‹‹የጦቢያ አራት ዓይና ፖለቲከኞች!!!›› ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር፤ ››

/**/

ለአቶ አሰፋ ጮቦ መታሰቢ ትሁን

‹‹በህብረ-ብሄራዊ የሃገር ፍቅር አገር ይገነባል፣ በጠባብ ብሄራዊ ስሜት አገር ይፈርሳል!!!››

የዲጂታል ዘመኑ ተመራማሪ ወጣት የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ  ኤርሚያስ ለገሠ የፌዴራል መንግሥቱ ከቻይና ተበድሮ ለትግራይ ክልል በሚሰጠው 8 ቢሊዮን ብር በመረጃ ላቀረበው ጹሁፍ የምናውቀውን እንድናጋራ በጠየቀን መሠረት፣ በስታትስቲክስ የተደገፈና መረጃው ምንጭ የተጠቀሰ፣ በአጭሩ  የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ ነው፡፡ ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር፤ ›› የሚቀርቡ ጥናታዊ ፁሁፎችን በኢሳት ለህዝብ በማካፈል ታሪካዊ ግዳጃችሁን በመወጣት ያለማስረጃ የሚወጡ ፁሁፎችንና ንግግሮችን እየተከታተሉ በማጋለጥ ምሁራዊ ባህል ከተጠናከረ ያለጥናት የሚቀርብ የካድሬዎች ንግግር የፕሮፓጋንዳ የወያኔ ካድሬ የወሬ ፍጆታ ይሆናል፡፡ የፖለቲካ ሳይንንስና የታሪክ ትምህርት፣ በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን እልፋ አዕላፍ መረጃ መዛቅ እየተቻለ የሃገራችን አንድ ዓይና የፖለቲካ ደብተራ፣ ዲስኩር በማሳመርና በየመድረኩ የሰላ ምላስ አፈ ጮማ ምላስ ይዞ፣ ያለጥናትና ማስረጃ የሚያደርጉት ንግግሮች ከአሁኑ መታረም አለባቸው እንላለን፡፡ ማንም ፖለቲካኛና ጋዜጠኛ ከማውራቱ በፊት፣ ከመጠየቁ በፊት ማንበብና የማስረጃ ምንጭ መጥቀስ ይጠበቅበታል፡፡ ቅዱስ መፅሃፈቱ  ቅፅና ቁጥር አንድ አስከ …፣ ህገመንግስቱ፣ ከአንቀፅና ቁጥር ጠቅሶ፣ የፍትሃ ብሄርና ወንጀለኛ መቅጫ ከአንቀፅና ቁጥር ጠቅሶ ነው የእውቀት አውድማ፣ ፍሬው ተዘርቶ፣ ምርቱ ታጭዶ፣ ለአካላችን እድገት በምግብነትና ለህሊናችን  የዕውቀት ብልፅግና ይሆናል፡፡ ጋዜጠኞች ሳያውቁ መጠየቅ፣ ፖለቲካኞች ሳያነቡ ማነብነብ፣ የመረጃውን ምንጭ አለማሳወቅ የዕውቀት መፋለስ ያስከትላል፡፡ ምንጩ ያልታወቀ፣ መረጃው ያልታወቀ ነገር ሁሉ፣ በህዝብ ዘንድ የፖለቲካ ጥላቻና የዘር ፍጅት ያስነሳል፡፡ አበው ‹ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም› ይላሉ፡፡

የእግዜር ውኃ!!!  ‹‹በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ 15 ሊትር በቀን ሲሆን በአፍሪካ አገራት የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ 47 ሊትር በቀን ነው!!!

