ እኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቋሚ ተጠሪ( ምክትል ሚኒስትር) ነበርኩኝ፡፡ ፈታኝና አሳፋሪ ጊዜ ነበር::

ስለሆነም ከኢትዮጵያ ደሀ ገበሬ የተውጣጣ 300,000 ሺህ ሚሊሺያ የእናት ኢትዮጵያን ጦር በአጭር ጊዜ ጦር ተቀብሎ፣ ሰልጥኖ፣ በጀግንነት ተዋግቶ በከፈለው መስዋትነት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ማስከበር ችሏል፡፡ የሶማሌ መንግሥት ምኞት የኢትዮጵያን መንግሥት አንበርክኮ ኦጋዴንን አሳልፎ ከመስጠት ሌላ አማራጭ እንዳይኖረው ማድረግ ነበር፡፡(ለዝርዝሩ Red Tear መጽሐፍን አንብቡ) በምዕራብ ሶማሌ የነጻነት ግንባርና በኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር የተሰነዘረው ጥቃትና የተቃጣው ድፍረት የኢትዮጵያን ሠራዊት ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ሕዝቡ ታላቅ መስዋዕትነት ክፍሏል፡፡ ቦታው ላይ ስለነበርኩኝ የመስዋዕትነቱን መጠን በቅርብ ሆኜ መስክሬአለሁኝ፡፡ (የመስዋዕትነቱን መጠን ክህደት በደም መሬት የሚለው መጽሐፌን አንብቡ)፡፡

ለዚህም ድፍረትና ለዚሁም ከፍተኛ መስዋዕት አፍራሽ ሚና የተጫወተው አንዱ ኢሀፓ ነው፡፡ ኢሀፓ ኦጋዴንን አስመልክቶ የኦጋዴን ሕዝብ ከፈለገ ከሶማሊያ ጋር ይቀላቀል የሚል አቋም ይዞ ቆይቶአል፡፡ የኢሀፓ አላማ ከሶማሊያ መንግስት መሣሪያና ገንዘብ ለማግኘት ነበር፡፡ ለዚህ ሲል የኢትዮጵያን አንደነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አደረገ::ከሶማሊያ መንግስትም ያገኝው እርዳታ እምብዛም አልነበረም፡፡ ቀጥሎም በእያንዳንዱ ቀበሮ ጉድጓድ በመቶ፣ በሻምበል፣ በሻለቃ፣ በብርጌድ በተሰለፈው ሠራዊቱ ውስጥ ሠርጐ በመግባት ሠራዊቱ እንዲያፈገፍግ በኢሀፓ ስም ጥሪ በማስተላለፍ ወረቀት በመበተን የአምስተኛ ረድፍ ሚና በመጫወት ሠራዊቱ እንዲሸሽና በሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ እንዲያልቁ ምክንያት ሆኖአል:: ምንም እንኳን ይህ አቋም የሁሉም የኢሀፓ አመራርም ሆነ ወይም ተራ አባላት እንዳልሆነ ቢገመትም ይህ ድርጊት ለመፈፅሙ ምንም ጥርጥር የለም:: የኢሀፓ መሪዎች ከመቋዲሾ መንግሥት ጋር በቅርብ እንደሚሠሩና ከዚያም አዲስ አበባ ካለው ኤምባሲ ጋር ቅርብ ግንኙነት እንደነበራቸውም የሶማሌ መንግሥት ኤምባሲ እንዲዘጋ ሲደረግ ከተገኙት ዶክመንቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡ እኔ በዚያን ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ስለነበርኩኝ ማስረጃዎቹን አይቻለሁኝ፡፡

 

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ከምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጪ ግንባር አብሮ ሲሠራ የነበረ፣ የአሁኑ መሪዎችም ከዚሁ ድርጅት የተመለመሉ መሆናቸውንና የምዕራብ ሶማሊያ ነፃ አውጪ ግንባር በዚያድ ባሬ ትዕዛዝ እንዲጠፋ ሲደረግ በእሱ እግር የተተኩ፣ የሞቃዲሾ ተወላጆች ለመሆናቸው ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡ የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ፕሮግራም ግልፅ ነው፡፡

  • ኦጋዴን የኢትዮጵያ አካል አልነበረችም አትሆንም
  • የኦጋዴን ሕዝብ ትግል የነፃነት ትግል ነው

የሚል ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ አባባሎች ሽፋን ተብለው የራስ ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል ድረስ ይላሉ፡፡ የኤርትራም ንቅናቄ ሲጀመር እንደዚሁ ነበር የሚለው፡፡

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር ኢሀፓን ተጠቅሞ ኢትዮጵያን እንደወረረ እየታወቀ ወያኔ ከእዚሁ ተገንጣይ ቡድን ጋር ግንባር ለመፍጠር መሞከሩ ወያኔ ቅድሚያ የሚሰጠው ለኢትዮጵያ አንድነት ሳይሆን ሥልጣኑን ለማጠናከርና ሕዝቡን በዘር ከፋፍሎ ለመግዛት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅትና፣ ኦብነግ ዋና መሥሪያ ቤታቸውን ኤርትራ(አስመራ) ማድረጋቸውም ብዙ ጥያቄ አስነስቶአል፡፡ “የኢትዮጵያን አንድነት እናከብራለን፣ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ወይንም ለመገነጣጠል ከሚዋጉ ሀይሎች ጋር አንተባበርም” እያሉ እነዚሁን ድርጅቶች ማስተናገድ የኤርትራን መንግሥት የዚህ እኩይ ዓላማ ተባባሪ ያደርገዋል፡፡

ዛሬ የሶማሌ መንግሥት ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ድርጅት ጋር ስምምነት የለውም፡፡ ድርጅቱ ከአልሻባብ ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ ስለሚጠረጠር፣ በፕሮግራሙ ላይም የሚንፀባረቀው የመገንጠል አላማ ከኢትዮጵያ ጋር ያጋጨናል ብሎ ስለሚያስብ የዲፕሎማቲክ አቋም ይዞአል፡፡ ሆኖም ይህ አቋም በኦጋዴን ያለውን አቋም አያጠፋውም፡፡ ቀድሞውንም የሶማሌን የመስፋፋት ፖሊሲና የኦጋዴንን መገንጠል የሚደግፉት ISIS ኢስላሚክ ኮርት (Islamic court) ሥልጣን ቢይዙ የኦጋዴንን መገንጠል በይፋ ደግፈው ኢትዮጵያ ላይ ውጊያ እንደሚከፍቱ ጥርጥር አይኖርም፡፡ ይህ የሶማሌ መንግሥትም አሁን ካለበት ሁኔታ ወጥቶ ፀጥታ የሰፊነበት ጠንካራ መንግሥት ቢቋቋም ኦብነግን በቀጥታ ሊደግፍ ይችላል፡፡ በእዚህም ምክንያት ነው የዚያድ ባሬ መንግሥት እንዲፈርስ ተቀዋሚ ድርጅቶች ተጠናክረው እንዲታገሉ የኢትዮጵያ መንግሥት የታገለው፡፡

 

የ1969 ዓ.ም. ጦርነት ካለቀ በሁዋላ በመንግሥት በኩል የተወሰነው ውሳኔ የሶማሌ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ ሌላ ጦርነት ማወጅ የማይችል ደካማ መንግስት ማድረግ ተቀዳሚ የኢትዮጵያ የሶማሌ ፖሊሲ ሆኖ በተግባር ዋለ፡፡በዚሁም መሠረት የተወሳሰበና ረቂቅ የሆነ ፕሮጀክት ተጀምሮ የሶማሌ ብሔራዊ ንቅናቄ(SNM) የሚለውን የተቃዋሚ ድርጅት በማስታጠቅና በማደራጀት ዚያድ ባሬን ከሥልጣን ማስወገድ ተቻለ፡፡ የሶማሌንም ብሔርተኝነትና የታላቋን ሶማሊያን ሕልም መግታትም ስኬታማ ሆነ፡፡ ሶማሊያ ነፃነት ከወጣች በኋላ ኢትዮጵያ በምሥራቅ ግንባር ሰላም አግኝታ አታውቅም፡፡ ዚያድ ባሬ ከወጣ በኋላ በጐሣ የተከፋፈለ ሕዝብ እርስ በእርሱ እንደሚጋጭ የተጠበቀ ነበር፡፡ ከ1969 ዓ.ም. እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ያላት ፖሊሲ ከመቻቻል (Continment) ወደ መንግሥትን ማናጋት(Destablization) ተለወጠ፡፡ ተቃዋሚው ድርጅት(SNM) አባላት አብዛኛው ከይሳቅ ጐሣ የተመለመሉ ሲሆን የዚያድ ባሬ መንግሥት ግን ከመሪሀን ነበር፡፡ ዚያድ ባሬ በአባቱ ከመሪሀን ይሁን እንጂ በእናቱ ኦጋዴን ነው፡፡ የሶማሌ ብሔራዊ ንቅናቄ (SNM) እየጠነከረ ሲሄድ የዚያድ ባሬም ሥልጣን እየተዳከመ ሄደ፡፡ ወደ መጨረሻው በጐሣው ጥላ ሥር ገብቶ የጐሣ ጦርነት አስጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲም ይህንን አፋፋመው፡፡ በአንድ ቋንቋ፣ በአንድ ሀይማኖት፣ በአንድ ባህል የተመሠረተችዉ ሶማሊያ በጐሣ ጦርነት ውስጥ ተነከረች፡፡ ዚያድ ባሬ በለኮሰው እሳት ተለበለበ፡፡ አገሪቱም እስከዛሬ ድረስ ሰላም አጥታ ትኖራለች፡፡ ኢትየጵያን ማሸበሩ ግን አላቋረጠም፡፡ ምንም እንኳን ቀጥታ የመንግሥት ድጋፍ ባይኖረውም ከሕዝቡ በሚያገኘው ድጋፍ ሌሎችም የኢትዮጵያን መዳከም ከሚሹ ድጋፍ እያገኘ ኦብነግ ሽብሩን ቀጥሎአል፡፡

በዚያም ሆነ በዚህ ኦብነግ በኢትዮጵያዊነቱ የማያምን በደቡብ ሱዳንና በኤርትራ እንደታየው ኢትየጵያን የሚያደማ፣ የሚያዳክም ረዥም ትግል አካሂደን መጨረሻ ላይ ነፃነት እንጐናፀፋለን ብለው ያምናሉ፡፡ በሁለተኛም ደረጃ ከሱማሊያ ጋር እንቀላቀላለን ብሎ የተነሳ ስለሆነ ከዚህ ድርጅት ጋር መሥራት፣ መተባበር ወይንም ድርጅቱ ሀሳቡን ለውጦአል ብሎ ማመን ራስን ማታለል ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ጽሑፋቸው፣ መግለጫቸው የሚያሳየው የተነሱበትን ያልለወጡ መሆናቸውን ነው፡፡ አንደ ቀድሞው ኢሀፓ የትሮይ ፊረስ በመሆን ያልተጠበቀ ችግር ውስጥ ገብቶ የኦብነግ ጉዳይ ፈፃሚ ላለመሆን መጠንቀቅ ያሻል፡፡ በኦጋዴን መሬት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አባቶቻች፣ እናቶቻችንና ወገኖቻችን ደም የተለወሰ የከበረ መሬት ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ አባቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በደማቸው በአጥንታቸው በሕይወታቸው በከፈሉት መስዋዕትነት አንዳችም እፍኝ አፈር ለሌላ አትሰጥም፡፡

ኢብራሂም አብደላ የተባለ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ተጠሪ በአንድ ወቅት ሲናገር የሚከተለውን አለ፡፡

“ድርጅታችን የሚከተሉት አላማዎች አሉት ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ማውጣት ነፃ መንግሥት መመሥረትና የሕዝቡን ፍላጐትና ምኞት ዕውን ማድረግ ከሶማሊያ ሕዝብ ጋር ያለውን የወንድማማችነትና የትግል አንድነት እንዲጠናከር በሌላ በኩል ደግሞ ከአረቡ ዓለም ጋር ያለንን ግንኙነት በጋራ ጥቅሞች ላይ ተመርኩዞ የሚያድግበትን መንገድ መሻት ነው፡፡” (የአፍሪካ ቀንድ የመጀመሪያው ዓመት ቁጥር 7-1985).

