የቀለም አቢዮት፤ የኢኮኖሚዉ ሁኔታና ሌሎችም | ከሚኪ አማራ

—————-
የቀለም አብዮት
———
ሲራጅ ፈጌሳ በቀለም አቢዮት መልክ ስልጣንን ከመንግስት እጅ የመቀማት ሁኔታ ይታያል ሲል በቀደም መግለጫ ሰቶ ነበር፡፡ በእርግጥ ነገሩ ቀልድ ቢመስልም ግን መልክት አለዉ፡፡ አንደኛ ለማሰር የሚፈለጉትንና የሚታሰሩትን ሰዋች ፍርድ ቤት ላይ ክስ የመመስረቻ መንገድ ነዉ፡፡ ሁለተኛ ስልጣንን ለመንጠቅ የሚለዉ ምናልባትም ከህዝቡ በላይ የራሱን ሰወች ወይም ፓርቲዎች ለምሳሌ ኦህዴድን የሚመለከት ይመስላል፡፡ በዚህም መሰረት በሚቀጥሉት ጊዚያቶች ያሰራቸዉን ባለስልጣናትና ተቃዋሚችን ምናልባትም የመንግስትን ስልጣን ለመቀማትና የቀለም አቢዮት ለማካሄድ ሙከራ ማድረግ በሚል የተንዛዛ ክስ ለመመስረት ነዉ፡፡ ሌላዉ ይሄ የቀለም አቢዮት የሚል ነገርም በ2008 አካባቢ የአማራ ከፍተኛ ተጋድሎ በነበረበት ወቅት የቴሌቪዥን ማድመቂያ ሁኖ ነበር፡፡ ልክ ያኔ እንዳደረጉት አሁንም እንግዲህ በዶክመንተሪ መልክ ይዘዉልን ይመጣሉ፡፡
ወታደሩ አገሪቱን መቆጣጠሩ (silent coup)
————-
የሃገሪቱ የሲቪል አገዛዙ ከሶስት አመት ወዲህ ጀምሮ እየተደናበረ ወንበሩ ላይ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን በጠቅላላዉ የወታደራዊ ክንፉ አገሪቱን ተረክቧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር የለም፤ ለችግሮቹ መፍትሄ እየመጣ አይደለም፤ የመንግስት ሰወች መግለጫ አይሰጡም፡፡ ወታደሩ ጸጥታ ብቻ ሳይሆን መሬት ያስተዳድራል፤ ፋብሪካ የቆጣጠራል፤ የትራንስፖርት ሰምሪት ያሰማራል፡፡ ስለዚህም የመንግስት ቢሮ የሆኑት የመሬትና ኢንቨስትመንት፤ የማእድን፤ ትራንስፖረትና የመሳሰሉት ቢሮወች አይሰሩም ማለት ነዉ፡፡ የሲቪሉ አካል አሁን በዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የዉጩን አለም የማረጋጋት ስራ ላይ ብቻ ተጠምዷል፡፡ በቴሌቪዥንና በራዲዮ የሚተላለፉ ዜናወችና ፕሮግራሞች በወታደሩ በጥብቅ ክትትል ዉስጥ ናቸዉ፡፡ ያልተደረገዉ ነገር ቢኖር ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ልክ እንደ ሙጋቤ በቴሌቪዥን የወታደሩ ቃል አቀባይ ቀርበዉ ከዛሬ ጀምሮ ጥቅማቸዉ ተከብሮላቸዉ ከስልጣን ተነስተዋል አገሪቱም እስከ ሚቀጥለዉ ምርጫ ድረስ በመከላከያ ሰራዊቱ ትጠበቃለች አለማለታቸዉ ነዉ፡፡በእርግጥ ብለዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና እስር
————-
