እስክንድር ነጋን ፓስፖርቱን ነጥቀው ቦሌ ላይ አገቱት (ክንፉ አሰፋ)

ክንፉ አሰፋ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር ለክብር እንግድነትበሆላንድ የጠራው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሊወጣ ሲል በህወሃት ታግቷል።

Ethiopian political prisoner Eskinder Nega released.

ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም። እስክንድር ነጋ ሃሳቡን በነጻ በመግለጹ ምክንያት የመጨረሻውን ሳንደምረው ለ8 ጊዜ ታስሯል። እ. ኤ. አ, በ 2013 በሽብርተኝነት ተከሶ 18 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር። እስክንድር ነጋ የካቲት 14 ቀን 2018 ከሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ጋር ቢለቀቅም እንደገና ለ 9ኛ ጊዜ ታሰሮ ነበር።

እስክንድር ከዘጠኝ በላይ የክብር ሽልማቶች ያገኘ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው።

1. በ 2011 PEN America (NY,)
2. በ 2012 Barbara Goldsmith Freedom to Write Award
3. በ 2014 World Association of Newspapers’ Golden Pen of Freedom Award
4. በ 2015 PEN Canada Freedom of Expression Award
5. በ 2017 International Press Institute World Press Freedom Hero
6. በ 2018 Oxfam Novib/PEN Award for Freedom of Expression (60 laureates)
7. ሂዩመን ራይት ዋች የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና አምነስቲ የኢንተርናሽናል የክብር ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ዶር አብይ አህመድ ለውጥ ሊያመጣ ቃል በገባ ሳምንታት ቢቆጠሩም የህወሃት አፈና እና ግድያ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የአለም መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ዛሬ በ እስክንደር ነጋ ላይ የተፈጸመው የተለመደ የህወሃት በደል በዶ/ር አብይ ፈንጥቆ የነበረውን ተስፋ የሚያጨልም ነው። የህግ ሳይሆን የህወሃት የበላይነት እስካለ ድረስ በአኢትዮጵያ ለውጥ አይታሰብም።

ሕወሃት አይታደስም። አይተገንምም። ህወሃት ከምድሪቱ ላይ መጥፋት ነው ያለበት። ይህ ደግሞ በሕዝባዊ አመጹ እውን ይሆናል።

እስክንድር ነጋ በሆላንድ ሃገር ከተዘጋጀለት የአምነስቲ ዝግጅት በኋላ ልጁን እና ባለቤቱን ለማየት ወደ አሜሪካ ሊያመራ እንደነበር ይታዋቃል።

የሆላንድ ንጉስ ዊለም አሌክሳንደር የሚገኙበት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ከብረ-በዓል በእስክንድር ያለመገኘት የተነሳ መልካም የነበረ ድባቡ እንዲጠፋ መደረጉን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተወካይ ገልጸውልናል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሽግሽግና ሹመትን አጸደቀ

/**/

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሙሉ የካቢኔ አባላት ዝርዝር
1-ደመቀ መኮንን- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2-ወርቅነህ ገበየሁ- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3-ሞቱማ መቃሳ- የመከላከያ ሚኒስትር
4-ታገሰ ጫፎ -የፐብሊክ ሰርቪስና እና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
5-አብርሃም ተከስተ- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
6-ከበደ ጫኔ- የፌዴራል ጉዳዮች እና የአርብቶ አደር አካባቢዎችልማት ሚኒስትር
7-መላኩ አለበል- የንግድ ሚኒስትር
8-ኡባ መሀመድ- የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
9-አምባቸው መኮንን- የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10-ሂሩት ወልደማሪያም- የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
11-ሽፈራሁ ሸጉጤ- የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትር
12-ጌታሁን መኩሪያ- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
13-ሲራጅ ፈጌሳ- ትራንስፖርት ሚኒስትር
14-ጃንጥራር አባይ- የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር
15-አይሻ መሐመድ- የግንባታ ሚኒስትር
16-ስለሽ በቀለ- የውሃ፣ መስኖና እና የኤሌክትሪክ ሚኒስትር
17-መለሰ አለሙ- የማዕድን፣ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
18-ገመዶ ዳሌ- የአካባቢ ጥበቃ፣ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
19-ጥላዬ ጌቴ- የትምህርት ሚኒስትር
20-ይናገር ደሴ- የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
21-አሚር አማን- የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
22-ተሾመ ቶጋ -የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
23 ብርሃኑ ፀጋዬ- ጠቅላይ አቃቤ ህግ
24-ፎዚያ አሚን- የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር
25-ያለም ፀጋዬ- የሴቶችና የህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
26-እርስቱ ይርዳው- የወጣትና ስፖርት ሚኒስትር
27-ኡመር ሁሴን -የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
28 አስመላሽ ወልደስላሴ- በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትየመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር
29- አህመድ ሸዴ- የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

Amhara Mass Media Agency

ጠቅላይ ሚንስትሩ የ6 ሚንስትሮችን የስልጣን ሽግሽግ፤ የ10 ሚንስትሮች አዲስ ሹመት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡

የሚንስትሮቹ የስልጣን ሽግሽግና ሹመት የተካሄደው በዋናነት የህዝብን ጥያቄና ቅሬታ እንዲሁም ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን ችግር ከመፍታት አንፃር ካላቸው አቅም አኳያ እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የአቅም ክፍተት ኖሯቸው እራሳቸውን ለመለወጥና ለመማር ዝግጁ የሆኑ ሚንስትሮች በካቢኔ ዝርዝር ውስጥ ተካቷል ብለዋል፡፡

የህዝብን አገልግሎት ፍላጎት ለሟሟላት ዋንኛ ትኩረታቸው በመሆኑ ይህ ሊታለፍ የማይቻል መሆኑን ማወቅ እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

የመንግስትን ሃብትና ጊዜን የማባከን ሂደትን በመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ከሁሉም በላይ ግን ህዝቡን በማማረር በመንግስት ላይ የከረረ ተቃውሞዋቸውን እንዲያኑሱ የሚያደርጉትን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የመጀመሪያ ስራቸው ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

ላለፉት ስድስት ዓመታት አፈ ጉባዔ ሆነው ባገለገሉት አቶ አባዱላ ገመዳ ምትክ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰየሙ፡፡ አቶ አባዱላ ከአፈ ጉባዔነት የተነሱት ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ ነው፡፡ ወ/ሮ ሙፈሪያት ቃለ መሃላ ፈጽመው ኃላፊነቱን ተረክበዋል፡፡

EBC

ጎንደርን በጨረፍታ አስጎበኝዎታለሁ! አማራ ክልልን ያዩበታል!


(ጌታቸው ሺፈራው)

ጎንደርን ያውቋታል ሲባል ሰምቻለሁ። እኔ ለአንድ ወር ያህል ጎንደር ቆይቻለሁ። እርስዎ ጎንደርን የሚያውቋት የየመከላከያ አመራር ወይንም ባለስልጣን ሆነው ነው። የሚያውቁት የመከላከያ እና የባለስልጣናቱን ጎንደር ነው። የህዝቡን ጎንደር አያውቋትም። በእርግጥም የድሮዋ ጎንደር ከዛሬዋ ትለያለች። ዛሬ መንገድ ላይ እያለፉም ቢሆን ሀቁን በግልፅ ይረዱታል። መረዳት የሚፈልጉና የሚችሉ ከሆነ! ጎንደርን ሲጎበኙ ሆን ተብሎ የደቀቀውን አማራ ክልልን በአንድ ከተማ ላይ ይመለከቱታል! በተለይ የሚከተሉትን ከልብ ከጎበኙ:_

1) መንገዶቹ

ምን ያህል በዘመናዊ መኪና ቢሄዱባቸው፣ ይህን ከአየር መንገድ እንደወጡ የሚረዱት ይሆናል። በአዘዞ በኩል ቢያሳልፉዎት እንዴት ደስ ባለኝ። መንገዶቹ ፈራርሰው አስፓልት የሚባል ነገር የሌለው መሆኑን ሲረዱ “የመጣሁት ሌላ ቦታ ነው?” ማለትዎ አይቀርም። ድሮ የሚያውቁት አስፓልት እንኳን የለም! ከተማ ውስጥ ሳይሆን ቋጥኝ የሚወጡ ይመስልወታል። በታችኛው መንገድ ሲመጡም የሚያገኙት ተመሳሳይ ነው። የሆስፒታሉን መንገድ ባስጎበኝዎት የማያምኑትን ይመለከታሉ!

2) የፋሲሊደስ ቤተ መንግስት
ጎንደር አለኝ ከምትላቸው ቅርሶች መካከል አንዱና ዋነኛው የፋሲለደስ ቤተ መንግስት ነው። በአሁኑ ወቅት የፋሲለደስ ቤተ መንግስት ሰው ደስ ብሎት የሚጎበኘው ሳይሆን “እየፈረሰ ነው” ብሎ ከንፈር የሚመጥለት ቅርስ ሆኗል። በአመት በርካታ ሺህ ዶላሮችን እያስገኘ የወፍ ላባ እና ኩስ እንኳ የሚጠርግለት አልተገኘም። ውጭ ላይ የነበሩት አግዳሚ ወንበሮች ተሰባብረዋል። ግንቡ እየፈረሰ ነው፣ ወለሎቹ ፈራርሰዋል። ቅርሱ ውስጥ የሚፈፀሙትን መቆጣጠሪያ ድብቅ ካሜራ ስለሌለው ግድግዳዎቹ የገባው ሁሉ የተሰማውን የሚፅፍባቸው ሰሌዳዎች ሆነዋል። ከቅርሱ የሚገኘው ገቢ የሚውለው ለፌደራል መንግስቱ መሆኑንም እንዲያስታውሱልኝ!

3/ ጎንደር ሆስፒታል

የጎንደር ሆስፒታል በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከሚባሉት ተቋማት መካከል መሆኑን አይረሱትም። ከላይ እንደገለፅኩልዎት በአዘዞ በኩል ወደ ሆስፒታሉ ቢያቀኑ አይንዎትን ማመን ያቅትዎታል። እርስዎ ስለ እናትዎ ያለዎትን ፍቅር በፓርላማው ገልፀዋል። የጎንደር እናቶች ለመውለድ ወደ ሆስፒታል ሲመጡ መንገዱ ከመፈራረሱ የተነሳ ፅንሱ ተዛብቶ የሞቱ እንደአጋጣሚ ሆኖም መንገድ ላይ የወለዱ እንዳሉ ይነግሩዎታል። ወደ ሆስፒታሉ ገባ ቢሉ እናቶች፣ ህፃናት ውጭ ላይ ተኝተው ያገኟቸዋል። ምን አልባት አጠር ሲል በአንድና ሁለት ወር ውስጥ የሚደርሳቸውን አልጋ እየተጠባበቁ ነው።

ይህ ሆስፒታል በትንሹ እስከ 10 ሚሊዮን ሕዝብ ለሚኖርበት አካባቢ ቅርበት ያለው ነው። ነገር ግን በመቶ የሚቆጠሩትን እንኳ በሚገባ እያገለገለ አይደለም። እስርን ካልፈሩ የዚህ ምክንያት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ባላቸው ግንኙነት ለሆስፒታሉ እርዳታ፣ ልምድና ባለሙያ በማምጣት ይሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች ተማርረው እንዲሰደዱ መደረጋቸው የቀሩት ሰዎች ይነግሩዎታል። በተጨማሪም ጠንካራ ሰዎችን ከሆስፒታሉ በማራቅ ለመንግስትዎ የሚመቸውን አቅመ ቢስ ሰራተኛ እንደቀጠሩበት ያጫውቱዎታል። ለአብነት ያህልም ከስር የተዘረዘሩት ባለሙያዎች በሰበብ ከዩኑቨርሲቲ ሆስፒታሉ እንዲርቁ ተደርገው አቅመ ቢስ ካድሬ እንደተተካበት ያጫውቱዎታል። ለምሳሌ ያህልም:_

1ኛ ዶ/ር መሰረት_ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት የነበሩ_ ወደጤና ጥበቃ ሚኒስትር
2ኛ ዶ/ር አበባው_ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ይሰራ የነበረ ወደ ክልሉ ጤና ጥበቃ
3ኛ ዶ/ር ዘኪ_ የጎንደር ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሀኪምና መምህር በአሁኑ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አንበዳ የተወሰደ
4ኛ ዶ/ር ካሳሁን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስታፒል የቆዳ ጥገና ሀኪምና መምህር በአሁኑ ሰዓት ወደ አሜሪካ ሀገር የተሰደደ
5ኛ ዶ/ር ተስፋዬ _ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል_ ትምህርት ሚኒስትር የተዛወረ
6ኛ ዶ/ር አለም ሰገድ _የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህር ወደ ጤና ጥበቃ
7ኛ ፕ/ር አፈወርቅ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የምርምርና የማህበረሰብ አገልህሎት ምክትል ፕሬዝደንት የነበሩ ወደሳይንስና ቴክኖሎጅ ተዛውረዋል
8ኛ ዶ/ር ኤባ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የማይክሮ ባዮሎጅ ትምህርት ቤት ክፍል ተመራማሪና መምህር_ በአሁኑ ወቅት ወደ ፓስተር ኢንስትቲትዩት
9ኛ ዶ/ር ደሳለኝ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህብረተሰብና ጤና ትምህርት ክፍል መምህርና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የነበረ፣ አሁን ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የተዛወረ
10ኛ ዶ/ር ማህሌት _ የጎንደር ሆስፒታል ስፔሻሊስት፣ ወደ ጳውሎስ የተዛወረች
11ኛ ዶ/ር በየነ _ የጎንደር ሆስፒታል የማክሮ ባዮሎጅ መምህርና ተመራማሪ የነበረ ወደ ፓስተር የተዛወረ
12ኛ ዶ/ር ኤርሚያስ ዲሮ _የጎንደር ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ትምህርት ክፍል መምህርና የአባላዘር በሽታ ተመራማሪ ~ወደ አሜሪካ የተሰደደ
ከላይ ለምሳሌ የተዘረዘሩት ባለፈው አምስት አመት ብቻ ወደተለያየ ቦታ ተዛውረው፣ ተማርረው ተሰድደው ሆስፒታሉ ባዶ ሆኗል። አንድ አቅመ ቢስ ካድሬን ወደ ጎንደር ለማምጣት “አትውሰዱን” እየተባሉ የረባ ስራ ወደማይሰሩበት ተቋማት ተዛውተው ሆስፒታሉ ባዶ እንደቀረ ያጫውቱዎታል!
3/ ጎንደርን በነፃ የሚጠቀሙባት ተቋማትን ይጎብኙ