ከፍተኛ የኦብነግ ጦር መኮንን ደግሞ አብዲራሺድ ሀልጋም እንዲህ ይላል

“The ONLF objectoves are to attain full independence from Ethiopian government and to have a country with no interference from other nations. We are fighters fighing for independence”

ሌላው ደግሞ ራሱን አድሚራል የሚለው የኦማር ኦስማን የኦብነግ ጦር መሪ እንዲህ ይላል

“Ogaden are arab muslim people, we have common enemy with Alshabab”

“የኦጋዴን ህዝብ አረብና እስላም ህዝብ ነው:: እኛና አልሻባብ የጋራ ጠላት አለን”

ደግሞ የኦብነግ መሥራችና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ እንዲህ ይላል;

“When you are fighting for your rights time is not an issue. My father was fighting for our rights and my children will fight for our rights. We want right to self determination including even leaving the country Free choice is not secession”.

“ስለመብታችን ስንታገል ጊዜ ዋና ነገር አይደለም:: አባቴ ስለ መብታችን ይዋጋ ነበር:፡ ልጆቼ ደግሞ ለዚሁ መብታቸው ይዋጋሉ፣ የራሳችንን እድል ራሳችን መወሰን አለብን:: መገንጠልንም ጨምሮ፣ ይህ መገንጠል አይደለም፣ ነጻ ምርጫ ነው”

የኤርትራን የነፃነት ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ ኦብነግ ለኤርትራ መንግሥት የላከው መልዕክት እንዲህ ይላል:

“From the trenches of battle fileds of Ogaden, where we struggle for our day of independence from Ethiopia, Convey the best wishes for a prosperous and peacefull future (ONLF 2002)”.

“አንድ ቀን ከኢትዮጵያ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ከሚታገልባቸው የኦጋዴን የጦር ምሽጐች የድርጅታችንን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር የነፃነት ተዋጊዎች የበለፀገና ሰላማዊ የወደፊት ጊዜ ይመኝላችሁዋል” ኦብነግ 2002).

ኦብነግ ለዜና ማሠራጫ በ June 2015, ባወጣው መግለጫ:

“We killed many colonial troops following heavey fighting”

“ብዙ የቀኝ ገዢ ወታደሮችን በጦርነቱ ላይ ገድለናል”.

ይህ እስከ ቅርብ ጊዜ ሲነገር ሲፃፍ የቆየ የኦብነግ አቋም ሕዝብ ሳያውቀው ተለውጦ እንደሆነ ሚስጢሩን የምታውቁ አስተምሩን፡፡ “ኦጋዴን ዛሬም በታሪክ የኢትዮጵያ አካልነች፡፡ የኦጋዴን ህዝባዊ የነፃነት ግንባር በኦጋዴን ህዝብ ኢትዮትያዊነት ያምናል፡፡ የኦጋዴን ህዝቡም አገሩም አረብ አይደለም፡፡ የኦብነግ የትግል ዓላማ እንደማናቸው ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ሀይሎች ወያኔን አስወግዶ የሚሞክራሲያዊ የሁሉም ህዝብ መብት በእኩልነት የሚጠበቅበት ሥርዓት እንዲፈጠር ነው” የሚል የቀድሞውን አቋም የሚሽር መግለጫ ካወጣ ሁላችንንም ያስደስተናል፡፡ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅትም(OLF) ከዚሁ አካል ጋር ተባባሪ ሆኖ የሚሠራ የመገንጠል አቋሙን ያለወጠ እስከሆነ ድረስ ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ከሆነ ተሳትፎ ተገልሎ መወገዝ ያለበት ድርጅት ነው፡፡

ኦብነግን በተመለከተ ተጨማሪ ንባብ ከእዚህ የሚከተሉትን ተመልከቱ፡፡

 

They are giving their own blood for the sake of their Independence so that they can hold their next or future celebrations in their homeland to honour all who have fallen in fight for the return of the Republic of Ogaden without fear of execution, arrest or humiliation. Ogaden, which is politically and economically marginalized was handed over to Ethiopia in 1954 by the Great Britain.

Sep 08, 2015

Ogaden: ONLF’s 31st Anniversary

http://unpo.org/article/18537

5) The ONLF adopts the long-term popular war and independent frontal resistance, supported by the mobilization of the people and their initiatives as the foundation of it’s struggle. 6) The program of the ONLF shall be carried out by a combatant cadre carefully selected among its ranks with special emphasis on their political …

Ogaden National Liberation Front (ONLF ) – Political Objectives

http://onlf.org/?page_id=14

Declaration Forming The ONLF. We the people of Ogaden. Recognizing that our country has been colonized against our will and without our consent by Ethiopia. Noting the misrepresentation of our struggle as a border conflict between Somalia and Ethiopia. Having witnessed the indiscriminate murder of our families and …

POLITICAL PROGRAMME – ONLF

http://onlf.org/?page_id=16

መራር እውነቶች። ወያንያዊ ነው (ዳዊት ዳባ)

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው መንግስታዊ (ወያንያዊ) ችግር እንጂ በህገ መንግስቱ ምክንያት የተፈጠረ ችግር አይደለም። አሁንም ኢትዬጵያ ውስጥ ያለው ችግር ወያንያዊ እንጂ ባለው አከላለል ምክንያት የተፈጠረ ችግር አይደለም። አሁንም ኢትዬጵያ ውስጥ ወያንያዊ ፍጅት እንጂ የእርስ በእርስ ፍጅት የለም። እንደገና አሁንም ኢትዬጵያ ውስጥ ወያንያዊ እንጂ የድንበር ግጭት አይደለም ያለው። የሱማሌ ህዝብ የኦሮሞ ህዝብ ላይ። የአማራ ህዝብ የትግሬ ህዝብ ላይ። የትግሬ ህዘብ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ላይ፤ የኦሮሞ ህዝብ የአማራ፤ የትግሬና የሱማሌ ህዝብ ላይ የሰማነው ሁሉ በወያኔዎች ቀድሞ የተቀደ የተመራና የተፈፀመ ፍጅት ነው። እውነቱ ይሄ ነው።

ገዢው ፓርቲ ውስጥ ያለው አለመግባባትና ፍጥጫ ዋናው ምክንያት ወያንያዊ የበላይነት አለ የሚልና ባለው የበላይነትን ተጠቅሞ በመንግሳታዊ ስልጣን ጀርባ በመደበቅ ወያኔ ፍጅት በህዝብ ላይ መፈፀሙ ነው። ዜጋው ሰላማዊ በሆነ መንግድ ለጠየቃቸው መብቱ የሆኑ ጥያቄዎች ባግባቡ መፍትሄ እንዳይሰራላቸው ይህ ክፍል ጋሬጣ ስለሆነ ነው። ይህ ክፍል መንግስታዊ ሽፋንን ተጠቅሞ ከዜጋው ጋር አላስፈላጊ ትግልና ብሽሽቅ ውስጥ ስለገባ ነው። የተፈጠረው ክፍፍል ወያንያዊ የበላይነት መቀጠል አለበት በሚሉና ይህ ነገር በዝቷል ገደብ ሊበጅለት ይገባል ባሉት መካከል ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ አምርሮ መብቱን እየጠየቀ ያለው የኦሮሞ ህዘብ ነው። የወያንያዊውን ስርአት ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የኦሮሞ ህዝብ ነው። የገዘፈ፤ መራርና የሚሰቀጥጥ መሰዋትነት እየከፈለ ያለውም የሄው ህዘብ ነው። እዚህ ህዝብ ላይ ፍጅት መፈፀሚያ ምክንያት ለመስራት ሲባል በአለፉት ሁለት አመታት በሂደቱ መሰዋት የተደረጉ ብዙ ንፁሀን ትግሬዎች፤ አማሮቸ፤ የሱማሌና፤ አፋሮ ዜጎቻችን አሉ። ያም ሆኖ ወያንያዊ ፍጅቱ በወናነት ያነጣጠረው የኦሮሞ ህዘብ ላይ ነው። ይህ ፍጅት በቀጣይ በሰፊው ሊፈፀም የታቀደውም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ዜጎቻችን ላይ ነው።

ሰለጠነ የሚባለው ማህበረሰብ ቀውስን ለቀናትና ለሳምንት መቋቋም እያቃተው የሚፈጠሩ አስገራሚ ክንውኖችን አይተናል። ታዝበናልም። አገራችን ለሁለት አመታት ባላቋረጠ ቀውስ ውስጥ ነች። መጎዳቱና መጠቃቱ አገራዊ ብቻ አይደለም ለተወሰነው የአገሪቷ ክፍል ህዝብ ጎጆ ቤታዊ ሆኗል። በእርግጥ ለጊዜው ቀውሱ በቀጥታ ያልነካውና የጭካኔው ድላ ያላረፈባቸው እርቀው ያሉ አንዳንድ ዜጎጃችን ችግሩን በቀጥታ ተጎጂ እንደሆነው የማህበረሰብ ክፍል ሊረዱት አለተቻላቸውም። ጎንደርና አንቦ ላይ ያለ ህዘብ ግን ችግሩ መንግስታዊ መሆኑን ለማየት ችግር የለበትም። አልፎም ባንዳንዶች ሚዛናዊ ነን ለማለት ሲባል ብቻ ጥፋቱን ከፊሉን ለተጎጂውም የማካፈል ነገር አለ። እውነታው ዛሬ መንግስት የሚባለው አካል አገራችን ውስጥ እየፈፀመ ያለውን ለንደን ወይ ኒዬዎርክ ላይ በክፊል ቢፈፀም እዚህ አዛም በሚፈጠር ትናንሽ ግጭት የሚያልፉት አይሆንም ነበር። አገሮቹ በጠቅላላ ተቃጥለው ይጠፋ ነበር።

ሌላው መዋሸቱ ለፖለቲካ ፍጆታ ስለተፈለገ ነው። የድንበር፤ የእርስ በእርስ ግጭት፤ ህገ መንግስቱ በሉት ክልሉ ላይ…የቆዩ ፖለቲካዊ ልዩነቶች አሉ፤ እንከኖችና መሻሻል የሚገባቸው እንደገና ሊታዩ የሚጋባቸው ነገሮች የኖሩ ይሆናል። እዚህ ላይ መከራከር ይቻላል። ነግር ግን አሁን ኢትዬጵያ ውስጥ ካለውና እየሆነ ካለው ነገር ጋር እነዚህ ቁም ነገሮች የቀጥታ ግንኙነት የላቸውም። የቀጥታ ግንኙነት ያለው ከጭቆና፤ ከአድሎ፤ ነፃነት ከመሻት ጋር ነው። የቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመንግስታዊ ሽብርተኛነት ጋር ነው። ይህንን አይደለም የአገራችንን የየለት ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉ ፖለቲከኛች ዘፈኞቻችንና ገጣሚዎቻችን ያውቃሉ። በግጥምና በዘፍን ፍፁም አንድ ስለመሆናችንና ስለመዋሀዳችን ተመንጥቆ ሰማየ ሰማያት ያስቀመጡትን ያህል ግን ወገንታዊ መሆን አልቻሉም። መዝፈን መግጠም ይቻላል የሚሉትን መኖር ግን ለነሱም አሳጭ ሆኗል። እንደውም በመሀበረሰባችን ውስጥ የሚታየው የወገንታዊነት ደረጃ ጤናማ ከሆነው ደረጃ በታች ነው። አሳፋሪ ነው።

እሳት ከሰማይ አውርዶ እንዲቃጠሉ የሚጠየቀውን ምህላ ስለሚከብድ እንተወው። አንዱ ገጣሚው ችግሩን ከመንግስት ጫንቃ ላይ ሲያወርደውና ሌላ ቦታ ሲወስደው አብረን እንይ እስቲ።

ባውድማው ላይ እኛን የሚያዋጉን
እዳር ሆነው እኛን የሚሞቁን፤
ቀዩን ከነጭ ከሰርገኛ
ወትሮ የሚለዩ እነሱ መለኞ። ይህን ላዳመጠ ችግሩ መንግስታዊ አይደለም።
አሳሳቢው የእስካሁኑ አልበቃ ብሎ ፍጅቱን በቀጣይ በሰፊው ለመፈፀም እቅድ ውስጥ የተገባው ቀላል የማይባል ምን አልባት እውነቱን ቢናገር ፍጅቱን ለማስቆም ይቻለው የነበረ የማህበረሰብ ክፍል እዚህ ጉዳይ ላይ በአመለካከት ደረጃ የትጋር እንዳለ ስላወቁና መበረታት ስለሆናቸው ነው። ቢመርም ይህ እውነታ ነው።

