ኢት-ኢኮኖሚ – ኢትዩጵያ የህዝቦች እስር ቤት!!! (ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም)

የማ ዘር፣ጎመን ዘር!!!
ዘር ቆጣሪ፣አጥር አጣሪ

በኢትዩጵያ የህሊና እስረኞች፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች በሽብርተኛነት ስም አስረዋቸው ከስድስት ዓመታት እስራት በኃላ በህዝብ ትግል ነፃነታቸውን አግኝተዋል፡፡  የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ መሪዎችን እነ ዶክተር መራራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ ሌሎቹም በሽብርተኛነት ስም አስረዋቸው ሲያሳቃዬቸው ቆይቶ በህዝባዊ አመፅ ነፃነታቸውን ተቀዳጅተዋል፡፡

  • ከየመን ታፍኖ ወደ ኢትዩጵያ የመጣው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ፣አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ በአስቸኮይ እንዲፈታ ህዝብ ይጠይቃል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተቃዋሚ የህዝብ ልጆችን እያደኑ በመግደል ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔዊ ተግባር ፈፅመዋል፡፡
  • የዴሞክራቲክ ጋርድ ህዝባዊ ኃይል አባላት እነ ብርጌደር ጀነራል ተፈራ ማሞ፤ ብርጌደር ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ እማዋይሽ አለሙ ወ/ሚካኤል፣ሌሎቹንም የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኮይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
  • ከወልቃይት ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ፣ ንግስት አዳነና ሌሎችም በአስቸኮይ እንዲፈቱ ህዝብ ይጠይቃል!!!
  • ከጋምቤላ ቱወት ፖል ሌሎችም ይፈቱ!!!
  • ከኦጋዴን አብዲከሪም ሼህ ሙሴ ሌሎችም ይፈቱ!!!
  • በኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እስረኞች በአስቸኮይ ይለቀቁ!!!

እውቁ ፕሮፊስር አስራት ወልደየስ የኢትዩጵያ አባት፣ የሃገራችንን የፖለቲካ ትርፍ አንጀት በኦፕሬሽን ለማውጣት ሲሞክሩ የበሽታው ደዌ ካንሰር እንደሆነና ካልተቆረጠ መዳን እንደማንችል አልገባንም ነበር፣ አባታችን በእስር ተሰቃይተው ተሠውልን፡፡ ካንሰሩ ከተስፋፋ የሃገር ሞት እንደማይቀር የተረዱ፣ ከሁለት አስርት በኃላ፣ ቆይቶ ጉዳዩ የገባቸው የአማራ ጀነራል መኮንኖች  የፕሮፊስር አስራት ጥያቄ በማንሳታቸው ለእስር ተዳረጉ፡፡ ቤተሰባቸው ተበተነ፣ የሚረዳቸው ወገንና አስታዋሺ አጡ፡፡ ዛሬ የኢትዩጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ይሄን የወያኔን የፖለቲካ ካንሰር ለመቁረጥ ቆርጦ ተነስቶል፣ ለልጆቻችን መሬታችንን ተነጥቀን፣ ነጻነታችንን አጥተን፣ ባርነት ከማውረስ ሞት እንመርጣለን ብለው ለትግል ተነስተዋል፡፡ ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል አይበግረንም፣ ‹‹ህወኃት ቤት ጥይት፣ህዝብ ቤት ክብሪት አይጠፋም!!!›› ለዚህ ነው የሚሉት፡፡