በኢትዩጵያ የወንዝ ተፋሰሶች፣ ኢትዮጵያ በዓለም ከሚገኙ ሃገራቶች በውሃ ኃብት ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘች ሃገር ናት፡፡ በሃገራችን መልክዓ ምድር የተለያዩ ወንዞችና ሐይቆች ይገኛሉ፡፡ ከሃገራችን ወንዞች ከሰሜን ምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች በመነሣት ወደ ምዕራብ ዝቅተኛ ሥፍራዎች የሚፈሱት ዓባይ፣ ተከዜና ባሮ ወንዞች ይገኛሉ፡፡ የጊቤ ወንዝ ደግሞ ከደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች በመነሣት ወደ ደቡብ ዝቅተኛ ሥፍራዎች ይፋሳል፡፡ ከደቡብ ምሥራቅ ከፍተኛ ቦታዎች የሚነሱ ወንዞች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ዝቅተኛ ሥፍራዎች ይፈሳሉ፡፡ የአዋሽ ወንዝ ከምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች በመነሣት ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በመፍሰስ ወደ ሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ ይጎዛል፡፡ አዋሽ ወንዝ የስምጥ ሸለቆን አካባቢን በስፋት ይሸፍናል፡፡ {1} ዓባይ ወንዝ ከሰሜን ምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች የፍሰት አቅጣጫው ምዕራብ ዝቅተኛ ሥፍራ ይፈሳል፡፡ {2} ተከዜ ወንዝ ከሰሜን ምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች የፍሰት አቅጣጫው ምዕራብ ዝቅተኛ ሥፍራ ይፈሳል፡፡ {3} ባሮ ወንዝ ከሰሜን ምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች የፍሰት አቅጣጫው ምዕራብ ዝቅተኛ ሥፍራ ይፈሳል፡፡ {4} ዋቢ ሸበሌ ወንዝ ከደቡብ ምስራቅ ከፍተኛ ቦታዎች የፍሰት አቅጣጫው ምሥራቅ ዝቅተኛ ሥፍራ ይፈሳል፡፡ {5} ገናሌ ወንዝ ከደቡብ ምስራቅ ከፍተኛ ቦታዎች የፍሰት አቅጣጫው ምዕራብ ዝቅተኛ ሥፍራ ይፈሳል፡፡ {6} ጊቤ ወንዝ ከደቡብ ምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች የፍሰት አቅጣጫው ደቡብ ዝቅተኛ ሥፍራ ይፈሳል፡፡ {7} አዋሽ ወንዝ ከደቡብ ምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች የፍሰት አቅጣጫው ሰሜን ምስራቅ ዝቅተኛ ሥፍራ ይፈሳል፡፡ የኢትጵያን ስነምድራዊ(ወንዞቹ፣ ሃይቆቹ፣ ተራሮቹ ሜዳና ሸንተረሩ፣ ዓየሩ) ግዛትን ሰው ሊገነጣጥለው፣ ሊከልለው፣ ሊሸነሽነው አይቻለውም፡፡ ተፈጥሮ ብቻ እንጂ!!! የኢትጵያና ኤርትራ ስነምድርና ህዝብ ትላንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አንድ ነው፡፡ ህልመኛ ገዥዎች ይሄዳሉ ይመጣሉ፣ ምናባዊው ክልልና የድንበር ወሰን ለህዝብ ህሊና ውስጥ የለምና!!! ከሃገራችን ወንዞች ከሰሜን ምዕራብ ከፍተኛ ቦታዎች በመነሣት ወደ ምዕራብ ዝቅተኛ ሥፍራዎች የሚፈሱት ዓባይ፣ ተከዜና ባሮ ወንዞች ሲሆኑ በጥናት በተረጋገተው መሠረት በኤርትራና በትግራይ ክፍለ ሃገራቶች ጣልያን አስመራን በተቆጣጠረበት ዘመን የመጠጥ ውኃ ችግር ከፍተና መሆኑን በጥናታቸው አረጋግጠዋል፡፡ እስካሁንም የመጠጥ ውኃ ችግር አለ፣ የከርሰ ምድር ውኃ አለመኖርና የተከዜ ወንዝ ፍሰት ዝቅተና በመሆኑ የተከዜ የሃድሮኤሌትሪክ ግድብ በውኃ እጥረት የተባለውን ኤሌትሪክ ኃይል እንደማያመነጭ ጥናቶች በተደጋጋሚ ገልፀዋል፡፡ በትግራይ ክልል ያለሳይንሳዊ ጥናት በጠባብ ብሄርተኝነት ስሜት ብቻ በመነሳሳት የሚሠሩ ብዙ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንደኛው የውኃ ልማት ፕሮጀክቶች ሃገሪቱን ለቻይና የውጪ ዕዳ የዳረጉን ናቸው፡፡ ‹‹በህብረ-ብሄራዊ የሃገር ፍቅር አገር ይገነባል እንጅ፣ በጠባብ ብሄራዊ ስሜት አገር አይገነባም!!!›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመረጃ ያልተረጋገጠና ጥናት ላይ ያልተመሠረተ ንግግር ውሎ አድሮ ምሁራዊ ዕሴቶን እየሸረሸረ የፖለቲካ አሽከርነትና ተራ ካድሬነት ህሊናዎን የሚያወርድ ይሆናልና ጠንቀቅ ማለት ደግ ነው፡፡ በህወሓት. ኢህአዴግ ፖለቲካ ልማታዊ መንግስት፣ አብዬታዊ ዴሞክራሲና ዴሞክራሲዊ ማዕካላዊነት የሚመራው ፓርቲዎ ከዚህ በላይ እንደማያሰራዎ አበው ፖለቲከኞች ማወቃቸውን ለሰከንድ አይጠራጠሩ፡፡ የሱማሌና የኦሮሞ ክልል ህዝቦች የተፈጠረውን ግጭት በንግግር ብቻ እርቀ ሰላም ወርዶል ማለት የህግ ሉዓላዊነትና በህግ ፊት ሁሉም እኩል መሆኑን በህገመንንግሥቱ የመኖር መብታቸውን ያጡ የሞቱ ሰዎች ገዳዬች ለፍርድ ማቅረብ ግድ ይላል፡፡ አንድ ልጃቸው የሞተባቸው እናት ፍየል የታረደ መሰለው እንዴ ብላዎታለች ለአሜሪካ ሬዲዮ ድምፅ !!! በመከላከያ ሠራዊቱ አባሎች በነገሌ ቦረና ሞያሌ የተገደሉ ሰዎች ለፍርድ ማቅረብ፣ በኦሮሚያ፣ አማራና ሌሎች ክልሎች የተገደሉተትን ሰዎች ገዳዮቹን ለፍርድ በማቅረብ፣ በሃገሪቱ የህግ ሉዓላዊነት መስከበር ሥራ ሀ ሁ ነው፡፡ ለዚህ ነው ኤች አር 128 በአሜሪካ የህዝብ ተወካች ምክርቤት የፀደቀውን ይረዳዎታልና ልብ ይበሉ፣ በሃገራችን የዛሬ አርባ አመት በፊት የተሠራ ወንጀል፣ የቀይ ሽብር ወንጀለኞች እየታደኑ ለፍርድ መቅረባቸውን አንድ ይበሉ፡፡ ህዝቡ  ጥያቄ ፍትህ ይስጠን ፣ የሙስና ወንጀለኛች ለፍርድ ይቅረቡ፣ አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ይነሳ፣ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉም ይፈቱ፣ የባህር ማዶና የሃገር ውስጥ ፖለቲከኞችን ያሳተፈ ሁሉን አቀፍ ጉባዔ ይጠራ፣ የፕሬስ ነፃነት ይከበር፣ ይህን በፍጥነት ካላሳዩ የህዝቡ እንቢተኛነትና ተጋድሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመላ ሀገሪቱ ይቀጥላል እንላለን፡፡  ሃገራችን አራት ዓይና ፖለቲከኞች እንዳሎት አይጠራጠሩ፡፡ ሃገሪቱ በሁሉ መስክ የተማረ አርቆ አስተዋይ ዜጋ እንዳላት ለቅንጣት ያህል ለማይክሮ ሰከንድ አይጠራጠሩ፡፡ በሃገሪቱም ፖለቲካ አንጋፋ ጥርሳቸውን የነቀሉ ጉምቱ ፖለቲካኛ ልሂቃን ስላሉ የስጥዎትን ዕድል ተጠቀሙበት!!! የሃገሪቱን ምሁር የሚያሰራው ሥርዓት ጠፋ እንጂ፣ ለሃገሩ ህዝብ አራት  ቢሊዮን ዶላር በዓመት ሃገርቤት በመላክ ዘመዶቹን የሚያስተዳድር ዲያስፖራ  ሲሦ መንግሥት መሆኑን መረዳት ያሻል፡፡ ዶክትር አብይ አህመድ ጥፋትዎ ሲገለፅልዎት በጊዜው ይቅርታ የመጠየቅ አልያም የማስረዳት ባህል ቢኖርዎ፣ ህዝብና ምሁሩ ዓይኖ ውስት የገባ ጉድፍ በማውጣት ሊያግዝዎ ይችላል እንላለን፡፡ ለዚህ ነው ይህ ጥናታዊ ፁሁፍ ለአራት ዓይናው ፖለቲከኛ ለአቶ አሰፋ ጮቦ የይቅርታው አባታችን መታሰቢ ትሁን ዘንድ የተበረከተው፡፡

