ይድረስ ለተጠቅላዩ የህወሃት ሚኒስትር (ከዳንዴው)

/**/

ይህን አጠር ያለ የትዝብት መልዕክቴን ለአዲሱ ተጠቅላይ ሚኒስትር ባሉበት ይድረስ ያልኩት የዘረኝነት ልጓም ይዞኝ አልያም ደግሞ የተቅውሞ በሽታ ተጠናውቶኝ እንዳልሆነ እሳቸውም ሆነ አንባቢው በቅድሚያ እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ :: ከማንም በላይ በየመድረኩ እና በሶሻል ሚድያዎች ሳይቀር ኢትዮጵያችንን ለማዳን እና ፖለቲካዊ ቀውሱን ለማርገብ ያላቸው ራዕይ የተሻለ ነው በሚል የሳቸውን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መመረጥ ጠቀሜታ ላንቃዬ እስኪበጠስ ቀን እና ማታ ስደገፍ የነበርኩ መሆኔን ብዙዎች ያውቃሉና ይህን አባባሌን ለማስረዳት ብዙ መድከም አይኖርብኝም ::

ተቃዋሚው ወይም ተፎካካሪው ኃይል በየምክንያቱ ጠንክሮ መውጣት ባለመቻሉ እና በኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ ለ 27 ዓመታት ተንሰራፍቶ የግፍ እና ሰቆቃ አገዛዙን ብሔር እና ሃይማኖቶችን ከፋፍሎ እያናከሰ የዘረጋውን ህወሃት የሚባል የባንዳ ሥርዓት ከሥር መሰረቱ ነቅሎ መጣል አለምቻሉ የሥርዓት ለውጥን በራሳችን የመስዋዕትነት ትግል ከመቀዳጀት ይልቅ ከራሱ ከገዥው አካል በሆነ ተአምር እንዲፈጠር እስከመጠበቅ ለመድርስ ተገደናል :: በተለይም ከ 97ቱ ሕዝባዊ መነቃቃት ከታየበት ምርጫ መክሸፍ በኋላ በተቃዋሚው ጎራ ተደጋግሞ የሚንጸባረቀው ግለኝነት ዘረኝነት መሰነጣጠቅ ብሎም የእርስ በእርስ መጠላላፍ ተስፋ ያስቆረጠው ሕዝባችን እኔን ጨምሮ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሥርዓቱ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍልን ሃገሪቱን ለማዳን እና ለመልካም ሥርዓት ግንባታ ምቹ አጋጣሚ ነው በሚል ዕምነት ስለ ለውጥ ማቀንቀን የጀመሩትን የነ ለማን-አብይ ቡድን መደገፋችን ሞኝነት ወይም አላዋቂነት አልነበረም :: እንዲህም እንዲያም ብሎ ተጠቅላዩ ሚኒስትር ከወራት ውዝግብ በኋላ ተመረጡ :: እዚህ ላይ ሁሉም ሰው ልብ ማለት የሚገባው አንድ ተጨባጭ ዕውነት አለ :: አራቱ የኢሃዲግ ግንባር ድርጅቶች ማለትም የአማራው ብአዲን የደቡብ ሕዝቦቹ ደኢሕዲን የኦሮሞው ኦፒዲኦ እና የትግራዩ ፓርቲ ህወሃት ግንባር የፈጠሩበት ኢሃዲግ እያንዳንዳቸው 45 አባላትን በአጠቃላይ 180 ሰዎችን ይዘው ነበር የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነውን ሊቀመንበራቸውን ለመምረጥ የታደሙት :: በኢትዮጵያ የደህንነት እና መከላከያ መዋቅሩን በመዳፉ ተቆጣጥሮ ላለፉት 27 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳሻው የሚዘውረው እና የደቡብ ህዝቦችን ንቅናቄ ድርጅትን ጭምር በእጅ አዙር የሚቆጣጠረው የትግራዩ ህወሃት የብአዲኑ አቶ ደመቀ መኮንን እንዲመረጡ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረው መዘንጋት አይኖርበትም :: አቶ ደመቀ በመጨረሻው ሰአት ራሳቸውን ከምርጫው ባያገሉ ኖሮ ከፓርቲያቸው , ከህወሃት እና ከደቡብ ህዝቦች አብላጫውን ድምጽ በማግኘት የሊቀመንበርነቱንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱንም ቦታ መያዝ በቻሉ ነበር :: ግን የሃገሬ ሰው አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ ብሎ እንዳቀነቀነው ገና በ 2ሳምንት የስልጣን እድሜያቸው በአማራው የነጻነት ትግል ላይ ማላገጥ ለጀመሩት ዶክተር አብይ ዕድላቸውን እንደዘበት አሳልፈው ሊሰጡ ችለዋል :: ውድ አንባብያን ልብ በሉ ! ጉዳዩ በዘር መስመር ላይ የተመሰረተን የሥልጣን ክፍፍልን የማቀንቀን አባዜ አይደለም :: ግና ታሞ የተነሳ እግዚአብሔርን ረሳ እንደሚባለው ተረት በውዝግብ እና እሰጣ ገባ የሞት ሽረት ትግል ተደርጎበት ለሁሉም ብሔረሰቦች የምትሆን ሁሉንም በእኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያ ትፈጠራለች በሚል ጽኑ ዕምነት የአማራዎች ድጋፍ ጭምር ታክሎበት የስልጣን ወንበር የተቸራቸው ዶክተር አብይ በሁለት ሳምንት የሥልጣን እድሜያቸው በትግራይ ወራሪዎች ከአምስት በላይ ለም የሰሜን ጎንደር ወረዳዎቹን ቃፍታ ሁመራ, ወልቃይት, ጸገዴ, ጸለምት እና ታች አርማጭሆ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከከተመበት ቀዬው በኃይል እና በግፍ እየተገደለ እና እንዲሰደድ እየተደረገ የተቀማውን የጎንደር ህዝብ እንዲሁም ከሰሜን ወሎም ከሰቆጣ ራያ እና ቆቦ እንዲሁም አለውሃ እና ሌሎችም ወረዳዎች ተባሮ በስደት የሚንከራተተውን የአማራ ሕዝብ በዲያስፖራ ሆኖ እሳት የሚጭረው የፌስ ቡክ አሉባልታ እየቃረመ ነው በሚል አፊዘውበታል ::

