የንፁሓን ደም ይጮሃል! – በላይነህ አባተ

ካርባ ዓመት በላይ ሆኖታል፣

የንፁሓን ደም ይፈሳል፣

ወልቃይት ጠለምት ጀምሮ

እስከ ሞያሌ ይጮሃል!

 

የንፁሓን ደም ይፈልቃል፣

ዓባይ ተከዜን አቅልሟል፣

አንገርብ ቀሃን አቅልቷል፣

ተምጫ ጨሞጋን ሱፋሌ

ጣና በለስን ጃኖ አርጓል፡፡

 

የንፁሓን ደም ይጎርፋል፣

ደዴሳ ጊቤን ሞልቶታል፣

ባሮ ገናሌን አጉሽቷል፣

አዋሽን ቆቃን ጢም አርጎ

የሞያሌን ምድር አርሷል፡፡

 

የንፁሃን ደም ይጮኻል!

ባድርባይ ምሁር ተከፍቷል፣

በጳጳሳቱ ልቡ አዝኗል፣

ሼሁን ፓስተሩን ታዝቦ

በአቦይ ማትያስ ያነባል!

 

የንፁሓን ደም ይጮኻል!

በሆድ አደሮች ቆዝሟል፣

ባዘን ወቅት አድፋጪ አልቅሷል::

 

 

የንፁሓን ደም ይጮኻል!

ደመ ከል ሆኖ እንዳይቀር

ጀግናን ሞረሽ ሲል ይጣራል፡፡

 

የንፁሓን ደም ይጮኻል!

ከዓለም ፍርድ ቤት እሚያቅርብ

ጠበቃ ወኪል ዳኛ አጥቷል፣

በሕግ ምሩቆች ተከፍቷል፡፡

 

የንፁሓን ደም ይጮኻል!

ጋዜጠኛውን ተማጽኗል፣

ኪነ-ጥበብን ለምኗል፣

ቀሳውስት ሼሁን ተማልዷል፣

በፀሎት ኪነት ዘላለም

እንዲዘክረው ጥይቋል፡፡

 

የንፁሓን ደም ይጮኻል!

ለሕዝብ መልክቱን አድርሷል፣

አደራን በምድር አስምሯል፣

ደመ-ከል ላይቀር ተማጥኗል፣

“ፍትህ አደራ” ብሎናል፡፡

 

የንፁሓን ደሞ ይጮኻል!!

ይጮኻል!!

ይጮኻል!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

መጋቢት ሁለት ሺ አሥር ዓ.ም.

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s