ሌላው በአገራችን ፖለቲካ ነክ በሆነ ጉዳይ ላይ ለመናገር ሚሚ ስባቱ፤ ዳዊት ከበደ፤ እርእዬትና አማረ አረጋዊ የመሳሰሉት …..አይነቶቹ ብቻ ሲቀሩ። ይህ ይሆን ዘንድ የጋዜጠኞች ፍጅት ስለተፈፅመ ብቻ አይደለም። እውነታው ያንድን ዘር ፍፁም የበላይነት ለማስጠበቅ ሲባል ሁለንተናዊ በሆነ ቀስ በቀስ ሲካሄድ የነበረ መንግስታዊ ሌሎችን የማጥፋት ዘመቻ ስለነበረ ነው። እውነቱ ይሄ ሆኖ ባለበት ተመርጠው የቀሩትን እያዳመጠ ማመን የሚፈልግ ማመን መብቱ ነው። በምንም መንገድ ሰርዓታቸው የሚጎዳበትን ነገር የዚህ አይነት ሜዲያዎች እንደማይንግሩን ግን እሙን ነው። ችግሩ ወያንያዊ ነው መቼም አይሉህም።

ዜጋው ግን፤- ክትናንት ዛሬ ነፃነትን የምንናፍቀው ብቻ ሳይሆን ሊኖረው የሚያውቅበት መሆኑን አሳይቷል። ኢትዮጵያዊነት፤ አንድነትና ፍቅር መቼም ቢሆን ችግር እንዳልነበረ ዳግም አስረግጧል። እፈሩ ሲል ይህ ማንነቴና ኑሮዬ ነው እያለ ነው ያለው።

ዜጋው ግን፤- ይህ ሁሉ ፍጅት፤ የሚያስተዛዝቡ ሁኔታዎች በበዙበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይህ ወያኔያዊ ስርዓት ሳይፈርስ ትግሉን ላያቆመው ተማምሎ ሰላማዊ ትግሉን አበርትቶ ቀጥሏል።

ዜጋው ግን፤-በብዙ ሺዎች ተገለው በሚሊዮኖች ተፈናቅለው፤ በሚሊዬኖች እየተሳደዱ ባለበት ክህፃን እስከሽማግሌ፤ ከገበሬ እስከ ምሁር ፍጅት ወያንያዊ መሆኑን ያውቃል። ወለም ዘለም በሌለበት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህንኑ ብቻ ይናገራል።

ዜጋው ግን፤- መሰረቱ የህዘብ አወንታ የሆነ የተገደበ ስልጣን ግድ መሆን አለበት እያለ ነው። እኩልነት ላይ የተመሰረተ ዜግነት፤ ነፃ የፍትህ ስርአት፤ ነፃ ፓርላማ፤ ነፃ ምርጫ ይቻላል እያለ ነው። ከዚህ ያነሰ በጭራሽ አንወሰድም ነው እያለ ያለው። ደግሞ ወደዚህ የሚያደርሰውን ትክክለኛ መንገድ ነው የያዘው። መዳረሻው ይህ እንደሚሆንና ጉዞው ወደዛ እንደሆነ ግልፅ ብሎ መታየት በመጀመሩ ይህንን መስካሪው እየጨመረ የሄደበት እውነታ ሀቅ ነው።

ለማና ገዱ በአስቸኳይ ኢህአዲግን አፍርሱ (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Lemma Megersa and Gedu Andargachew

የዘንድሮው ህወሀት በሁለት መልኮች ይገለጻል። አንደኛው በፍርሃት የሚናጥ፡ በማያባራ ህዝባዊ ማዕበል ወንበሩ የተናጋ፡ ወድቀቱን በቅርበት እያየ በስጋት እየተርገፈገፈ የሚገኝ፡ ሳር ቅጠሉ የተጠየፈው፡ ድርጅት ነው። ሌላኛው መልኩ ደግሞ መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚፎክር፡ በመጨረሻው ሰዓት ንሰሀ መግባት ሲገባው ሃጢያቱን የሚከምር፡ ሞት ደጃፍ ቆሞ የሚሸልል፡ ዕብሪትና ጥጋብ በስተርጅናም ያለቀቀው፡ ለአንድም ቀን ቢሆን በስልጣን ለመቆየት ሀገር ከማፍረስ ወደኋላ የማይል፡ ሃላፊነት የጎደለው፡ ሞራል የደረቀበት፡ ”እኔ ከሞትኩ…” መስመር ላይ ወጥቶ ወደግዙፍና መጠነ ሰፊ ጥፋት የሚጋልብ ድርጅት ነው።

ለጊዜው ወደተቋረጠው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላምራ። የደህነንቱ ሹሙ ቦግ ብሏል። ተቆጥቷል። ፊቱ ቲማቲም መስሏል። ዓይኑን ያጉረጠርጣል። እንደልማዱ ማስፈራራት ላይ ነው። ባሳደግን ተናቅን፡ ባጎረስን ተነከስን ዓይነት ስሜት ውስጥ ሆኖ በንዴት ይወራጫል። ወዲያውኑ ደግሞ ይቀዘቅዛል። ስሜቱ ይበርዳል። “ከሀይ ስኩል ጀምሮ ያሳደግናችሁ እኛ ነን። በጣም ጠንካሮችና ጎበዞች በመሆናችሁ እኔ በግሌ እኮራባችኋለሁ። ብዙዎች አገር ትተው ሲሸሹ እናንተ ግን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሕዝብ ጎን በመቆማችሁ ምስጋና ይገባችኋል፤ ሆኖም ግን አገር ሲመራ መቸኮል አያስፈልግም፤ ሰከን ማለት ይገባል” ዓይነት ምክር ለመስጠት ይሞክራል። ጭንቀት። ስጋት። ፍርሃት። ደግሞም ትዕቢት፡ ድንቁርና፡ እየተፈራረቁ ያንገላቱታል።

ቀን በገፋ ቁጥር ልዩነት እየጎላበት የመጣው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በጌታቸው አሰፋ ድንፋታ፡ ማስፈራሪያ የተሞላ ሆኗል። ከመነሻው ወጥረው የህወሀትን ማንቁርት አንቀው ”እኩልነት ወይሞ ሞት” የሚል መፈክር ያነገቡት እነለማና ገዱ ከዚህ ሰውዬ ጋ የገቡበት ፍጥጫ በስብሰባ አዳራሽ ያለውን የሃይል ሚዛን እየቀየረው ነው። ህወሀት በጌታቸው አንደበት እየተናገረ ነው። እነደብረጺዮን፡ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የህወሀት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከደህንነት ሹሙ ጀርባ አድፍጠዋል። አቶ ለማ መገርሳና ዶ/ር አብይ አህመድ የስብሰባው የመጀመሪያ ቀን ቆፍጠን፡ ኮስተር ብለው ያስቀመጡት አቋም፡ ያንንም የገዱ ቡድን ድጋፍ መስጠቱ ለህወሀት ያልተጠበቀ መርዶ ነበር የሆነው። ”ህዝብ ቀውስ ውስጥ ገብቶ፡ ሀገሪቱ በትርምስ እየተናጠች እኛ የምንሰብሰበው ለምንድን ነው? ቅድሚያ ለህዝባችን መድረስ አለብን” የሚለው የእነ ለማ አቋም እንደተሰማ የደህንነት ሹሙ ብድግ አለ። ሁኔታው አላማረውም። ህወሀት አደጋ ላይ ነው። የሆነ ነገር ማድረግ አለበት።

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጥሩ አድርጎ አስተምሮታል። መለስ በፓርላማ የኦሮሞ ተወካዮች በጥያቄ ወጥረው ሲይዙት ”እናውቃለን። ቀን ከእኛ ጋር ማታ ከኦነግ ጋር እንደምታወሩ የማናውቅ እንዳይመስላችሁ” ብሎ አጀንዳ ማስቀየስ፡ አፍ ማሲያዝ ለምዷል። ጌታቸው አሰፋ ይህን የመለስ ሸልፍ ላይ አዋራ ጠጥቶ የከረመ ስትራቴጂ አራግፎ መጠቀም ፈልጓል። እናም ሁኔታዎች የህወሀትን የበላይነት ህልውና አደጋ ውስጥ የሚከቱ ሆነው ሲመጡ፡ ”ከሀይስኩል ጀምሮ ያሳደግናችሁ……” አለና ጀመረ። ለአቶ ለማና ለዶ/ር አብይ መሆኑ ነው። ረጅም በማስፈራሪያ የታጀበ ዲስኩር ከለቀቀ በኋላ ”ከኦነግ አመራር ጋር የተጻጻፋችሁት፡ በስልክ ያወራችሁት በእጃችን አለ። አይተን እንዳላየን በዝምታ አለፈን እንጂ የማናውቅ እንዳይመስላችሁ”

ጌታቸው አሰፋ ገዱ ላይም ዞረ። “ገዱ የአማራ ክልልን ማረጋጋት አልቻልክም፤ ክልሉ በቁጥጥር ስር ነው ማለት ያዳግታል” አለው። ቀጠለ- ሰውዬው። ” “ለሀገር አይጠቅምም ብለን ነው እንጂ ብዙ ማስረጃ በእጃችን አለ” በማለት ጌታቸው የተቀረፀ ድምጽ አሰማና ተዝናንቶ ተቀመጠ። ገዱ የዋዛ አልነበረም። ”ክልሉን ማረጋጋት እንዳንችል የእናንተ ጣልቃ ገብነት አስቸገረን። አሁን የሰማነው ድምጽ ደግሞ የእኔ አይደለም። ከሆነም በፍርድ ቤት ክሰሰኝ እንጂ እዚህ ማሰማት ምን ይጠቅማል?” በማለት በድፍረት ተናገረ።

ከዚህ ቀደም ለመጥቀስ እንደተሞከረው እነለማ ከዚህ ስብሰባ ከሚያገኙት ይልቅ የሚያጡት ይበልጣል። ስብሰባውን ረግጠው መውጣት፡ ከሆነላቸውም ኢህአዴግ የተባለውን የኩሸት ቤት ማፍረስ፡ ከዚያም አልፈው በህወሀት አምሳያ፡ አሻራና የበላይነት የቆመውን መንግስት ገንድሰው በመጣል አዲስ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ማድረግ ካልቻሉ ይህ ስብሰባ በረዘመና ጊዜ በወሰደ ቁጥር ለህወሀት አፈር ልሶ መነሳት እድሉን ይሰጣል የሚል ሀሳብ ተሰንዝሮ ነበር። አሁን እየሆነ ያለው ይሄው ነው። ህወሀት አንገቱን ከደፋበት ቀና እያደረገ ነው። ከተከላካይነት ወደ አጥቂ መስመር ላይ ወጥቷል። እነለማ እንደአጀማመራቸው ሊቀጥሉ አልቻሉም። እንደምንሰማው ከሆነ አቶ ጌታቸው አሰፋ በእነለማና ገዱ ላይ የጀመረው ማስፈራራት መስመር ይዞለታል። በተወሰነ ደረጃም ተሳክቶለታል። በተለይ ከኦህዴድና ከብአዴን ተንሸራተው ህወሀት ጎጆ ውስጥ የገቡ ሰዎች እነለማንና ገዱን አጋፈጠው ሰጥተዋል።

”“ችግሩ አማራ ላይ ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያም ላይ ነው“ ብሎ መጀመሪያ የተነሳው ወርቅነህ ገበየሁ ነበር። የተጠና አካሄድ ይመስላል። ህወሀቶች የቤት ስራቸውን ሲሰሩ ቆይተዋል ማለት ነው። አንገታቸውን ሰብረው፡ የተሸነፉ፡ እጅ የሰጡ መስለው ከቆዩ በኋላ አሁን ቀና ብለው የበቀል ጅራፋቸውን እያስጮሁ ነው። ወርቅነህ ገበየሁ፡ የእነለማን ቡድን በማጥቃት፡ ለጌቶቹ ህውሀቶች ጥብቅና በመቆም ተናገረ። አቶ ዲሪባ ኩማም የጌታቸው አሰፋን ልብ በደስታ ያዘለለ፡ ህወሀቶችን ያስቦረቀ፡ እነለማን እንደይሁዳ አሳልፎ የሰጠ ንግግር አደረገ። ሌላኛው የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማም ጨመረበት። እነለማ ላይ ሁለት ግንባሮች በይፋ ተከፈቱ። ከበብአዴን በኩልም በተመሳሳይ አለምነው መኮንንና ከበደ ጫኔ ከህውሀት በላይ ህወሀት ሆነው በመቅረብ እነገዱ ላይ የውግዘት መዓት አወረዱ። ከኦህዴድና ከብአዴን ስራ አስፈጻሚ አባላት የመጣው ተቃውሞና መንሸራተት ለጊዜው የእነለማንና ገዱን የለውጥ ግስጋሴ አስቁሞታል።