እናንተ ወርቅ የትግራይ ሕዝቦች ሆይ ከጎንደር ጋር ያላችሁን ችግር በያዛችሁት መንገድ ብቻ እንደሚፈታ አረጋግጥላችኋለሁ ቃል እገባላችኋለሁ ብለውም አፍ በፈቱበት የትግርኛ አንደበታቸው በተለይም ከ 300ሺህ በላይ የወልቃይት ጸገዴ አማራ ሕዝብ ሕይወቱን የገበረበትን ሴቶቹ እንዳይወልዱ መርፌ እየተወጉ እንዲመክኑ የተደረገበትን ሰቆቃ ዛሬም ድረስ የሞት ሽረት የመስዋዕትነት ትግል የሚያደርግበት የማንነት ጥያቄ ላይ ሲዘባበቱበት ተስተውለዋል :: ገና የስልጣን ኮርቻን ሲቆናጠጡ የትላንቱን ደም አፋሳሽ ግጭት ዓብይ መንስኤ ረስተውት እንደሆነ ነው እንጂ የወንድሞቻችን የኦሮሚያ ቄሮዎች ወጣቶች ትግል የተቀጣጠለው እና የተጠነሰሰው በአዲስ አበባ ዙሪያ እሳቸው የሚመሩት ገዥው እና ነፍሰበላው የወያኔ ሕወሃት አመራሮች በከተማዋ መስፋፋት ሰበብ መሬት ለመቀራመት እና ለመቸብቸብ የነደፉት መሰሪ ዕቅድ እንደነበር ታሪክ ምስክር ነው ::