የቻይናውያኑ ዜድቲኢ እና ሀዊ  ካንፓኒዎች ከኢትዩጵያ የህዝብ ደህንነት መስሪያ ቤትና፣  ከኢትዩጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ጋር የስለላ ሴራ በኢትዩጵያ ህዝብ ላይ ያከናውናሉ፡፡ የቻይና መንግሥት በኢትዩጵያ የስለላ መረቡን በዜድቲኢና ሀዊ ቴሌኮሙዩኒኬሽን በኩል የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በመደገፍና ህዝባዊውን ትግል በመሰለልና በማፈን ከፍተኛውን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት፣ቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd.ድርጅቶች ለህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍን ውስጥ በመሰለልና የሃገሪቱን ምስጢርና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስለላ መረብ በማስገባት ከፍተኛ ጥቃት አድርሰዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ በዋቢነት የሚጠቀሰው በ2009 ዓ/ም የሃገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ የስልክ ጥሪዎች የሰዎችን የስልክ ቁጥርን በመጥለፍ ለወያኔ መንግሥት ያበረከቱት የስለላ ሥራ በማስረጃ ይጠቀሳል፡፡ በዓለም ዓቀፍ የስልክ ጥሪዎች በመጥለፍ ከግንቦት ሰባት ፀሃፊና ሊቀመንበር ጋር የስልክ ግንኙነት አድርጋችኃል በማለት፡-1/ ከአንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ያደረገው ግንኙነት 2/ ከብርሃኑ ነጋ ጋር ያደረገው ግንኙነት እንዲሁም በሃገር ውስጥ የስልክ ጥሪዎች በማድረግ የምትገናኙት መንግሥት ለመገልበጥ እያሴራችሁ ነው፡፡ ከግንቦት ሰባት ጋር ትገናኛላችሁ ተብለው ለብዙ ወራቶች የስልክ መስመሮቻቸውን በመጥለፍ የሚያደርጉትን ንግግር በመቅዳት ህገ መንግሥታዊ መብታቸውን በመጣስ መንግስታዊ ስለላ ከተካሄደባቸው የአማራ ጀነራል መኮንኖችና የሲቨል ዜጎች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ታሪክ የማይረሳው አንድ ቀን እነዚህ ጀግና የህዝብ ልጆች ለኢትዩጵያ ህዝብ ሲሉ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግሥት የታገልንለት ህዝባዊ ዓላማን ሳተ፣ የታገልንው ለዚህ አይደለም በማለት በኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት ስብሰባዎች በግልፅ ሲናገሩ እንደነበር ሠራዊቱ ያውቃል፡፡

በኢትዩጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኢህዴን/ የጀነራል መኮንኖቹ ገድል በተለይ ብርጌደር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ብ/ጄ አሣምነው ፅጌና ጀነራል ሃይሌ ጥላሁን የደርግን መንግሥት ለመጣል በተደረገ የሽምቅ ውጊያ ትግል ታሪክ በኢህዴን ዓመታዊ የምስረታ በዓል ላይ ገድላቸው ሲተረክና ሲወጋ እንደነበር የኢትዩጵያ ቴሌቨዚንና ሬዲዩ ጣቢያ ገሃድ ምስክሮች ናቸው፡፡           ህብረ-ብሄር የነበረው የኢትዩጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኢህዴን/ ወደ ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/በዘር ሲከለስና ሲቸለስ እነዚህ የወሎ፣ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም አማሮች ነገሩ እየጎረበጣቸው እንዴት ከኢትዩጵያዊ ህብረ-ብሄር አመለካከት ወርደን ስለ አማራ ዘውግ/ዘር እንድናስብ እንደረጋለን? እንዴት ከኢትዩጵያዊ ብሄርተኝነት ወርደን የዘውግ/ዘር ክልላዊነት ጥላ እንይዛለን? እንዴት ከዓለም ዓቀፋዊነት እምነት ወርደን ብሄርተኝነት ወርደን ክልላዊነት እንጠባለን? ከዓለም ዓቀፋዊነት/ኢንተርናሽናሊዝም በዘመርንበት አንደበት የክልላዊነት ልሣን እንዘምራለን?  እንዴት ሶሻሊዝምን ትተን ካፒታሊዝምን እንጋታለን እናንተ ማርክሲዝምን ለ17 ዓመታት ግታችሁን ዛሬ ድል አርገን ስንገባ ነጭ ካፒታሊዝምን ታስታውኩብናላችሁ? ብለው በግዜው የተሞገቱ፣ የዋህ እውነተኛ የሃገሪቱ ልጆች ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ ‹‹በሙስናና በሌብነት›› ወያኔ በየስብሰባው ሲለን  ከድርጅቱ አሳልፈን ሰጠንው፣ የህዝብ ቃልኪዳንና የተሰውትን ሰማዕታት ቃል ባለማክበሩ አሳልፈን ሰጠንው!!! በህወኃት/ ኢህአዴግ መንግሥት በማመን ከጫካ ትግል ጀምረው ለዚህ ስልጣን የደረሱት ጀነራል መኮንኖች ቃል በገቡትን መሠረት በሃቅ ለሃገርና ለወገን በማገልገል ተጎዙ፡፡