በፓርላማ አባላቱ አስቸኳይ ጥሪ ምክንያት ስብሰባው ተቋርጧል። የሃይል ሚዛኑ ወደ ህወሀት ያጋደለ መስሏል። ገዱ ወደአሜሪካ መምጣቱ ታውቋል። ለህክምና ነው። ጨርሶ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ይመለሳል ተብሏል። አስደናቂ ለውጥ አሳይተው በብዙዎች ዘንድ ተስፋን የጫሩት የፓርላማ አባላት ከአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ምን እንደተነጋገሩ የሚነግረን እስከአሁን አልተገኘም። ከአቶ ሃይለማርያም የሚሰማው ቁምነገር ያለው ባይሆንም የፓርላማው አባላት ወክለነዋል ለሚሉት ህዝብ መረጃ መንፈጋቸው ወይም እንዳይናገሩ አፋቸው መቆለፉ የህወሀትን ማንሰራራት ያመላክታል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። በእርግጥ በዝጉ የፓርላማ ስብሰባ አዲስ ነገር እንደሌለ ጭምጭምታው ተሰምቷል። ”በኢህአዴግ የውስጥ ዲሞክራሲ መሰረት የተፈጠሩትን ችግሮች እንፈታለን” በምትል አንዲት አረፍተ ነገር የፓርላማው ግርግር ተቋጭቷል።

እነለማና ገዱ ሁለት ግንባሮች ጋር መላተማቸው በስብሰባው አዳራሽ ውስጥ ያለውን የበላይነታቸውን እንዳሳጣቸው ማረጋገጥ ተችሏል።ከጌታቸው አሰፋ ድንፋታ፡ ማስፈራሪያ ይልቅ ከጎናቸው የሚገኙ ጓዶቻቸው መንሸራተት ለእነለማ በጀመሩት ፍጥነት እንዳይራመዱ አድርጓቸዋል። እነወቅነህ ገበየሁ በዚህን ቀውጢ ወቅት ከዳር እስከዳር ለሚሰማው የህዝብ የለውጥ ድምጽ ጆሮአቸውን ዘግተው ለጌታቸው አሰፋ ቡራ ከረዩ ማስፈራሪያ እጅ ሰጥተዋል። ለጊዜው የእነለማ ቡድን መለሳለስ ማሳየቱም እየተነገረ ነው። ገፍተው እንዳይሄዱ ከጓዶቻቸው የተከፈተባቸው አዲስ ግንባር በዚያ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ጉልበታቸውን አዝሎታል። ሁለቱንም ግንባሮች ለመመከት የሚያስችል አቅም እዚያ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የላቸውም። እንደሚባለውም፡ ለመገመትም የሚቻለው እነለማ ለጊዜው ተለሳልሰው ተስማምተው ከመውጣት ውጪ ያለው አማራጭ ፊት ለፊት መላተም ነው።

እንግዲህ የቁርጡ ጊዜ ደርሷል። ከአፍንጫችን ስር ነው። በእኔ እምነት እነለማ/ገዱ አማራጭ አላቸው። እዚህ ነገር ውስጥ ሲገቡ ከህውሀት ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል ቀድመው እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ። ከህወሀት መሪዎች ጋር በተለይም ከደህንነቱ ሹም ጋር ለዓመታት የሚተዋወቁ በመሆናቸው የህወሀትን ቁማር አስቀድመው ያውቃሉ ብሎ መናገር ይቻላል። እንኳን እነሱ የውጭ ታዛቢም የህወሀትን እያንዳንዷን እርምጃ በሚገባ ያውቃል። ህወሀት በሀሳብ ድርቀት የሚሰቃይ፡ በድንቁርና በተሽቆጠቆጡ መሪዎች የሚመራ ኋላ ቀር ድርጅት በመሆኑ ስለሚያደርጋቸው ነገሮች መገመት በጣም ቀላል ነው። እናም እነለማ አሁን እየሆነ ያለው ያልጠበቁት ዱብ እዳ ነው ለማለት ይከብዳል። ጌታቸው አሰፋ ቢላዋ ስሎ፡ በሀሰት ማስረጃ፡ ለማስፈራራት እንደሚመጣ ቀድመው ልቅም አድርገው ያውቁታል። በዚያ የስብሰባ አዳራሽ እናሸንፋለን የሚል ተስፋ ከውስጣቸው ከነበር የተሳሳተ ስሌት ነበራቸው ማለት ነው። የእነሱ ጉልበት ከውጭ ነው። አሸናፊነታቸው ከአዳራሹ ባሻገር ነው።

አዎን። ህወህት ካደፈጠበት ቀና እያለ ነው። ለጥቂት ቀናት አንገቱን ከቀበረበት አውጥቶ የበቀል በትሩን ሊሰነዝር ተዘጋጅቷል። የመጀመሪያ ሰለባዎቹ እነለማ መሆናቸው ጥርጥር የለውም። የኦሮሞ ህዝብ ያነሳውን ተቃውሞ የጥቅላይ ሚኒስትርነቱን ወንበር በመስጠት እናስቆመዋለን በሚል ከኦህዴድ ሰው እያፈላለጉም እንደሆነ ይነገራል። ይህ ህወሀት ለኦሮሞ ህዝብ ያለውን ንቀት ከማሳየት ባለፈ ለውጥ የለውም። ነጻነት፡ ፍትህና እኩልነት ለተራበ ህዝብ የሞግዚት ወንበር በመስጠት አጠግባለሁ ብሎ መነሳት አሳፋሪ ነው። የኦሮሞ ህዝብ እኩልነትን ጠይቋል። በገዛ ሀገሩ የባይተዋር ኑሮ በቃኝ ብሏል። ለዚህም መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። ይህን የህዝብ ጥያቄ በህወሀት የሞግዚት ወንበር ላይ አንድ የኦሮሞ ልጅ በማስቀመጥ ይመለሳል የሚል ድፍረት ከህወሀት መንደር እየተሰማ ነው። መከላከያውንና ደህንነቱን የማይቆጣጠር የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ለኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ መልስ አይሆንም።

እነለማ/ገዱ ከፍርሃት ቆፈን የተላቀቁ እንደሆነ ይሰማኛል። ከጌታቸው አሰፋ ድንፋታ በላይ የህዝባቸው የለውጥ ረሃብ እንደሚያንበረክካቸው እረዳለሁ። በመጨረሻው ሰዓት በጓዶቻቸው ቢካዱ እንኳን የጀመሩትን መስመር መልቀቅ አደጋው ከማንም በላይ ለእነለማ/ገዱ ነው። በአዳራሹ የታመቀውን ሚስጢር ለህዝባቸው በይፋ ገልጸው የሚመጣውን ሁሉ መቀበል እንጂ ከዚህ በኋላ ማፈግፈግ አደገኛ ነው። ህወሀት ከእንግዲህ ለእነለማ ጉድጓድ ከመማስ ውጪ በስልጣን እንዲቆዩ የሚፈቅድ አይሆንም። ደጋፊዎቻቸው ሰልቅጧቸው፡ ብሏቸው እያለ ነው። ቅስቀሳው ከወዲሁ በህወሀት መንደር ጦፏል። ጌታቸው አሰፋ የህወሀት የጋዜጠኞች ስኳድ ወደ ሶማሌ ክልል በመላክ የዘር ፍጅት ፕሮግራሞችን እንዲያዘጋጁ ያዘዘው ያለምክንያት አይደለም። ለእነ ለማ ወጥመድ እያዘጋጀ መሆኑ አይጠፋንም።

እነለማ/ገዱ ላይጨርሱት አልጀመሩም። የትኛውንም ዋጋ በመክፈል የህወሀትን መርዝ ማርከስ አለባቸው። በዝግ የሚደረገውን ስብሰባ ለአደባባይ ያበቁት ዘንድ ይጠበቃሉ። ከህወሀት ጋር ሚስጢር ከህዝብ ያጋጫል። ከህዝብ ልብ ያጠፋል። ብሎም ለአሳፋሪ አወዳደቅ ይዳርጋል። በቃ! እየሆነ ያለውን ያፍርጡት። ለህዝብ ይንገሩ። የተሸፈነውን ይግለጡት። የተደበቀውን ያጋልጡት። ህወሀት ቢተፋቸው ህዝብ ይቀበላቸዋል። ሳምባው አልቆ በአርቴፊሻል ኦክሲጅን እየተነፈሰ ካለ አገዛዝ ጋር ከዚህ በላይ አብሮ መጓዝ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ለማና ገዱ ኢ- ህ -አ -ዴ- ግ ን አፍርሱና ከህዝብ ተቀላቀሉ። ዛሬ አይደለም። አሁኑኑ።

በአማኙ የተረሱት መነኮሳት በደል በርትቶባቸዋል (በጌታቸው ሽፈራው)

በጌታቸው ሽፈራው

The Waldeba priests in prison

በእስር ላይ ከሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት መካከል አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት ፀሎት ያደርጋሉ፣ ለእስረኞች ምግብ ያካፍላሉ፣ ፀበል ይሰጣሉ ተብለው ጨለማ ቤት ከገቡ ሰነባብተዋል። የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ ሲጠየቁ አላወልቅም በማለታቸው ተደብድበዋል።

ትናንት ታህሳሰ 19/2010 ዓም ደግሞ ዞን ሁለት የነበሩት አባ ገ/እየሱሰ ኪ/ማርያምም ፀሎት ያደርጋሉ፣ የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ ሲጠየቁ እምብይ ብለዋል በሚል ጨለማ ቤት ገብተዋል።

ያው በእኛ ሀገር በሁሉም መስክ ባለ ጊዜን እንጅ መከረኛን ብዙ ሰው አያስታውሰውም። እነዚህ ለእምነታቸው የቆሙ መነኮሳት በሲኖዶሱ ሰፈር ቢሆኑ ዘመናዊ መኪና ልግዛላችሁ የሚለው ብዙ ነበር። ደጅ የሚጠናው ደጁን ይሞላው ነበር። አሸርጋጁ ብዙ ነበር። እነዚህ መነኮሳት መከታ ያደረጉት እውነትን እንጅ ስልጣን ላይ ያሉትን ስላልሆነ ብዙ አማኝ “የራሳቸው ጉዳይ” ብሎ ትኩረት የነፈጋቸው ይመስላል።

መምህር ግርማ የታሰሩ ሰሞን የጠያቂያቸው መዓት፣ ፍርድ ቤታቸውን የሚከታተለው ሰው ብዛት ታይቷል። እነዚህ መነኮሳት ህዝብ አለኝ የሚለው ገዳም በመነካቱ አቤት ሲሉ ጥርስ ተነከሰባቸው። ታሰሩ። እየተሰቃዩ ነው። በግል ጉዳይ ጮሌ “ሰባኪ” ታሰረ ሲባል የሚጎርፈው ገዳማት መፍረሰ የለባቸውም ብለው ሲታገሉ ለኖሩት ትኩረት የለውም! ረስቷቸዋል። አሳሪዎቹም የሚጮህላቸው የለም ብለው የስቃይ በተራቸውን አጠንክረውባቸዋል!

ከኢትዮጵያውያን የእርቅና የዲሞክራሲ መድረክ በሚኒሶታ የተሰጠ አስቸኳይ ሕዝባዊ መግለጫ

Ethiopian Forum for Reconciliation and Democracy

አስቸኳይ ህዝባዊ መግለጫ

እኛ በአሜሪካን አገር በሚኒሶታ ስቴት የምንኖር ከተለያዩ ማህበረሰብ (የኦሮሞ፤ የአማራ የከምባታ፤ ጉራጌ ወዘተ) የተሰበሰብን ኢትዮጵያውያን በጎሳ፤ በቋንቋ ፤በሃይማኖትና በፖለቲካ ተለያይቶ የነበረውን ወገናችንን ለማቀራረብ፤ ልዩነታችን በውይይት ለመፍታት ደስታውንም ሀዘኑንም አብረን ለመወጣት፤ኢተዮጵያ ላሉትም ወገኖቻችን በችግራቸው ለመድረስ እንድንችል እንዲሁም በፍቅርና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነት በመፍጠር የሆነ የህዝብ ለህዝብ የዉይይት መድረክ አቋቁመን ከ8ወር በላይ ስንወያይ ቆይተናል።
እንደምታዉቁት ባለፉት 27 ዓመታት ህዝባችን አብሮ እንዳይኖር በተለይም አገራችን ኢትዮጵያን ብሎም ለአፍሪካ አህጉር የነጻነት ተጋድሎን እንዲሁም ነጻ አገር በማቆም ሰፊ ድርሻ ያለዉን የኦሮሞና የአማራን ማህበረሰብ በመከፋፈል የወያኔ ጠባብ ቡድን ብቸኛ ዘራፊ በመሆን የጥፋት ዘመቻ በማራመድ የተሰማራዉ ማቆሚያ የሌለዉ የግፍ አገዛዝ የሚያካሂደዉ ጀምላ ጭፍጨፋ እጅግ አሳስቦናል። የሁለቱን ትልቅ ማህበረሰብ የአብሮነት ሃረግ የሆነዉን የትስስር ገመድ ለመበጣጠስ በጠላትነት አይን እንዲተያዩ ሲቀርጽ የነበረዉ የጥላቻ ግድግዳ አደገኛና አፍራሽ ተልኮ ዓለም ያወቀዉ ምስጢር ሁኖ ቆይቷል። ይህ እኩይ ሴራ በህዝቡ የአንድነት ትግል በመፍረስ ላይ ይገኛል።