መቼም የፓርቲዎ አጋር ከሆነው ዳሸን ቢራ ፋብሪካ ውጭ ጎንደር ውስጥ ሌላ ፋብሪካ እንደሌለ ይገነዘባሉ። አልፎ አልፎ በከተማው የሚያዩወቸው ግንባታዎች የወልቃይት ተወላጆች ንብረት ናቸው። መቀሌ ሄደው ቢገነቡ ብዙ ነገር እንደሚመቻችላቸው እየተነገራቸው “አንፈልግም” ብለው በጫና የሰሯቸው ናቸው። አልፎ አልፎ ከሚታዩት ውጭ ቀሪዎቹ የቆዩ የህዝብ ህንፃዎች ናቸው። ህንፃዎቹ በወር ከ30 እስከ 100 ሺህ ብር መከራየት የሚችሉ ናቸው። ይሁንና የተለያዩ የመንግስትና የፓርቲ ድርጅቶች እነዚህን ህንፃዎች በነፃ ወይንም ነፃ በሚባል ዋጋ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ። ጥቂቶቹን ልጥቀስልዎት:_

1)ቴሌ
2)መብራት ኃይል
3) ከፍተኛ ፍርድ ቤት
4)ዞን ፖሊስ
5) የከተማው ፖሊስ
6) ዞን አስተዳደር
7)ከንቲባ ፅ/ቤት
8 / ጤና ቢሮ
9)ትምህርት ቢሮ
10) ጉምሩክ
11)ኢንቨስትኘንት ቢሮ
12) የከተማው ፖሊስ ቢሮ
13)የከተማው ፋይናንስ
14) የከተማው ፋይናንስ
15)ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
16) ቀበሌ 3 ፅ/ቤት
17) ቻምበር ፅ/ቤት
18)ብሔራዊ ሎተሪ
19)ፖስታ ቤት
20)ጅንአድ
21)አምበሳ ጫማ
22) ጅምላሸቀጣሸቀጥ
23) የሰነዶች ማረጋገጫ
24) የከተማው ሲኒማ ቤት
25) አልማ
26) የወረዳ ፍርድ ቤት
27) ንግድ ባንክ
28) ሜጋ

እነዚህ ተቋማት በወር ከ30 እስከ 100 ሺህ ብር ኪራይ መክፈል ነበረባቸው። በአጠቃላይ ሲታይ የጎንደር ሕንፃዎች ለእነዚህ የመንግስት፣ የህወሓት የንግድ ድርጅቶች፣ የፓርቲ ድርጅቶች በርካታ ሚሊዮን ብሮ ዋጋን በነፃ ሲሰጡ ቆይተዋል። እነዚህ ተቋማት ህንፃ ቢገነቡ ይኖር የነበረው ኢንቨስትመንት እንዲሁ ቀርቷል። በነፃ የሚያገለግሉትን የጎንደር ተቋማት ሲጎበኙ ፋና ሬድዮ ጣቢያ የሚጠቅምባቸውን የደሴው የንጉስ ሚካኤል ቤተ መንግስት፣ የደብረማርቆሱ የንጉስ ተክለሀይማኖት ቤተመንግስትና ሌሎች ቅርሶችም የንግድ ቤት እንደሆኑ አስታውስዎታለሁ!

4/ ውሃና መብራት
መንግስትዎት ያለ ባለሙያ ስንት ፕሮጀክቶችን ሰርቻለሁ ብሎ ከለፈለፈ በኋላ ፕሮጀክቶቹ መና ሆነው እንደሚቀሩ የጎንደር ውሃ ፕሮጀክት ቋሚ ምስክር ይሆንዎታል። እናቶች፣ ልጆች በጀርባቸው ጀሪካን ተሸክመው ወደ ቀሃ ወንዝ ሲጓዙ አስጎበኝዎታለሁ። የመብራቱን ጉዳይ አንድ ቀን ብቻ በከተማዋ ቢያድሩ በደንብ የሚረዱት ይሆናል!

5/ ነጋዴዎች
አዲስ አበባ ላይ ነጋዴዎችን አነጋግረዋል። በየሱቁ ዞረው ማነጋገር አይችሉም እንጅ ዞረው ቢያነጋግሩ እውነታውን ያዩት ነበር። አንድ ሁለት ነጋዴዎችን ቢጠይቁ ምሬቱን ይነግሩዎታል። ነጋዴዎች ለፌደራል ወይ ለክልሉ መንግስት ግብር የሚከፍሉበት መንገድ አለ። ለፌደራል መንግስቱ የሚከፍሉት “plc” ብለው ሲከፍቱ ነው። ከዚህ በታች ያሉት የሚከፍሉት ለክልሉ መንግስት ነው። ሆኖም ግን የክልሉን ገቢ ፌደራል መንግስቱ (ህወሓት ማለቴ ነው) ሆን ብሎ ቀምቶታል። ለክልሉ የሚከፍሉት በጣም ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ ተፈርዶባቸዋል። plc ብሎ ያቋቋመ ለፌደራል መንግስት ስለሚከፍል ለክልሉ ከሚለፍሉት ጋር ሲነፃፀር በጣም ቅናሽ ግብር እንዲከፍል ይደረጋል። በዚህም ምክንያት የአማራ ክልል ገቢ እንዳይኖረው መደረጉን መፍትሄ ለማልሰጣቸው እኔ የነገሩኝን ለእርስዎማ በደንብ ይነግሩዎታል!

6/ የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ መኖርያ ቤት የነበረውን
ቀበሌ 18 የሚገኘውን ኮ/ል ደመቀ እስከ ሀምሌ 5 /2008 ዓም ይኖርበት የነበረውን ቤት ከፋሲለደስ ቤተ መንግስትም ቀድመው ቢጎበኙት ብየ እመክርዎታለሁ። 1ኛ እርስዎም የነበሩበት፣ አሁንም የሚመሩት መንግስት በሕዝብ ላይ የፈፀመው ጥቃት ነው። 2ኛ አንድ መከላከል የሚችል ንፁህ ዜጋ ላይ የመንግስት ነኝ የሚል ጦር ይህን የመሰለ ጥቃት ከፈፀመ፣ ለመከላከል አቅም የሌለውን ምን ሊያደርገው እንደሚችል መገመት ይችላሉ። ይህ ቤት መንግስት በአማራው ላይ ለፈፀመው፣ አማራውም በመንግስት መገፋቱ በቃኝ ያለበት ትልቅ ምልክት ነው! መንግስት ለሚፈፅመው አረመኔያዊ እርምጃ ምሳሌ ከመሆኑ ባሻገር ልብ ላለው ለወደፊት ቆም ብሎ ለማሰብ የሚያስችል ምልክት ነው!
ከላይ የተጠቀሱት የጎንደር ብቻ አይደሉም። ጎንደርን ለአማራ ክልል መነፀር አድርገው ይጠቀሙበት ዘንድ ነው። ይህ ስል እርስዎ ኢህአዴግ መሆንዎትን ረስቼ አይደለም! ኢህአዴግም ልቦና ይሰጠዋል ብየ አይደለም! ይህ ሁሉ መበደል፣ መበዝበዝ፣ መደህዬት ምን ሊያመጣ እንደሚችል ይገምታሉ ብየ ነው! የወልቃይት ጉዳይ ሌላ ነው! እኔ ከምነግርዎት ይልቅ ስታዲዬም ላይ ይዘመርልዎታል!

የእሳት አደጋ ተከላከይ ወይስ የለውጥ ሐዋሪያ? (ጎበና ጉግሣ)

„ኢትዮጵያ የሁላችንም ቤት ናት፡፡..የሓሳብ ልዩነት በረከት ይዞልን ይመጣል፡፡….እኛ ኢትዮጵያውያን ዲሞክረሲና ነጻነት ይስፈልገናል፣ይገባናልም፡፡….ነጻነት ከመንግሥት ለሕዝብ የሚበረከት ስጦታም አይደለም፡፡ከሰበዓዊ ክብር የሚመነጭ የእያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ጸጋ ነው፡፡“ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ

…አብይ አህመድ „የእሳት አደጋ ተከላከይ ወይስ የለውጥ ሐዋሪያ !“ ይህ አሁን ከያለበት የሚሰማ ጥያቄ ነው፡፡ ሰውዬውም በሕዝብ ጥያቄና በወያኔ መካከል የቆመ ነው፡፡ እሱ ብቻውን ምንም የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ ግን ደግሞ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ከተፈለገ …አብይ እህአዴግን ወክሎ፣ ከተለያዩ የሕብረተሱ ክፍሎች የተወጣጣ የሽግግር መንግሥት በአስቸከኳይ አዲስ አበባ ላይ መመሥረት ይኖርበታል፡፡“ የአንድ ጸሓፊ አስተያየት!

/**/

1

ምን ዓይነት „አዲስ“ አነጋገር ነው፡፡ እንዴትስ ያለ ግሩም አቀራረብ ነው፡፡ ለአለፉት 27 አመት በአገሪቱ ሚዲያ ቀርቶ ፣ከአንድም የመንግሥት ተወካይ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በጨረፍታ እንኳን ያልተሰማ ቃል ነው፡፡ ይህ፣ ያውም እንዳንዶቹ እንደሚሉት „..በወያኔዎች ተኮትኩቶ“ የሥልጣን ኮርቻ ላይ ከወጣ ከአንድ ጎልማሣ ቀርቶ፣ተቃዋሚ ነን ብለው ከሚመጻደቁ „…ነጻ-አውጪዎችም አፍ“ እስከ ዛሬ ድረስ ያልተሰመ አነጋገር አብይ በየሄደበት ያሰማል፡፡

ዲፕሎማት ወይስ የተደበቀ አጀንዳ አራማጅ! የለውጥ ሐዋሪያ ወይስ አፍዝ አደንግዝ! የእሳት አደጋ ተከላካይ ወይስ የለውጥ እንቅስቃሴው መሪ!

ጊዜው ተቀይሮአል፡፡ በዚያውም አገሪቱን ለአለፉት ረጅም አመታት ሲያምስ የቆየው „የኮሚኒስቶቹ የስታሊን“ የፖለቲካ ቲዎሪ እና ርዕዮተ ዓለሙም ፣ቢያንስ ከሦስት አመት ወዲህ ቀስ የእያለ አብሮ ተለውጦአል፡፡

የአገሪቱም ሊህቃን ለክፎአቸው ከሰነበተው ከ20ኛው ክፍለ ዘመን „…የእብደት ፖለቲካ“ ወደ ተጨባጩ መፍትሔ ፍለጋ የተመለሱ ይመስላል፡፡

የዓይን ምስክር ሁነን እንደምናየውና እንደምንሰማው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሁን አንደኛውና ግንባር ቀደም ፖለቲከኛ መሆኑ ነው!

ግን እንደገና መልሶ ለመጠየቅ፣ …አብይ ምን ይፈልጋል! ወያኔዎችስ ምን ይፈልጋሉ! ሕዝቡስ ምን ይላል! ተቃዋሚ ኃይሎችስ ምን ምን ይፈልጋሉ! ምንስ ይላሉ!

2

ወዶ ሥልጣኑን የሚያስረክብ ቡድን የትም አልታየም፡፡ ያውም ደግሞ የአገሩቱን ሐብት ፣ከመሬት እስከ ባንክ፣ከሕንጻ እስከ የእርሻ ቦታ፣ከሠራዊት እስከ ጸጥታና ፖሊስ፣ከውጭ ጉዳይ እስከ አስመጪና ላኪነት …. ይህን ሁሉ በእጁ ላይ የሚገኘውን ንብረት ወያኔ ዝም ብሎ አስረክቦ ወደ አደዋና ወደ መቀሌ አንገቱን ደፍቶ አይመለስም፡፡

ሁለት ሁኔታዎችን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ አንደኛው ደርግ እንዴት „ተጠናክሮ „ እንደወጣና ፣ሁለተኛው ሻቢያ፣ ወያኔ እና ኦነግ አዲስ አበባና አሥመራን እንዴት „ሊቆጣጠሩ ቻሉ“ የሚሉትን ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል፡፡

አሁን ብዙ ቦታዎች መሄድ አያስፈልግም፡፡ ንጉሠ-ነገሥቱ ሆኑ፣ልጅ እንዳልካቸው መኮንን፣ ተቃዋሚ ነን የሚሉትም የአገሪቱ ምሁራን ያኔ „….ለጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት“ ትንሽ ዕድል ቢሰጡ ኑሮ ደርግ የሚባል ፍጡር መጥቶ አገሪቱን ለአሥራ ሰባት አመታት ባልገዛት ነበር፡፡

ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያምም ከመፈርጠጡ በፊት „… ብሔራዊ እርቅ ብሎ ሁሉንም ለሚያሳትፍ ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት“ ምሥረታ በሩን ከፍቶ ቢሄድ ወያኔና ሻቢያ ብቻቸውን አሥመራና አዲስ አበባን ይዘው 27 አመታት በተከታታይ በአልጨፈሩብንም ነበር፡፡

አሁንም ያለነው ከዚሁ ሁኔታ ፊት ነው፡፡

„አብይ ይህን አለ፣…አብይ ይህን ብሎአል፣…አብይ፣ለማ መገርሣና ቆሬዎችን የሚያሸነፍቻው የለም፣ ቆሬና ፋኖ፣ፋኖና አማራ…“ ይህ ሁሉ ግምት ምኞት ሁኖ ይቀራል እንጂ „ሁሉን ነገር“ ጠቅልሎ ከያዘው ከወያኔ እጅ ሥልጣኑን በቀላሉ ፈልቅቆ ማውጣት አይቻልም፡፡ አንድ መንገድ ግን አለ፡፡

3

እሱም የቱኒዚያው መፍትሔ ነው፡፡

„…ሁሉንም የሚያሳትፍ …የክብ ጠረጴዛ ንግግር“ በአብይና – እሱ እንደ አለው „…በተፎካካሪ „ ቡድኖች መካከል የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስና ለ27 አመታት የቆየውን የወያኔን አምባገነን አገዛዝ ለማሰወገድ „ንግግር „ መጀመር ይኖርበታል፡፡

ይህ „…የክብ ጠረጴዛ ወይይትም“ ሰፋ ብሎ ሌሎቹን የሕብረተሰቡን ክፍሎችን ማሳተፍም ይኖርበታል፡፡

ግን አንድ ተዘሎ ሳይነሳ የማይታለፍ ነገር አለ፡፡

በ20ኛው እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን ፍልስፍና እና በዚያ „…ሃይማኖት የተጠመቁና“ በእሱም አስተሳብ እና አመለካከት ላይ „ቆመው“ የቀሩ ሰዎችና ድርጅቶች አሁንም በአገሪቱ አሉ፡፡ ይህ ለማንም ምሥጢር አይደለም፡፡ እነሱን ምን እናድርጋቸው!!

