በጠራራው ፀሐይ ጧፍ አብርቼ እንደ ዲዮጋን ለፈለግኋቸው አባቶቼ | ሰላሞቻችንን ፍቱልን – ዲ/ን አባይነህ ካሴ

እልፍ ደስታ በልቡናየ የደም ሥሮች ሁሉ ይወጣሉ ይወርዳሉ፡፡ ብዙ የሀገር ልጆች በአጥር ከተዘጋው እስር ቤት ወደ ክፍቱ እስር ቤት ስለወጡ፡፡ ይህም አንድ ጋት ነፃነት ነውና፡፡ በመገደድም ይሁን በመፍቀድ ይህን ያደረጉትን ሁሉ ማመስገን ይገባናል፡፡ በቂም ቋጠሮ የትም አንደርስምና ልቦናችን ሁሉ በይቅርታ ደም ይገንባ!

ከተፈቱት መኻል ዐይኖቼ አሁንም ይንከራተታሉ፣ ማረፊያቸውን ግን አላገኙም፡፡ እነ አባ ገብረ ኢየሱስ የታሉ? አዎ እነርሱ ሰው የላቸውም፡፡ ፓርቲም የላቸውም፡፡ ወዳጅ ዘመድም የላቸውም፡፡ መናኞች ናቸዋ! የሰማይ እንጅ የምድር ጠበቃ የላቸውም፡፡ ግን አገር አላቸው፡፡ ለአገርም ይጸልያሉ፡፡ ለአንዲት ሃይማኖት ክብር ይታገላሉ፡፡ ሥጋቸውን እንጅ ነፍሳቸውን የሚያስርም የሚገድልም የለባቸውም፡፡

እነ አህመዲን ጀበልን የፈቱ በተመሳሳይ አመክንዮ እነ አባ ገብረ ኢየሱስም ይፈቱ ዘንድ ግዴታ አለባቸው፡፡ የግፉን ተራራ ጫፍ ለማሳየት ከኾነ ከበቂ በላይ ዐይተነዋል፡፡ አባ ገብረ ኢየሱስን እና አባ ገብረ ሥላሴን አስሮ ማስቀረት ዋልድባን ማሠር ነው፡፡ ዋልድባን ማሠር መላው ገዳማትን ማሠር ነው፡፡ ዋልድባን ማሰር ለሀገር አደጋ አለው፡፡ በዋልድባ ላይ የተዋለው ክፋት መዘዙ እስካሁን አላባራም፡፡ ነገሩን እናስረዝመዋለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ቀጣዩ መዘዝ በራሳቸው በደጃቸው እንደቆመ ሊያውቁት ይገባል፡፡ ይልቁንስ ፍቷቸውና ለሀገር ሰለም ይጸልዩ!

የኢትዮጵያ መነኮሳት መናኞች ብቻ ሳይኾኑ ጥርት ያሉ ኢትዮጵያውያንም ናቸው፡፡ አቡነ ሚካኤልና አቡነ ጴጥሮስን ለሚያውቅ ትውልድ ይህ እንግዳ አይኾንበትም፡፡ ሰውን ብቻ ሳይኾን ምድርንም ይገዝታሉ፡፡ ለሥልጣናቸው ገደብ የለበትም፡፡ እናም ለጣልያን ሰው ብቻ ሳይኾን ምድሪቱም አልተገዛችም፡፡ ይህ የነፃነት ጽሑፍ በታሪክ ማማ ላይ ዛሬም በኩራት ይነበባል፡፡ ለዋልድባ መነኮሳት ኢትዮጵያ ትገዛለች፡፡ ዋልድባን ለሚዳፈሩት ቅጣታቸውን ከደጃቸው ትሰፍርላቸዋለች፡፡ ለሰላማችን ሲባል የሰላም ሰዎችን መፍታት ይገባናል፡፡ ሰላምን አስሮ ሰላም ማምጣት አይቻልም፡፡ ሰላሞቻችንን ፍቱልን፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s