ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY: ‹‹ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት የህወሓት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ድምፅ እቀባ በማድረግ ታሪክ ሥሩ!!!››

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

‹‹ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት የህወሓት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ድምፅ እቀባ በማድረግ ታሪክ ሥሩ!!!››

‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ዶክተር እሸቱ ጮሌ ክበብ››

‹‹ባትዋጋ እንኮ በል እንገፍ እንገፍ፣

የአባትህ ጋሻ ትኃኑ ይርገፍ!!!››

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች ሁሉ፡- ብሄራዊ ትግሉን አቀናጅታችሁ እንድትመሩ ህዝቡ ይጠይቃል፡፡

ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ድምፅ እቀባ አድማ  

{1} የሚኒስትሮች ምክርቤት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› አውጆል በህገመንግስቱ በተደነገገው የጊዜ ወሰን ውስጥ ፣የታወጀውን  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል፡፡ በዚህ መሰረት ሁለት ዓመት የሥራ ጊዜ ዘመን የቀራችሁ ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት የተደነገገውን ፋሽስታዊ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክር ቤቱ የድምፅ እቀባ ውድቅ እንዲያደርግ ህዝብ ይጠየቀል፡፡  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ውድቅ ላደረጉ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ህዝቡ በሚቀጥለው ምርጫ እንደሚመርጣቸው ቃል ይገባል፡፡ አዲሱ የፓርላማ ወጣት ትውልድ በኢትዮጵያዊያን ወገኞቹ ጋር በመቆም ታሪክ መሥሪያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በመቃወማችሁ ምክንያት ለሚደርስባችሁ ሁሉ በአገር ውስጥና በባህር ማዶ ወገኞቻችሁ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ‹የፓርላማ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ›በማዋቀር ለመርዳት ቃል ይገባል፡፡ በኢትዮጵያዊያ ህዝብ የታሰሩትን የህዝብ ልጆች እንዳስፈታ ልብ ይበሉ፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ፣ የእንግዚዝ መንግስት፣ የካናዳ መንግስት፣ የጀርመን መንግሥት፣የኖርዌ መንግሥት እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አገራቶች ይህን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› መቃወማቸውን ይወቁ፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ኤች አር 128 ኢትጵያ መንግሥት የዓለም ስብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃገሪቱ ውስት ገብተው ግድያውን እንዲያጣሩ  የካቲት 28 ድረስ ቀነገደብ አስቀምጠዋል ካለበለዛ ልልዩ ማእቀቦች በህወኃት/ኢህአዴግ ሹማምንትና በሃገሪቱ ላይ የኢኮኖሚ እቀባ ይከተላል፡፡ የወያኔን ፋሽስታዊ  አዋጅ የህዝቡን ዴሞክራሲዊና ስብዓዊ መብቶች የሚያፍን  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የደገፈ የህዝብ ወኪል በህብረተሰቡ ይገለላል እንዲሁም ዳግም የመመረጥ ዕድላቸው የጨለመ ይሆናል፡፡

{2} ህዝቡ የመንግሥት ግብር ለወያኔ መንግሥት የኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ባለመክፈል አድማ ይምታ

{3} ህዝቡ የብሄራዊ ሎተሪ ትኬቶች ባለመግዛት የወያኔን ገቢ ምንጭ የማሽምመድ አድማ ተጀምሮል፣ ሎተሪ ትኬት ባለመግዛት የወያኔን ገቢ በመቀነስ የወያኔን ጥይት መግዣ ማድረቅ ይቻላል፡፡ የተሠው ሠማዕታት ወንድሞቻችንን ደም ለማስታወስና ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› እስኪነሳ የብሄራዊ ሎተሪ ትኬቶች ባለመግዛት የአድማ ጥሪ ለህዝብ ቀርቦል፡፡

{4}ብሄራዊ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ማዘጋጀት፣

{5}የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››ካወጁ ልክ ከምስቱ ዎስት ሰዓት ላይ በመላ ሃገሪቱ የኡኡታ፣የፉጨት፣ የጡሩንባና የፌሽካ ድምፅ ማሰማት አድማ ይካሄዳል፡፡ ይህንንም ጥረ በሃገር ውስትና የባህር ማዳ በሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መረጃውን ለህዝብ እንዲያዳርሱ  ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

{1} የአገር ውስጥ ታክስ፣ የውጭ ንግድና ቀረጥ ገቢዎችና የብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ ገቢ አሽቆልቁሎል

በ2008ዓ/ም 133 ቢሊዩን ብር ከህዝብ በግብር ሰበሰቡ፤ወያኔ በ2009ዓ/ም የኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 173.19 ቢሊዩን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 113.56 ቢሊዩን ብር ብቻ በመሰብሰቡ የጎደለውን 59.63 ቢሊዩን ብር በቀሪው ሁለት ወራቶች ውስጥ ለመሰብሰብ በመገደዱ ከህብረተሰቡ ተጨማሪ ግብር ለመሰብሰብ አስቸኮይ የስራ ዘመቻ ነበር የከፈተው፡፡ በዛም የተነሳ ህዝብ ላይ የተጫነው ግብር ዋናው ምክንያት ለ‹‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ›› በኮማንድ ፖስቱ አወጣ፡፡ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የአጋዚ ጦር፣ልዩ ኃይል፣ ወዘተ የደሞዝ፣ የቀን አበል ያልተጠበቀና በበጀት ያልተያዘ ወጪ ሥርአቱን አናግቶታል፡፡ በሃገሪቱ በ2008 ዓ/ም  የተጀመረው እስከ 2009 እሰከ 2010ዓ/ም በተቀሰቀሳ ሕዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ምክንያት የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት ከህዝብ፣ ከግብርና እና ታክስ የሚሰበስበው ገቢ በጣም ቀንሶል፡፡

‹‹በ2010ዓ/ም መንፈቅ ዓመት ከአገር ውስጥ ታክስ፣ ከውጭ ንግድና ቀረጥ ገቢዎችና ከብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ 199.11 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ነው የታቀደው፡፡ በስድስት ወራት ታዲያ መሰብሰብ የተቻለው ከ90 ቢሊዮን ብር ብዙም የዘለለ አይደለም፡፡ ይህ አኃዝ ከዓመታዊ ዕቅዱ አንፃር ሲመዘን ከ40 በመቶ በታች ነው፡፡ ለገቢው መቀነስ የግብር ከፋዮ የህግ ተገዥነት ዝቅተኛ መሆን በምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የቁጥጥር መላላትና የአሰራር ክፍተቶች፣ የግንዛቤ ማነስና የግብር ሥወራም የግብር አሰባሰብ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ እየተስፋፋ የመጣው ኮንትሮባንድ የግብር ትልቅ ፈተና ሆኖል፡፡ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ብቻ 436.74 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ዕቃዎች በኮንትሮባንድ  ወደ አገር ውስጥ ሊገቡና ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተመልክቶል፡፡ ይህን ህገ ወጥ ድርጊት መግታት ካልተቻለ በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው፡፡››… ‹‹የገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት፣ የኮንትሮባንድ ሰለባ እንደሆነ የሚጠቁሙት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 109ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ  አቅዶ አለመሳካቱን በማሳያነት ያቀርባሉ፡፡… ለኮንትሮባንድ መሥፋፋት የገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ህጉን የማስፈፀም አቅም ደካማ መሆን ነው ይላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በየክልሉ የድንበር ንግድ ተብሎ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ዕቃ በገፍ እገባ እንደሆነ ገልፀው በዚህ አጋጣሚ የኮንትሮባንድ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ አካላት መኖራቸውን ያመለክታሉ፡፡ ይህን ማሰወገድ እንደሚገባም ይጠቁማሉ፡፡›› አቶ ዮሃንስ ወልደገብርኤል፡፡

የህወኃት/ኢህአዴግ መንግስት ‹‹በ2010ዓ/ም መንፈቅ ዓመት ከአገር ውስጥ ታክስ፣ ከውጭ ንግድና ቀረጥ ገቢዎችና ከብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ 199 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶል፡፡ በ2010 ዓ/ም በስድስት ወራት ውስጥ  መሰብሰብ የተቻለው ከ90 ቢሊዮን ብር ሲሆን አፈፃፀሙ የእቅዱን 45 በመቶ ሆኖል፡፡

 

{2} የመደበኛው ባጀት ወጪ መጨመር የኢኮኖሚ ውድቀቱን አፋጥኖል

በሌላ በኩል መደበኛው ባጀት(ለመንግስት ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ  ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የመደበኛው ባጀት በየግዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በ2002 እኢአ 14.5 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት(22.48) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ2004 እኢአ  23.0 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (19.52) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2006 እኢአ  32.56 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (21.01) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2007 እኢአ  45.05 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የመደበኛው ባጀት (25.22) በመቶኛ እድገት አሳይቶል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የ2008ዓ/ም በጀት 223 ቢሊዩን 397 ሚሊዩን 819 ሽህ 216 ብር እንዲሆን ለሚንስትሮች ምክር ቤት አስወስኖ ለፓርላማ እንዲፀድቅ አስደርጎል በጀቱ ከአለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር 44.58 ቢሊዩን ብር ብልጫ እንዳለው ታውቆል፡፡የ2008ዓ/ም መደበኛው በጀት 50,288,442,902 ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ የ2010ዓ/ም መደበኛው በጀት 82 ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ በመንፈቅ ዓመቱ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ወያኔ አፀድቆ ሃገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ገደል እየከተተ ይገኛል ይህም አልበቃ ብሎት ህወሓት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››በማወጅ የክልል መንግሥቶችን ሥልጣን በመንጠቅ ወታደራዊ አስተዳደር በመመሥረት የህዝብ ልጆችን ለመግደልና ለማሰር አቅዶል፡፡ ለዚህ ፋሽስታዊ ድርጊት ተባባሪ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት በታሪክ ያስጠይቃል፡፡

 

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ባጀት(ቢሊዩን ብር)

ከ2002/2009 እንደ ኢትጵያዊያን አቆጣጠር

የባጀት ዓይነት 2002ቢሊዩን ብር 2004ቢሊዩን ብር 2006ቢሊዩን ብር 2007ቢሊዩን ብር 2008ቢሊዩን ብር 2009ቢሊዩን ብር
ለመደበኛ ወጪ 14.5 23.0 32.56 45.05 50.288 82
ለካፒታል ፕሮጀክቶች ወጭ 29.1 48.0 64.29 66.99 84.300 115
ለክልል መንግስት ድጋፍ 20.9 31.4 43.09 51.50 76.808 117
ለምዕተ አመቱ የልማት ግቦች ማጠናከሪያ 15.0 15.00 15.00 12.000    7.0
ጠቅላላ ዓመታዊ የፌዴራል መንግስት ባጀት 64.5 117.8 154.94 178.6 223.3 321.8

 

የ2009 ዓ/ም መደበኛው በጀት

የ2009 ዓ/ም መደበኛው በጀት 82 ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2010 ዓ/ም የተያዘው ዓመታዊ በጀት 321.8 ቢሊዩን ብር ውስጥ የመደበኛ በጀት ወጪ ከ2008 ዓ/ም ጋር ሲወዳደር በ31 ቢሊዩን 712 ሚሊዩን ብር ሲጨምር፣ጭማሪው የ61 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡ ይህ አምራች ላልሆነው ለመንግስት ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት፣ለፖሊስ ሠራዊት፣ ለአጋዚ ጦር፣ ለልዩ ኃይል በአጠቃላይ ህዝቡን ለማፈን ለተሰማራው ፀረ ህዝብ ሠራዊት ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ፣ የመኪና ነዳጅ መግዣ ወጪ የሚሆን በጀት መሆኑን ህዝብ ሊያውቀው ይገባል፡፡ በህዝቡ ላይ የተጫነው ግብር የቀጣዩን ዓመታዊ በጀት ለመሸፈን ‹‹ገበሬ የሚበላው ቢያጣ የሚከፍለው አያጣም!›› እንደሚባለው ነው፡፡

የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣በተጨማሪ አዲስ የመከላከያና ፖሊስ ሠራዊት መመልመያ፣ አዲስ ሚሊሽያ ሠራዊት መመልመያ፣ አዲስ እስር ቤቶች መገንቢያ፣ አዲስ ፖሊስ ጣቢያዎች ለመገንባትና የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ህዝባዊ ተጋድሎ ለማፈን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ/ም ባወጣው አዋጅ የተበጀተልን መደበኛ ወጪ ለሃገሪቱ ልማት ቢውል፣ ለረሃብተኛው ህዝብ እህል መግዣ ቢውል፣ ከዩኒቨርሲቲ ለተመረቁ ወጣቶች የሥራ መስክ ፈጠራ ላይ ቢውል፣ ለህብረተሰቡ የውሃ፣ ጤና፣ ትምህርትና መብራት አገልግሎት ላይ ቢውል መልካም ነበር፡፡

የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መደበኛው ባጀት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ለመንግስት ሠራተኛ ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ ያውለዋል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለኦሕዴድ) ሹማምንትና ካድሬዎች ለኦሮሚያ ክልል፣ ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ለብአዴን) ሹማምንትና ካድሬዎች ለአማራ ክልል፣ የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ) ሹማምንትና ካድሬዎች ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ ለሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለሶዴድ) ሹማምንትና ካድሬዎች ለሶማሌ ክልል፣ ለህወሃት ሹማምንትና ካድሬዎች  ትግራይ ክልል ፣ለአዴድ ሹማምንትና ካድሬዎች  የአፋር ክልል፣ ቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ለቤህነን)  ሹማምንትና ካድሬዎች የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ለጋሕነን) ሹማምንትና ካድሬዎች ለጋምቤላ ክልል፣ ለሃዴድ ሹማምንትና ካድሬዎች ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሃራሪ ክልል ሹማምንትና ካድሬዎች፣ ለአዲስአበባ አስተዳደር ሹማምንትና ካድሬዎች በ2002 እኢአ 14.5 ቢሊዩን ብር የነበረ ሲሆን በ2007 እኢአ 45.05 ቢሊዩን ብር፣ በ2008ዓ/ም መደበኛው በጀት 50,288,442,902 ቢሊዩን ብር ከፍ ማለቱ ተገልፆል፡፡ በ2009ዓ/ም መደበኛው በጀት 82 ቢሊዩን ብር ከፍ ማለቱ በአንድ ግዜ የ31 ቢሊዩን 712 ሚሊዩን ብር ጭማሪ ህብረተሰቡን ለከፍተኛ ግብር እንደዳረገው የምጣኔ ሃብት ጠበብት በማስረጃ ለህዝብ ያቀርባሉ፡፡

ህወሃት በመላ ሃገሪቱ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጂ፣በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለማፈን ከ2008 እስከ 2009 ዓ/ም መጨረሻ፣ ኮማንድ ፖስቱ ለመንግስት ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ የመኪና ነዳጅ፣ ለስራ ማስኪጃ፣ ለስብሰባ፣ለኮንፍረንስ፣ለመጎጎዣ፣ለአዲስ እስር ቤቶች መገንያና ለፖሊስ ጣቢያዎች መስሪያ ወዘተ የተለያዩ  ወጭዎች፣ በብዙ መቶ ቢሊዩን ብር የሚገመት ኪሣራ ተከናንቦል፡፡ ይህ ያገሪቱ አንጡራ ሃብት ለልማት ሥራ ውሎ ቢሆን፣በትንሹ ለተራቡ ወገኖቻችን በደረስልላቸው ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ አዲሱን 2010 ዓ/ም አመታዊ ባጀት መንፈቅ ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊዮን ብር በጀት ለወታደሩ ደሞዝ፣ለሥራ ማስኪጃ ወጪ ለማዋል ታቅዶል፡፡ የወያኔ መንግስት ወታደራዊ ወቺ በየግዜው በመጨመሩ የተነሳ ብዙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ለካፒታል በጀት የተያዘ 115 ቢሊዩን ብርና፣ ለክልሎች 117 ቢሊዩን ብረና ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ  ሰባት ቢሊዩን ብር የተደለደለው በጀት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ኮማንድ ፖስት ለወታደራዊ ወጪ መደልደሉን ታውቆል፡፡ የወያኔ መንግስት ቤሳቢስቲ ከካዝናው የለውም፡፡  በ2010 ዓ/ም  የተመደበው የፌዴራል መንግስት ባጀት የገቢ ምንጮች ከአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች፣ ከውጭ ብድርና እርዳታ የሚሞላ መሆኑ ተገልፆል፡፡ በአገሪቱ አምራቹ የሰው ሃይልና ግብር ከፋይ ዜጋዎች አምራች ባልሆኑ በሰው ተከሻ የሚኖሩ ጥገኛ የመንግስት ሹማምንት፣ካድሬዎች ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል ቀለብ ሲሰፍር ይኖራል፡፡

ከነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ‹መንግሥትና የህዝብ አስተዳደር›በሚል ርዕስ በ1916 እኢአ የታተመ መፅሃፋቸው ውስጥ የዛሬ ዘጠና ዓመታት እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹ብረት ሠሪውም ማረሻ አበጅቶ ጤፍ ይቀበላል፡፡ አራሹም ጤፍ ሰጥቶ የተሻለ ማረሻ ያገኛል፡፡በሌላም ነገር ሁሉ እንደዚሁ ነው፡፡ ዕውቀት ባለው ሕዝብ መካከል ግን በከንቱ የሚሰጥ ሰው የለም፡፡ በከንቱም የሚበላ ሰው የለም፡፡ የሁሉም  ትዳሩ ተለዋውጦ ነውና እንካ ሥራ አምጣ ሥራ ይባባላል፤ይህ ሳይሆን ቀርቶ በላተኛው ከሠራተኛው ሲበዛ በማናቸውም ቤት ሀብት ሊገባ አይችልም፡፡ ዕውቀትም ከሌለው ሕዝብ ውስጥ ከሠራተኛው በላተኛው፣ሹም ወታደር ነጋዴ እየሆነ ይበዛልና ባገሩ ሀብት ሊከማች አይችልም፡፡ የሥራው ፍሬ እንደ ገባ ወዲያው ያልቃል፡፡  ከነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ (መንግሥትና የህዝብ አስተዳደር ገፅ 64)

ለ/ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ባጀት

በተመሳሳይ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የካፒታል ባጀት በየግዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በ2002 እኢአ 29.1 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት(45.12) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ2004 እኢአ  48.0 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (40.75) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2006 እኢአ  64.29 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (41.49) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2007 እኢአ  66.99 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የካፒታል ፕሮጀክቶች ባጀት  (37.51) በመቶኛ እድገት አሳይቶል፡፡ የ2008ዓ/ም የሃገሪቱ አጠቃላይ በጀት 223.3 ቢሊዩን ሲሆን ከዚህ ውስጥ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት 84,300,732,449  ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡

የ2009 ዓ/ም የሃገሪቱ አጠቃላይ በጀት 321.8 ቢሊዩን ሲሆን ከዚህ ውስጥ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት 115  ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ የ2009 ዓ/ም የተያዘው በጀት ከአለፈው ዓመት የ30 ቢሊዩን 700 ሚሊዩን ብር ማለትም 73 በመቶ የበጀት ጭማሪ አሳይቶል፡፡

ሐ/ የክልል መንግስት ድጋፍ ባጀት

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ባጀት ለክልሎች መንግስት ድጋፍ ወይም ድጎማ ከ20.9 ቢሊዩን ብር ወደ 117 ቢሊዩን ብር እድገት ማሳየቱ ይስተዋላል፡፡ በ2002 እኢአ 20.9 ቢሊዩን ብር፣በ2004 እኢአ 31.4 ቢሊዩን ብር፣ በ2006 እኢአ 43.09 ቢሊዩን ብር፣ በ2007 እኢአ 51.50 ቢሊዩን ብር፣በ2008 እኢአ 76.8፣በ2009ዓ/ም 117 ቢሊዩን ብር አድጎል፡፡

የመንግስት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት የሚደረገው ጠቅላላ የክፍፍል ባጀት ድጎማ በየግዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በ2002 እኢአ 20.9 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (32.4) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ2004 እኢአ  31.4 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (26.7)በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2006 እኢአ  43.09 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (27.8) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2007 እኢአ  51.50 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (28.8) በመቶኛ እድገት አሳይቶል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2009 ዓ/ም ዓመታዊ በጀት

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2009ዓ/ም ዓመታዊ በጀት 321.8 ቢሊዩን ብር ሲሆን ይህም በዩኤስ 14  ቢሊዩን ዶላር ይተመናል፡፡ ከመደበኛና ከካፒታል ወጪ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያገኙት እነማን እንደሆኑ አልተገለፀም፡፡ በአጠቃላይ ለመሠረተ ልማት፣ለኢትዩጵያ መንገዶች ባለሥልጣን፣ ለትምህርት ዘርፍ፣ ለውሃ፣ ለጤና፣ ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን፣የውጭ ዕዳ ክፍያ ወጪ፣መከላከያ ሚኒስቴር፣ግብርና ሚኒስቴር ስንት ቢሊዩን ብር በጀት እንደተመደበላቸው አልተገለፀም ነበር፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2010 ዓ/ም የተያዘው ዓመታዊ በጀት 321.8 ቢሊዩን ብር መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ ገልጧል፡፡ ከዚህ በጀት ለመደበኛ 82 ቢሊዩን ብር፣ ለካፒታል 115 ቢሊዩን ብር፣ ለክልሎች 117 ቢሊዩን ብረና ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ  ሰባት ቢሊዩን ብር መደልደሉን አስታውቀዋል ነበር፡፡

በዚህ መሠረት ከአገር ውስጥ ገቢ ስንት ቢሊዩን ብር ለመሰብሰብ እንደታቀደ፤ እንዲሁም ከመሠረታዊ አገልግሎት፣ ከፕሮጀክት ዕርዳታ፣ከፕሮጀክት ብድር በድምሩ ስንት ቢሊዩን ብር  እንደሚሰበስብ አልተገለፀም ነበር፡፡

የ2009 ዓ/ም በጀት ለመሸፈን መንግስት ከጠቅላላ ዓመታዊ ባጀት ውስጥ የ53.9 ቢሊዩን ብር ጉድለትን ለመሸፈን ያቀደው ከአገር ውስጥ ብድር፣ማለትም ከባንኮች እንዲሁም ከውጭ ዕርዳታና ብድር እንደሚሸፈን ተገልጾል፡፡ የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2009ዓ/ም ዓመታዊ በጀት 9.6 በመቶ የ2008ዓ/ም ዓመታዊ በጀት ብልጫ እንዳለው ተገልፆል ነበር፡፡

