ደህንነቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በ24 ሰዓታት ውስጥ ከሃገር ለማስወጣት ቢዘጋጅም ዶ/ር ዓብይ ይህን ማስቆማቸው ተገለጸ | አንዳርጋቸውን ጥየቃ የአባቱ ቤት ዛሬም ተጨናንቋል

 

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ከ እስር ቤት ተፈትተው በአባታቸው ቤት ያልጠበቁት የሕዝብ አቀባበል የተደረገላቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከቤተሰብም ከደጋፊዎቻቸውም ጋር ሳይገናኙ በ24 ሰዓታት ውስጥ ደህነንቱ ከሃገር ሊያስወጣቸው ሲል ያስቆሙት ዶ/ር ዓብይ አህመድ መሆናቸው ተነገረ::

በደህነቱ ውሳኔ ውስጥ ጣልቃ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገ መቆየት እንደሚችል ማረጋገጫ ለቤተሰቡና ለ እንግሊዝ መንግስት እንደሰጠ ታውቋል::

በሃገር ውስጥ ሲቆይም የአንዳርጋቸው ደህንነት እንዲጠበቅ መንግስታቸው እንደሚሰራ ለ እንግሊዝ መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በኩል ማረጋገጫ እንደሰጡ ነው የተዘገበው::

የአቶ አንዳርጋቸው መለቀቅ ጉዳይ የህወሓት ተከፋይ ብሎገሮችን እጅጉን እያንገበገበ መሆኑ እየታየ ነው:: ዳን ኤል ብርሃኔ የተባለው የሕወሃት ብሎገር አንዳርጋቸው  በቀጥታ አለመሸኘቱ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያለውን ትርምስ የሚያሳይ ነው ሲል በአደባባይ ጽፏል::  አንዳርጋቸው ጽጌ ካለ ቭዛ ሃገር ውስጥ ያለ የውጭ ሃገር ዜጋ በመሆኑ ወዲያውኑ ዲፖርት ሊደረግ የገባው ነበር በሚል ተቃውሞውን አሰምቷል:: ትግራይ ኦላይን የተባለው ድረገጽም የአንዳርጋቸው ጽጌን መፈታት ኮንኖ ጽፏል::

በሌላ ዜና አዲስ አበባ ከጌቱ ኮመርሽያል ሴንተር ጀርባ (በኦሮሚያ ኢንተርናሽል ባንክ ጎን ባለው የውስጥ መንገድ) ቀጥታ ተሄዶ በሚገኘው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ቤት ሕዝብ ዛሬም እየጎረፈ መሆኑ ታውቋል:: ከአዲስ አበባ መረጃውን ያደረሱን ወገኖች እንደነገሩን “እንኳን ተፈታህ, ጀግናችን ነህ” የሚሉ ሰዎች አንዳርጋቸው ቤት በመምጣት ደስታቸውን ሲገልጹ ውለዋል::

አንዳርጋቸው አሁንም ለምን ያህል ጊዜ ኢትዮጵያ እንደሚቆይ ባታወቅም በትናንትናው ዕለት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ደስታቸውን ተሰብስበው ሲገልጹ አምሽተዋል:: በዋሽንተን ዲሲ, በቴክሳስ, በካሊፎርኒያ, በ እንግሊዝ, በስዊድን, በስዊዘርላንድ, በኖርዌይ, በደቡብ አፍሪካ እና በተለያዩ ከተሞች ሕዝብ በአጭር ጊዜ በመሰባሰብ ደስታውን ሲገልጽ ያመሸ ሲሆን በተለይ በካናዳ ቶርንቶ ከተማ ሕዝቡ በመኪና ተጭኖ በአደባባይ እየተዟዟረ ደስታው ሲገልጽ እንዳመሸ ብርሃን ቲቭ ከስፍራው በምስል አስደግፎ ካሰራጨው መረጃ ለመረዳት ተችሏል::

የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገለጹ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር በመለቀቃቸው የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን እንዳሉት የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለእንግሊዝ መንግስት ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ ከእስር ለማስፈታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። እናም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከረጅም እስር በኋላ ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መገናኘቱ ለእንግሊዝ መንግስት ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል። በአንዳርጋቸው ጽጌ መለቀቅ በርካታ ሰዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከየመን ታፍነው በኢትዮጵያ ደህንነቶች ከተወሰዱ በኋላ የእንግሊዝ መንግስት የእስር ርምጃውን በማውገዝ ከኢትዮጵያው አገዛዝ ጋር ሲወዛገብ ቆይቷል። በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች ኢትዮጵያ በመጡ ቁጥር ቀዳሚ አጀንዳቸው በማድረግ ከሀገሪቱ አገዛዙ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል፣ከፍተኛ ጫና ለማድረግም ሞክረዋል።

በኢትዮጵያ አገዛዝ ባላስልጣናት በኩል ግን የሕዝብ ተቃውሞ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ ጉዳዩን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ነው የቆዩት። እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ በመቀነስም ማድረግ የምትችለውን  ጥረት ሁሉ ማድረጓም ነው የሚታወቀው።

ሪፕሪቭ የተባለው የእንግሊዝ የሲቪክ ተቋምና የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች እንዲሁም የሃገሪቱ የተወሰኑ ዜጎች የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ በቂ ግፊት አላደረገም በሚል ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር።

ጉዳዩ እየተጠናከረ ሲመጣም እንግሊዝ ከ2 ጊዜ በላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን እስከመላክም ደርሳለች። ይህ ሁሉ ሆን በመጨረሻ የሕዝቡ ተቃውሞ ገፍቶ የፖለቲካ እስረኞች መለቀቅ ከጀመሩ በኋላ አቶ አንዳርጋቸው የመለቀቅ ተስፋ ይኖራቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ ቆይቷል።

እንደተገመተውም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ተለቀው ከቤተሰባቸው ጋር ለመገናኘት በመብቃታቸው የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸዋል። እናም የኢትዮጵያ መንግስት የጀመረውን የለውጥ ሒደት መነሻ በማድረግ አቶ አንዳርጋቸውን መልቀቁ የሚያበረታታ ርምጃ ነው ብለዋል።

አቶ አንዳርጋቸው ከእስር ባለመለቀቃቸው ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ መንግስት ልታገኝ የምትችለውን በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ማጣቷን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ መግለጻቸው ይታወሳል።

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010)

የኢሕአዴግ መንግሥታዊ ቅርጽና ኢኮኖሚ (ጌታቸው አስፋው)

ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በሁለተኛው ዓመት ባወጣው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዓላማዎችና ቀጣይ ተግባራት የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዞውን አመላከተ፡፡ በኢኮኖሚ አመራሩ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ናቸው ያላቸውንም ለየ፡፡ በድርጅቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ዓላማዎች ተጠቃሚ የሚሆኑና የማይሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች እነማ እንደሆኑ በመለየት በፖለቲካው ጭቁን ሕዝብና ጭቁን ያልሆነ ሕዝብ በማለት ሲከፋፍል በኢኮኖሚው መንገድም የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ኀይሎች እና ጥገኛ ካፒታሊስቶች ብሎ ከፋፈላቸው፡፡

የግል ንብረት ባልነበረበት የደርግ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዳተር ማግስት በጣት ይቆጠሩ የነበሩት የደርግ የፓርቲና የመንግሥት ሹማምንት እስር ቤት ከገቡ እና የጦር ኀይሉ ሙሉ በሙሉ ከተበተነ በኋላ፣ የተቀረውን ሕዝብ ጭቁንና ጭቁን ያልሆነ ብሎ በፖለቲካው ለመከፋፈልም ሆነ በኢኮኖሚው ጥገኛ ካፒታሊስት ተብሎ ሊጠራ የሚችል ማን እንደሆነ ለኢሕአዴግ ካልሆነ በቀር ለማንም ግልጽ አልነበረም፡፡ የመንግሥትነት ሥልጣን ከመጨበጤ በፊት በትግል ሜዳ ላይ ከጠላት የማረኳቸው የኢንዶውመንት ንብረቶቼ ናቸው ያላቸውን በበጎ አድራጎት ድርጅት ስም ተመዝግበው፣ ሕጋዊ አድርጎ ካቋቋመ በኋላ፣ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ኀይሎች አድርጎ በጋራና በተናጠል የግዙፍ መዋዕለንዋይ ባለቤት ድርጅቶች ሆነው ኢኮኖሚውን እንዲቆጣጠሩ አደረገ፡፡
የዴሞክራሲ ኀይሎች ከተባሉት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት ፓርቲው ያቋቋማቸው ከሕወሓት “ኤፈርት”፣ ከብአዴን “ጥረት”፣ ከኦሕዴድ “ዲንሾ” እና ከደኢሕዴን “ወንዶ” ሲሆኑ፣ በውስጣቸው በርካታ ማምረቻና አገልግሎት መስጫ ድርጅቶች ይገኙባቸዋል፡፡ በምርትና በአገልግሎት አሰጣጥ ንግድ ሥራ የመንግሥት ድርጅቶችንም ሆነ የግል ባለሀብቱን ድርሻ በልጠውና ተክተው ከሚሠሩ ከእነዚህ የፓርቲ ድርጅቶች ውስጥም ልቆ የሚገኘው የሕወሓቱ ኤፈርት ሲሆን ካሉት ወደ ዘጠና የሚጠጉ ድርጅቶች ካፒታል የዐሥራ አንዱ ብቻ ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ምን ያህል እንዳደገ ከአንድ የታተመ ጽሑፍ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሰባት መቶ ዘጠና ስምንት ሚልዮን ወደ ሐምሳ ሰባት ቢልዮን ብር አድጓል፡፡ ‹ኤፈርት› ለራሱ አድጎ በአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ ድርጅት ከመሆኑም ባሻገር በመንገድና በሕንጻ ተቋራጭነት ከባዶ አንስቶ የሰቀላቸው ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅቶችም በምርት በግንባታና በንግድ አገሪቱን ተቆጣጥረዋል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም የእነኚህን ድርጅቶች አነሳስ ስለሚያውቅ ሆድ ሆዱን እየበላው ይኖራል፡፡ ከብአዴንና ከሃያ አምስት መሥራች አባላት በተገኘ ሃያ ስድስት ሚልዮን ብር እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1987 የተመሠረተው “ጥረት” ዳሸን ቢራን ጨምሮ ዐሥራ ስምንት ኩባንያዎች እንዳሉት የሚታወቅ ሲሆን ይህ ጽሑፍ በሚጻፍበት ሰዓት የባሕር ዳርና ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅን ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች በሰባት መቶ ስልሳ አምስት ሚልዮን ብር ለመግዛት በዝግጅት ላይ ነበር፡፡