ጀነራል መኮንኖቹ ብሄረ አማራን ለማቅናት ደፋ ቀና ሲሉ፣ አንድ ቀን ዞር ሲሉ ጥላቸው የለም? የአማራው ክልል ህዝብ የጤና፣ የመብራት፣ የውሃ አገልግሎት የለውም፡፡ የመንገድ መሠረተ ልማት አልተዘረጋለትም፡፡ የትምህርት አገልግሎት  ተቆማትም አልተሞሉለትም!!! በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በኩልም፣የኤሌትሪክ ኃይል አገልግሎት ባለማግኘታቸው  ወደ ሥራ መግባት ያልቻሉ ኢንቨስተሮች ቁጥር የትየለሌ መሆኑን ታዘቡ፡፡

የጀነራል መኮንኖቹ በኢህአዴግ ጉባዔዎችና በመከላከያ ሠራዊቱ ስብሰባዎች ላይ ባነሱት ጥያቄዎች የበላይ አለቆቻቸውን ይጠይቁ ጀመረ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የትግራይ የበላይነት እያደገ መጥቶል! በሠራዊቱ አመራር መኮንኖች፣ የተባለው የብሄር ብሄረስብ ተዋፅኦ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ በሠራዊቱ ውስጥ በተለይ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ውስጥ የሙስናና ንቅዘት፣የዝምድና የመጠቃቀም ሥራ በዝቶል ይስተካከል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ፣ የኢትዩጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ሆነው በሰላም አስከባሪነት የሚሄዱት በአመዛኙ የትግራይ የሰራዊቱ አባላቶች ናቸው ከሌሎቹም ብሄር ብሄረሰብ የሠራዊቱ አባላቶች ቅሬታና ጥያቄ አስከትሎል በአስቸኮይ ይስተካከል፡፡ ሰላም አስከባሪ ኃይል በአፍሪካ ሃገራት በአስከባሪነት ከሚላኩ ወታደሮች  የጉቦና የዝምድና ሥራ ይብቃ፣የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት በወታደራዊ ሣይንስ አመራር ችሎታ ያላቸው መሪዎች ይመራ የሚሉ ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡

በህወኃት/ኢህአዴግ መለስ ዜናዊ ስካር ይሁን ስካEር? ዴሞክራሲ አረገ አላቸው፡፡ ከትቢያ አንስተን ሰው አረግናችሁ ሊያውም ጀነራል መኮንኖች! ቪላ ቤት ሠጠናችሁ! መኪና ከአንድም ሦስት ሠጠናችሁ!!! መሬት መራናቸው!!! ሸራተን፣ሂልተን ወዘተ ቤታችሁ አደረጋችሁ!!! እናም እኔን ለመገልበጥ ታሴሩ ጀመር?  አላቸው፣ ጀነራል መኮንኖቹ የጠፋባቸውን ጥላቸውን አዩት! ‹‹አስራ ሰባት አመታት የታገልነው ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት ነው? ስንት ጎዶች መሠዋት ሆነዋል? እኛ ለሆዳችን አይደለም የምንኖረው? እኛ የህዝብ ልጆች ነን? ያን ሁሉ ዘመን የተጋትነው ፖለቲካ ለግል ጥቅም ነውን? እናንተን ቤተ መንግሥት ለማስገባት ስንት ሰው አለቀ፡፡››አሉት!!! እነዚህ የአማራ ጀነራል መኮንኖቹ  በሠራዊቱ ውስጥ ያለ የዘር አድሎ፣ የእድገት አድሎ፣ የክልላዊነት የቡድን ሥራ ይቁም፣ ወዘተ የሚሉ የሰራዊቱ ጥያቄን በመጠየቃቸው ብዙዎቹ አማራዎች  ከስራ ገበታቸው በመለስ ዜናዊ ቀጭን ትእዛዝ ተባረሩ፡፡