የ2010 ዓ/ም በጀት

 • ከኦሮሚና ከሶማሌ ክልሎች ለተፈናቀሉ አንድ ሚሊዮን ወገኖች 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት በህዝብ ተወካች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡ የወያኔ መንግስት መንንም ተጠያቂ አላደረገም፡፡
 • በህዝብ አመጽ እየወደሙ ያሉት ንብረቶች በብዙ ቢሊዮን ብር ይገመታል፡፡በአገሪቱ በተፈጠረው የፖለቲካና የፀጥታ ችግር የተነሳ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዝቀዛቸውና መሽመድመዳቸው ሰተዋላል፡፡ ከግንባታ በፊት ውይይት ይቅደም፡፡ የሰው ነፍስ ማጥፋት ህዝባዊ አመፅና የግንባታ ውድመት ያስከትላል፡፡

 

የ2009 እኢአ ለክልሎች ድጎማ

የ2009 እኢአ ለክልሎች ድጎማ የፀደቀው ባጀት 117 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ለክልሎች የተመደበው ባጀት ክፍፍል ለህዝብ በይፋ አልተገለፀም፡፡ የ2009ዓ/ም በጀት በ40 ቢሊዩን 192 ሚሊዩን ብር ማለትም 66 በመቶ እድገት ከአለፈው ዓመት በጀት ብልጫ እንዳለው ማስተዋል የቻላል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያፀደቀው ቀመር የበጀት ክፍፍል ምደባ አድሎዊነት በተለያዩ ክልሎች ተቃውሞ ከገጠመው አመታት ቢቆጠርም ህወኃት መንግስት ተሰሚነት አላገኘም፡፡

ህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት ለመከላከያ ዘርፍ የሚመድበውን በጀት ወጪ፣ በክልሎች ድጎማ ስም በመመደብ በመላ ሃገሪቱ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ኮማንድ ፖስት፣በተለይ በአማራና በኦሮሚያና በሁሉም ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለማፈን ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ የመኪና ነዳጅ፣ ለስራ ማስኪጃ፣ ለስብሰባ፣ለኮንፍረንስ፣ለመጎጎዣ፣ለአዲስ እስር ቤቶች መገንያና ለፖሊስ ጣቢያዎች መስሪያ ወዘተ የተለያዩ  ወጭዎች፣ በብዙ ቢሊዩን ብር ከክልሎች ድጎማ በጀት ለመከላከያ ወጪ እንደሚሆን ባለሙያዎች በመረጃ ይተነትናሉ፡፡

ለክልሎች የሚደረግ የበጀት እርዳታ/ድጎማ

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የበጀት ድጎማ ሚያደርግበት ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት የክልሎች መንግስታት ያላቸውን የተፈጥሮ፤ የሰው ሃይልና ካፒታል ሃብቶችን በአግባቡ ማደራጀት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ አስተዳደራዊ ወጫቸውን መሸፈን ባለመቻላቻ ምክንያት ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ መንግስት በሁሉም ክልሎች እኩል የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ማምጣት ሃላፊነት ስላለበት ነው፡፡ መንግስት በሁለተኛው ምክንያት የተነሳ እኩል ያልሆነ የሃብት ክፍፍል ፖሊሲ በመንደፍ በክልሎች መኃል እኩልነት መፍጠር ይሻል፡፡

 

የመንግስት ለክልሎች የሚያደርገው የእርዳታና ድጎማ ስርዓት ለክልሎች እድገት ጠቃሚ መሣሪያ በመሆን የኢኮኖሚና የማህበረሰብ እድገት ለማፋጠን ታላቅ ጠቄሜታ ሳያስገኝ ቀርቶል፡፡ በዚህም ምክንያት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታትና አስተዳደር የሚደረገው ጠቅላላ የካፒታል ባጀት ክፍፍል ድጎማ በየግዜው እየጨመረ ቢሄድም በክልሎች መኃል የተፈጠረው ያልተስተካከለ ዕድገት በተለይም በትምህርት፣ በጤና፣ በመብራት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በመሠረተ-ልማት ማለትም በመንገድ ሥራ፣ በባቡር መስመር፣ በኤርፖርት፣ በግድቡ፣ በኢንዱስትሪያል ዞኖች ግንባታ አይን ያወጣ አድሎ እንደአለ ገሃድ ሆኖል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የበጀት ድጎማ መሠረታዊ ደንብና መመሪያ ሲኖረው የኢኮኖሚውን እድገት ቱሩፋት በፍታዊነት ለማከፋፈል ዋናው መሥፈርቶች መኃል፤የክልሎች የህዝብ ብዛት፣የእድገታቸው ደረጃ፣የገቢ ምንጫቸው ከካፒታል ባጀት ጋር ያለው የንፅፅር ድርሻ፣በማስላት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን አጥኝዎች ይገልፃል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት አጠቃላይ ባጀት (Regional Government Budget)፤ የፌዴራል ገንዘብ ክፍፍል ለክልሎች ባጀት በመቶኛ (Federal money as % of total) እና የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ ድርሻ ( Percapita share of Federal Money) ከአዲስ አበባ በስተቀር ሁሉም ክልሎች የፌዴራል ገንዘብ ተደጎሚዎች እንደሆኑ ማስተዋል ይቻላል፡፡ለክልሎች የበጀት ድጎማ መሠረታዊ ደንብና መመሪያ ቢኖረውም በፍትሃዊና እኩልነት ላይ የተመሠረተ ቢመስልም፤በሌላ ገፅታው ሲታይ በሌሎች ተለዋዋጭ ምክንያቶች የክልሎች የፌዴራል ገንዘብ ክፍፍል ኢፍትሃዊነትና አድሎን ያሳያሉ፡፡

አንደኛ በለጋሺ ሃገራት ተጨማሪ የባጀት ድልድል በሚያገኙ ክልሎች ክፍፍሉን የተዛባ ያረገዋል፣ዝቅተኛውን የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ ድጋፍ ያገኘ ክልል ሌላ የገንዘብ ምንጭ ስለሚያገኝ የመንግስት ድጎማን ኢፍታዊና አድሎዊ ያደርገዋል፡፡

ሁለተኛ የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ፣ወይም አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የገንዘብ እርዳታ ድምር ሂሳብ በማየት ፍትሃዊነትና እኩልነት መኖሩን ማረጋገጥ አይቻልም፡፡ ውስጣዊ ክፍፍልና ዳግማዊ ክፍፍል ጥቅምና የጥቅሙን የማግኛ መድረሻና መግቢያ ዘዴ መንገድ ማወቅ  ትልቅ ተፅዕኖ  ያደርጋሉ፤በክልሉ ህዝብ በእኩልነት የኢኮኖሚ እድገቱን ቱሩፋት ለመቆደስ አይቻልም፡፡ በኢትዩጵያ ኃላቀር ክልሎች በተለይ የጋምቤላ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በጣም ኃላ ቀር የኢኮኖሚ እድገት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም የተነሳ ባለፉት 26 ዓመታት አንባገነናዊ አገዛዝ፣ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል በፌዴራል ሥርዓቱ እንደሌለ ህዝቡ ተገንዝቦል፡፡

 

{3}የባህር ማዶ ልማት ትብብር (ODA፡ Official Development Assistance) ከ1991 እኤአ እስከ 2012 እኤአ ለህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት አርባ ቢሊዩን ዶላር የልማት እርዳታ ሰጥተዋል፡፡ በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በአማካኝ በአመት ሁለት ቢሊዩን ዶላር እርዳታ ሃገሪቱ እንዳገኘች ያስረዳል፡፡ በይፋ የተለያዩ ለጋሽ ሃገራት የሰጡትን ገንዘብ ብዛትን ለማስላት ያህል በትንሹ ስምንት ታላቁን የህዳሴ ግድብ ኤሌትሪክ ማመንጫን የሚችል ሜጋ ፕሮጀክቶችን በእርዳታ ገንዘቡ መስራት የሚያስችል ነበር፡፡ አልያም የቻይና መንግስት በ200 ሚሊዩን ዶለር ያሰራውን የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ህንፃን ዓይነት ሁለት መቶ ህንፃዎች ሊገነባ የሚችል ገንዘብ ነበር፡፡ የባህር ማዶ ልማት ትብብር እርዳታ ከ2008 እስከ 2015እኤአ ያለውን ብቻ ብናይ ከ3 እስከ4 ቢሊዩን ዶላር ሃገራችን የልማት እርዳታ አግጥታለች፡፡ በኦዲኤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ አድራጊ መንግስቶችና ተቆማት አሜሪካ መንግሥት፣ የእንግሊዝ መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት ኢንስቲቲዉሽኖች፣ ኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስና ግሎባል ፈንድ ናቸው፡፡  የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›እንዲያነሳ ጫና እንዲደረግበት የዲያስፖራው የትግል እንቅስቃሴ በነዚህ አገሮችና ድርጅቶች ላይ ማነጣጠር ይኖርበታል፡፡ ወያኔ የተነቃነቀ በትረ ሥልጣኑን ዴሞክራሲን በማፈን፣ ስብዓዊ መብቶችን በማፈን፣ ህገ-መንግስቱን በመጣስ የኢትዮጵያ ህዝብን አፍኖ በመግዛት ላይ መሆኑን በሠላማዊ ሠልፍ መግለፅ አስፈላጊ ነው፡፡

የህወሓት መንግሥትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›የሃገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ የዴሞክራሲ ስርዓት የሃዲድ መሥመር የጣሰና ወደ አንባገነን ስርዓት የጨለማ ሃዲድ የዘረጋ በመሆኑ የባህር ማዶ ልማት ትብብር  አጋር አገራቶች  ድጋፍ ለኢትዮጵያ ይቀንሳል ብሎም ይቆማል፡፡

የዲጅታል ቴክኖሎጅ ወጣት ትውልድ የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት፣ በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመመስረት የብዙሃን ፓርቲዎች የውድድር ሥርዓት ዘርግቶ፣ በህዝብ ድምፅ አሸናፊው ሥልጣን የሚይዝበት የምርጫ ስርዓተ-አሥተዳደር መገንባት አለበት፡፡ በኢትዩጵያ የወያኔ ልማታዊ መንግሥት› ስም የወያኔ መንግሥታዊው ዘርፍ(ኢፈርት ሜቴክ፣ ኢዛና፣ ጥረት፣ ዲንሾ፣ ወንዶ ወዘተ) የግሉን ዘርፍ ኃብትና ሊሠራ የሚችለውን ኢንቨስትመንት ሥራ ሁሉ በመሻማት የግሉን ዘርፍ እድገትና ሚና በመላ ሃገሪቱ አጨናግፎታል፡፡ የወያኔ ኢፈርት ኢንተርፕራይዞች፡- በወያኔ ባለሥልጣኖች የሚተዳደሩ የሜቴክ ድርጅቶች የሙስና መፈልፈያዎች፣ የእውቀትና የብቃት ችግር የተንሠራፋባቸው፣ በሥልጣን በመጠቀም የግል ፍላጎት ተጠቃሚነትን የሚያስፋፉ፣እንዲሁም ከለላን የሚያበረታቱ፣ የፖለቲካና የዝምድና አሰራር የነገሰበቸው ናቸውና ለቀጣዮ ትውልድ የሥራ ዕድል ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡  በሃገሪቱ 30 ሚሊዮን ወጣቶች ሥራ አጥ ናቸው፡፡ ወጣቶች በሃገራቸው ሠርተው መኖር መብት አላቸው፡፡ አድሎዊና ተመጣጣኝ ያልሆን የክልሎች እድገት ይወገድ!! በክልላችን የሚካሄድ የመሬት ቅርምት ይቁም!! በክልላችን ኃብት የዘረፉ ለፍርድ ይቅረቡ! ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም! ወጣቶች የሚሉት ለዚህ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የኢህአዴግ መንግሥት ያወጣውን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ተቃወመ የህዝቡን የመሰብሰብና ሃሳብ መግለጽን መከልከልን፣ የዴሞክራሲዊ መብቶችን የመጸፍ፣ መናገር፣ መደራጀት፣ የሠላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማካሄድና መሰረታዊ መብቶች ክልከላ መፍትሄ አይሆንም በማለት ምክረ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት በሃገሪቱ ዴሞክራሲን ማስፈን፣ የምጣኔ ሃብት እድገት ማስመዝገብ፣ ለህዝቡ ብልፅግና ሰላምና መረጋጋት ያመጣል እንጂ የስድስት ወር ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ማወጅ መፍትሄ አይሆንም በማለት ኮንነዋል፡፡ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አገራቶች የኢህአዴግ መንግሥት ያወጣውን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› ተቃውመዋል፡፡

 

{4} ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት (Foreign Direct Investment Inflows) ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ለሃገሪቱን የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያስከትለው ጉዳት በተመለከተ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ይቀንሳል፡፡ ሰላም በሌለበት ሃገር የባህር ማዶ ኢንቨስተሮችን አይስብም፣ እንዲያውም ያፈሰሱትን ምዋለንዋይ ሸጠው ለመውጣት  ይገደዳሉ፡፡ በሃገራችን የኢኮኖሚ ነፃነት ከሚገለፅባቸው ዋና ዋና መርሆዎች ውስጥ አንዱንም አታሞላ፡፡ አንደኛው የህግ የበላይነት፣የፍትህ ሥርዓት መከበር፣የንብረት ባለቤትነት መብት መከበር፣ የመንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ያለው አቅም የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች የህግ ሉዓላዊነት ያለበት ሃገር መዋለ-ንዋያቸውን አፍሰው በነፃነት ኃብት ማፍራት ይሻሉ፡፡ ህግና ፍትህ ባለበት ሃገር ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት ከአመት አመት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያ ህግ የለም፣ ፍትህና ርትህ አይሠራም፣ የዜጎች ንብረት የማፍራት መብት የለም፡፡ በኢትዩጵያ የህወሓት መንግሥት በሞኖፖል የተያዙ ንብረቶችና ኃብቶች መካከል፡-በሃገሪቱ የመሬት ኃብት የህወሓት መንግሥት በመሆኑ የግብርና፣የማኑፋክቸሪንግና አገልግሎት ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ እድገቱ የቀጨጨ ለመሆን በቅቶል፡፡ ህዝባችን የመሬት ኃብት ንብረት የመያዝ መብትና ነፃነት ስለሌለው በርሃብ አለንጋ ይሰቃያል፡፡ ህዝቡን መመገብ የማይችል መንግሥት ህዝቡን መግዛት አይችልም፡፡ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2008እኤአ (109 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2009እኤአ (211 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2010እኤአ (288 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2011እኤአ (627 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2012እኤአ (279 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2013እኤአ (1281 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2014እኤአ (2132 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2015እኤአ (2168 ቢሊዮን ዶላር)፣2016እኤአ (አልተገለጸም)፣ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ነበር፡፡‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት በጣም ይቀንሳል፡፡››

 

{5} ከሆቴልና ቱሪዝም የሚገኝ ገቢ ይነጥፋል፣  ባህር ማዶ ጎብኝዎችንና በኢትዮጵያ ቁጥር ይቀንሳል በዚህም ምክንያት ከቱሪስቶች የሚገኝ ገቢ ያሽቆለቁላል፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ይቀንሳል፣

በ2008 እኤአ ኢትዩጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 383 ሽህ  ሲሆን ከዘርፍ 355400 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) 10.4 በመቶ እንዲሁም ለሥራ ዕድል 6.3 በመቶ አበርክቶ ነበር፡፡ በ2014 እኤአ 770 ሽህ ጎብኝዎች ወደ ሃገራችን መጥተው ነበር፣ በ2015እኤአ 717 ሽህ ቱሪስቶች መጡ (በ60 ሽህ ቀነሰ) በ2016እኤአ 491 ሽህ ሃገር ጎብኝዋች መጥተው ነበር(279 ሽህ ጎብኝዎች ቁጥር ቀነሰ)፡፡ ከ2008 እስከ 2009ዓ/ም  ወያኔ  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› አውጆ የነበረበት ዓማታት መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

በ2014 እኤአ ኢትዩጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 770 ሽህ  ሲሆን ከዘርፍ 730436 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) 9.6 በመቶ እንዲሁም ለሥራ ዕድል 5.8 በመቶ አበርክቶ ነበር፡፡ በ2015አና 2016እኤአ የቱሪስቶች ቁጥር መቀነሱን፣የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) መቶኛ እንዲሁም ለሥራ ዕድል መቶኛ ቀንሶል ይታያል፡፡ የተገኘው ገቢ መጨመሩን ግን ያሳያል ከሠንጠረዡ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከ2008ዓ/ም እስከ 2010ዓ/ም በተቀሰቀሰው የኦሮሚያ ህዝብ የአንገዛም እንቢተኝነት ትግልና የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ምክንያት ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክንት የቱሪዝም ዘርፍ በቱሪስቶች ቁጥር መቀነስና  የዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) መቶኛ እንዲሁም ለሥራ ዕድል መቶኛ ቀንሶል ይታይ ነበር፡፡ ከዚህ መረጃ በመነሳት የካቲት 9 ቀን 2010 የታወጀው ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ያሽመደምደዋል፣ የሆቴሎች ገቢ ይቀንሳል፣ የቱሪስት አስጎብኝ ድርጅቶች ገቢ ይቀንሳል፣ የውጪ ምንዛሪ ገቢ ይወድቃል፡፡

በ2008፣በ2009ና 2010ዓ/ም በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና በአማራ ህዝባዊ ተጋድሎ የግብርና የታክስ ገቢ ቀንሶል፣ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክንት ለመከላከያ  ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ኃይል፣ ሚሊሽያ ወዘተ ከመደበኛ በጀት ሌላ ከፍተኛ ወጭ ያስከትላል፡፡ በ2010እኤአ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አስከትሎል፡፡ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ ያልቻለ መንግሥት በህዝብ የተጠላ መንግሥት ነው፡፡ የስልጣን እድሜውም አጭር ነው፡፡ ህወሓት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ህዝብ ግብር በመሰብሰብ የንግዱን ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል ህዝቡን በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡  ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ዳግም በማወጅ በጉልበት ግብር ሊሰበስብ ይፈልጋል፣ የህዝብ ልጆች እየገደለ መግዛት ይፈልጋል፣ በሙስናና በኮንትሮባንድ ንግድ የከበሩ አይነኬ የጦር መኮንኖች በመላ ሃገሪቱ ህገወጥ የድንበር ዘለል ንግድ በመዘርጋት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ አውድመዋል፡፡ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የህዝቡን በነጻነት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት ኢኮኖሚ ነፃነት ያሳጣዋል፡፡ የወያኔ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ንግድን በወያኔ መንግሥት ሠራዊት እየተጠበቁ እንዲነግዱ ሲያመቻች የግል ዘርፉን ንግድ እንቅስቃሴ እንዲታሸግ፣ የግብር ጫናና አድሎ በኮማንድ ፖስቱ ይፈፀምባቸዋል፡፡ በዚህም የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ፣ የንግድ መዛባትን በመፍጠር፣ ውድድርን በማክሰም፣ በመንግሥት እጅና ጥበቃ ከውድድር ውጭ ሆነው የሚተዳደሩ ድርጅቶች ይፈጠራሉ፡፡

ከ2008 እስከ 2009/2010ዓ/ም በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሁልም ክልሎች በተነሳ ህዝባዊ አመፅ የሃገር ውስጥ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ንብረት የሆኑ ፋብሪካዎችና እርሻዎች መውደም ምክንያት የታቀደው አልተሞላም፡፡‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የውጭ ንግድ ገቢ አሽቆለቆለ፣ በአንጻሩ የገቢ ንግድ ወጪ በማደጉ የንግድ ሚዛኑ ተናግቶል፡፡ በዚህም የተነሳ ያልተረጋጋ የብር ምንዛሪ ተመንና የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት፣ የመንግሥትና የልማት ድርጅቶች በዕዳ ክፍያ ጫና ተከስቶል፡፡ በአጠቃላይ  የአገሪቱ የፋይናንስና የባንክ ኢንዱስትሪው ልማቱ የሚጠይቀውን ፋይናንስ የማቅረብ ብቃት ወድቆ ነበር፡፡ በሃገሪቱ የፋይናሻል ዘርፍ ውድቀትና ኪሣራ ደርሶባቸዋል፡፡ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበቱንና የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፣ የውጪ ንግድ ገቢ በድርቅ ተመቶል፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በጣም ተባብሶል፣ በእጥረቱ ምክንያት የኮንስትራክሽን ስራዎች በአብዛኛው ተቆርጠዋል፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች ቆመዋል፣ በሃገሪቱ በታወጀው ‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ› የተነሳ በባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ሽሽት የተነሳ፣ ይደረግ የነበረው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት አሽቆልቁሎል፣ የሆቴልና ቱሪዝም ገቢም ይነጥፋል፡፡ ከዚህ ባለመማር ወያኔ ዳግም ‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ› አውጆል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በርሃብ፣በድህነት፣በበሽታ፣በስደትና በጦርነት አዙሪት ቀለበት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በሃገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት አለመኖር፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አለማበብ፣ የመልካም መሪዎችና መልካም አስተዳደር እጦት፣ የስራ አጦች ብዛት፣ ገበያ መር የኃብት አጠቃቀም አለመኖር፣ የረዥም ግዜ  ኢንቨስትመንት እቅድ አለመኖር፣ የተትረፈረፈ ምርቶች ለውጭ ንግድ አለማምረት፣ የውጭ ምንዛሪ እጦት እንዲሁም የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚክ ስርዓት ዘላቂ ያልሆነ፣ ፊሲካልና ከዓለም አቀፍ ንግድ የውጭና የገቢ ንግድ የተዛባ ሚዛን፣  የንግድ ኪሳራ መሆን በችግር ቀለበት ውስጥ እንድትሽከረከር ያደርጋታል፡፡ይህን ችግራችንን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› እና ኮማንድ ፖስቱ አይፈቱትም፣ ከመካላከያ ሠራዊት መደበኛ የደሞዝ፣ የቀን አበል፣የትራንስፖርትና የነዳጅ ወጪ በጀት መጨመር ሌላ ለሃገሪቱ ኃብት አይጨምርም፡፡  ከመካላከያ ሠራዊት በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ዘርፍ አምራች ሳይሆን እንደ ጥገኛ ተሃዋሲያን ሆኖ አምራች ኃይሉን የሚጣባ ወታደራዊ ዘርፍ ነው፡፡ ከግብርናው ዘርፍ አምራቹ ገበሬና ከማኑፋክቸር ዘርፍ ከላብአደር አምራች ከሚሠበሰብ ገቢ መንግሥት የግብርና የታክስ ቀረጥ ሰብስቦ ደሞዝ የሚከፈላቸው ናቸው፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ወደ ሌላ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››  መሸጋገር ኢትዩጵያ ከደካማ መንግስትነት (weak states)፣ ወደ ሚሰበርና የሚፈረካከስ ሃገር (fragile states)፣ብሎም ወደ ወደቀች መንግስት  (failed states) ጎራ የመቀላቀላችን ግዜ  በእርስ በእርስ ጦርነት እየተፋጠነ መምጣቱ  አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ የወያኔ የጥላቻ ፖለቲካ የሚከሰተው የዘር ፍጅት (የጀኖሳይድ) አዙሪት ቀለበት ውስጥ  ለመውጣት፣ ከዚህ ከማያባራ የህዝብ አመፅ፣ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለአንዴና ለዘለቄታው ለመውጣት፣ ብሄራዊ እርቅና የሰላም ጥሪ ውይይትና የዴሞክራሲ ስርዓት ሀ፣ሁ ለመገንባት የሽግግር መንግሥት መመሥረት ግዜው አሁን ነው፡፡ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››  እንዲነሳ ህዝባዊው አመፅ በኢትዮጵያ ምድር ተቀጣጥሎ ወያኔ ይወገዳል፣ እንደ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ ህዝባዊ ትግል፣ ጭቁን መከላከያ ሠራዊት ከህዝብ ጋር ወግኖ ታሪክ እንደሠራ የእኛም ሠራዊት አፈሙዙን ወደ ገዥዎቹ አዙሮ ህዝባዊውን ትግል ይቀላቀላል፡፡

 

ዳክተር ፍቅሩ ማሩ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ መቶ አለቃ ማሽረሳ ሰጤ ይፈቱ!!!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በህዝብ ትግል ይነሳል!!!

ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም!!!

ኮማንድ ፖስቱ የሚወጣው የመከላከያ ሠራዊት በጀት ህዝባዊ አይደለም!!!

ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት፣ መጨረሻው ጥፋት ነው!!!

የታሠሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

የወያኔ ባለሥልጣኖች፣ አንባሳደሮችና ጀነራል መኮንኖች ኩብለላ ይቀጥላል!!!

የወያኔ ሹማምንቶችና የጦር መኮንኖች ወደ ወደ ሃገረ ቻይና ይኮበልላሉ!!!

የዋልድባ መነኮሳት ምስክር ሊሰማባቸው ነው (በጌታቸው ሺፈራው)

 

በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ክስ መዝገብ የ”ሽብር” ክስ የተመሰረተባቸው የዋልድባ መነኮሳት ለመጋቢት 18/2010 ዓም ምስክር ይሰማባቸዋል ተብሏል።

በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ክስ መዝገብ ተከሰው ከነበሩት 35 ተከሳሾች መካከል 32ቱ ክሳቸው ተቋርጦ የተፈቱ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ነጋ ዘላለም መንግስቴ፣ 4ኛ ተከሳሽ አባ ገ/ እየሱስ ኪ/ማርያም እና 5ኛ ተከሳሽ አባ ገ/ስላሴ ወ/ሐይማኖት ብቻ ክሳቸው ቀጥሏል።

የዛሬው የካቲት 19/2010 ዓም ቀጠሮ ተይዞ የነበረው በመዝገቡ ከተጠቆጠሩት ምስክሮች መካከል ጉዳያቸው ይቀጥላል በተባሉት 3ቱ ተከሳሾች ላይ የሚቀርቡትን አቃቤ ህግ ለይቶ እንዲያስመዘግብ እና መነኮሳቱ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ነበር። በዚህም መሰረት 1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ምስክሮች በመነኮሳቱ እና በ2ኛ ተከሳሽ አቶ ነጋ ዘላለም ላይ ይመሰክራሉ ተብሏል። የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማትም ለመጋቢት 18 ቀጠሮ ተይዟል።

በሌላ በኩል የቂሊንጦ እስር ቤት መነኮሳቱ የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ እንያገደዳቸው መሆኑን ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን እስር ቤቱ ለካቲት 30 መልስ እንዲሰጥ ታዟል።

4ኛ ተከሳሽ አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም እና 5ኛ ተከሳሽ አባ ገ/ስላሴ ወ/ሐይማኖት ልብሳቸውን አናወልቅም በማለታቸው ባለፉት ቀጠሮዎች ያልቀረቡ ሲሆን በአቤቱታቸው ላይ ቅጣት ቤት እንደሚገኙ መግለፃቸው ይታወሳል። የሁለቱም መነኮሳት አካል ላይ ባለፉት ጊዜያት ያልነበረ ጉስቁልና ይስተዋላል።

“ሰኞ የወጣ ስም ማክሰኞ አይመለስም” – (አብመድ)

ባህር ዳር፡የካቲት 19/2010 ዓ/ም

የዛሬ ቅኝቴ የአማራ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ባህርዳር ከተማ የሚገኘው ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ነው::

ሆስፒታሉን የሚያውቀውም የማያውቀውም የትኛውም ሰው ቢሆን በጥሩ የሚያወሳው የለም:: ማለትም “ሆስፒታል ዘመድ ከሌለህ ዋጋ የለህም:: በሰው፣ በዘመድ አዝማድ ነው የሚሰሩት፤ ጥሩ ህክምናና ክትትልም የምታገኙት እዚያው የሚሰራ ሰው ሲኖራችሁ ነው” ነበር የሚባለው::

አስታውሳለሁ እኔ የመጀመሪያ ልጄን ለመውለድ ቀናት ሲቀሩኝ በእጅጉ ያሳስበኝ የነበረው ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ ሰው ለማወቅ ነበር፤ ነገር ግን ሊሳካልኝ አልቻለም:: ከዚህም ባሻገር የህክምና ባለሙያዎቹ፣ “ታካሚዎችንና አስታማሚውን የሚያመናጭቁበት ስነ ምግባር የጐደላቸው፣ የሆስፒታሉ የጽዳት ሁኔታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባበት፣…” እየተባሉ ለብዙ ዓመታት ሲብጠለጠሉም እሰማ ነበር:: ነገር ግን “ማየት ማመን ነው” እንደሚባለው ሰሞኑን ዘመድ ታሞብኝ በሆስፒታሉ ተገልጋይ ሆኘ ስገኝ ነገሮች ሁሉ ተለዋውጠው ጠበቁኝ::

ሆስፒታሉን ገና ከበር ስገባ ስመለከት በወቀሳ ስናብጠለጥለው የነበረውን የህክምና ተቋም ዛሬ ላይ ተሻሽሎ በማየቴ ያለኝን አድናቆትና ምስጋና ለመግለጽ ወደድኩ:: ምክንያቱም ይህ ተቋም ሲያጠፋ እንደተወቀሰው ሁሉ ተሻሽሎና ተለውጦ ሲታይ ለሰራው ሥራ ዕውቅናና አድናቆት መስጠት ግድ ይለናል::

በመጀመሪያ እና በዋናነት መግለጽ የምፈልገው ሆስፒታሉ ከግቢው አንስቶ ውስጥ ካሉ የህክምና አልጋዎች፣ የህክምና ክፍሎች፣ የመፀዳጃ ቤቶች፣… ሁሉም ፅድት ብለዋል:: በፊት አፍንጫችንን ይዘን ለህክምና ሄደን በሽታ ይዘን እንወጣ ነበር::

ፅዳቱን ከጠበቀው የሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ታካሚውን ለመርዳት ወዲያ ወዲህ ተፍ ተፍ ወደሚሉት የህክምና ባለሙያዎች ልውሰዳችሁ::

እኔ የቆየሁበት ድንገተኛ ክፍልና ማገገሚያ የታካሚውን ብዛት ልነግራችሁ አልችልም:: ሁሉም ታካሚ እዚህ ነው ያለ ለማለት ያስገድዳል::

በዚህ ላይ ግን በጣም ሊመሰገኑና ሊደነቁ የሚገባቸውና ትክክለኛ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ የጤና ባለሞያዎች አሉንና እነዚህን ብርቅዬ ልጆች ከወገቤ ጐንበስ በማለት ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ::

አስተውላችሁ ከሆነ ከዚህ በፊት በህክመና ሙያ ላይ በስፔሻሊስት፣ በዶክተር ደረጃ የነበሩት የሴቶች ቁጥር አናሳ ነበር:: ነገር ግን አሁን ላይ ያየኋቸው ድንገተኛ ክፍል የሚሰሩ የሴት ዶክተሮች ቁጥር መጨመር፣ የሥራ ብቃታቸውና ስነምግባራቸው ታካሚንና አስታማሚን ለመንከባከብ ያላቸውን ፈገግታ የምገልጽበት ቃላት ያጥሩኛል:: እዚህ ላይ ጥሩ ሰብዕና ያላቸውን ወንድ ዶክተሮችንና ነርሶችንም ሳንዘነጋ::

ብዙዎቻችን አንድ ሰው ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥመው መሄድ የምንፈልገው ወደ ግል የህክምና ተቋም ነው:: ነገር ግን በድሮ በሬ አይታረስም እና የሆስፒታሉን የቆየ መጥፎ ስሙን አሁን ድረስ ሰው እየተጠቀመበት ይገኛል::

እኔ ያየሁትን ልንገራችሁ፤ አንድ ሰው ድንገተኛ አደጋ ይደርስበት እና ጓደኞቹ “የግል ይሻላል፤ ከግል እንውሰደው” በማለት ወደ ግል ህክምና ተቋም ወሰዱት:: “ይተኛ” ተብሎ አንድ ቀን ውሎ አድሮ ከፍተኛ ገንዘብ ከከፈሉ በኋላ ብዙም እርዳታ ሳይደረግለት፣ “የለም ወደ ሆስፒታል ውሰዱት” ተባሉ። ቤተሰቦቹም መሄዱ ቁርጥ መሆኑን ሲያውቁ ፊታቸው በሀዘን ተዋጠ::

ነገር ግን ከቦታው ሲደርሱና የተደረገለትን ርብርብ ሲያዩ በጣም ተደነቁ:: እኔም የእነሱን ሁኔታ ስመለከት፣ “ሰኞ የወጣ ስም ማክሰኞ አይመለስም” የሚለውን አባባል አስታወስኩ::

ስለሆስፒታሉ ይህን ያህል አድናቆት ካቀረብኩ በኋላ መቼም የሚሰራ ሰው ይሳሳታልና እኔም በዚህ ተቋም ያየኋቸውን አንዳንድ ህፀፆች ልጠቁም::

በፍጥነት መስተካከል አለበት የምለው ዋናውና ትልቁ ጉዳይ እርስ በርስ ያለመናበብ ችግር ነው:: ያየሁትን ልንገራችሁ:: አንድ ባለሙያ መጥቶ ጉልኮስ ይተክላል፣ ሌላኛው ሲመጣ ደግሞ የለም ይነቀል ይላል:: በዚህ ጊዜ የነቃ አስታማሚ የሌለው ታካሚ ባለሙያዎቹ በተፈራረቁ ቁጥር ችግር ሊደርስበት እንደሚችል ታዝቤያለሁ::

ከዚህ በፊት በታካሚ አልጋዎች ላይ የህክምና ባለሙያው የታካሚውን ታሪክ፣ የመድኃኒት አሰጣጥ አስተያየት የሚሰፍርበት በክላሴር ከአልጋው ጫፍ ላይ ይንጠለጠል ነበር:: ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት አልጋዎች ላይ ተንጠልጥሎ ቢታይም ምንም ዓይነት ጽሁፍ ግን አይሰፍርበትም:: በአብዛኛው ደግሞ ምንም ያልተንጠለጠለባቸው አልጋዎች ነው የነበሩት::

ይህ አለመኖሩ ደግሞ ባለሙያዎቹ እንዳይናበቡ አድርጓቸዋል:: በህክምና እየተናበቡ የማይሰሩ ከሆነ ትንሿ ስህተት ለከፋ ችግር ትዳርጋለችና ለዚህ ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው:: የህክምና ስህተትንም ሊያመጣ እንደሚችል አስባለሁ። በእኔ አስተሳሰብ ይህ የህክምና ታሪክ ማስፈሪያ ታካሚው በዕለቱ ምን ዓይነት መድኃኒት እንደተሰጠው በየትኛው ሰዓት … የሚለውን የሚይዝ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

በየቀኑ ዶክተሮች ተሰባስበው ታካሚዎችን ይጐበኛሉ:: አንድ ቀን እኔ ከማስታምምበት ክፍል የነበረ ታካሚን የጐበኙት ዶክተሮች መድኃኒት አዘዙለትና አስታማሚዎቹ በፍጥነት ገዝተው አመጡ:: እነሱ እንደወጡ በግምት 30 ደቂቃ እንኳን ባልሞላ ጊዜ በመደበኛነት የምትከታተለው ሐኪም መጣችና፣ “ዛሬ ትወጣለህ” አለችው:: በዚህ ጊዜ እኔ በጣም ደነገጥኩ፤ ከ30 ደቂቃ በፊት የብዙ ብር መድኃኒት ገዝቶ እንደሚውል እንደሚያድር ከተነገረው በኋላ እንደገና ዛሬ ትወጣለህ ሲባል አስታማሚዎችም እኔም ግራ ተጋባን:: አስታማሚዎችም አዲስ የገዙትን መድኃኒት እና ሌሎች ያልተጠቀሙባቸውን መድኃኒቶች በሙሉ ሰብስበው ወጡ:: አንባቢያን እናንተ ብትሆኑ የየትኛውን ትዕዛዝ ነው የምትፈጽሙት?

በዚህ ጊዜ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለብኝና ይህን ሁሉ መድኃኒት ምን ታደርጉታላችሁ? ብዬ ስጠይቃቸው፣ “ታዲያ ገንዘባችን ወጥቶበት ትተነውማ አንሄድም!” አሉኝ::

ከሁለት ወር በፊት አደጋ ደርሶበት ህክምና አድርጐ ህመሙ ስላገረሸበት ቀዶ ህክምና ተሰርቶለት በወጣው ታካሚ አልጋ የተተካው አስታማሚ ደግሞ ጉሉኮስ፣ ማስታገሻ እና ሌሎች የተለያዩ መድኃኒቶች ሲታዘዙለት፣ “አይ ወይኔ የባለፈው አንድ ካርቱን መድኃኒት እኮ እቤት ነው ያለው” በማለት ስትቆጭ ሰማኋት።

“ብዙ መድኃኒት ነው ያለው? እንዴት ሊተርፍ ቻለ?” አልኳት::

“ኧረዲያ! መድኃኒት በላይ በላይ ነው የሚያዙት፤ የሚጠቀምበትን ተጠቀመ የተረፈውን ደግሞ ወደ ቤቴ ይዠው ሄድኩና አስቀመጥኩት” አለችኝ::

“ግን ከዚህ እንዴት ማውጣት ቻልሽ? ጥበቃ ላይ አልጠየቁሽም?”

“ከእቃዎቼ ጋር አብሬ ስለያዝኩት አልጠየቁኝም” በማለት መለሰችልኝ::

አስቡት እስኪ ምን ያህል መድኃኒት ያለአግባብ ጥቅም ላይ እንደሚውልና ብክነት እንደሚፈጠር:: እነዚህን እንደምሳሌ ያቀረብኩላችሁ ሁለት ሰዎች መድኃኒቱን ወደ ቤታቸው ወስደው ያስቀምጡታል:: ምክንያቱም ከቤት ያለን መድኃኒት ማንም ስለማይገዛው:: በውድ የዶላር ምንዛሬ የሚገቡ መድኃኒቶች እንደዚህ በየሥርቻውና በየቤቱ ጥቅም ላይ ሳይውሉ ሲቀሩ በጣሙን አመመኝ::

እነዚያ መድኃኒቶች በአግባቡ ብንጠቀማቸው ኖሮ የስንቱን ህይወት በታደግንበት ነበር:: ከማስታምምበት ክፍል ወጣ ብዬ ሌሎች ታካሚዎችን ስቃኝ በአጋጣሚ አንድ የማውቃት ታካሚ አልጋ ላይ ሳያት ከአጠገቧ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩ እና መጫወት ጀመርን:: በዚህ ጊዜ ከእሷ ጐን የተኛው ታካሚ ህክምናውን ጨርሶ ሊወጣ ነበርና የተረፈውን መድኃኒት ለአንች ይጠቅም ይሆናል በማለት ብዙ መድኃኒቶች ሰጣት::

መድኃኒት ከግቢው ካልወጣ ለተገቢው ዓላማ መዋሉ አይቀርም እና ጥሩ መረዳዳት ነው በማለት ገለፅሁላቸው።

“እሱማ ጥሩ ነበር:: ነገር ግን መድኃኒት ሲተርፍሽ የህክምና ባለሙያዎቹ ካዩ እነሱ ይወስዱታል:: አሁንም ቢሆን ቶሎ ብዬ ስለተቀበልኩት ነው እንጂ መጥተው መጠየቃቸው አይቀርም:: ከዚህ በፊት እዚህ የነበረ ታካሚ ሲወጣ በሙሉ ሰጥቶኝ ስለነበር የህክምና ባለሙያው ሲጠይቀኝ ለእኔ ሰጥቶኛልና እኔ ነኝ የምጠቀምበት ብዬ አስቀረሁት::”

“ለመሆኑ እነሱ ወስደው ምንድን ነው የሚያደርጉት?” ጠየቅኋት።

ፈራ ተባ እያለች፣ “ታዲያ ጥቅም ካላገኙበት ለምን አምጭ አታምጭ ይታገሉኛል” በማለት መለሰችልኝ:: በዚህ ጊዜ የተወሰነ ደስታ ተሰማኝ:: ምክንያቱም ሌላው ቢቀር መድኃኒቱ ለተፈለገለት ዓላማ ውሏልና::

ይህን ሁሉ ስህተት እንዲሁ ማለፍ ስለማልፈልግ ችግሩን መጥቀስ ብቻ ሳይሆን መፍትሔውንም ማስቀመጥ እንዳለብኝ አምናለሁ። መድኃኒቶች እንዳይተርፉ በአግባቡ ማዘዝ፣ ካልሆነ ደግሞ መድኃኒቶች ሲተርፉ ወደ መድኃኒት ቤት እንዲመለሱና ለታካሚው ደግሞ ገንዘቡ የሚመለስበት የአሰራር ስልት ቢዘረጋ ታካሚውንም ሆነ በውድ ምንዛሬ የምናስገባቸውን መድኃኒቶቻችንንም መታደግ ይሆናልና ፈጣን የሆነ ምላሽ ቢሰጥ እላለሁ::

ሌላው በጣም ያስደነቀኝን ጉዳይ ላቅርብ:: ከዚህ በፊት የማህበረሠብ አቀፍ ጤና መድን ሲባል ምንም ጥቅም ያለው አይመስለኝም ነበር:: ነገር ግን ሁሉም ነገር ወደ ተግባር ሲመጣ ነውና ግልፅ የሚሆነው አንዱ አርሶ አደር ለቀዶ ጥገና የሚያገለግል ብዙ መድኃኒት ተሸክሞ ሲመጣ ሲያየው አንድ ተገልጋይ ለጓደኛው ጠጋ ብሎ፣ “ይህን ሁሉ መድኃኒት በነፃ እኮ ነው” አለው። በዚህ ጊዜ ጓደኛው ስላልገባው፣ “እንዴት?”