በሌላ በኩል ተስፋ ሰጭ የሆነዉ ደግሞ በቅርብ ወራት የሁለቱ ትልቅ ህዝቦች በአገር ቤት እየተካሄደ ያለዉ የአንድነት ህዝባዊ ምክክር በሚኒሶታ ለጀመርነዉ የመተባበር ስራ ዋና የትብብር ህብረት መነሻ መሰረት እና መልካም የታሪክ ክስተት ሁኖ አግኝተነዋል። በተለይ የጎንደር፤ የባህርዳርና የአዳማ የሰልፍ መልዕክት የሚረሳ ታሪክ አይደለም። በጣና ሃይቅ በኦሮሞ ወንድሞችና እህቶቻችን የተደረገው የእምቦጭ ነቀላ ትብብር፤ የባህርዳር ህዝባዊ ምክክር የእዉነተኛ የሁለቱን ህዝቦች ታሪክ አጸባራቂነቱ ለሁሉም አርአያ እንደሆነ እርግጠኛ ነን። እኛም አራያነቱን በሙሉ ልብ ተቀብለናል።

በተለይ በአሁኑ ወቅት ወደ ግፍ አገዛዝ ማስወገድ የህዝባዊ ትብብር መሸጋገሩ ከዛሬ ሥምንት ወራት በፊት የጀመርነዉ የምክክር መደረክ ለፍትህ አዋጭ መሆኑን ተገንዝበናል-። በመሆኑም በሚኒሶታ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ከሁሉም ማህበረሰብ ጋር በትብብር ተደራጅተን አገር ቤት ላለዉ ወገናችን ሙሉ ድጋፍ መስጠት ጊዜ የማይሰጠዉ አገራዊ እና ሰብአዊ ግዴታችን መሆንን ተቀብለን የሚቻለዉን አስተዋጽኦ ለማድረግ አጠንክረን በመስራት ላይ እንገኛለን። በዚህ እረገድ በጥሩ ቀን አገር ያፈራቻቸዉ ብርቅዬ የሃይማኖት አባቶች ፤ታዋቂ ምሁራን፤ ወንድምና እቶች ለዚህ ህዝባዊ የትብብር ዓላማ በሙያቸዉ ፤በገንዘባቸዉ፤በጉልበታቸዉ ለመርዳት ከጎናችን መሰለፋቸዉን በደስታ መግለጽ እንወዳለን።

ሌላዉ ማስገንዘብ የምንፈልገዉ በአገራችን በአሁኑ ወቅት በእዬለቱ የሚከሰተዉ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ነዉ። ህዝባችን በሞት ሽረት ትግል ላይ ይገኛል። በተለይም ለዘመናት በደስታም ሆነ በመከራ ተባብሮና እና ተቻችሎ የኖረዉን ህዝባችን በማጋጨት የዝርፊያና የስልጣን እድሚያቸዉን ለማራዘም በጥላቻ የተሞሉ መሪወች 24 ሰዓት እሣት በመለኮስ ሥራ ተጠምደዋል፤ ነገር ግን ህዝባችን ዘርና ሃይማኖት ሳይለየዉ በአብሮነት ቁሞ በመጋፈጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ነዉ።

ባሁኑ ጊዜ ወሳኙ ወጣቱ ትዉልድ እጅና ጓንት ሁኖ ጀግንነት የተሞላበት ታሪካዊ ተጋድሎ በማካሄድ ላይ ነዉ። የነጻነቱን የአመጽ መዓበል ወደ ድል አቅጣቻ እዬዘወረ የማይቆምበት ደረጃ ደርሷል። ይህን የህዝብ ነጻነት ትግል ተባብረን በሙሉ ልብ እንደግፋለን። ለዚህም ቃል እንገባለን ። ጥላቻን ጥበብ አድርጎ የተነሳዉ የወያኔ ቡድን ኦሮሞና አማራን ለማጋጨት ያልቆፈረዉ ጉድጓድ የለም፤ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ሱማሌና በኦሮሞ ማህረሰብ መካከል በታጠቀ ወታደራዊ ሃይል የደም ማፋሰስ እኩይ ሴራን አሁንም በድጋሜ እናወግዛለን።

ሰላማዊ ጥያቄ ባቀረቡ በትምህርት ተቋም ባሉ ተማሪወች ህይወት መጥፋት የገዥሁ መደብ ቅንብር የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የከፋፍለህ ግዛ የ27 ዓመታት አጀንዳ መሆኑን በመረዳታችን እጅግ ስላሳዘነን ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ትግሉ የኛ (ኬኛ) ብለ የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ጣና ላይ እምቦጭን ለማጥፋት ፈጥነዉ እንደደረሱት የጎንደር/ባህርዳር ሰልፈኛ የኦሮሞ ደም የኛ ደም ነዉ እንዳለዉ አዳማም የትግል ምላሽ እንደሰጠ እኛም በሚኒሶታ የምንኖር የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ጭፍጨፋዉ፤ ግርፋቱ፤ በእስር መንገላታቱ፤ በበሽታ፤ በረሃብ መጎዳቱ እንዲሁም ሥደቱ ሁሉ በቃ ያመናል ብለን ትግሉ የሚጠይቀዉን መስዋዕትነት ለመክፈል ከጎናችሁ መሆናችን እንድታዉቁት እንፈልጋለን።

ይህ መድረክ የነጻነት ትግሉን የሚደግፈዉ ዋና እራይና ማግኘት የሚፈልገዉ የትግል ዉጤት ዘረኛውንና አገር አፍረሹን ስርአት አዉርዶ ሌላ አዲስ ጨቋኝ ገዥ ለመተካት አይደለም። ይልቁን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ያለ ተጽዕኖ ሁሉን የአገሪቱ ዜጋ ያሳተፈ በዘር፤ በጾታ፦

በሃይማኖት ፤ በእድሜ አድሎ ሳያደርግ የሚያስተዳድር ፍትህ/እርትዕ የሰፈነባት፤ ዜጎች በህግ የበላይነት የተከበሩባት መሰረቱ ድሞክራሲያዊ የሆነ የህዝብ ሥርዓት እዉን ለማድረግ ነዉ። ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ለመተግበር እና ህዝቡ የሚያካሂደዉን ትግል ለማሳካት በቅድሚያ ሃላፊነቱ እና የትግሉ መሪ ኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለዉ ቢሆንም በዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን በህብረት ቁመን ለሰዉ መብት ተቆርቋሪ ከሆኑ መንግስታት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፤ ከማህበራዊ ድርጅቶችና ከአገር ወዳዶች ጋር ተባብረን ድምጻችን በማሰማት አስፈላጊ የሆነዉን እገዛ ለማድረግ ከጎናችሁ መሆናችን እናሳዉቃለን:-

በመሆኑም
1ኛ) ሁሉም በሽብር ስም የታሰሩ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ (ሕክምና የሚያስፈልጋቸውም ባስቸኳይ ሕክምና እንዲያገኙ
2ኛ) የ27 ዓመታት የግፍ አገዛዝ በቃን ላለዉ ህዝብ ጥያቄ አስቸኳ ምላሽ ይሰጥ
3ኛ) ሁሉን ኢትዮጵያውያን ያካተተ ህዝባዊ ምክክር ይደረግ/ገዥዉ መንግስት ያለ መዘግየት
ስልጣን ለህዝብ ያስረክብ
4ኛ) በኦሮሞና በኢትዮጵያ ሱማሌ ማህበረሰብ ላይ የሚካሄደዉ ጭፍጨፋና ማፈናቀል በአስቸኳይ ይቁም
5ኛ) በትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት ዉስጥ በሚገኙ ወንድሞችና እህቶቻችን መካከል የመንግስት ወታደሮች ማዋከብና ማሳደድ ይቁም። ለጥያቄያቸዉ አስቸኳይ መልስ ይሰጥ::

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!! ሴንት ፖል ሚኒያፖሊስ፤ ሚኒሶታ

“አላቲኖስ” – መጽሐፍ በእኔ ዕይታ | መስከረም ለቺሣ (ዶ/ር)

አገራችን ኢትዮጵያ፡ አሁን ላለችበት የሥነ-መንግሥትና የነገረ-ሃይማኖት ክፍፍልና ቀውስ የዳረጋትን ታሪካዊ ሂደት በትክክል የሚመረምሩ ጸሓፍት፡ በዘመናችን ብዙ አይደሉም። አብዛኞቹ የነገረ መለኰት፣ የሥነ—መንግሥትና የታሪክ ልሒቃን፡ ለኢትዮጵያ ሃይማኖትና ሉዓላዊነት ጥሩ አመለካከት በሌላቸው የአገር ውስጥና የውጭ ኃይላት ዘንድ ይሁንታን ያገኙ መደበኛ አተራረኮችን (official history) ብቻ የሚከተል የሥነ-እውቀት ምርምር መርሕ የሚከተሉ መኾናቸው፡ ከአብዛኞቻችን የተሰወረ አይደለም። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸው የታሪክና የሃይማኖት ምሥክርነቶቻቸውም፡ ማንንም የማያስቆጣ አተራረክን እየተከተሉ መኼድ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ መኾናቸው፡ ብዙ እውነቶች ጎልተው እንዳይወጡና መጪው ትውልድ፡ እንደሕዝብ፡ በትክክለኛ መረጃዎች ላይ ተመርኩዞ፡ የነፍሱንና የስጋውን አቅጣጫ እንዳያስተካክል መሰናክል ፈጥረውበታል።

በሌላ በኵል ደግሞ፡ ደራሲዎች፣ ሙዚቀኞችና ሌሎች የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፡ እነዚህን ርእሰ ጉዳዮች ለመድፈር ብዙ ጊዜ ሲቸገሩ እናያለን። በ“ሃይማኖት” ስም አገርን የሚጎዱና አንድነትን የሚያናጉ አመለካከቶች እየተበራከቱ ሲመጡ፡ ጉዳዩን በቀጥታ አንስተው ትውልድን የመታደግ ሥራ እንዳይሠሩ፡ የሰዎችን “የሃይማኖት ነጻነት” የሚነኩ እየመሰላቸው፡ ዳር ዳሩን ብቻ ሲዞሩ የምናስተውለው ነገር ነው። ምናልባት፡ በጉዳዩ ላይ ከማናችንም የተሻለ ግንዛቤ ቢኖራቸው እንኳ፡ የአገሪቱን የፖለቲካና የሃይማኖት ግጭት እሳት የበለጠ እንዳያጋግሉት በመፍራት፡ ከርእሱ ወደኋላ ያፈገፍጋሉ። ፍርሓታቸው፡ አንዳንድ ጊዜ ትክክል ቢኾንም፡ አንዳንድ ጊዜ ግን አይደለም። ስለአገር ጉዳይ በይፋ መልእክት የሚያስተላልፉ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የመኖራቸውን ያኽል፡ ከርሱ ተነጥሎ ሊታይ ስለማይችለው ስለሃይማኖት ግን በቀጥታ የሚያነሱ ብዙ አይደሉም።

ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ ግን፡ ይህን ማመንታት “ወዲያ!” ብሎ፡ ያስጨነቀውን የኢትዮጵያዊነትና የተዋሕዶ ሃይማኖትን ዕጣ ፈንታ በዚህ ልብወለድ ውስጥ ፍርጥርጥ አድርጎ ጽፎታል! ይህ “አላቲኖስ” የተሰኘ ልብወለድ፡ የወቅቱን የአገራችንን መንፈሳዊና ፖለቲካዊ ቀውስ፡ በዋናነት፡ በክርስትና ሃይማኖት ውስጥ ያለውን መከፋፈል በሚመረምር መነጽር የተጻፈ ድርሰት ነው። ልብወለዱን፡ “ልብወለድ” እንበለው እንጂ የሚወክለው የገሃዱን ዓለም ግለሰቦች፣ ማኅበራትና ተቋማት ነው። አንዳንዶቹ በቀጥታ የተጠቀሱ ሲኾኑ፡ የሌሎቹን ማንነት ደግሞ ከገጸ ባሕርያቱ መገመት አይከብድም። በድርሰቱ ውስጥ፡ የደራሲው አቋም፡ ከገጸ ባሕርያቱ ግልጽ ቢኾንም፡ ጥሩ የኾነ ሚዛናዊነትና መልካም የስምምነት ተስፋም ይታይበታል። ቃልኪዳን፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን፡ ከሌሎች አብያተ እምነቶች ጋር የገባችበትን የወቅቱን ፍትጊያ፡ በተለይ፡ “ተሃድሶ” ስለሚባለው የእምነት አቋሟንና የኢትዮጵያዊነት መሠረት ያደረጓትን እውነታዎች የመሸርሸር እንቅስቃሴ፡ በሚገባና በቀላል አተራረክ ለአንባቢው ያሳየበት የተዋጣለት ሥራ ነው።