በሚቀጥሉት ወራቶች አሁንም በገፍ ሊያስሩ እንደሚችሉ ያመላከተ ድርጊቶች እየወሰዱ ነዉ፡፡ በተለይም ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ እየወሰዱት ያለዉ እርምጃ ግልጽ ምልክት ነዉ፡፡ ከዚህ በፊት እንዳልኩት ህወሃት እየሄደበት ያለዉ አካሄድ የአዲሱን ኦህዴድ ስሪት በመበጣጠስ የቀድሞዉንና ተላላኪዉን ኦህዴድ መመለስ ነዉ፡፡ አሁን ኦሮሚያ ላይ እየተደረገዉ ያለዉ ነገር በ2008 አማራ ክልል ላይ የተደረገዉ ነዉ፡፡ በ2008 አማራ ክልል ላይ የዞንና የከተማ አስተዳዳሪዎችን አስረዋል፤ የዞንና የክልል ፓሊስ ኮሚሽን አባረዋል፡፡ ለምሳሌ የአዊ ዞን አመራር አንስተዋል፤ የሰሜን ጎንደር ዞንና የጎንደር ከተማን አመራሮችን ሙሉዉን አንስተዉ አስረዋል፤ የደቡብ ጎንደርና የደብረታቦር አመራሮችን አንስተዋል፤ የምስራቅ ጎጃም ዞንና ደብረማርቆስ፤ የባህርዳር ከተማ አመራሮችን አንስተዋል፡፡ ክልል ላይ የፖለሲ ኮሚሽንሮችን አንስተዋል፡፡ የክልል የቢሮ ሃላፊዎችን አንስተዋል፡፡ ያደራጃሉ ያሏቸዉን ባለሃብቶችና ወጣቶች አስረዋል፡፡በዚሁ ስሌት ነዉ ኦሮሚያ ላይ እየተደረገ ያለዉ፡፡ ዉጤት ይኖርዋል ወይ ለሚለዉ ጥያቄ፡፡ አሁንም መልሱ ከ 2008 ወዲህ ያለዉን አማራ ክልልን ማይት ነዉ፡፡ ተቃዉሞዉ ለሰሞን በረደ እንጅ አልጠፋም፡፡ ከዛ ወዲህ አምና ባህርዳር ላይ የቤት ዉስጥ መቀመጥ ተካሂዷል፤ ጎንደር ላይ ዘንድሮ ተካሂዷል፤ ጭራሽ ነገሩ ወደ ምስራቅ አማራ ሰፍቶ እነ ወልድያንና ራያን አዳርሷል፡፡ ባጠቃላይ ሰላማዊ ሰለፍ መዉጣት መቀነሱ ነዉ እንጅ አማራ ክልል በተገኘዉ አጋጣሚ ተቃዉሞ አለ በእግር ኳሱ፤ በህዝባዊ በአላት፤ በህቡእና በሌሎች ዘዴወችም እንዲሁ፡፡ ስለዚህም ኦሮሚያ ላይም የተለየ ነገር አይኖርም፡፡ ተቃዉሞዉ ይቀጥላል፡፡
ኢኮኖሚ
——-
የሃገሪቱ የማምረት አቅም በእጅጉ ተዳክሟል፡፡ ወደ ዉጪ የሚላክ ምርት ብቻ ሳይሆን በድርጅቶችና መስሪያ ቤቶች የሚሰጠዉ አገልግሎት በጣም ተዳክሟል፡፡ የመንግስት ሰራተኛዉ እንዲሁ ሲብሰከሰክ ይዉላል፤ የድርጅቶች አገልግሎት አሰጣት ቀንሷል፤ ለኢኮኖሚ እድገት ብዙ ቦታ ይዞ የቆየዉ የግንባታና የሰርቪስ ሴክተር ቆሟል፡፡ የግብርና ምርት በአየር ንብረት ተጽእኖ ምክንያት ተዳክሟል፡፡ የተመረተዉ ምርትም በጸጥታ ምክንያት ወደ ገቢያ አልወጣም፡፡ የተሻለ ምርት ዘንድሮ የተገኘዉ አማራ ክልል ቢሆንም መሃል አካባቢ ያለዉን ምርት በመንገድና መሰል መስረተ ልማት እጦት ወደ ገቢያ ማዉጣት አልተቻለም፡፡ ትልልቅ ፕሮጀክቶች በዉጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት አብዛኞቹ አቁመዋል፡፡ባጠቃላይ እነዚህ ተደማምረዉ አመታዊ የሃገሪቱ ምርት እንዲያሽቆለቁል ያደርጋሉ ማለት ነዉ፡፡