“እንዴት ማለት ጥሩ! እኔ ወደ አንድ ሺህ ብር የሚጠጋ ስከፍል እሱ ግን የጤና መድን አባል ስለሆነ በነፃ ተሸክሞት መጣ::”

እኔም ወሬያቸው ሳበኝና ተቀላቀልኳቸው:: በዚህ ጊዜ አንዱ አርሶ አደር “ለካ እንደዚህ ይጠቅማል? በአሁኑ ሰዓት እንደአንተ በመቶዎች የሚቆጠር ገንዘብ ቢጠየቅ ምን ይውጠው ነበር?” በማለት የራሱን ስሜት ገለፀ:: በዚህ ጊዜ አንደኛውን አርሶ አደር “አንተስ የጤና መድን ተጠቃሚ ነህ?” ብዬ ጠየቅሁት::

“አዎ! በእኛ አካባቢ እኮ አባል አለመሆን አትችይም፤ በአንድ ወቅት አንከፍልም ያሉት ግለሰቦች ታስረው ነበር:: ያኔ እኔ ለምን እንደዚህ ያደርጋሉ ብዬ እነሱን ወቅሻቸው ነበር:: እንደተመለስኩ ግን ይቅርታ ነው የምጠይቃቸው:: ምክንያቱም ሁሉም ነገር ለእኛ ጥቅም ነበርና::” ከዚያም ሲያዳምጠን የነበረው አንድ አስታማሚ “እኔም ይህን በማየቴ የጤና መድን አባል መሆንን ተመኘሁ” ብሎ የተሰማውን ገለፀልን::

አንዱን የጤና መድን ተጠቃሚ መስተንግዶው እንዴት እንደሆነ ስጠይቀው፣ “አንዳንዶቹ ከእኔ አይደለም፤ እዚያኛው ነው በማለት ያዋክቡናል እንጂ ጥሩ ነው” በማለት መለሰልኝ::

አሁን ደግሞ ወደ አስተዳደር ሠራተኞች ልውሰዳችሁ። ሥራቸው የቱንም ያህል ከባድና አስቸጋሪ ቢሆንም ሠራተኞቹ ግን ጥራትና ትህትና በተሞላበት ሁኔታ ሥራቸውን እያከናወኑ የሚገኙትን የተቋሙን የጽዳት ሠራተኞች ቆሜ ላጨበጭብላቸው እወዳለሁ::

የጥበቃ ሠራተኞችም ቢሆኑ መመስገን አለባቸው:: ምክንያቱም የተለያየ ባህሪና መልክ ካለው ሰው ጋር ነው ግንኙነታቸው::

በጥበቃዎች ላይ አንድ ያየሁትን ስተት ግን ልንገራችሁ:: ማታ ከሁለት ሰዓት በኋላ ጥበቃዎቹ ከአስታማሚ ውጭ ያሉትን በሙሉ አስወጥተው የግቢውን በር ይዘጋሉ:: በዚህ ጊዜ በሩ ላይ መኪና እየጠበቅሁ ነበርና የጥበቃዎችን ሁኔታ እመለከት ጀመር:: ሁለት ሴቶች፣ “አዳሪ ነን እንግባ” ሲሉት “የለም አትገቡም” አላቸው። “እባክህን ከውስጥ ያሉት አስታማሚዎች ሙሉን ቀን የዋሉ ስለሆነ እኛ መተካታችን ግድ ነው” በማለት ቆሙ::

በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ከኋላችን መጥቶ ብዙም ሳይጠይቁት ገባ:: በቀጠልም እኛ እንደቆምን ሌሎች ሁለት ሰዎች ገቡ:: በዚህ ጊዜ መግባት የተከለከሉት ሰዎች፣ “ለምንድን ነው እኛን ከልክለህ ሌሎችን የምታስገባ? እኛም መግባት አለብን” ብለው በቁጣ ጠየቁ።

ከጥበቃዎች መካከል አንደኛው ጠጋ ብሎ፣ “እስኪ እባካችሁ ምንድን ነው ችግራችሁ?” ጠየቃቸው። ነገር ግን መፍትሔ ይሰጣቸዋል ብዬ ስጠባበቅ አትገቡም! አትገቡም! ብሏቸው አረፈው::

እናም ይህ በዘመድ አዝማድ ከምትሰሩትና በማን አለብኝነት ከምትፈጽሙት ተግባር ልትታረሙ ይገባል እላለሁ::

አንድ ፈገግ ያደረገኝን ነገር ልንገራችሁ:: ጥበቃዎች ከሁለት ሰዓት በኋላ ከአስታማሚ ውጭ ሌላ ሰው ስለማይፈቀድ እየዞሩ ከምኝታ ክፍል ያስወጣሉ። እንዲሁም ሌሊት ላይ በሚዞሩበት ጊዜ ሁለቱም ሰዎች ከታካሚ አልጋ ላይ ተኝተዋል:: በዚህ ጊዜ የጥበቃ ሠራተኛው ግራ ይጋባና ሁለቱንም በእጁ እየነካ፣ “የትኛው ነው ታካሚ ወይም አስታማሚ?” ሲል እኔንም ሌሎችንም ፈገግ አሰኘን:: አስታማሚውም ታካሚውነ ከማስታመም ይልቅ እንቅልፉን ለሽ ብሏል:: ይህ ድርጊት ታካሚውንም የሚረብሽ ነውና ከዚህ ድርጊታችን እንቆጠብ እላለሁ::

እመቤት አህመድ

በኩር ጋዜጣ የካቲት 19/2010 ዓ/ም ዕትም

“እኔ ተፈታሁ እንጂ፤ የታሰርኩበት ዓላማ አልተፈታም” ኢየሩሳሌም ተስፋው

Eyerusalem Tesfaw Eneyew, Ethiopian activist and former prisoner of conscience.

የሐበሻ ወግ፡- ኢየሩሳሌም ተስፋው፤ በቅድሚያ በቅድሚያ ከእስር ስለተፈታሽ እንኳን ደስ አለሽ?
ኢየሩሳሌም፡- ለወጉ ያህል “እንኳን ደስ አለህ” ልበልህ እንጂ፤ እኔ እንኳን ብዙም ደስ አላለኝም፡፡
የሐበሻ ወግ፡- ማለት?
ኢየሩሳሌም፡- ገና ነው፤ ደስታችን ሙሉ አይደለም፡፡

የሐበሻ ወግ፡- መልካም፤ አንቺም የተከሰስሽውና የታሰርሽው በግንቦት ሰባት የተነሳ ነው….
ኢየሩሳሌም፡- አዎ፤ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ በሰላማዊ ትግል ስሳተፍ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ተደብድቤአለሁ፡፡ በዚህ የተነሳ ይህ መንግስት በሰላማዊ ትግል ይለወጣል ብዬ ማሰብ አልቻልኩም፡፡ እናም ከእኔ ጋር አብረው ከተከሰሱት ልጆች ጋር ብዙ ተመካከርን፡፡ ከረዥም ጊዜ ምክክር በኋላ ያለን አማራጭ ሁለት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስን፡፡ አገር ጥሎ መሰደድ ወይም የትግል አማራጭ መቀየር፡፡
ሀገር ጥሎ መውጣት ወይም መሰደድ በእኛ እምነት ተመራጭ አልነበረም፡፡ ስለዚህ የትግል አማራጭ መቀየርን ነበር ምርጫ ያደረግነው፡፡ በዚህ ውሣኔአችን መሰረት የግንቦት ሰባትን ትግል ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ስንሄድ ነው መንገድ ላይ የተያዝነው፡፡

የሐበሻ ወግ፡- ይቅርታ ላቋርጥሽ፤ አሁን ዕድሜሽ ስንት ነው?
ኢየሩሳሌም፡- ሃያ ስድስት፡፡የሐበሻ ወግ፡- እስር ቤት ስንት ዓመት ቆየሽ?
ኢየሩሳሌም፡- ሶስት ዓመት፡፡ ፖለቲካ ትግል ውስጥ ከገባሁ ደግሞ 5 ዓመት ሞላኝ፡፡
የሐበሻ ወግ፡- በ20ዎቹ እድሜ መጀመሪያ ማለትም በ23 ዓመት ዕድሜሽ የትጥቅ ትግል ውስጥ ለመግባት መወሰን ከባድ ይመስለኛል …..
ኢየሩሳሌም፡- ከባድ ነው፡፡ ግን ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ በሰላማዊ ትግል ስሳተፍ የነበሩት ሂደቶች፣ የደረሱብን በደሎችና ግፎች ካለ ዕድሜዬ እድሜዬ እንድበስል ያደረጉኝ ይመስለኛል፡፡ እና እንዳልከው እዚህ ውሣኔ ላይ (በተለይም ሴት ሆነህ) መድረስ ከባድ ነው፡፡ በተለይ በዚያ ወቅት ስለ ግንቦት ሰባት ማሰብ በራሱ በጣም ያስፈራ ነበር፡፡ ነገር ግን የሰላማዊ ትግሉ በር ስለተዘጋ በውሣኔአችን መፅናት ነበረብን፡፡

የሐበሻ ወግ፡- አስታውሳለሁ፤ ፍ/ቤትም በቀረብሽ ጊዜ “የሰላማዊ ትግል በር ስለተዘጋ ነው በትጥቅ ትግል መሣተፍን አምኜበት ነው ወደ ኤርትራ ያመራሁት” ነው ያልሽው ….
ኢየሩሳሌም፡- አዎ፤ እኔም ጓደኞቼም ማይካድራ ላይ ከተያዝንበት ቅፅበት ጀምሮ ይህንኑ ነው ፊት ለፊት የነገርናቸው፡፡

የሐበሻ ወግ፡- እስቲ ወደ ኤርትራ ስትሄዱ በቁጥጥር ስር እስከዋላችሁበት ጊዜ በመንገድ ላይ የነበረውን/የገጠማችሁን ውጣ ውረድ አውጊኝ?
ኢየሩሳሌም፡- የተነሳነው ከዚህ ከአዲስ አበባ ነው፡፡ ያን ዕለት ባህርዳር ገብተን አደርን፡፡ በበነጋታው ከመሃላችን አንዱ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ፡፡ የቀረነው ወደ ጎንደር ጉዞ ቀጠልን፡፡ … እናም ጎንደር ገባን፡፡ ከዚህ በኋላ የነበረው ጉዞአችን አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሙቀቱ፣ ውጣውረዱ ወ.ዘ.ተ ሁሉ እጅግ ፈታኝ ነበር፡፡ በተለይ ለእኔ ከቤቷ ወጥታ ርቃ ሄዳ ለማታውቅ ወጣት ጉዞው ከባድ ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላለህ፡፡ በነገራችን ላይ ከጎንደር በኋላ ፍፁም መንቀሳቀስ በማንችልበት ደረጃ ክትትል ይደረገብን እንደነበርና እንደምንያዝም እናውቅ ነበር፡፡ ቢሆንም ጉዞአችንን ቀጠልን፡፡ ማይካድራ ላይ ተያዝን፡፡

የሐበሻ ወግ፡- ከተያዛችሁ በኋላስ ምን ሆነ? ምን ገጠማችሁ?
ኢየሩሳሌም፡- ከተያዝን በኋላ ለረዥም ሰዓት በቪዲዮ ቀረፁን፡፡ ከዚያም ዐይናችንን አስረው በመኪና ወሰዱንና አንድ ቤት ውስጥ አስገቡን፡፡ ዐይናችን ስለታሰረ ያ ቦታ የት እንደሆነ አላወቅንም፡፡ ብቻ እዚያ ቤት ውስጥ ሶስት ቀን ካሳደሩን በኋላ እንደገና ዐይናችንን አስረው ወደ ሌላ ቦታ ወሰዱን፡፡ ስገምት፤ ይኼኛው ቦታ ጎንደር ይመስለኛል፡፡ እዚያም አራት ቀን ከቆየን በኋላ ነው ወደ ማዕከላዊ ያመጡን፡፡ ማዕከላዊ መሆኑን ያወቅነው ከመኪና ከመውረዳችን በፊት መዓት ፖሊሶች ከበባ ሊያደርጉብን ሲጯጯሁ በሰማነው ድምፅ ብዛትና ትርምስ ነው፡፡

የሐበሻ ወግ፡- አዲስ አበባ ማዕከላዊ ግቢ ከደረሳችሁ በኋላ ከበባ?
ኢየሩሳሌም፡- አዎ፤ ስንያዝ ጀምሮ የነበረው ሁኔታ በጣም ያስቅ ነበር፡፡ (ሣቅ) በአየር ወለድ ጭምር ታጅበን ነበር ወደ ከቦታ ቦታ የምንወሰደው፡፡ እኛ ሶስት ወጣቶች ነን፤ በዚያ ላይ በእጃችን ምንም ነገር እንዳልያዝን ይታወቃል፡፡ መንግስት እኛን ለማጀብ ከፖሊስ በተጨማሪ አየር ወለድ ጭምር ማሰለፉ በጣም ያሳዝናል፤ ያስቃል፡፡
የሐበሻ ወግ፡- በአየር ወለድ ጭምር መታጀባችሁን በምን አወቅሽ?
ኢየሩሳሌም፡- ስገምት ጎንደር ሊሆን ይችላል ብዬ የነበርኩህ ቦታ ለቀናቶች ቆይተናል፡፡ አጃቢዎቻችን (ጠባቂዎቻችን) በሙሉ መሣሪያ ታጥቀዋል፡፡ አንዱ አጃቢያችን ግን መሣሪያ አልያዘም ነበር፡፡ እናም “ሁሉም መሣሪያ ታጥቀዋል፤ አንተ ግን መሣሪያ አልያዝክም፤ ለምንድነው?” ብዬ ጠየቅኩት፡፡ ያኔ ወገቡ ላይ ያለውን ገመድ አሳየኝ፡፡ “ይኼ መሣሪያ ነው እንዴ?” ስለው፤ “አዎ” አለኝ፡፡ ገረመኝ፡፡ ያ ሁሉ ፌዴራል ፖሊስ መሣሪያ ወድሮብን ነው እየተጠበቅን ያለው፡፡ ለእኛ በጥፊ ለምንወድቅ ምንም ነገር ላልያዝን ወጣቶች አየር ወለድ ማሰለፍ ለምን እንዳስፈለገ አላውቅም፡፡

የሐበሻ ወግ፡- በነገራችን ላይ፤ እንዲህ ዓይነት ውሣኔ ላይ መድረስሽን ጉዞ መጀመርሽን ለአንድ ሰው፣ በጣም፣ እጅግ በጣም ለምትቀርቢው ሰው እንኳ አልነገርሽም?
ኢየሩሳሌም፡- በፍፁም! እንዴት ይነገራል!? ቅድም እንዳልኩህ ውሣኔአችን እጅግ ከባድ ነው፡፡ ሲጀመር፤ የትጥቅ ትግል የኔ ምርጫ አልነበረም፡፡ ደም አፍስሶ፣ ህይወት ቀጥፎ ለውጥ ማምጣትን አላምንበትም፤ ጓደኞቼም አያምኑበትም፡፡ በመንግስት እርምጃ ተገደን ነው እዚህ ውሣኔ ላይ የደረስነው፡፡ ስለዚህ መጠንቀቅ ነበረብንና እዚህ ውሣኔ ላይ መድረሴን ለማንም ትንፍሽ አላልኩም፡፡

የሐበሻ ወግ፡- አሁን ከእስር ቤት ወጥተሽ “ሰፊውን እስር ቤት” ተቀላቅለሻል፡፡ ከወጣሽ በኋላ ያለውን ሁኔታ አየሽው?
ኢየሩሳሌም፡- አሁን በውጪ ያለው ነገር ጥሩ ይመስላል፡፡ ቅድም እንዳልኩህ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ለ2 ዓመታት በሰላማዋ ትግል ተሳትፌአለሁ፡፡ ያኔ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻልንም ነበር፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ገና ከፓርቲው ግቢ ወጣ ስንል ነበር ታፍነን፣ ስንደበደብና ስንታሰር ማንም ዞር ብሎ አያየንም ነበር፡፡ አሁን ግን ሕዝቡ ዳር እስከዳር ተንቀሳቅሷል፡፡ በሕዝቡ አመፅ እጃቸው ተጠምዝዞ ሳይወዱ በግዳቸው የፖለቲካ እስረኞችን እንዲለቁ አስገድዷል፡፡ ይኼ የሕዝብ አንድነት መንፈስ ጥሩ ነው፡፡

እንዲያም ሆኖ አንዳንድ ቦታዎች የሚከሰቱ ሁኔታዎች አሁንም ሕወሐት/ኢህአዴግ በከፈተልን መንገድ እየፈሰሰ ያለ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ የዘረኝነት አዝማሚያ ጫፍ እየነካ ያለ ይመስለኛል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ከተለያየ ክልል የመጣን እስረኞች ነን አንድ ላይ የነበርነው፡፡ ከሱማሌ፣ ከኦሮሞ፣ ከአማራ፣ ወ.ዘ.ተ፡፡ ሁላችንንንም የፖለቲካ እስረኞች አንድ የሚያደርገን ነገር ነበር፡፡ እርግጥ ነው ሁላችንም የምንታገለት ዓላማ አለን በመሃላችን የሃሳብ ልዩነት አለ፤ ግን…..የጋራ የሚባል አገር የሚባል ነገር አንድ ያደርገን ነበር፡፡ ከእስር ቤት ውጪ ግን የዘረኝነት አስተሳሰብ እየገነነ ያለ ይመስለኛል፡፡ ዘረኝነት የሚባለውን ነገር ከመሃላችን ካላስወጣን የምንፈልገው የሥርዓት ለውጥ ቢመጣ እንኳን ዋጋ አይኖረውም፡፡ ስለዚህ በአንድነት ጠንክረን መውጣት አለብን፡፡

የሐበሻ ወግ፡- መልካም፤ ከዚህ በኋላ በፖለቲካ ትቀጥያለሽ?
ኢየሩሳሌም፡- አዎ እቀጥላለሁ፡፡ ጥያቄዬ እኮ ገና አልተመለሰም፡፡ እኔ ተፈታሁ እንጂ፤ የታሰርኩበት ዓላማ አልተፈታም፡፡ ስለዚህ በትግሌ እቀጥላለሁ፡፡
የሐበሻ ወግ፡- ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ፡፡

የሬሚታንስ ተአቅቦ ዘመቻው ተጠናክሮ ይቀጥላል! አለምአቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረሀይል

አለምአቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረሀይል

Worldwide Ethiopians Remittance Embargo, social media campaign.

ወያኔ-ህወሓት የገባበት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተባብሶ ቀጥሏል። በተለይም በውጭ ምንዛሬ ረገድ የሚታየው ችግር አድማሱን እያሰፋ የሄደበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የሬሚታንስ ዘመቻው ከተጀመረ በኋላ እየወጡ ያሉት ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአገዛዙ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየከፋ መጥቷል። በዚህ ረገድ የሚከተሉት አስረጅዎች የሚጠቀሱ ናችው፦

 • ከውጭ የሚገባ ብረት እና ጥሬ እቃ በመቀነሱ የተነሳ፣ የአርማታ ብረት ዋጋ መናር እና ከገባያ መጥፋት፤ ይህንንም ተከትሎ
  የግንባታ መስኩ መቀዛቀዝ፣
 • በምንዛሬ እጥረት ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤምባሲዎች የሚመድበው በጀት እየቀነሰ መምጣቱ፣
 • በኢትዮጵያ ውስጥ መዋእለ ነዋይ ያፈሰሱ እንደ ሄኒኬን የቢራ ፋብሪካ የመሰሉ ድርጅቶች ትርፋቸውን በውጭ ገንዘብ
  ወደውጭ ማውጣት ያልቻሉበት እና የመስፋፊያ ምንዛሬ ያጡበት ሁኔታ መከሰት፣
 • ከውጭ አበዳሪዎች ብድር ወስደው ሥራቸውን የሚያከናውኑ እንደ ቴሌኮሙዩኒኬሽን እና መብራት ሀይል ባለስልጣን ያሉት
  ድርጅቶች እዳቸውን ለመክፈል የተቸገሩበት ሁኔታ መኖሩ፣
 • የፋርማሲውቲካል፣ ኬሚካል፣ የፕላስቲክ እና የጠርሙስ ፋብሪካዎች ከውጭ በሚገቡ ጥሬ ዕቃዎች እጥረት ምክንያት
  ምርታማነት መቀነስ፣
 • የህዳሴውን ግድብ ጨምሮ ለትላልቅ ግንባታ ፕሮጀክቶች ከቻይና እና ሌሎች አበዳሪዎች የተወሰደውን ብድር መክፈል
  አለመቻል እና በምንዛሬ እጥረት መክንያት በግድቡ ግንባታ ለተሰማሩ ሳሊኒ ኮንስትራክሽንን ለመሳሰሉ ተቋራጮች በውሉ
  መሰረት ክፍያ ለመፈጸም አለመቻል፣
 • የተፈጠረውን የምንዛሬ እጥረት ያቃልል ይሆናል በሚል እሳቤ አገዛዙ ተጓዦች ይዘውት የሚገቡትን እና የሚወጡትን የውጭ
  ገንዘብ ለመቆጣጠር ያለመ ቀቢፀ-ተስፋ እርምጃ ውስጥ መግባቱ፣
 • የብር ተመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ፤ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው በጥቁር ገበያ የአንድ ዶላር ዋጋ ወደ ሰላሳ ስድስት
  ብር ማሻቀቡ፣

አገዛዙ የገባበትን ኢኮኖሚያው ቀውስ በማባባስ ረገድ የሬሚታንስ ተአቅቦ ዘመቻው የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል። ለዚህም ነው ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት። በተለይም የወያኔ-ህወሓት ፖለቲካዊ ቀውስ ተባብሶ ጠቅላይ ሚኒስተር ለመቀየር እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በድጋሜ ለማወጅ በተገደደበት በዚህ ወቅት ኢኮኖሚያዊ ጫና ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው። የፖለቲካ ቀውሱን ለማርገብ ይረዳኛል በሚል ግምት ወያኔ-ህወሓት በድጋሜ ያወጀው የጭንቀት አዋጅ እየተዳከመ የመጣውን ኢኮኖሚ የበለጠ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት እርምጃ ነው። አዋጁ የውጭ ባለሀብቶችን የበለጠ ያሸሻል፣ ቱሪስቶችን ያደናግጣል፣ በማህበረሰቡ ላይ የስነልቦና ጫና በመፍጠር የአገር ውስጥ የምርት እና አገልግሎት እንቅስቃሴዎችን ያዳክማል፣ የአፈና አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ በየቦታው ለሚሰማሩት ሰላዮች እና ነፍሰገዳዮች ከፍተኛ በጀት እና የውጭ መንዛሬ ስለሚያስፈልግ በኢኮኖሚው ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል፣ የፖለቲካ መፍትሄ ያስፈልጋል ብለው የሚያምኑ አበዳሪ እና ለጋሽ አገሮችን ተስፋ በማስቆረጥ እርዳታ እና ብድር መስጠታቸውን እንዲያቆሙ ምክንያት ይሆናል። በጥቅሉ ኢኮኖሚውን ከድጥ ወደ ማጡ የሚገፋ ቀቢፀ-ተስፋ እርምጃ ነው።

አገዛዙ በራሱ አንገት ላይ ያጠለቀውን ይህን ኢኮኖሚያዊ ሸምቀቆ በማጥበቅ እና የስርአቱን ፍጻሜ በማፋጠን ረገድ በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ትልቅ አቅም አለን። ይሄም የሬሚታንስ ተአቅቦ ዘመቻውን አጠናክሮ መቀጠል ነው። ወያኔ- ህወሓት የጭንቀት አዋጅ በማወጅ የህዝቡን የነጻነት ትግል ለመቀልበስ የሞት-ሽረት ትግል በሚያደርግበት በዚህ ወቅት፣ በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የአገዛዙን ኢኮኖሚያዊ ምሰሶ ለመናድ የበለጠ ቁርጠኝነት ማሳዬት ይኖርብናል። የሬሚታንስ ተአቅቦ ዘመቻውን የበለጠ በማፋፋም በአገዛዙ ለይ ጠበቅ ያለ ርምጃ መወሰድ እና ወያኔ-ህወሓት የደገሰው የአፈና አዋጅ እንዲከሽፍ የበኩልን ድርሻን መወጣት ውጭ ካለነው ኢትዮጵያዊያን የሚጠበቅ ሞራላዊ እና ወገናዊ ግዴታ ነው።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ትግል የነጻነት አገር ትሆናለች!!

አለምአቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረሀይል

‹‹ስሚኝ እማምዬ፣ለምን ታለቅሻለሽ፣ በወፍጮ ላይ መጁ፣ሲጨፍር እያየሽ!!!›› ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ዶክተር እሸቱ ጮሌ ክበብ››

ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት TPLF WARLORDS STATE የወያኔ ፋሽስታዊ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሳ!!!

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡- ቀጣዮን ብሄራዊ የወጣቶች የትግል አቅጣጫ ማሳየት ይጠበቅባችኃል፡፡

‹‹የኦሮሞ ቄሮ፣ የአማራ ፋኖ፣ የደቡብ አቦሸማኔ (የጉራጌ ዘማር)፣ የሰሜኑ አናብስት!!! ጥያቄዎች ይመለሱ!!! ወጣት የነብር ጣት!!! ››

ለሚቀጥለው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የቀረቡ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ሴቶች ጥያቄዎች!!!

{0} ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ማንሳት!!! የተቀሩት የፖለቲካ እስረኞች መፍታት!!! የአጋዚ ጦር ገዳዬች ለፍርድ ማቅረብ!!! ይሄ ሳይፈፀም ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን በእራስ ላይ መርዛማ ኮብራ መጠምጠም ነው፡፡ የወያኔን ሥርዓት ከመውደቅ የሚያድን ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ የኑሮ ውድነት የሸቀጣ ሸቀጦች ዎጋ የዋጋ ግሽበት ጣራ ነክቶል፡፡ የመድኃኒት፣ የነዳጅ፣ መግዣ የውጭ ምንዛሪ የለም፡፡

{1} በፋይናንሻል ኢንቲግሪቲ ድርጅት፣ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ  ከዓለም 180 ሃገራት 107ኛ ደረጃ፣ እንዲሁም ከአፍሪካ ሃገራት 20ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሙስና ከመቶ 35 በመቶ ውጤት በማግኘት ወድቃለች፡፡ በሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ የተጀመረው የሙስና እንቅስቃሴና የታሰሩት ግለሰቦችና የተወረሰው ንብረት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለህዝብ በየወሩ ሪፖርት ጠቅላይ ሚንስትሩ ማድረግና ለህዝብ የማሳወቅ ሃላፊነት አለበት፡፡ የፀረ ሙስና ባህላችሁ ያዝ ለቀቅ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ነው፡፡ እንደ ሳውዲ አረቢያ ንጉስ የፀረ ሙስና  ዘመቻ 100 ቢሊዮን ዶላር የህዝብ ኃብትና ንብረት አድርገዋል፡፡ ሙስናን ማምከን ቆራጥነት ከሌላችሁ በውርደት ትወርዳላችሁ! ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ልጆቹ ቤት 6 የመንግስት መኪኖች እንዳሉ ህዝብ ያውቃል፣ ለልጆቹ የመንግሥት ቤት አሰጥቶል፣ ልጆቻቸውወን የዳሩት ቤተመንግሥትና ጊዮን ሆቴል ነበር ህዝብ ያውቃል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ንስሃ ገብተው ወደ ፓስተር ስራቸው እንደ ታምራት ላይኔ ቢመለሱ እንመክራለን!!! ማነሽ ባለሳምንት…… ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ኃብትና ንብረታችሁን አስመዥግቡ!!! የደሃ ህዝብ የደም ገንዘብ ያንቃልና!!!  የወያኔ ጭንብል ካጠለቀ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ይሠውራችሁ!!! ህይወት አጭር ናት ህዝብን ከርሃብ፣ ከስደት፣ ከበሽታ፣ ታደጉት!!!

{2} የጠቅላይ ኦዲተር ፅህፈት ቤት በተደጋጋሚ ለፓርላማ ያቀረቡት የኦዲት ሪፖርት ድጋፍ ተሰጥቶት በፍርድ ቤት ፍትህ እንዲሰጥና የህግ ተፈፃሚነት ተግባራዊ ማድረግ፡፡ የጸረ- ሙስናውን ትግል በነጻነት እንዲመሩና በሃገሪቱ ውስጥ የተስፋፋውን ሙስና፣ ኮንትሮባንድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገወጥ ግለሰቦችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ ኃላፊነት መስጠት፣ ከህግ በላይ ማንም ሰው መሆን እንደማይችል በተግባር መገለፅ አለበት፡፡

{3} ሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ ከነሰንኮፉ ነቅሎ መጣልና የአይነኬ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ንብረታቸውና ሃብታቸው በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማስመዝገብና የሃብትና የንብረት ምንጫቸው ለህዝብ ማሳወቅ ግድ ይላል፡፡

{4} የከተማና የገጠር የመሬት ቅርምት፣ የእርሻ መሬት፣ የሪል ስቴት መሬት፣ የአበባ መሬት፣ ወዘተ ህገወጥ የሙስና ተግባር፣ ህዝብ የተሳተፈበት የማጋለጥ ሥራ በመገናኛ ብዙሃን ሬዲዮ፣ቴሌቪዝን፣ ጋዜጣ ፣ ኢንተርኔት ይፋ ማድረግ

{5} በፕራይቬታይዜሽን የተሸጡ የህዝብ ሃብቶችና ንብረቶች የእርሻ ቦታዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሆቶሎች፣ ወዘተ በጸረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ እንዲካሄድባቸው ማድረግ፣

{6} የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃብትና ንብርት የሆኑ ድርጅቶች የህወሓት ኢፈርት፣ የበአዴን ጥረት፣ የኦህዴድ ዲንሾ እንዲሁም የደህዴን ወነወዶ የንግድ ድርጅቶች ፋብሪካዎች፣እርሻዎች፣ የማዕድን ሓብቶች ወርቅ፣ ብር ፣ታንታለም፣ እብነበረድ፣ሲሚንቶ ፣ የአገልግሎት ሰጪ የንግድ ድርጅቶች፣ የመድሃኒት ፋብሪካ፣ የማዳበሪያ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ወዘተ የፓርቲ የንግድ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍና ተቆማት  ያለው የሙስና ተግባር ሥራዎች ተጋልጠው እንዲወጡ ማድረግ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች ንብረት የሆኑት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ተወርሰው ፣ ባንኮቹ ለህዝብ በአክሲዮን ተሸጠው የህዝብ ሃብት ማድገር፣

{7} የፋይናንሻል ዘርፍና ተቆማት በመንግሥት ባንኮችና የግል ባንኮች፣ በማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ያለው የሙስና ተግባር ብድር በመስጠት፣ በመሰብሰብ፣ በውጭ ምንዛሪ፣ ለመንግሥት፣ ለክልሎች፣ ለግለሰቦች በአድሎ የተደረጉ ሥራዎች ተጋልጠው እንዲወጡ ማድረግ፤ የህወሓ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች ንብረት የሆኑት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ተወርሰው ፣ ባንኮቹ ለህዝብ በአክሲዮን እንዲሸጡ ማድገር፣

{8} የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የመከላከያ ሠራዊት የብረታብረት ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ቁጥጥር ሥር ያሉ የሲቪል የግሉ ዘርፍ ሊሰሮቸው የሚችሉ ፋብሪካዎቸ ተወርሰው ለህዝብ በአክሲዮን እንዲሸጡ ማድረግ፡ ሜቴክ ከንግዱ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ መውጣት ይኖርበታል፡

{9} የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ቤት እያከራዩ የመንግሥት ቤት ውስጥ የሚኖሩ በአስቸኮይ እንዲወጡ፣ እንዲሁም ቤት እያከራዩ በቀበሌና በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦች ተጣርቶ እንዲለቁ ማድረግ፣

{10} የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ከአንድ መጠቀሚያ የመንግሥት መኪና በስተቀር ሌሎቹን ማስመለስ

{11} የህወሓት/ኢህአዴግ የሲቪልና ወታደራዊ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ሠራተኞች የጡረታ እድሜ 55 ዓመት እንዲሆን መወሰንና ለመጭው ትውልድ ለመተካትና የሥራ ዕድል መፍጠር አስፈላጊ

{12} የህወሓት/ኢህአዴግ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የተቆቆሙ የሚንስትሪዎች፣ ፅህፈት ቤቶች፣ ኤጀንሲዎች፣ ድግግሞሽ መንግሥታዊ መዋቅሮች   ተጠንተው እንዲታጠፉ ማድረግና የመንግሥት መደበኛ ወጪ (ደሞዝ፣ አበል፣ ነዳጅ፣ ልዮ ልዮ ወጪዎች፣ ወዘተ) ቅነሳ ማድረግ

{13} በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ሑለት ሦስት የመንግሥት ቦታ የወሰዱ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንት፣ የጦር መኮንኖች፣ ካድሬዎች ለመሬት ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ፡፡ ሜድሮክ አጥሮ የያዛቸው 11 ቦታዎች ካርታ ማምከን!!! በ‹‹ልማት ተነሺ›› በማለት የሚነሱ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት ይቁም፡፡ በግፍ የተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው ካሳና ቤት እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡ በሙስና ሁለት ሦስት የኮንዶሚኒየም ቤቶች የተሰጣቸው ግለሰቦች እንዲመልሱና ተጀምሮ የነበረው የኮንዶሚኒየም ቆጠራ፣ የህዝብ ሃብት እንዲጠናከር ማድረግ፡፡ የቤቶችና ቁጠባ ባንክ (ሞርጌጅ ባንክ)ን ድጋሚ ማቆቆምና የኮንዶሚኒየም ግንባታዎች በሙሉ በባንኩ ሥር እንዲከወኑ ማድረግ፡፡

‹‹የወጣቶችና ሴቶች የልማት ሚኒስቴር ማቆቆም››

የወጣቶችና ሴቶች የልማት ሚኒስቴር ማቆቆም፣ ርዓይ፣ዓላማዎች፣ሥራ፣ተግባር ወዘተ ለማስጠናት፣ ከየዮኒቨርሲቲዎች የወጣቶችና ሴቶች የሥራ ፈጠራ የጥናት ማዕከል በማቆቆም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የገቢ ምንጭ ማስገኛ ዘለቄታዊና ቀጣይነት ያለው የተለያዩ ቢዝነስ ፕላኖች እንዲጠኑ በማድረግ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት መነሻ ጥናት በማቅረብ  ጉዳዩ ያገባናል የሚሉ ዜጎችና ወገኖች አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት ግብዣ  ቀርቦል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥታዊ ዘርፍ የኢትዮጵያ ሥራ አጥ ወጣቶችና ሴቶችን ዜጎቻችን ችግር መፍታት አልቻለም፡፡ የሥራ አጥነት ችግርን መፍታት የሚችለው የግሉ ዘርፍ ሲሆን የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥታዊ ዘርፍ፣ የፖለቲካ የንግድ ኢንተርፕራይዞች በአክሲዮን ህዝብ እንዲገዛቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የመንግሥታዊ የንግድ ኢንተርፕራይዞች በሙስናና በዘመድ አዝማድ የፖለቲካ ሹማምንትና ካዴሬዎች የተሰገሰጉበት ኃብትና ንብረት ነው፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት፣ የፌዴራልና የክልሎች ያልተመጣጠነ እድገት፣ ኢፍትሃዊ የኃብት ክፍፍል፣ አድሎዊ የበጀት ክፍፍል ቀመር፣ በአጠቃላይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ችግሮቻችን አንዱን የእናት ልጅ አንዱን የእንጀራ ልጅ ያደረገውን ሥርዓት በሰላምና በውይይት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት በቀና ልብ የወጣቶችና ሴቴች ችግርን ለመፍታት የመሻትና እምነት ብቻ ነው፡፡

{1} የወጣቶች ሪል ስቴት ዲቨሎፕመንት ማቆቆም፣ የወጣቶች የቤቶች ልማት ግንባታ ዘርፍ በማቆቆም ወጣቶች የቤቶች የገንዘብ ቁጠባ ባንክ አባላት በማድረግ ከቤቶች ዲዛይን፣ ግንባታ፣ የቤት ግንባታ ምርቶች ማምረቻ አነስተኛ ተቆማት (ብሎኬት፣ በር፣መሥኮት፣ ኮብል ስቶን፣ወዘተ)፣የቤት ካንተራክተሮች ጠቅላላ ሥራ በማቀናጀት  ለወጣቶች የቤት ግንባታ፣የብድር አቅርቦት፣ የመሬት ማመቻቸት የጋራ ሥራን ማመቻቸት

{2} የወጣቶችና ሴቶች የልዩ ልዩ የትራንስፖርት መኪናዎች ሥልጠናና ፍቃድ ሥራ ቢሮ ማቆቆም፣ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት የሚገኙ የትራንስፖርት ሥልጠናና ፍቃድ ሥራ፣ብዙ ወጣቶችን የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም በሙስና የተጨማለቀው የኢትጵያ የትራንስፖርትና የመኪና ስልጠናና ፍቃድ በወጣቶችና ሴቶች የልማት ሚኒስቴር ሥር መሆን ብዙ የሥራ እድልና የገቢ ምንጭ ያስገኛል፡፡

{3} የወጣቶችና ሴቶች የልዩ ልዩ አነስተኛ ማንፋክቸሪንግ ማሽነሪዎች ማሠልጠኛና  ሥልጠናና የዕቃ መሸጫ ድርጅቶች በማቆቆም ልዩ ልዩ ዓይነት የልብስ ስፌት መኪኖች፣የሹራብ መሥሪያ ማሽኖች፣ የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖች፣ የኬክ መጋገሪያ ማስኖች፣ የዘይት መጭመቂ ማስኖች፣ የዕቃ ማሸጊያ ማሽኖች ወዘተ በማሠልጠንና ማቅረብና ለወጣቶችና ሴቶች በግል ወይም በቡድን ተበድረው እንዲሰሩ ማድረግ፣ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣ በብረት ሥራ፣ በእንጨት ሥራ፣በጋራዥ ሥራ፣ የዱቄት ፋብሪካ፣ ወዘተ

{4} የቴሎኮሙኒኬሽን ዘርፍ 50 በመቶ ኢትዮ-ቴሌን ለባህር ማዶ የቴሎኮሙኒኬሽን የግል ካንፓኒዎች ፕራይቬታይዝ በማድረግ የወጣቱን የሥራ ዕድል ምንጭና የገቢ ምንጭ ከፍ እንዲል ማድረግ ማድረግ ይቻላል

{5} ግብርና ዘርፍ በተለይ የመስኖ እርሻ ሥራ ላይ በግብርና ሙያ ከዮኒቨርሲቲ በዲግሪና ዲፕሎማ የተመረቁ ተማሪዎችን መሠማራት፣ የእርሻ መሬት፣ የብድር አገልግሎት፣ የትራክተርና የመኪኖች አቅርቦት እንዲመጣችላቸው ማድረግ

{6} የወጣቶችና ሴቶች የጅምላና የችርቻሮ ሥራ ማቆቆም፣ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት የሚገኙ መንግስታዊ ድርጅቶች የሚካተቱ ውስጥ፣

 • የመሬት ማዳበሪያ የዮሪያና ዳፕማከፋፈያ ሥራ ለወጣቶችና ሴቶች ገበሬዎች የማዳበሪያ አቅርቦት/ የፍርትላይዘር የማከፋፈል የስራ እድል፣የምርጥ ዘር፣ ጸረ-ተባይና አረም ወዘተ ሥራ ላይ እንዲሠማሩ ማድረግ
 • ‹‹አለ በጅምላ›› የሸቀጣሸቀጥ አከፋፋይ ድርጅት ከነ ቅርንጫፎቹ፣
 • የሜጋ ማተሚያ ድርጅትና በፕራይቬታይዤሽን የተሸጡ የሜጋ አሳታሚ ድርጅቶች ከነቅርንጫፎቻቸው፣ የመፅሃፍ ማተምና መሸጥ ሥራ ለወጣቶችና ሴቶች በዕውቀትና ባላቸው ክህሎት በሃገር አቀፍ ፈተናና የሥራ መመዘኛ ያለፍት ሥራውን ተረክበው እንዲሠሩ ማድረግ፣ በቀጣይነትና በዘለቄታዊነት ለወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል መፍጠርና የገቢ ምንጮቻቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ
 • በትምህርት ቢሮ የህትመትና የትምህርት መፅሃፍት የማከፋፈልና ሽያጭ ሥራ እንዲሰሩ ማድረግ

{7} በፌዴራል መንግሥት የተያዙ 17 መንግሥታዊ የልማት ድርጁቶች ኢንዱስትሪል ፓርኮች፣ ከልማት ድርጅቶቹ ምርትና አገልግሎት ሽያጭ  የሚገኘው ብዙ ቢሊዮን ብር ገቢ ለወጣቶችና ሴቶች የሥራ ፈጠራ እንዲውልና በሙያተኞች እየተጠና አዳዲስ ፋብሪካዎች በየጊዜው እንዲከፈት ማድረግ፣ አዳዲሶቹን ፋብሪካዎች ለህዝብ በአክሲዩን እንዲሸጡ ማድረግ ፣ እነዚህ የልማት ድርጅቶች ኢንዱስትሪል ፓርኮች፣ ለህዝብ በአክሲዮን ተሸጠው ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የሥራ ዕድል እያስፋፉ እንዲሄዱ በየዩኒቨርስቲዎቹ ጥናት ማስጠናት፣ከየዮኒቨርሲቲዎች የወጣቶችና ሴቶች የሥራ ፈጠራ የጥናት ማዕከል በማቆቆም እነዚህን  17 መንግሥታዊ የልማት ድርጁቶች፣ ዘቄታዊነትን ማጥናት  ‹‹›ከልማት ድርጅቶቹ ምርትና አገልግሎት ሽያጭ 19 ቢሊዮን ብር መገኘቱ ተገለጸ፤ ባለፈው ስድስት ወራት ከልማት ድርጅቶቹ ምርትና አገልግሎት ሽያጭ 19 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የመንግሥታዊ የልማት ድርጁቶች ሚኒስቴር ዶክተር ግርማ አመንቴ አስታወቀ፡፡ የየልማት ድርጁቶቹን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም   ›

{8} የወጣቶችና ሴቶች ማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት ማቆቆም፣ ያለውን የህወሓት/ኢህአዴግ ማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት የፖለቲካ ድርጅቶች የፋይናንስ ዘርፍች መውረስ፡፡ በሃገሪቱ የወጣቶችና ሴቶች ማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት በማስፋፋት ለወጣቶችና ሴቶች ዘለቄታዊ የሥራ ዕድል መፍጠርና የገቢ ምንጫቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ ማድረግ፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቀõማቱ ከየክልሎቹ ዮኒቨርሲቲዎች ጋር በህብረት በመሥራት በጥናት ላይ የተመሰረተ የፕሮጀክት ፕላኖች በአነስተኛና ጠቃቅን የተደራጁ የወጣቶችና ሴቶች በግብርና (በእርሻ፣በከብት፣ በግ፣ ዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነባነብ ወዘተ) በማኑፋክቸሪንግ (የዱቄት ፋብሪካ፣ የልብስና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች፣ የዘይት ፋብሪካዎች፣ የአገር ልብስ፣ የዶርዜ ሃይዞ የጥበብ ሥራ ፋብሪካዎች፣ወዘተ) የአገልግሎት ዘርፎች፣(የቱሪስት አስጎብኝ ድርጅቶች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና ሥልጠና መስጠት፣

ኢህአዴግ ፓርቲዎች የተፈበረኩ ማይክሮ ፋይናንስ ተቀማት  Party machine MFIs  በኢትዩጵያ በኢህአዴግ ፓርቲዎች የተፈበረኩ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት በመንግስታዊ ዘርፍነት፣ በክልል ፓርቲዎቹ ንብረት ባለቤትነትና የሚንቀሳቀሱትም በካድሬ አባሎቻቸው ነው፡፡ እነዚህ ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች ንብረት የሆኑ የአውራው ፓርቲ የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽንስ  ድርጅቶች ከኢትጵያን ብሄራዊ ባንክ ፍቃድ ተሰጥቶቸው በአዲስአበባ ከተማና በክልሎች ውስጥ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ {1} አማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣{2} ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣{3} ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ {4} ኦሞ ማይክሮፋይናንስ፣ {5} አዲስ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ {6} ቢኒ-ሻንጉል ጉሙዝ ማይክሮ ፋይናንስ  {7} ድሬ ዳዋ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽንስ  በዋናነት ሲገኙበት ሁሉም በነፃነት በግሉ ዘርፍ  የተመሠረቱ የብድርና ቁጠባ ተቆማት እንደሆኑ ለህብረተሰቡና ለዓለም ህብረተሰብ በውሽት ይተውናሉ፡፡  በአጥኝዎቹ በተለይ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ባገኙት ከህዝብ ቃለምልልስ መረጃ መሠረት እነዚህ የማይክሮ ፋይናንስ ተቀEማት መነሻ ፍሬ ካፒታላቸውን ያገኙት ከክልል መንግሥት፣ ከክልል በጎአድራጎትና መልሳ ማቆቆም ተቀማት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማቱ፣የክልሉ መንግሥት፣ ሹማምንትና ካድሬዎች ዋናዎቹ ባለአክሲዩኖች/ ሼር ሆልደርስ ተጠቃሚ ሲሆኑ የሚገኘውን ትርፍና የፋይናንስ ገበያ ከፍተኛ ድርሻ ‹በደሃ ስም› በመነገድ ይገኛሉ፡፡ The MFIs we section in this category are all owned and run by regional governments and party members of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRDF).These are namely Amhara Credit and Saving Institution S.C, Addis Credit and Saving Institution S.C., Benishangul Gumuz Micro finance S.C, Dedebit Credit and Saving Institution S.C., Diredawa Micro finance Institution S.C, Omo Micro finance Institution S.C, and Oromia Credit and Saving Institution S.C. They all act and reach the mass and international community as ‘independent’ MFIs, however, the populous we interviewed in the Amahra and Oromia region perceive them rather as ‘partial’. These MFIs received their major funding (seed money) from their respective regional governments and endowments. The regional governments and their top cadres are the major shareholders in these MFIs making them the highest profit makers out of these so called ‘pro poor’ MFIs.  ( “Poor Helpers” or “Poor Killers?”