ከዚህ ቀደም በመካከለኛው ዘመን ማብቂያና በዘመናዊው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ (15ኛው — 16ኛው ክፍለ ዘመን)በአውሮፓ ተቀጣጥሎ የነበረው “ተሃድሶ” ወይም “Reformation” እና “ኅዳሴ” ወይም “Renaissance” የሚባለው እንቅስቃሴ፡ ምን ይመስል እንደነበረና፡ የካህኑ ዮሓንስ ( “Prester John”) ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ደግሞ ምን ያኽል ለእንቅስቃሴው ቀጥተኛ ምክንያት እንደኾኑ ያሳየሁበትን “(ኢ)ዩቶፕያ” የተሰኘውን መጽሓፌን፡ በመጀመሪያ በ2006፥ ከዚያም በድጋሜ በ2008 አሳትሜ ለንባብ አብቅቻለሁ። መጽሓፉ፡ የቶማስ ሞር “Utopia” የተሰኘው ድርሰት ትርጕምና የእኔ የምርምር ማስታወሻዎች የሚገኙበት ኹለት ክፍል ያለው ሲኾን፡ በተለይ ኹለተኛው ክፍል፡ እንግሊዝና ከርሷም ቀጥላ አሜሪካ፡ ”Renaissance” እና “Reformation” ብለው የሚጠሩት እንቅስቃሴ፡ ላለፉት 500 ዓመታት የኢትዮጵያን መንፈሳዊ ማንነት ነጥቆ በመውሰድ የራሳቸው ለማድረግ የተጓዙትን ረዥም ርቀት እንደኾነ፡ በማስረጃዎች በተደገፈ ትንታኔ ለማሳየት ሞክሬያለሁ። ደራሲ ቃልኪዳን ታድያ፡ እኔንም ባስደመመኝ መልኩ፡ የተነተንኳቸውን ዋና ዋና እውነታዎች፡ ከአሁኑ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የ“ተሃድሶ” ፈተና እና ሌሎችም ተግዳሮቶች ጋር ፍሬ ነገሮቹን በቀላሉ እያገናኘ፡ ለአንባቢ ቀላልና ሳቢ በኾነ የልብወለድ አጻጻፍ፡ በጥሩ ሁኔታ ተርኮታል።

እንግዲህ፡ በግልጽና በትክክለኛ የታሪክ መረጃዎች እየተደገፍን የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ስጋዊ ማንነት እንዲህ የምንመረምር ከኾነ፡ በጨለማ በእውር ድንብር ከመነታረክ ዘለን፡ በብርሃን መነጋገር እንችላለንና፡ አላቲኖስን የመሰሉ ሥራዎች የሚኖራቸው ሚና ቀላል አይኾንም። “ ‘አላቲኖስ’ ማለት ‘እውነት’ ማለት ነው” ይለናል፡ ደራሲው። እውነት ደግሞ፡ ነፃ ያወጣል፤ ያስማማል እንጂ ከፋፍሎ አይጨቁንምና፡ ጥሩ ውጤት ለትውልድ እንድናስገኝ፡ እውነታውን እንወቅ፤ እንመርምርም እላለሁ።

በዚህ አጋጣሚ፡ አንባቢዎች፡ አላቲኖስን አንብበው ሲጨርሱ፡ “(ኢ)ዩቶፕያን” ደግሞ አንብበው፡ ሙሉ እውነታውን በመረዳት፡ የሰፋ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስታወስ እወድዳለሁ።
አላቲኖስ ይቀጥላል!

ኢህአዴግ ሳይፈቅድ የህወሀትን ተጽእኖ ማስወገድ ይቻላል?

መንደርደሪያ – አሁን ያለው ሁኔታ (the status quo) (በአኖኒመስ)

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሀገሪቱ በፌደራላዊ ስርአት እንድትደዳደር ከመደንገጉ በተጨማሪ በውስጡ በርካታ ጥሩ ነገሮችን አዝሏል። በአለም አቀፍ ደረጃ (universally) የታወቁ ሰብአዊ መብቶች መጠበቅ እንዳለባቸው፣ ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር እንዳለባቸው፣ የመንግስት ስልጣን ገደብ እንዳለው፣ የፍትህ አካላቱ ገለልተኛና ከመንግስት ተጽእኖ ነጻ መሆን እንዳለባቸው፣ ወዘተ ደንግጓል። ሕገ መንግስቱ በነዚህና በውስጡ በያዛቸው ሌሎች ተራማጅ (progressive) ድንጋጌዎች ምክንያት በተለይ መጀመሪያ አካባቢ በብዙ ሰዎች ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትና ተስፋ ፈጥሮ ነበር። ነገር ግን የመንግስት የተለያዩ አካላት ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ ሕገ መንግስቱን በሰፊው ይጥሱታል፤ በዚህም ምክንያት በዜጎች ላይ ከፍተኛ እንግልትና ጉዳት ደርሷል።


ላለፉት 26 አመታት ኢህአዴግ የፌደራል መንግስቱንና አራት ክልሎችን (ማለትም አማራ፣ ኦርሚያ፣ ደቡብና ትግራይ) እንዲሁም አዲስ አበባን ብቻውን ሲገዛ ኖሯል። ኢህአዴግ የሚባለው ግንባር በውስጡ አራት ድርጅቶችን፤ ማለትም ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደህዴንና ህወሀትን ያቀፈ ይሁን እንጂ ዋናውና አዛዡ ህወሀት እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። የተቀሩት ሶስቱ “እህት” ድርጅቶች፣ በፌደራሊዝሙ አወቃቀር መሰረት በሚያስተዳድሯቸው ክልሎች እንኳ ሳይቀር፣ ያለህወሀት ፈቃድ ያሻቸውን ማድረግ ሳይችሉ እንደኖሩ ይታወቃል።

ህወሀት በፌደራል ፓርላማ ውስጥ ያለው ወንበር/ድምጽ 37 (6.7%) ብቻ ነው ። ስለዚህ የሚፈልገውን ፖሊሲ ፓርላማው በህግ መልክ እንዲያወጣለት ለማድረግ የሚያስፈልገው ወይም እርሱ የማይፈልገውን ህግ ፓርላማው እንዳያወጣ ለማደረግ የሚያስችለው አብላጫ ድምጽ ፓርላማ ውስጥ የለውም። ከሌላ አንድ ፓርቲ ጋር ቢቀናጅ እንኳ አብላጫ ድምጽ ማግኘት አይችልም። በአንጻሩ ኦህዴድ 178 (32.5%)፣ ብአዴን 134 (24.5%)፣ ደህዴን 108 (19.7%) ወንበር/ድምጽ አላቸው። ስለዚሀ ኦህዴድና ብአዴን ብቻ እንኳ ተቀናጅተው 57% ድምጽ ይኖራቸዋል። ኦህዴድና ደህዴንም ቢሆኑ በጋራ 52% ድምጽ ይኖራቸዋል። ነገር ግን የፓርላማው አባላት ያለ ህወሀት ፈቃድ ወይም የህወሀትና ደጋፊዎቹን ጥቅም የሚጻረር አንድም ህግ ማውጣት ሳይሳናቸው ኖረዋል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

አንዱ ይህ እንዲሆን ያስቻለው ምክንያት ህወሀት የፊደራል መንግስቱን የማስገድጃ ተቋማት አመራር ቦታዎች (ማለትም መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስና የደህንነት መ/ቤትን) ሙሉ ለሙሉ ለማለት ትንሽ እስኪቀረው ድረስ በቀድሞ ታጋዮቹና የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የህወሀት ደጋፊዎች ወይም አባላት ስላስያዘና ተቀናቃኞቹን ለማጥፊያ ወይም ለማዳከሚያ ሲጠቀምባቸው ስለሚታይ የሶስቱ “እህት” ድርጅቶች መሪዎችና አባላት በእጅጉ ይፈሩታል።

ሁለተኛውና ከዚህ ጋር የሚያያዘው ምክንያት አራቱ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ያስመረጧቸው የፓርላማው አባላት ፓርቲዎቻቸው ያልፈቀዱትን ህግ (በተለይ የህወሀትና ደጋፊዎቹን ጥቅም የሚጎዳ ከሆነ) ፓርላማው እንዳያሳልፍ/ እንዳያወጣ ማድረጋቸው ነው። ፓርቲዎቻቸው ደግሞ ኢህአዴግ (በጋራ) ያላጸደቀው (በሌላ አነጋገር ህወሀት ያልፈለገው) ህግ ከሆነ ተመራጮቻቸው ፓርላማ ውስጥ እንዲጥሉት/ እንዳያሳልፉት መመሪያ ይሰጣሉ። የሚያፈነግጥ የፓርላማ አባል ቢገኝ እንኳ ወንጀል ተፈልጎለትና ያለመከሰስ መብቱ እንዲነሳ ተደርጎ ወደ እስር ቤት ይወረወራል። ይህ አሰራር በግልጽ የህገ መንግስቱን አንቅጽ 54(4) የሚጻረር ነው።

ከጥቂት አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ፣ በተለይ ደግሞ በአማራና ኦሮምያ ክልሎች ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ሲካሄድ ቆይቷል። ተቃውሞው በአብዛኛው ያተኮረው የህወህት የበላይነትንና ለትግራይ ተወላጆች የሚደረገውን አድሎ በማስቀረት ላይ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የራሱ የኢህአዴግ አባል የሆኑት ሁለት ድርጅቶች (ማለትም ብአዴንና ኦህዴድ) ከፍተኛ መሪዎች የድርጅቶቻቸውንና የህዝባቸውን ድጋፍ መከታ በማድረግ የህወሃትን ተጽእኖና አዛዥነት ለማስቀረት ከፍተኛ ትግል ሲያደርጉ ይታያሉ። እንዲያውም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ውስጥ የህወሃት ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ተጽእኖ በእጅጉ እንዲቀንስ ማድረግ ችለዋል ማለት ይቻላል።

ሁለቱ ድርጅቶች በክልሎቻቸው ውስጥ የጀመሩትን የህወሀትን ተጽእኖ የማስወገድ ወይም የመቀነስ ትግል አሁን ደግሞ ወደ ፌደራል ደረጃ እያሳደጉት እንደሆነ ይታያል። ለምሳሌ እየተካሄድ ባለው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በሁለቱ ድርጅቶች ተነስቶ ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት አንዱና ዋነኛ ጉዳይ የህወሀት የበላይነት ማብቃት አለበት የሚለው ነው። የህወሀት መሪዎች እንዲህ አይነት ነገር የለም፤ ይህ የጠባቦችና የትምክህተኞች አመለካከት ነው፤ ወዘተ እያሉ ክደው ተከራክረዋል። ሆኖም የኦህዴድና የብአዴን መሪዎች በበኩላቸው የፌደራል መንግስቱ የማስገደጃ ተቋማት የአመራር ቦታዎች ሙሉ ለሙሉ ለማለት ትንሽ እስኪቀረው ድረስ የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የህወሀት ደጋፊዎች ወይም አባላት መያዛቸው፤ እነዚህን ተቋማትም በአዛዠነትና መሪነት ባስቀመጣቸው ሰዎች አማካይነት ህወሀት ላሰኘው ተግባራት ሲጠቀምባቸው እንደኖረ ጠቅሰው ይህ ከዚህ በኋላ መቀጠል እንደሌለበት፣ እነዚህ የመንግስት የማስገደጃ ተቋማት ህገመንግስቱ አንቀጽ 87(1) ላይ ባስቀመጠው መሰረት የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ስብጥር ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ ያካተቱ መሆን እንዳለባቸው አስምረው ተከራክረዋል።

እስካሁን የተመጣበት መንገድ ሀገሪቱንም፣ ህዝቧንም፣ ኢህአዴግንም፤ ህወሀትንም ጭምር አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደጣለ ለማንም ግልጽ ነው። በዚህ መቀጠል አይቻልም፤ ከዚህ ችግር መውጫ ሌላ መንገድ መገኘት አለበት።