ጠጋ ብለው ሲያዩአቸው ጽሑፎቻቸው ሲመረመሩ አብዛኛዎቹ በምንም ዓይነት ከአቋማቸው „ፈቀቅ „ የማይሉና የማይቀየሩ ናቸው፡፡ እነሱም አሁን አገሪቱ ለአለችበት ችግር የሚያቀርቡትም „…መፍትሔ“ የታወቀ ስለሆነ፣እነሱንም እንደአለ መርሣት ያስፈልጋል፡፡ ዱሮንም ከቁም ነገርም አይገቡም!

አቋማቸውን ቀይረው ለዲሞክራቲክ ሥርዓት ምሥረታ ከቆሙ የንግግሩ ተሳታፊዎች ማድረጉ ከጉዳቱ ጥቅሙ ይበልጣል፡፡

ሌሎቹስ!

የላይኖቹን ተክተለው „…አገሪቱ …ለሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በዕድገቱዋ አልደረሰችም „ የሚሉ ክፍሎች አሉ ፡፡ እነሱም ጥቂት አይደሉም፡፡ ግን ጊዜው ጥሎአቸው የሄደ ስለሆነ እንደ ትልቅ ነገር አመለካከታቸውን በአሁኑ ሰዓት ማዳመጥ ትርፉ ጊዜ ማጥፋት ነው፡፡

በአለፉት ጊዜያት ኢትዮጵያን ለማዳን „..የጦር ትግል „ያስፈልጋል የሚሉ „ኃይሎች“ ተነስተው እንደ ነበር ለማንም ግልጽ ነው፡፡እነሱን እና ደጋፊዎቻቸውን አብይ አህመድ ሸንጎ ውስጥ በአሰማው „ግሩም“ ንግግሩ ከጫዋታ ውጭ አድርጎአቸዋል፡፡

ከእነሱም ጋር „…እኛ የምርጥ ዘሮች ልጆች ነን“ እሰከ ማለት ድረስ የዘለቁ ወያኔዎች አሉ፡፡ሕዝቡ ግን „ይበቃችኋል! ውረዱ…!“ ከአላቸው ወዲህ ይህ የትግሬዎች ፣የአደዋና የአክሱም የመቀሌ ልጆች ስብስብ አሁን ይክበር ይመስገና „ለሦሰት“ ተከፋፍለዋል፡፡

ስለዚህ „ወያኔን“ አሁን እንደ አለፉት አመታት እንደ „…አንድ ወጥ ኃይል“ መመልከት ጊዜው ያለፈበት አመለካከት ነው፡፡

4

በዚህ የኃይል „አሠላለፉ“ በአገሪቱ ተቀይሮአል፡፡

አንደኛው ወገን በአንድ አረፍተ ነገር ለማስቀመጥ „… በመሣሪያ ኃይል፣ሁሉንም አንበርክከን „ እንደድሮው እንደ አለፉት 27 አመታት ሕዝቡን እንግዛው የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ክፍል„…በጥገናዊ ለውጥ ፣…በሪፎርም „ ቀስ እያለ፣የሕዝቡ ቁጣ „…እሰከሚበርድ ድረስ“ እናዝግም ባይ ናቸው፡፡ ሦስተኛውና የመጨረሻው ቡድን ደግሞ „….ብሔራዊ እርቅን አውርዶ… የኢትዮጵያን አንድነት ጠብቆ፣….በአንድ ዲሞክራቲክ ሥርዓት ውስጥ አብሮ መኖር ይቻላል“ ብሎ የሚያምን ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ንግግር በደንብ የተከታተለ፣ አስተዋይ ሰው እንደሚረዳው አብይ አህመድ በአሁኑ ሰዓት ከየትኛው ወገን ጋር እንደቆመ ፣ብዙ ሳይደግም በቀላሉ ይረዳል፡፡

ይህ ከሆነ ደግሞ እሱና „ቁጥራቸው ቀላል ነው“ የማይባሉ የሸንጎ አባሎች እላይ የተጠቀሰውን „…ሦስተኛውን ክፍል“ የሚወክሉ „የለውጥ“ ኃይሎች ናቸው፡፡ ያም ሆኖ ግን ማንም ሰው እንደሚያውቀው ጠቅላላውን የሸንጎ አባሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አልመረጣቸውም፡፡

ስለዚህ ሸንጎው ሕዝቡ ስለአልመረጣቸው „…መፍረስና መበተን“ አለበት፡፡ ጥለውት ወደ መጡበትም ወደ ሥራቸው ተመልሰው መሄድ ይገባቸዋል፡፡

ሸንጎው ፈርሶ „…የሚቋቋመው ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት“ አዲስ ምርጫ ከሁለት ወይም ሦስት አመት በኋላ ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

ወያኔ ይህን አይፈልግም፡፡

ወያኔ የሚፈልገው በአብይ ካቢኔ ውስጥ የእራሱን ሰዎች ሰግስጎ በጀመረው ለመቀጠል ነው፡፡ የመከላከያው ሚስትር፣የአገር አስተዳደሩ፣ ጄኔራሎቹና የጸጥታው ፖሊሶች፣….የውጭ ጉዳዩ፣…የባንክ ገዢዎች፣…ከንቲባዎቹና፣ቀበሌው…. በእነሱ እጅ ሁኖ አብይ እየተዘዋወረ „ጥሩ፣ጥሩ „ ሰው መስማት የሚፈለገውን ነገር እየተነጋገረ ወደፊት እንዲያዘግም ነው፡፡

„…በታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ“፣እሱንም እንደማስፈራሪያ አድርጎ አብይንም ሆነ ጓደኛውን ለማን ፣እንዲሁም የሕዝቡን እንቅስቃሴ ጭምር „ ጊዜ ገዝቶ“ እሱን መሣሪያ በማድረግ እንደ አለፉት አመታት አገሪቱን ከፋፍሎ „…መዝረፍ“ ይቻላል ብለው አክራሪ ወያኔዎች ድግሳቸውን አለጥርጥር ደግሰዋል፡፡

ግን ደግሞ አንድ እዚያ አውሮፓ እየታተመ የሚወጣ ዕለታዊ ጋዜጣ በትክክል አዲሱን ሁኔታ አይቶ እንደ ጻፈው „….ከጠርሙሱ ውስጥ አንዳች መንፈስ አፈትልኮ ወጥቶአል፡፡ …ያ ! እንዳይወጣ ጥርቅም ተደርጎ፣ለዘመናት ታሽጎ ተቀምጦ የነበረው አንድ መንፈስ „ – ጋዜጣው ይህን መንፈስ “…ጂኒ“ ይለዋል – „….ከሕዝብ የተቃውሞው ቁጣ ጋር ጠርሙሱን ለቆ አምልጦአል፡፡… ያንን በአራቱም ማዕዘን አሁን ተኖ፣ አፈትልኮ አገሪቱን ያዳረሰውን መንፈስ፣ እንደገና በቀላሉ ሰብስቦና ለቅሞ ጠርሙሱ ውስጥ ከእንግዲህ መክተት – በኢትዮጵያ- አይቻልም…„ ብሎ ጋዜጠኛው ሓቁን በጥቂት ቃላት አስቀምጦአል፡፡

ጸሓፊው ዕውነት አለው፡፡

ከእንግዲህ ለጥያቄዎቻቸው ሕዝቡ መልስ ሳያገኝ ያ! „መንፈስ“ ተመልሶ ጠርሙስ ውስጥ አይገባላቸውም፡፡

ግን የፈነዳው አብዮት በጥንቃቄ ከአልተያዘ እና የተደረጃ የተቀነባበረ አንዳች „ዝግጅት“ ከአልመራው በቀላሉ „…ሊከሽፍም“ ይችላል፡፡

ቢቀር ቢቀር ወያኔ አገር ከሚያበጣብጥ ተንኮል ከመሥራት አይመለስም፡፡„… እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል“ ብሎ አፈጅቶን ሊሄድም ይችላል፡፡ ግን ይህን ለማድረግ ከእንግዲህ ኃይል አለው!

5

እሱን ከግምታችን ውስጥ አስገብተን ከመዘርዘራችን በፊት በመጀመሪያ አብይ ምን አለ! ብለን ንግግሩን እንደገና እንመለከተው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአሁኑ ሰዓት „….በረሃብ አለንጋ ስለ ሚጠበሱት በሚሊዮን ስለሚቆጠሩት የአገሪቱ ልጆች „ በንግግሩ ላይ አላነሳም፡፡ የጡራታ ገንዘባቸው ስለማይበቃቸው ፣እንዲያውም ምንም ስለሌላቸው፣እንደዚሁ በሚሊዮን ስለሚቆጠሩት እናትና አባቶች አንዳችም አረፍተ ነገር አልሠነዘረም፡፡

በየቤተ ክርሲቲያኑ ደጃፍና በየመንገዱ፣በልመና ስለሚተዳደሩት ዜጎቻችን ምንም ቃል ዞር ብሎ ለእነሱ አላሰማም፡፡

በቀን አንዴ በልተው ስለሚያድሩ፣የቤት ኪራይ መክፈል ስለማይችሉ፣….ለልጆቻቸው፣ልብስ ቀርቶ ለትምህርት ቤት የሚሆን ደብታርና እረሳስ፣ የምሰሳ ዳቦ እንኳን ማቅረብ ስለማይችሉት ቤተሰቦች ምንም አላለም፡፡

ከሁሉም „ሥራ እና ዳቦ ፣መሬትና ቤት“ አምጡልን ብለው ስለ ተነሱት ወጣቶች ጥያቄ አስቸኳይ „ማስታገሻ“ መልስ አላቀረበም፡፡

በሺህና በአሥር ሺህ „የኢትዮጵያ ባንዲራ አነሳችሁ „ ተብለው ወሕኒ ቤት ስለ ተወረወሩት እሥረኞችም እሱ አብይ አህመድ ምንም አላለም፡፡

50 ዶላር በማይሞላ የወር ደመውዝ ከአሥር ሰዓት በላይ በየፋብሪካው ለአውሮፓ ኩባንያዎች ስለሚሰሩት ሠራተኞች ጉዳይ አልተናገረም፡፡

ቤታቸው በአናታቸው ላይ ፈርሶ ፣እነሱ ተበትነው መሬታቸው ለቱጃሮች ስለተሸጠባቸው ቤተሰቦች ምንም አላለም፡፡

ያም ሆኖ ግን አብይ ስለ „….የሁላችንም ቤት ስለሆነችው ስለ ኢትዮጵያ „ አንስቶ ግሩም ድንቅ አረፍተ ነገሮችን ሸንጎው ላይ በአደረገው ንግግሩ አሥምሮበት ሄዶአል፡፡

በዚህም አንዱ የአውሮፓ ጋዜጠኛ እንደ ጻፈው „…ቡና ቤት ተቀምጠው ንግግሩን ያዳምጡ የነበሩ ሰዎችም፣ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጭብጨባቸው“ አብይን ሲያጅቡት ያየውን ስሜት ተገርሞ አምዱ ላይ አሥፍሮአል ፡፡

ቀጥሎ አብይ„… ልዩነቶቻችን እናስተናግድ“ ብሎአል፡፡“….በሓሳብ ፍጭት መፍትሔ እናገኛል“ ብሎ እሱም ያምናል፡፡ „….የሓሳብ ልዩነት እርግማን አይደለም“ ይለናል፡፡

„… እኛ ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲና ነጻነት ያስፈልገናል፣ይገባናልም“ ብሎ „….መጪው ጊዜ የፍቅርና የይቅርታ ጊዜ ነው“ ብሎ … እቅጩን አብስሮአል፡፡

„…በአገራችን ዲሞክራሲ እንዲያብብ“ ስለ ነጻነትና ስለ ፍትሕ፣ስለ የሕግ በላይነትም አንስቶ ስለ መተማመንና እና ስለ መግባባት ስለ በሠለጠነ መንገድ ቅራኔዎችን መፍታት ግሩም ሓሳቦችን አብይ በንግግሩ ላይ ሠንዝሮአል፡፡

ለመነሻ! ከዚህ የበለጠ ምን ያስፈልጋናል፡- ለመነሻ!!! ግን ይህን ተከትሎ ለአገሪቱ ችግር መፍትሔ ለማምጣት፣እቅዶቹን በደንብ ሰብሰብ አድርጎ አላስቀመጠም፡፡

በሕዝብ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙትን ወታደሮች ፍርድ እንዲቀበሉ አደርጋለሁ ብሎ ቃል አልገባም!!

