የእነ ንግስት ይርጋ መከላከያ ምስክርነት አከራከረ ~ ፍርድ ቤቱ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ራሱ የሰጠውን ትዕዛዝ እንደገና እመረምራለሁ ብሏል

(በጌታቸው ሺፈራው)

በ2008 ዓም በአማራ ክልል በነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሰበብ የ”ሽብር” ክስ የተመሰረተባቸው እነ ንግስት ይርጋ ምስክርነት አከራክሯል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት እነ ንግስት ይርጋ ምስክርነት ለማሰማት ታህሳስ 12 /2010 ዓም በነበራቸው ቀጠሮ ወደ ችሎት ሳይገቡ በመመለሳቸው ምስክር ለማሰማት እንዳልፈለጉ እንደሚያሳይ ገልፆ፣ የተከሳሾቹን አስተያየት ጠይቋል።

1ኛ ተከሳሽ ንግስት ይርጋ በተባለው ቀን ወደ ችሎት ገብታ እንደነበር፣ ነገር ግን የቃሊቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ከችሎት እንድትወጣ እንዳደረገች ለፍርድ ቤቱ ገልፃለች። በተመሳሳይ 3ኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ ተላይ ወደ ችሎት ለመግባት ተሰልፈው በነበረበት ወቅት በእስር ቤቱ ጉዳይ አስፈፃሚ ትዕዛዝ እንደተመለሱ ገልፆአል። የተከሳሾቹ ጠበቆች አቶ አለልኝ ምህረቱ እና አቶ ሄኖክ አክሊሉም ተከሳሾቹ በራሳቸው ችግር እንዳልቀሩ ገልፀው መከላከያ ምስክር እንዲያሰሙ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ዐቃቤ ሕጉ ሰኢድ ተማም ተከሳሾቹ ታህሳስ 12/2010 ዓም በነበራቸው ቀጠሮ ወደ ችሎት ለመግባት ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ገልፆ፣ ይህም ምስክር ማሰማት እንዳልፈለጉ ስለሚያሳይ መከላከያ ምስክር ሳያሰሙ እንዲፈረድባቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ከተከሳሾች አንደበት ካዳመጠ በኋላ አለመግባባት እንደነበር እንደተረዳ ገልፆ የዐቃቤ ሕግን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተከሳሾቹ ምስክሮቻቸውን እንዲያሰሙ ለመጋቢት 11፣12 እና 13 ተከታታይ ቀጠሮ ይዟል።

በሌላ በኩል የተከሳሾቹ ጠበቆች እነ ንግስት በምስክርነት የጠሯቸው የአማራ ክልል ባለስልጣናትን አድራሻቸውን ስለማያውቁ ፍርድ ቤቱ መጥሪያ እንዲልክላቸው ጠይቀዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 4/2010 ዓም ባለስልጣናቱ እንዲቀርቡ በተፃፈውን መጥሪያ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ዛሬ የካቲት 6/2010 ዓም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎቹ የክልሉ ባለስልጣናት በምን ጭብጥ ላይ እንደሚመሰክሩ ጠበቆች ጭብጡን እንዲያስገቡ እና ጭብጡን መርምሮ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ፍርድ ቤቱ ባለስልጣናቱ የሚመሰክሩት ጭብጥ ይቅረብልኝ ያለው በመዝገቡ ላይ ከተመዘገቡት ሌሎች ምስክሮች በተለየ ሲሆን ታህሳስ 4 በሰጠው ትዕዛዝ ባለስልጣናቱ እንዲቀርቡ ወስኖ እንደነበር ይታወሳል። የካቲት 15/2010 ዓም ባለስልጣናቱ በምን ጭብጥ ላይ እንደሚመሰክሩ መርምሮም በባለስልጣናቱ ምስክርነት ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ኮማንደር ዋኛው እዘዘው፣ ኮምሽነር ሙሉጌታ ወርቁ፣ አቶ ተቀባ ተባበል እና ሌሎችም የአማራ ክልል ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክርነት እንዲሰጡ ታህሳስ 4/2010 ዓም መጥሪያ መፃፉ ይታወሳል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ጉርሜሳ አያኖ ክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩትን ባለስልጣናት እንዲቀርቡ ካዘዘ በኋላ ራሱ የሰጠውን ትዕዛዝ እንደገና “መርምሮ” እንዳይመሰክሩ መወሰኑ ይታወሳል።

በእነ ንግስት ይርጋ ክስ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ ንግስት ይርጋ እና 3ኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ ተላይ ብቻ በዛሬው ችሎት የቀረቡ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ አለምነህ ዋሴ፣ 4ኛ ተከሳሽ አወቀ አባተ፣ 5ኛ ተከሳሽ በላይነህ አለምነህ እና 6ኛ ተከሳሽ ያሬድ ግርማ “ለስልጠና” እንደተወሰዱ ፍርድ ቤቱ ገልፆአል።

(የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ወንጀል ችሎት ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ለአቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ለአቶ ተቀባ ተባበል፣ ለኮማንደር ዋኛው እዘዘው እና ለኮምሽነር ሙሉጌታ ወርቁ ታህሳስ 4/2010 ዓም የፃፈው መጥሪያ ከስር ተያይዟል)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s