“ሰይፍህን  ወደ ሰገባው መልስ” (ከታምራት ይገዙ)

ህጻን ዩሴፍ እሸቱን

በአሁን ሰዓት የአግራችን የኢትዮጵያ አየር በህጻናት ደም እየታወደ ይገኛል:: ልጅ እያለን እናቶቻችን በህዳር  ወር ላይ ወረርሽኝን ለማጥፋት በሚል ሰበብ  በየጎራችን ቆሻሻ እየሰበሰቡና እያቃጠሉ ያውዱን ነበር:: በኢሀዼግ/ህወሀት ዘምን በተለይ ባለፉት ወራቶች የ13 ዓመት ህጻን ዩሴፍ እሸቱን በመሳሰሉት የህጻናት ደም አገራችን እየታወደች ትገኛለች:: እንዲሁም በሞያሌ  በኩል በአስቸኮይ ሰዓቱ ስም የተበከለ የህዝብ ደም ይጮሃል የወገን ያለህ ይላል:: በተለይ የሚገርመው ነገር በኢህኣዴግ/ህወሀት በኩል አሁንም የማስፈራሪያው: የጉራውና የማስጠንቀቅያው ጫጫታ ከምንግዜውም በላይ ይሰማል:: ቅጥፈትና ባዶ ፕሮፓጋንዳው ውጪ ባላሉት የህወሐት ደጋፊዎችና በትግራይ ህዝብ ደም የሚነግዱ የትግራይ ተወላጆ ሙህራኖችና ባለሃብቶች  ይስተጋባል:: በዚህ ትንኮሳ በዚህ ማስፈራሪያና ድፍረት የተኛው አንበሳ ማግሳት ቢጀምር በግ ሕብረተሰባችን ወደ ተኩላነት ቢለወጥ ለማነው ኪሳራው? በኢህኣዴግ/ ህወሀት መሪዎች በሚያፈሱት የንጹሃን ደም አእምሮቸው በጥፋተኝነትና በተጠያቂነት እያሳቀያቸው ይገኛል <<ጥፋተኛ አእምሮ ባለቤቱን ያሰቃያል>> ብሎ የለ” ቾውሰር”::

በሰይፍ ማመን አግባብ አይደለም:: በሰይፍ የሚያምኑ ሁሉ በመጨረሻ የሚሞቱት (የሚያልቁት) በሰይፍ ነውና:: በዓለማችን በህዝባቸው ላይ ሰይፍ አሊያም የጦር መሳሪያ የመዘዙ እብሪተኞችና ቀጣፊዎች እስከ መንገዱ ጫፍ ድረስ ተጉዘው አያውቁም ይህንን ለማስተዋል የሰው ህይወት የሚቀጥፉት የህወሀት መሪዎችና  ደጋፊዎቻቸው የትግራይ ተወላጆች ታሪክ ማንበብ አሊያም እሩቅ መሄድ የለባቸውም ባለፉት ሶስትና አራት አመታት በሊቢያው መሪና በግብጹ መሪ ላይ የደረሰን ማስታወስ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው::

ዛሬ የህወሃት/ኢህኣዴግ ገዥዎች በቤቱ ላይ እሳት በእሱ ላይ ጥይት የሚለቁበት ሕዝብ በግድ ወደ ነብርነት ወደ አንበሳነትና ወደ ተኩላነት ሊለወጥ እንደሚችል የማያውቁ ከሆኑ ሂሊናቸው በስልጣን የናወዘ መሆኑን ነው የሚያስረዳው ሌሎቹም የህወሓት ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይም ሆኑ የሌሎች ቤሄረሰብ ተወላጆች ይህ ካልተረዱ ጊዛዊ ጥቅም ምን ያህል ሂሊናቸውን አንደሸበበው ነው የሚያሳየው:: ህወሐቶች በሚገዙበት አገር እንደ በግ ዝም ማለት ራስን ምንኛ ለጥቃት ማጋለጥ ማዋረድ መሆኑን እነሆ ከሃያ አምስት አመት የውጣ ውረድ ጉዞ  ብንቆይም አሁን የተረዳን ይመስለኛል:: የሰፈራችን ድንጋይ ፈላጭ ቀበና ያለውን ድንጋይ ሲፈረካክሰው የተመለከት መንገደኛ <<ድንጋዩም መጎለቱን አብዝቶት ነበር>> አለ ይባላል::