6

ለአንድ አገር ዕድገትና ለዜጎች በአንድነት በጋራ ቤት ውስጥ ተቻችለው አብረው ለመኖር ቢያንስ „…ሁለት ቁልፍ ነገሮችን“ አንድ መንግሥት – በመመሪያ ደረጃ – ቁልጭ አድርጎ በማያሻማ ቋንቋ በሕገ መንግሥቱ ላይ ማስፈር አለበት፡፡ የሥልጣኔ ምንጩ ይህ ነው፡፡

አንደኛው „ሐሳብንና አመለካከትን በነጻ የመገልጽ መብት“ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ለማንም የማያዳላው „የሕግ በላይነት“ መኖር ነው፡፡

እነዚህ ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላሉ፡፡ ይህን የጨብጥ ሕዝብ ለገባበት ችግር „…ከፊል መፍትሔ“ አገኘ ማለት ነው፡፡

በአንድ በኩል፣ ….ነጻ ፍርድ ቤትን ፣ በሌላ በኩል…. ነጻ-ፐሬስን፣….በአንድ በኩል በነጻ ሕብረተስብ ውስጥ መኖርና መተንፈስን፣….በሌላ በኩል ተደራጅቶ መምረጥ እና መመረጥን….በአንድ በኩል መመራመርን፣ በሌላ በኩል ሠርቶ ጥሮ ግሮ፣ንብረትን ማፍራት….አንድ ሕዝብ የሚቻለው „….የሕግ በላይነት“ በአንድ አገር ሲሰፍንና፣“…..የፕሬስ ነጻነት …ሲረጋገጥ“ ብቻ ነው፡፡

የአውሮፓና የአሜሪካ ዕድገት፣የጃፓንና የህንድ … ሥልጣኔም የተገነቡትና የተመሠረቱት በእነዚሁ „ጡቦች“ ላይ ነው፡፡

ሦስተኛው „የሥልጣን ክፍፍል“ ነው፡፡ ሥልጣን ተሸንሽኖና ተከፋፍሎ፣አንዱ ሌላውን ከመስመር እንዳይወጣ“ የመቆጣጠር“ መብቱን ሕገ-መንግሥቱ ላይ መሥፈር ይኖርበታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን በአገሪቱ ለአለፉት ሺህ አመታት ያልታየውንና ያልተሰማውን „…. በሥራ ላይ ለማዋል ተነስቼአለሁ ተባበሩኝ“ የሚለውን ጥሪውን ሸንጎ ላይ ለአገሪቱ ዜጎች ፣ለተቃዋሚውም ጭምር አሰምቶአል፡፡ ይህን ጥሪ አሁን ዘሎ ማለፍ አይቻልም ፡፡ ይህን ጥሪ እንደ አልሰሙም ችላ ማለት ስህተት ነው፡፡

„…በፖለቲካ ዓለም አርፍዶ የመጣውን“- ሚካኤል ጎርባቾቭ -„ ታሪክ ትቀጣዋለች..“ ብለዋል፡፡ እንደምናውቀው ይህን ያሉትንም ሰው ፣ጎርባቾቭን፣ ታሪክ ፍርዱዋን ሰጥታ ቀጥታቸዋለች፡፡

አብይ አቅጣጫውን ሰጥቶአል፡፡ አብይና የአገሪቱ ሊህቃን፣ ደግሞ በንግግሩ ላይ እንደተሰማው „…አንድ ላይ ሁነው“ ተባብረው፣ እንደ „አንድ ሰው“ ይህን ጥሪ „….በሥራ ለመተርጎምና ለማሳየት“ መነሳት ይኖርባቸዋል፡፡

ይህን ለማድረግ ግን በመጀመሪያ ምን መደረግ አለበት!!

ትልቁ ጥያቄ በአሁኑ ሰዓት ይህ ነው!….ምን መደረግ አለበት! መልሱ „ በቤተ – መንግሥት፣የራት ግብዣ ማካሄድ“ አይደለም፡፡

የአለፈው ስህተት እንደ ገና በሌላ መልኩ „ ተደግሞ“ ብቅ ብሎ በአናታችን ላይ እንዳይጨፍር ከምንስ መጠንቀቅ አለብን!

7

ለአቢይ „ጊዜ እንስጠው“ የሚል አነጋገር በአሁኑ ሰዓት ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል፡፡ አንድ ቀን፣ ሁለት ሳምንት፣ ሦስት ወራት፣ወይስ አንድ አመት!

ይህን ማድረግ ስህተት ነው፡፡እንዲያውም ለወያኔዎች በቂ ጊዜ እንዲገዙ ዕድል መስጠት ነው፡፡

እንቅስቃሴው አለውጤት „… ተዳፍኖ፣ከሽፎ..“ እንዳይቀር ከተፈለገ፣ በመጀመሪያ ከሁሉም ነገር ቅድሚያ በአስቸኳይ ለአንድ ጉዳይ መስጠት ይኖርብናል፡፡

ሁሉንም ወገን የሚያሳትፍ „የራት ግብዣ ሳይሆን…የክብ ጠረጴዛ ስብሰባ „ መጥራት የጊዜው ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ንግግር ሲካሄድ -ምሥጢር መሆን የለበትም- ተመልካች „ሽማግሌዎች „ ፣ ዘጋቢ ጋዜጠኞች በቦታው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

በዚያ! የክብ ጠረጴዛ ንግግርም ላይ ፣…የሃማኖት አባቶች፣ የሙያ ድርጅት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተጠሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ተማሪዎች ጠበቆች፣ዳኞችና ደራሲያን ጸሓፊዎች….በጠቅላላው የአገሪቱ ምሁራን እና የሲቪል ማህበርሰብ ተወካዮች በሚሉ ማሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡

የንግግሩ ውጤትም ደግሞ – ሌሎች አገሮች እንደታየው- ለጊዜው በሁለት ነገሮች ላይ ብቻ ቢያተኩር ውጤቱ የተሳካ ይሆናል፡፡

አንደኛው አሁን ከአለው ሁኔታ ጋር አብረው የማይሄዱትን የሕገ-መንግሥቱን „አንቀጾች ማሻሻል“ ነው፡፡ አሻሽሎም በአዲስ እንዲተካ ማድረግ ነው፡፡ ይህን የሚሠሩና የሚያስተካክሉ ጠበብቶችን መሰየም ይኖርበታል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የንግግሩ ውጤት፣ „ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት“ እንዲመሠረት መንገዱን ይጠርጋል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ተገለው የነበሩትን የሕብረተስቡን ክፍሎች፣…የሃይማኖት አባቶች፣የተደራጁና ያልተደራጁ ምሁሮችን፣ተማሪዎችን፣ወጣቶችን… – እላይ የተባለውን እንደገና ለመድገም- ያቀፈ ከእነሱም የተውጣጣ አንድ„…..ጊዜያዊ …የሽግግር መንግሥት „ ኃላፊነቱን ተቀብሎ አገሪቱን ይመራል፡፡ ይህ „ ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት“ ከሁለት፣ግፋ ቢል ከሦስት አመት በላይ መቆየት የለበትም፡፡

ከዚያ በሦስተኛው ደረጃ „…ነጻ-ምርጫን“ በአገሪቱ አካሂዶ ሥልጣኑን፣ለተመረጡት ድርጅቶች ያስረክባል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ „ …ዲሞክራሲ ለእኛ ባዕድ አይደለም“ ብለው የሚያምኑ ከሆነ „…ነጻ- ፔሬሱን“ ከመንግሥት ቁጥጥርና ከመንግሥት ሳንሱር ነጻ ሁነው እንዲንቀሳቀሱ „መብታቸውን“ በመንግሥት ደረጃ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ከእሱም ጋር እንደዚሁ የእህአዴግ የግል ቤትና ተቀጥላ ሆነ ይሰራ የነበረውን ፍርድ ቤት አስተካክለውና ሽረው„… ነጻነቱ „ በይፋ የታወቀ ፍርድ ቤትና ዳኞች በአስቸኳይ ሥራቸውን እንዲጀምሩ ማረጋገጥ፣ይኖርባቸዋል፡፡

8

ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ ሥርዓት የሚደረገው ጉዞ እንዲሳካ፣ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች ደማቸውን ያፈሰሱበት አላማቸው እንዳይቀለበስ፣ እላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡እሱ ብቻ አይደለም፡፡ የሕዝቡም ጥያቄ በአስቸኳይ መልስ የሚያገኘው በዚሁ መንገድ ብቻ ነው፡፤

እነዚያ „ዓለምን የሚያንቀጠቅጥ „ ….የሚያስፈራ ጦርና የስለላ ድርጅት፣እንዲሁም አንዴ በግዛት ዘመናቸው በሚሊዮን ይቆጠሩ የነበሩትን ካድሬዎችን ሰብስበው የነበሩት „…. የፖላንድና የሩሜንያ ፣የቡልጋሪያና የምሥራቅ ጀርመን፣የቼኮዝሎቫኪያና የሶቪየት ኮሚኒስት ፓርቲዎች“ ደም ሳይፈስ የሥልጣን ሽግግር በየአገራቸው ያካሄዱት „በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ“ ነው፡፡

ይህን መፍትሔ አንቀበልም ያሉት እንደ ቻውቼስኮ ዓይነቶቹ ደግሞ ተይዘው – ለማስታወስ- በጥይት ተደብድበው ከሥልጣናቸው ወርደዋል፡፡

„…ለውጥ „ በአገሪቱ በኢትዮጵያ እንዳይመጣ የሚፈልገው አንደኛው የወያኔ ክንፍ „ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ „ ዕድሜአቸውን አራዝመው እንደገና ሊገዙን ይፈልጋሉ፡፡ ይህቺን ዓይነቱዋን ዕድል ግን እንደገና መልሰን ለእነሱ መስጠት የለብንም፡፡

ሌላም „ሕልምም“ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በሐምሌ እና ነሓሴ ወር „…እህአዴግ ተዋህዶ“ አንድ ፓርቲ ሆኖ ሊቀመንበሩንም አብይ አህመድ አድርጎ ተቀበሉኝ ሊለን ይፈልጋል፡፡

ምናልባት ስማቸውን ቀይረው „….የሶሻል ዲሞክራቲክ“ ብለው ብቅ ሊሉ ይችላሉ፡፡ ወይም እንደ ኢሳያስ አፈወርቂ „… የፍትህና የእኩልነት ፓርቲ „ የሚለውንም ስም ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ወይም….“ አዲሱ አብዮታዊ ዲሞክራቲክ ፓርቲ …“

ወያኔ በዝርፊያ ያካበተውን ሐብት እና ሥልጣኑን ከመዳፉ ለአለማስወጣት ገና „ብዙ „ የሚያደርጋቸው ነገሮች አይጠፉም፡፡

እንደ ቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ወይም እንደ ግብጹ ጄኔራል አዚዚ „ከሕዝቡ ቁጣ „ በአንዳንድ ብልሃቶች „….እናምልጣለን“ ብለው ለተመልካቹ አዲስ የሆነ „መላ ምትም „ ሊመቱ ይችላሉ፡፡

ግን የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሆነ የግብጽ ሠራዊት …ጄኔራል አዚዚም እንደ ወያኔ „…በዘር ላይ የተሰባሰበ…. የተደራጀም“ ዘርንም መሠረት አድርገው፣ አገራቸውን የዘረፉ ሰዎች አይደሉም፡፡

ወያኔ … እንደ ቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ወይም እንደ አዚዚ „ተቀባይነት“ የሚኖረው፣ „….ከሥልጣኑም ፣….ከዘረፈውም ሓብቱም“ ለሕዝቡ መልሶ ሲያካፍላቸው ብቻ ነው፡፡

በአጭሩ የቻይና እና የግብጽ መሪዎች „…በዘር“ ተደራጅተው „እፍኝ የማይሞሉ ሰዎች“ አገራቸውን አላራቆቱም፡፡ ከዚያም በላይ የሁለቱ አገር መሪዎች „…ዳቦና ሥራ፣…ብልጽግና እና ዕድገትን „ ለሕዝባቸው አምጥተዋል፡፡ ከተገኘውም ለዜጎቻቸው አካፍለዋል፡፡ የአገራቸውን መሬትም ለባእድ መንግሥታት፣….ለአውሮፓና፣ለአረብ፣….ለቻይናና እና ለቱርክ ቱጃሮች እንደ ወያኔ እነሱ አልሸጡም፡፡

የፈነዳው አብዮት ተኮላሽቶ እንደይከሽፍም ፣ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በጀመረው አላማ መቀጠል የሚችለው እላይ የተባሉትን እርምጃዎች በሥራ ተርጎሞ ሲያሳይ ብቻ ነው፡፡ አብይ ለእራሱም ሆነ፣ ሸንጎ ውስጥ የተናገረውን „ቃሉን ለማክበር“ ፣ከእሱም ጋር የቆሙትን ሰዎች ደህንነት ለመጠበቅ፣ „ ሁሉም በተቻለ መጠን አስተዋጽዎውን ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ እንዲያበረክት“ …የክብ ጠረጴዛ ስብሰባ „ ሲጠራ ብቻ ነው፡፡

ወደፊት መቋቋም ያለበት „አዲሱ የአብይ ካቢኔም „ ዱሮ የምናውቃቸው ሰዎች፣ ወያኔዎች መሆን የለባቸውም፡፡ „ አዲሱ ካቢኔ“ ከሁሉም የሕብረተሰቡ ክፍል የተወጣጣ ፣ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ነው፡፡

„ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረትና ታፍራ፣ተከብራና በልጽጋ ለዘለዓለም ትኑር፡፡ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ“

ይህ አነጋገር በትክክል በሥራ ላይ የሚተረጎመው ደግሞ – ከአምባገነን ሥርዓት ወደ ዲሞክራሲ የተሸጋገሩትን አገሮች መንገድ ስንከተል ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ መፍትሔ ፍለጋ ላይ ከሌሎቹ አገሮች በምንም ዓይነት አትለይም፡፡ ዪኒቨርሳል መፍትሔ ነውና!

