ኦህዴድ ሆይ ለምሳ ታስበሃልና ለራስህ ስትል እወቅበት። (መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር))

በመጀመሪያ የዶ/ር አብይ አህመድ ጠ/ሚንስትር ተብሎ መሰየምም ሆነ መመረጥ የሕዝብ ትግል ዉጤት ነዉ ብዬ አምናለሁ። ስለዚህም መስዋህትነት እየከፈለ ያለዉን ሕዝብ ማመስገንም ማበረታታትም እፈልጋለሁ። ሁሉም ወገን በደንብ ሊያዉቀዉ የሚገባ ቁም ነገር ግን የወጣቱ ሙሁር በቦታዉ መሰየም የመጨረሻዉ መጀመሪያ ደዉል ብቻ ሳይሆን የሶስትዬሽ የትርፍ ሰዓት የጥሎ ማለፍ ጫወታ ጅማሬመሆኑን ነዉ።

ቡድን አንድ ኦህዴድ እና በተወሰነ መልኩ ብአዴን

የፕሬዘዳንት ለማ መገርሳ ኦህዴድ የመጨረሻዎቹን የትርፍ ሰዓት የጫወታ ጊዜያት በድል ለማጠናቀቅ የሚያስችል ብስለት የለዉም ብዬ ለመናገር አልደፍርም። ከአዉሬዉ ጋር በትህግስት ብዙ ዘመናት የኖሩ በመሆናቸዉም ከመቁሰሉ በፊትም  ሆነ ከቆሰለ በኋላም ያለበትን ደካማ ጎንና አሁንም ያለዉን የጣር ሰዓት ኀይል ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ። ይህም መረዳታቸዉ ነዉ ከሕዝቡ ትግል ጋር ተዳምሮ እዚህ ያደረሳቸዉ። ይህም መረዳታቸዉ ህወኣትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቀብሩት ዘንድ ሊያበቃቸዉ ይችላል። በእርግጥ ነፃነት ለራበዉና ለጠማዉ ሕዝብ የቡድን አንድ ድል አዝጋሚ ይሆናል።

ይህን የትርፍ ሰዓት ሹኩቻ ኦህዴድና የብአዴን ተራማጆች ከሕዝባቸዉ ጋር የበለጠ ለመናበብ ከሞከሩበትና መለስተኛና ከፍተኛ የክልሉ መሪዎቻቸዉ የስልጣናቸዉ ባለቤት ማድረግ ከቻሉ፤ በተጨማሪም ጠንካራ ቄሮና ፋኖ እንዲኖር ከፈቀዱ ብቻ ሳይሆን መዋቅሩ እንዲጠነክር ተግተዉ ከተንቀሳቀሱ፣ በኢዮትጲያ ሕዝብ ልብ ዉስጥ ከሞተ የሰነባበተዉን ህወኣትን መመከት ብቻ ሳይሆን መቅበር ይችላሉ። ቀድሞ እንደተገለፀዉ የዚህ አቅጣጫ ሂደት አዝጋሚ ቢመስልም ጉዞዉ የበርካታ   ትናንሽ ድሎች ስብስብ በመሆኑ ነፃነት የጠማዉን ሕዝብ አቅጣጫ እያመላከቱ ይታገስ ዘንድ ማድረግ ይቻላል።

ይህ ጉዞና መዳረሻዉ ለአዉሬዎቹም የሚበጅ ነዉ። ቢያንስ ቢያንስ ጥቂቶቹ ከተጠያቂነት ሊያመልጡ ይችላሉ።  ወይም የያዙትን ይዘዉ ወይ መቀሌ አልያም ቤጅንግ ሊከትሙ በቂ ጊዜ ሊያገኙ ይችላሉ። ምንም ይሁን ግን ከእንግዲህ ከኢትዬጲያዊያን ጋር የደስታ መሃድ ይቋደሳሉ ብዬ  ተስፋ አላደርግም። ደም የተቃባ ሕዝብ አድርገዉናል።