ህዝባዊ ዴሞክራቲክ ጋርድ፡- የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት፣ የቻይና ቴሌኮም ካንፓኒ፤ ዜድቲኢና ሀዊ ድርጅቶች ለህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ በመሰለልና የሃገሪቱን ምስጢርና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስለላ መረብ በማስገባት ከፍተኛ ጥቃት በማድረሳቸው የአንድ ወር የሞባይል ስልክና ካርድ ያለመጠቀም አድማ እንዲደረግ ለአስተባባሪዎቹ ህዝባዊ ጥያቄ አቅርበናል፡፡ የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት በ14 ጁላይ 2009 እኤአ የሰዎችን የስልክ ንግግሮች ጠልፎ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ (የወንጀል መዝገብ ቤት) በማስረከብ በተከሳሾቹ ላይ ፍርድ ቤት እንደማስረጃ ተቆጥሮ ባደረጉት የስልክ ንግግር ብቻ ስለምን ጉዳይ እንደተወያዩ ሳይገለፅ በመንግሥት መገልበጥ ወንጀለኛ ተብለው በአሰቃቂ ግርፋትና ድብደባ ተደርጎባቸው እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የቻይናውያኑ ዜድቲኢ እና ሀዊ  ካንፓኒዎችና የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የጠለፈውን የስልክ ንግግሮች የያዘ የስለላ ሠነድ ከመኃተምና ከፊርማ ጋር ተያይዞ በማስረጃነት ቀርቦል፣እንደነበር ልብ ይበሉ፡፡

የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይማር ያስተማራቸውን ህዝቡ ጥያቄ መሠረት በማድረግ በቀ.ኃ.ሥ ዘመን በ1953፣ በደርግ ዘመን በ1981 እና በወያኔ ዘመን በ2002 ዓ/ም የአገዛዝ ሥርዓት ላይ ተቃውመው መንግሥት ለመቀየር ተንቀሳቅሰው የነበረበት ወርቃማ ታሪክ ያፃፉበት ዘመን ነበር፡፡ በዚህም የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት  ትግል ህብረ-ብሄር የሚወክሉ ብዙ ጀነራል መኮንኖች ክብር ህይወታቸውን ለኢትዩጵያ ህዝብ ተሠውተዋል፡፡ ክብርና ሞገስ ለተሠው ህብረ-ብሄር የኢትዩጵያ ሠራዊት አባላት ይሁን፡፡ ለሃገር ሉዓላዊነትና ለወገን ፍቅር ብለው ውድ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ምርጥ ጀግኖች ለዘላለም ሲዘከሩ ይኖራሉ፡፡ህዝባዊ ዴሞክራቲክ ጋርድ፡-የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት፣ቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. ድርጅቶች ለህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍን ውስጥ በመሰለልና የሃገሪቱን ምስጢርና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስለላ መረብ በማስገባት ከፍተኛ ጥቃት አድርሰዋል፡፡በ2002 ዓ/ም መለስ ዜናዊ ለማውረድ በተደረገው ሙከራ የታሰሩ ጀነራል መኮንኖች የኢትዩጵያ ልጆች ሳናስፈታ እንቅልፍ የለም!!!እናስታውስ፡-