ጎበና ጉግሣ

የአማራ ወላድ እናቶችን የማምከንና ዘር የማጥፋት ወንጀል በአማራ – ባህር ዳር (አያሌው መንበር)

/**/

የባህር ዳር ጤና ጣቢያ እናቶችን በግዳጅ የ5 ዓመት የወሊድ መከላከያ እየሰጠ ነው፦ ተጠቃሚ

ባህር ዳር ቀበሌ 03 ሙሏለም አዳራሽ ጀርባ ያለው ጤና ጣቢያ የአጭር ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያ (በተለይም የ3 ወር) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የ3 ዓመትና የ5 ዓመት ብቻ እየተሰጠ መሆኑን የአገልግሎቱ ፈላጊ እናቶች መረጃውን አድርሰውናል።

እነዚህ እናቶች እንደሚሉት ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ለመዉሰድ በሚመጡበት ጊዜ የ3 እና የ5 ዓመት ነዉ መዉሰድ /መርፌ መወጋት / ያለባችሁ እየተባሉ በግዴታ አብዛኞችን እየወጓቸዉ ነዉ።

እነርሱ ግን የ3 ወር ነዉ የምንፈልገዉ በማለት ሲከራከሩ መመልከቱን ደግሞ ሌላ ሰው አረጋግጦልኛል። ይህ ግለሰብ እንደሚለው ግማሾቹ ባሌ ይቆጣል ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ አንፈልግም እያሉ ሳይወጉ ሚሄዱም አሉ፡፡

በጣም ሚያሳዝነዉ ግን በጣም ብዙዎቹ “የመንግስት አቅጣጫ ነዉ እያሉ በግድ ይወጋሉ። ስለዚህ ለሚመለከተዉ አካል አድርሱ ይላሉ እነዚህ ታዛቢዎችና የአገልግሎቱ ፈላጊዎች።

የአማራ እናቶች የረጀም ጊዜ የወሊድ መከላከያ እንዲወስዱ ከመገደዳቸው ባለፈ የማምከኛ መርፌ ተወግተው ልጅ መውለድ እንዳልቻሉ ከአመታት በፊት ፀበል ተጉዘው ፈጣሪያቸውን እየለመኑ ያሉ በጎጃም የአንድ አካባቢ እናቶችን ሮሮ በቪዲዮ መመልከታችን ይታወሳል።

አጋዚና ልዮ ሃይል በሞያሌ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ቦንብ ወርውርው ከባድ ጥቃት አደረሱ 3 ሰዎች ገደል፣ 64 ሰዎች አቆሰለ

/**/

በትግራይ ጀንራሎች እና በአጋዚ ጦር የሚደገፈው የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይሎች በሞያሌ በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የቦንብ ጥቃት ፈፀሙ። በተወረወረውና በደረሰው የቦንብ ከሶስ በላይ ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል።

በሞያሌ ከተማ በአብዲ ሊሌ የሚመራው የሱማሌ ልዩ ሀይል በፈፀመው የቦንብ ጥቃት እስካሁን አራት ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸው አልፏል:: የቆሠሉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ64 በላይ ነው።

የቦንብ ጥቃቱ የደረሰው በርካታ ሰዎች ተሰብስበውበት በነበረው በሞያሌ ከተማ የአቶብስ መናሀርያ ውስጥ ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ እንዴት ኖት ደና ኖት ወይ ታርቀናል ካሉ ሁለት ሳምንት ሳይቆጠር በአብዲ ሊሌ የሚመራው የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይል በሞያሌ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የቦንብ ጥቃት ፈፅሟል ጥሩ ንግግር ማድረግ አገርን መምራትትና ማስተዳደርን አይወክልምና እርሶም ስልጣኔን ለቅቄያለው ከማለቶ በፊት ይህን ግድያና የማፈናቀል ጉዳይ አስቡበት:: ሌላው የወልቃይትንም እንዲሁ:: በወልቃይት ጉዳይ ላይ እርሶ ከተናገሩት በላይ አደጋ አለው ይህ አደጋ ደሞ ለማንነቱ መሰዋት ሊሆን የተዘጋጀ ማንነቱንና መሬቱን ንብረቱን ለሀያ ሰባት አመት የተቀማ የአማራ ህዝብ እንዳለ አይዘንጉት:: ይህን ጉዳይ በቶሎ መፍትሄ አበጁለት:: የህወሀትን ሰዎች ለማስደሰት ብለው በወልቃይት ጉዳይ ላይ ማኖ ነክተዋልንና ከባድ ችግር እንዳይፈጥሩ:: አልያ ከዚህ በኃላ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው ግድያ ቀጥተኛ ተጠያቂ ኖት:: ደሞ ይህንንም የዲያስፖራ የፌስቡክ ወሬ ነው እንዳይሉ::

በሀይለማሪያም ግዜ የአጋዚ ታጣቂዎችና ልዩ ሀይሎች ግድያ በክላሽ ነበር:: እድሜ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ልዩ ሀይሎችና አጋዚዎች ተሻሽለው በቦንብ አረገውታል:: ትንሽ ከቆየን በታንክና ፀረ አውሮፕላን በመጠቀም ይጨሩስናል::

 

ሁሉንም ሰዎች ሁሌም ማታለል አይቻልም! (ጌታቸው አስፋው)

/**/

ጌታቸው አስፋው (የብሔራዊ ኢኮኖሚ  ዕቅድ ባለሙያ)

ብዙ ሰው መንግሥት ስለ ኢኮኖሚው ዕድገት የሚያቀርበው መረጃ እውነት ነውን? ለምንስ ሁልጊዜ በዐሥራ አንድ በመቶ ያድጋል? የሚል ጥያቄ በጭንቅላቱ ውስጥ ይመላለሳል፡፡ ዐሥራ ሦስት ዓመታት ድርቅ ሲኖርም ሳይኖርም፣ የውጭ ምንዛሪ እየተሟጠጠም፣ ሥራ አጥነት እየበረከተም፣ ኢኮኖሚው በዐሥራ አንድ በመቶ አደገ ይባላል፡፡ ይኽ የሕዝብ እንቆቅልሽ መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

ራስ ለራስ ምስክር መሆን አይከብድም፡፡ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የዓለምን አምስት እጥፍ የአፍሪካን ሁለት እጥፍ በሆነ የዕድገት መጣኝ በየዓመቱ እያሳደግን ለዐሥራ ሦስት ዓመታት ያህል ዘልቀናል፤ ከሚሉት የራስ ለራስ ምስክርነት የኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ መረጃዎች ተነስተን፣ ከገበያው ሁኔታ ጋር አነጻጽረን የተደበቀውን እውነት ከተሸፈነበት መጠቅለያ በመግፈፍ እርቃኑን እናያለን፡፡

ዓይን ራሱ በቀጥታ አይቶ ስለሚለካና ስለሚገምት እንደ ጆሮ ከሌላ ሰው በሰማው አይታለልም፡፡ ራሱ ባዘጋጀው ስታቲስቲክስ ከራሱ ከመንግሥት ባለሟል አፍና በሁለት ቀን ቆይታው የተነገረውን መልሶ ከሚነግር የውጭ እንግዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አልታለልም ካለ ቆይቷል፡፡ ቀባጣሪዎች ብዙ ቀባጥረው ስለ ኢኮኖሚው የተባለው ሁሉ ውሸት ሆኖ ራሳቸውን ሊቆጫቸውም አየጀመረ ነው፡፡

የመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ኢኮኖሚው ከ2003 እስከ 2007 ለአምስት ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ በ10.1 በመቶ አድጓል ተባለ፡፡ ዓመታዊ አማካይ የነፍስ-ወከፍ ገቢ በ2002 ከነበረበት 377 የአሜሪካን ዶላር በ2007 መጨረሻ ወደ 691 የአሜሪካን ዶላር አድጓል፤ በ2017 ዓ.ም. መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ የማሰለፍ አገራዊ ራዕይ ተይዟል ተባለ፡፡ እነ ጂቡቲ፣ እነ የመንና እነ አፍጋኒስታን ኢትዮጵያን ቀድመው መካከለኛ ገቢ ውስጥ ይገባሉ ስለተባለ መካከለኛ የከፍተኛና የዝቅተኛ መሃል ቤት ከሆነ፣ ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ውስጥ ስትገባ የዝቅተኛ ገቢ አገር ስለማይኖር መካከለኛ የሚባለው ነገር ትርጉም አይኖረውም፡፡

በ1997 የበጀት ዓመት 38.7 በመቶ የነበረ የድህነት መጣኔ በ2003 ዓመት ወደ 29.6 በመቶ ዝቅ ብሎ ነበር በ2007 በጀት ዓመት መጨረሻም ወደ 23.4 በመቶ ገደማ ዝቅ ብሏል፡፡ በዓለም ዓቀፍ የገቢ ክፍፍል ፍትሐዊነት መለኪያ በ ‹Gini Coefficient› አመልካች ከአንድ በታች ሆኖ ወደ ዜሮ የተጠጋ ዝቅተኛ ክፍልፋይ ቁጥር መሆን ደርግ ንብረትን ከሀብታሞች ወርሶ የሕዝብ በማድረጉ የመጣ ውጤት ቢሆንም፣ የኢሕአዴግ ስኬት በማስመሰል በ1997ም በ2003ም 0.3 ሆኖ እኩልነት ተረጋግጧል ተባለ፡፡

ይኽ ከዚህ በላይ የቀረበውን የመንግሥት የኢኮኖሚ ስኬት ስታቲስቲክስ ዘወትር የምንሰማው፣ ከመንግሥት ባለሥልጣናትና ባለሙያዎች ሲሆን ማረጋገጫው ራሳቸው ለራሳቸው ምስክር በመሆን የራሳቸው የባለሙያዎቹ ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችና መረጃ እና መረጃውን ከነርሱ ያገኙት ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ናቸው፡፡

ዘወትር በአገር ዐቀፍ ደረጃ ስለ ኢኮኖሚው ዕድገት ወሬ እና የሀብት ሥርጭት ፍትሐዊነት ዲስኩር ተዓማኒ አለመሆን በግለሰብ ደረጃ ተቃራኒ በመረጃ አቅርቦ ማፍረስ ባይቻልም እንኳ፣ በገበያ ውስጥ መገለጫ አረጋግጦ ሊሞግት የቻለ ባለሙያ ባለመኖሩ፣ ሁኔታው ራሱ ገፍቶ መጥቶ የሕዝቡን አመጽ ቀስቅሷል፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የምርት ገበያውም የሠራተኛ ገበያውም፣ የካፒታል ገበያውም የመሬት ገበያውም መዛባታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ አውቋል፡፡ የምርት ገበያው ዋጋ ሰው አስመርሯል፡፡ በሠራተኛ ገበያው ውጥንቅት ወጣቱ ትውልድ ሥራ አጥቷል፣ ለራስህ ሥራ ፍጠር፤ አለበለዚያ መሞት ወይም መሰደድ ትችላለህ ተብሏል፡፡ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት በዝቶ የሸቀጦችን ዋጋ አንሯል የውጭ ምንዛሪ መጣኙን አዛብቶታል፡፡ በዓለም ታላላቅ ከተሞች እንኳ ባልታየ ዓይነት በአዲስ አበባ የአንድ ካሬ ሜትር መሬት ዋጋ ሦስት መቶ ሃምሳ አምስት ሺሕ ብር ደርሷል፡፡ በእነኚህ ሁሉ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ድምጽ ሆኖ ሁላችንንም ሁሌም ማታለል አይቻልም ብሏል፡፡

የወጣቱ ሥራ አጥነት ለአገር ህልውና የሚያሰጋ ኹከት ቀስቅሶ የከፍተኛ ባለሥልጣናትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ መቆየቱን እናስታውሳለን፡፡ በውጭ ምንዛሪና በካፒታል እጥረት ምክንያት ብዙ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች ተጓትተዋል መዋዕለንዋይ ማፍሰስም አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ የከተማና የገጠር መሬት ሽሚያው ሕዝብ ከሕዝብ ከማጋጨቱም በላይ ለፀጥታ አስከባሪዎችም ፈታኝ ጊዜ ሆኖ ከርሟል፡፡

ናይጄሪያዊው ቁጥር አንድ ከበርቴ የሆኑትን የዳንጎቴን ሲሚንቶ ፋብሪካ ሊያዘጋ የደረሰ የመዋዕለንዋይ አፍሳሽ መብት ያልተጠበቀበት ሁኔታ ተፈጥሮ ግጭቱ በውይይት ተፈቷል፡፡ እያንዳንዱ ክልል የክልሉ መሬትና የክልሉ ማዕድናት ለክልሉ ወጣት ብቻ እያለ ወጣቱን በቋጥኝ ፍንቀላ ሥራ አሰማርቷል፡፡ ለምን ያህል ጊዜ እንዲህ በተፈጥሮ ላይ ብቻ ተመርኩዞ መኖር እንደሚቻል ማወቅ አይቻልም፡፡

እህል በጆንያ እየለኩ የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራትም ነፍሶባቸዋል፤ ‹ብሪክስ› የተባሉትና በቅርቡ በፍጥነት ስለማደጋቸው የተመሰከረላቸው ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካም አርጅተዋል፤ አሁን ዓለም እያወራ ያለው ስለ እኛ ዕድገት ነው ብለው፣ እስከ ዐሥራ አንደኛው ሰዓት አውርተው የነበሩ የመንግሥት ባለሟሎችና ጋዜጠኞች በዐሥራ ኹለተኛው ሰዓት ላይ የዋጋ ንረቱን አመኑ፡፡ ሁከት የቀሰቀሰው የወጣቱ ሥራ አጥነት ነው አሉ፣ የብራችሁን ዋጋ አርክሱ ላሉ የዓለም ባንክ ሰዎች ከጆንያ ምርት ውጪ ለዓለም ገበያ የሚቀርብ ሸቀጥ ሳይኖረን ለምን ብራችንን እናረክሳለን አሉ፡፡

የኢኮኖሚ ሊቆች፣ “በመንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንዳንድ ሰዎችን ሁሌም ማታለል ይቻላል፤ ሁሉንም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ማታለልም ይቻላል፤ ሁሉንም ሰዎች ሁሌም ማታለል ግን አይቻልም፤” የሚል የአብርሐም ሊንከንን ንግግር ጠቅሰው ደካማ ፖሊሲ በስተመጨረሻ አግጦና አፍጥጦ በአደባባይ ተገልጦ በሕዝብ እንደሚታወቅ ይናገራሉ፡፡

