ያላስከበርከውን ማንነትን ወድቆ አታገኘውም!

✍ ፍፁም አየነው

ኢትዮጵያ ሀገራችን የትግል ህንጻ ናት፡፡በተለያዩ ጊዜና ወቅት በመራራ መስዋዕትነት ስትገነባ የኖረች ፤ ዛሬም ሁልጊዜም ስትታነፅ የምትኖር የማታረጅ የማትገፋ እናት ናት፡፡ለዚህች እናት ሀገር ያልተፈለ ዋጋ የማይከፈል መሰዋዕነት የለም፡፡ይኽም በአፍ ተነግሮ ሳይሆን፤በተግባር በጥላቻም ሳይሆን በፍቅር የተተገበረ ነው፡፡አማራም ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት መሃንዲስነቱን በእነዚያ ዘመናት በተግባር አረጋግጧል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ታፍኖ የበሰለ፣ስር ሰዶ የተተከለ ግን መሰረት የሌለው ጥላቻ ሀገሪቷን እያመሳት ይገኛል፡፡ይህም የአማራን ህዝብ ጥላቻ….ሲጀመር ጥላቻ ለማንም አይጠቅምም ደግሞም ጥላቻ መጀመሪያ ሰላም ሚያሳጣው በጥላቻ የተሞላውን አካል ነው፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ይህን ስለተፈጠረበት ብዙ ተብሏል አማራም በአማራነቱ እየጠፋ ችሎ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በአንድነት ትግል ይህን ለመቅረፍ ብዙ ደክሟል በቃላት ከሚገለፀው በላይ መሰዋዕትነትም ከፍላሏ፤ነገር ግን የተለጠፈበትን መጥፎ ስምም ሆነ የተዘራበትን ጥላቻ ብሎም የሚያሳድደውን የዘር ጥፋት መቀልበስ ግን አልቻለም፡፡ለዚህ ትልቅ ምክንያት የነበርም በአንድነት ጥላ ሲዋደቅ ሌሎች ነገዶች እና ብሔረሰቦች በማንነታቸው ተደራጅተው የአንድነቱንም ትግልም ሆነ በተናጥል አማራውን ሲያጠቁና ሲያጠፉ ዘመናት ማስቆጥራቸው ነው፡፡…..ዛሬ ታዲያ አማራ በዘሩ ምክንያት ብቻ ሲሳደድ ፣ሲገደል ፣ሲዘረፍ ፣በማንነቱን ብቻ ሲያርዱትም ሆነ ገደል ሲወረውሩት አጥፊዎች ሳጠላ የኖረ አስተዋይ ህዝብ ነው፡፡አጥፊዎቹ ግን ይህ ተግባሩን አልወደዱለት፡፡….ሁሉም ነገር እንዳለ አይቀጥልምና ጊዜው ሲደርስ አማራም በአማራነቱ መደራጀት ማንነቱን ለማስጠበቅም ሆነ ለማስጠበቅ መታጠቅ ጀመረ፡፡በዚህ ወቅት አራጆቹ አደረጃጀቱን ለማላላት የአንድነት አቀንቃኞች ፣በኢትዮጵያ ፍቅር የተጠመቁ ይመስል ዲስኩራቸውን በትላልቅ ድምፅ ማጉያቸው ስሙን ብለው ይጮሁ ጀመር…..ግን ጩኸታቸው የአማራን አደረጃጀት ፍራሃቻ ወይስ የሀገር ፍቅር…?አማራ ሌላው በጠላትን ፈርጆ አልተደራጀም ነገር ግን አራጁንም ጠላቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው፡፡ስለ አንድነትም ሆነ ስለ ሀገሩ ኢትዮጵያ ማንም ሊግረው፣ሊያስተርምረውም አይችልም፡፡ለምን ቢባል ደሙ ተጨምቆ ፣አጥንቱ ተፈጭቶ ላቡ ተንጠፍጥፎ ሀገሩና አንድነቷን እንዳስጠበቀ የባዕድ የውጭ ወራሪዎቿ ብቻ ምስክርነት በቂ ነው፡፡ይህን እውነት መቀበል ከብዷቸው ወይም በአዙሪት የአማራ ጥላቻ ትግል ውስጥ ሲገላበጡ አዕምሯቸው የነሆለለ ፓለቲከኞች ወይ ጡረታ ወይ ዝምታ ቢትመርጡ የተሻለ ነው!፡፡አለበለዚያ ግን የዘራችሁት ጥላቻ ረመጥ ሆኖ ይፈጃቹሃል፡፡አማራ ማንነቱን ለማትረፍ ብሎ እንደ ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ነፃ ሆኖ ለመኖር ላይመለስ ተደራጅቷል፡፡ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል ወደ ኋላ ሚመለስ ትግል የለውም፡፡መሬቶቹንም ሆነ ማንነቱን ለማስከበርም ታጥቋል፡፡ጥያቄዎቹንም ሆነ ትግሉን ለማስከበር አይለማመጥም፡፡

የአማራው የትግል መስመሮቹ ሁሉ በጦርነት ብቻ የሚወሰንም ሆነ የሚፈፀምም አይደለም በዘላቂ የትስስር አንድነቱ ማንነቱን እንዳስከበረና እንዳጠበቀ ይቀጥላል፡፡አማራ ሆኖ ለተዘናጋህ ከአናጆችህ ቢላዋ እና ከአጥፊዎቹህ ሴራ አማራ ስለሆንክ ብቻ አታመልጥም፡፡እመነን ደግመን ደጋግመን እንልሃለን አታመልጥም፡፡በሌላ አደራጃጀት ውስጥ ወድቀህ የጎደለ መሙያ ለሆንክ ወገኔ ትግልን ማወዳደር ይቻል ይሆናል የማንነትን ትግል ግን ማበላለጥ አትችልም፡፡ከፈጣሪ የተሰጠህን ዘር የመተካት ሂደት በሰው ልጅ መነጠቅም መብት አይደለም፡፡ሁሉም ትግል ለአላማውን ትክክል ነው፡፡ትግልን በአንድ አይን መመልከትም ትክክል አይደለም፡፡ያላስከበርከውን ማንነትም ወድቆ አታገኘውም!፡፡ሁሉም ነገር በእጅህ ነው፡፡ሁሉም አማራ በየትኛው የአማራ አደረጃጀት ጥላ ስር ሊሆን ይገባዋል፡፡የአማራ አደረጃጀቶች ሁሉ ሊጠናከሩ ይገባቸዋል፡፡አጥፊዎቻችን ለአፍታ መዘናጋት አይታይባቸውም፡፡ከምታውቃቸው በላይ ጥላቻቸውን በአደባባይ እየነገሩህ ነው፡፡በር ዘግተውም እየመከሩበህ እና የተማማሉብህ እንደሆነ አትዘንጋ፡፡በተዘናጋህላቸው ልክ ተደራጅተውብሃል፡፡ ንቃ ከዚህም በላይ ወገኔ ፤ እንደ አባቶቻችን ሀገራችንን ለማቆም እንደከፈሉት ተዋድቆ አጥንታችንን ከስክሰን፣ደማችንን አፍሰን ፣ላባችንን አንቆርቁረን አማራነትን እናስከብር፡፡ከጠፋነው በላይ ልንጠፋ አይገባም!፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s