ምነው በመሀሉ አንድ ሌላ ዜና ቢያስገቡበት! – በድሉ ዋቅጅራ

.

በምርጫ 97 ሰሞን፣ አዲስ አበባ ላይ ለተቃውሞ በወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ሀይሎች የፈጸሙትን ድብደባና ግድያ NRK በሚባል የስዊድን የቴሌቪዥን ጣቢያ የተመለከተ፣ ኖርዌጂያን መምህሬ፣ ‹‹በድሉ እናንተ ሀገር ፖሊሶች እንዴትና ከየት ነው የሚመለመሉት?›› ብሎ ጠየቀኝ፡፡ ለምን እንደጠየቀኝ የገባኝ ያየውን ከነገረኝ በኋላ ነው፡፡ ‹‹እንዴት ፖሊስ ህዝብ ላይ እንደዚያ ያለ ጥቃት ይፈጽማል?›› አለኝ አከታትሎ፡፡ ፖሊስ ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ የጦር ሰራዊት አባላት እንዴት እንደሚመለመሉ ነገርኩት፡፡

.

በጣም የመሰጠኝ ግን ከዚያ በኋላ ያጫወተኝ ነው፡፡ ‹‹ጎረቤታችን የሚኖር አንድ የህክምና ዶክተር አለ፡፡ ልጁ ከሁለት አመት በፊት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲጨርስ ከጓደኞቹ ጋር ሲጠጣ አምሽቶ፣ ከለሊቱ 9 ሰአት ወደ ቤቱ እየተመለሰ፣ እኔ በር ላይ ሲደርስ ትንሽ ጩቤ አውጥቶ የቤታችን በር ላይ ሰካውና ትቶት ሄደ፡፡ ጊዜው ሰመር ስለነበር ከለሊቱ 9 ሰአት ጻሀይዋ ወጥታለች – ማን እንደሆነ ለመለየት አልተቸገርንም፡፡ ፖሊስ ጠራን፡፡ ልጁ እስከነጩቤው ወደፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡ አየህ እዚህ ሀገር እንዲህ አይነት ትግር ሲፈጠር ፖሊስ ጉዳዩን አጥንቶ፣ ክስ የሚያስመሰርት ከሆነ ክስ ይመሰርታል፡፡ ክስ የማያስመሰርት ከሆነ ደግሞ ይለቀዋል፡፡ ክስ የተመሰረተበት ሰው ፍርድ ቤት በነጻ ቢለቀውም እንኳን፣ በየትኛውም የሀገሪቱ የጦር ሀይል ውስጥ (ፖሊስ፣ የምድር ጦር፣ አየር ሀይል፣ ባሕር ሀይል . . ) መስራት አይችልም፡፡ . . . . የልጁ አባት በማግስቱ ደውሎልኝ ቢሮዬ መጣና፣ ‹እባክህ ልጄ ድርጊቱን የፈጸመው ሰክሮ ነው፡፡ ፖሊሶች አንተ ይቅርታ ካደረግክለት ክስ አይመሰርቱበትምና እባክህ ይቅርታ አድርግለት› አለኝ፡፡ እኔም እራሱ ልጁ መጥቶ ይቅርታ ከጠየቀኝ ይቅርታ እንደማደርግለት ነገርኩት፡፡ ሰውዬውም ደስ ብሎት፣ ‹የባህርሀይል ውስጥ መስራት ስለሚፈልግ ክስ ይመሰረትብኛል ብሎ ፈርቶ ነበር› አለኝ ከቢሮዬ ሲወጣ፡፡ ይህን ሲነግረኝ ሀሳቤን ለወጥኩ፡፡ በፍጹም ይህ ሰው በሀገሬ የጦር ሀይል ውስጥ እንዲሳተፍ እንደማልፈቅድ ነገርኩት፡፡ ይቅርታ ሳላደርግለት ቀረሁ፡፡ እሱም የባህር ሀይል የመሆን ፍላጎቱ ተጨናገፈ፡፡›.

.

ኖርዌጂያን መምህሬ የነገረኝ፣ ሀገሬ ላይ ፖሊስና መከላከያ (አግአዚ) ተኩሰው በገደሉ ቁጥር ትዝ ይለኛል፡፡ እንደ ኖርዌይ አይነት የአመላመል ስርአት ይኑረን ብዬ አልቀናጣም፤ ግን የጸጥታ ሀይሎቻችን፣ ህዝብን መጠበቅ እንዳለባቸው በስልጠና ላይ ምንም አየነገራቸውም!? እያልኩ እብሰለሰላለሁ፡፡

ሰሞኑን የሀገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት ቀን እየተከበረ ነው፡፡ ሌላውን ትቼ ትላንት በኢቢሲ የሁለት ሰአት ዜና ላይ ያየሁትን ላጋራችሁ፡፡ ዜናው የተጀመረው በሀረርጌ፣ ሀማሬሳ በመከላከያና መህዝብ መካከል በተከሰተ ግጭት ሰዎች እንደሞቱና እንደቆሰሉ በመናገር ነው፡፡ (የሚገርመው ዜና አንባቢው የኦሮምያ ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ነው የዘገበው፤ ዘገባው እንደደረሰን እናቀርባለን ቢልም አልቀረበም፡፡ ኢቢሲ ሀረርጌ ዘጋቢ የለውም? እንደ ቢቢሲ፣ ሲኤንኤንና አልጀዚራ የኦሮምያን ቲቪ ጠቅሶ ማቅረቡ አሳስቦኛል)፡፡ ከዚህ ዜና ቀጥሎ የቀረበው የመከላከያ ሰራዊት ቀን አከባበር ነው፡፡ ሰራዊቱ የህዝብ አገልጋይና ጠባቂ እንደሆነ ተዘገበ፡፡ ‹‹ምነው በመሀሉ አንድ ሌላ ዜና ቢያስገቡበት›› ብዬ አሰብኩ፡፡

በዚህ አመት በየአካባቢው ከጸጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት የሞቱትንና የቆሰሉትን የተመለከተ፣ የጸጥታ ሀይሎች የህዝብ ጠባቂዎች ናቸው ብሎ ለማመን ማበድ አለበት፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s