የኢትዮጵያም ህዝብም ህወሃቶች ነገ ከስተታቸው ተምረው ይመለሳሉ ሲሉ ይህው ግዜው ነጎደ እነሱም አልተማሩም በመጨረሻም በነሱ አገዛዝ ዘመን ተወልደው ያደጉ ቄሮ አርበኞችና ፋኖ አርበኞች እምቢ ለአገራችን እምቢ ለህዝባችን በማለት በአራቱም የአገራችን መዓዘናት እየተነሱ ይገኛል :: እነዚህ የዘመናችን አርበኞች የሚሞቱበት አላማ እንጂ የሚገሉበት ተልኮ የሌላቸው በመሆኑ በየሚሄዱበት ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉ እጃቸው ላይ ምንም የመሳሪያ አይነት የማይታየው:: የነሱ እምነት  በሰላማዊ መንገድ መንግስትን ማንንበረከክ ነው እየታየ ያለው እውነታውም ይሄው ነው:: << ዋ! ለህወሃቶች ዋ! ለደገፊዎቻቸው እኔን አያርግርኝ ሰዓቱ ሲደርስ ጽዋው ሲሞላ:: መሬት እንኮን ተከፍታ ብትውጣቸው ከነዚህ የዘመኑ አርበኞች ማምለጥ አይችሉም::

ህወሃቶችም ሆኑ የትግራይ ደጋፊዎቻቸው ክፉና አጥፊ ራዕይን ተከትለው የሚመጡ መሆናቸውን የማያውቅ ያለ አይመስለኝም:: ዘወትር ግድያ በሚፈጸምበትና ሕይወት ዋዛ በሆነበት አገር ይልቁንም መንግስታዊ ሽብር በነገሰበት ሥፍራ የኮማንድ ፖስቱ የግድያ ራዕይ ፍንትው ብሎ ይታያል:: የህጻናትን ደም ካፈሰሱ ቦሓላ እንኮ እንደ ገና ተመሳሳይ የበለጥ እልቂት ለማካሄድ በሚፎከርበትና ሰአት በዊጪ ያሉ የህወሃት ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ስብሰባ ተሰብስበው የሰራችሁትና ልትሰሩ ያሰባችሁት ትክክል ስለሆነ እንደግፋችዋለን የሚል መግለጫ ሲያወጡ ለጥቅማቸውና ለሆዳቸው ሲሉ ምን ያህል የትግራይን ህዝብ እንደጠሉ ነው የሚያሳየው::  የህወሃት መንግስት የበለጥ እልቂት ለማካሄድ በሚፎክርበትና ማስጠንቀቅያ በሚያጎርፍበት አገር ከደም ጥማት ይልቅ የደም ስካር እንዳለም ግልጽ በሆነበት ሰዓት ለዚህ ክፉ ራዕይ እየተባበራቹ ያላችሁት የትግራይ ተወላጆች ከህዝባችሁና ከወላጆቻችሁ ከእህት ከወንድሞቻችሁ ከትግራይ ተወላጆች በላይ ጥቅማችሁንና ሆዳችሁ በማስቀደማቹ  የነገሰባችሁን  የደም ጥማትና የደም ስካር በስሙ መጥራት እየፈራችሁ ባለባችሁበት  ሰዓት ነው አሜሪካኖችና አውሮፓዊያኖች ወጥተው ያወገዙት ከማውግውዝም ያለፈ የአሜሪካኑ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ኢትዮጵያ የተጎዙት::

እነዚህ የህወሓት መሪዮችና በጥቅማ ጥቅም እጃቸው በደም የተለወሰው የትግራይ ሙህራኖችና በላጸጋዎች ከንግግራቸውና ክተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያቸው እንደምንረዳው በኮማንዶ ፖስቱና በህወሃት መሪዎች አእምሮ ውስጥ የመሸገው ጥላቻና ንቀት በየሰበቡ እየፈነዳ በአገራችን ወደ ፊት የበለጠ የሰው ህይወት እንደ ቅጠል እንደሚቀጠፍ ለመናገር የግድ ነብይ መሆን አይጠበቅብንም::  በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተሉ የምእራባዊያን መሪዎችም ሆኑ ግለሰቦች  የህወሃት መሪዎችና ኮማንዶ ፖስቱ እንዲሁም በውጪ ያሉ የህወሃት ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በደም የተጨማለቁና በደም የሰከሩ መሆናቸውን ጥንቅቀው እየተረዱ ይገኛሉ::