{1} ተከዜ ኃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ ትግራይ ክልል፣ ከ1994-2001 እኤአ  የተሠራ  የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት ግድብ ሲሆን ግድብ በተከዜ ወንዝ ላይ  በ2007 ዓ/ም ለማጠናቀቅ ታቅዶ በመሬት መንሸራተት ችግር ምክንያት ፕሮጀክቱ የተጠናቀቀው በ2009 ሲሆን አጠቃላይ የግንባታ ስራው የፕሮጀክቱ ወጭ በ1.5 ቢሊዩን ብር ወይም 365 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲደርስ 360 ሜጋ ዋት ያመነጫል ቢባልም 75 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ሃይል እንደሚያመነጭ ይታወቃል፡፡  የፕሮጀክት ተቆራጭ  ኮንትራክተር የቻይናው ዳንግ ፉንግ ግሩፕ(ሲጂጂሲ) ነበር፡፡ ዳንግ ፉንግ፣ የቻይና ኩባንያና የተከዜ የኃይል ማመንጫ፣ ‹‹ጉዳት የደረሰበትን የተከዜ ኃይል ማመንጫ ለመጠገን የቻይና ኩባንያ ምላሽ እየተጠበቀ ነዉ››የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግንባታው በ2001ዓ/ም ተጠናቆ ወደ ሥራ የገባው የተከዜ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እያንዳዳቸው 75 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይልን ማመንጨት የሚችሉ አራት ተርባይኖች ሲኖሩት ፣ በአጠቃላይ 300 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ቢታቀድም ከ75 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ከማመንጨት ያልዘለለና በውሃ እጥረትም ምንም  ማመንጨት ያልቻለ  ነው፡፡ የተከዜ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን ለመጠገን ፣ዳንግ ፉንግ የተባለው የቻይና ኩባንያ ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን የኢትዩጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ገለፀ፡፡ ድርቁ ባስከተለው የዝናብ እጥረት ግድቡ በቂ ውሃ ማጠራቀም ባለመቻሉ፣ እንዲሠሩ ከተደረጉት ኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ከአራቱ ሶስቱ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ተጠቁሞል፡፡ ሁለቱን ተርባይኖች ለመጠገን ቀድሞ ጀኔሬተሮችን አምርቶ የገጠመው የቻይናው ዳንግ ፉንግ ኩባንያ ለጥገና የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን አቅርቦ እንዲተክል የተጠየቀ እንደሆነ ተገልፆል ነበር፡፡ ኤስጂዲሲሲ፣ የቻይና መንግስት ኩባንያ ኤስጂዲሲሲ የተባለው የቻይና መንግስት ኩባንያ በ80 ሚሊዩን ዶላር መቐለ፣ደሴ፣ባህርዳር፣ድሬዳዋን ጨምሮ በስምንት የክልል ከተሞች የኮንክሪት ማሠራጫ ግንባታ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ መስመር ከመለወጡ ጎን ለጎንም የትራንስፎርመር እድሳት ያከናውናል፡፡ ወያኔ መንግስት ተከዜ ኃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስም፣ በውኃ ፕሮጀክቶች ስም! በትግራይ ህዝብ ሰም ፕሮጀክት ገንዘቡን እንደሚመዘብር ግልፅ ነው፡፡

{2} በትግራይ የውሃ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት፣ በመቀሌ በ8 ቢሊዮን ብር የውሃ ግድብ ግንባታ ሊጀመር ነው(ኢሳት ዲሲ- ሚያዝያ 5/2010 ) በመቀሌ ከተማ ያለውን የውኃ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት የፌዴራል መንግሥት ከቻይና መንግስት ባገኘው  8 ቢሊዮን ብር የግድብ ግንበታ እንደሚጀምር ተገለፀ፡፡ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅም ለከተማዋ ከሚያስፈልገው የውሃ መጠን ከሁለት ዕጥፍ በላይ ተጨማሪ ውሃ እንደሚያስገኝ ተመልክቶል፡፡የህወሃት ንብረት የሆነው ሬዲ ፋና እንደዘገበው የመቀሌ ከተማ በየቀኑ የሚያስፈልገው 50 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ቢሆንም እየቀረበ ያለው ግማሽ ያህሉ 25 ሺ ሜትር ኪዮብ ውሃ ነው፡፡ችግሩን ለመፍታት የክልሉ መንግሥት እያደረገ ባለው ጥረት ተጨማሪ 18 ሺ ሜትር ኪዮብ ውሃ የሚያስገኝ ግድብ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ሆኖ የከተማዋን የውሃ ፍላጎት ለማርካት ተጨማሪ 7 ሺ ሜትር ኪዮብ ውሃ የሚያስፈልግ በመሆኑ ከቻይና መንግሥት በተገኘ 8 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ግድብ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ትግራይ ክልል ውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ተስፋ ሚካኤል ገብረዮሀንስ ገልፀዋል፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ ከቻይና ተበድሮ ለትግራይ ክልል በሚሰጠው 8 ቢሊዮን ብር  ተጨማሪ 147 ሺ ሜትር ኪብ የመጠት ውሃ በቀን እንደሚመነጭም ተመልክቶል፡፡ በዚህም በአጠቃላይ በትግራይ በቀን የሚመነጨው የመጠጥ ውሃ ከፍላጎቱ በ140 ሺ ሜትር ኪዮብ ባልጫ እንደሚኖረው ተመልክቶል፡፡ በርዕሰ መዲናዋ አዲስ አበባ ወደ 4 ሚሊዮን ህዝብ በመጠጥ ውሃ በሚቸገርበት ወቅት የፌዴራል መንግሥት 8 ሚሊዮን ብር ተበድሮ በአሁኑ ወቅት 220 ሺ ነዋሪ ላላት መቀሌ ከተማ ቅድሚ መስጠቱ በምን መክንያት እንደሆነ አልታወቀም፡፡ በውሃ ጉዳዮች ላይ ጥናት የሚያደርገው ወተር . ኦርግ ባደረገው ጥናተት ከኢትጵያ 100 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 61 ሚሊዮን የሚሆነው የንጹህ መጠጥ ዉሃ እንደማያገኝ አረጋግጦል፡፡ የመቐለ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውህ ችግርና ይፈታል የተባለ ግድብ በ8 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነው፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)‹‹ስለሆነም የትግራይ ክልል መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ባደረገው ትረት ቤቀኑ 18 ሺህ ሜትር ኪብ ውሃ ማቅረብ የሚስችል የገረብ ሰገን ግድብ ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን የትግራይ ክልል ውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ተስፋሚካኤል ገብረየውሃንስ ገለፁ፡፡የፈፌዴራል መንግስት ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን ሚችል የገረብ ጋባ ግድብ ለመገንባት የሚያስችል ብድር በማፈላለግ ላይ እንደነበር አንስተዋል፤ በዚህም መንግስት በብድር መልክ ሊሰጥ ፈቃደኛ የሆነው የገንዘብ መጠን በግናቦት ወር ስምምነቱ እንደሚፈረምም ጠቁመዋል፡፡ ግድቡ ግንባታም መስከረም ወር 2011 ዓ/ም ለመጀመር ሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ዕየተደረገ እንደሆነ የጠቀሱት ዶክተር ተስፋሚካኤል ግድቡ ግንባታ አሶስት ኣመት እንደሚጠናቀቀቅ ተናግረዋል፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ በየቀኑ 147 ሽህ ኪብ ሜትር ንፁህ መጠጥ ውሃ ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡››