ከ1983 እስከ 1990ዎቹ መጨረሻዎች ድረስ ኢሕአዴግ አርሶ አደሩን እንደ ጭቁን በመቁጠር የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዋነኛ አጋር መደቡ አድርጎ ነበር በአንጻሩ የከተማው ሕዝብና የኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች ወዝአደሮች ጭቁን ያልሆኑ ተብለውና እንደ ጥገኛ ተቆጥረው ትኩረት አልተሰጣቸውም ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ የዓለም ባንክ፣ የዓለም ዐቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ የዓለም የንግድ ድርጅት ከኒዮ-ሊብራል ምዕራባውያን መንግሥታት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈጸም ዓለም በሙሉ በግል ገበያ ኢኮኖሚ እንዲመራና በኢኮኖሚው ውስጥ የመንግሥት ሚና እንዲቀንስ የዋሽንግተን መግባቢያ ስምምነትን ተፈራርመው በሁሉም አገሮች ለማስረጽ ሲንቀሳቀሱ ወደ ኢትዮጵያም ጎራ ብለው ነበር፡፡ ይህም ለኢሕአዴግ የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት የሆኑትን ድርጅቶች ለወዳጅ ዘመድ ከበርቴዎች ለማከፋፈል የሚያመቸው ንፋስ ያመጣው ዕድልና በረከት ነበር፡፡ በመዋቅር ማሻሻያ ፕሮግራም ስም በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1980 እና 90ዎቹ ዓመታት ብዙ ሰው ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶች አፈናቅለዋል፣ የመንግሥት ድርጅቶች ለግል እንዲሸጡ አድርገዋል፡፡ በሮቿን ለውጭ ሸቀጥ ክፍት እንድታደርግ መክረው በከፊል ተሳክቶላቸዋልም፡፡

የጋራ ንብረቱን ወደ ግል በማዞር እርምጃቸው በዐፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የተካበቱ የአገሪቱ ሀብቶችን ደርግ የሕዝብ አድርጓቸው ከዚያም በኋላ በዐሥራ ሰባት ዓመት የደርግ ዘመን የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ላብ የፈሰሰበትን አንጀታቸውን አስረው የቆጠቡትንና የጋራ ሀብቶቻችን ናቸው ያሏቸውን ማምረቻና አገልግሎት መስጫ ድርጅቶች ባንኮችና ኢንሹራንስ የመሳሰሉትን የገንዘብ ተቋማት ያለካሳ መንግስት ራሱ፣ ጥቂት ግለሰቦችና የታጋዮች ኢንዶውሜንት ናቸው የተባሉ ድርጅቶች ተቀራመቷቸው፡፡ በዚህ መልክ ነው እንግዲህ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ የላቡ ዋጋ የሆነውን ንብረቱን በመንግሥት ባለሥልጣናት ለግል ወይም ለፓርቲ ድርጅቶችና ለግለሰቦች የሕዝብ ንብረት ከነበረው ንግድ ባንክ በተወሰደ የማይከፈል ብድር ራሳቸው ገዢ ራሳቸው ሻጭ ሆነው የተነጠቀው፡፡ ይህ የምዝበራው ቁጥር አንድና ጅማሮ ነው፡፡ ከዚህም ተነስተው ነው በሁለተኛው የምዝበራ መንገድ በዋጋ ንረትና በሦስተኛው የምዝበራ መንገድ ድሃው ጥሬ ገንዘብ ቆጥቦ በኪሳራ ወለድ ለንግድ ባንኮች በማበደር ሕዝቡን እያቀጨጩ እነርሱ የደለቡት፡፡ ይህን መነሻ ሀብት ተጠቅመው ነው ከበርቴዎች ሕንጻ እንዲገነቡ በማድረግ በሃያ ስድስት ዓመት ምዝበራ በድሃ አገር ውስጥ የቢልየነርነት የሀብት ጉዟቸውን የጀመሩት፣ ቢጠሯቸው የማይሰሙ ቱጃሮች የሆኑት፡፡

ከሦስቱ የብዝበዛ መንገዶች አንደኛው የሕዝብ የነበረውን ሀብት ሻጭም ገዢም ሆነው መውረሳቸው ብዙ ሙያዊ ትንታኔ የሚሻ ጉዳይ ባይሆንም በሶሻሊስት ማኅበረሰብ የሕዝብ የነበረው ሀብት ሕዝባዊ የአክስዮን ኩባንያዎችን በማቋቋም ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለራሱ ለሕዝብ ሊከፋፈል ይችል የነበረን የሕዝብ ሀብት ጥቂት ከበረሃ የመጡና እዚህ የቆዩ ዘመዶቻቸው ተቀራመቱት፡፡ የጋራ የነበረው በኢፍትሐዊ መንገድ ተከፋፍሎ በተከታይም በተወሰዱት በሁለተኛው በዋጋ ንረትና በሶስተኛው በቁጠባ አማካኝነት የአገርና የሕዝብ የጋራ የነበረው ሀብት ከድሃው ወደ ሀብታሙ ከገጠሩ ወደ ከተማው እንዴት እንደተሸጋገረ በክፍል አምስት ከምዕራፍ ስምንት እስከ ዐሥራ ሦስት የተግባር ሃተታዎች በጥልቀት እናያለን፡፡

ከ1990ዎቹ መጨረሻ በኋላ ባሉት ዓመታት ግብርናው ካፒታል ሊያፈራና ለኢንዱስትሪው ጥሬ ዕቃ ምርት ሊያመርት ይቅርና ለምግብ ፍጆታ እንኳ ስለአልበቃው የግብርና መር ኢኮኖሚ ፖሊሲው ምንም ለውጥ እንዳላመጣ ታወቀ፡፡ በ1997ቱ ምርጫ የከተማው ሕዝብ በኢሕአዴግ ፖሊሲ አለመደሰቱ ሁከት በመቀስቀስ በመገለጡ ገጠርን ማዕከል ያደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደማያዋጣ አምኖ ፊቱን ወደ ከተሜው መለሰ፡፡ ከተማውና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትኩረት ተሰጣቸው፡፡

የከተማውን ኗሪ ወጣቶችና ሴቶች በድርጅት አባልነት እየተመለመሉ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አደራጀ፣ የውጭ ባለሀብቶች በማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማት እንዲሳተፉ የሚስቡ የኢነቨስትመንት ማበረታቻ ሕጎችን ደነገገ፣ በምህንድስና ዘርፍ ላይ ያተኮሩ የከፍተኛ ትምህርትና የሙያና ቴክኒክ ተቋማት ተስፋፉ፣ ለኢንዱስትሪዎች በብዛት የሰው ኀይል ለማፍራት ሥልጠና በስፋት መሰጠትም ተጀመረ፡፡ መንግሥት ራሱም በመሠረተልማት ግንባታና ለገበያ በሚቀርቡ ሸቀጦች በአምራችነት ተሳታፊ ሆነ፡፡ የግል አምራቾችን ልማታዊ ካፒታሊስትና ጥገኛ ካፒታሊስት ብሎ ከፋፈላቸው፡፡

የኢኮኖሚ አስተዳደሩን ወደ ልማታዊ ኢኮኖሚ ካዞረ በኋላ የተሻለ የኢኮኖሚ ዕድገት አፈጻጸም ቢታይም ልማታዊ ኢኮኖሚ አገራዊ ብሔርተኝነትን ስለሚጠይቅ በቋንቋ ላይ በተመሠረተ የጎሳ ፌዴራሊዝም ፖለቲካዊ አስተዳደር ምክንያት ሕዝቡን ስላሳተፈ ስትራቴጂዎቹን ለማስፈጸም አልቻለም፡፡ ልማታዊ ኢኮኖሚ ማሟላት ያለበትን የሲቪል ማኀበረሰቦችን፣ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ፣ በአጠቃላይም ኅብረተሰቡንና የኅብረተሰብ ተወካዮችን አጋር የማድረግን ጥበብ አልተካነም፡፡ በሌላ በኩልም በልማታዊ ኢኮኖሚ መርህ ልማት መተዳደር ያለበት በችሎታቸው በላቁ ሰዎች ቢሮክራሲ መሆን ሲኖርበት፣ በኢትዮጵያ ግን የፌዴራል መንግሥት ቢሮክራሲን ለማዋቀር ዋናው መስፈርቱ የብሔር ተዋጽኦ እንጂ ችሎታና ብቃት አለመሆኑ ልማቱ ስኬታማ እንዳይሆን አደረገው፡፡

የኢሕአዴግ መንግሥት አገር የማስተዳደር ሕጋዊነት አንድነትን በሚሹም፣ የክልል መንግሥታትን ነጻነት በሚሹም ገና ያልፀደቀና ያልተፈታ ጥያቄ በመሆኑ እነዚህን አካላት የልማት አጋሮች ማድረግ አልቻለም፡፡ አንድነትን የሚሹት ክልሎች አካባቢያችን ለክልላችን ሰው ብቻ ነው በማለታቸው ማዕከላዊ አመራሩ ተዳክሟል ሲሉ በብሔረሰብ ደረጃ መጥበብን የሚሹት ሕገ መንግሥቱ በደነገገው መጠን ክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር በቂ ሥልጣን አልተሰጣቸውም ይላሉ፡፡

ከአንዳንድ መሠረተልማትና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማቅረብ በቀር መንግሥት በአገር አስተዳደር ሚናው በታሪካዊ ጸጥታ ማስጠበቅና ሕግ ማስከበር ሥራዎች ተወስኖ ገበያውን በፖሊሲ ቢመራውና ገበያው ኢኮኖሚውን ቢያስተዳድረው ኖሮ ገበያው ለዚህ ክልል ሰው ለዚያ ክልል ሰው ብሎ አያደላም ነበር፡፡ መንግሥት ገበያውን ተክቶ ኢኮኖሚውን ሲያስተዳድረው ግን ወደ ክልሎች ወደ ታች በወረደው መንግሥታዊ ፌዴራላዊ መዋቅር ተጠሪነቴና ኀላፊነቴ ለክልሌ ሕዝብ ነው የክልሌን ሀብትም በፍትሐዊነት የማከፋፍለው ለክልሌ ሕዝብ ብቻ ነው ተባለ፡፡ መካከለኛ ገቢ ውስጥ ያስገባናል የተባለው አገራዊ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አስታዋሽ አጥቶ ብሔራዊ አጀንዳ በክልላዊ አጀንዳ ተተክቷል፡፡ ክልሎችም የማዕከላዊው መንግሥት የዘመቻ ኢኮኖሚ አስተዳደር ተጋብቶባቸው የዘመቻ ኢኮኖሚ አብዮቶች ነድፈዋል፡፡