የእኛ ኢኮኖሚስቶች በሙያቸው የተረዱትን ቀድመው ባይናገሩም ሁሉንም ሰዎች ማታለል አይቻልም የሚባልበት ደረጃ ተደርሶ ሕዝቡ እየተናገረ ነው፡፡ ሕዝቡ የመንግሥት ኢኮኖሚ ባለሟሎችን እየሞገታቸው ነው፤ ኑሯችን የምትሉትን አይመስልም እያለ ነው፤ አደገ የምትሉትን በወረቀት ላይ ራሳችሁ ጽፋችሁ ራሳችሁ ከምትነግሩን በአካል አምጡና በገበያ ውስጥ ዘርግፉትና በዓይናችን አሳዩን አለ፡፡ ከመንግሥት አገልግሎት ውጪ የሆኑ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችስ እንዴት ለሕዝቡ እውነቱን ማስረዳት አቃታቸው፡፡ ሙያቸውን እንዴት ሕዝቡ ቀድሟቸው አወቀ፡፡

በፍጥነት አደገ የተባለው ኢኮኖሚ ራሱን ኢሕአዴግን እየፈተነው ነው፡፡ ምክንያቱም ኢሕአዴግ ራሱን ያዘጋጀው የግብርና ኢኮኖሚን ለማስተዳደርና ለመምራት ብቻ ሲሆን፣ በኢንዱስትሪ የበለጸገች የግሎባላይዜሽን ዘመን አገር መሪ ለመሆን ቀደም ብለን እንደተመለከትነው ከፍተኛ የገንዘብ አስተዳደር ችሎታንና ኢኮኖሚን በመጠን ሳይሆን በአመልካቾች (indices) የመለካት ችሎታን ይጠይቃል፡፡ የአቅም ማነስ ምልክቶቹ አሁን መታየት ጀምረዋል፡፡

በሦስት መቶና በአራት መቶ ዶላር ዓመታዊ ነፍስ ወከፍ ገቢያችን በሸቀጦች ዋጋ ሰማይ መንካት ከአውሮፓና ከአሜሪካ ተስተካክለናል፡፡ እንደነርሱ ነፍስ ወከፍ ገቢያችን ሠላሳ ሺሕና አርባ ሺሕ ዶላር ሲደርስ የሸቀጦቻችን ዋጋ የት ሊደርስ ነው፡፡ የዋጋ ንረትና ግሽበትን አሁን ካለበትም በላይ እንዳይሆን መንግሥት በቁጥጥርና በራሽን ለወደፊት እየገፋውና እያስተላለፈው ነው እንጂ እየቀረፈው አይደለም፡፡

ባለሟል ኢኮኖሚስቶች የሚበልጡና የሚያንሱ ቁጥሮች መፈብረክ ላይ ችግር የለባቸውም ችግሩ ቁጥሩን መተርጎሙ ላይ ነው፡፡ ቁጥርን መተርጎም ሳይቻል ሲቀር ደግሞ ኢኮኖሚክሱ ተጠቃሎ ማሳረጊያው ይበልጣል ያንሳል ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሟሎች ክህሎትና ችሎታ ይበልጣል ያንሳል ብቻ ሆኗል፡፡ ይበልጣል ያንሳል ለማለት ከሐምሳ ዓመት በፊት የነበረውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ኢኮኖሚና ከሠላሳ ዓመት በፊት የነበረውን የደርግ ዘመን ኢኮኖሚ ካለበት ቦታ ቆፍረው ያመጣሉ፡፡

መሠረታዊ ሁኔታዎች ተሟልተውለት እንደ ሰው ለመኖር የሚፈልገው ሕዝብ እና በይበልጣል ያንሳል ትንታኔ ቁጥር ቆልለው እንደ ቻይና ለማደግ የሚፈልጉት የኢኮኖሚ ባለሟሎች የኢኮኖሚ ቁጥሩን በመተርጎም ላይ አልተግባቡም፡፡ ፍጆታ ለዛሬ፣ መዋዕለንዋይ ለነገ ነው፡፡ ዛሬ ሙትና ነገ ትኖራለህ የተባለ ሕዝብ ነገ ለመኖር ዛሬ መሞትን አልመረጠም፡፡ ዛሬን ሳይሞት ነገ መኖር የሚችልበት መንገድ ባለሟሎቹና መንግሥታቸው አላወቁትም እንጂ ዛሬን ሳይሞት ነገንም መኖር ይቻላል፡፡

የዛሬ ኑሮ ፍጆታና የነገ ዕድገት መዋዕለንዋይ ሀብት የሚሻሙ ተጻራሪ ሁኔታዎች ሳይሆኑ የሚደጋገፉ ናቸው፡፡ ነገር ግን መደጋገፋቸው ችሎታ ባለው ባለሙያ መገራት አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ችግርም ከይበልጣል ያንሳል ትንታኔ ወጥቶ፣ የፍጆታን እና መወዕለንዋይን መደጋገፍ የሚፈጥር ባለሙያ ባለመኖሩ፣ እየኖሩ ማደግ ሲቻል እየሞቱ ማደግ እንደ አማራጭ መወሰዱ ነው፡፡

ለድህነት መቀነስም ሆነ ለሌሎች የሰብዓዊ ልማት መለኪያዎች መሠረቱ የጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ዕድገት ስለሆነ ስለ አለካኩ በጥቂቱም ቢሆን ማወቅ ይጠቅማል፡፡

የአገር ውስጥ ምርት መጠን ዕድገት የሚጋነንበት ሦስት ምክንያቶች አሉ፡፡ አንዱ የተባበሩት መንግሥታት የብሔራዊ ገቢ አለካክ ሥርዓት ለውጥ ሲያደርግ ሲሆን፣ ሁለተኛው አገራት የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት መለኪያ ዋጋቸውን ሲከልሱ ነው፡፡ ሦስተኛው ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት መጠን የሚለካው በሙያዊ ግምት ስለሆነ የፖለቲካ ሰዎች በባለሙያው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በሦስቱም መንገዶች ዕድገቱ ተጋኖ ቀርቧል፡፡

የብሔራዊ ኢኮኖሚ ገቢ ሒሳብ መለካት ከተጀመረበት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 1947 ጀምሮ የአለካክ ዘዴው በ1956፣ በ1968፣ በ1993፣ አና በ2008 ተከልሷል፡፡ በክለሳዎቹ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት ምክንያት ወደ ገበያ የገቡ አዳዲስ ምርቶች፤ ከክለሳው በፊት በኢ-መደበኛነት ተመድበው ሳይለኩ የቆዩ ሥራዎች፣ የቤት እመቤቶች እቤት ውስጥ የሚሠሩት ሥራዎች፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተሠሩ የሚባሉትና ጥቂት ሳይቆዩ የሚደርቁ ችግኞችና የሚደፈኑ ጉድጓዶች ተገምተው በቆጠራው ተካተዋል፡፡

በጥቅል የአገር ውስጥ ምርት መለኪያ ዋጋ መከለስ ምክንያትም ኢትዮጵያ የጥቅል አገር ውስጥ መለኪያ ዋጋዋን ከ1992 ወደ 2003 ስትከልስ ኢኮኖሚዋ በቅጽበት ሦስት እጥፍ እንዳደገ የመንግሥት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በፖለቲካ ተጽዕኖ ግምቱን ከፍ አድርግልኝ ማስረጃ የሚፈልግ ጉዳይ አይደለም፡፡

በወረቀት ላይ በእነዚህ ሦስት ምክንያቶች ስታቲስቲክሱ ያድጋል፡፡ አገሮች በዕድገት ደረጃ ይነጻጸራሉ፤ በኑሮ ደረጃ ግን ምንም የተለወጠ ነገር ስለሌለ የሕዝቡ ኑሮ አይሻሻልም፡፡ እቤት ውስጥ ለግል ፍጆታ ይመረት የነበረው ገበያ ስለወጣ ወይም መለኪያ ዋጋው ስለተቀየረ ወይም በፖለቲካ ጫና ግምቱ በመዛባቱ ኢኮኖሚው ያድጋል ኑሮ ያው ነው፡፡ በወረቀት ላይ በእነዚህ ሦስት ምክንያቶች ስታቲስቲክሱ ያድጋል፤ አገሮች በዕድገት ደረጃ ይነጻጸራሉ ደረጃቸውም ይገለባበጣል በኑሮ ደረጃ ግን ምንም የተለወጠ ነገር ስለሌለ የሕዝቡ ኑሮ አይሻሻልም፡፡

ይኽ ስታቲስቲካዊ አሃዝ አርተፊሻል ቁጥር እንጂ በሕዝብ የኑሮ ደረጃ ላይ ለውጥ እንደማያመጣ እንደ አውሮፓ ዘመን አቆጣጠር በ2013 ናይጄሪያ ጥቅል የአገር ውስጥ ምርቷን የምትለካበትን የአውሮፓ ዘመን አቆጣጠር 1990 ወደ 2010 ከልሳ በቀድሞው ዋጋ ሁለት መቶ ሰባ ቢልዮን ዶላር የነበረውን ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ወደ አምስት መቶ ዐሥር ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር አሳድጋ፣ ቀደሞ በሦስት መቶ ሰባ አምስት ቢልዮን ዶላር ከአሕጉሪቱ በአንደኝነት ደረጃ ስትመራ የነበረችውን ደቡብ አፍሪካን በልጣ ከአፍሪካ ቁጥር አንድ እና ከዓለም ሃያ ስድስተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ እንደተባለችና ናይጄሪያ በዋጋ ክለሳው ምክንያት በቅጽበት የጨመረችው ሁለት መቶ አርባ ቢልዮን ዶላር ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ብቻ እንኳን የኢትዮጵያን የዓመት ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ሰባ ቢልዮን ዶላር ሦስት እጥፍ ያህል እንደሆነ ከዚህ ቀደም እንደ ምሳሌ አንስተናል፡፡ በባለሙያዎቹ ስሌት ቁጥር ቢቆለልም የሕዝብን ኑሮ አይለውጥም፡፡

የኢኮኖሚ ዕድገት መለኪያዎች በአገራችንም ሆነ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ማከራከራቸውም አልቀረም፡፡ የኖቤል ተሸላሚው ኢኮኖሚስት ጆሴፍ ስቲግሊዝ እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክሪስቲና ላጋርድን ጨምሮ ሌሎችም ዓለም ዐቀፍ ምሁራን ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ሁነኛ የዕድገት መለኪያ አለመሆኑን ይገምታሉ፡፡ ኢኮኖሚው ምን ያህል አድጓል ከሚለው ክርክር ጋር አብሮ የሚነሳው ጉዳይ በምንም ያህል ይደግ ለሕዝቦች ፍትሐዊ ክፍፍልስ አለ ወይ? የሚል ጥያቄ ነው፡፡ ስለ ሀብት ክፍፍል ፍትሐዊነት የተለያዩ ሥርዓተ ኢኮኖሚዎች ተፎካክረዋል፡፡

ፍትሐዊ ሥርዓት ተብሎ ለሰባ ዓመታት ስሙ ገኖ በነበረው በሶሻሊዝምም ጥቂቶች የአገሬውን ሀብት ወደ መንግስት ይዞታነት አዙረው እንደፈለጋቸው ሲያዙበት ለራሳቸው መዝናኛ ሥፍራዎችን ሲገነቡ የአብዛኛው ሕዝብ የኑሮ ደረጃ ከካፒታሊስት አገራትም አንሶ ሥርዓቱ ደጋፊ አጥቶ ለመክሰም በቃ፡፡

ልማታዊ መንግሥታትም ከሶሻሊዝምና ከካፒታሊዝም የሚለዩት በደረጃ ብቻ ነው፡፡ የግል ኢኮኖሚን እና የመንግሥት ኢኮኖሚን በመቀየጥ ደረጃ ከገበያ ኢኮኖሚውም ከሶሻሊስት ኢኮኖሚውም ቢለዩም ወይም የሁለቱን ዲቃላ ቅይጥ ቢመስሉም ውድድር በጎደለው የዋጋ ንረት በገበያ ነጋዴዎች ብዝበዛ እና ራሳቸው ሳይለሙ ሌላውን አልሚ በሆኑ በአፋቸው ብቻ እንጂ በእጃቸው የማይሠሩ ሹመኞች ሕዝቡ ለድርብ ብዝበዛ ተጋልጧል፡፡

ምን ይሻላል?

