የቴዲ አፍሮ የባህር ዳር የሙዚቃ ዝግጅትና “ጃ ያስተሰርያል”

የቴዲ አፍሮ የባህርዳር የሙዚቃ ዝግጅት በአስር ሺዎቹ የሚቆጠሩ የተገኙበትና ኢትዮጵያዊነት ነግሶ ያመሸበት ድንቅ የሙዚቃ ድግስ እንደነበር ብዙዎች ይስማማሉ፣ ይሁንና በስተመጨረሻ ታዳሚው ቴዲ አፍሮ “ጃ ያስተሰርያል” የሚባለውን ተወዳጅ ዘፈኑን እንዲዘፍን ጠይቆ ተግባራዊ ሳይሆን በመቅረቱ አንዳንዶች በጣም አዝነዋል።

ቴዲ አፍሮ፣

በአስራ ሰባት መርፌ በጠቀመው ቁምጣ
ለለውጥ ያጎፈረው ዙፋን ላይ ሲወጣ
አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ…

የሚለውን በገዢዎቹ (ህወሃት) ጥርስ ውስጥ ያስገባውን ዘፈኑን እንዲዘፍን በተጠየቀበት ሰዓት ላለመዝፈን ሲያንገራግር ታዳሚው “ቴዲ አይፈራም” እያለ በመጮሁ ቴዲ ከባንዱ አባላት ጋር ጥቂት እንደተነጋገረና በመሃሉ ማናጀሩ ወደ መድረኩ ገስግሶ ከቴዲ ጋር ካንሾካሾከ በኋላ በጃህ ያስተሰርያል ምትክ “ጥቁር ሰው” ተዘፍኖ ዝግጅቱ ተጠናቋል።

ምናልባት ቴዲ አፍሮ “ጃ ያስተሰርያል” የሚለውን ዘፈን ላለመዝፈን ከአማራ ክልል (ብአዴን) ሹማምንት ጋር ውል ገብቶ ይሆን? ከአመታት ወዲህ ለቴዲ አፍሮ ይህ የመጀመሪያው ዝግጅት ነው ምናልባት እያሟማቀ ይሆን? እንደ ቴዲ አፍሮ አይነት አርቲስቶች በህወሃት ሰማይ ስር ሆነው የፈለጉትን ሊዘፍኑ አይችሉም ኑሮዋቸው ሁሉ በክር ላይ እንደመራመድ ነው። ታዳሚው ይህንን አልተገነዘበ ይሆን? ወይንስ ወቅቱ ሁሉም ያለውን የሚያወጣበት እና ትንሽ ትንሽ መስዋእትነት መክፈል ያለበት ነው? አስተያየቶን ይለግሱ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s