በአገራችን በኢትዮጵያ የጀግናም የፈሪም የሰላማዊውም የታጋዩም ሆነ የማናቸውም ዜጋ ሕይወት መንግስትታዊ ጥበቃና ዋስትና እንደሌለው ከማናቸውም የህወሓት/ኢሃዴግ መሪ ጋር መከራከር ይቻላል:: ሕይወት በማይከበርበትና ዋጋም ባጣበት አገር ደግሞ ሳይታሰብ የእነዚያም ሕይወት የተበዳዮች ኢላማ ይሆናል:: ሕይወት የማያከብሩ ህወሓቶችም ሆኑ የነሱ አጋር የሆኑ የትግራይ ተወላጆችም ሆኑ ሌሎቹ ከሰባዊነት ጋር በጠላትነት የሚቆሙ ወገኖችና ደጋፊዎቻቻው መዘንጋት የሌለባቸው የነሱም ሕይወት በዒላማ ክልል ውስጥ እንደሚገባ ነው::  ጊዜ ይፍጅ እንጂ መግደል ስትጀምሩ ሞት ወደ እናንተም ያነጣጥራል:: በእኔ እምነት በስልጣን ላይ ያሉት የህወሓት አመራሮችም ሆኑ የህወሓት ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይ ሙህራኖችና ባለ ሀብቶች ማየትና ማስተዋል የተሳናቸው ከፊት ለፊታቸው እየመጣ ያለውን አደጋ አለማስተዋላቸው ነው::

እርግጥ ነው ይህን የህወሓት መሰሪ ተግባር በትግራይ አባቶቻችንና እናቶቻችን አሊያም በትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ እያንዣበበ የለውን ክፉ ቀን የተገነዘቡ የትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር መቆም ጀምረዋል ምሳሌም ለመጥቀስ ወይዘሮ አብርህት ኪሮስ አርያ ትውልደ ትግራይ ሲሆኑ በኢሳት ቴሌቭዥን ቀርበው እንባ እየተናናቃቸው ነበር ቃለ ምልልስ ያደርጉ የነበሩት:: ሌላው ደሞ ወንድማችን አቶ አምባሳደር አለፎም ናቸው  እኝህ ሰው አገር ቤት በነበሩበት ጊዜ የየካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆኑ  እኝህ ወንድማችን በኦሮሞ ሚዲያ ቴሌቭዥን ላይ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው በትግራይ ውስጥ የሚኖሩት የትግራይ እናቶቻችንና አባቶቻችን እንዲሁም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በምን ዓይነት መጥፎ አገዛዝ ስር እንዳሉ በማያሻማ ሁኔታ ግልጸውታል:: ሌላው ደሞ በውጭ የሚገኙት የአርና ትግራይ ደጋፊዎች ሰሞኑን የህወሃትን አገዛዝ በማውገዝ መግለጫ እያወጡ ይገኛሉ እንደነዚህ አይነቶቹ ግለሰቦችም ሆኑ የደርጅት ተወካዮች የትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሊበረታቱ ይገባል:: ከዚህ በፊት ቀደም ብዪ ባወጣሁት ጹሁፊ  እንዳልኩት ሁሉ ዛሬም የምለው <<  የትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለምን አይነሱም ማለት ሳይሆን ጥያቄው መሆን ያለበት ያልተነሱበት ምክንያት ከአብራካቸው የወጡት የእንግዴ ልጆች የሆኑት የህወሓት መሪዎችና ተከተዮቻቸው ምን ያህል ተጽኖ ቢያደርጉባቸው ነው ሊነሱ ያልቻሉት? ምን ዓይነት ትብብር ቢደረግላቸው ነው ከዚህ ጨቆኝ መንግስትና ከአብራካቸው ከተፈጠረው ከህወሀት ሊላቀቁ የሚችሉት የሚል ጥያቄ ነው  መቅደም ያለበት እላለው::