  1 ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ጨርቆስ         2 ብ/ጄ አሣምነው ፅጌ ተበጀ      3 ሌ/ኮ ደምሰው አንተነህ ደመላሽ
4 ሻለቃ መኮንን ወርቁ አለሙ        5 ሌ/ኮ አለሁበል አማረ ዋሴ      6 ሌ/ኮ አበረ አሰፋ አበራ
7 ሌ/ኮ አለሙ ጌትነት አባተ       8 ሌ/ኮ ሰለሞን አሻግሬ አምበርብር 9 ሌ/ኮ ጌታቸው ብርሌ ደሴ
10 ሻ/ል ተመስገን ባይለየኝ ፀጋው  11 ሻለቃ አዱኛ አለማየሁ ገ/ማ እሸቴ 12 ሌ/ኮ ፋንታሁን መሃባ መፍቲ
13 ሻለቃ መሠከረ ካሣ ወንድም 14 ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ ተገኝ 15 ሻለቃ ፋናዬ ውቤ ሙጬ
16 መ/አ አባቡ ተፈሪ አለሙ 17 ሻለቃ አደፍርስ አሣምነው ክብረት 18 ያረጋል ይማም ሚኪ           
19 ክፍሌ ስንሻው ታገደ 20 መዘምር የሸዋስ መንገሻ በየነ 21 መንግስቱ አበበ አረጋዊ ሳሚ    
22 እማዋይሽ አለሙ ወ/ሚካኤል 23 ጎሽራድ ፀጋው አጋፋሪ 24 መላኩ ተፈራ ጥላሁን
25 ዳን ያባቱ ስም ያልታወቀ            26 አማኑኤል ያባቱ ስም ያልታወቀ 27 አወቀ አፈወርቅ            
28 ዋና ሣይጅን አመራር ባያብል ካሣ 29 ኢንስፔክተር አራጋው አስፋው ረታ 30 ም/ሣጅን ጎበና በላይ አየለ
31 ረ/ሣጅን ይበልጣል ብርሃኑ ተፈራ 32 ም/ሣጅን የሸዋስ ምትኩ ቸኮል 33 ሣጅን ወድነሽ ተመስገን አለሙ
34 ሣጅን አይተን ካሣ መኮንን   35 ጌቱ ወልዴ አባይ ሆይ      36 ጌቱ ወርቁ ንዳው                   
37 ፅጌ ኃብተማሪያም ጨሚሣ 38 ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር      39 አንዳርጋቸው ፅጌ ኃብተማሪያም
40 ሙሉነህ እዩኤል ፋኔ       41 ኤፍሬም ማዴቦ 42 ዳንኤል አሠፋ
43 ቸኮል ጌታሁን  44 መስፍን አማን 45 ፋሲል የኔአለም
46 ደረጀ ሃብተወልድ                               

የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት በ14 ጁላይ 2009 እኤአ የሰዎችን የስልክ ንግግሮች ጠልፎ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ (የወንጀል መዝገብ ቤት) በማስረከብ በተከሳሾቹ ላይ ፍርድ ቤት እንደማስረጃ ተቆጥሮ ባደረጉት የስልክ ንግግር ብቻ ስለምን ጉዳይ እንደተወያዩ ሳይገለፅ በመንግሥት መገልበጥ ወንጀለኛ ተብለው በአሰቃቂ ግርፋትና ድብደባ ተደርጎባቸው እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የጠለፈውን የስልክ ንግግሮች የያዘ የስለላ ሠነድ ከመኃተምና ከፊርማ ጋር ተያይዞ በማስረጃነት (በክፍል ሁለት) ቀርቦል፣ ያንብቡትና የቴሌን ጆሮ ጠቢዎች ጠንቀቅ ይበሉ፡፡ የቻይናውያኑ ዜድቲኢ እና ሀዊ  ካንፓኒዎች ለዚህም ስራቸው ያለ አንዳች ነፃ ውድድርና ጨረታ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ሥራን ሁሉ እንዲሰሩ ተሰጥቶቸዋል፡፡ የቻይናዊያን ሾተላይ ሰላዬች፤ የቻይና መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽንና የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ኃብት  በመቆጣጠርና የቻይና ኢንፖርት ኤክስፖርት ባንክ ደግሞ ብድር በማመቻቸት  99 በመቶ የኃብቱን ድርሻ በመያዝ ኢትዩቴሌኮም ፕራይቬታይዝ ለማድረግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ኢትዩቴሌኮም ዋናው መ/ቤት የህወሃት ዶ/ር ደብረፂዎንና የደህንነት መስሪያ ቤት ሹም ጌታቸው አሰፋ እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ የስልክ/ የሞባይል/ ኢንተርኔት የተለያዩ ድረ ገፆች፣ኢሜል (የፅሁፍ መልእክቶች)፣ በሃገር ውስጥና በባህር ማዶ በሚገኙ ኢትዬጵያዊያን ዜጎች ላይ ስለላ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ከነዚህም መኃል በዴሞክራቲክ ጋርድ፣ የኢትዩጵያ የነፃነትና ዴሞክራቲክ ሃይል፣ በግንቦት ሰባት አባላቶች (አንዳርጋቸው ፅጌና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ)፣ጋዜጠኞች (ውጭ የተሰደዱ ሃያ በላይ ጋዜጠኞች)፣ጦማርያን (ዞን 9)ና ምሁራኖች (ዶ/ር ታደሠ ብሩ) የሙስሊም ህብረተሰብ፣ በፅንፈኝነት፣ አክራሪነትና መንግስት ግልበጣ ወዘተ  ፍርጆ በኢትዩጵያ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ መጠቀሚያ በማድረግ ዜጎችን በማሰቃየት፣ በማሰር በመግረፍና በመሰወርና በመግደል የፈፀሙት ወንጀል ታሪክ ይቅር የማይለው የስለላ ተግባር በኢትዩጵያ ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤትና የኢትዩቻይና የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በማህተም ያረጋገጡትና  ያቀረቡት የስለላ ማስረጃነት በወህኒ ቤት የሚገኙት የህዝብ ልጆች የመከላከያ ሠራዊት አባላቶች ገሃድ ምስክሮች ናቸው፡፡ የጀነራል መኮንኖቹ (በዴሞክራቲክ ጋርድ) በስብሰባዎች ላይ ባነሱት ጥያቄዎች ውስጥ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የትግራይ የበላይነት ይወገድ፣ በሠራዊቱ ውስጥ በተለይ በሜቴክ የሙስናና ንቅዘት ይቁም፣ በኢትዩጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በአፍሪካ፣ የሙስናና የዝምድና ሥራ ይብቃ፣የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት በወታደራዊ ሣይንስ አመራር ችሎታ ያላቸው መሪዎች ይመራ፣ በሠራዊቱ ውስጥ ያለ የዘር አድሎ፣ የእድገት አድሎ፣የክልላዊነት የቡድን ሥራ ይቁም፣ወዘተ የሚሉ የሰራዊቱ ጥያቄን በመጠየቃቸው የታሰሩ ህብረ ብሄር የሃገራችን ብርቅያ ልጆች ናቸው፡፡  የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ፤የቻይና መንግስትና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ምን ዓይነት እንደሆነ ለአመል ታህል እንመልከት፡፡ የቻይና መንግስት በአንድ ሃገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት መርህ አለኝ ቢልም ከኢትዬጵያ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ጋር በቴሌኮምኒኬሽን ዘርፍ በተለይ በኢንተርኔትና  በሞባይል አገልግሎቶች ላይ ስለላ በማድረግ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ነፃ ጋዜጠኞችን፣ዲያስፖራዎችንና ምሁራኑን በመሰለል ትልቅ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ስብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች፣የነፃ ፕሬስ፣የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ (የፓርቲዎች ውድድርና ምርጫ፣የሲቨል ሶሳይቲ የፕሬስ ነፃነት፣ሬዲዩ፣ቲቪ፣ጋዜጣ፣ድረ-ገፅ፣ ኢንተርኔት፤ ወዘተ በቻይና መንግስትና ኮምኒስት ፓርቲ፤ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ መሬት፣ ባንክ ኢንሹራንስ፣ ቴሌኮምኒኬሽን፣ መብራት ኃይል ወዘተ በአጠቃላይ የግብርና፤ኢንደስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች በልማታዊ መንግስት ቁጥጥር ስር ሲሆኑ ስርአቱ በፖለቲከኛ ካድሬዎች ሙስናና ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት ውስጥ እንደሚገኝ እሙን ነው፡፡