  • የመቀሌ ከተማ በየቀኑ የሚያስፈልገው 50 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ቢሆንም እየቀረበ ያለው ግማሽ ያህሉ 25 ሺ ሜትር ኪዮብ ውሃ ነው፡፡
  • የትግራይ ክልል መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ባደረገው ጥረት በየቀኑ 18 ሺህ ሜትር ኪብ ውሃ ማቅረብ የሚስችል የገረብ ሰገን ግድብ ግንባታ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡
  • የመቀሌ ከተማ በየቀኑ የሚያገኘው 25 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ እንዲሁም እየተጠናቀቀ ያለው 18 ሺህ ሜትር ኪብ ውሃ ሲደመር 43 ሺህ ሜትር ኪብ ውሃ ይሆናል፡፡የከተማዋን የውሃ ፍላጎት ለማርካት ተጨማሪ 7 ሺ ሜትር ኪዮብ ውሃ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡
  • የፌዴራል መንግሥቱ ከቻይና ተበድሮ ለትግራይ ክልል በሚሰጠው 8 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ 147 ሺ ሜትር ኪብ የመጠት ውሃ በቀን እንደሚመነጭም ተመልክቶል፡፡ ወያኔ መንግስት በውኃ ፕሮጀክቶች ስም! በትግራይ ህዝብ ሰም ገንዘቡን እንደሚመዘብር ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በ380 ሚሊዮን ብር ወጪ የውሃ ግድብ ተሠርቶ ተጠናቆ ነበር፣ ግድቡ ከትንሽ ጊዜ በኃላ ደረቀ ይህ የሚያሳው ያለ አንዳች ጥናት የሚገነባና ውጤት አልባ ሥራ መሆኑ የትግራይ ህዝብ ይመሠክራል፡፡ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ጋምቤላ፣ መቐለ፣ ወዘተ ህዝብ እንደማንናውም የሃገራችን ህዝብ በውኃ ጥም በወያኔ መንግሥት የሚሠቃይ ህዝብ ነው፡፡  ህዝቡን ውኃ ማጠጣት ያልቻለ መንግስት ሊገዛ ከቶውንም አይችልም፡፡ ወያኔ መንግስት በውኃ ፕሮጀክቶች ስም! በትግራይ ህዝብ ሰም ገንዘቡን እንደሚመዘብር ግልፅ ነው፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት 8 ቢሊዮን ብር በፌዴራል መንግሥቱ ስም ከቻይና ተበድሮ፣ ተከዜ ኃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስም፣ በውኃ ፕሮጀክቶች ስም!፣ የመቐለ የባቡር ፕሮጀክት ብድር፣ የአድዋ የፓን አፍሪካ ዮኒቨርሲቲ ግንባታ የፌዴራል መንግሥት 200 ሚሊዮን ብር ሲለግስ በቀጣይነት ሌሎች ክልሎችና የአፍሪካ አገራቶች ይቀጥላሉ ፕሮጀክት በመቅረፅ ገንዘብ መዝረፍ የደደቢት ወያኔዎች የቆየ ምሁራዊ ባህል ነው!!!  ወዘተ   በወያኔ ትግራይ ህዝብ  ስም ያለሳይንሳዊ ጥናት በጠባብ ብሄርተኝነት ስሜት ብቻ በመነሳሳት የሚሠሩ ብዙ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንደኛው የውኃ ልማት ፕሮጀክቶች ሃገሪቱን ለቻይና የውጪ ዕዳ የዳረጉ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ  ህዝብ ሰም ገንዘቡ ከውጭ እየተበደሩ በመዝረፍና በመጨረሻም የውኃው  ፕሮጀክት ውጤቱ የከርሰ ምድር ውኃ ጠፋ እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ ‹‹በህብረ-ብሄራዊ የሃገር ፍቅር አገር ይገነባል እንጅ፣ በወያኔ ጠባብ ብሄራዊ ስሜት አገር አይገነባም!!!›› በኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም ክልሎች የተማሩ ዜጎች እንዳሎቸውና ምሁራኑም የህዝቡን የተፈጥሮ ኃብትና ንብረት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ማታለል አይችልም፡፡ ያለኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት ወንዝ አያሻግርም!!! ዳክተር አብይ አህመድ የፌዴራል መንግሥቱ ከቻይና ተበድሮ ለትግራይ ክልል በሚሰጠው 8 ቢሊዮን ብር   ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ብድሩ ሳያፀድቀው የሚሠራ ወንጀል በመሆኑ ብድሩ ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት እንዲመራና እንዲፀድቅ ካልተደረገ ህዝባዊው ትግል ይቀጥላል፡፡

የእግዜር ውኃ!!!  ‹‹በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ 15 ሊትር በቀን ሲሆን በአፍሪካ አገራት የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ 47 ሊትር በቀን ነው!!!

የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ (Per Capita water Consumption)፣ የአንድ ሰው የውኃ ድርሻ በቀን፣ ለመጠጥ ውኃ፣ ለአከላት መታጠቢያ፣ ለምግብ ማብሰያ፣ ለልብስ ማጠብያ፣ ወዘተ የውኃ ፍጆት ሊትር በቀን ድርሻ የሚያሳይ ዓለም አቀፋዊ መለኪያ ነው፡፡በዚህም መሠረት የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ ድርሻ፣ በአፍሪካ አገራት 47 ሊትር በቀን፣ በእስያ አገራት 85 ሊትር በቀን፣ በእንግሊዝ 334 ሊትር በቀን፣ በአሜሪካ 578 ሊትር በቀን የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ በቀን እንደሆነ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድረ-ገፆች ሪፖርቶች የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡ የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ ድርሻ፣ የአንድን አገር የእድገት ደረጃ መለኪያ የውሃ መጠጥ አቅርቦትና የንጽህና አጠባበቅ (Access to watersupply and sanitation) የሚያሳይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የውሃ መጠጥ አቅርቦትና የንጽህና አጠባበቅ፣ በአንደኛውና ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መረጃ መሠረት በብሄራዊ ደረጃ፣ በገጠርና በከተማ ያለውን የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ ሊትር በቀን ጥናቱ ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ 15 ሊትር በቀን ድርሻ በብዙ የሃገሪቱ ክልሎች የአንድ ቤተሰብ የቀን ፍጆታ ሆኖ እናገኘዋለን፣ በዚህ መሠረት የአንድ ቤተሰብ አባወራ/እማወራ አማካ የቤተሰብ ብዛት 5 ሲሆን 15 ሊትር ውኃ ድርሻ ወደ 3 ሊትር ይሆናል፡፡ ጥናቱ መሠረት በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ 3 ሊትር በቀን ሆኖ ይገኛል፡፡

{1} በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፤ GTP I (2010-2015)፣ የአንድ ሰው የውሃ ፍጆታ በቀንና የአገልግሎቱ ድርሻ ሽፋን ርቀት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በዚህም የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን መረጃ መሠረት፡-በሃገሪቱ ብሄራዊ  የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን 84%  በመቶ፣የገጠር የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን 82% በመቶ፤15 ሊትር በቀን፣የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ በቀን ሲሆን ተደራሽነቱም በ1.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ነበር፡፡ የከተማ የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን 91% በመቶ፤20 ሊትር በቀን፣የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ በቀን ሲሆን  ተደራሽነቱም በ0.5 ኪሎ ሜትር ርቀት  ተብሎ በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፤ ያለጥናት ወያኔ መንግሥት ገልፆ ነበር፡፡