የዚህች አጭር ጽሁፍ አላማ ኢህአዴግ/ህወሀት ሳይፈቅድ ወይም ኢህአዴግ/ህወሀትን ወደጎን በመተው ፓርላማው ህዝቡ እየጠየቀ ያለውን ለውጥ (የህውሀትን የበላይነት ማስቀረትን ጨምሮ) ማምጣት እንደሚችል ለማመላከት ነው።

የዚህ አመለካከቴ ምርኩዝ (premise) ኢህአዴግ ተፈጥሮአዊ ድክመት (inherent weakness) ያለው ሲሆን በተጻራሪው ደግሞ ፓርላማው ተፈጥሮአዊ ጥንካሬ (inherent strength) አለው የሚል ነው። ከዚህ ተነስቼም መደምደሚያዬ ላይ ፓርላማው እንዴት ተፈጥሮአዊ ጥንካሬውን በአግባቡ ተጠቅሞ ህዝቡ እየጠየቀ ያለውንና፣ ሀገሪቱም በእጅጉ የሚያስፈልጓትን ለውጦች ያለኢህአዴግ/ህወሀት ፈቃድ ማምጣት እንደሚችል እጠቁማለሁ።

የኢህአዴግ ተፈጥሮአዊ ድክመት (inherent weakness)

ከላይ እንደተጠቀሰው ኢህአዴግ አራት ድርጅቶች አባል የሆኑበት ግንባር ነው። ግለሰብ በኢህአዴግ ውስጥ አባል መሆን አይችልም። በየደረጃው የተዋቀሩት የግንባሩ የተለያዩ የስልጣን አካላትም ቢሆኑ (ማለትም ኮንግረስ፣ ምክር ቤት፣ ስራ አስ ይፈጻሚ) የተሞሉት በአራቱ ድርጅቶች ተወካዮች ነው። እያንዳንዱ ድርጅት እኩል ተወካይ ያዋጣል።

ከፍተኛው የስልጣን አካል ኮንግረሱ ሲሆን በተዋረድ ሁለተኛው የስልጣን አካል ምክር ቤቱ፣ ሶስተኛው ደግሞ ስራ አስፈጻሚው ናቸው። የኢህአዴግ አደረጃጀት ከላይ እንደተጠቀሰው ይሁን እንጂ እስካሁን ባሉት አመታት ኢህአዴግ በተግባር የተለያዩ ድርጅቶች/ፓርቲዎች እንዳሉበት ግንባር ሳይሆን እንደ አንድ ወጥ ፓርቲ ሲንቀሳቀስና ሲታይ ቆይቷል። ይህም ሊሆን ከቻለባቸው ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙብታል፤

የግንባሩ የተለያዩ አካላት ህወሀት የደገፈውን/የፈለገውን ውሳኔና አቋም ብቻ እንጂ እነሱ ቢፈልጉትም እንኳ ሌላ ውሳኔ ማስተላልፍ አይችሉም።
በዚህ አይነት ግንባሩ (በህወሀት ፍቃድ) የሚያስተላልፈውን ማንኛውንም ውሳኔ አባል ድርጅቶቹ በዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት መርህ መሰረት በአባሎቻቸውና በሚመሩት ክልል ውስጥ ተፈጻሚ የማደረግ ግዴታ አለቸው። የፓርላማ ተመራጮቻቸውንም ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያዙዋቸዋል።
በዚህ ምክንያት እንግዲህ ኢህአዴግ ጠንካራ ድርጅት መስሎና ሆኖ ቆይቷል። ይህ የሆነው ግን ግንባሩ ተፍጥሯዊ ጥንካሬ (inherent strength) ኖሮት ሳይሆን የህወሀትን ትእዛዝ አስፈጻሚ፣ አራቱም አባሎቹ እኩል ይሁንታ (say) የሌላቸው ስለነበረና ይህም በተግባር (effectively) እንደ አንድ ፓርቲ እንዲንቀሳቀስ ስላደረገው ነው። እንዲህ አይነቱ የግንባሩ ጥንካሬ ሊቀጥል የሚችለው የህወሀት ጥንካሬና በመንግስት የሀይል ማስፈጸሚያ መ/ቤቶች ውስጥ ያለው የበላይነት እስከቀጠለ ድረስ ብቻ ነው። ይህ ሲቀየርና አራቱም ድርጅቶች ያለተጽእኖ ወይም ያለፍራቻ መንቀሳቀስ ሲችሉ የኢህአዴግ ተፈጥሯዊ ድክመት ጎልቶ የሚወጣ፣ ጊዜያዊ ጥንካሬውም በኖ የሚጠፋ ይሆናል። በምትኩ ተፈጥሯዊ ድክመቱ ጎልቶ ይወጣል።

ለኢህአዴግ ተፈጥሯዊ ድክመት ምክንያት ከሚሆኑት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፤

የአራቱ ድርጅቶች ተውካዮች ሆነው በኢህአዴግ የተለያዩ የስልጣን አካላት ላይ የሚሳተፉት ሰዎች የላካቸውን ድርጅት አቋም ማንጸባረቅ ይጠበቅባቸዋል። ከዚህ ውጭ የግላቸውን አቋም ቢከተሉ የላካቸው ድርጅት ውክልናቸውን ሰርዞ በምትካቸው ሌላ ሰው ሊልክ ይችላል። ይህ አሰራር በአባል ድርጅቶቹ መሀል አለመግባባት/ሽኩቻ በሚኖርበት ጊዜ (ለምሳሌ አሁን ከህወሀት ጋር እንደተፈጠረው) የኢህአዴግ አቋም ተብሎ የሚወሰድ ውሳኔ ማስተላለፍ ብዙ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፣ ወይ ደግሞ ከነአካቴውም ውሳኔ ማስተላለፍ አይቻላቸውም። በዚህ ምክንያት ግንባሩ ውስጥ ሽባነት (paralysis) ይፈጠራል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ እየተካሄድ ባለው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ ይህ እየታየ ነው።
በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረ አለመግባባትና ሽባነት (paralysis) ወደ መንግስት አካላትም ሊዛመት ይችላል። ለምሳሌ ፓርላማው ለሀገሪቱ አስፈላጊ የሆኑ ህጎችን ለማውጣት የኢህአዴግን ውሳሌ የሚጠብቅ ከሆነ (እስከዛሬ ሲደረግ እንደነበረው) እንደዚህ አይነት ህጎች ሳይወጡ ረጅም ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ፤ ወይም ከናካቴውም ላይወጡ ይችላሉ። የህጉን መውጣት የተወሰኑ ድርጅቶች የሚፈልጉት ከሆነ ደግሞ (የግንባሩ አባል ሆኑም አልሆኑ) በፓርላማ ውስጥ መቀመጫ ካላቸው ሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር ህጉ እንዲወጣ ማድረግ ይችላሉ። ይህ ደግሞ ኢህአዴግን የበለጠ እንዲዳከም ወይም ተሰሚነቱ እንዲቀንስ ያደርገዋል።
ኢህአዴግ ተሳክቶለት የፖሊሲ ውሳኔዎች በሚፈለገው ፍጥነት ቢያሳልፍ እንኳ፣ የፓርላማው አባላት ለኢህአዴግ ውሳኔ ተገዢ በመሆን ያንን የፖሊሲ ውሳኔ ወደ ህግ የመቀየር ግዴታ የለባቸውም። እንዲያውም ለኢህአዴግ ተገዢ ሆነው ህግ ቢያወጡ ድርጊታቸው ከህገመንገስቱ ጋር የሚጋጭ ይሆናል፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 54(4) ላይ እንዲህ ይላልና፤
የምክር ቤቱ አባላት የመላው ህዝብ ተወካዮች ናቸው። ተገዥነታቸውም፤

ሀ) ለሕገ መንግስቱ፤
ለ) ለሕዝቡ፤ እና
ሐ) ለሕሊናቸው ብቻ ይሆናል።
የፓርላማው ተፈጥሮአዊ ጥንካሬ (inherent strength)

ፓርላማው የተቋቋመው በህግ፣ በተለይ ደግሞ የሀገሪቱ ህጎች ሁሉ ቁንጮ በሆነው በህገ መንግስቱ ነው። ተፈጥሮአዊ ጥንካሬውም የሚመነጨው ከዚህ አፈጣጠሩ ነው። በአንጻሩ ኢህአዴግ የተቋቋመው በአባሎቹ “መልካም ፍላጎት” እንጂ በህግ አይደለም።

ፓርላማው (በተለይ ደግሞ የተውካዮች ምክር ቤት) ከፍተኛው የሀገሪቱ ህግ አውጪ አካል ሲሆን ሕገ መንግስቱ በአንቀጽ 55 ስር ለፓርላማው እጅግ ብዙ ስልጣን (sweeping powers) ይሰጣል። አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፤

የጠቅላይ ሚኒስትሩን፤ የሚኒስትሮችን፤ የዳኞችንና የሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን ሹመት ያጸድቃል፤ ወይም ውድቅ ያደርጋል።
የፌደራል መንግስት፤ የሀገርና የህዝብ መከላከያ፤ የደህንነትና የፖሊስ ሀይል አደረጃጀትን ይወስናል። በስራ አፈጻጸማቸው ረገድ የሚታዩ መሰረታዊ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶችና የሀገር ደህንነት የሚነኩ ጎዳዮች ሲከሰቱ ያጣራል፤ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎት የፌደራል መንግስት ባልስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የህግ አስፈጻሚውን አካል አሰራር የመመርመር ስልጣን አለው።
ያስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያወጣል። የተለያዩ ህጎችን ያወጣል። የጦርነት አዋጅ ያውጃል፡፡
ከሁሉ በላይ ደግሞ መሰመር ያለበት ጉዳይ፤ ማንኛውም የፓርላማው አባል በሕገ መንግስቱ ውስጥ የተዘረዘረውን ስልጣኑን ተግባራዊ ሲያደርግ፤

ተገዢነቱ ለህዝቡ፣ ለሕገ መንግስቱና ለህሊናው ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል። ለፓርቲው አይደለም። ከፓርቲው ጋር ሳይግባባ ቀርቶ ፓርቲው ባይፈልገው እንኳ የፓርላማ ዘመኑ (term) ከማለቁ በፊት ከፓርላማ ሊያወጣው አይችልም።
በፓርላማው ውስጥ በሚሰጠው ድምጽ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም። አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም።
ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ፓርላማው ፍቃድ አይታሰርም፤ በወንጀል አይከሰስም።
ፓርላማውና የፓርላማ አባላት እነዚህና ሌሎችም በርካታ ስልጣኖች በህግ ተሰጥተዋቸዋል። እነዚህ በህግ የተደነገጉ ስልጣኖቻቸውና ጥበቃዎች ናቸው እንግዲህ ፓርላማውና አባላቱ ተፈጥሮአዊ ጥንካሬ (inherent strength) አላቸው የሚያስብለን።

ፓርላማው ምን ማድረግ አለበት?

ላለፉት 26 አመታት የታየው ፓርላማው የኢህአዴግ ታዛዥ (rubber stamp) ሆኖ ሲያገለግል እንጂ ተፈጥሮአዊ ጥንካሬውን በአግባቡ ሲጠቀምበት አይደለም። እንዲያውም በሕገ መንግስቱ የተጣለበትን ሀላፊነትና የተሰጠውን ስልጣን ችላ ብሎ ወይም ዘንግቶ የህዝብን በደልና የሀገርን ጉዳት ማስቆም ሳይችል ቀርቷል። ለምሳሌ፤

