የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ በሚል በኦሮሚያ ክልል ቄሮዎች ለሶስት ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል

የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ በሚል በኦሮሚያ ክልል ቄሮዎች ለሶስት ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል።

በአብዛኞቹ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች አድማው በተሳካ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ሲሆን በአንድንድ ከተሞች ህዝብ አደባባይ ወጥቶ “ግድያ ይቁም፣የታሰሩት ይፈቱ፣ የመከላከያ ሰራዊት ስራው ድንበር መጠብቅ እንጂ ህዝብ መግደል አይደለም ከአካባቢያችን ይውጣ ፣ጥቂቶች እየዘረፉ የሚኖሩበት ስርዓት በቃን፣ፍትህ፣ዲሞክራሲ፣በቃን ባርነት” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ተቃውሞው ወደ ግጭት እንዳያመራ ህዝብ ላይ ትንኮሳ ባለማድረግ ወገናዊነቱን ያሳየ ሲሆን የህውሐቱ አጋዚ በባሌ ዞን በመዳ ወላቡ ወረዳ “መዳ” በተባለች ቀበሌ የገበያ ቦታ ላይ ያለምንም ምክንያት የሦስት ሰዎች ሕይወት ያጠፉ ሲሆን ሰባት ሰዎች ቆስለዋል።
ከሟቾቹ ውስጥም አንዲት የስምንት ልጆች እና አንዲት የሰባት ልጆች እናት ወተት በመሸጥ ላይ እያሉ በመከላከያ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s