ለ ዶ/ር አብይ አህመድ፤ አቅጣጫ ማሳያ ወሳኝ ማስታወሻ! (ከሙሉቀን ገበየው)

ከሙሉቀን ገበየው

Dr. Abiy Ahmed, Oromia region of Ethiopia official.

የገዢው ፓርቲ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መጋቢት 18፣ 2010 በመምረጦው እንኳን ደስ አለዎት።  በአሰራር ደንባችሁ መሰረት በቅርብ ቀን ደግሞ የኢትዮጲያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናሉ። እርሶዎ ስልጣን ላይ የመጡበት ግዜ  በአገራችን ታሪክ እጅግ ወሳኝ  ሰአት ላይ ነው። ኢትዮጲያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት። እጅግ ፈታኝና የተወሳሰበ ስራ ይጠብቆታል።

በልጅንትዎ ገና 15 ወይም 16 አመት ወጣት ሁነው  በ1980ዎቹ መጀመርያ በወታደርነት የተቀላቀሉት  ወያኔ መራሹ ኢሕአዴግ ወስጥ አደገው፣ ጎልመሰው፣ ከተራ ታጋይነት እስክ ሌትና ኮሎኔል ማእርግ የበቁ አዋቂ ሰው ሆነዋል። በታማኝነትዎ፣ በልጅነት ቅልጥፍናዎ፣ እንዲሁም ለማደግ በሚያድርጉት ጥርትዎና የቤሄር ተዋጾ  ተጭምሮ በተለይም ተወልደው ባደጉበት የሁሉ ሃይማኖትና ጎሳ አስተናግጅና በቡና ንግድ በከበርችው አጋሮና ጅማ ከተማ ቀምስ መሆኖው ጠቅሞታል። በትምህርትዎ መጎብዘውና  መትጋቶት የከተማን ኑሮ ቀምሰው ቀልጠው በቀሩ የጫካና የበርሃ ታጋዮች መካከል እርሶን ጎላ ብለው ለእድግት  እንዲበቁ እድል ገጥሞታል።

ባጋጥሚም ይሁን የእድል ጉዳይ ሆኖ በ1999 አ.ም. ከውትድርና  ተሰናብተወ  የፖለቲካ ሰው  በመሆን የሲቪሉን ኑሮ ቢጀምሩም በቀላሉ በኦህዲድ አመራር የስልጣን እርከን  ተመቻችቶለታል።

እርሶው ከሌሎቹ የቀድሞ በዋናው ስልጣን ወንበር ላይ ከተቀመጡ  ጓደኞቾዎ በተለየ፣ ለዚህ ስልጣን ብቁ የሚያደርጎት ዝግጁነት አሎዎት። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገር በወታደሩ ሞያ  የነብሮት ልምድና አሁን ደግሞ በሲቭል የፖለቲካ ስልጣን ከክልል እስከ ፌድራል ሚኒስቴር ማእርግ ደርሰው ቢሮክራሲውን በደንብ ማወቆው ለሚገጥሞት ፈትና ዝግጁ ያደርጎታል። መቼም ለዚህ ስልጣን የበቁት ድርጅቶውና ገዢው ፓርቲ ወዶ ፈቀዶ እንዳይመስሎት፤ ይልቅስ በመላ አገሪትዋ የተቀጣጠለው ተቃውም ሰልፈና አመጽ ነው። አንዳንድ ወገኖች የርሶው ስልጣን አወጣጥ ወያኔ ህዝቡን ለማድናገር የሰራው ቲያትር ነው ብለው የሚያምኑ ቢኖሩም፤ ብዞዎቻችን ግን ተስፋ ሰንቀን እንመለኮቶታለን።