እነዚህ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማትም  አጠቃላይ 35 አነስተኛ ብድር አገልግሎት የሚሰጡ የሃብት መጠናቸው 50 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ብሄራዊ ባንክ ገልፆል፡፡ የካፒታል ክምችታቸውም 10.7 ቢሊዮን ብር ደርሶል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማትበ2008 ዓ/ም የሃብት መጠናቸው 36.6   ቢሊዮን ብር ነበር፡፡  የካፒታል ክምችታቸውም 8.87 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡  የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት በ2009 ዓ/ም የሰጡት የብድር መጠን 32.3 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን ፣ በ2008አ/ም 25.2 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ በተመሳሳይ በ2009 ዓ/ም 26.3 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ሲያሰባስቡ በ2008አ/ም 18.43 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ ከእነዚሁ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት ከፍተኛውን ብድር የሠጡትና ተቀማጭ ገንዘብ የሠበሰቡት ውስጥ የአዲስ፣ የደደቢት፣ የኦሞና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቆማት የአንበሳውን ድርሻ  ተቀራምተወል፡፡ ከ35ቱ ተቆማት ውስጥ የ85 በመቶ ድርሻ  በመያዝ ዘርፉን በበላይነት የሚመሩት እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች የገንዘብ ተቆማት የሆኑት ያለተቀናቃኝ ህብረተሰቡን በመበዝበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡  የወጣቶችና ሴቶች ማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት  በማቆቆም፣ ያለውን የህወሓት/ኢህአዴግ ማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት የፖለቲካ ድርጅቶች የፋይናንስ ዘርፍች  በመውረስና በማስፋፋት ለ30 ሚሊዮን ወጣቶችና ሴቶች ዘለቄታዊ የሥራ ዕድል መፍጠርና የገቢ ምንጫ በመሆን እንዲቀጥል ማድረግ፡፡

በኢትዮጵያ ጉዲፈቻ ህፃናት፣ የወጣቶችና የሴቶች ህይወት

{1} ኢትዮጵያዊያን ጉዲፈቻ ህፃናት፣ የህፃናቶች ፍርድ በጉዲፈቻ የህፃናቶች ለሸጡ ለተሰማሩ ኤጀንሲዎች፣በኢትዮጵያ የተቆቆሙ የሃገር ውስጥና የባህርማዶ የጉዲፈቻ/ማደጎ ህፃናት ኤጀንሲ ተመዘገበው ህጻናት ወደውጪ የላኩ ኤጀንሲዎች 7000 ህፃናት ያሉበት ደብዛቸው የጠፉ ልጆችን የላኩ ድርጅቶች ተጣርተው ለፍርድ ቀርበው እንዲጠየቁ ወንጀኛ ሆነው ከተገኙ ያላቸው ንብረት ተሸጦ ለወላጆቻቸው ካሣ እንዲከፈል፡፡ ‹የጉዲፈቻ መርማሪ ኮሚሲዮን እንዲቆቆም› ከሃገር ውጪም ህጋዊ በሆነ መንገድ ህፃናት በጉዲፈቻ ሲሰጡ ቆይቶል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ ከአፍሪካ ወደ 35 ሽህ ልጆች በጉዲፈቻ መሰጠታቸውንና ከእነዚህም መካከል 25 ሺዎቹ ከኢትጵያ መሆናቸው በህዝብ ተወካች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቆሚ ኮሚቴ የቤተሰብ ህግ  እንደገና ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ውይይት ላይ ተጠቁሞል፡፡›› ኅዳር 1/2010ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ መሠረት

 • 25,000 ህጻናት ልጆች በአማካኝ ከአንድ ሕፃን 20 ሽህ ዶላር ሽያጭ ቢሆን 500,000,000 ዶላር በ20 ብር ምንዛሪ ተመን በ10,000,000,000 ቢሊዮን ብር ህፃናት ተሸጠዋል፡፡
 • 25,000 ህጻናት ልጆች በአማካኝ ከአንድ ሕፃን 30 ሽህ ዶላር ሽያጭ ቢሆን 750,000,000 ዶላር በ25 ብር ምንዛሪ ተመን በ18,750,000,000 ቢሊዮን ብር ህፃናት ተሸጠዋል፡፡

የጉዲፈቻ/ማደጎ ህፃናት ሽያጪ፤የጦር አበጋዞች ከማደጎ ህፃናት ሽያጪ የሚያግበሰብሱት የነፍስ ሽያጪ በተመለከተ ጥናቶች ያካተቱት መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 70 የውጪ ሃገር የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች በሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር Ministry of Women’s Affairs ፍቃድ ሰጪነት ተመዝግበው በመስራት ላይ ናቸው፡፡ በሃገራቶች መኃል የሚከናወነውን የጉዲፈቻ ሥነ-ስርዓት ከሚያቀላጥፉ ድርጅቶች/ ተቆማት መሃክል የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች፣ የግልና የመንግሥት ህፃናት ማሳደጊያ ድርጅቶች፣ ፍርድ ቤት፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የሚመለከታቸው ኢንባሲዎች፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ኢሚግሬሽን አውቶሪቲ፣ የፍትህ ሚኒስትር፣ የፖሊስ ኮሚሽን፣ እና የሃገር ውስጥ የመንግስት ባለስልጣናት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የጉዲፈቻ ሥነ-ስርዓት ያመቻቹ በዚህ የሙስና የተሠማሩ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ፡፡

{2} ከ18-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ወጣቶች ያሉበት የኢኮኖሚ ሁኔታ

ከ18-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ወጣቶች ብዛት በክልሎችና በከተማ መስተዳደሮችችና

የፈንድ ገንዘብ (ብር 10 ቢሊዩን) ድርሻ

ተ/ቁ ክልል/ከተማ ከ18-34 ዕድሜወጣት ብዛት ከጠቅላላ ወጣትያለው ድርሻ () ከብር 10 ቢሊዩንያለው ድርሻ
(1) (2) (3) (4= 3 x 10 ቢሊዩን
1 አፋር 618,827 2.06 206
2 ትግራይ 1,578,463 5.27 527
3 አማራ 8,024,773 26.79 2679
4 የኢትዩጵያ ሶማሌ 1,806,539 6.03 603
5 ኦሮሚያ 10,314,270 34.39 3439
6 ቤኒሻንጉልጉሙዝ 338,433 1.13 113
7 ደቡብ 5,643,731 18.82 1882
8 ጋምቤላ 150,414 0.50 50
9 ሐረሪ 80,259 0.27 27
10 አዲስ አባባ 1,255,486 4.19 419
11 ድሬዳዋ 164,762 0.55 55
ጠቅላላ ድምር 29,975,958 100 10 ቢሊዩን

ምንጭ፡- የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

 • ለኦሮሚያ ክልል ለ10,314,270 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ 3,439 ቢሊዩን ብር ብድር ተመድቦል፣ የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ 333 ብር ነው፡፡
 • ለአማራ ክልል 8,024,773 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ 2,679 ቢሊዩን ብር ብድር ተመድቦል፣ የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ 334 ብር ነው፡፡
 • ለሰላሣ ሚሊዩን ወጣቶች አሥር ቢሊዩን ብር ብድር ማለት 334 ብር የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ ነው፡፡ ከኢትዩጵያ ህዝብ 70 በመቶ ወጣቶች ስትሆኑ፣ መጪውን ህይወታችሁን ለማስተካከል የህወሓት ሥርዓት ለመገርሰስ ታገሉ፡፡

በሃረሪቱ በተቀሰቀሰ ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ ተጋድሎ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ውድ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩት ቆስለዋል በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ለወህኒ ቤቶች ተሰቃይተዋል፣ ሰማንያ ስምንት ሽህ ዜጎች ሃገር ጥለው ተሰደዋል፡፡ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ የነፃነት ታጋዩች፣ ጠመንጃ የታጠቁ፣ክላሸን ኮቨ ያነገቡ፣ መትረየስ የደገኑ፣ ላውንቸር የተሸከሙ፣የእጅ ቦንብ የታጠቁ፣ የወያኔን ቅጥረኛ ሠራዊትን እነ ዝናር በቅፊን ድባቅ እየመቱ እብስ ማለት ጀምረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ያስደነገጠው የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት በየክልሎቹ ወጣቶቹን እየሰበሰቡ የሥራ እድል ልንከፍትላችሁ ነው!!! ህይወታችሁን ሥርታችሁ ትቀይራላችሁ!!! ‹‹ፀረ ህዝብ›› ኃይሎችን አትቀላቀሉ!!! መንግሥት ለወጣቶች አሥር ቢሊዩን ብር የብድር በጀት በመመደብ ወጣቶቹን ለመደለል በመሞከር ላይ ናቸው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ዳግም ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጅ የወጣቱን ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ ተጋድሎ ለማፈን እየጣረ ይገኛል፡፡

 

{3} የኢትዩጵያ የቤት ሠራተኞች ዜጎች ስደት Migrant Domestic Workers

የሰራተኛና ማህበራዊ ኑሮ ጉዳይ ሚኒስቴር ( MoLSA Ministry of Labour and Social Affairs) በተገኘው መረጃ መሠረት በኢትዩጵያ በአምስት ክልሎች ወደ ውጭ አገራቶች የፈለሱ የቤት ሠራተኞች ብዛት በአራት ዓመት ከ8 ወራቶች ውስጥ ያለውን ህጋዊ የቤት ሠራተኞ ስደተኞችን በግል ሠራተኛ ቀጣሪ ኤጀንሲዎች( PEAs Private Employment Agencies) አመቻችነትና የሰራተኛና ማህበራዊ ኑሮ ጉዳይ ሚኒስቴር አፅዳቂነት የተላኩ ኢትዩጵያዊያን ናቸው፡፡

Table 1:- Number of migrant domestic workers from five regions for 4 years and 8 months time

Region 2008 Sept.-2009 August 2009Sept.- 2010 August 2010Sept.-2011 August 2011Sept.-2012June 2012 July-2013 February Total 
Tigray  949 573 1,582 8,592 4,966 16,662
Amhara  3,551 1,952 10,769 62,836 33,831 112,939
Oromia  3,600 2,757 10,430 64,431 39,185 120,403
SNNP 1,981 1,300 4,547 23,392 13,813 45,033
Addis Ababa 7,251 6,860 11,813 26,774 11,472 64,170
Total  17,332 13,442 39,141 186,025 103,267 359,207

 

በግል ሠራተኛ ቀጣሪ ኤጀንሲዎች የሠራተኛ ቅጥር ፎርም በማስሞላት፣ከኤጀንሲው ጋር የሚላኩት የቤት ሠራተኞች በመፈራረም፣  የቤት ሠራተኞች ወጪ በመሸፈን፣የቪዛ አገልግሎት ለሚሄዱበት አገር በመክፈል፣ደርሶ መልስ የዓየር ትኬት በመቁረጥ፣የመኖሪያ ፍቃድና የሥራ ፍቃድ ክፍያና ዋስትና ሽፋን (ኢንሽራንስ)በመግባትየመሳሰሉት ወጪዎች በኤጀንሲው ይሸፈናሉ፡፡ ቀጥሎ ያለው ሠንጠረዥ ከኢትዩጵያ ወደ አረብ አገራቶች የፈለሱ የቤት ሠራተኞች ብዛት ያሳያል በዚህም መሰረት ሳውዲ አረቢያ 76 በመቶ እጁን ሥትይዝ በመቀጠል ኩዌት 24 በመቶ የቤት ሠራተኛ እንደቀጠሩ ማስረጃው ያሣያል፡፡

Table 2:- The number of migrant domestic workers to the Gulf from September 2008 to February 2013

Country 2008 Sept.-2009 August 2009Sept.-2010 August 2010Sept.-2011 August 2011Sept.-2012June 2012July-2013 February Total 
Saudi Arabia 9,399 2,395 13,446 158,959 92,691 276890
Kuwait 6,976 10,837 25,457 28,476 11,440 83186
Dubai  113 142 510 321 0 1086
Others 905 19 115 175 59 1273
Total 17,393 13,393 39,528 187,931 104,190 362435

 

ኢትዩጵያ የሠራተኛ ስምምነት የፈረመችው ከኩዌት ጋር ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ሳውዲ አረቢያ በቀን 1500 የቤት ሠራተኞች በቀን የምትወስደው አገር የሠራተኛ ስምምነት ጥያቄን ውድቅ በማድረግ ለመፈረም አሻፈረኝ ብላ ቆይታለች፡፡ የዜጎች ሞት፣በአመዛኙ እራሳቸውን የማጥፋት ስበብ/ምክንያት፣የወሲብ ትንኮሳ፣ የሥነ-ልቦና ቀውስ፣ የአካል ጉዳት ስቃይ ለመከታተል፣ የኢንባሲዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድጋፍ ይጠይቃል፡፡

ኢትዩጵያ መንግስት ከሳውዲ ዓረብያ በግፍ የተባረሩ ከ150 ሽህ ዜጎች ሠራተናችና ስደተኞች እንደ አውሬ እየታደኑ መባረራቸው የቅርብ ግዜ ትዝታ ነበር፡፡ የህወሓት መንግሥት ከኩዌት፣ከ£ታርና ከዩርዳኖስ መንግስታት ጋር የቤት ሠራተኞች ለመቅጠር የሁለትሽ የሥራ ሥምሪት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ለኢትዩጵያውያን ትልቅ ገበያ የሆኑትን ሳውዲ አረብያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አገራቶች የህወሓት መንግስት ሹማምንቶች በማማለልና በመደለል ላይ ይገኛሉ፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች ልጆቻቸውን ወደ ባህር ማዶ አገራቶች ዶላር ከፍለው እያስተማሩ ሌሎቹን የእንጀራ ልጆች አረብ አገራት በቤት ሠራተኝነት ስራ አሰማርተው እነሱ ወደሃገር ቤት ለዘመዶቻቸው የሚልኩትን ዶላር የሃገሪቱ ትልቁ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ፣ የሃዋላ ገቢ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ከውጪ የሚላክ ገንዘብ/ ሃዋላ ከሃገሪቱ ከምታገኘው የውጪ ንግድ መብለጡን ይታወቃል፡፡ ዲያስፖራው በእጁ ላይ ያለውን የገንዘብ መብት በመጠቀም የህወሓት መንግስትን መቅጣት ችሎል፡፡

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት  ወደ ውጭ አገራቶች የቤት ሠራተኞች በብዛት በመላክ የውጪ ምንዛሪ ያግበሰብሳል፡፡ በኢትጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ሐዋላ ፍሰት ከመደበኛ (ህጋዊ) በሆነ መንገድ (መኒ ግርሃም፣ ዌስተርን ዩኒየን፣ድሃብሽን ወዘተ) እንዲሁም በአመዛኙ መደበኛ ባልሆነ (ህገወጥ) መንገድ የውጪ ምንዛሪ ውጭ ካሉ ዜጎቹ ይሰበስባል፡፡ ከ2008 እስከ 2013 እኤአ ከአረብ ሃገራት ከሚኖሩ 362435 የቤት ሠራተኞች፣ ኢትዬጵያዊያን ነዋሪዎች /ዲያስፖራ/ ሃገር ቤት ላሉ ቤተሰቦችና ዘመዶች በመኒ ግርሃም፣ ዌስተርን ዩኒየን፣ድሃብሽን ወዘተ የላኩት ዶላር በኢትዩጵያ ባንኮች ገቢ ሆኖ ባንኮቹ ለዘመዶቻቸው በብር ይሠጡላቸዋል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት   የቤት ሠራተኞች ወደ አረብ አገራቶች በመላክ ሠራተኞቹ ለወላጆቻቸው ውጭ የሚልኩት ዶላር (ሃዋላ) ትልቁ ገቢው ነው፡፡

አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ታህሥስ 17 ቀን 2009ዓ/ም ‹‹ምጣኔ ሃብት ሲያድግ ስደት ለምን?›› በሚል ርዕስ በኢትዩጵያ በዓመት ከአንድ ሽህ ዜጎች መካከል ዘጠኙ ወደ ሌሎች አገራት ይሰደዳሉ፡፡ በ2015እኤአ በኢትዩጵያ የሥነ-ህዝብ  ቁጥር  99,465,819 ሚሊዩን ውስጥ 895,192 ሽህ ህዝብ በዓመት እንደሚሰደዱ ተገልፆል፡፡ በአይኦኤም መረጃ የሚያመለክተው፣ በህጋዊና ህገወጥ መንገድ 8 ሽህ ህዝብ በየዓመቱ ይሰደዳል፡፡ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር ወልዳይ አምሃ እራሳቸው በጀርመን ሃገር ተሰደው ለስደተኞች የሚሰጥ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ተቀብለው ወደ ሃገር ቤት የገቡ ምሁር ናቸው፡፡ አሁን በስርአቱ ተጠቃሚ ሆነው ፎቅ ገንብተው ሆቴል ቤት ከፍተዋል፡፡ የኢትጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበርን ለህወሓት መንግስት አጎብዳጅ እንዲሆን ያደረጉ ካድሬ ናቸው ስለስደት ጥናት የሚያደርጉት፡፡ በኢትጵያ ውስጥ በየዓመቱ ሁለት ሚሊዩን ታዳጊዎች ወደ ወጣት የዕድሜ ክልል ይገባሉ በዚህም የተነሳ 1.4 ሚሊዩን ወጣቶች አዲስ የስራ እድል ሊከፈትላቸው ይገባል ማለት ነው፡፡ ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አሳየች የምትባለው ሃገር የስደት ችግርን ለመፍታት አቅቶታል፡፡  

Population  99,465,819, and expected to be 120 million in 2030 (CIA Fact book, August 2015)

ከዓለም ባንክና ከኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር በመተባበር የተሰናዳው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት መሠረት ‹‹በፋይናንስ ረገድ በተለይ በባንክ አገልግሎት እንዲሁም በመድህን ሽፋን አኮያ በተደረገው ጥናት  መሠረት በአገሪቱ መደበኛ የፋይናንስ ተቆማት ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች ብዛት 22 በመቶ ብቻ ናቸው፡፡ (ማለትም ከ100 ሚሊዩን ህዝብ ውስጥ 22 ሚሊዩን ህዝብ የባንክና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው፡፡) ይህም ሆኖ የመንግስት ባንኮችና አነስተኛ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰቱ ሆነው ሲገኑ፤ለቁጠባም ትልቁን ድርሻ የሚይዙት እነዚሁ ድርጅቶች ሆነዋል፡፡ 32 በመቶ ግለሰቦችና 48 በመቶ ቤተሰቦች እንደየአቅማቸው የቁጠባ ልምድ እንዳላቸው ተመዝግቦል፡፡ ይሁንና በአገር አቀፍ ደረጃ 600 ብር ለመቆጠብ አቅም ላቸው ሰዎች ብዛት ከ30 በመቶ ያልበለጠ ሆኖል፡፡››

በኦሮሚያና በአማራው ክልሎች በሌሎችም ክልሎች በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ከባህር ማዶ ሃገራት ከሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን ሰደተኛች በቤተሰቦቻቸውና በዜጎች ላይ ለደረሰ የህይወት መሰዋትነት፣ እስራት፣ስደትና ንብረት መውደም ያደረጉት ድጋፍ፣ በ2008ዓ/ም ከውጭ የተላከ የገንዘብ 4 ቢሊዩን ዶላር መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦል፡፡ ይህም የውጭ ሃዋላ አገሪቱ ከውጪ ንግድ ካገኘችው 2.86 ሚሊዩን ዶላር 71.5 በመቶ  ብልጫ እንዳለው ተስተውሎል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ላይ በተደረገ ዓለም አቀፍ የሃዋላ እቀባ ፕሮግራም የተሳካ እንቅስቃሴ አሳየረቶል፡፡ ወያኔ በኢኮኖሚ እንዳያንሰራራና በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲወድቅ እያደረገው ይገኛል፡፡ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን ይሄን የመንግስት የገቢ ምንጭ እስካደረቁ ድረስና በሌላ መንገድ ገንዘብ በመላክ ዘዴ እስከተጠቀሙ ድረስ፣ ህዝባዊውን ትግል ማበቡ አይቀሬ ሆኖል፡፡ ስለዚህ  የውጭ ሃዋላ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የተለያዩ ዘዴዎችን በመፍጠር የሙሰኞችን መንግስትን የውጪ ምንዛሪ ገቢ ለማድረቅ መሞከርና ልዩ ልዩ ዘዴዎች በመፍጠር ወገኖቻቸውን መርዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  

በአጠቃላይ ወጣቶች ለህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተራ ፕሮፓጋንዳ ሳይወናበድ ህዝባዊውን እንቢተኛነትና ተጋድሎ በመቀጠል ነፃነቱን መቀዳጀት የግዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ የወያኔ ፋሽስታዊ ሥርዓት መውደቁ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ወያኔ በሙስናና በህዝብ ደም የተጨማለቀ የሽፍታ መንግሥት ነው፡፡ ወያኔ በመንግስት መዋቅር በመጠቀም፣ ኢፈርት፣ሜቴክ፣ሜድሮክ፣ ወዘተ በአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ የወያኔ ጀነራሎች፣ ባለሥልጣኖች፣ ዲፕሎማቶችና የጊዜው ባለፀጎች በዘረፉት ገንዘብ ፎቅ በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ የህዝብ መሬት  ነጥቆና ዘርፎ በጨረታ በመሸጥ በግፍ የተገነባ ሁሉ ነገ በህግ ፊት የህዝብ ኃብት መሆኑ መጠራጠር የለብንም!!! ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ሸበጥ ተጫምቶና ቁምጣ ታጥቆ እንደመጣ ህዝብ ያውቃል ሌላ ምንም ንብረት አልነበራቸውም፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ዳግም ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጅ የወጣቱን ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ ተጋድሎ ለማፈን እየጣረ ይገኛል፡፡

 

