የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል በአስቸኳይ ይፈጽም !!!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ የካቲት 5ቀን 2010 ዓ.ም.

[[ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጨምሮ ፣ከገዥው ስርዓት በአመለካክት በመለየታቸው ብቻ በግፍ ለእስር የተዳረጉ ፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት፣ የሰብዓዊ መብት ተመጋቾች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም የእምነት አባቶች፤ በሙሉ ከእስር ተፈተው ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ድርድር ተካሂዱ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በአገራችን በአስቸኳይ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል በማለት ሰማያዊ ፓርቲ በጽኑ ያምናል]]


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ የካቲት 5ቀን 2010 ዓ.ም.
በባለፈው ሃያ ስድት (26) ዓመት የግፍ አገዛዝ በሃገራችን ኢትዮጵያ የአገዛዙ ሥርዓት፤ጉልበታችንን አዝሎ፣ ትከሻችንን አጉብጦ ሊጥለን ቢሞክርም ፤ በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተደረገና እየተደረገ ባለ የነቃ ተሣትፎ የገዢዎቻችን ክፉ ምኞት ቅዥት መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ገዥዎቻችን በየቀኑ የሚየደርሱብን ግፍ እና በደል ከፊትለፊታችን እንደሻማ እየቀለጡ ጥንካሬያችንን በህመማቸው ለገነቡልን፣የሥርዓቱን ቅጥ ያጣ አረመኔያዊ ተግባር በአደባባይ ማንም ሣያስገድዳቸው ፤ የወገኔ በደል ሊቆም ይገባል በማለት የተጋፈጡ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች !! ዛሬ እነሱ የለኮሱት ሻማ የህዝብን ትግል ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ጥግ አነቃንቆ ገዥዎቻችን የህዝብን ትግል ሊያዳፍኑት ወደማይቻልበት ፣ሞክረውም ወደማይሣካላቸው ጥግ ደርሷል፡፡ ሕዝባዊ ትግሉ እየተጋጋመ ፣ ሃገራችንኢትዮጵያ ወደ ማይቀረው የለውጥ ጎዳና እየተመመች ነው፡፡

የሕዝብን አንገት ለማስደፋትና ሕዝባዊ ትግሉን ለመቀየር ያልተማሰ ጉድጓድ፣ ያልተወጣ አቀበት ፣ ያልተወረደ ቁልቁለት ባይኖርም ትግሉ ከቀን ወደ ቀን አቅጣጫውን እየቀየረና እየጠነከረ መጥቶ የሕዝብ ትግል ፍሬ አፍሮቶ ፤የአገዛዙን ሥርዓት እያስጨነቀ፣ድል የሕዝብ መሆኑ እየቀረበ ይገኛል ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የመሰለ በታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን፤ በሃገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ሃገር የሚገኙ የኢትዮጵያዊያንን ትግል በእጅጉ ያደናቃል !! ከዚህ ቀደም እንደነበረው ወደፊትም በተጠናከረ መልኩ የሕዝቡን ትግል በማገዝ ተገቢውን ኃላፊነቱን ፓርቲያችን ይወጣል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግሥት ከደረሰበት ሁለንተናዊ ጫና በመነሳት ፤‘‘ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ከእስር እንደሚፈቱ ” ለሕዝብ ቃል መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡ በይፋ ለሕዝብ የገባውን ቃል ተግባራዊ ያደርጋል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት፤ አስቀድሞ ያልተገለጸ ‘‘በይቅርት” ወይም ‘‘የይቅርታ” ፎርም/ማመልካቻ ካላስገባችሁ ከእስር አልፈታችኹም፤ የሚል አጎጉል ፈሊጥ በማምጣት ቀድሞ የገገባውን ቃል በአደባባይ እየካደ ይገኛል፡፡ ክህደት የሥርዓቱ ዋንኛ መገለጫ በህሪ መሆኑ እሁን ቢሆንም ፤የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገዛዙ ሥርዓት ክህደት የመሸከም ፍላጎቱ ባበቃበት በዚህን ወሳኝ ወቅት ፤ በሕዝብ ላይ ክህደት መፈጸም የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግሥት ከማይወጣው አርንቋ ውስጥ የሚከተው እንጂ ከቶውንም የሚያድነው አይደለም !!

በመሆኑም የአገዛዙ ሥርኣት ቀድሞ ለሕዝብ የገባው ቃል እንደተጠበቀ ሆኖ እያለ፤ለተሻለ ሃገራዊ መግባባት እና የተረገጋ ሰላማዊ የፖለቲካ ስርዓት በሃገራችን እሁን እንዲሆን፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጨምሮ ፣ከገዥው ስርዓት በአመለካክት በመለየታቸው ብቻ በግፍ ለእስር የተዳረጉ ፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት፣የሰብዓዊ መብት ተመጋቾች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም የእምነት አባቶች፤ በሙሉ ከእስር ተፈተው ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ድርድር ተካሂዱ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በአገራችን በአስቸኳይ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል በማለት ሰማያዊ ፓርቲ በጽኑ ያምናል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ የህዝቡን ትግል ግንባር ቀደም በመሆን ሲመሩ የቆዩ ጅግኖች !! መራራ ፅዋ ተቋቋመው ወደህዝብ በመቀላቀላቸው፤ ሕዝብ ትግሉን አይመለከተኝም ወይም ሌላ ምክንያት ሣያቀርብ በፅናት ታግሉ መሪዎቹን በማስፈታቱ ፤ ህዝቡንና መሪዎቹን በማገናኘት ሁለቱም በጋራ ምስጋና የሚሰጣጡበትን የአቀባበል ስነ-ሥርዓት ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ከታሳሪ ቤተሰቦች፣ ከታዋቂና ከምሁራን ጋር በመተባበረ የሚያዘጋጅ ሲሆን፤ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ለስኬታማነቱ አስፈላጊ ትብብራችሁ እንደቀድሞ አሁንም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ የዴሞክራሲ፣የፍትህ እና የነፃነት ጥያቄ ዋንኛ መሆኑን መሠረት በማድርግ ፤እነዚህ ጥያቄዎች በሚመለሱበት ደረጃ ሰማያዊ ፓርቲ በትኩረት በመስራት የሕዝቡ ትግል ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአጽንኦት ይገልጻል ፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

የካቲት 5ቀን 2010 ዓ.ም.

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s