ቡድን ሁለት ህወኣት

በዚህ ትርፍ ሰዓት ህወኣት የሚንቀሳቀሰዉ ወይም ሊቀምም የሚሞክረዉ መርዝ የኦህዴድንና ብሃዴንን መዋቀር ለመበጣጠስ የሚያስችለዉን ብቻ ሳይሆን ከሕዝቡም ለመነጠል ነዉ። ስለዚህም የመጀመሪያ እርምጃቸዉ መለሳለስ ሆናል። ሴይጣን መልሃክ መስሎ የሚመጣዉ ያህል ሊሆኑም ይችላሉ። አዲስ ጅማሬ በሚል ነጠላ ዜማ ጥቂት ሊያዳምቁ የሚችሉ ተቃዋሚ ተብዬዎችንም ይዘዉ በመምጣት ዳግም ሊያላምዱን መሞከራቸዉ አይቀርም። እርግጠኛ ነኝ ጥቂት የማይባሉም አባዱላዎች አሁንም   በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለዉ የትንሳኤ ማግስት የሆነ እስኪመስለን ማደንቆራቸዉን እንጠብቅ። ይህ ግን የመጨረሻዉ የወያኔ ካርድ በመሆኑ ለአፍታም መዘናጋት የለብንም። እባብ ሁሌም እባብ ነዉ። አበቃ!! ህወኣት ትናንትም ዛሬም እስኪቀበር ድረስም ኢትዮጲያ ለምትባል ሀገርና ኢትዮጲያዊ ለሚባል ሕዝብና ዘይቤ ጠላት ነዉ። ከመፈጠሯ ጀምሮ እጆቿን ወደ አምላኴ ዘርግታ ያለችዉ ይህ ቀድሞዉኑ ታይቷት ይሆን?  አዎን!!  አምላክ ደግሞ የለመኑትን የሚነሳ አይደለምና ጠሏቷ ከእግሯ ስር የመሆኛ ጊዜዉ ተቃርቧል።

ቡድን ሶስት ለነፃነቱ ተፋላሚዉ ሕዝብ

ቄሮም ፋኖም ዘርማም ግንቦት ሰባትም ሌላኛዉም የዉስጥም ይሁን የዉጭ አርበኛ ጥያቄዉ ነፃነት በመሆኑ መልሱም ነፃነት ብቻ ነው። አለመታደል ሆኖ ፍልሚያዉ በአመለካከትም ይሁን በባህሪ ሰዉን ከማይመስሉ ኋላቀሮች ጋር በመሆኑ በዚህ ዘመን ነፃነቴን ብለን መጠየቁ በራሱ አፋሪ ቢመስልም እንደ እንሰሳ መኖና የራሳቸዉ ቀንድ  ብቻ የሚታያቸዉ ዘረኞች ጋር ነዉና ትግሉ መደማማቱ ይቀጥላል።

ይህ ቡድን ተወደደም ተጠላም፣ ጊዜው ይርዘም ወይም ይጠርም  አሸናፊ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነዉ፤ ምክንያቱም ሕዝብ እንደ ሕዝብ ተሸናፊ ሆኖ ሊቀር አይችልም። የእነ ለማና ዶ/ር አብይም ጥንካሬ ይህዉ ብቻ ነዉ። ወያኔም ከሕዝብ ሊነጥላቸዉ የሚንቀሳቀሰዉ ለዚሁ ነዉ። ስለዚህ ይህ ቡድን ኦህዴድንና ጠ/ሚ አብይን ለጊዜዉም ቢሆን ይቀበላል ወይም ታግሶ ጊዜ ሊሰጥ። ቢሆንም ግን በቋፍ ላይ እንዳለ ኦህዴድ ከዘነጋ ከነፃነት ዉጪ ማንም የማያነሳዉ ሰደድ እሳት ይነሳል። እሳቱም የህወኣትን ሬሳ ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም ይበላል። ስለዚህ ኦህዴድ ሆይ ለምሳ ታስበሃልና ለራስህ ስትል እወቅበት።

 

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር። አሜን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s