መጋቢት 13 ቀን 2009፣ በሪፖርተር ጋዜጣ አንድ ምሁር ስለ ኢሕአዴግና የዘመቻ ሕይወቱ፣ “ተደምሮ–ዜሮ አገርን በዘመቻ የመምራት ጥበብና ውጤቱ፤” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ጽሑፍ አስፍረው ነበር፡፡ “አገራችን ጦቢያ ለዘመቻ አዲስ ባትሆንም በእኛ ዕድሜ ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት ብቻ እንኳ ስንት ዘመቻዎች መጥተው ስንት ዘመቻዎች ተፈራረቁ የውሃ ማቆር ዘመቻ፣ የጤና ልማት ሠራዊት ግንባታ ዘመቻ፣ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ዘመቻ፣ የግብርና ምርታማነት ማሳደግ ዘመቻ፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዘመቻ፣ የመልካም አስተዳደር ማስፈንና ኪራይ ሰብሳቢነት ማክሰም ዘመቻ፣ የሲቪል ሰርቪስ አሠራር ማሻሻያ ዘመቻ፣ የፀረ ሙስና ዘመቻ፣ የጥልቅ ተሐድሶ ዘመቻ፣ … ዘመቻ … ዘመቻ“

የኢሕአዴግ መንግሥት በገበያ ኢኮኖሚ መርሁም ሆነ በልማታዊ ኢኮኖሚ አስተዳደሩ ከላይ ከተጠቀሱት ሦስቱ የመንግሥት ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች በክፍለ ኢኮኖሚ የሀብት ድልድል፣ በለሰዎች የሀብትና የገቢ ፍትሐዊ ክፍፍልና የብሔራዊ ኢኮኖሚ መረጋጋት የትኛውንም በትክክል አልተወጣም፡፡ መንግሥት በሚሠራቸው ኢኮኖሚያዊ ሥራዎች ሁሉ የሕዝቡን ፈቃድና ድጋፍ አላገኘም፡፡ ያለ ሕዝብና ግብር ከፋዩ ፈቃድ ዐሥር አክሳሪ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች ሲነድፍ አንድ መቶ ሃያ ቢልዮን ብር የፈጀ የባቡር ትራንስፖርት ወጪ አውጥቶ አገርን ሲያከስር ማን እንደፈቀደለትም መናገር አይችልም፡፡

ከእነኚህ በተጨማሪ መንግሥት ማምረቻና አገልግሎት መስጫ ድርጅቶችን አቋቁሞ ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶችንም እንዲያመርት ማን ፈቀደለት፡፡ ግብር ከፋዩ ሕዝብ ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ማምረት የመንግሥት ሥራ አይደለም ቢልስ እንዴት ሊከለክለው ይችላል፡፡ ማን ይጠይቃል ማንስ ይመልሳል?

መንግሥት ከድሃው ሕዝብ በሚሰበስበው ግብር ለውጭ ኢንቬስተሮች የፋብሪካ ተከላ ቤት መገንባትና ጓዳቸው ድረስ መሠረተልማት ማንጠፍ ሕዝቡና ግብር ከፋዩ መክሮበት የተሰራ ሥራ ስላልሆነ ውጤት አልባ ከሆነ በኀላፊነት የሚያስጠይቀው ማንን ነው፡፡ ድሃውን አስገብሮ ለሀብታሙ ደጁ ድረስ ድንጋይ ማንጠፍስ ከሰዎች ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ኢኮኖሚያዊ ግብ አንጻር እንዴት ይታያል፡፡ ብዙ ያልተመለሱና በኢሕአዴግ ዘመን የማይመለሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ከኢሕአዴግ ሥልጣን የሚረከብ መንግሥት ይህንን በኢሕአዴግ ዘመን ተቆልሎ ሰማይ ሊነካ የተቃረበ ፍርደ ገምድልነት እንዴት ይሸከመው ይሆን?

ብአዴን አዉራዉ እንደጠፋበት ንብ ወዲያ እና ወዲህ እየተንገዋለለ ነዉ! (ሚኪ አማራ)

ብአዴን እስከ 2012 እንኳን የሚቆይ አይመስለም፡፡ ምኑን ይዞ ምኑን እንደሚጨብጥ ግራ ገብቶታል፡፡ ተከፋፍሎና ተኮራርፎ መግለጫ እንኳን ለመስጠት ወኔ አጥቶ አይተነዋል፡፡ መቀሌ ላይ የተገኘዉ የብአዴኑ ቁንጮ ህላዊ ዮሴፍ «ብአዴን በስብሷል፣ የኛ ያልሆነ የዘቀጠ አስተሳሰብ ግብቶበታል፣ ትምክተኛ እና ነፍጠኛ ማለት እንኳን ማለት አልቻለንም» ብሎ በቴሌቪዠን የራሱን ድርጅት መቀሌ ላይ አንበላዉሶታል፡፡ እኔ ብአዴንን ብሆን እንደዚህ ዝቃጩ ነዉ የተጠራቀመበት ብሎ እየተሳደበ እዛዉ መቀሌ ሳይወጣ ሁለት መስመር ደብዳቤ ከድርጅቱ የሚያሰናብት ፋክስ አደርግለት ነበር፡፡ ግን ማን ያደርጋታል፡፡ እንደዚህ እየተባሉ ብአዴን ከመሆን እዉነት ወደ ነበሩበት የዲኤ ስራ መመለስ ይሻላል፡፡

ለማንኛዉም ብአዴን ህወሃትን ቢንከባከበዉም ከዉግዘት አልተረፈም፡፡ መቀሌ ላይ እንዲሰማ ተብሎ በአማረኛ ስብሰባ ተዘጋጅቶለት «ብአዴን የሚባል ቡድን ቢስተካከል ይሻለዋል» አይነት ዛቻ ተላልፎለታል፡፡ እኔ ግን የሚገርመኝ ብአዴን እንዲህ ለህወሃት እያሽቋለጠ ህወሃት ግን ሁሌም ይከሰዋል፡፡ ነገ አዲሱ የአማራ ፓርቲ ወደ ስልጣን ሲመጣ ህወሃት ምን ሊዉጠዉ ነዉ፡፡

ህወሃት በነገራችን ላይ ኦህዴድንና ደህዴንን ሲናገር ሰምቼ አላዉቀም፡፡ ብአዴንን እንደ ዉሽማዉ ስለሚያየዉ እንደፈለገ ነዉ የሚጫወትበት፡፡

ለማንኛዉም አዉራዉ እንደጠፋበት ንብ ብአዴን ወዲያ እና ወዲህ እየተንገዋለለ ነዉ፡፡ በተለይም ሰሞኑን ገዱ አንዳርጋቸዉ በጉብኝት፣ እንዲሁም የባልተቤቱን ህክምና ለመከታተል ከባህርዳር አካባቢ በመጥፋቱ ብአዴን አባት እና እናት እንደሌለዉ ልጅ ተበታትኖ የት እንደሰነበተ አልታወቀም፡፡

ባጠቃላይ መቀሌ፣ አዳማ እና አዲስ አበባ ላይ እየተወራ ያለዉ የፖለቲካ ልዩነት እና ባህርዳር ላይ ያለዉን ጉምጉምታ ስናየዉ በዚህ ድርጅት ዉስጥ ያለዉ ጦርነት ገና እየተፏፏመ እንጅ እየቀነሰ አይመስልም፡፡ በዚህም ምክንያት ሃምሌ ላይ ኢህአዴግ ወደ አንድ ግንባር ያድጋል የሚለዉ ሃሳብ ዜሮ ነዉ፡፡ ህወሃት በዚህ እርግጠኝነት በሌለበት ሁኔታ ወደዚህ ዉሳኔ ደፍሮ ይሄዳል ተብሎ አይታሰብም፡፡

*****

አቶ በረከት ስምዖን አምባሳደር ሆኖ እንዲሾም ቢጠየቅም እምቢ ማለቱ ተሰማ

(ዘ-ሐበሻ) ከንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀንበርነቱን ከ6 ወር በፊት ራሱን ያነሳው አቶ በረከት ስምዖን አምባሳደር ሆኖ እንዲሾም ቢጠየቅም እምቢ ማለቱ ተሰማ::

እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በረከት ስምዖን እንዲሾም የተፈለገው በብራሰልስ ቤልጂየም. ነበር:: ሆኖም ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በርከት ጥያቄውን እንዳልተቀበለው ነው የተገለጸው::

በርከት በድርጅቱ ውስጥ የመገፋት ስሜት እንደሚሰማው የሚገልጹት ምንጮች በተለይ ከዚህ በፊት አሰናብቱኝ ብሎ የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገባ በኋላ እንደገና በድርጅቱ ውስጥ መታየቱ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል:: አሁንም የቤልጂየሙን የአምባሳደርነት ጥያቄ ያልተቀበለው በሃፍረት አልያም በጤና ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል::

አቶ በረከት ከኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስተርነቱና ከንግድ ባንክ የቦርድ አባልነቱ ራሱን ማንሳቱ አይዘነጋም::

አቶ በረከት ስምዖን፣ ከህወሃት ጋር በመሆን የእነ ዶ/ር አብይንና ለማን ቡድን ለመምታት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝና በኢህዴግ ውስጥ ያለው ተቀባይነት እየተመናመነ የመጣው አቶ በረከት፣ ከብአዴን ይልቅ ከህወሃት ጋር ጥምረት በመፍጠር እርሱና በህወሃት ዙሪያ የሚገኙ ጓደኞቹ የሚቆጣጠሩትን ስርዓት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ይህም እየከሸፈበት መሆኑ መዘገቡ አይዘነጋም::

****

የበረከት ስምኦን ሴራ እና የሁለቱ ብአዴኖች ፍጥጫ!