አሁን ሊያስተርዳድርዋት  የተዘጋቸችው ኢትዮጲያ፡ ያኔ እርሶ ልጅ ሁነው ወያኔ ሕወሃት መራሹ ኢሕአዴግ ስልጣን ሲቆጣጠር 1980ቹ መጀምርያ  ከነብረው ግዜ ፍጹም የተለይች ናት። እርሶ የንጉሳዊው ስርአትን ገፍትሮ ከጣለው ታላቁ  የ1966  አብዮት ቦኋላ ከተወለዱ ትውልድ መካከል ኖት። ከመቶ ሚሊዮን ሀዝብ በላይ በዲሞክራሲያዊ መብት ረገጣ ፍጹም አስከፊ በሆነ ለ 27 አመታት ሲገዛ  የኖረ፤ በ ጎሳ፣በሃይማኖት ና በተበላሸ ፖለቲካ የተወጠርች አገር ናት። በከፋፍልሀ ግዛው መርሆ ሲሰቃይ የከረመ ትውልድ፤ የጭቆና አገዛዝ አንገፈገፎት ነጻነት ወይም ሞት ብሎ በሰላማዊ መንገድ ህይወቱን ለመሰአውት ያቀረበበት ዘመን ነው።

ስለ እርሶው አመራር ተስፈኞች ሁነን መስተዳደሮትን እንጠብቃለን። ታድያ ፈትና የበዛበት፣ ውስብስብና የተጠላለፈ ስራ እንድሚገጥሞው እናወቃለን። አይወጡትም  ይሆን  የሚል ጥርጣሬ ቢያድርብንም ተስፋ ግን ሰንቀናል። ምን ያህል ከወያኔ (ህወሃት) ተጽኖ ውጪ ነጻ ሰው እንድሆኑ  ማወቅ ባንችልም፡ ወያኔ ሕወሃት  ግን ከአሰበው የህልውናና ዋና ተጽኖ ፈጣሪ መንገዱ ዝንፍ እንዳይሉ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ  እውን ነው። ሆኖም ግን ስራውን ሳይጀምሩ በርሶዎ ተስፋ እንቆርጥም። የቀድሞው ሲቭየት መሪ የነበሩት ጎርቫቾቭ  አባል ከነበሩበት  ከሚጠላው ኮሚኒስት ፓርቲ ተነሰተው ነበር ግልጽነት እና እኪኦኖሚያዊ ጥገና ለውጥ በሚል መሪ መፈክር ትልቅ ሙከራ ያደርጉት። ታድያ ከሳቸው የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ምኞታችን ነው። መቼም ጎርቫቾቭ  ያን አለም ሁሉ ሲያስድነግጥ የነበርወን የቀዝቃዝው ጦርነትን ቢያስቀሩም  አገራቸውን ሶቪየትን ግን ከመገንጣጠል ሳያድኑ ቀርተዋል።

የኢትዮጲያ ህዝብ በተለይም ወጣቱ በርሶዎ ተስፋ አድርጎል፤ ብዙም ይጠብቆበታል። ዋናው ግልጽ እንዲሆንሎት የሚገባው ወሳኝ ነገር ግን ሰላማዊ በሆነ መንግድ ከአስቃቂ አገዛዝ ወደ ዲሞከራሳዊ አስተዳድር የሚያደርጉት ለውጥ ብቻ ነው ሀገሩቱን፣ ክልሎችን  ህዝቡን አቅፎ ሊይዝ የሚችለው።

በኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ ጎሳዎች ሁሉ፣ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ወገኖችን  ቀርበው ማየት ማነጋገር ይኖርቦታል። ይህም በህዝብ አመኔታንና ክብርን እንዲሁም ከወያኔው (ሕወሃት) ለሚሰነዘርቦት ተንኮልና መሰሪ የሚከላከሎት የሚጠብቆት ወሳኝ የጀርባ አጥንት ድጋፍ ይሆኖታል። ወያኔ ሕወሃት ስልጣኑን በቀላሉ አሳልፎ  ይሰጥል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ሲሆን  የህዝብን ብሶት የሚያስተካከል መንገድ ከመርጡ  ይልቁንስ መሰሪ ተግባሩን የረቀቀ ተንኮሉን ተጠቅሞ ሊያከሽፈው እንደሚሞከር ግልጽ ነው። እርሶም በስራእቱ ውስጥ በነበሩበት ወቅት  በጸጥታና መርጃ ስራ ልምዶው የወያኔውን ተንኮል ይስቱታል አይባለም። ዋናው ማርከሻውን መድሃኒት አስቀድሞ ማዘጋጀት አለቦት። በሻርክ የተሞላ ባህር ላይ የሚቀዝፉትን ጀልባ አስተማማኝ ወደብ ላይ የሚያደርሶትን  አቅጣጫ ማሳያ (ኮምፓስ) መጠቀም ይገባዎታል።  ከዚህ ዝንፍ ብለው የወያኔው አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚንስቴር መሆኑን ከመርጡ ግን በህዝብ ተንቀው፣ እጣ ፈንታዎ ዳግማዊ ሐይለማርያም ደሳለኝ ወይም ከዚያ የባሰ ነው የሚሆነው።

ይህን አደገኛ ባህር በሰላም ይሻግሩት ዘንድ፤ ህዝባችንንም ከመሪር አገዛዝ ተገላግሎ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ጅምሬ እንዲገባ የሚረዳ፣  አቅጣቻ ማሳያ የሚጠቁሞት (ኮምፓስ) ፍሬ ሃሳብን   ከታች ስዘርዘር  ቅድሚያ እንዲሰጡት በማሳሰብ ነው፡