ይሄ የተዳከመ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ዉጤቱ ምን ይሆናል፡፡ አንደኛ አሁን ያለዉ 15.5 በመቶ የዋጋ ግሽበት በሚቀጥሉት ወራቶች በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር እስከ 30 በመቶ ሊደርስ ይችላል፡፡ ለዚህ ግሽበት ዋና መንስኤ ሊሆን የሚችለዉም ሀገሪቱ ከምታመርተዉ ምርት በላይ ብር ማተም ትጀምራለች፡፡ ለምሳሌ ገና አመቱ ሳይጋመስ ሰሞኑን የመንግስት መስሪያ ቤቶች በጀት የለንም (በጀት የለንም ሳይሆን ካሽ የለንም) በማለት ስራ እየሰሩ አይደሉም፡፡ አንዳንዶቹ ለሰራተኞቻቸዉ የሚከፍሉት ገንዘብ የለም፡፡ ይሄን ችግር ለመወጣት የመጀመሪያዉ የመንግስት እርምጃ የሚሆነዉ፡ ብሄራዊ ባንኩ በቢሊየን ብር እንዲያትም ማድረግና ወደ ገቢያዉ መበተን ነዉ፡፡ ሸቀጦችን እንደልብ ማግኘትም አይቻልም፡፡ የገንዘብ ገቢያዉ ላይ በብዛት መዘዋወርና የእቃወች እጥረት ለተወሰኑ ነጋደዌወች market power እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ ዋጋ በራሳቸዉ ግዜ ይተምናሉ፤ ቢፈልጉ የሚፈለገዉን እቃ አሽገዉ ያስቀምጣሉ፤ አለያም ለትቂት ገንዘቡ ላላቸዉ ሰወች ብቻ ገቢያዉ ክፍት ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ኢኮኖሚስቶች market inefficiencies or market failure የሚሉት ነገር ይከሰታል፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ገቢያ በዉድቀት የተቃኘ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ትቂት የስረአቱ ሰወች ናቸዉ የገቢያዉን ሁኔታ የሚወስኑት፡፡ በኢኮኖሚክስ ህግ መስረት ገቢያዉ ከአቅራቢም ከተጠቃሚምም በኩል በሚደርስ ተጽእኖ የማይዋዥቅ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ለኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቻዉ ጥቃቅን ቢዝነሶች ከገቢያ ይወጣሉ በዚህም ምክንያት መንግስት ታክስ መሰብሰብ አይችልም ስራ አጥነትም ይስፋፋል፡፡
ሁለተኛዉ እርምጃዉ ሊሆን የሚችለዉ ከባለፈዉ ተጨማሪ የብርንና የዶላርን ምንዛሬ ማስተካከል ነዉ፡፡ ባለፈዉ የ15 በመቶ ጭማሪ እንዳደረገ ይታወቃል፡፡ ወይም እንደ ኢኮኖሚስቶች ባብዛኘዉ መሬት ላይ ሲወርድ ተጽእኖዉ በእጥፍ ይሆናል፡፡ ይሄም ማለት የብር የመግዛት አቅም በፖሊሲ ደረጃ በ15 በመቶ ቢቀንስም መሬት ላይ ሲደርስ ያለዉ ተጽእኖ ግን 30 በመቶ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባለፈዉ አይ.ኤም.ኤፍ መንግስት ሪፎረም እንዲያደርግ ያሳሰበዉን ሳይፈልግ በግዱ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የተወሰነዉን መንግስት የሚቆጣጠራቸዉን ድርጅቶች (ቴሌ፤ ንግድ መርከብ) ለባለሃብት የመስጠት፤ የገንዘብ ቁጥጥር ፖሊሲዉን ማሻሻልና አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፖሊሲዉን የማስተካከል ስራ በመስራት የተወሰነ ገንዘብ ከ አይ.ኤም.ኤፍ ሊያገኝ ይችላል፡፡