ጌታቸው አምባዬን የብአዴን ሊቀ መንበር፣ ቀድሞ አባዱላን ኋላ ደግሞ ሽፈራው ሽጉጤን ጠቅላይ ሚኒስትር ለማደረግ የእነ በረከት ሴራ፤

(አንጀቱ ያረረው ሞረሽ ነኝ፣ ከብአዴን ቤት)

፩. የሁለቱ ብአዴኖች ፍጥጫ፤
———————————
የስምኦን ልጅ በረከት አማራ ላይ ከሚሸርበው ተንኮል መቼም ተዘናግቶ አያውቅም፡፡ አጋዦች ሞልተውታል፡፡ ሲያስፈልገው ከህወሃት መንደር ይመዝዛል፡፡ ወደ ህወሃት መንደር ከመጓዙ በፊት ግን በብአዴን ቤት ያሉትን አጋሮቹን ይጠቀማል፡፡ ዋነኛ አጋሮቹ ደግሞ ሽማግሌዎቹና ባልቴቶቹ (በረከት፣ አዲሱ፣ ህላዌ፣ ታደሰ፣ ሁለቱ ገነቶች፣ ዝማም…።) ብአዴኖች ናቸው፡፡ ግቡን ለማሳካት ደግሞ አንዳንድ በብሔር አማራ፣ በተግባር ግን ጸረ አማራዊ ድረጊት ውሥጥ የተነከሩ ባንዳዎችን (እንደ ጌታቸው አምባየና አለምነው ዓይነቶቹን) ይጠቀማል፡፡

በብአዴን ቤት የመረረ የውስጥ ትግል ከተጀመረ ሁለትና ሦስት ዓመታት ሞልቶታል፡፡ ትግሉ በአማራነት ዙሪያ ነው፡፡ የነ በረከት ቡድን፣ “ትምክህት”እና “ነፍጠኝነት” የሚሉ ቃላትን በዱላነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ይወዷቸዋል፡፡ በእነዚህ ቃላት አማካይነት አማራን ሲሰድቡና ሲያዋርዱ ኖረዋል፡፡

አዲሶቹ ብአዴኖች ትምክህተኛና ነፍጠኛ የሚሉትን ቃላት ጠልተዋል፡፡ በእነዚህ መለኪያ የሚደረግ ፍረጃን አይቀበሉም፡፡ እንደውም ነውር (ታቡ) መሆን አለባቸው ይላሉ፡፡ እነ በረከት ግን የአማራን ሕዝብ ጥቅም ለማስከበር የሚንቀሳቀሱትን አዲሶቹን ትምህተኛና ነፍጠኛ በማለት ለማሸማቀቅ ይጥራሉ፡፡ በየስብሰባው በነጋ በጠባ ቁጥር መገምገሚያቸው ትምክህተኛና ነፍጠኛ የሚሉት ቃላት ናቸው፡፡ አዲሱ ብአዴን እነዚህን ጸረ አማራ አንድምታ ያላቸው ቃላቶች አይቀበልም፡፡

የነባሩ ብአዴን አቋም ያው የድሮውንና የነበረውን ማስቀጠል ነው፡፡ ለእነ በረከት አዲሱ ትውልድ አማራን የመምራት ብቃት የለውም፡፡ የለውም ብሎ ማመን ብቻ ሳይሆን በየቦታው ማጣጣል የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡

፪. ንጉሡ፣ ላቀ፣ አምባቸው፣ ለገሰና ተስፋዬ
———————————————
በተለይ ከአዲሱ የብአዴን አመራሮች ውስጥ ንጉሡ ጥላሁን፣ዶ/ር አምባቸው መኮነን፣ ላቀ አያሌው (የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ የነበረው) እና ለገሰ ቱሉ ከአሁን በኋላ አሮጌው ብአዴን የአዲሱን አመራር እጅ መጠምዘዝ እንደማይችል በግልጽ አማርኛ ነገረዋቸዋል፡፡ እጅን ጠምዝዞ ያሻውን ማስፈጸም ቀርቷል፣ የፈለጋችሁትን ማስፈጸም ከእንግዲህ የለም አሏቸው፡፡ እነ ንጉሡ (የገዱ ቡድኖችና ደጋፊዎች) ከዚህ በታች የተገለጹትንና ሌሎች ሐሳቦችን አንስተዋል፡፡ እንዲህ አሉ፣

• ከውስን አመራሮች ውጭ ብአዴን ተላላኪ ነው፡፡

• የሕወሃት የበላይነት አለ፣ ብአዴን አማራን እንዳይመራ ነጻነቱን ተነፍጓል፡፡

• አማራ ሲፈናቀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምበት ብአዴን ከአማራ ጋር አልቆመም፤ አሁንም እየተፈጸመበት ነው፡፡

• በፌደራል ሥርኣቱ አማራ ተጠቃሚ አልሆነም፣ አይደለምም፡፡

• የመብት ጥያቄ ስናነሳ እስራትና ግርፋት ይደርስባናል፣ ግንቦት ሰባት እንባላለን፣ የሱዳን ታርጋ ባለው መኪና በርካታ የበታች አመራሮች ተወስደው ተገርፈዋል፡፡

• ክልሉ ከየትኛውም ክልል በባሰ ሁኔታ ወደ ኋላ ቀርቷል፡፡

• የደህንነት እና የመካላከያ አመራሩ በአንድ ብሔር የተጥለቀለቀ ነው፡፡

• የተባረሩ የአማራ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ ሥራቸው ይመለሱ፡፡

• መላኩ ፈንታ ይፈታ ወዘተ…

በነገራችን ላይ ንጉሡ ጥላሁንን እና ላቀ አያሌውን ለመገሰጽ ከሞከሩት ውስጥ አንዱ ጌታቸው አምባዬ ነበር፡፡ ገነት ገብረ እግዚአብሔር የምትባለው ሕወሃት ደግሞ ስለ መላኩ ፈንታ ሲነሳ ስለምን ገብረዋህድስ እንዲፈታ አትጠይቁም አለች፤ ያው ዘር ከልጓም ይስብ የለ!

እንደውም ተስፋዬ ጌታቸውማ (በአለምነው የተተካው አዲሱ ብአዴን) አመራሩን ለማፍረስ በብአዴን ውስጥ የቀለም አብዮት እያካሔዳችሁ ነው አለ፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ የብአዴን የቀለም አብዮት በማለት ተስፋዬ የገለጸው ግቡ ደመቀ እና ገዱን በማንሳት የብአዴንን ሊቀመንበር ጌታቸው አምባዬን በማድረግ አመራሩን መበታተን ነው፡፡ በታትኖ ዳግም ሙቅረት (reconfiguration) በመሥራት በእነ በረከት “ክሊኮች” ብአዴንን ማጥለቅለቅ፤ ያው ይህም ከሸፈባቸው፡፡

፫. ደመቀ መኮንን
——————
ደመቀ መበርታት ከጀመረ ዋል አደር ብሏል፡፡ የደመቀን ቃል በመጠቀም “ብአዴን የራሱ ወርድና ስፋት ያለው ድርጅት እንጂ የማንም ተላላኪ አይደለም፡፡ ብአዴን ሌላ አንጋሽ አያስፈለገውም ፤ ብአዴን የሚታገለው የሚታመነው ለራሱና ለህዝቡ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ‘ኦን አወር ዴድ ቦድይ’ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ሊሆን አይፈቀድም” አለ፡፡ የስምኦን ልጅ በረከት እና አጋሮቹ እንደ ድሮው በብአዴን ቤት በማዳከር ወደ ፈለጉት መንገድ ለመጎተትም ለመጠምዘዝም ያደረጉት ፍልሚያ ከሸፈ፡፡ መክሸፍ እንደ እነ በረከት ሴራና ተንኮል!

፬. እነ በረከት አባዱላን ጠቅላይ ሚኒስትር ለማድረግ፤
———————————————————-
በረከት የብአዴንን ብሩህ ልጆች በልቷል፤ አስበልቷል፤ አቁስሏል፤ አስቆስሏል፤ አስሯል፤ አሳስሯል፡፡ በጣት የሚቆጠሩት ብቻ በማገገም ላይ ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ አድርጎም የበረከት ሆድ አይጠረቃም፡፡ በመሆኑም ሌላ ሴራ ጎነጎነ፡፡ በረከትና አሮጌዎቹ፣ ጌታቸው አምባዬን የብአዴን ሊቀመንበር ለማድረግ ደፋ ቀና አሉ… በዚህ ልፋታቸው ተደፍተው ቢቀሩም፡፡ ጌታቸው አምባዬ ሳይልኩት ወዴት፣ ሳይጠሩት አቤት ባይ ነው፡ ለነበረከትና ለህወሃት፡፡

ለበረከትና ለጌታቸው አምባዬ ሕወሃታዊ ጥምረት ምሳሌው መላኩ ፈንታ ላይ የሰሩት ደባ ነው፡፡ መላኩ ፈንታን ለማሳሰር የክስ መረጃዎችን ለበረከት ስምኦን የሰጠው ቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቤ ሕግ የነበረው ሳሙኤል ታደሰ ሲሆን መረጃ በመስጠት ለአደረገው አስተዋጽኦ ወሮታውን ለመመለስ ሲባል እንዲሁም የአቶ በረከትም ሚስት ጋር ወዳጅ ስለሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ሲለቅ በረከት የቦርድ ሰብሳቢ የነበረበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕግ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ተሹሟል፡፡ ንግድ ባንክ ሠርቶ ያማያውቅ የንግድ ባንክ የሕግ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ቪላ ቤት ቪ8 መኪና ጋር ተሰጠው፡፡ አማራን ማሳሰር እንዲህ ያሸልማል፤ ሸላሚዎቹም እነ በረከት ናቸው፡፡

ጌታቸው አምባዬ ብአዴንን ከተቀላቀለበት ጊዜ አንጻር ሲታይ መሆን የነበረበት ከአዲሶቹ ብአዴኖች ጋር ነበር፡፡ ያው እንደ አለምነው መኮንን አማራን የሚዋጋ ባንዳ ሆነ እንጂ፡፡ ይህ ሰው ክፍለ ሕዝብ ከመሆኑ በፊት የችግኝ ጣቢያ ውሃ አጠጪ ከዚያም የኅብረት ሱቅ ሠራተኛ ነበር፡፡ ጌታቸው የጤና እክል እንዳለበት (ኤች አይ ቪ፣ ኤድስ እንዳለበት) የታወቀ ነው፡፡ መጠጥና ሴት ነፍሱ ነው፡፡ የፍትህ ሚኒስትር ሆኖ የተሰጠውን ቪ8 ታርጋውን ቀይሮ ከቺቺኒያ ቦሌ፣ከቦሌ ቺቺኒያ ማታ ማታ ሲዘል አንድት ሴተኛ አዳሪን ባለጥቁር መስታዋት መኪና ውስጥ አስገብቶ ያለ ኮንዶም ካለደረግን በማለቱ ጩኸትና እሪታ በመፈጠሩ በፖሊስ ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ አድሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ ኮማንደር ግርማ ነው ያስፈታው፡፡ ያሠሩት ፖሊሶችም ከሥራ ተባረዋል፡፡ በተለይ ይቺ ታሪኩ በእነ እንቶኔ ቤት ስለምትታወቅ ያሻቸውን ያስደርጉታል፡፡ እሱም ተመችቷቸዋል፡፡ እንደውም ባልተቤቱ እሱን በያዘው በሽታ ስትሞት ሌላ አገባ፡፡ እሷን በመፍታት ከሕወሃት ሰፈር ትግሬ አገባ፡፡ ያው ተጠቃሎ ወደ ሕወሃት ዘንድ ገባ ማለት ይቻላል፡፡

