አዲስ አበባ በጭንቅ ላይ ወድቃለች!

ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች በያሉበት ቆመዋል ከተማዋ ላይ ከባድ ድባብ ተንሰራፍቷል ነዳጅ ያልቀዱ ቀድተዉ ለማስቀመጥ እየተሯሯጡ ነዉ መበራት እንደሚቋረጥ ጭምር እየተነገረ ይገኛል ወፍጮ ቤቶች በወረፋ ተጨናንቀዋል የዉሀ ማጠራቀሙ ስራ ወከባን ፈጥሯ ከሰማይ የሚወርድ ዱብ እዳ ያለ እስኪመስል የፍርሀት ቆፈን ከተማዋን እያጨማደዳት ነዉ::  የወያኔ ኮማንድ ፖስት ላይ ህዝባዊ አዋጅ ተጥሎበት ግራ የተጋቡ መከላከያዎችን መመልከት ነጻነት ለናፈቀዉ ተስፋ ነዉ አራቱም የከተማዋ በሮች ቦቴ ደህና እደሪ ብለዋል ።

liul aleme

ሰበር መረጃ…በአዲስ አበባ ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር እየተካሄደ እንደሚገኝ ታወቀ

አዲስ አበባ ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር እየተካሄደ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ የከተማዋን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ አስተያየታቸውን ለቢቢኤን የሰጡ ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ እንደ ልብ መንቀሳቀስ አዳጋች ሆኗል፡፡ ዩኒፎርም የለበሱም ያለበሱም የፖሊስ አባላት የህብረተሰቡን እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከታተሉ እንደሚገኙ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ በቀበሌ የተመለመሉ ወሬ አቀባዮች በየሰፈሩ መበተናቸውንም ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ፡፡ ከተማዋ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንድትገባ የሚደረገው፣ ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል የአገዛዙ ስጋት እንደሆነ ታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ሶስት ወይም አራት ሆኖ መቀመጥ አልያም ሻይ ቡና ማለት እንኳን ክልክል እየሆነ መምጣቱን ለቢቢኤን የገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ በየጫት ቤቱ ሳይቀር ክትትል እንደሚደረግም ነዋሪዎቹ ነግረውናል፡፡ ጫት ቤት ተቀምጠው በጋራ ሲቅሙ የተገኙ ሰዎች በወሬ አቀባዮች አማካይነት በፖሊስ ሲያዙ ማየታቸውን የዋሪዎቹ ገለጻ ያስረዳል፡፡ በሌሎች ቦታዎችም አራት ሆኖ መቀመጥ አልያም በጋራ መንቀሳቀስ ክትትል ውስጥ እንደሚያስገባ የሚናገሩት እማኞች፤ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊትም ቢሆን በአፈና ውስጥ የሚገኘው የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአዋጁ በኋላ ደግሞ የባሰ የጭቆና ቀንበር ውስጥ እንዲገባ መደረጉን እማኞቹ ያስረዳሉ፡፡

አገዛዙ የነዋሪዎችን ዕለታዊ እንቅስቃሴ በይበልጥ የሚቃኘው እና ወሬ የሚሰበስበው በየቀበሌው በተሰገሰጉ ካድሬዎች አማካይነት ሲሆን፤ ሲቪል የለበሱ የፖሊስ አባላትም የስለላ ስራ እንደሚሰሩ ይገልጻሉ-የመረጃው ምንጭ የሆኑ ነዋሪዎች፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ መሸት ሲል ደግሞ በከተማዋ ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን፤ ከምሽቱ 3 እና 4 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አዳጋች ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በከተማዋ ድንገተኛ ፍተሻን ጨምሮ ሌሎች ድርጊቶች እንደሚከናወኑ የገለጹት እማኞች፤ የከተማዋ ነዋሪ በተለይ ከአዋጁ መጽደቅ በኋላ ድርብ አፈና ውስጥ መግባቱንም የእማኞቹ ገለጻ ይጠቁማል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s