የወህኒ ቤቶች ሁኔታ Prison and Detention Center Conditions

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የወህኒ ቤቶች ሁኔታ በተመለከተ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ ሦስት የፊዴራል እስር ቤቶችና 120 የክልል መንግስቶች እስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ብዙ ይፋ ያልሆኑ እስር ቤቶች በሃገሪቱ ውስጥ ሲገኙ ከነዚህ መኃከልም በዴዴሳ፣ በብር ሸለቆ፣በጦላይ፣ሆርማት፣ብላቴ፣ታጠቅ፣ጅጅጋ፣ሆለታና ሰንቀሌ የጦር ካንፖች ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የወህኒ ቤቶች ሁኔታ ለእስረኛዎች ህይወት በጣም አስጊና ብዙ ሰዎች ተፋፍገው የታሰሩበትና ለመተኛት አመች ያልሆኑ ቦታዎች ናቸው፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ለእስረኞች በቀን ስምንት ብር ወይም ግማሽ ዶላር ለምግብ፣ ለውሃና ለጤና ጥበቃ ወጪ ያወጣል፡፡ ብዙዎቹ እስረኞች ተጨማሪ ምግብ ቤተሰቦቻቸው እየገዙ ያቀርቡላቸዋል፡፡ የእስረኞች ጤና ጥበቃ በተመለከተ በፊዴራል እስር ቤቶች ውስጥ አስተማማኝ ህክምና አያገኑም፤ በክልል እስር ቤቶች ውስጥም የህክምና አገልግሎት የለም፡፡ በሃገሪቱ በሚገኙ ወህኒ ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመኖሩ የተነሳ እስረኞች ንፅህናቸውን ለመጠበቅ ባለመቻላቸው ብዙዎቹ በጤና ችግር ይሰቃያሉ፡፡ እስረኞች አነስተኛ የህክምና አገልግሎት ብቻ ያገኛሉ፡፡ በወርሃ የካቲት በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ አንድ የጣልያን ዜጋ በህክምና እጦት የተነሳ ህይወቱ አልፎል፡፡ በአመቱ መገባደጃ ላይ በአጠቃላይ በግምት 86,000 ሽህ እስረኞች ሲገኙ ከዚህ ውስጥ 2,474 ሴት እስረኞች ሲሆኑ፣ 546 ህፃናቶች ከእናታቸው ጋር ታስረው ይገኛሉ፡፡ የወጣት ጥፋተኞች አንዳንድ ግዜ ሞት ከተፈረደባቸው ጎልማሶች ጋር በአንድ ላይ ይታሰራሉ፡፡ በአጠቃላይ ወንድና ሴት እስረኞች በተለያዩ ቦታዎች ታስረው ይገኛሉ፣ ቤተሰቦቻቸውም ይጠይቆቸዋል፡፡ በሌላ በኩል  ቤተሰቦቻቸው የማይጠይቆቸው የተከለከሉ ጥቂት እስረኞች ይገኛሉ፡፡ The country has three federal and 120 regional prisons. There also are many unofficial detention centers throughout the country, including in Dedessa, Bir Sheleko, Tolay, Hormat, Blate, Tatek, Jijiga, Holeta, and Senkele. Most are located at military camps. Prison and pretrial detention center conditions remained harsh and in some cases life threatening. Severe overcrowding was common, especially in sleeping quarters.  The government provided approximately eight birr ($0.50) per prisoner per day for food, water, and health care. Many prisoners supplemented this with daily food deliveries from family members or by purchasing food from local vendors. Medical care was unreliable in federal prisons and almost nonexistent in regional prisons. Water shortages caused unhygienic conditions, and most prisons lacked appropriate sanitary facilities. Many prisoners had serious health problems in detention but received little treatment.  In April an Italian citizen died after receiving allegedly substandard medical treatment in Kality prison. At year’s end there were an estimated 86,000 persons in prison, of whom 2,474 were women and 546 were children incarcerated with their mothers. Juveniles were sometimes incarcerated with adults who were awaiting execution. Male and female prisoners generally were separated. Authorities generally permitted visitors. In some cases family visits to prisoners were restricted to a few per year.