 1. በሀገርችን ኢትዮጲያ ያሉትን ጎሳዎች ሁሉ፤ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን፣በእድሜ፣በጾታ፤ በሀይማኖት፣በአካል ጉዳት በመሳሰለው ሳይመርጡ ያቅርቡ፣ያነጋገሩ። ይኄም አላማዎን ሊቀለብስ የሚነሳውን ማንኝወንም ሃይል ወይም የወያኔ ሴራ ይቋቋሙሎታል።
 2. እጅግ ግልጽና ጎላ ባለ መልክ  ሊፈጽሙት ያሰቡትን መንግስታዊና ፖለቲካዊ ለውጦች በቅርብ ቀናት ለአትዮጲያ ህዝብም ለጠላቶችዎም ያሳወቁ፤
 3. ለዲሞክራሲያዊ አስተዳድርና ለለውጥ የተዘጋጁ በትምህርትም፣ በችሎታም እንዲሁም ለለውጥ የተነቃቁ ባለሞያዎች፣ የፖለቲካ ሰዎችና  መልካም ዜጎች  በአማካሪነት  ይሰብሰቡ/ይቅጠሩ።
 4. አገር አቀፍ  ምክክርና መግባባትን እንዲሁም የህዝብ-ለሀዝብ መልካም ግንኙነቶችን  ያጠናከሩ ያበረታቱ።
 5. በኢቲዮጲያ እንዲሁም በውጭ ሀገር ያሉ የፖለቲካ ደርጅቶችን የታገዱትን  ሁሉ ጨምሮ በሰላም በሀገራችወ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ያደርጉ፣ ያበረታቱ።
 6. በህገ-መንግስት በተሰጦው ስልጣን መሰረት በተለይ የጸጥታውና መርጃ  እንዲሁም ወታደራዊ ክፍሉን የመቆጣጠር ስልጣኖን ያረጋግጡ። ሊይስፈጽሙ ያሰቡትን ለውጥ እንቀው ሊይዙ የሚችሉትን የአሁኑን የነዚህ ከፍል አመራሮችን ለመቀየር ይሞክሩ፤
 7. በወያኔ የበላይነት በተመራው የህዝብ መሬት ነጠቃና ዝርፊያ ላይ፣እንዲሁም ኤፈርት በሚባል በሚታወቀው የወያኔ ንግድ ድርጅት ህገ-ወጥ ተጽኖ የኢኮኖሚውን ዘርፈን ማላቀቅና በአገዛዙ የተደርጉ የኢኮኖሚ ምዝበራና ዝርፍያ፣ እርስ በርስ መጠቃቀሚያና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት  ያላቅቁ። ይህን የሚመርመር ኮሚሽን ይመስርቱ።
 8. የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን፤ታዋቂ ሙሁራኖችን እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎችን ያካተተ የምርጫ ቦርድን ገለልትኛነት የሚያረጋግጥ ተግባር ይፈጽሙ።
 9. ነጻ ሃሳብ መግልጫ  መድርኮችን ( የህትመት፣ የድምጽ ና ምስል የህዝብ መገንኛ ) እንዲስፋፉ ያበርታቱ፤
 10. የፍትህ አካሉን፣ የፖሊስና የአገር መክላከያ ሰራዊትን ከፖለቲካ ተጽኖ ወጪ ለማድርግ አጥብቀው ይስሩ። ይህ እጅግ አስቸግሪ ስራ እንድሚሆን ይታወቃል። ገዢው ድርጅት ለለውጥ ካልተዘጋጀ የሚፈጸም አይሆንም።
 11. ሁሉንም የፖለቲካ እስርኞች ይፍቱ። የማሰቃያ እስር ቤቶችን እንዲዘጉና ሙዚየም እንድሆን ያበርታቱ፤
 12. የሚቻል ከሆነ ( አገዛዙ መቼም አይፈቀደወም) ሁሉን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ታዋቂ ሙሁራንና የአገር ሽማግሌውችን፣እንዲሁም ሲቪክ መሃበሮችን ያቀፈ ጊዛያዊ  ምክር ቤት ተቋቁሞ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ቢደረግና፤ ይህም ምክር ቤት እውነተኛ ህገ-መንግስትና ምርጭ በሁለት አመት እንዲያዘጋጅ ቢያበርታቱ፤
 13.  ቁጥር 12 የማይቻል ከሆነ፣ የሚቀጥለው ምርጫ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰልማዊና ፍታሃዊ መንገድ የሚወዳድሩበት መድርክ ተዘጋጅቶ በአለምአቀፈ  ታዛቢዎች የሚገኙበት ከ 1997 አ.ም  ምርጫ የተሻለ እንድሆን መጣር፤
 14. በየሳምንቱ  በራድዮ ፣ቴሌቪዥን እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያ እየቀርቡ ያቀዱትን ፣የተልሙትን የፈጸሙትን እንዲሁም የገጥሞትን ፈትና ለህዝብ  ቢያቅርቡ፤ ዘመኑ የመረጃ ዘመን መሆኑን አይዘነጉትም።
 15. ሊያመጡ ላሰቡት ፖለቲካዊ ለውጦች ያግዞት ዘንድ የአለም ሃያላን ከሆኑ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪ ከሆኑ አገሮች ጋ መልካም ግንኙነት ይፈጥሩ።

ነገ ምን ይዘው እንደሚመጡ  የማያወቀው ብዙሃኑ ህዝብ በርሶ መመርጥ ታላቅ መነቃቃትና ተስፋ ማሳደሩ ህዝቡ ምን ያህል ለወጥ ነፍቆት እንደነበር ያሳያል።

ያሰቡትን መልካም ነገር ያሳክሎት ዘንድ መልካም ምኞቴን እየገልጽኩ፤ ነገር ግን ዋናው ጉዳይ አገራችንና ህዝባችንን ሰርንቆ ለያዘን እኩይ አግዛዝ፣ መብት ረገጣ መፍቴሄው ሰላምዊ ዲሞክራስያዊ ስርአትን መገንባት ብቻ መሆኑን ሳልጠቁሞት አላልፍም።

እግዚሓቤር  አገራችን ኢትዮጲያንና  ህዝባችን ላይ ከወረደው መከራ እንድናወጣ ይረዳን!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s