የመከላከያ ሰራዊት፤ የደህንነት መ/ቤትና የፌደራል ፖሊስ አመራር የተያዘው በአብዛኛው በትግራይ ተወላጆች ነው። በተለይ በመከላከያ ውስጥ ከ90% በላይ የሚሆኑት ጄነራሎች የትግራይ ተውላጆች ናቸው። ይህ አሰራር የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 87(1) የሚጻረር ሆኖ ሳለ ፓርላማው በአንቀጽ 55(7) የተሰጠውን ስልጣን ተጠቅሞ ለማስተካከል የሞከረው ነገር የለም።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች፤ በተለይ ደግሞ በኦሮምያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በኮንሶ፣ ወዘተ እጅግ ብዙ ንጹሀን ዜጎች በሕገ መንግስቱ የተደነገጉ መብቶቻቸው እንዲከበሩ በሰላማዊ መንገድ ስለጠየቁ ብቻ ተገድለዋል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። ግድያዎቹና የመብት ጥሰቶቹ የተፈጸሙት በአብዛኛው በመከላከያ ሰራዊት፣ በደህንነትና ፌደራል ፖሊስ አባላት ነው። ፓርላማው በእነዚህ ተቋማት ስራ አፈጻጸም ረገድ የሚታዩ መሰረታዊ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶችና የሀገር ደህንነት የሚነኩ ጎዳዮች ሲከሰቱ እንዲጣሩና አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የማድረግ ስልጣንና ሀላፊነት ቢኖረውም እስካሁን በዚህ ረገድ ምንም ሚዛን የሚያነሳ ስራ ሲስራ አልታየም።
መንግስትን አጥብቀው የተቃወሙ መሪዎችና ግለሰቦች ሽብርተኛ ተብለው መታሰራቸውና መከሰሳቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ አሰራር ነው። ሰዎቹ በርግጥ ሽብርተኛ ሆነው ቢሆን ኖር መታሰራቸው ተገቢ በሆነ ነበር፤ የሆነው ግን ይህ አይደለም። መንግስት የሽብር ህጉን እየተጠቀመበት ያለው የኢህአዴግ/ህወሀትን ጠንካራ ተቀናቃኞች ለማጥፊያና ለማስፈራሪያ ነው። መንግስት ይህን ህግ ዜጎችን ለመጨቆኛና መብታቸውን ለመጣሻ ሲጠቀምበት ህጉን ያወጣው ፓርላማ በቸልተኝነት ሲመለከት ኖሯል።
ፓርላማው ሀላፊነቱን በአግባቡ ስላልተወጣና ስልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ስላልተጠቀመበት፤ እንዲሁም አስፍጻሚው አካል ለፓርላማው ያለው ተጠያቂነት (accountability) ስለተመናመነ ሀገሪቱ አሁን ያለችበት አደግኛ ሁኔታ ውስጥ ወድቃለች። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ አሁን ያለው ሁኔታ (the status quo) መቀጠል የለበትም፤ የህወሀት የበላይነት ያብቃ፤ ለውጥ እንፈልጋለን፤ ሕገ መንግስቱ ይከበር እያለ ይጮሀል። ግድያውም ሆነ እስራቱ እንደዚሁ ቀጥሏል።

ኢህአዴግ ሀገር መምራት እንዳቃተው ራሱ እየተናገረ ነው። አባላቱም እየተጣሉ ነው። በቅርብ ጊዜ ሪፖርተር ጋዜጣ በርእስ አንቀጹ እንዳለው ሀገሪቱን ያቆማት የህዝብ ጨዋነት እንጂ የኢህአዴግ የአመራር ብቃት አይደለም። ፓርላማው በዚህ የደከመ ሁኔታ ላይ ላለ ግንባር እራሱን ተገዢ አድርጎ የሚቀጥል ከሆነ ህገመንግስቱን መጣስ ብቻ ሳይሆን ሀገር እንድትጠፋና ህዝብ እንዲጎዳ ተባባሪ ሆነ ማለት ነው። የፓርላማው አባላት ተገዢነታቸው ለህዝቡ፣ ለሕገ መንግስቱና ለህሊናቸው ብቻ እንጂ ለኢህአዴግ እንዳልሆን በሕግ መንግስቱ ውስጥ ተደንግጓል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፓርላማ ውስጥ (በተለይ ደግሞ የተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ) ተስፋ የሚሰጡ አካሄዶች እየታዩ ነው። ለምሳሌ የብአዴንና ኦህዴድ ተመራጮች ተቀናጅተው መስራት ጀምረዋል። የሁለቱ ድርጅቶች ተመራጮች ብቻቸውን 57% ድምጽ ያላቸው በመሆኑ የኢህአዴግ/ህወሀትን ትእዛዝ ሳይጠብቁ ወይም ወደ ጎን ብለው አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን ማምጣት ይችላሉ። እንዲሁም የሁለቱን ድርጅቶች ህብረት በማስፋት ሌሎች የህወሀት ተጽእኖ ያንገሸገሻቸውን ክልሎች/ድርጅቶች ተወካዮችም ተሳታፊ/ተባባሪ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል/ይገባል።

ፓርላማው በሕገ መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን ተጠቅሞ በርካታ ለውጦችን ማምጣት ቢችልም ቅድሚያ መስጠት ያለበት የሰብአዊ መብቶችን መከበር ማረጋገጥና የመከላከያ/ደህንነት/ፖሊስ መስሪያ ቤቶች ላይ የአሰራር ለውጥ (reform) ማምጣት ላይ ቢሆን የተሻለ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። በዚህ ረገድ፤

የመከላከያ ሰራዊት፤ የደህንነት መ/ቤትና የፌደራል ፖሊስ አመራር በአብዛኛው በትግራይ ተወላጆች የተሞላ መሆኑ ቀርቶ ሕገ መንግስቱ በሚደነግገው መሰረት የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ስብጥር ሚዛናዊ በሆነ ሁኒታ ያንጸባረቀ እንዲሆን ማድረግ ይኖርበታል።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚታዩት መሰረታዊ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች የሚጥሱና የሀገር ደህንነት የሚጎዱ ድርጊቶች እንዲቆሙና ባጥፊዎቹ ላይ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ማድረግ አለበት። በተለይ ደግሞ የመብት ጥሰቶቹ የሚከናወኑት በየከተሞቹና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሕገ መንግስቱን በጣሰ መንገድ የፖሊስን ስራ እንዲሰሩ በተላኩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመሆኑ፣ እነዚህ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአስቸኳይ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ መደረግ አለበት።
ፓርላማውና አባላቱ እነዚህ ለውጦች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲመጡ ለማድረግ የሚያስችላቸው ስልጣንና ብቃት አላቸው። ፍላጎቱ አላቸው? ቆይተን የምናየው ይሆናል።

የፓርላማው አባላት ህዝቡ እያለ ያለውን አድምጡ። የሕገ መንግስቱን መከበር አረጋግጡ። የህዝብ መበደል፤ የሕገ መንግስቱ መጣስ፤ የኢትዮጵያ አደጋ ላይ መውደቅ ህሊናችሁን ይቆጥቁጠው።

ጸሀፊውን ለማግኘት ይህን የኢሜል አድራሻ ይጠቀሙ፡ anonymous2018@gmail.com

የመጨረሻው መጀመሪያ! (ዘውድአለም ታደሰ)

ሐገራችን የመጨረሻው መጀመሪያ ምእራፍ ላይ ትገኛለች። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ በአንድ ወቅት «ህዝብ እንቢ ካለ እንደሚያበቃ ከኤርትራ ህዝብ ተምረናል። የኤርትራ ህዝብ እምቢ ሲል አበቃ። የኦሮሞ ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ በብዙ ቁጥር ይበልጣል። የኦሮሞ ህዝብ በቃ ካለ ያበቃል!» የሚል ትንቢት የሚመስል ንግግር ተናግረው ነበር።
አሁን የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የአማራው ህዝብ በቃ ብሏል። ሌላው ህዝብም እንደሁለቱ ህዝቦች አደባባይ አልወጣም እንጂ ስርአቱን አንቅሮ ተፍቶታል። ስለዚህ በአቶ መለስ አባባል ነገሩ ሁሉ አብቅቷል።

አሁን ኦህዴድ የጡት አባት አልፈልግም ብሏል። ብአዴንም በአመዛኙ ከኦህዴድ ጋር ነው። ከዚህ በኋላ ይህ ስርአት መውደቁ አይቀርም አሁን የማይታወቀው አወዳደቁ እንዴት ይሆናል? የሚል ነው። ኳሷ በአመዛኙ በህውሃት እጅ ነች። የህዝብን ጥያቄ አድምጠው፣ ኩራትና ትእቢታቸውን ትተው ለሃገራቸውና ለህዝባቸው የሚጠቅም ውሳኔ ያስተላልፉ ይሆን ወይስ የአቶ መለስን ምክር ቸል ብለው በተለመደ የፖለቲካ ጨዋታ ለመጫወት ሞክረው ሃገሪቷን ወዳላስፈላጊ ሽኩቻ ውስጥ ይከትቷት ይሆን? (በቅርቡ የሚመለስ ጥያቄ ነው)

በትጥቅ ትግሉ ወቅት ብዙ የትግራይ ልጆች ተሰውተዋል። ይሄ የማንፍቀው ሃቅ ነው!! ብዙ ጀግኖች ሜዳ ላይ ቀርተዋል። ብዙ እናቶች ልጆቻቸውን አጥተዋል። ከአንድ ቤተሰብ ብዙ ሰው አልቋል። እርግጠኛ ሆኜ ምናገረው እነአሞራውን የሚያህሉ የገበሬ ልጆች ነፍሳቸውን የሰጡት ደርግን ጥለው ደርግን የሚመስል ስርአት ለማቆም አልነበረም። ዛሬ ከአምስት መቶ በላይ የህሊና እስረኞች ወህኒ ናቸው። የትግራይ እናት የወለደቻቸውን ልጆቿን ለሞት አሳልፋ የሰጠችው ለዚህ አይደለም። ዛሬ ላይ የህውሃት ባለስልጣናት ከግል ህይወታቸው በላይ ዞር ብለው ህዝባቸውን ማየት ፣ በየጥሻው የተሰዉ ወንድሞቻቸውን ማሰብ አለባቸው።

ከዚህ ሁሉ መስዋእትነት በኋላ የትግራይ ህዝብ ምን አገኘ? ከድህነት ወጣ? የሚፈልገውን አካል የመቃወምና የመደገፍ መብት ተጎናፀፈ? ብዙ ኮረኔልና ጀነራል የትግራይ ተወላጅ መሆኑ ለገበሬው የትግራይ ህዝብ ምን ይጠቅመዋል? የህውሃት የበላይነት ለትግራይ ህዝብ ምን ይረባዋል? ምንም ነው መልሱ!!

ስለዚህ ኳሷ በህውሃት እጅ ነች! ትናንት በበረሃ ያሳዩትን ጀግንነት ዛሬ ይደግሙት ይሆን? ትናንት ነፍሳቸውን ለሰጡለት ህዝብ ዛሬ ስልጣንና ምቾታቸውን ይሰዉ ይሆን? እንደጀግና ለሐገርና ለህዝባቸው የሚጠቅማቸውን ውሳኔ ይወስኑ ይሆን? ወይስ እንደፈሪ ስልጣናቸውን የሙጥኝ ብለው የታሪክ መቀለጃ ይሆኑ ይሆን?

የመጨረሻው መጀመሪያ የሚፃፈው በህውሀት እጅ ነው!

መራር ግፍ!

ዋዜማ ራዲዮ-በሀገሪቱ በፖለቲካ አመለካከታቸው አልያም በጥርጣሬ ብቻ ታስረው ስቃይ የሚፈፀምባቸው በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች አሉ። የስቃዩ መጠን ይለያያል። ይህ ገዥው ፓርቲ አፋፍሞ የቀጠለው ግፍና እስር ዛሬ በሀገሪቱ ለተከሰተው ህዝባዊ አመፅ አንዱ ምክንያት ነው። ግፍ እየተፈፀመባቸው ያሉ የተወሰኑ እስረኞችን እናስተዋውቃችሁ። [በድምፅ የተሰናዳውን ዘገባ ከግርጌ ያድምጡ]

የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመባቸውን ዜጎች ሁሉ ዘርዝሮ በደላቸውን ለማንሳት ቢያሰቸግርም ዋዜማ ራዲዮ ከኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት ጋር በመተባበር መንግስት የሽብር ክስ መስርቶባቸው በማዕከላዊ፣ በቅሊንጦ፣በቃሊቲ እንዲሁም በሽዋ ሮቢት ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ ሳሉ በሶስት እስረኞች ላይ የተፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከራሳቸው ከእስረኞቹ ያገኘነውን መረጃ አጠናቀረነዋል።

አግባው ሰጠኝ የ38 አመት ጎልማሳ ነው፡፡ በሽብር ክስ ተመሰርቶበት ከተመሰረተበት ክስ ነፃ ቢባልም አሁንም በቅሊንጦ ይገኛል። የቅሊንጦን ማረሚያቤት በማቃጠል ሰው እንዲሞት አድርገሃል በሚል ዳግም የሽብር ክስ ተመሰርቶበታል።

የዋቄ ፈናን ሃይማኖት መከተሉ ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የዳረገው ለማ ባየ በቅሊንጦ ከክርስትና እና እስልምና ውጪ ምንም አይነት የአምልኮ ሰርዓት አትፈፅምም ተብሎ ጫና እንደደረሰበት ተናገሯል፡፡

ከኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት አሰተባባሪ ሶሊያና ሽመልስ ጋር ኤዶም ካሳዬ በማዕከላዊ፣ በቅሊንጦ፣በቃሊቲ እንዲሁም በሽዋ ሮቢት ማረሚያ ቤቶች በተቋማዊ አደረጃጀት ሰለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን የሶሰቱ ታሳሪዎችን ገጠመኝ አያነሱ ይወያያሉ።