በሌላ በኩል ደሞ ተቃዋሚ ኃይሎችም ሆኑ ሁላችንም የምናቀርበው ጥያቄ <<ወንጀሉን የፈጸሙት ሰዎች ከፍርድ ፊት ይቅረቡ>> ከሚል የዘለለ አይደለም በዓሁኑ ሰዓት አንድ ሰራዊት የሚንቀሳቀሰው ወይ ትዕዛዝ የሚቀበለው ከአንድ የበላይ አዛዡ ከህወሀቶች አሊያም ከኮማድ ፖስቱ ነው:: <<አህያውን ፈርቶ ዳውላውን>> እንደሚባለው ዙሪያውን ከመሸከርከር የሁላችንም ጣቶች ወደ ትክክለኛው ተጠያቂ ወደ ሆኑት ወደ ህወሃት መሪዎችና አቶ ስዩም መስፍን; ወደ አቶ ደብረ ጺዮን ገ/ማርያም; አቶ ስባሐት ነጋ; አቶ በረከት ስመዖን; አቶ አቦይ ጸሃዪ; እና ወደ ኮማድ ፖስቱ ወደ ሲራጅ ፈርጌሳ ማመልከት አለባቸው ባይ ነኝ::

በሌላ በኩል ለኢትዮጵያ የጣር ሰራዊትም ሆነ የፀጥታ  አስከባሪ ፖሊሶች ይህንን ቅዱስ ቃል ከዚህ በፊት ሰምታችሁት ብታውቆም በድጋሚ ላስታውሳችሁ ” ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ሰለ ነበረው መዘዘው የሊቀ ካህናቱንም ባርያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠ የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበር:: ኢየሱስም ጴጥሮስን እንዲህ አለው ሰይፍ የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን   ወደ ሰገባው  መልስ አለው :: <<የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 26: ከ51-53>> ስለሆነም እናንት  የጦርና  የፖሊስ ሠራዊት የሆናችሁ ሁሉ ህዝቡ ላይ አንተኩስም እናት አባቴን እህት ወንድሞቼን አልገድልም በማለት ከዚህ አይነት የታሪክ ውርደት ራሳችሁ የምታወጡበት ሰዓቱ አሁን ነው:: ለህዝብ ደህንነትና እንክብካቤ የቆምክኝ በአገሪቱ ዳር ድንበር ላይ ለመሞት የተዘጋጀው የክፉ ቀን የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት ነኝ ብላችሁ ፍርሃትን ሳትፈሩ ለህወሃት መሪዎች ቁርጡን መናገር ይጠበቅባችዎል ያን ግዜ ነው ከታሪክ ተወቃሽነት የምታመልጡት::  

በተጨማሪ እናንት የጦር ሰራዊት የሆናችሁና የፖሊስ ሰራዊ የሆናችሁ የኢትዮጵያውያን ብርቅዪ ልጃች እስቲ እራሳችሁንጠይቁት ከተራ ወታደር አስከ ሻለቃ ባሻ በውስጣቹ የትግራይ ተወላጅ ሆኖ የህወሓት ታዛዥ ምን ያህል አለበኔ ግምትአንድ እጅ:: ከምክትል መቶ አላቃ እስከ ሻለቃ ምን ያህል የትግራይ ተወላጅ የህወሓት ቅጥረኛ አለሁለት ሦስት እጅ:: ከሌተና / እስከ መጨረሻው እርከን ያሉ የትግራይ ተወላጆችና የህወሓት ቅጥረኞች ምን ያህሉ ናቸው ምናልባትአምስት እጅ:: ታዲያ አሥር እጅ የማይሞሉ የትግራይ ተወላጆች የህወሓት ደጋፊ ወታደሮች እንዴት ነው መሳሪያ የታጠቀንዘጠና እጅ የሚሆነውን ኢትዮጵያዊ ወታደርን ሊመሩት አሊያም ሊያሸንፉት የሚችሉት:: በእኔ እምነት እናንት የጦርሰራዊቶችና የፖሊስ ሰራዊት የሆናችሁ ሁሉ ከዘመኑ አርበኞች ከቄሮዎችና ከፋኖዎች ጋር በመሆን እናንተንም መላውንየኢትዮጵያዊ ከህወሀት አገዛዝ መታደግ የምትችሉበት ሰዓቱ አሁን ነውና የያዛችሁትን መሳሪያ አፈ ሙዙን ወደ ህዝብሳይሆን እናንተንም ቤተሰቦቻችሁንና መላውን ህዝብ ወደ ሚያሰቃዩት ወደ ህወሀት መሪዎች መሆኑን ለነንተ መንገርማለት << ለቀባሪው አረዱት>> እንደማለት ነው::

ደል ለዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችፋኖዎችና ለጦር ሰራዊታችንና ለፖሊስ ሰራዊቶቻችን:: 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s