{2} በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፤ GTP II (2016-2020)፣ የአንድ ሰው የውሃ ፍጆታ በቀንና የአገልግሎቱ ድርሻ ሽፋን ርቀት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በዚህም የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን መረጃ መሠረት፡-በሃገሪቱ ብሄራዊ የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን መረጃ መሠረት 58%  በመቶ፣ የገጠር የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን መረጃ መሠረት 59% በመቶ፤ 25 ሊትር በቀን የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ በቀን ሲሆን ተደራሽነቱ በ1 ኪሎ ሜትር ርቀት ይሆናል ተብሎ ታቀደ፡፡ የከተማ የውኃ አቅርቦት ድርሻ ሽፋን መረጃ መሠረት 51% በመቶ ሲሆን ፤(100፣ 80፣ 60፣ 50፣ እና 40 ሊትር በቀን) የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ በቀን ሲሆን ተደራሽነቱም ኪሎ ሜትር ርቀት አልተገለጸም፡፡ አማካይ ሊትር በቀንና ርቀቱ ሳይገልፁ አምታተው አለፉት፣የወያኔ መንግሥት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን፤ ያለጥናት ሲያጸድቅ፡፡

Sector/IndicatorPotable water coverage (%) Baseline 2009/1068.5 Plan Target 2014/1598.5
Urban potable water coverage ( within 0.5km) 91.5 100
Rural potable water coverage (within 1.5km) 65.8 98
Developed irrigable land (%) 2.5 15.6

Potable Water Supply and Irrigation Development:-During the GTP I period, development and expansion of reliable water supplies to rural and urban areas were undertaken. According to GTP I standard, national potable water supply coverage recorded was 84%, with rural coverage being 82% and urban 91%  in 2014/15 (GTP I standard: rural 15 l/c/d within 1.5km radius, urban 20 l/c/d, within 0.5 km radius). However, according GTP II standard (rural; 25 l/c/d within 1km radiusUrbanbased on demand categories1 of 100, 80, 60, 50 and 40 l/c/d from the highest to the lowest level, respectively) the rural, urban and national level water supply coverage were estimated as 59%, 51% and 58% respectively.

የህወሓት /ኢህአዴግ መንግስት፣ በኢትዮጵያ በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መረጃ የተጋነነና ያለ አንዳች ጥናት የቀረበ በመሆኑ ምክንያት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ክለሳ በተደረገበት መሠረት በብሄራዊ ደረጃ፣ በገጠርና በከተማ ያለውን የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ ሊትር በቀን ዝቅ ያለ እቅድ መጣሉን አንባቢው ሊያስተውል ይገባል፡፡

ኢትዮጵያ የውኃ ማማ ናት! በኢትዩጵያ ዋና ዋና የሆኑ አስራ ሁለት የወንዞች ተፋሰሶች ይገኛሉ፡፡ ታዲያ የአንድ ሰው የውኃ ድርሻ በቀን፣ በአማካይ ከ15 እስከ 20 ሊትር በቀን በመሆኑ  ለመጠጥ ውኃ፣ ለገላ መታጠቢያ፣ ለምግብ ማብሰያና ለልብስ ማጠብያ፣ ወዘተ ለየቱ ሊሆን ነው፣ የውኃ ችግር ካለ፣ ንፅህና ለመጠበቅ አያስችልም፡፡ በአገራችን የአንድ ሰው የውኃ ፍጆት ድርሻ፣ በዓለም አቀፋዊ መሥፈርት መለኪያ ደረጃ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ወያኔ ኢኮኖሚያችን በሁለት አሃዝ አደገ፣ በምግብ ራሳችንን ቻልን፣ ኢንዱስትሪው ተመነደገ፣ ሮኬት ልናመጥቅ ነው! ከአፍሪካ አንደኛ! መካከለኛው ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ልንገባ ነው!!! ይለናል፡፡ ወያኔ በ27 ዓመታት አገዛዙ የሃገሪቱ ህዝብ ከውኃ ችግር ሊቀርፍ ያልቻለ ወሬ አደር! ካድሬ አደር! ውሸታም መንግሥት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ በገጠር ጉድጎድ ውኃ፣ ምንጭ፣ የወንዞች ውኃ ይጠቀማል፣ እናቶችና ሴቶች እህቶቻችን እንስራ ሙሉ ውሃ ተሸክመው በቀን ሁለት ሶስት ሰዓታት አዝለው በማመላለስ ብዙ ኪሎሜትር መንገድ ይጎዛሉ፡፡ ህብረተሰቡ የውሃ አገልግሎት ማግኘት ባለመቻሉ በውኃ ወለድ በሽታ እየተጠቃ፣ ጤናውን መጠበቅ አልተቻለውም፡፡ ወያኔ የምግብ ጥያቄን ሳያሞላ፣ የውኃ ጥያቄን ሳይመልስ፣ የመብራት ጥያቄን ሳይፈታ፣ 27 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ በሙስና የተዘፈቀው ወያኔ ህዝቡን ሊታደገው አልቻለም፡፡ የህዝቡ ጥያቄ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑት ዳቦ፣ ወኃና መብራት ይቅደምልን ይላል፡፡ ይሄን ያላሞላ የወያኔ መንግሥት ግብር ሊያስከፍለን አይገባም ይላል፡፡ ወኃ ለጁቡቲ መንግስት መስጠት፣ መብራት ለጅቡቲ፣ ለሱዳንና፣ ለኬንያ መሸጥ ህዝባችን ጨለማ ውስጥ እየኖረ፣ ለህዝብ ሳይዳረስ ለጎረቤት ሀገራት በርካሽ ኮረንቲ ኃይል መሽጥ ለወያኔ ሙሰኝነትና ሌብነት ገሃድ ምስክር ነው!!! ህዝቡ ያለ ዳቦ፣ ያለ ውኃ፣ ያለ መብራት ህይወቱ ምን ሊረባው!!! ወያኔ በደደቢት በረሃ ሳለ የእንጀራ፣ ውኃና፣ መብራት ችግርን እንዴት ዘነጋው!!! ውኃ በማጣት ጤናውን መጠበቅ ያልቻለና ተመጣጣኝ ምግብ በማጣት የቀነጨረ ትውልድ ስታዲም ቢገነባለት!፣ መንገድ ቢገነባለት!፣ ባቡር ቢገነባለት! ምን ሊረባው፡፡ ለዚህ ነው ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት፣ የፖለቲካ ነፃነት የለም የሚባለው!!!

በኢትዩጵያ ዋና ዋና የሆኑ አስራ ሁለት የወንዞች ተፋሰሶች 122 ቢሊዩን ሜትር ኪዩብ ውሃ መጠንና ይዘት ሲኖራቸው፣ በሃገሪቱ የከርሰ ምድር ውሃ /የመሬት ውስጥ ውሃ ከ2.6 እስከ 6.5 ቢሊዩን ሜትር ኪዩብ ውሃ ይገኛል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንን በአሃዝ ስናያይዘው በአማካይ 1575 ሜትር ኪዩብ ውሃ የነፍስ ወከፍ የአመት ድርሻ እያንዳንዱ  ኢትዩጵያ ዜጋ ይደርሰዋል፡፡ የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው!!! ሆነና ነገሩ ባለመታደል 3 በመቶ የሚሆነው የውሃ ሃብት ልማታችንን ብቻ ነው ለመጠቀም የቻልነው፡፡ ከዚህ ውስጥም 11 በመቶው (0.3 በመቶ ከአጠቃላዩ) የውሃ መጠጥ አቅርቦት፣ ለቤት ውስጥ ፍጆት የሚውል ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ዋነኛ የውሃ መጠጥ አቅርቦት ምንጭ የገፈርሳ ግድብ ሲሆን የተገነባውም በጣሊያን ወረራ ግዜ ነበር፡፡ በ2009 እኤአ ግድቡ መልሶ የማቆቆምና እድሳት ተከናውኖል፡፡ እንዲሁም የጉድጎዶችና ተጨማሪ የግድቡ ውሃ አቅርቦት ተደርጎል፡፡  ‹‹ Ethiopia has 12 river basins with an annual runoff volume of 122 billion m3 of water and an estimated 2.6 – 6.5 billion m3 of ground water potential. This corresponds to an average of 1,575 m3 of physically available water per person per year, a relatively large volume. However, due to large spatial and temporal variations in rainfall and lack of storage, water is often not available where and when needed.[5] Only about 3% of water resources are used, of which only about 11% (0.3% of the total) is used for domestic water supply.[6] The capital Addis Ababa‘s main source of drinking water is the Gafsara dam built during the Italian occupation and rehabilitated in 2009. Wells and another dam complement the supply.[7][8]  ››