መወያየት መልካም ነው፡፡ እስኪ እንወያይ …

የፈርጣጩ ነገር – ሳምሶን ገነነ

 

አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት በሰው በላው ህውሃት ኢህዲግ አገዛዝ ከማሳለፉ ጋር በተያያዘ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ፣ ፍትህ ስርአት እጦት ባሻገር ያጣችው ነገር ቢኖር የህዝብን ብሶት በአደባባይ የሚናገር የአደባባይ ሰው ነው። በሃገራችን እንደ ፕ/ሮ መስፍን ወ/ማርያም ፣ዶ/ር መራራ ጉዲና ፣ ቄስ ጉደታ ወዘተ ያሉ የአደባባይ የህዝብ ተቆርቁዋሪዎችን ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ውሰጥ ብናይም እንደ ልደቱ አያሌው አይነት በህዝብ ድምጽ የሚያታልሉ በወጣት ላብ ላይ በርበሬ የሚነሰንስ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደሞ ኧንደ ፈርጣጩ ሀይሌ ገብረስላሴ አይነት ራስ ወዳድ ግለሰብ ሀገራችን አፍርታለች።

ሩዋጩ ሀይሌ ገብረስላሴ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነቱን የሚያሳዩ ምን አገባኝ እና በህዝብ ቁስል እንጨት ስደድበት አይነት አስተያየት በአደባባይ በማን አለብኝነት ሲናገር እና ሲለፈልፍ ይደመጣል። በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 2002 አ.ም ናዝሬት በተካሄደው የህውሀት ኢህአዲግ መደበኛ ስብሰባ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊን ፊት ለፊት እያየ ስለ እድገት እና ትራንስፎርሜኑ ኧቅድ ወርቃማነት እና ተአምራዊነት በመናገር ለአራጁ ስርአት ተቆርቋሪነቱን በአደባባይ በመግለጽ ሀ ብሎ የጀመረው አትሌት ሀ/ገብረሰላሴ በህዝብ ቁስል እንጨት መስደዱን ቀጥሎበታል።

ፈርጣጩ አንዴ “ዲሞክራሲ ለአፍሪካ ህዝብ ቅንጦት” ነው ሲል ሲቀጥል ደሞ የወጣቱን የፍትህ ፣ የኧኩለነት ጠያቄ የግብጽ ኧጅ አለበት ሲል አሁን ደሞ የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመጀመሪያ ስራ የማህበራዊ ሚዲያዎቸን ማዘጋት ነው አይነት መልክ ያለው ንግግሩን ኧያሰማን ይገኛል።

አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ኧንዲል ያገሬ ሰው፣ ዲሞክራሲ በሰፈነባቸው የማእራብ አውሮፓ ኧና የሰሜን አሜሪካ ሃገራት ሮጦ ያካበተውን ሃብት ምንጩ ዲሞክራሲያዊ ስረአት መሆኑን ዘንግቶ ዲምክራሲ ስር አት ለአፍሪካ ቅንጦት ነው ብሎ መናገር በኧኔ ኧምነት የ አ ኧምሮውን የማሰብ አቅም ከማመላከት ባለፈ ፈርጣጩ ምን ያህል ከህዝብ ኧና ከሃገር ጥቅም ይልቅ ለግል ጥቅሙ ቅድሚያ አንደሚሰጥ የሚያመላክት ይመስለኛል።

መሰረታዊ ከሆኑት የሰው ልጆች መብቶች ውስጥ ያለገድብ የመናገር ኧና የመጻፍ መብት ይገኙበታል። ይህ መብት በዋነኝነት የሌላውን ሰው መብት ባልነካ መልኩ ያለ ገደብ የመናገር ኧና የመጻፍ መብትን ማኧከል ያደረገ ነው። ለዚህ ክቡር ለሆነው የሰው ልጆች መብት መከበር በመላው አለም ከማርቲን ሉተር ኪንግ ኧስከ በአሉ ግርማ ድረስ መስዋትነት ከፍለውበታል። በሌላ በኩል ግን ራጭ ሃይሌ ገብረ ስላሴ ይህንን መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት ነው ኧንግዲህ ይገደብ ኧያለ ያለው።

ኧንደ ኧኔ ኧምነት አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ የህዝብን ብሶት ወደ ጎን በመተው የብዙሃኑ ህዝብ ቁስል ላይ ኧንዲህ ኧንጭት ኧየሰደደ የሚገኘው በሁለት ምክንያት ነው። አንደኛው የኧውቀት ማነስ ሲሆን ሌላኛው ደሞ ከልክ ያለፈ ኧራስ ወዳድነቱ ነው።
ኧኔ ኧስከማውቀው ድረስ ከሩጫ የሚገኘው ብር ኧንጂ ኧውቀት አይደለም። ነገር ግን ከሩጫ በሚገኘው ብር ኧራስን በኧውቀት ማጎልበት ይቻል ይሆናል። ከሁሉም ባለፈ ደሞ ኧራስን በኧውቀት ለማጎልበት ቅን ልቦና ያስፈልጋል። ስግብግብነት የሞላው ልብ ደሞ ለቅንነት በጣም ኧሩቅ ነው።

በኧኔ ኧምነት በሃገራችን ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት በህወሃት-ኢህአዴግ ስርወ መንግስት የሃገራችን ሃብት በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን ሲዘረፍ ከርማል። የቀድሞው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴታ የነበረው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ” የመለስ ቱርፋቶች” በሚለው መጽሃፍ ኧንደገለጸልን በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት በህዝብ ድምጽ ተሸንፎ ስልጣን ማስረከብ ከነበረበት የ አቶ አርከበ ኧቁባይ ካቢኔ ላይ አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ ከ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በህገወጥ መንገድ ወስዳል። ይህም በኧኔ ኧምነት አትሌቱ ሲሮጥ ሲሮጥ የኢትዮጲያ ወዳጅ፣ ሲነግድ ግን ኢትዮጲያን ሽፍቶች ጎን በመቆም በህዝብ ቁስል ኧንጭት የሚሰድ ኧራስ ወዳድ ግለሰብ ስለምሆኑ ነው።

የተዓቅቦ ጥሪ የወያኔ ሕገ ወጥ የንግድ ተቋም በሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ እና ግብረአበሮቹ ላይ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው )

/**/

እንደምታውቁት ፋና ብሮድካስቲንግ (ስርጭት) በመባል የሚታወቀው የራዲዮና የቴሌቪዥን (የነጋሪተወግና የምርዓየ ኩነት) ጣቢያ ከወያኔ የንግድ ተቋማት አንዱ ነው፡፡ ፋና ብሮድካስቲንግ (ስርጭት) እየሠራ ያለው በሕገ ወጥ መንገድ ነው፡፡ ፋና ራዲዮንና ቴሌቪዥንን (ነጋሪተ ወግንና ምርዓየ ኩነትን) ሕገ ወጥ የሚያደርገው ወያኔ ሥልጣን እንደያዘ ያወጣውና ሀገሪቱን አሥተዳድርበታለሁ በሚለው ሕግ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች (የእምነተ አሥተዳደር ድርጅቶች) የኤሌክትሮኒክ ሚዲያን (ነርኸላዊ የብዙኃን መገናኛን) እና የንግድ ተቋማትን ማቋቋምና ማንቀሳቀስ እንደማይችል ስለደነገገ ነው፡፡

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ያው እንደምታውቁት ወያኔ ሕግ ሲያወጣ ሌላውን ሊቀፈድድበት እንጅ ለአንድም ቀን ቢሆን እራሱ ላወጣቸው ሕጎች ተገዝቶበትና አክብሮት አያውቅምና ይሄንንም ሕግ ተላልፎ አስቀድሞ ፋና ራዲዮ የሚባለውን ጣቢያ የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት ከጨመረ በኋላ ደግሞ ፋና ብሮድካስቲንግ በሚል ሥያሜ እየተገለገለበት ይገኛል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ (ስርጭት) በቅርቡ የከፈተው የቴሌቪዥን (የምርዓየ ኩነት) ስርጭት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ “ጅብን ሲወጉ በአህያ ተጠግተው ነው!” እንዲሉ ፋና ጥቂት አንጋፋና ተዋቂ ከያኔያንን (ተዋንያንን፣ ዘፋኞችን፣ ገጣምያንን፣ ደራስያንን፣ ጸሐፍያንን ወዘተረፈ.) በመጠቀም ራሱ ጣቢያው ትኩረት ይስብልኛል፣ ተወዳጅነትን ያስገኝልኛል ብሎ የቀመረላቸውን የቀረጸላቸውን ዝግጅቶቻቸውን የሚያቀርቡባቸውን የአየር ሰዓት በመመደብ ወደ ሕዝብ ለመቅረብ፣ ተመልካች ለማፍራት፣ ተቀባይነት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሁንና ጣቢያው ለቀረጻቸው ዝግጅቶችና ላስጻፋቸው ተከታታይ ድራማዎች (ትውንተ ኩነቶች) በፈለገው መጠን ብቃትና ጥራት ለማሠራት ብዛትና ብቃት ያላቸውን ከዋኞች ማግኘት ስላልቻለ በአብዛኛው በሥራቸው ያልተሳካላቸውንና ማንም ሊያገኛቸው የሚችላቸውን ጀማሪ የኪነት ሰዎችን ለማካተት ተገዶ ከንነሱ ጋር እየሠራ ይገኛል፡፡

ፋና ስርጭት የቴሌቪዥን (የምርዓየ ኩነት) አገለግሎትንም የከፈተው ለሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች ነው፡፡ አንደኛው ፋና ራዲዮ (ነጋሪተ ወግ) ለዘመናት ሲያደርገው እንደኖረው ሁሉ የሆነውን እንዳልሆነ ያልሆነውን እንደሆነ እያደረገ በመንዛት የወያኔን የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አሁንም ፋና ራዲዮ ለዘመናት ሲያደርገው እንደኖረው ሁሉ የወያኔን የትግሮችንና የአጋር ባለሀብቶችን ሁሉን አቀፍ የተሳሰረ የቢዝነስ ኢምፓየር (የንግድ ግዛት) በበለጠ ደረጃ ስኬታማ ለማድረግ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ይህ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንደምታዩት፦

1ኛ. ሬዲዮ ፋና ሲያደርገው እንደኖረው ሁሉ ወያኔ ላለበት የፖለቲካ ቀውስ ሕዝብን የመደለያና የማታለያ፣ ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ (ልፈፋ) መንዣና ቀውስ መቆጣጠሪያ በመሆን፣ ወያኔ ጠላቴ የሚለውን አካል መውጊያ፣ ስም ማጥፊያና ቅስም መሥበሪያ በመሆን፡፡

2ኛ. ገና ከመጀመሩ የወያኔን፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናትን፣ የትግሮችንና የጥቂት አጋር ባለሀብቶችን የንግድና የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን በተለያዩ ዝግጅቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ አገልግሎታቸውንና ሸቀጦቻቸውን እያጋነኑ በማስተዋወቅ ለድርጅቶቹ ሽፋን በመስጠት የገበያው አቅጣጫ ወደእነሱ እንዲያመራ የተጠናና የታሰበበት ሥራ መሥሪያ በመሆን በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡

ይታያቹህ! እነኝህ የወያኔ፣ የትግሬና የአጋር ባለሀብቶች የንግድና የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች አብዛኞቹ ቀረጥና ግብር ሳይከፍሉ የሚነግዱና አግባብ ያልሆነ ሕገወጥ ጥቅም የሚያግበሰብሱ ከመሆናቸው በተጨማሪ እነኝህ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ጥራት ያለው አገልግሎታቸው የብዙኃን መገናኛን ትኩረት የሳበ ባስመሰለ አቀራረብ እንዲያ ባሉ ዝግጅቶች ሽፋን በመስጠት ገበያውን ጠቅልለው እንዲወስዱት በብዙኃን መገናኛዎቻቸው ሲታገዙ የቆዩ በመሆናቸው የንግዱ ማኅበረሰብ ከነሱ ጋር ፈጽሞ መፎካከር ስላልቻለ ብዙኃኑ የንግድ ማኅበረሰብ በከባድ ኪሳራ ከገበያ ውጭ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት አጠቃላዩ የንግዱ እንቅስቃሴ በትግሬ ተጠቅልሎ እየተያዘ ይገኛል፡፡

እንግዲህ ይታያቹህ እንዲህ ዓይነት ሸፍጥና ሴራ በሕዝብ ላይ እየፈጸመ የወያኔ ዘረኛ አንባገናዊ አገዛዝን ዕድሜ ለማራዘም፣ ሀብት ሁሉ በትግሬ በሞኖፖሊ (አጠቃሎ መያዝ) ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ ተግቶ ለሚሠራ የወያኔ የብዙኃን መገናኛ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ እነኝህን ሸፍጠኛ ተግባሮቹን በብቃት መሥራት እንዲችል ለሱ መጠቀሚያ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስቡት!!!

ፋና የማንና ምን እንደሚሠራ ጠንቅቀው እያወቁ በቀረበላቸው አማላይ ጥቅም ተደልድለው ሀገርንና ሕዝብን በመካድ እያደረጉት ባለው መልኩ ወያኔን እየተባበሩና እያገለገሉ ካሉ አንጋፋ ከያኔያን ውስጥ አቶ ደበበ እሸቱ፣ አቶ ፈቃዱ ተክለማርያም፣ አቶ ተፈሪ ዓለሙ፣ ወ/ሮ ዓለምፀሐይ በቀለ ይገኙበታል፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ አቶ ደበበ እሸቱ ይመስለኛል ድለላውን የሠራው ዓለም ፀሐይ ወዳጆ የቀድሞ የጥላሁን ጉግሳ ባለቤት ወ/ሮ ሔለንና ሌሎች ሦስት ሴቶች በሚያዘጋጁት ወርቃማ ሴቶች ለተሰኘ ዝግጅት ተባባሪ አዘጋጅ ሆና ልትሠራ ነው፡፡

ከወጣቶቹ ደግሞ አቶ ዓለማየሁ ታደሰ፣ ወ/ሮ አዜብ ወርቁ፣ አቶ ሚካኤል ታምሪ፣ አቶ ሰኢድ ሙሔ ይገኙበታል፡፡ ከጀማሪዎቹ ውስጥ ደግሞ ዳሸን ቢራ በሕዝብ በመጠላቱ ስሙን ለመቀያየር ተገዶ ማስታወቂያ የሚሠራለት ዘፋኝ ባጣ ጊዜ ማስታወቂያ የሠራለት የጃኖ ባንዱ ዘፋኝ ዲበኩሉ ታፈሰ፣ በቅርቡ የሙዚቃ አልበሙን (የዘፈን ጥራዙን) የለቀቀው መሳይ ተፈራ ይገኙበታል፡፡

ስለእውነት ነው የምላቹህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ ለመውጣት ከወያኔ ጋር ጉርቦ ለጉርቦ ተናንቆ እየታገለና መራራ መሥዋዕትነትን እየከፈለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሕዝቡ በወያኔ የንግድ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጥሎ እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ፣ ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን ያለመጠቀም ያለመገብየት ተዓቅቦ አድርጎ ብዙዎቹን ኪሳራ ላይ በመጣል ድል እያስመዘገበና ወያኔን እያንበረከከ ባለበት በዚህ ሰዓት እነኝህ አንጋፋ ከያኔያንና ታዋቂ ሰዎች የግል ጥቅማቸውን ብቻ በማሰብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ በመቆም የወያኔ ቅጥረኛና መጠቀሚያ ሆነው የፋና ሥርጭት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝና ወያኔ የራሱን ጥቅም ማስጠበቅ እንዲችል በሙሉ ፈቃደኝነትና በጋለ ስሜት እየረዱት እየተባበሩት እንደሆነ ሳይ እውነቴን ነው የምላቹህ እጅግ በጣም ነው ሐዘን የተሰማኝ የከፋኝም፡፡

“እንዴት በዚህ ጊዜ እነኝህ ሰዎች እንደዜጋ በቻሉት መጠን ሕዝባዊ ትግሉን ማገዝ ሲኖርባቸው እንዴት በሚቃረን መልኩ የወያኔ ተባባሪው ሊሆኑ ቻሉ?” የሚለው ጥያቄም፦

* ግን እነኝህ ሰዎች በትክክልስ ማሰብ ይችላሉ ወይ???