እነ በረከት በብአዴን ቤት ያልተሳካላቸውን ሴራ ወደ ኢሕአዴግ ዘንድ ይዘው በሌላ ሴራ መጡ፡፡ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫንም ልክ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ እንደወጣ ሁሉ ሰው መመልመል ጀመሩ፡፡

በምልመላው አባዱላን ለጠቅላይ ሚንስትርነት አጩት፡፡ ሽፈራውን (ሞሪንጋን) ደግሞ ምክትል ለማድረግ ደፋ ቀና አሉ፡፡ አባዱላን ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ ረገድ አሁንም ድፍት አሉ፣ ይህ ሁሉ የሚሆነው በነበረከት ነው፡፡

ከተደፉበት ቀና ለማለት ፕላን B ያሉትን ካርታ መዘዙ፡፡ ሽፈራው ሽጉጤን ጠቅላይ ሚንስትር ማድረግ፡፡ እንግዲህ ይህ ሴራ ታወቀ፡፡ ሽፈራው ሽጉጤን ለማስሾም ደፋ ቀና ቢሉም አሁንም ተደፍተው ቀሩ፡፡ ደመቀ መኮንንም ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እራሱን አገለለ፡፡ ሌላ ተቀያሪ ፕላን አመጡ፤ ምክንያቱም በሁሉም ተደፉ፡፡ ያመጡትም የሊቀ መንበር ምርጫው እስከ ጉባኤ ደረስ እንዲራዘም ነበር፡፡

በዚህ ሁለትና ሦስት ዓመት በነበረው የብአዴን የውስጥ ትግል፣ በአዲሶቹ ቆራጥነት ድርጅቱ ከመፍረስ ድኗል፡፡ እነ በረከትን በከፍተኛ ሁኔታ ተገዳድረዋል፣ አማራን ለመወከል ጥረዋል፣ ይብላኝ ለእነ በረከት፡፡

“የኃጢአተኞች መንገድ ትጥፋ”፣ እንዲል ዳዊት በመጀመሪያው መዝመሩ፣ የእነ በረከትና የነጌታቸው አምባዬ መንገድ ትጥፋ፤ ፀረ-አማራ ናትና::

በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ (ፋሲል የኔአለም)

ፋሲል የኔአለም

Professor Mesfin Woldemariam's opinion about Ethiopia's new PM Dr. Abiy Ahmed.

ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ከተመረጡ ወዲህ በሁሉም ወገን ያለው ግራ መጋባት እንደቀጠለ ነው። በተቃውሞው ጎራ ትልቅ የመረጃ ክፍተት ያለ ይመስለኛል። ትንታኔዎች ይበዛሉ ነገር ግን ትንታኔዎች በጠንካራ መረጃዎች ካልተደገፉ፣ መረጃዎችም እንዲሁ በትንታኔ ካልዳበሩ ሁለቱም ዋጋ የላቸውም። ብዙዎቻችን የመተንተኛ መሳሪያዎችን እናውቃቸዋለን፣ ችግራችን የሚተነተነውን ተጨባጭ መረጃ ማግኘቱ ላይ ነው። አሁን በተቃውሞው ጎራ የሚታየው ግራ መጋባት ከመረጃ እጥረት የሚነሳ ይመስለኛል። በገዢው ፓርቲ በኩል ያሉ ሰዎች ደግሞ መረጃው አላቸው ነገር ግን ትንታኔ ላይ ችግር አለባቸው። ችግራቸው የመተንተኛ መሳሪያዎችን ሳያውቁ ቀርተው ሳይሆን፣ ትንታኔውን ከራስ ጥቅም በተላቀቀ መንገድ ለመተንተን አለመቻለው ነው። ለማንኛውም በእኔ በኩል አንዳንድ የሰማሁዋቸውን መረጃዎች ማካፈሉ ለተንታኞችም ለአጠቃላይ ትግሉም ይጠቅም ይሆናል በሚል እምነት የተወሰኑትን ብቻ እንዲህ ጽፌያቸዋለሁ፦

1ኛ) ኢህአዴግ ከሁለት መከፈሉ ግልጽ ነው። በአንድ በኩል በቀድሞው አካሄድ መጓዝ የሚፈልጉ በሌላ በኩል ደግሞ በአዲስ አስተሳሰብ መመራት የሚፈልጉ( በአብዛኛው ወጣቶችን ያቀፉ) ቡድኖች አሉ። በኢህአዴጎች መካከል ያለው ጦርነት እስከ ነሃሴው የድርጅቱ ስብሰባ ድረስ ይቀጥላል። ከዚያ በሁዋላ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም፤ ለውጥ ፈላጊው ያሸንፋል ወይም ይሸነፋል። ለውጥ ፈላጊዎችን ከደገፍናቸው የማሸነፍ እድላቸው ከፍተኛ ይሆናል።

2ኛ) ዶ/ር አብይንም ሆነ የኦህዴድና የብአዴን አመራሮችን በጅምላ የህወሃት ተላላኪ አድርጎ መፈረጁ ትክክል አይደለም። አብይን ነጥሎ የለውጡ ብቸኛ “ስትራቴጂስት” አድርጎ መሳሉም እንዲሁ ትክክል አይደለም።

3ኛ) ለውጥ ፈላጊው ቡድን በዋናነት የሚመራው በለማና በደመቀ ነው። ገዱም ዋናው የለውጡ ደጋፊ ሆኖ ከአቶ ደመቀ ጋር በጥምረት የሚሰራ ነው። እስካሁን የለውጡ አቀንቃኞች ለውጡ ጥገናዊ እንዲሆን የመፈለግ አዝማሚያ አይታይባቸውም። ታሪክ የመቀየር ፍላጎት እንዳላቸው ይነገራል።

4ኛ) ለአብይ መመረጥ ትልቁን ሚና የተጫወተው ደመቀ መኮንን ነው፤ ከተወዳዳሪነት በመውጣት ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ባሳየው ድንቅ መድረክ የመምራት ችሎታው ቀጣዩን መንገድም የሰመረ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል። ድሮ ስለደመቀ የምንሰማውና የዛሬው ደመቀ ፍጹም የተለያዩ መሆናቸውን የብአዴን አባላት የሚመሰክሩት ነው። ደመቀ በምርጫ ያልተወዳደረው ለአብይ እድሉን ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ምክንያቶችም አሉ። ሃይለማርያምም እንደተነገረለት ስልጣን በፈቃዱ ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረበው በስልጣኑ እንደማይቆይ ስላወቀ ነው፤ በሴራ ፖለቲካ ውስጥ እጅ ከፍንጅ የተያዘበት ስራ ሲሰራ መገኘቱንም ከእሱ ጋር በቅርብ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች የሚመሰክሩት ነው።

5ኛ) ለውጡን ለማደናቀፍ እየሰሩ ያሉት በብአዴን በኩል በረከት፣ አለምነው፣ ዝማም፣ ፍሬህይወት፣ ገነት፣ ከበደ፣ አዲሱና ህላዊ በዋናነት ሲጠቀሱ፣ ህወሃት ከጀርባ ሆኖ ድጋፍ ይሰጣቸዋል። እነዚህ ሰዎች የደመቀንና ገዱን ቡድን ለመምታትና ብአዴንን ለህወሃት ለማስረከብ ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ነው። ደግነቱ አብዛኛው ለውጥ ፈላጊው የብአዴን ወጣት አመራር ከእነ ገዱ ጋር መሰለፉን በርካታ አባላቱ የሚገልጹት ሃቅ ነው። ህወሃት ከኦህዴድ በኩል የሚያሰልፈው ተላላለኪ በማጣቱ ችግር ውስጥ ወድቋል፤ ለማ በወሰደው “ቆራጥ” እርምጃ ኦህዴድ ውስጥ ያሉ የህወሃት ተላላኪዎች ተጠራርገው ወጥተዋል። ህወሃት በኦህዴድ በኩል በረከቶችን ማግኘት አልቻለም። ለማ መገርሳን የገጠመው ፈተና ህወሃትን እንቃወማለን የሚሉ በአብዛኛው በውጭ ያሉ “ የኦሮሞ አክቲቪስቶች” የሚፈጥሩበት ጫና ነው። አሁን በሚያደርጉት ቅስቀሳ ለማን ህዝባዊ ድጋፍ ካሳጡት፣ በህወሃት ሊበላ ይችላል። ልብ በሉ! እነ ለማና ገዱ ( ደመቀ) ተሸንፈው እነ በረከት ካሸነፉ ( የማሸነፍ እድላቸው ዝቅተኛ ቢሆንም) በዚች አገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ይደርሳል ።

6ኛ) አብይ ያለ ለማ እና ገዱ( ደመቀ) እንዲሁም ያለ ህዝብ ድጋፍ በሚቀጥሉት ወራት ከህወሃት እና ከእነበረከት ጋር የሚኖረውን ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት አይችልም። የአብይ ቀጣዩ የለውጥ አጀንዳ በመከላከያውና ደህንነቱ ላይ በመሆኑ ፍልሚያው ቀላል አይሆንም።

በአጭሩ፣ የተቃውሞው ጎራ ኢህአዴግን በጅምላ መቃወሙ ትክክል አይመስለኝም። አዲስ አስተሳሰብ እንከተል የሚሉትን ቡድኖች ለይቶ መደገፍ ከስትራቴጂ አንጻር በጣም አዋጪ ነው። እኛ ከምናስበው በላይ በመካከላቸው ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ነው። አንገቷ የረዘመ ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልጉት ሃይሎች ትግላቸውን በብልጠትና በጥንቃቄ ማካሄድ እንደለባቸው አምናለሁ።

በጓዳችን መፈታት ደስ ብሎናል፤ የሚጠብቀን ብዙ መሆኑን እናውቃለን – የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