በኢትዮጵያ ሐይቆች፣ በስምጥ ሸለቆ ውስጥና በከፍተና ሥፍራዎች ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሥፍራ የሚገኙ ሃይቆች {1} ጣና ሃይቅ፣ በስፋት ትልቁ ሐይቅ ነው፡፡ {2} ወንጪ ሃይቅ  {3} ሐይቅ ወሎ የሚገኝ ሃይቅ ነው፡፡ {4} አሸንጌ ሃይቅ ፣ ወሎ የሚገኝ ሃይቅ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ በስምጥ ሸለቆ የሚገኝ ሃይቆች {5} አባያ ሐይቅ {6} ጫሞ ሐይቅ {7} ዝዋይ ሐይቅ፣ ዝቅተኛ ጥልቀት ያለው ሃይቅ ነው፡፡ {8} ሻላ ሐይቅ፣  ከፍተኛ ጥልቀት ያለው ሃይቅ ነው፡፡ {9} ሐዋሳ ሐይቅ {10} አቢያታ ሐይቅ {11} ቢሾፍቱ ሐይቅ {12} ባቦ ጋያ ሐይቅ {13} አርሰዲ ሐይቅ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሥፍራዎች፣ {1} ራስ ደጀን ተራራ ከፍታው 4620 ሜትር በአማራ ክልል፡፡{2} ላገዳ ተራራ ከፍታው 4532 ሜትር በአማራ ክልል፡፡ {3} ኦናሎ ተራራ ከፍታው 4480 ሜትር በአማራ ክልል፡፡ {4} ወንበራ ተራራ ከፍታው 4472 ሜትር በአማራ ክልል፡፡ {5} አባያሬድ ተራራ ከፍታው 4460 ሜትር በአማራ ክልል፡፡ {6} ጣፈው ለዘር  ተራራ ከፍታው 4456 ሜትር በአማራ ክልል፡፡ {7} ባሂት ተራራ ከፍታው 4437 ሜትር በአማራ ክልል፡፡ {8} ሙሰሪያ ተራራ ከፍታው 4360 ሜትር በአማራ ክልል፡፡ {9} ካራ ተራራ ከፍታው 4307 ሜትር በኦሮሚያ ክልል፡፡ {10} ባቱ ተራራ ከፍታው 4300 ሜትር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፡፡  በኢትዩጵያ አስራ ሁለት የወንዝ ተፋሰሶች፣ትልቁ የአባይ ወንዝ ሲሆን ዜጎቹ ለመጠጥ ውሃ የሚጠቀሙት ከወንዝ ሳይሆን በአመዛኙ፣ ከከርሰ ምድር ጉድጎዶች ማለትም፣ጥልቀት ከሌላቸው ጉድጎዶች፣ ከጥልቅ ጉድጎዶችና ከምንጮች ነው፡፡ ከዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ ዜጎች ደግሞ ከወንዝ፣ ካልጎለበቱ  ምንጮች፣ በእጅ ከተቆፈሩ ጉድጎዶችና የዝናብ ውሃ በማቆር ለመጠጥ ውሃና ምግብ ለማብሰል ወዘተ ይጠቀማሉ፡፡ በ2006 እኤአ የኢትዮጵያ መንግስት ባፀደቀው የዓለም አቀፍ ተደራሽ መርሃግብር( Universal Access Plan (UAP) ፖሊሲና ደንብ መሠረት 98% በመቶ የገጠር ውሃ አቅርቦት ተደራሽነትና 100% በመቶ የከተማ ውሃ አቅርቦትና ንፅህ ውኃ ተደራሽነት በ2012 እኤአ ለመተግበር ተስማሙ፡፡ የመርሃግብር ወጭ በግምት 2.5 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ነበር፡፡ በገጠር 15 ሊትር የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ በቀን፣በ1.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ተደራሽነት እና በከተማ 20 ሊትር የነፍስ ወከፍ የውሃ ፍጆታ በቀን፣ በ0.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ተደራሽነት ታቅዶ ነበር፡፡ በመንግስት መርሃ-ግብር በ2005 እስከ 2010 እኤአ መሠረት የተፋጠነና ዘለቄታዊ ልማት እንዲሁም ድህነት ቅነሳ በተመለከተ  84% በመቶ የውሃ አቅርቦት ለማሻሻልና ለማሳደግ እንዲሁም 80% በመቶ  ውሃ አቅርቦትና ንፅህና ተደራሽነት እስከ 2010 ለመተግበር ታቀደ፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት  የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር በቀረበው ማስረጃ መሠረት በ2010እኤአ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽነት 68.5% በመቶ እንደሆነ ተገልጾ ነበር፡፡ በሌላ መንግስታዊ መረጃ በዓለም አቀፍ ጤና ጥበቃ ድርጅትና በዩኒሲኤፍ ብሄራዊ ሰርቬ መረጃ መሠረት በ2008እኤአ የምዕተ-አመቱ ልማት ግብ፣ ደግሞ 38% በመቶ የውሃ አቅርቦት ለማሻሻል  እንዲሁም 12%  በመቶ  ንፅህና ለማሻሻል  እንደሆነ ይገልፃል፡፡ In 2006 the government adopted a Universal Access Plan (UAP) to achieve 98% access for rural water supply and 100% access for urban water supply and sanitation by 2012. Its cost was estimated at US$2.5bn. During the first phase until 2012 the focus is on affordable and appropriate technologies, with the following service standards:

Setting Per capita consumption Service radius Rural 15 liter/capita/day 1.5 km Urban 20 liter/capita/day 0.5 km

