ያልተፈቱት ወገኖቻችን አብዛኛዎቹ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ናቸዉ…. (ልዑል ዓለሜ)

የብሄራዊ መረጃዉ ግፍን ሰማን

የእስረኞች ተፈቱ ደስታም መከነብን።

በእስር ከተፈቱት ወንድሞቻችን ዉስጥ አብላጫዎቹ በእንባ እየተራጩ ዘመድ ከዘመድ ቤተሰብ ከቤተሰብ እንደሚለያይ ሁሉ ያልተፈቱትን ወገኖቻቸዉን በታላቅና በመሪር ሐዘን እንደተለዯቸዉ ሰማን ምክንያቱ ምን ይሆን ለምን አልተፈቱም ብለን ስንጠየቅ ከመረጃ ክፍል ምንጮች የሰማነዉ ከባድ ሐዘን ነዉ።

አብዛኛዎቹ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ናቸዉ….

የዉስጥ አካላቸዉ እንዳይሰራ ሁሉ ተደርገዉ የተደበደቡ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ የተገረፉ፣ ኩላሊታቸዉ የፈረሰ፣ አይምሯቸዉን የሳቱ፣ በነፍስ ግቢና በንፍስ ዉጪ ላይ የሚገኙ አሉ ተባልን….  ዝዋይ ቂሊንጦ ከርቸሌ አሉ የሚባልላቸዉ የት እንደደረሱ የማይታወቁም ይገኛሉ… ለህወሃት ወያኔ እነዚህን ታራሚዎች መልቀቅ ማለት በራሱ ላይ ጋዝ አርከፍክፎ እንደመለኮስ ይቆጠራል ሲሉ የብሄራዊ መረጃ ምንጮች እየተናገሩ ነዉ።

እጅግ የሚያሳዝነዉ በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት እንዳይሆን ሆነዉ እንዲነዱ የተደረጉ ወንድሞቻችን ሞት እየተመኙ  በህይወት ኖረዉ ሐዘናቸዉ እንዲጸና በክፉ ቁስል የሚንገላቱ እንደ ላስቲክ የቀለጡ አሉ።

አንድ የህሊና እስረኛ በትለቀቃለህ ዜና ወቅት ለእስር ቤት ዘበኛ ” ጉደኞቼስ እገሌን ማን ይንከባከበዋል እኔ ከጎኑ ከሌለዉ የሚጠብቀዉ ሞት እኮ ነዉ ” ብሎ በመናገሩ ዘቡ ተደብቆ ማልቀሱን ሰማን በህወሃት የእስር ዘመን ይህን ታላቅ ትምህርት ተማርን “በዉጭ ያለዉን ለማግኘት ከመናፈቅህ በፊት በዉስጥ ጥለህ የምትሄደዉን ዘወር ብለህ ተመልከት”

ወገኖቼ የተፈቱት ጥቂት ቢሆኑም እነርሱ ለኛ የከፈሉት መሰዋት እኛን ከፊት ሊያስቀድመን ይገባል አሁን እነርሱን ከኋላችን አድርገን ደረታችንን ከፊት እናስቀድም ብዙ የሚነግሩን ጉድ አለ እኛ ብዙ የምንወጣዉ ግዳጅ ይኖረናል።

አማራዉ ወገን አንዳች ነገር ተንፍሷል ተብሎ ከያለበት እየታፈነ ተከርችሟል ኦሮሞዉ በሐዘን ልቡ ተሰብሯል ጉራጌዉ የእገሌ ደጋፊ ተብሎ በየ ማጎሪያዉ ታጭቋል ደቡቡ ሱማሌዉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህወሃት ወያኔ እስር ቤት ዉስጥ በስቃይ ላይ ይገኛል።

አንዳንዶች አጥንታቸዉ ተሰብሮ ፍርድ ቤት መሄድ በሚገባቸዉ ወቅት ላይ ሚስጥሩን ለመደበቅ ሲባል ታፍነዉ ተይዘዋል።

ሌሎ  ከፍተኛ ስቃይ የደረሰባቸዉ ህዝብ ዘንድ ደርሰዉ እንዳይተነፍሱ ተገድለዋል።

ሌሎች በተለየ መልኩ አንዳች ነገር ብትናገር  ልጅህን ሚስትህን ታጣለህ ተብለው ዋስትና ተይዞባቸዋል።

እንግዲህ ምን እንጠብቃለን………………!

ዉድ ኢትዮጵያዊያን ያልተናገርነዉን ሁሉ ነገር ግን የሰማነዉን ግፍ ስናጤነዉ የእስረኞች መፈታት ደስታዉ መከነብን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s