ትላንት ወያኔ በሠላማዊ ሠልፍ ስናረግ የአጋዚ ጦር ገድሎናል!!! ሠላማዊ ሠልፍ በቃ!!! የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ውጤታማ ሆኖል!!! ቀጣዮ የመንገድ መዝጋት ዓይነት ድልድይ መስበር፣ የኢፈርት ፋብሪካዎችን የመብራት ትራንስፎርመሮችና የከፍተኛ ኤሌትሪክ ዥረት ቆት ተሸካሚ ምሶሶዎችን በማጋየት የወያኔ/ኢፈርትን ኢኮኖሚ ድባቅ በመምታት ብቻ ወያኔ እጅ እንደሚሠጥ የአገር ሽማግሌዎች ለህወሓት /ኢህአዴግ መንግሥትን እንዲያማልዱን ይህችን ደብዳቤ ልከናል!!! አማረ አረጋዊ፣ በሪፖርተር ጋዜጣ አትመህ አድርስልን አደራ!!! ወያኔ የታገለው በወጣትነት ህይወት ጨልሞበት፣ ኑሮ መሮት አይደለም እንዴ? አንድ ሽህ አንድ ጥያቄዎች በየመድረኩ ጠይቀናል? መልስ የለምበባርነት ለ27 ዓመታት ከመኖር፣ የአንድ ቀን ነፃነት ብለናል፡፡  ‹‹አንበሣ ምን ይበላል? ‹ተበድሮ› ምን ይከፍላል? ‹ማን ተናግሮ!!!›› ተረት እያወጋችኝ አሳደገችኝ እማምዬ፡፡

ወጣት የነብር ጣት!!! እኛ ወጣቶች ዘረኞች አይደለንም፣ አንድ ዘር ለይተን የማጥቃት ባህሪይ የለንም፣ የሃይማኖትና የዘውግ ልዩነታችን ውበታችን ነው፡፡ ሃገራችንን እንወዳለን፣ ይሄን ለማድረግ የተገደድነው መኖር ስላልቻልን ነው!!! ወያኔን ለ27 ዓመታት ታገስን!!!  የወጣትነት እድሜችን አለፈ!!! እኛም እንደሰው አግብተን ወልደን መኖር እንፈልጋለን! ዮኒቨርሲቲ ጨርሰን ሥራ አጥ ሆነን ኮብል ስቶን ጠርበን ኖርን፣ እሶም እንጀራ ሆን ጠፋች፡፡ ትግላችን የኢኮኖሚ የዳቦ ድርሻ፣ ጥያቄ ነው፡፡ ፍትሃዊ የኃብትና ንብረት ክፍፍል እንዲኖር፣ ግልፅነት፣ እኩልነትና፣ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን እንሻለን፡፡ ኢኮኖሚ የፖለቲካ ነፀብራቅ ነውና፣ ከአሁን በኃላ የኢኮኖሚ ጥያቄችን ከፖለቲካ ጥያቄን ጋር አንግበን ከሥልጣን መንበራችሁ ልቀቁ የሽግግር መንግሥት ይቆቆም ብለናል!!! ዛሬ ለነፃነትህ ዱር ቤቴ ብለህ የነፃነት ኃይሎችን የተቀላቀልክ ወጣት ነገ ሆ ብለህ በድል መግባትህን ለቅንጣት ያህል አትጠራጠር፡፡ በሃገራችን ዝናብ ሲጥል ሲንጠባጠብ፣ ብሎም ሲያካፋ፣ ዶፉ ሲከተል፣ ከጠቡታ ውኃ ወደ ጎርፍ፣ ብሎም የወንዝ ሙላት፣ ገዛፊ ፈረሰኛ ውኃ፣ ሱናሚ የምድር መጥለቅለቅ፣ የዓባይ ወንዝ ሙላት እንኮን ለሃገር ለኑብያ፣ ለምስር ይተርፍ አይደል፡፡ ለዚህ ነው ወጣት የነብር ጣት!!! አበው የሚሉት ዛሬ ትንሽ ሆኖ የተጀመረ ትግል ነገ እልፍ አዕላፍ እንሆናለንና በትግሉ እንፅና፡፡ በጎበዝ አለቃህ በቄሮ፣ በፋኖ፣ በዘማር፣ በአቦሸማኔ፣በአናብስት እየተመራህ ብሄራዊ የዜግነት ክብርህን ትቀዳጃለህ፡፡ ወጣቶች ከነፃነት ምሽጋችሁ ሆናችሁ፣ ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ …..ላንቺ ነው!!! እየዘመራችሁ፣ ድቅድቁ ጨለማ ሲረታ፣ የጎህ ብርሓን ሲቀድ ከሩቅ ይታያልና!!!  አንዳርጋቸው ፅጌን ሳናስፈታ አናሸልብም !!!

 

 

‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በህዝብ ትግል ይከሽፋል!!!

የሽግግር መንግሥት ይቆቆም!!!

ክብር ለወደቁ የኢትዩጵያ አርበኞች!!!

በለውጥ ማዕበል ውስጥ የምትናወጠው የኢህአዴግ መርከብ! (ዳዊት ከበደ ወየሳ)

The TPLF ship is sinking.

ኢትዮጵያዊነት ሞቶ ፍታት እየተደረገለት ነው ከሚባለው ኦሮሚያ ምድር፤ የአዳዲሶቹን መሪዎች ንግግር እየሰማን ቀልባችን ወደነሱ መሳብ ከጀመረ ሰነባበተ። ህዝቡ ይህን ያህል ስሜት ሰጥቶ ሊሰማቸው የቻልንበት ዋና ምክንያት ደግሞ፤ ሲባልለትና ሲጮህለት የነበረውን ኢትዮጵያዊነት ካልጠበቀው ወገን፤ ጎልቶ እና ጎልብቶ ይሰማው ስለጀመረ ነው። እናም ይህን መልካም ጅምር የሚቃወም አንደበት ባይኖረንም፤ አሁንም ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎችን ግን ደጋግመን ማንሳታችን የማይቀር ነው። ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎችና ያልታበሱ እንባዎች አሉ። እርግጥ ነው… ዛሬ ከኦህዴድ/ኢህአዴግ አመራሮች የምንሰማቸው የኢትዮጵያዊ ማንነት ዘርፈ ብዙ ትንታኔዎች፤ “ምነው እስከዛሬ የት ነበራቹህ?” እያልን እንድንቆጭ ማድረጉ አልቀረም። የነዚህ በሳል ኢትዮጵያውያን ንግግም… የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ እድሜ ልኩን እየተፋጨ እና እየተጋጨ እንዲኖር ይፈልጉ ለነበሩት ወገኖች፤ ልብ የሚያስከፋና አንገት የሚያስደፋ ሆኗል።

በዳዊት ከበደ ወየሳ

ከአስርቱ ቃላት አንዱ… “ግብዝ አትሁን!” ይላል። ዛሬ እነዶ/ር አብይ አህመድ ለምታደርጉት መልካም ንግግር፤ ከመቀመጫችን ብድግ ብለን ልናጨበጭብላቹህ እንችል ይሆናል። ነገር ግን የመጣችሁበት እና ከዚህ ያደረሳችሁን ኢህአዴጋዊ መንገድ ስለምናውቀው፤ ከጭብጨባ አልፈን፤ እየሰመጠች ባለችው የኢህአዴግ መርከብ ላይ ለመሳፈርም ሆነ በምትሄዱበት መንገድ ለመሄድ የሚቸገሩ ብዙ ናቸው። በጌተሰማኒ ኢየሱስን አቅፎ ከሳመው በኋላ ምሽቱን የከዳው የአስቆሮቱ ይሁዳና ኢህአዴግ ተወራራሽ ጸባይ ስላላቸው፤  መቼ ልትከዱን እንደምትችሉ አናውቅምና፤ በግብዝነት ተሞጋግሰን፤ ይሄም ቀን አልፎ እንዳንተማማ… ለግዜው እሩቅ ለሩቅ ሆነን የሆድ የሆዳችንን እንጨዋወት።

እንደእውነቱ ከሆነ… ዛሬ እናንተ የምትናገሩትን የኢትዮጵያዊነት መልዕክት፤ ትላንት በተለያዩ መድረኮች የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ይናገሩት የነበረ በመሆኑ፤ ለብዙዎች አዲስ ነገር አይደለም። አዲስ የሆነብን ነገር… ኢትዮጵያዊነትን እንዲጠሉና እንዳይቀበሉ ብዙ ስራ ከተሰራበት የኦሮሚያ ምድር፤ ጥቂት የኦሮሞ ልሂቃን ከያላችሁበት ብቅ ብቅ ብላቹህ፤ ስለኢትዮጵያዊነት ስትመክሩ እና ስትመሰክሩ መስማታችን ነው። በዚህ ኢትዮጵያዊነት እንደቀጭን ፈትል እየሰለለ መጥቶ ሊበጠስ በተቃረበበት ዘመን፤ እነሆ ከናንተ አንደበት ስለኢትዮጵያዊነት መስማት… እንደመልካም ሙዚቃ፤  ደስ የሚያሰኝ እና የማይሰለች ሆኖብናል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ እና ተሰምቶ በማይታወቅ ደረጃ፤ አንድ በስልጣን ላይ ያለ መንግስት አንደኛው ህዝብ በሌላኛው እንዲነሳሳና እንዲጠላው፤ በሃይማኖት ልዩነት አንደኛው ሌላውን በጥርጣሬ እንዲያየው የሚያደርግ ስራ የሰራ ብቸኛ አካል ቢኖር ኢህአዴግ ብቻ ነው። ከኢህአዴግም ደግሞ ይህንን የ“ከፋፍለህ ግዛ!” ስልት በመጠቀም ግንባር ቀደም ሚና የተጫወተው ህወሃት ወይም የትግራይ ወያኔ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በተለይ ኦሮሞው በአማራ ላይ እንዲነሳ እና እድሜ ልኩን አማራውን እየወቀሰ እና እያለቀሰ እንዲኖር ሰፊ ዘመቻ ሲሰራ ቆይቷል።

የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ አንድነት ታሪክ ውስጥ ሰፊ ድርሻ ያለው ህዝብ ቢሆንም፤ ይህንን ታሪክ በመሰረዝና በመደለዝ፤ የኦሮሞ ህዝብ በአማራ ህዝብ ሲጨቆንና ሲገደል እንደነበር ተደርጎ በተደጋጋሚ ተለፍፏል። በትምህርት ቤት ጭምር የኦሮሞ ልጆች እንዲህ አይነት የጥላቻ ታሪክ እንዲማሩ ተደርጓል፤ እየተደረገም ነው። የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በአማርኛ ቋንቋ እንዳይግባባ፤ ፊደሉንም እንዳይማር ተደርጓል። ለ27 አመታት በተደረገ የጥላቻ ፖለቲካ ምክንያት… የኦሮሞ ህዝብ እንኳንስ በአማርኛ ሊጽፍ ቀርቶ፤ በአማርኛ የተጻፉ ታሪኮችን ቀዳዶ የሚጥል፤ እንኳንስ የአንድነት ታሪኩን ሊያነበው ቀርቶ፤ በአንቀጽ 39 ቀቢፀ ተስፋ አገሩን በሃሳብ ሲገነጣጥል የሚውል አዲስ ትውልድ ለማፍራት፤ በህወሃት በኩል የማያቋርጥ ዘመቻ ሲደረግ እንደነበር የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ካለ፤ በራሱ ታሪክ ላይ ተኝቶ ሲያበቃ ገና አሁን ከእንቅፉ የባነነ ምስኪን መሆን አለበት።

ስለኢትዮጵያ ክብር አድዋ ድረስ ዘምተው ደረታቸውን ለጣልያን ጥይት የሰጡት፤ የፊታውራሪ ገበየሁ አባጎራው እና የኦሮሞ ፈረሰኞች ታሪክ፤ የነፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግሴ እና የነባልቻ አባነፍሶ ገድል በኦሮሚያ ምድር አይነገርም። በ19ኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞን ህዝብ ከዳር እስከዳር  አንድ ያደረጉት፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉት ራስ ጎበና ዳጨ… እንደከሃዲ እንጂ፤ እንደጀግና ክብር አልተሰጣቸውም። የ“ኦሮሞን ህዝብ አትንኩ!” ብለው፤ ህዝቡን ለመከላከል በእምባቦ ጦርነት ትልቅ ትግል ያደረጉት አጼ ምኒልክ… እንደወራሪ እንጂ እንደኦሮሞ ህዝብ ወዳጅ ተደርገው ሲቀርቡ ከቶውኑ በኦሮሚያ ምድር ላይ አንሰማም። የሌሎች አገር ዜጎችን በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ስር በማሰባሰብ በጣልያን በርሃዎች በመዋጋት፤ አለምን ያስደነቀው ጀግናው አብዲሳ አጋ በተወለደበት የወለጋ ምድር ሃውልት አልቆመለትም። እነደጃዝማች ገረሱ ዱኪ፣ እነአቢቹ፣ እነጄነራል ጃጋማ ኬሎ፣ የነጄነራል ሙሉጌታ ቡሊ… የኦሮሞ ምድር ያፈራቸው፤ ለኢትዮጵያ አንድነትና ፍቅር ከፍ ያለ ስራ ሰርተው ያልፉ ጀግኖች፤ ዛሬ መልካም ስማቸውና ስራቸው በኦሮሚያ ክልል አይዘከርም።

በአጠቃላይ… በዘር ተደራጅቶ ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ እንዲያስብ፤ ለ27 አመታት ኢትዮጵያዊነትን እንዲጠላ ትምህርት ሲሰጠው የነበረው የኦሮሞ ህዝብ፤ እንኳንስ የሌላውን ሊያደንቅ ቀርቶ የራሱንም ጀግኖች እንዳያውቅ እና እንዳይመርቅ ተደርጎ፤ በጨለማ ውስጥ እንዲኖር ለማድረግ ህወሃት ቀዳሚውን ሚና ተጫውቷል። ከነሌንጮ ለታ እስከነሃሰን አሊ ድረስ፤ በዘር መስመር ወደታች የሚያስብ እንጂ በኢትዮጵያዊነ መንፈስ ስለአንድነት የሚሰብክ አንድም የኦህዴድ ባለስልጣን ሳናይ፤ እነዶር መረራ እና በቀለ ገርባን እያደነቅን ብዙ አመታት አስቆጠርን።

በአንድ ወቅት አባ ዱላ ገመዳ ላይ የሆነውን ጉዳይ በዚህ አጋጣሚ እንጨዋወት። አባዱላ ገመዳ ሰፊ የኦሮሞ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት፤ ወደ ሰላሌ ይዘልቃል። የሰላሌ ኦሮሞ በባህሉ መሰረት ለአባ ዱላ ገመዳ አስፈላጊውን አቀባበል አደረገለት። ከደብረሊባኖስ ማዶ “ሽንኩርት ሚካኤል” የተባለችው መንደር በአባ ዱላ ገመዳ ድግስ ደመቀች። የአገር ሽማግሌዎች ምርቃት አደረጉ። በሬ ታረደ፤ ጠጅ ተጠጣ። ደስታ በደስታ ሆነ። በመጨረሻም ጭፈራ ተጀመረ። ይሄን ግዜ ኢጆሌ ሰላሌ ፈረሱ ላይ ሆኖ ዳንጋላሳ እያረገ… “ያ ሆ!” ይል ጀመር። አባዱላ ገመዳን የሚያሞግስ ዘፈን እና ጭፈራ ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ…

“ያ መረራ… ኦ!

ያ በቀለ ገርባ… ሆ!” እያሉ ዘፈን እና ጭፈራውን፤ ሽለላ እና ሙገሳውን በቦታው ላልተገኙት፤ ከቶውኑም ላልጋበዟቸው፤ ነገር ግን ለሚወዷቸው ሰዎች ሰጡ። ይሄ ከሆነ ጥቂት አመታት ተቆጠረ። እኛን ፈገግ አሰኘን፤ ለኦህዴድ የኦሮሞ ባለስልጣኖች ግን ትምህርት ሰጥቶ አለፈ።

እናም ይሄ ሁሉ ሆኖ… በኦሮሚያ ላይ ከተዘራው የአረም እርሻ ፈንጠር ብለው፤ እነበቀለ ገርባና እነዶ/ር መረራ ጉዲና መብቀላቸው ደስ የሚለንን ያህል፤ እንደነለማ መገርሳ እና ዶ/ር አብይ አህመድ አይነት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዘረኝነት አረም መሃል እንደዋርካ ዛፍ በቅለው፤ ከስር የበቀለውን የዘረኝነትን አረም ሲያቀጭጩት ማየት፤ በመንፈስም ሆነ በስጋ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል።

ዛሬ እነዶ/ር አብይ አህመድ የሚናገሩትን አይነት የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተላበሰ ንግግር ከአማራ፣ ከትግራይ ነጻ አውጭዎች ወይም ከኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች አንሰማም። ይልቁንም የሁለቱ ህዝቦች ቄሮዎችና ፋኖዎች በደም ያስተሳሰራቸውን መሃላ ፈጽመዋል። እናም የኦሮሞ ልጆች ደም ሲፈስ፤ የአማራ ህዝብ ተቆጥቶ… “የኦሮሞ ህዝብ ደም፤ ደሜ ነው!” ሲል፤ አማራው ሲገደል ደግሞ… “የአማራው ህዝብ ደም፤ ደሜ ነው!” የሚል ሞጋች ትውልድ ተፈጥሯል። እንዲህ አይነቱ የህዝብ ለህዝብ መደጋገፍ ጥንትም የነበረ ኢትዮጵያዊነት ቢሆንም፤ ሌላውን በማጣላት… እሱ ዳኛ ሆኖ መሰንበት የሚፈልገውን ህወሃት ግን ትልቅ የትውልድ መርዶ ነው የሆነበት።

እንግዲህ በዚህ ሁሉ ምስቅልቅል መሃል ነው… በኦሮሚያ ጥሻ ውስጥ የተጣለውን ኢትዮጵያዊነት አንስተው፤ በአንድነታችን ላይ ላይ የተጋረጠውን ጥቀርሻ አጽድተው ወደፊት ለመሄድ የተዘጋጁ አፍላ ጉልበት እና ጎምቱ እውቀት ያላቸውን የኦሮሞ ልጆች ለማየት የበቃነው።

በአጠቃላይ… የአማራ፣ የትግራይ፣ የደቡብ እና ሌሎች የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች በዘር ላይ ያነጣጠረ ፖለቲካዊ አደረጃጀት ይዘው፤ ህወሃትን በማስደሰትና በማሸርገድ መሃል ዥዋዥዌ ሲጫወቱ፤ ኢትዮጵያዊነት ሞቶ ፍታት እየተደረገለት ነው ከሚባልለት ኦሮሚያ ምድር፤ የኢትዮጵያን ትንሳዔ መስማት እኛን የሚያስደስተንን ያህል፤ ጥቂቶችን ህወሃትን ብቻ ሳይሆን፤ በህወሃት ሳንባ የሚተነፍሱትን ጥቃቅን ነፍሳቶች ጭምር ሊያስኮርፋቸው እንደሚችል ይታወቃል።

ይህ የኢትዮጵያዊነት ትንሳዔ… ለህዝብ መነሳሳት የሚሰጠው ፋይዳ ከፍተኛ ቢሆንም፤ “የህዝቡ ጥያቄ ተመልሷል፤ እንባውም ታብሷል” ማለት ግን አይደለም። ላለፉት 27 አመታት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተሰራው በደል እና ግፍ አደባባይ ወጥቶ በዳይ እና ተበዳይ ይቅር መባባል አለበት። እርግጥ ነው፤ እርቅና ሽምግልና አራራ እና ጃርሱማ በአማራ እና በኦሮሞ ባህል ይዘወተራሉ። ለሰላም እና ለእርቅ እራሱን የማያዘጋጅ የሰዎች ስብስብ በህገ አራዊት የሚመራ ኋላቀር በመሆኑ፤ ይህንን መልካም ባህል እንደህወሃት ላሉ የራስን ህዝብ ጠላት አድርገው በቂም በቀል መቅጣት ለሚፈልጉ ድርጅቶች ጭምር ማስተዋወቅ ያስፈልጋል።

እኛም የኦቦ ለማ መገርሳንና ዶ/ር አብይ አህመድን ንግግር በሰማን ቁጥር፤ ኢትዮጵያውያንን ወደ ብሄራዊ እርቅ የሚወስደው መንገድ ከርቀት ሊታየን ይችል ይሆናል። ይህ ማለት ግን “ኢህአዴግ ያደረሰብንን በደል እንረሳው” የሚል ማዘናጊያ እንዳይፈጥርብን መጠንቀቅ አለብን። በዚህ ሁካታ እና ግርግር መሃል የስንትና ስንት ወገኖቻችን እንባ እና ደም ሊረሳን አይገባም። አሁን በተፈጠረው የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ላይ ቆመን፤ ብሔራዊ እርቅ የመናፈቃችንን ያህል፤ …የበደሉ በህግ የሚጠየቁበትን፤  የተበደሉም የሚካሱበትን መንገድ ማሰብ ይኖርብናል። ይህች ኢትዮጵያ ማለት… በህዝቦቿ ባህል እና ታሪክ የከበረች፤ “በአያቶቻችን ደም እና አጥንት፤ ጸሎት እና ጉልጥምት የተገነባች አገር ናት።” ከዚህ በኋላ የምትገነባው ኢትዮጵያ በደም ሳይሆን፤ መሰረቷን ህግ እና እርቅ ልታደርግ ይገባታል። ይህ በሆነ ግዜ… የኛ እና የነሱ፤ ብሎም የዚህ ትውልድ ታሪክ በወርቅ ቀለም ይጻፋል።

እስከዚያው ግን… በዚህ ሁሉ የለውጥ ማዕበል ውስጥ የምትናወጠው የኢህአዴግ መርከብ፤ በነለማ መገርሳ እና በነዶ/ር አብይ አህመድ ካፒቴንነት ከመስጠም ከተረፈች፤ እንደአንድ ጨዋ ኢትዮጵያዊ “እንኳንም እግዜር አተረፋቹህ!” የምንልበትን ቀን በመናፈቅ፤ ካልተመለሱ ህዝባዊ ጥያቄዎቻችን ጋር ዳግም እንደምንገናኝ በማሰብ፤ “ጋሪቲ” ብለን እንሰነባበት።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በምሁራን እና በፖለቲከኞች እይታ

በይርጋ አበበ/ ሰንደቅ

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በ2007 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ ካሸነፈ በኋላ በአገሪቱ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አውጇል። ከመስከረም 28 ቀን እስከ ሐማሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ለአስር ወራት በአገሪቱ ላይ ተጥሎ የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተነሳ በወራት ልዩነት አገሪቱ እንደገና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር እንድትመራ የሚያስችለውን ውሳኔ መንግስት ያሳለፈው ባሳለፍነው ቅዳሜ ረፋዱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