The government’s Plan for Accelerated Sustained Development and to End Poverty (PADEP), covering the period 2005-2010, aimed at increasing access to an improved water source to 84% and access to improved sanitation to 80% by 2010. These ambitious targets go well beyond the water and sanitation targets of the Millennium Development Goals, which aim at halving the share of people without access by 2015. According to one set of government figures, which is used by the Ministry of Finance and Economic Development for planning purposes, access to drinking water reached 68.5% in 2010. According to another set of government figures, based on national survey data and used by the WHO and UNICEF to monitor the Millennium Development Goals, in 2008 access to an improved water source was only 38% and to improved sanitation 12%. በኢትዮጵያ የውሃ መጠጥ አቅርቦትና የጤና አጠባበቅ ሳይንስ ከንፅህና ጋር በተያያዘ ረገድ፣ ከሳህራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሃገራቶች ዝቅተኛው ደረጃና ከዓለምም በጣም የመጨረሻ ደረጃ ይዛለች፡፡ በ2001 እስከ 2002እኤአ በኢትዩጵያ የውሃ መጠጥ አቅርቦትና የጤና አጠባበቅ የሚያስፈልገው ኢንቨስትመንት/ መዋለንዋይ 39 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ነበር፡፡በ2005 እኤአ ሕወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ፈጣንና ዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ መርሃግብር ከ2005 እስከ 2010እኤአ ድረስ 300 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር በአመት መዋለንዋይ  ያስፈልገኛል በማለት በጣም አስጎምጂና በባዶ የሚቆምጥ ፕላን ነደፈ፣ ተግባራዊም አልሆነ፡፡ በ2010እኤአ  ሕወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን ከ2011 እስከ 2015እኤአ አወጣ፡፡ ዓላማውም በሃገሪቱ  የውሃ መጠጥ አቅርቦት ከ68.5 በመቶ ወደ 98.5 በመቶ አደርጋለሁ ብሎ እንደተለመደው በጉጉት የልማት አጋሮች ገንዘብ ይሰጡኛል ብሎ በመቆመጥ የታለመ ስለነበር ዳግም ችግር ገጠመው፡፡ ‹‹ In 2005 the government announced highly ambitious targets to increase coverage in its Plan for Accelerated Sustained Development and to End Poverty (PASDEP) for 2010. The investment needed to achieve the goal is about US$300 million per year, compared to actual investments of US$39 million in 2001-2002. In 2010 the government presented the equally ambitious Growth and Transformation Plan (GTP) 2011-2015, which aims at increasing drinking water coverage, based on the government’s definition, from 68.5% to 98.5%.[2] While donors have committed substantial funds to the sector, effectively spending the money and to ensure the proper operation and maintenance of infrastructure built with these funds remain a challenge.›› According to data from the Joint Monitoring Programme for Water Supply and Sanitation of WHO and UNICEF, which are in turn based on data from various national surveys including the 2005 Ethiopia  Demographic and Health Survey (DHS), access to an improved watersource and improved sanitation was estimated as follows in 2008: 38% for improved water supply (98% for urban areas and 26% for rural areas) 12% for improved sanitation (29% in urban areas, 8% in rural areas)[1]

According to figures used by the Ministry of Finance and Economic Development for planning purposes, however, access was much higher. In 2010, access to drinking water was estimated at 68.5%: 91.5% in urban areas (within 0.5 km) and 65.8% in rural areas (within 1.5 km).[2] The higher figure for rural areas may be because the distance to an improved water source used in this definition is higher than the distance used by the Demographic and Health Survey. In communities that lack access to an improved water source, women bear the brunt of the burden of collecting water. For example, according to an article by Tina Rosenberg for National Geographic, in the mountain-top village Foro in the Konso special woreda of southwestern Ethiopia  women make three to five round trips per day to fetch dirty water from the Koiro river. Each roundtrip lasts two to three hours and water is carried in “50-pound jerrycans“.[13]

Investment and financing/ Actual investment. There are no recent reliable estimates of actual investment levels in the sector, and available estimates vary greatly. A detailed estimate of investment and financial flows in the Ethiopian water sector was carried out by the World Bank’s water and Sanitation Program (WSP) for the financial year 2001-02. It estimated total sector investments at US$39 million or less than half a dollar per capita, being one of the lowest recorded sector investment levels in the world.[26] water and sanitation have declined as a share of total poor-focused expenditure from 7.4% in 2005/06 to 3.4% in 2009/10. External cooperation./The African Development Bank provided a US$64 million grant for rural water supply and sanitation approved in 2005.[23]/In November 2011 it was announced that China would provide a US$ 100 million loan for water supply in Addis Ababa.[28]/ The British NGO WaterAid is engaged in Ethiopia since 1983. It works closely with established local NGOs. In Oromia Region, water projects tend to be spring-fed gravity schemes, some of which are very large, providing water for tens of thousands of people. In Southern Nations, Nationalities, and People’s Region schemes have included deep boreholes as water is sometimes only found below 200 metres.[29] For example, in the village of Orbesho residents – mainly women – built themselves an access road to allow drilling equipment to be brought in, dug trenches for pipes and collected stones for structures.[13] In Amhara and Tigray the main technologies have been hand-dug wells and spring development. In Benishangul-Gumuz rope pumps are also used. In sanitation, WaterAid supports the construction and use of latrines. Hygiene education has increasingly focused on the close links between proper handwashing at critical times, like before eating and after going to the toilet, and improved health. In all cases WaterAid works closely with communities from the start. Particular attention is now being paid to engaging women. Since 1998 WaterAid has also been engaged in the slum areas of Addis Ababa. Projects include establishing communal water points linked to the city’s piped systems, as well as shower and latrine blocks.[29] በ2012 እኤአ የዓለም ባንክ 150 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ለከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ፕሮጀክት አፀደቀ፡፡ በተጨማሪም በ2007እኤአ 100 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ቀላል ብድር የፕሮጀክቱ ሥራ በአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ሃዋሳ፣ ጂማ፣ መቐሌና ድሬዳዋ ከተሞች ላይ አፀደቀ፡፡ በ2010እኤአ የዓለም ባንክ 80ና 100 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ለገጠር የውሃ አቅርቦትና ጤና አጠባበቅ፣ ከንፅህና ጋር በተያያዘ ጉዳይ የሚውል አፀደቀ፡፡ በዚህም መሠረት የፕሮጀክቱ ሥራ፣ ለከርሰ ምድር ጉድጎዶች አገልግሎት ማለትም፣ ለ576 ርቀት የሌላቸው ጉድጎዶች፣ ለ99 ጥልቅ ጉድጎዶችና ለ835 የተጠበቁ ምንጮችን ለማጎልበት፣ 75 የገጠር የቦንቡሃ ውሃ ተጠቃሚዎች፣ 1288 በእጅ ለተቆፈሩ ጉድጎዶችና 35 የዝናብ ውሃ ለማቆር ለመጠጥ ውሃና ለምግብ ማብሰል ወዘተ የግንባታ አገልግሎት ወጭ ዋሉ፡፡ በዚህ ፕሮጀክት  87 የገጠር ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ 143,000 ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ In May 2012 the World Bank provided approved a USD 150 million soft loan for an urban water   and sanitation project as additional financing to a USD 100 million soft loan approved in 2007.[30] The project covers Addis Ababa, Gondar, Hawassa, Jimma, Mekelle and Diredawa.  In March 2010, the World Bank approved additional financing of USD 80 million for a USD 100 million rural water supply and sanitation project approved in 2004. According to the World Bank, until 2010 the original project had financed the construction of 1288 hand dug wells, 835 protected springs, 576 shallow wells, 99 deep wells, 75 rural piped systems and 35 rainwater harvesting, as well as conducting hygiene and sanitation promotion. In rural areas alone, according to the World Bank the project facilitated access to clean water and improved sanitation facilities to about 1.4 million people. In urban areas, the project provided “immediate service improvement” in 87 towns which benefited about 143,000 people.[32][33]