Patriotic Ginbot 7 logo

ዛሬ  ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓም ጓዳችንና መሪያችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  ከእስር ቤት ወጥቷል። አቶ አንዳርጋቸው ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም በሰንዓ አውሮፕላን ጣቢያ በህገወጥ መንገድ ተይዞ ያለአንዳች የህግ አግባብ ለህወሓት አገዛዝ ተላልፎ ላለፉት አራት ዓመታት በስቃይ አሳልፏል።

አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ ተፈቶ ከጉጉት ከሚጠብቀው ሕዝብና ቤተሰቦቹ ጋር ሲቀላቀል እንደተናገረው “ሰው እየሳቀ ለመብቱም ለሕዝቡም መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ” ማለት የቻለ መሪ ነው።

ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ለሁሉም የህሊና እስረኞች መፈታት የበርካታ ወገኖቻችን ሕይወት መስዋትነት ተከፍሏል፤ ብዙዎች ታስረዋል፤ ተደብድበዋል፤ ተሰደዋል ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። ትግላችን እሚፈለገው ግብ ላይ ለመድረስ ገና ብዙ መንገድ የሚቀረው ቢሆንም ዛሬ የደረስንበት ለመድረስ ዋጋ ተከፍሎበታል። በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ የለውጥ ኃይሎች ለዚህ ድል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን እንገነዘባለን።

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር መፈታት የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ይገልፃል። ይህ እውን እንዲሆን ጥረት ላደረጉ ኢትዮጵያዊያንን ዜጎች እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ከጎናችን ለቆሙ የውጭ አገር ዜጎችና ድርጅቶች ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል።

ደስታው የሁላችንም ነው፤ እንኳን ደስ  ያለን!!!

ደስታችን የተሟላ የሚሆነው ግን ወገኖቻችን የሞቱለት፣ የታሰሩለት፣ የተሰደዱለትና የተሰቃዩበት ዓላማ ሲሳካ ነው። ዛሬም አቶ አበበ ካሴ፣ ሰይፉ አለሙ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ማስረሻ ሰጤ እና ሌሎች በርካታ ወገኖቻችን በእስር ላይ ይገኛሉ። ለእነዚህ ሁሉ ወገኖቻችን ነፃነት የምናደርገው ትግል አጠናክረን መቀጠል ግዴታችን ነው።

ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ የምናደርገው ትግል ገና በጅማሮ ላይ ያለው ነው። ዛሬ በአገራችን ያየነው መልካም ጅማሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ እውነተኛ  የስልጣን ባለቤት ወደሚያደርግ መሠረታዊ ለውጥ እንዲያመራ ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል።

ስለሆነም በጓዳችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ምክንያት ደስታችን ከፍተኛ  ቢሆንም ከእንግዲህ የሚጠብቀን ትግል ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ መስዋትነት ሊጠይቅ የሚችል መሆኑን በመገንዘብ  ተዘጋጅተናል።  እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሀገሩ ባለሙሉ መብት ዜጋ እስኪሆን ትግላችንን እንቀጥላለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ጭንቁ ሌቦቹ አቅም አገኙ ነው። ለውጡን የመቀማትም ዕድል ሊኖር መቻሉ መጤን አለበት (ሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 28.05.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)

ሥርጉተ ሥላሴ
ሥርጉተ ሥላሴ

„የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፤ በጥሩ ወርቅ አትገመትም። እንግዲያሳ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው? ከሕይዋን ዓይን ሁሉ ተሰውራለች። ከሰማይ ወፎች ተሸሽጋለች። ጥፋትንና ሞት ወሬዋን፣—  በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል።“ (መጽሐፈ እዮብ ምራፍ ፳፰ ከቁጥር ፲፱ እስከ ፳፪)

 • መቅድም።

ታዲያ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንን ጎፈሬ እንዲያበጥር ይጥበቃል? የቡላ አጥሚቱን፤ የጎን አጥንት ሾርባውን አዘጋጅተን ስናገጠግጠው በጡጧ ሰነባብተን የለም። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ አቅሙን ያደራጀንለት እኛው እራሳችን ነን። ለውጡ ሊቀለበስ እንደሚችልም ማሰብ ይገባል። ምክንያቱም ትግሉ ከለውጡ ጋር ነውና።

በተቃዋሚ ሥም ገንዘብ የከፈለ ሁሉ ምርጥ ዜጋ ነው። ስለሆነም በአገኘው ተቀባይነት እና ዕወቅና ሽንጡን ገትሮ ቀን ሲገነባ ሌሊት ሲያፈርስ ነው የከረመው። የትኛው ሚዲያ ነው ይህን ለውጥ ደግፎ የተነሳ? የትኛው? አንዲት ነገር እዬመዘዘ ሲታመስ አይደለም የተከረመው። እያንዳንዱ ሂደትን በስላቅ ሲዥጎረጎር አይደለም የተከረመው። ለውጡን የሚቃወሙ ሰዎች እዬተፈለጉ አይደለም ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ ሲደረግ የተከረመው። በምክንያቶች ላይ ሳይሆን በሳቢያዎች እና በዘሃቻው ላይ ብቻ ነበር ውርክቡ።

የትኛው ሰው ነው ለውጡን በጤነኛ መንፈስ የሚይ ቃለ ምልልስ የተደረገለት። አንድ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ብቻ ነው። ሲጀመር ትንሽ ሰሳ ያለች ክፈተት ነበረው። ያ ደግሞ የተገባ ነው። ማመዛዘን ማገናዘብ የተገባ ስለነበር። ከዚያ በኋዋላ ግን በፍጥነት እንደ ሰብዕናው ሙሉነት ደልዳላነት በስክነት እና በብልህነት „አናስደንግጣቸው“ ነበር ያለው። „ሌላው ቢቀር እስከ አሁን ያደረጉት ይበቃል“ ሲል ሁሉ አዳምጨዋለሁኝ።

አሁን እፍታ ላይ እሱ ስሌለ ታድሜ አላውቅም። አሁን ያለውን አቋሙን አላውቅም። ቀደም ባለው ሰሞናት ግን  በአቋሙ ውስጥ እንደ ነበር አንድ ቃለ ምልልስ ላይ አስተውያለሁኝ። አሁንም ተስፋዬ ሙሉ ነው ክብሩን የጠበቀ ጋዜጠኛ መሆንኑን ስለማምን በዛው „አናስደንግጣቸው“ አቋሙ ይቀጥላል ብዬ አስባለሁኝ። ከዕድሜው በላይ የተረጋጋ ሁለገብ ማስተዋል ያለው፤ ጋዜኛ ለሚለው ሚዛናዊ ሰብዕናም ናሙና ነው። ርግጥ ነው የራሱ ሚዲያ ስሌለው ሁልጊዜ ላዳምጠው እንደ ዶር አቦንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ባለመቻሌ ተጎድቼያለሁኝ። በሁሉ ዕይታው መስማማት የግድ የለብንም። እኔም ሥርጉተ ነኝ እሱም ጋዜጠኛ ሲሳይ ነው። በመደገፍ እና በመቃወም ዝንባሌያችን ይለያያል፤ ተመክሯችን ሆነ ያለፍንበት የህይወት መስመርም እንዲሁ የተለያዬ ነው። የሆነ ሆኖ እንደ እሱ ያለ ምራቁን የዋጠ ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል።

በተረፈ እንደ ሳጅን በረከት ኦርጅናሉ መጣ እስከሚባል ድረስ የታዬው መታመስ ታሪክ አንድ … ሁለት … ሦስት እያለ ቆጣጥሮታል። ለውጣዊ ሂደቱ እኮ ለወያኔም አንጡራ ጠላቱ፤ ለነፃነት ፈላጊውም አንጡራ ጠላት ነው የሆነው። አኩል ለእኩል። ሁሉም ሲያብጠለጥል አይደለምን የባጀው? የትኛው ሚዲያ የትኛው ጋዜጠኛ የትኛው የፖለቲካ ተንታኝ፤ የትኛው የፖለቲካ ድርጅት መሪ ለዚህ ለውጥ ቅናዊ ንጹህ ልቦና ቅርብ የነበረው፤ ካለ አንጋፋው መኢሶን በስተቀር። መኢሶን እንደ ድርጅት፤ ዶር ነገደ ጎበዜ እንደ ፖለቲካ መሪ እጅግ ቅን የሚባል ግልጽ አቋማቸውን ከግል ኢጎ በፍጹም ሁኔታ በራቀ መልኩ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። የተመክሯቸው አቅም ለዚህ የወቅት እቅም ጋር የሚመጥን ነበር። እሳቸው ይሰበስቧቸው ከነበሩት ብሄራዊ ጉባያት ሁሉ በወጣትነት ዘመኔ ታድሜያለሁኝ። የረጋ መንፈስ እንዳላቸው አውቃለሁኝ። በዛ በማከብርላቸው ሰብዕና ውስጥ ስለመቀጠላቸውም ሰሞኑን አዳምጫለሁኝ እስኪገርመኝ ድረስ። ይህን ሰብዕናቸውን ጠንቅቄ ስለማውቅም አንድም ቀን በወቀሳ አንስቼው አላውቅም ድርጅቱን። የደነቀኝ የጠበኩትን ጥንካሬ በጽናት በቋሚነት ማግኘቴ ነው። ዛሬ እኮ አይደለም ሰው፤ ዕቃ ካኖሩበት አልገኝ ካለ ዘመን ተቆጠረ። የሃሳብ ልዩነት መኖሩ የተገባ ሆኖ ንጹኽ ተግባርን እንደ አመልማሎ የጥጥ መሰናዶ መደመጠጥ ግን የህሊና ሽፍትነት ነው።