* ላከበራቸውና ለዚህ ደረጃ ላበቃቸው ሕዝብስ ክብር አላቸው ወይ???

* እነኝህ ግለሰቦች ይሄንን እያደረጉ እንዴት ነው ሀገርንና ሕዝብን እንደሚወዱ የሚናገሩትን ነገር ሕዝቡ እውነት አድርጎ እንዲያስብላቸው የሚጠብቁት???

* ለሕዝብ ክብር ቢኖራቸውና ዘወትር እንደሚሸነግሉን ሀብታቸው ሕዝብ እንደሆነ ቢያምኑ ኖሮ፣ ቢወዱት ኖሮ ከጠላቱ ከገዳዩ ጋር ተሰልፈው ለጠላቱ ለገዳዩ ስኬት ተግተው በመሥራት ሕዝብን ከጀርባው ይወጉት ነበረ ወይ???

* ከሕዝብ ጠላት ጋር ተሰልፈው ለሕዝብ ጠላት እየሠሩ እንዴት ነው የሕዝብ ጠበቃነት፣ የእውነት መስካሪነት፣ የሕዝብ ብሶት መተንፈሻ መሣሪያ የሆነን የተከበረ ሞያ ባለቤት ነን ብለው “የከያኔ ነፍስ አለን ከያኔያን ነን!” ሊሉ የሚችሉት???

* ሕዝብ ስለወደደና ስላከበረ በዚህ ደረጃ መናቅ፣ መካድ ነበረበት ወይ???

* ካልናቁት በስተቀር እንዴት ነው በሕገወጥነቱ መዘጋት ላለበት ለወያኔ የንግድ ተቋማት መልማትና መደርጀት በመሥራት በሕዝብና በሀገር ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚጥሩት??? አሰኝቶኛል፡፡ ግን በእርግጥስ እነኝህ ሰዎች ይሄንን ሁሉ ነገር ማሰብ ማገናዘብ አለመቻላቸው ምንን ያመለክታል???

እነኝህና ሌሎቹ ያልተጠቀሱ ግለሰቦች የጥፋት ኃይል የሆነውን ወያኔን በዚህ መልኩ ሲያገለግሉ ሀገርንና ሕዝብን እየወጉ እያደሙ በመሆናቸው በግል የቱንም ያህል አማላይ ክፍያ ቢከፈላቸው እንኳ በምንም ተአምር ቢሆን ተጠቃሚ አለመሆናቸውን መገንዘብ የሚያስችል ንቃተ ሕሊናና ማስተዋል ስለሌላቸው ነው ለፍርፋሪ ብለው የሀገርንና የሕዝብን ጠላት እያገለገሉ መጠቀሚያ ሆነው የሚገኙት፡፡ እንዲያው ግን ሀገርንና ሕዝብን ማሰብ ባይችሉ እንኳ እንዴት ለስማቸውና ለግል ታሪካቸው አይጨነቁም??? ስንት ዓመትስ ሊኖሩ ነው ባለቀ ሰዓት የሚያልከሰክሳቸው???

እባካቹህ እነኝህን አንጋፋና ታዋቂ ከያኔያንን ማለትም በፋና ቴሌቪዥን በሚተላለፉና በፋና ወጪ በተዘጋጁ ተከታታይ ድራማዎች (ትውንተ ኩነቶች) ፣ የተለያዩ የፋና ዝግጅቶች አዘጋጅ የሆኑ ታዋቂ ሰዎች፣ በተለያዩ የፋና ውይይቶች የሚሳተፉ ምንም የማይገባቸውና የማይነቁ ፖለቲከኛ (እምነተ አሥተዳደራዊ) ነኝ ባዮችና ታዋቂ ሰዎች ለፋና በመሥራትና በፋና ዝግጅቶች በመቅረብ ፦

* መጠቀሚያ መሆናቸውንና የሕዝብን ትግል እየተቃረኑ፣ ለሕዝባዊ ትግሉ እንቅፋት እንደሆኑ እየነገራቹህ ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ንገሩ፣ ምከሩ፣ አስጠንቅቁ???

* ለሕዝብና ለሀገር ጠላት ሆነው እየሠሩ መሆኑን እንዲያውቁ እንዲረዱ እንዲገነዘቡ አድርጓቸው???

* የማይታረሙ፣ የማይታቀቡ፣ የሕዝብን ምክር መረዳት መቀበል የማይፈልጉ ከሆኑ እኛም በስውር የያዙትን ካድሬነት (ወስዋሽነት) በይፋ ለማስታወቅ እንደፈለጉ ቆጥረን ወያኔን በምናይበት ዐይን እንደምናያቸውና በሥራዎቻቸው ላይ ማዕቀብና ተዓቅቦ እንደምንጥልባቸው፣ ከጠላታችን ከወያኔ ጋር ተባብረውብናልና ከወያኔ ጋር ደርበን እንደምናጠቃቸው ወይም እርምጃ እንደምንወስድባቸው፣ ወያኔ የሚከፍለውን ዋጋ ለመክፈል የሚገደዱ መሆናቸውን ንገሯቸው፣ አስጠንቅቋቸው??? ቀልድ የለም!!! ሕዝብ እየሞተና መራራ ዋጋ እየከፈለ ነው ያለው፡፡ ከወያኔ ጋር ተሰልፎ ሕዝብንና ሀገርን ለሚወጋ ባንዳ ቅጥረኛ ሁሉ ምንም ዓይነት ምሕረት ሊኖረን አይገባም!

ከሕዝቡ በኩልም ፋና ቴሌቪዥንንና ሬዲዮን ባለመመልከትና ባለማዳመጥ፣ ከዚህም በላይ የወያኔና የትግሬ የንግድና የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን ባለመጠቀም ወይም ተዓቅቦ በማድረግ፣ በፋና የሚተዋወቁ የንግድ ድርጅቶች ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ባለመጠቀም ባለመገበያየት፣ ነጻ የንግድ ድርጅቶችም በፋና ማስታወቂያን ባለማስነገር ለወያኔ ሕገወጥ የብዙኃን መገናኛና የንግድ ድርጅቶች ያለንን ተቃውሞ እንግለጥ፣ ሕዝባዊ ትግሉንም ልድል እናብቃ!!! ተዓቅቦው እንደአስፈላጊነቱ ኢቴቪንም ይመለከታል፡፡

በዚህ አጋጣሚ እንዳለኝ መረጃ ፋና በጥቅማጥቅም በመደለል የአየር ሰዓት ወስዳቹህ አብራቹህት እንድትሠሩ ሲጠይቃቹህ፣ በዝግጅቶቹ በእንግድነት እንድትቀርቡ ሲጠይቃቹህ የወያኔ መጠቀሚያ ላለመሆን፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ ላለመቆምና የሕዝብ ጠላት ላለመሆን “ጥቅሙ በአፍንጫዬ ይውጣ!” ብላቹህ የተለያየ ምክንያት በመስጠት ጥያቄውን ያልተቀበላቹህ ከያኔያን፣ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች አድናቆቴን መግለጥና ማመስገን እወዳለሁ ጀግኖች ናቹህ! ተባረኩ! ያጽናቹህም!!!

የእነኝህ ጀግና ከያኔያን ፈቃደኛ አለመሆን ነው ፋና ያገኘውን ሁሉ እንዲሰበስብ ያደረገው፡፡ ምሳሌ ብጠቅስ ፋና ለአንድ ኮሜዲያን (አሳቂ) ነኝ ለሚልና ሁሌም ሥራውን ሲያቀርብ ለሕፃናት የሚያቀርብ ለሚመስለው ደረጀ “ጥበብ በፋና!” የሚል አቅሙ የማይፈቅድለትን ዝግጅት አሸክመውት ዝግጅቱን እንዲመራ በጋባዥነት (በሆስትነት) ሠይመውታል፡፡ ይገርማቹሀል እኔ በግሌ ይሄ ሰው ቀልድ ብሎ በሚያቀርባቸው ነገሮች በስሕተት ለአንድ ጊዜም እንኳ አስቆኝ አያውቅም፡፡ እናም ኃላፊነት የሚሰማቸው ከያኔያን፣ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች እምቢታ ፋናን እንዲህ እንዲህ ዓይነቶችን ያልተሳካላቸውንና አቅም የሌላቸውን ሰዎች በአዘጋጅነት እንዲሁም ጀማሪ ዘፋኞችን በተዋናይነት እንዲያካትት አስገድዶታል፡፡

የተዓቅቦ (boycott) እርምጃ ከወያኔ ጋር የተያያዝነውን የሞት ሽረት ትግል በድል ለማጠናቀቅ ቁርጠኝነትን እንጅ ምንም ዓይነት ወጭንና የደም መሥዋዕትነትን የማይጠይቅ ለድል የሚያበቃ ዓይነተኛ መሣሪያ ነው፡፡ ሲቻል ደግሞ የማዕቀብ (sanction) እርምጃም እንዲሁ አስፈላጊና ጠቃሚም ነው፡፡ እናም በደንብ ልንጠቀምበት ይገባልና እባካቹህ በዚህ ላይ እንረባረብ ተግተን እንሥራበት??? ሕዝባችን ተዓቅቦን የሚያክል ትልቅ መሣሪያ እንዲጠቀምበት እናንቃው???

ተሿሚው ጠ/ሚ ለይስሙላም ቢሆን እስከአሁን ስንቱን ነገር ሲወሸክት ሀገር እየበዘበዙ፣ እየዘረፉ፣ እያራቆቱ ስላሉት ኤፈርትና ሌሎች ሕገወጥ የወያኔ የንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ስለዚህ ስለ ፋና እና ድምፀ ወያኔ የመሳሰሉ ሕገወጥ የብዙኃን መገናኛዎች አንድም ያለው ነገር የለም! ይኖራል ብለንም አንጠብቅም፡፡ ዐቢይ በእነዚህ ሕገወጥ ድርጅቶች ጉዳይ ላይ ምንም ነገር ማለት ካለመፈለጉና እርምጃም መውሰድ ካለመፈለጉ መረዳት የምንችለው ዐቢይ ቁምነገር ቢኖር ዐቢይ “እንዲህ እንዲሆን ይደረጋል!….፣ ጽኑ እምነት አለን!…” እያለ የሚደሰኩረው ነገር ሁሉ ባዶ ፉገራ መሆኑን ነው ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው፡፡

በወያኔ ሕገወጥ የብዙኃን መገናኛ እና ሕገወጥ የንግድ ድርጅቶች ተዓቅቦ እና ማዕቀብ እናጧጡፍ!!! አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወያኔን በቀላሉ ማንበርከክ የምንችልበት ታላቅ መሣሪያችን ይሄና ይሄ ብቻ ነውና እባካቹህን አንድ ኢትዮጵያዊ ሳይቀር እዚህ ላይ እንረባረብ!!! ያለጥርጥር አሸናፊዎች እንሆናለን!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

ትግሬ ያልወደደው ወንበሩ አይረጋለትም አይነት አካሄድ ይዘው የአማራውን አይን መውጋት መዘዝ አለው !

/**/

መስከረም አበራ

ትናንት አቶ አታላይ ዛፌ በቪኦኤ ቀርበው በርቱዕ አንደበት የወልቃይትን ጉዳይ አስቀምጠዋል፨ ነገሩ ከአብይ አቅም በላይ እንደሆነ እግዜርም ሴጣንም ያውቃሉ፨ ሆኖም ዶ/ር አብይ ከአቅማቸው በላይ የሆነን ነገር በማድበስበስ ባራድኛ ከልለው የተቀመጡበትን ወንበር የሚያዙበት ማስመሰላቸውን ማቆም አለባቸው፨

ጠሚው የተቀመጡበት ወንበር የእውነት ነው ካሉ፣ አፋቸው የሚያወራው ልባቸው ያሰበውን ከሆነ፣ በምላሳቸው ላይ ጠበንጃ የያዘ ዘበኛ ከሌለ ደግሞ የወልቃይትን ጉዳይ ማንሳት ያለባቸው ወልቃይት የእኔ ነው የሚሉትን ሁለቱንም አካላት ሰብስበው መሆን አለበት፨ እንጅ ትግሬ ያልወደደው ወንበሩ አይረጋለትም አይነት አካሄድ ይዘው የአማራውን አይን መውጋት መዘዝ አለው! በአማራው ላይ መሳለቅ ከመለስ ጋር ተቀብሯል!

ለሰው ሁለተኛ እድል በመስጠት አምናለሁ በግሌ፤ ለሁለተኛው እንዲህ ባለ መውጫ በሌለው ስህተት ውስጥ ከመቦራጨቃቸው በፊት አሰብ ማድረጉ አይከፋም፨ ካልሆነም አለቆቻቸው በሚዘውሩት አጀንዳ ላይ ፖርላማ ቀርተው ቅዝምዝምን ባሳለፉበት ስታይል ዝም ብሎ ማሳለፍ ይሻላል – ከንግግር ብዛት ስህተት አይጠፋም እንዲል መፅሃፍ !

“ጥያቄያችን የማንነት ነው”- አቶ አታላይ ዛፌ

http://www.satenaw.com/amharic/archives/54892/embed#?secret=KYbCVffN7M