ቻይና ኮምኒስት ፓርቲና ከህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ጋር የኢሳት ሳተላይት ቲቪና ሬዲዩ፣ የሱማሌ፣ የጋምቤላ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ ወዘተ  ህዝብ ላይ የደረሰውን እልቂት ዜናን ለኢትዮጵያ ህዝብ  በማጋለጥ የኢሣት መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ያበረከተውን ታላቅ አስተዎፆኦ ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል፡፡ ኢሳትን ለመዝጋት የቻይና ህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት በመቃወምና አሁንም የቀሩት የህሊና እስረኞች፣ የኢትዩጵያ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የግንቦት 7  የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ!!! እነ ብርጌደር ጀነራል ተፈራ ማሞ፤ብርጌደር ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ እማዋይሽ አለሙ ወ/ሚካኤል፣ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ!!! ከወልቃይት ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ፣ ንግስት አዳነና ሌሎችም በአስቸኮይ እንዲፈቱ ህዝብ ይጠይቃል!!! ከጋምቤላ ቱወት ፖል ሌሎችም ይፈቱ!!! ከኦጋዴን አብዲከሪም ሼህ ሙሴ ሌሎችም ይፈቱ!!! ተፅዕኖ ለማድረግ ኢትዩቴሌኮምን ያለመጠቀም አድማ በተግባር እናሳይ፡፡ በዚህም የኢትዩቴሌኮምን የገንዘብ ምንጭን ለመዝጋት የኢትዩጵያን የትግል ሥልት ለዓለም ዐቀፍ ህብረተሰብ ዘንድ በማስመዝገብ የህወኃት ኢኮኖሚ እናንኮታኩት፡፡ ይህንንም የህብረት የትግል ጥሪ የኢትዩጵዊያን ድረ-ገፆች፣የኢትዩጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን (ኢሣት)፣ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ፣ ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች አስተባባሪ፣ የአማራ ወጣቶች አስተባባሪ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር፣ ግንቦት ሰባት፣ በማህበራዊ ድረ,ገፆች አክቲቪስቶች (በፋስቡክ፣ ቲውተር፣ ወዘተ) በልዩ ልዩ መገኛኛ አውታሮች ወዘተ በኢትዩጵያ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱና በህወኃት እስርቤቶች ውስጥ የሚደረጉ ኢሰባዓዊ ግርፋትና የወሲብ ጥቃትን ለዓለም ህብረተሰብ ለማጋለጥ የሚደረግ ህዝባዊ ጥሪ እንዲደረግ የማስተባበርና የአድማውን ቀን የመቁረጥ  አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የወያኔ መንግሥታዊ ነጭ ሽብር በህዝባዊ አመፅ ይከሽፋል!!!   ብሄራዊ የፖለቲካ ጠቅላይ መምሪያ ይቆቆም!!!

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡- የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት የአግዓዚ ጦር መንግሥታዊ ነጭ ሽብር ቀጥሎል፣ የኢትዮጵያዊያንን ህዝባዊ ትግል በጠመንጃ አፈሙዝ ለማፈን ግን ጭራሽ አይቻለውም፡፡ ፋሽታዊው የአግዓዚ ጦር  ነፍሰበላ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ፣ የአግዓዚ ጦር ትጥቅ ፈትቶ በመከላከያ ሠራዊት ይተካ ፡፡ ይህንን ትግል ከዳር ለማድረስ ሃገር አቀፍ ትግል ግድ ይላል፣ ትግሉን የምትመሩ ድርጅቶች የሦስት ቀን የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ፣ በመላ ሃገሪቱ እንድትጠሩ እንጠይቃለን፡፡ ኢትዩቴሌኮምን ያለመጠቀም የአስር ቀን ብሄራዊ አገር አቀፍ አድማ በማድረግና የገንዘብ ምንጭን በመዝጋት የወያኔን ኢኮኖሚ ለማድቀቅ ለትግል የአድማውን ቀነ ቀጠሮ  ወስናችሁ ግለፁ ወይ ምሩ ወይ ውረዱ!!!በተግባር አሳዩ፣ ቆራጥ አመራር ከእናንተ ህዝብ ይጠብቃል፡፡‹‹ባትዋጋ እንኮን በል እንገፍ እንገፍ፣ ያባትህ ጋሻ ትኃኑ ይርገፍ!!!!››

የህወሓት አግአዚ ጦር ሠራዊት ለፍርድ ይቅረቡ!!! ክብር  ለተሠው ኢትዮጵያውያን ሠማዕታት ይሁን!!!   በአንድ ላይ በህብረት እንነሳ!!!

የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት አፈሙዝህን ወደ ወያኔ አዙር!!!  የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!

በወያኔ እስር ቤቶች ውስጥ ኢስብዓዊ ግርፋትና ማሰቃየት ይቁም!!!

በወያኔ እስር ቤቶች ውስጥ ኢስብአዊ የወሲብ ጥቃት ይቁም!!!

የወያኔ እስር ቤቶች በዓለም ዓቀፍ ስብአዊ መብት ኮሚሽን ይጎብኙ!!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s