ኢጎ አዎንታዊም አሉታዊም ቢሆንም አሉታዊ ብቻ እንዲገዛ መፍቀድ ጠረኑ የጨለማ ነው። ፕሮፖጋንዳ ለአዎንታዊ እርቅ፤ ለአሉታዊ ጠብ ወይንም አሉታዊ ግን ለሚያግዝ የሚጠበቅ ቢሆንም የሚታዩ ተጨባጭ ሰብሎችን አረም እንዲወጣቸው ለመፍቀድ መጣር ደግሞ ጎንድ ተ/ ሃይማኖት አንድ በለው ይህን የጸላዬ ሰናይ መንፈስ ያስብላል። አንድ ዕጩ ለምርጫ ሲወዳደር የምረጡኝ ፕሮፖጋንዳ ይኖረዋል ያ አዎንታዊ ነው። ተፎካካሪው ደግሞ እሱን ለማሸነፍ ተቃራኒውን ቢፈጽም ያም አዎንታዊ ነው። በሃሳብ ገብያ ሚዛኑ በህዝብ የሚዳኝ ነው የሚሆነው። አሁን የእኛ ተግባር ግን መልካም ነገር እያገኘህም፤ እያዳመጥክህ አይደለም፤ ጭላንጭል ብርሃን ውስጥ አይደለህም፤ ጨለማ ውስጥ ነህ ቢባል የሚሆን አይደለም። ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ ስለሌለ። 84% ግብረ ምላሹ ኢ – መልካምነት ዘመቻው እርቃኑን እንደ ቀረ አመላካች ነው። ስለዚህ ጨርሶ እርቃናችን ሳንቀር ስልት ቀይሮ ሊደመጥ የሚችል፤ ሸፍጥ የሌለበት የህሊና እጠባ ላውንደሪ ያስፈልገናል። እኔ ይገርመኛል በግል እማገኛቸው ሰዎች ሁሉ እርካታቸውን የሚገልጹበት ስንኝ ሁሉ። መጻፍ ጀምርኵኝ ያለችኝ እህት ሁሉ አለች። ለዛውም ከዘማሪነት ወጥታ ፖለቲካ ጉዳዮዋ ሆኖ። ይህ የመንፈስ ልዕልና ያመጣው የመንፈስ መረጋጋት እና ተስፋን ማግኘት ነው።

 • ጥገናዊ ለወጥ እና ተስፋው።

ለውጡ እኮ ጥገናዊ ነው። ያውም በራስ ውስጥ ባለ የፖለቲካ የሥልጣን ሽግሽግ። በዚህ እንኳን እኩል ግንዛቤ ሊኖር አልቻለም። በጥገናዊ ለውጥ መርህ ሰጥቶ መቀበል፤ ተቀብሎ መስጠት፤ ማትረፍ እና መክሰር፤ ዕድል ከቀናህ ሦስት ትወስዳለህ ሁለት ትሰጣለህ። የምትፈልገውን ለማግኘት የማትፈልገውን ማስጠጋት እና የእኔ ማለት ግድ ነው። ኢህአዴግ ድርጅቱ የአራት ፓርቲ ስብስብ ነው። ድርድሩ ኮታዊ መሆኑ አይቀሬ ነው። ወሳኙ እኮ ድምጽ ነው። 4% እኩል ድምጽ ነው ያለው። ይህ ዝበት በራሱ መርህን ተጠዬቅ የሚያሰኝ ነው ለወደፊት። በዛ ላይ በሁሉም የበላይ የሆነ ልዕልናዊ አቅም አለ ከ4%። ይህን ወደ ተመጠነው ሁኔታ ለማምጣት አንተም አታስፈልግም ተብሎ አይሆንም። ለዚህ ፈቃጅም ነሺም አቅም ነው። የመንፈሱን አቅም ቤሳ ቤሲቲ ሳያወጣ በነፃ ለመሸለም ያልቻለ የነፃነት ፈላጊ ሌላ የኤዶም ጸጋን ይመኛል።

መጀመሪያ የማይከፈልበትን የመንፈስ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃድ ይኑር፤ ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ። መደገፍ ቢቀር ባንበጠብጥ፤ በራሳችን ተግባር ብንጠመድ ምን አለበት? ምን ሥንሰራ ነው ውለን እምናድረው። ጉድፍ ስንለቅም፤ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ዱላ ስናቀብል ነው። ከዬትኛውም ማህብረሰብ መልካም የሆኑ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ መልካም ያልሆኑም ይኖራሉ። ይህም መመጣጠን አለበት። ተጠያቂነቱ በሁሉም መስክ ሊታይ ይገባል። ሰው መሆን ህሊናዊነት ነው። የመኖር ስጋት የሁሉም ዜጋ ሆኗል። ጋንቤላ ላይ ያለው ኦሮሞ „ልጄን ለማን ጥዬ ነው እማልፈው“ እያለ ነው። „የትስ ነው እምቀበረው“ እያለ ነው። „ደም ስትጠጣ ያኖረች መሬት፤ በደም ዝናብ የበቀለ ሰብል ስንበላ የኖርን“ እያተባለ ነው። ይህ መራራ ነገር ነው። ይህን አመጣጥኖ ለመምራት እና የውስጥ ሰላሙን ለመመለስ የግድ ለሌቦች የትንፋሽ ጊዜ መስጠት ግድ ይላል። በስተቀር ቁርሾ በእጥፍ ቀጣይ ነው የሚሆነው። ቁርሾ ከቀጠል በሁሉም ቦታ አንዱ ሌላውን መጨራረሱ አይቀሬ ነው። አደጋ ላይ ነን። ግን … ግን እግዚአብሄር መቼ ይሆን የሚታወቀው? ስላደረገው መልካም ነገርስ መቼ ይሆን ተመስገን የምንለው?

ይህም ሆኖ ኤርትራ ያህል በጎ የማታስብ ጎረቤት አገር አለችብን ይሄ አንድ ይባል፤ ሁለተኛ፣ — የነፃነት ፈላጊው አዲስ ፋስ ገዝቶ የተያዘ የተረዘዘውን ሁሉ ባልራራ አንጀቱ እዬፈለጠው ነው ኔት ላይ፤ ሦስት፣ — ማህበረ ደራጎን ሴራውን አደራጅቶ መሬት ላይ ትንፋሽን ሰቅዞ ይዟል፤ አራት፣ — በራሱ በለውጡ ውስጥ ያሉ ማህል ሰፋሪዎች በዚህ ውጥረት ውስጥ ተሁኖ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የለውጥ መንፈሱ ከሚጠበቀው የጥገናዊ ለውጥ በላይ የላቀ ኢትዮጵያን እናት አገሬ ያለ ድንቅ አዬር ነበረው። ማን አገዘው? ማን ደገፈው? ማን የእኔ አለው? ጥቂት አንድ ሁለት ሦስት የሚባሉ ሙሁራን ንጹህ ልብ ያላቸው፤ ሥልጣን፤ ማህበረ ፍቅረ ማንፌስቶ ምንትሶ ቅብጥርሶ የማይፈልጉ ኢትዮጵያ ደግማ የማታገኛቸው ሊሂቃን ፕ/ አለማዬሁ ገ/ ማርያም፤ ዶር ፈቃዱ በቀለ፤ ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ፤ ዶር ፈቃዱ እሸቴ፤ አቶ የሱፍ ያሲን በቃ ሌላ ማን? ከድህረ ገጽ ዘሃበሻ እና ሳተናው በትጋት አዳዲስ ሃሳቦችን ሁሉንም በእኩልነት የደጋፊውንም የተቃዋሚውንም ድምጽ ሲያስተነግዱ ታዝቢያለሁኝ።

በተደራጀ በተቀነባበረ ሁኔታ ማዕቱን ስናፈስ ነው የከረምነው። ህዝብን ለመምራት ከህዝብ መሃል ተገኝቶ የህዝብ ስሜት ማጥናት በራሱ ወንጀል ነው፤ ሽርሽር የጫጉላ ጊዜ፤ ድግስ ነው ነው የሚባለው። በቃ። የቀድሞ ሰዎችም ግብር ማብላት ልማዳቸው ነው። ስለሆነም ወደ ትፊውታችን ምልሰት እየተደረገ ነው። ቤተ መንግሥት የጥቂታን ሳይሆን የሁሉም ነው መሰረተ ሃሳቡ።

ዕድሜ ልክ እኛ ውጪ አገር ስብሰባ ስንጠራ ሽርሽር የጫጉላ ጊዜ አልነበረም? ማታ ላይም መንፈሳችን ስናዝናናው ያ የሱባዔ ጊዜ ነበር። በ27 ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ ላይ ከጥግ እስከ ጥግ ኢትዮጵያውያን ለማድመጥ የተሄደበት መንገድ ቢያንስ የወገኖቻችን ጠረን ለማድመጥ፤ ለእኛ ለአገር ፍቅር እራህብተኞች ምን ማለት እንደሆን ራሱ ሳንጠዬቅ ያ ተዘሎ የሚዲያ አቅም ያላቸው እንዳሻቸው ሲተረትሩት ነው የከረሙት። ተፎካካሪዎች የፖለቲካ ድርጅት መሪነታቸው አቻዊ ሆኖ አቅሙን አጠናክሮ በውስጥ ድርጅቱን ማብቀል ሲጋባ፤ የጠ/ ሚር ጉዞ ክንውን ዘጋቢ እና ገምጋሚ ሆነው ነው ያረፉት።

ማዘዝም መታዘዘም ባደራጀኽው፤ በደከመክብት፤ ባበቀልከው፤ በመረጥከው ማሳ እንጂ  ዘው ብሎ ገብቶ ሰብሌ ካልሆንክ፤ እኔ ካልመራሁህ፤ ይህን አድርግ // አታዳርግ እዛው ሥራ ሰርትህ ጠብቅን ምን ያለተዘረዘረ ጉድ አለ … ዛሬ ሁሉ ደክሞታል። አቅም አለኝ አለደከመኝም የሚል ካለ ደግሞ በራሱ አቅም ወጥቶ አዲስ ሃሳብ እብቅሎ ሰብልን መሰብሰብ ጌታ የለበትም። አሁን አቦ በቀለ ገርባ ጎንደሬዎች ቢፈቅዱልኝ የትግላቸው አጋራ ብሆን የሚል ውሃ ያልነካው ንጹህ ሃሳብ አብቅለዋል። ኧረ መከራን እቀበላለሁ ላለ ወገናችን ደግሞ የከብር አባልነቱን ማን ወስዶት ጸሎቱንስ ማን ነፍጎት ነው መልሱ።

ብቻ እንኳንም ከጎንደር የአማራ ተጋድሎ በፊት አልሆነ። ምክንያቱም የዚያን አብዮት የማሰብ ልቅና፤ ሚስጥራዊ የበቃ የአብሮነት ሥልጣኔ፤ የተዋጣለት የፍቅራዊነት ንጡር ሃብቱን አቅም ልክ ስለሚልጠው። አቦ በቀለ ገርባ በግላቸው ያላቸውን የመሆን ፈቃድ አሰምተዋል። ግልጽ አቋማቸውንም ገልጸዋል። ድሮም ያከበራቸው ህዝብ ነው ጠረናቸው ሳያውቀው፤ ዛሬም ያነን አሳድገው በውስጥ ሊደመጥ የሚገባ ዕውነት ሆነዋል። አቅምን ማምጣት በብልጠት ሳይሆን በቅንነት ነው መሆን የሚገባው። ያለው አይቸገረም አጋጣሚውን ሲያገኝ ያፈልቀዋል። ዕንቁ ነውና።