በኢትዩጵያ የውኃ መጠጦች ያሉ ተግዳሮቶች የእግዜር ውሃ፣ የኢትዩጵያ ህዝብ የውሃ መጠጥ አቅርቦት በአመዛኙ የሚገኘው፣ከከርሰ ምድር ጉድጎዶች ሲሆን፣ርቀት ከሌላቸውና ጥልቅ ከሆኑ ጉድጎዶች፣ከምንጮች፣ከወንዝ፣ንጽህናቸው ካልተጠበቁ ምንጮች፣በእጅ ከተቆፈሩ ጉድጎዶችና የዝናብ ውሃ በማቆር፣ ለመጠጥ ውሃና ለማብሰል ወዘተ ይጠቀማሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ህብረተሰቡ በውሃ ወለድ በሽታ ተጠቂ ነው፡፡ የጤና አጠባበቅ ሳይንስ ባለሙያዎች፣ እንደሚሉት ከንፅህና ጋር በተያያዘ ችግር ብዙ ሰዎች በውኃ ወለድ በሽታ ይጠቃሉ፡፡ የኢትዩጵያ ህዝብ 70 በመቶው መፀዳጃ ሽንት ቤቶች እንደሌሉት በጥናት ተረጋግጦል፡፡ ምስጋና ይግባቸውና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን በሃገራችን ውስጥ መፀዳጃ ሽንት ቤቶች በመስራት፣ የውሃ መጠጥ አቅርቦትና ንጽህና ጥበቃ መርሃግብር ነድፈው ሕዝቡን በመርዳት ላይ ይገኛሉ፡፡ የሌላው የለስላሳ መጠጦችና የተፈጥሮ መዕድን ውሃ  ኢንድስትሪ ዘርፍ የታሸጉበት ፕላስቲክ ጠርሙስ አካባቢ ፈቀር ስላልሆኑ በቀላሉ የሚበሰብሱና የሚፈራርሱ ባለመሆናቸው ከባቢያችንን በመበከል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላሉ፡፡ ‹‹Service quality:-WHO and UNICEF in 2004-2005. It shows that 72% of samples complied with the values for coliform bacteria in the Ethiopian drinking water standard ES 261:2001 and the WHO guidelines for drinking water. In the case of piped water supply by utilities compliance was highest at 88%. Open wells and unprotected springs were not included in the survey. Besides bacterial contamination, natural contamination with fluoride is an issue in the Rift Valley.  In 2010, 20 percent of rural water systems were malfunctioning, down from 25% in 2007.[3] About 35 percent of the estimated 30,000 hand pumps in Ethiopia, serving an estimated 2 million people, were non-functioning in the mid-2000s.[15] In piped water systems rationing and service interruptions are frequent.[16] There are no wastewater treatment plants in Ethiopia, so all wastewater collected in sewers is discharged without any treatment to the environment.››

በኢትዩጵያ የቢራ፣የለስላሳ መጠጦችና የተፈጥሮ መዓድን ውሃ  ኢንድስትሪ ፋብሪካዎች የሚለቀቁ ኬሚካሎች የወንዞችን ፣ሃይቆችንና የከርሰ-ምድር ውሃን ብክለት አስከትለዋል፡፡ ፋብሪካዎቹ የውሃ ስርገት መጋረጃ / ሃይድሮ-ከርቴንስ/ ውስጥ የተበከለውን ውሃ እንዲከማች  ባለማድረጋቸው የሚከሰት ችግር ነው፡፡ የሚሰራው የውሃ ስርገት መጋረጃ (የተበከለ ውሃ ማከማቻ ኩሬ) ስፍራው ምንም ፈሳሽ የማያስተላልፍ  አለታማ መሬት ላይ ተመርጦ መሠራት አለበት፡፡ በዚህም ዘዴ የከርሰ-ምድር ውሃን ከብክነትና ብክለት መከላከል ይቻላል፡፡ በ2004/05 እኤአ የዓለም ጤና ድርጅትና ዩኒሲኤፍ፣ በኢትዩጵያ የውሃ መጠጥ አቅርቦት በአመዛኙ 72% በመቶ በኮሊፎርም ባክቴሪያ(coliform bacteria) እንደተበከለ በጥናታቸው አረጋግጠዋል፡፡ በተመሳሳይ የቦንቡሃ ውሃ ተጠቃሚዎች የባሰውኑ 88በኮሊፎርም ባክቴሪያ የተበከለ ውሃ ተጠቂዎች ናቸው፡፡ በጥናቱ በእጅ የተቆፈሩ  ክፍት ጉድጎዶችና ምንጮች አልተካተቱም፡፡ በስምጥ ሸለቆ በሚኖሩ ዜጎች የውሃ መጠጥ የባክቴሪያ ብክለትና የተፈጥሮ በፍሎራይድ ብክለት ያጠቃቸዋል፡፡ በ2007 እኤአ 25 በመቶና በ2010 እኤአ 20 በመቶ፣ በገጠር የተሠሩ የውሃ መጠጥ አቅርቦት ስርአት የተበላሹ ነበር፡፡ በ2000እኤአ በኢትዩጵያ ለሁለት ሚሊዩን ህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ በግምት 30,000 በእጅ የተቆፈሩ ጉድጎዶች ውስጥ 35 በመቶ (10,500 ጉድጎዶች) ተበላሽተው አገልግሎት አይሰጡም ነበር፡፡ የቦንቡሃ ውሃ ተጠቃሚዎች በፈረቃ ውሃ ማግኘትና ተደጋጋሚ የውሃ እጥረት ችግር አለባቸው፡፡ በኢትዩጵያ የቆሸሸ ውሃ ማጣሪያ ስልት የለም፣ በዚህም የተነሳ የተበከለ ውሃ በቁሻሻ መውረጃ ተለቀው ከባቢውን ይበክላሉ፡፡

 

ምንጭ ድረ-ገፆች

1-http://www.ethiopiainvestor.com/index.php?option=com_docman&task=doc_download&gid=May 2010,Access Capital Research

2-http://www.ethiopianchamber.com/Data/Sites/1/psd-hub-publications/baseline-survey-on-competition-and-markets-in-ethiopia.pdf. © Private Sector Development Hub/Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations, 2009:P. O. Box 2458, Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia: Email: psdhub@addischamber.co

3- For further information, please contact the commercial section of the U.S. Embassy in Addis Ababa. Lords of poverty/ e-mail: charlescl@Addisababa.us-state.gov

4-http://www.ethiopianembassy.org/AboutEthiopia/InvestmentProjectProfiles/Services/MineralWater/MineralWater.pdf/

5-‹‹የኢኮኖሚው ስነ-ምኅዳር›› በአቶ ውብሸት ጌታሁን፣ 2002 እኢአ

6- የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ/1999፡6/ ዓመታዊ የስታቲክስ መፅሔት

Leave a comment