ባጠቃላይ ግን ምንም አይነት የኢኮኖሚ ርምጃ ቢወሰድም ገቢያዉን ማረጋጋት አይቻልም፡፡ አገሪቱ በየትኛዉም ሁኔታ 100 ሚሊየን ህዝብ ሊሸፍን የሚችል ምርት ልታመርት አትችልም፡፡ ለጊዜዉ ለምሳሌ የስራ አጥ ቁጥር በገጠር 52 በመቶ አካባቢ በከተማ ደግሞ 24 በመቶ አካባቢ የደረሰ ሲሆን አሁን ባለዉ ሁኔታ ይሄ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡ ይሄን ሰፊ ችግር የተወሰነ ገንዘብ በመበጀት የምትቀርፈዉ ነገር አይደለም፡፡
ምን ያዋጣል
———-
ከዚህ በመነሳት ሁለት ነገር አዋጪ ነዉ፡፡ አንደኛዉ መንግስትን ከጦርነት በላይ ኢኮኖሚዉ እንደሚያዳክመዉ፡፡ ጦርነት ለኢሃዴግ የሚቀለዉ ይሆናል፡፡ ሁለተኛ ሌላ አገር ሆኖ መንግስት ለመጣል ከመሞከር ይልቅ አገር ዉስጥ ያለዉን ሃይል ማስተባበር የተሻለ እንደሆነ፡፡ አገር ዉስጥ ደግሞ ከህዝቡ ትግል በተጨማሪ እራሱ ድርጅቱ ዉስጥ ያለዉን መፈራቀቅ በሚገባ መጠቀም ነገሮችን ያፋጥናል፡፡
ለኢህአዴግ ምን ያዋጣዋል
————
እስረኛ መፍታት፤ ዲሞክራሲን ማስፋት፤ ወታደሩን ወደ ደንበር መመለስ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳት፤ ህገመንግስት ማሻሻል፤ ሁሉን አቀፍ መንግስት ማቋቋም፤ ብሄር ተኮር ፌደራለዊ ስርአትን መተካት፤ ብሎም ስልጣን መልቅቅ ያዋጣዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴርነቱ
———-
ኢህአዴግ የአሜሪካኖችን ምክር ለመስማት ስብሰባዉን ያራዘመ ሲሆን እንግዲህ አሜሪካ ትናንት አስፈላጊ ነዉ ያለችዉን በዉጪ ጉዳዩ መሰረት ተናግራለች፡፡ ስለዚህም ኢህአዴግ ከዚህ በኋላ የሚጠብቀዉ ሌላ ነገር ስለሌለ ወደ ስየማዉ ይሄዳል ማለት ነዉ፡፡ የባለስልጣኑ መምጣት በግልጽ የፖለቲካ ቀዉስን በተመለከተ መሆኑን የሚያሳየዉ ከመንግስት ጋር ያደረጉት የኢኮኖሚያዊ፤ የጸጥታ ወይም ሌላ ማህበረሰባዊ እድገትን ሊያመጣ የሚችል ይሄ ነዉ የሚባል የተፈራረሙት ትብብር የለም፡፡ ዶ/ር አብይን ጠቅላይ ሚኒስቴር አድርገዉ ከመረጡ ምናልባትም የአሜሪካ ተጽእኖ ነዉ ብለን መዉሰድ እንችላለን፡፡ ሽጉጤ ከሆነ የህወሃት ተጽእኖ ሲሆን፡፡ ደመቀ ከሆነ የብአዴን ተጽእኖ ነዉ ማለት ነዉ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s