እንደ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ መግለጫም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውሳኔ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ተፈጻሚ ይሆናል። በስድስት ወራት ውስጥ የሚፈለገው ለውጥ ካልተገኘ ደግሞ እንደገና ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ይደረጋል።

“በአገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ በተለመደው የህግ አሰራር መምራት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ስለተደረሰ” መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ መገደዱን አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ አያይዘውም ውሳኔው አሁን ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ እንጂ ኢሕአዴግ ለ17 ቀናት ባካሄደው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባው ወቅት የተፈጠረው ችግር በ15 ቀናት ውስጥ እልባት ካላገኘ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ውሳኔ ላይ ደርሶ እንደነበር ገልጸዋል። አሁን በአገሪቱ ላይ የተጣለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳለፈው ዓመት ዝርዝር መመሪያ የወጣለት ባይሆንም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሊከለክል የሚችላቸውና ሊወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።

ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት በወሰደውን ውሳኔ “አልስማማም” አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል አቋሙን ገልጿል። ምሁራን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችም በዚህኛው ሃሳብ የሚስማሙ መሆናቸውን ተናግረዋል። ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ የሰጧቸውን መግለጫዎች ለአንባቢያን በሚመች መልኩ አጣምረን ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈላጊነት

በ1987 ዓ.ም የጸደቀው የአገሪቱ ህገ መንግስት በአንቀጽ 93 ቁጥር 1(ሀ) ‹‹የውጭ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን፣ ማናቸውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝቡን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፤ የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ስልጣን አለው›› ሲል ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ የሚዳርጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀምጣል።

በአሁኑ ወቅት የታወጀውንም ሆነ ቀደም ሰል በአገሪቱ ላይ ለአስር ወራት ታውጆ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ ምክንያት ሆኖ የቀረበው ‹‹ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን›› የሚለው ምክንያት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሰጠው የፕሬስ መግለጫ (ፕሬስ ሪሊዝ) ላይ ደግሞ ‹‹ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የተከሰተው አለመረጋጋት በህዝቦቻችን ደህንነትና በአገራችን ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል። ችግሩን ለመከላከልና ለመቀልበስም በተለመደው አሰራር እና አካሄድ ለመፍታት ጥረት ተደርጎ ባለመሳካቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ሁኔታዎች የመሻሻል አዝማሚያ አሳይተው የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ስርዓት አልበኝነት ተፈጥሮ የዜጎች ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ እየጠፋ እና ዜጎች ለዘመናት ያፈሩት ሀብት እና ንብረት በቀላሉ እየወደመ ይገኛል። ይህ አጠቃላይ ሁኔታ ህዝባችንና መንግስት ከሚሸከሙት እና ከሚታገሱት በላይ እየሆነ መጥቷል›› ሲል የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣለበትን ምክንያት ያስታውቃል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዚህ ምክንያት ከሆነ የታወጀው አገሪቱ ውስጥ ያለው የጸጥታ እና የዜጎች ህይወት ምን ይመስላል? የሚለውን ጥያቄ ለምሁራን አቅርበን ነበር። በአምቦ ዩኒቨርስቲ የማኔጅመንት መምህር የሆነው አቶ ስዩም ተሾመ ‹‹በህገ መንግስቱ አንቀጽ 93 በተቀመጠው መሰረት ካየነው በዚህ ወቅት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የሚያስችል ምንም ምክንያት የለም›› ሲል ተናግሯል። በአብዛኞቹ የአገራችን ክፍሎች የተነሱ ግጭቶችና ብጥብጦችም ቢሆኑ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንጂ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈልጋቸው አይደለም ይላል። ‹‹በአገራችን የተከሰተው ችግርም ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ኢህአዴግ የወሰዳቸው እርምጃዎች ድምር ውጤት ነው›› ያለው መምህር ስዩም፤ በ2007 ዓ.ም የተካሄደው ምርጫ ደግሞ ለችግሩ የመጨረሻው ምክንያት መሆኑን ተናግሯል።

በቅርቡ ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩሉ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለኢህአዴግ ጊዜያዊ እፎይታ ሊያስገኝለት ይችል ይሆናል እንጂ ዘላቂ መፍትሔ ግን ሊያመጣ አይችልም። ምክንያቱም ያለው ብጥብጥና ግጭት የጸጥታ ችግር ሳይሆን በኢህአዴግ ፊት ተጋርጦ ያለው የፖለቲካ ጥያቄ ነው። የፖለቲካ ችግር ደግሞ መፍትሔውም ፖለቲካዊ ነው›› በማለት ተናግሯል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አያይዞም በኢትዮጵያ የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአሜሪካ መንግስት እንደማይደግፈው የገለጸበትን መግለጫ በተመለከተ ‹‹የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚጠቅማትን ትክክለኛና ወቅታዊ መግለጫ ስላወጣ በጣም ላመሰግናቸው እወዳለሁ›› ብሏል።

በዚህ ጉዳይ አስተያየታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት ሌላው ምሁር ደግሞ ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማሪያም ናቸው። የህግ ባለሙያው በጉዳዩ ዙሪያ ከሰንደቅ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹በእውነት ይህ ለችግሩ ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል ብዬ አላምንም። ህዝቡ ችግሩን ከእነ መፍትሄው ነው የገለጸው። መንግስትም ይህን የህዝብ ጥያቄና ድምጽ ሰምቶ ወደ መፍትሔ መሄድ እንጂ በዚህ መልኩ ችግሩን እፈታለሁ ብሎ መነሳቱ አዋጭ ሊሆነው አይችልም›› ብለዋል። ዶክተር ያዕቆብ ሃሳባቸውን ሲያጠናክሩም ‹‹አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው የውጭ ወረራ ሲያጋጥም ጦርነት ለመክፈት፤ እና ህዝቡን አደጋ ላይ የሚጥል የተፈጥሮ አደጋ (የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጎርፍ፣ ወረርሽኝ እና ቃጠሎን ጨምሮ የተለያዩ አደጋ አምጭ ምክንያቶች) ሲደርሱ ለመከላከል ሲባል የተወሰኑ ሰብአዊ መብቶች ሊጣሱ ይችላሉ። አሁን በእኛ አገር ባለው ሁኔታ ግን መፍትሔም አይሆንም አስፈላጊም አልነበረም። እንዲያውም በህዝብ እና በመንግስት የጸጥታ ሀይሉ መካከል ልዩነትን የሚያሰፋ ስለሆነ ለሰላም የበለጠ ጠንቀ ይሆናል›› በማለት ተናግረዋል።

 

በኮማንድ ፖስት የሚወሰዱ እርምጃዎችና የተሰጡ አስተያየቶች

አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈጻሚ ኮማንድ ፖስት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በተመለከተ የሚከተለውን ተናግረዋል።
1. የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበር እና ከአደጋ ለመጠበቅ የህዝብና የዜጎችን ሰላም ጸጥታ ለማስጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፤ ማንኛውም ሁከት ብጥብጥና በህዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃር የሚፈጥር ይፋዊ ሆነ የድብቅ ቀስቀሳ ማድረግን፣ ጽሁፍ ማዘጋጀትን፣ ማተምና መሰራጨትን፣ ትዕይንት ማሳየትን፣ በምልክት መግለጽን ወይም መልእክትን በማንኛውም ሌላ መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግን ይከለክላል።
2. ማንኛውም የመገናኛ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም ደግሞ እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል።
3. የህዝብና የዜጎች ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ሲባል የአደባባይ ሰልፍ እና ሰልፍ ማድረግን፣ መደራጀት፣ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስ ይከለክላል (ዝርዝሩ በመመሪያ ይወጣል)
4. በህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የሚቃጡ ወንጄሎችን የጠነሰሰ፣ የመራ፣ ያስተባበረ፣ የጣሰ ወይም ደግሞ በማንኛውም መንገድ በወንጄል ድርጊቱ የተሳተፈ ወይም በወንጄል ድርጊቱ ተሳትፏል ተብሎ የሚጠረጠርን ማንኛውም ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ያደርጋል፤ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ በመደበኛው ህግ ተጠያቂ እንዲሆን ያደርጋል።
5. ወንጄል የተፈጸመባቸው ወይም ሊፈጸምባቸው የሚችሉ እቃዎችን ለመያዝ ሲባል ማናቸውንም ቤት፣ ቦታ እና መጓጓዣ ለመበርበርና እንዲሁም ማናቸውንም ሰው በማስቆም ማንነቱን መጠየቅና መፈተሸ ይቻላል።
6. በብርበራ ወይም በፍተሻ የተያዙ እቃዎችን በማስረጃነት ለፍርድ ቤት መቅረባቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ተጣርቶ ለባለመብቱ ይመለሳል።
7. የሰዓት እላፊ ተፈጻሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ይወስናል።
8. ለተወሰነ ጊዜ አንድን መንገድ፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ ለመዝጋት እንዲሁም ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ ወደ ተወሰነ አካባቢ እንዳይቡ ወይም ደግሞ ከተወሰነ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል።
9. የተቋማትን የመሰረተ ልማት ጥበቃ ሁኔታ ወስናል።
10. የህዝብ እና የዜጎችን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ሲባል የጦር መሳሪያ፣ ስለት ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ይዞ መንቀሳቀስ የማይቻልባቸውን ቦታዎች ለይቶ ይወስናል።
11. በሰላም መደፍረስ ምክንያት የፈረሱ የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖችን ከክልል እና ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር መልሶ እንዲቋቋሙ ያደርጋል።
12. ብሔር ተኮር በሆኑ ወይም በሌሎች ግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎችን ከክልል መንግስታትና ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመተባበር ወደ ቀድሞ መኖሪያ ሰፈራቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙና ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሩ ድጋፍ ያደርጋል።
13. የሚገለገልባቸው አገልግሎት ተቋማት የንግድ ስራዎች ወይም የመንግስት ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት እንዳይስተጓጎሉ ተገቢውን ጥበቃ ያደርጋል። ይህን ተላልፎ አገልግሎትን ያቋረጠ ማንኛውም ሰው በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
14. የመሰረታዊ ሸቀጦችና አገልግሎቶችን አቅርቦት የዝውውርና የስርጭት ደህንነት ያረጋግጣል። የትራንስፖርትን ፍሰት ደህንነት ያረጋግጣል።
15. በትምህርት ተቋማት በመማርና ማስተማር ሂደትን ከሚያውኩ ተግባራት የጸዳ እንዲሆኑ እንዲሁም መደበኛ የሆኑ ስራን የሚያስተጓጉሉ እንከኖች እንዳይፈጠሩ ይሰራል።
16. ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስተርዓቱን ለማስከበር፣ ከአደጋ ለመጠበቅ፣ የህዝብንና የዜጎችን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። እነዚህ እርምጃዎች ቀጣይ በሚወጡ በአፈጻጸም መመሪያዎች የሚዘረዘሩ እንደሚሆኑ አቶ ሲራጅ ተናግረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈጻሚ ኮማንድ ፖስት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ተከትሎ ተቃውሞን በማሰማት የአሜሪካን መንግስት የቀደመው አልተገኘም። አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የመንግስታቸውን አቋም በሚገልፅ መግለጫ ላይ ‹‹የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ይጋፋል፣ የሰዎችን መሰረታዊ መብቶች የሚጥስ ነው። በመሆኑንም አልስማማም›› ሲል አስታውቋል።

 

የተሻለ አገራዊ መፍትሔ

አገሪቱ ውስጥ መጠነ ሰፊ ግጭቶች መኖራቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት የተነሱ ግጭቶችን ለማብረድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን እንደ መፍትሔ ወስዶታል። ለዚህም ከየካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በሁለም የአገሪቱ ክፍሎች ለስድስት ወራት (እስከ ነሃሴ 9 ቀን 2010 ዓ.ም) ተፈጻሚ የሚሆን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። ይህ አዋጅ በስድስት ወራት ውስጥ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት ካልቻለም ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ይደረጋል ሲል አስታውቋል።

ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን የሰጡ ፖለቲከኞችና ምሁራን ደግሞ ከኢህአዴግ የተለየ አቋም እንዳላቸው ገልጸዋል። የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ያካሄደውን የማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ እንደጨረሰ የወሰደውን አቋም እንደተመለከተው የገለጸው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹ኦህዴድ በአገር ውስጥም በውጭ አገር ከሚኖሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እንደራደራለሁ ማለቱን ስመለከት በኢህአዴግ ውስጥ መሻሻል እየታየ እንደሆነ አመላክቶኛል። አሁንም ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው ከሁሉም ሀይሎች ጋር ድርድር እና ውይይት ማካሄድ ነው›› ሲል ይበጃል ያለውን አገራዊ መፍትሔ ተናግሯል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ‹‹በሄዱበት መንገድ መመለስ ነው›› ያለው መምህር ስዩም ተሾመ በበኩሉ ‹‹አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ህዝባዊ ተቃውሞ ማካሄድ እና ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድን ይከለክላል። ከዚህ ቀደምም የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ባስቀመጠው መመሪያ ማንኛውንም አይነት የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ ክልክል ነው ብሎ ነበር። ያ ክልከላ ባለበት ሁኔታ ነው አገሪቱ ውስጥ እንደዚህ አይነት ሰፋፊ የተቃውሞ ሰልፍ እያየን ያለነው። ይህ የሚያሳየው ደግሞ የተነሳውን ተቃውሞ ክልከላ እንደማያቆመው ነው። አሁን የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅም የተነሳውን የህዝብ ለውጥን የመሻት ጥያቄ ከማፈን ውጭ መፍትሔ ሊሆን አይችልም›› ብሏል። መፍትሔ ይሆናል ያለውን ሲያስቀምጥም ‹‹ለህዝብ ጥያቄ መልስ መስጠት የችግሩ ብቸኛ መፍትሔ ነው›› ሲል አስቀምጧል።

ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማሪያም በበኩላቸው ‹‹ኢህአዴግን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ አባሎችና የሲቪክ ማህበራትን ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ዘላቂ መፍትሔ ይሆናል። ይህን ለማድረግ ግን ኳሱ በኢህአዴግ እጅ ላይ ነው ያለው። አገርን መውደድ እና ህዝብን ማክበር ይጠይቃል። ከዚህ በተረፈ ግን ሀይል መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ችግሩን ያባብሰዋል›› በማለት አሳስበዋል።

ሰበር መረጃ…የህወሃት ኮማንድ ፖስት አመራር ጄኔራል ሲራጅ ፈጌሳ ወደ ታች ያወረደዉ ትእዛዝ (ልዑል ዓለሜ)

የህወሃት ኮማንድ ፖስት አመራር ጄኔራል ሲራጅ ፈጌሳ ወደ ታች ባወረደዉ ትእዛዝ መሰረት በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች አጠቃላይ ስብሰባ ተጠርቶ በዉይይት ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ጠቅሰዋል በዛሬዉ እለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስተዳደር ዉስጥ የሚገኙ ሰራተኞችን ሰብስቦ እየሰበከ የሚገኘዉ የኮማንድ ፖስቱ መመሪያ ተቀባይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በተመለከተ እንዲሁም ስለተፈቱ እስረኞችና ስለሚፈቱ እስረኞች ሁኔታ ለማብራራት እየሞከረ እንደሆነ ታዉቋል።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ የተለያየ ስፍራ የሚገኙ ምድብ ችሎት ሰራተኞችን ሰብስቦ እየደሰኮረ የሚገኘዉ የኮማንድ ፖስቱ የህወሃት ካድሬ እሁን እየተፈቱ ያሉት የህሊና እስረኞች ቀደም ሲል እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ብቻ ናቸው በማለት ካለ ወዲህ እንደእግባቡ እየተመለከትን ወደፊት የሚፈቱ ሊኖሩ ይችላሉበማለት የማላገጥ እና የንቀት ንግግር ተናግሯል።

በሁሉም ቦታ እየተካሄደ የሚገኘዉ ስብሰባ አስቸኳይ ተብሎ የተጠራ ሲሆን ዋና አላማዉ ኮማንድ ፖስቱ ወታደራዊ ሐይል መሆኑን እና ፍርድ ላይ ስለሚከናወነዉ ሂደት ጣሺ እና የበላይ መሆኑን ማስገንዘብ ጭምር ነዉ ።

በዚህም መሰረት እስረኞች ተፈቱ ማለት ከእንግዲህ እስር የለም ፍርድ የለም ማለት እይደለም ኮማንድ ፖስቱን የጣሰ ማንኛዉም አካል ከተገኘ በራሱ በኮማንድ ፖስቱ ህገ ደንብ መሰረት ይቀጣል አይነት ምልእክት አስተላልፏል።

አቃቤ ህግ እና ዳኞች ላይ ግልጽ የሆነ ጫና ተላልፍዋል።

ይህን አስቸኳይ ስብሰባ ለየት የሚያደርገዉ ነገር ቢኖር አብዛኛዉ ተሰብሳቢ የተሰላቸና ያንገሸገሸዉ አይነት ምልክት ማሳየቱ ሲሆን ስልክ የሚጎረጉሩ እንቅልፍ ይዟቸዉ የሄደ በሄር ፎን የተመሰጡ መሆናቸዉ ናቸዉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

ምነው እግዚአብሄር ተረሳ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ  2.22.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። )

“ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝሙረ ዳዊት (፷፰፥፴፩)

የትኛው ሐገር ይሆን በአሳነባሪ ሆድ መንግሥት አልባ እራሱን ጠብቆ፤ ሌላውንም ጠብቆ፤ በመከባበር ውሎ የሚያድረው፧ ኢትዮጵያን ያቆማት የፈጣሪ ቸርነት እንጂ የሰውማ ቢሆን ስባሪዋም አይገኝም ነበር። ህዝቧን ጠብቆ አውሎ የሚያሳድረው ከቶውንም የማይመረመረው ዕዮራዊ ጥበብ መሆኑ ተረሳ። ትራፊ በሰልፍ ተገዝቶ እንደ ሰው ቁሞ ለመሄድ ያስቻለው የአጋይስታለሙ ጥበብ መሆኑ በሰውኛ ስሌት እንሆ ተዳጠ። ማህከነ!

ቅዱስ ሚኬኤል በጠራራ ጸሃይ በሰሞናተ አስትእሮዬ በታእቢት ቦንብ ጢስ መደብደቡ ፈጣሪ አምላክ ይረሳዋል ተብሎ መታሰቡ ዕምነቱ ከአንጀት ወይስ ከአንገት ያሰኛል፤ የሁለቱ የሃይማኖት አቮው የህዝቦቿን መከራ እንዲዩ ፈቃዱ ስለምስክርነትስለመሆኑ የቁስ ሰውነታችን እንሆ አጋለጠው። ተሳህለን!

እንሆ ማስተዋሉን አጥተን ብለን ብለን በፈቃደ እግዚአብሄር ጥበብ ገብተን እንታመሳለን። እስልምና እና ተዋህዶ ነብያቱ አብረው በማህበረ ፈርዖን ጎመራ ውስጥ መቀቀላቸው ስለምን እንደሆነ ጥበቡ አልተገለጠልንም። ይቅርበለን!

“የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።”
(ኦሪት ዘፍጥረት ፪፥፲፫)

የአማራ ተጋድሎ ተነስቶ ያሳዬን ምልክት የደወል ድምጽ መሆኑን ሚስጢሩ አልተገለጠልንም። እኛ አሁንም ቁስ፤ ሸቀጥ ላይ እንዳክራለን። አውሬው ጠበንጃን ከፈጣሪ በላይ አምልኮ ዘውድ ደፍቶለታል።

“ሀገርን እግዚአብሄር ካልጠበቀ ሰራዊቶች በከንቱ ይደክማሉ” የዲያቢሎስ አምላኪው አውሬ ከመጤፍ ባይቆጥረው ምንም አልነበረም፤ እኛ ይህ የሆነው ስለምን ስለመሆኑ በሱባኤ ልንታደምበት ሲገባ፤ ትምህክታችን በልዑል እግዚአብሄር ማድረግ ሲገባ አልፈን ተርፈን በነጮች ብዕር ውሳኔ መጽናናትን አግኝተንበታል። እግዚኦ!

“በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?” (ትንቢተ ኤርምያስ ፲፫፥፳፫)

መከራ ያጋራው ህዝብ ጥንካሬውን፤ ሃይሉን እያገኘ ደወሉን በፆም፤ በሰጊድ፤ በሱባኤ፣ በምህላ፤ በድዋ በግልም ይሁን በጋራ መጪው ዘመን የዕንባ፣ የቂም የበቀል የሴራ የጥላቻ እንዲሆን የፉክክር ዓውድ የስብሰባ አዳራሽ ነፍሳችን አድርገን ስንደምር ስንቀንስ መንፈሳችን በትነን ታምሰን እናምሳለን። በፋክክር ለዛውም በቅብዕ መንግሥት ላይ የፈጠሪን / የአላህን ሥልጣን መጋፋት ስለሆኑ መታደም ቀርቶ ማድመጥ አለመቻል አምልዕኳችን ስለ ዕንባ ሳይሆን ስለሸቀጥ ሆነ።

…. ግን ሰሞኑን ስንት ወንበር ገዛን፧ ስንትስ  የወንበር መሸጫ ቤት ጎበኘን፧ ዕምነት አነሰን፤ በእያንዳንዱ ሰከንድ አዲስ ነገር አለ መሰብሰብ፤ ማስታወስ እስኪያቅተን ድረስ። ይሄ የሚመነዘረው በገሃዱ ሰውኛ አቅም ነው የሚተረጎመው። ፋከራ ነው። ተመስገንን አሳደድነው።

አቤቱ ፈጣሪ ሆይ! እንደኛ መተላለፍ ሳይሆን እንደ አንተ ቸርነት ወጀቡን ቀጥተህ መቅደሽን  ጠብቅ!

ልዑል እግዚአብሄር ሆይ! የአንድአርጋቸው ጽጌን ድምጽ አሰማን! አደራህን!

ከእያንዳንዱ መከራ በስተጀርባ መዳን እንዳለ እናዳምጠው። አቤቱ አማኑኤል ሆይ በቃችሁ በለን፤ የምንተቃቀፍበትን ዘምንን አምጣልን፤ አሜን ለዘለዓለም።

“የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፦” (ትንቢተ አሞጽ ፱፥፯)

ወስብሃት ለእግዚአብሄር።