እናም የትግራዩ ወያኔ ከአማራው በርካታ ለም ወረዳዎችን በግፍ ወሮ ሚልዮኖችን እየገደለ እና እያሰደደ የግዛት ክልሉን ከ 65 በመቶ በላይ ሲያሰፋ አማራው በውጭ ሆኖ የሚጮኸው በፌስ ቡክ አሉባልታ ተሞልቶ ነው ብሎ መሳለቅ በኦሮሞ ሥም ለሚነግዱት እንደነ አብይ ላሉ ውስጡን ለቄስ ሥውር የህወሃት አባላት የሰለጠኑበት ያደጉበት ህዝብን የመናቅ እኩይ ተግባር እንጂ ከምንም የመነጨ ሊሆን አይችልም :: ያለ ሃጢያቱ እና ያለበደሉ ለኢትዮጵያ አንደበት በጮኸና የህይወት መስዋዕትነት በከፈለ በጠላትነት ተፈርጆ በመላ ሃገሪቱ እነ ዶክተር አብይ በሚመሩት የኢህአዲግ ግንባር አሉባልታ እና የሃሰት መርዝ እየተረጨበት የግፍ ሰቆቃ ሰለባ የሆነው ጭቁኑ የአማራው ህዝብ 10 ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ በመድሃኒት እና ቫይረስ ጭምር የህዝብ ብዛቱ በሚልዮኖች እንዲቀንስ ከፍተኛ ምሥጢራዊ የዘር ማጽዳት ዘመቻ / Genocide and Ethnic cleansing / እንደተካሄደበት የሥርዓቱ የህዝብ ቆጠራ እና ስታትስቲክስ ሃላፊ አንድ ወቅት የአማራ ህዝብ ቁጥር በ 2.5 ሚልዮን በላይ ቀንሶ መገኘቱን ለፓርላማ ካቀረቡት መረጃ እንዲሁም የእስራኤል እና የሎችም ሃገራት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በአማራ ሴቶች ላይ የሚያመክን መርፌ የመውጋት ወንጀልን የሚያጋልጡ የግፉ ሰለባ የሆኑ ሴቶች ቃለ መጠይቆች ከተካተቱባቸው ዘጋቢ ፊልሞች መገንዘብ ይቻላል ::

እንግዲህ ለዘመናት ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ደሙን እየገበረ ኢትዮጵያ አትፍረስ ባለ መከራውን እንዲበላ እና በዓለም ታይቶ እና ተሰምቶ በማያውቅ ጭካኔ እንዲያልቅ የተፈረደበትን በድህነት እና በጭቆና ቀንበር የሚማቅቀውን ደግ እና ሃገር ወዳድ የአማራ ህዝብ ነው የሥልጣን ጥመኛው ተጠቅላዩ ሚኒስትር የፌስቡክ አሉባልታ የሚቃርም ነው ሲሉ የተሳለቁበት :: በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብም ይሁን ከአለቆቻቸው ህወሃቶች ድጋፍ ላለማጣት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት የሚጥስ ብሎም የቁም እስረኛ እና የትግራይ ማፍያ ቡድኖች ባርያ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲጸድቅ ፓርላም ተገኝቶ ድምጽ ከመስጠ ይልቅ ቤታቸው ተደብቀው ያሳለፉት ዶክተር አብይ የድብብቆሽ ድራማቸውን የጀመሩት እና ብዙዎች የትዝብት ዓይን የወደቁት ከዚህች ወሳኝ የሞት ሽረት ዕለት ጀምሮ ነበር ::

የኦሮሞ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እንደነ የኦሮምያው ክልል የፍትህ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ታየ ደንደአ የሞያሌው ከንቲባ አቶ አስቻለው ዮሃንስ እና በወለጋም ከፍተኛ የኦህዲድ አመራር አባላት እንዲሁም በርካታ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም በትግራዩ ህወሃት ወታደራዊ እዝ የተዋቀረው የኮማንድ ፖስት በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍ እና ሰቆቃ በአደባባይ እና በሚዲያዎች ጭምር በመቃወማቸው ታፍነው ታስረው በግፍ እስር ቤት አበሳ በሚበሉበት በአሁኑ ሰዓት አንድም ተቃውሞ ትንፍሽ ያላለው እና ለማስፈታትም ጥረት ያላደረገው የእነ ለማ-አብይ ሥልጣን ጥመኛ ቡድን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደዘገበው ወያኔ ባቀነባበረው የኦሮሞና ሶማሌ ብሔሮች ግጭት ከአንድ ሚልዮን ህዝብ በላይ ከቀዬው በተሰደደበት እና ብዙዎችም ሕጻናት ጭምር ሕይወታቸውን ባጡበት ግጭት ዙሪያ ተገቢውን ካሳ እና መልሶ የማቋቋም እንቅስቃሴ ከማድረግ ይልቅ 28 የትግራይ ዜጎች መፈናቀላቸው አሳዝኖናል በሚል የብር የድጎማ ካሳ ተሸክሞ ትምበርክኮ በእምባ የይቅርታ ተማጽኖውን ሲያሰማ ብዙዎች እንድንታዘብ አድርጎናል :: ከሁሉም በላይ ኦሮምያ ክልል ውስጥ ታስረዋል ከተባሉት የትግራይ ተወላጆች መካከል ቦምብ እና መሳሪያ ታጥቀው ሽብር ሊፈጽሙ ሲሉ የያዝናቸው አሉ ለህዝቦች ሰላም ስንል እንደምንለቃቸው ቃል እገባለሁ እያሉ ንጽሃን በግፍ አይገደሉ የሚል ጥያቄ አንስተው በእስር የሚማቅቁትን ወገኖች ጉዳይ ችላ ብሎ ሕዝብን ለሚያርዱ ወንጀለኞች ጥብቅና ቆሞ የመታየቱ ጉዳይ የግለሰቡን አድርባይነት እና የዘቀጠ ሰብእና ቁልጭ አድርጎ ከወዲሁ እንድናይ ረድቶናል ::

ለም መሬታቸውን ተቀራምቶ ለትግራይ እና የውጭ ኢንቨስተሮች ለመቸብቸብ የህወሃት ማፍያ ቡድን በጋምቤላ ኮንሶ እና ሌሎችም አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃንን መግደሉ እና ማሰደዱም ትኩረት ሳይሰጠው ነው እነ ዶክተር አብይ የገንዘብ ከረጢታቸውን ይዘው ትግራይ ሄደው ከገዳዮች ጋር ጀግናው ድርጅታችን እያሉ ከበሮ ሲደልቁ ያስተዋልነው :: በአጠቃላይ ለእንዲህ ዓይነቱ የበሉበትን ወጭት ሰባሪ በየሄዱበት ፊት እና መልካቸውን እየቀያየሩ እኛ የምንናፍቃትን አንድ ኢትዮጵያ እየሰበኩ የእኛን የዲሞክራሲና የነጻነት መዝሙር እየዘመሩ መቀበሪያ ጉድጓዳችንን አጥልቀው ለሚምሱት የፋኖን የቄሮዎችን የዘርማ እና ነብሮ ትንታግ ወጣቶችን የነጻነት እና መብት መከበር ጥያቄዎችን በማር በተለወሰ መርዛቸው አዳፍነው የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት የሆነውን የህወሃት ጨቋኝ እና ነፍሰገዳይ ሥርዓት በጥገናዊ ለውጥ ለማስቀጠል የሚሯሯጡትን አዲሱን ተጠቅላይ ሚኒስትር ማንነት እና ምንነት በጥልቅቀት በመፈተሽ ” ጥቂት ጊዜ እንስጣቸው ” የሚለውን የዘረኞች የወያኔ ደጋፊዎች እና አንዳንድ የዋሃን ማዋከብ ወደጎን ትተን ትላንት በቁርጠኝነት አንድ ብለን በጋራ የጀመርነውን የአንድነት እና የነጻነት የትግል ጉዞ ይበልጥ እንድናጠናክር በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ :: ” ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም ፍቅሬ ፍቅሬ በዛ እኔ አላማረኝም ” ብሎ የለም ድምጻዊው ::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s