 • ግራሞት።

አሁን በቅርቡ „ለማ እና ገዱን ልንደግፋቸው ይገባል፤ ለውጡን እኛ ካለመጣን አንልም“ የሚል መርህ ተኮር ነገር እዚህ ሳተናው ላይ አንብቤያለሁኝ ከግንቦት 7። የት ነበር ግንቦት 7 በሚዲያው፤ በጸሐፍቱ፤ በጋዜጠኞቹ፤ በተንታኙ የነበረው ያን ያህል ጉግስ፤ የአቶ ኤርምያስ ለገሰ ኢሳት ላይ „ለማም ገዱም ገዳይ ናቸውስ“ ያ አፍርሽ መንፈስ እንደዛ ኔት ላይ ሲፈረሽ? ኦህዴድ እንደ ድርጅት አቦ ለማ መግርሳ ወደ ፊት ሲመጡ ምንድን ነው የነበረው፤ ድምጹን አጥፍቶ የእጅ ውዝዋዜው ቢታይ እኮ ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ ስንት የሰው ዓይነት ነው ያለን ያሰኛል? ለአንድ ለማከብረው የኢሜል ወዳጄ „ጋዜጠኛን ሀን“ ድምጹን አጥፍተህ የእጅ እንቅስቃሴውን ብቻ እዬው ብዬ ልኬለት ነበር። ከዚያ ቀጥሎ ዶር አብይ አህመድ ተዞረ። ወደ ፊት ሲመጡማ ምንድን ነው የነበረው? አብይ ኬኛ! ከክፍል አንድ እስከ ስድስት „ህሊና“ በጣም ብዙ ጹሑፎች የጻፍኩት እኮ በዚህ ምክንያት ነው። ሃግ የሚል፤ ተዉ የሚል መሪም ድርጅትም በመጥፋቱ። አይደለም ከተጀመረ ለወራት የዘለቀ ውጊያ ቀርቶ የአንዲት ሰከንድ የቃል ወለምታ ስንት ነገር እንደሚበክል አይታወቅም። ህዝብ መንፈሱ ተስፋ ሲያደርግ፤ ነፍሰ ጡር እናቶች በሰላም አምጠው ይገላገላሉ። እኔ ወያኔ ሃርነት ጎንደር ሊጋባ ዋዜማው ላይ ምጥ ላይ የነበረች እናቴ ብላት ይሻለኛል የአንደኛ ደራጃ መምህሬ የነበረች በስጋት እያማጠች አልፋለች። ልጁ ተረፈ። እናቴ ስተንገርኝ በህወቴ እንዲህ አይነት መረባባሽ አይቼ አላውቅም ነበር ያለችኝ። ጭንቀት እኮ ራስን መምራት ያቅታል። ሰው ሲደነግጥ የሚይዘውን የሚጨብጠውን ነው የሚያጣው፤ እና በዬቀኑ ያን ያህል ሚዲያ ላይ ጭንቅ መላክ መርዝ የመላክ ያህል ነበር። በዚህ ማህል ልጆችም አክሰሱ ያላቸው ያዳምጡታል። ፍርሻ እኮ ህግ የለውም። የምንጥብቀው ቀርቶ የማንጠብቀው ሰቀቀን ነው የሚመጣው። ልመናው ያ ነው የነበረው …

የትጥቅ ትግል አንዱ አማራጬ ነው ያለ ድርጅት በሚመራው ሚዲያ „ለማ እና ገዱ ገዳይ ነው“ ብለህ ህዝብ እንዳይደግፋቸው ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ሰርተህ አሁን ይሄ ማለት ምን ማለት ነው? አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈቅድም። መሽቷል። ውጪ አገር በሚዲያው በሽታሽቶሽ የተበተነው አቅም፤ አቅሙን በስውር ሲበሉ ሲገዘግዙ የኖሩ ሰንት ሰዎች ናቸው ያሉት?

የት አላችሁ ብሎ ደጋፊዎቹን ፊት ለፊት ስንሟገትለት የኖርነውን ጠይቆን፤ ሰብስቦን፤ አነጋግሮን፤ አይዛችሁ ብሎን ያውቃልን ግንቦት 7? ለመሆኑ ሥማችን ያውቀዋልን? በእሱ ምክንያት የወጣልነን አዲሱን ማንነት „ጉዲት“ የተባለ ሥም የተሰጠን ኢትዮጵያዊ ዜጎቹን። ለመሆኑ ሰው ስለሚለውስ ክብር አለውን? ዛሬ አንድ የሀገር መሪ እታች ድረስ ወርደው ህዝብን ሲያዳምጡ ነውር ሆነባቸው። እኛ ስላለደርገነው ብቻ። አቅም እኮ ሜዳ ላይ አይታፈስም ህዝብን የአንተ ነኝ ብለህ ተረገጡን መስጠት ብቻ ሳይሆን ዱላውን ለመቻል መሳናዳት ይጠይቃል። ምነው አቅሙ ጊዜው በኖራቸው እና ሙሁራንን አዲስ አበባ ላይ ራሳቸው ሰብሳቢ ሆነው ሰብብስበው ባነጋገሩ። ያን ያህል ካድሬዎች በሚሰበስቡት ስብሳባ ላይ ሃሳባቸውን የሚገልጹት ሊሂቃን በፍጥጫና በእርግጫ እንዲያቆርጡ ባልተደረገ ነበር። በአዲሶቹ የወያኔ ሃርነት ምላጮች ትንተና ተብዬውም በመርዝ ተስፋው ባልተደለዘ ነበር። እኔ አዲስ አበባ ላይ የተካሄዱ አገራዊ ስብሰባዎች ዓላማቸው ተስፋን ቀሚዎች ሆነው ነው ያገኘኋዋቸው። ስለሆነም በዬክልሉ በጠ/ ሚሩ ሰብሳቢነት የተካሄዱ ስብሰባዎች ዕንቁ ናቸው። ካድሬያዊ መንፈስ የሌለባቸው። ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ፍላጎት በእጅጉ የራቁ በብዙ ኪሎሜትር። የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና የአዲስ አባባ ከተማው ግን አሳንጋላ ነበር። ያው የተመለደው ማለገጥ ዴሞክራሲያው ማዕከላዊነት የዘፈነበት ቤተ ዋይታ።

 • እውቅና።

ሌላው „ኢትጵያዊነት ሱስ ነው“ ስላለለት ነው ሰማያዊ ስለ አርበኛ አንደርጋቸው ጽጌ አዲስ አበባ ላይ ስብሰባ አካሄደ የሚልም አንብቤያለሁኝ። እንኳንስ በሥሙ ስብሰባ በዚህ ዘመን „ጽጌ“ የሚባል አባት አንዳርጋቸው የሚል ልጅ ማውጣት በማይፈቀድለት ወቅት። ስለ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ፊት ለፊት ወጥቶ መቀቀል ቅዱስ ቁርባን መስሎታል ግንቦት 7? ራዲዮ ፕሮግራሜ የቆመው „ላንቺ ነው ኢትዮጵያ“ መግቢያ ላይ ስለምጠቀም ነው። ስንት ኑሯችን እንዳፈነቀለው አያውቀውምን ግንቦት 7? በእትብቴ መንደር የሰው እርድ አዬር ላይ ከፍቶ፤ ከዚህ ደግሞ የተሻለ የተስፋ ብርሃን ይሆናል የተባለው መሪው ሲታሰር ቢያንስ በሳምንት ሁለት ቀን ማንሳት የተገባ ስለነበር ስንት የሽብር የመንፈስ እንደ ደረስ የት አውቆን? ቀድሞ ነገር በመንፈስ አቅም ስለሚባለው ጥበብ ግንቦት 7 አልነበረበትም።

የግድ ነፃነት መፈለግ በማንፌሰቶ ከፈን መጠቅልል ማለት ነው። አሁን ነው አርበኛ አንዳርጋቸው እስር መፈታት ቀን ጊዜ ይቆጠራል፤ ሞት የተፈረደበት አቡነ ጵጥሮስ እኮ ነው። ለዛውም አሁን ዘነዘናውን ስለማግኘታቻን እርግጥ የሚያደርግ ነገር የለም። ሴራ ስለሚጋለጥ። በዓመት አንዲት ቀን ሥሙ የማይነሳው ምንዱብ። አጀንዳ ሲጠፋ አጀንዳ ዛሬ ሆነ። አሁን ደግሞ እሱን ከነነፍሱ ለማግኘት ሰጥቶ በመቀበል የጥገናዊ ለውጥ መርህ እሳት የላሱ ሌቦች ከነበረው መረባቸው ጋር የተቋረጣው እንዲቀጥል ያስፈልግ ነበር፤ ሆኗል። አንዱን መምረጥ ነው። ወይ አንዲን ወይ ሌቦቹ ሳይፈቱ እንዲቀሩ። ሁለት እግር አለኝ ተብሎ በአንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ አይወጣም። ይህ ዕድል የሚገኘው ቃብቲ ላይ ከፍትን የተባለው የወታደራዊ ማስልጠኛ ጣቢያ¡ በ እጥፍ ድርብ ወታዳሩን አምርቶ፤ በዝናር ሙሉ ወኔ እና መትረዬሱ በአፋር አድርጎ አዋሽን ቆርጦ አራት ኪሎ በመንፈስ ሰረገላ ቁብ ሲል ብቻ ነው። ሌባም ፍርዱን የሚያገኘው የአራት ኪሎ ህልሙም የሚወራረደው። ለዚህም ያበቃው የቄሮ እና የአማራ ተጋድሎ አብዮት ነው እንጂ ያን ደንዳ የማህበረ ሳኦልን በር የሚደፍራት አንድስም እንኳን አቅም አለነበረም። ይህ ሁሉ በዬዕለቱ የሚደመጠው የምሥራች ለወያኔ ሃርነት መርዶ እና ራድ የላከው የዛ 50 ሺህ ልጁን ለእስር ቤት የገበረው ሺዎቹን ነፍሱን የሰጠው የሁለቱ ተጋድሎ ፍሬ ነው። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የነበረው መታወክም እነዚህ ሁለት ታጋድሎዎች ያስገኗቸው ፍሬዎችን ለመቀልበስ ነው። በቅንጅት እንደ ተለመደው … ድካሙ ተበትኖ እንዲቀር ነበር የተሰላው …

 • መባጃው።

የተከረመው ክራሞት እኮ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እርግፍ ተብሎ ተረስቶ በአብይ በለማ በገዱ በአንባቸው መንፈስ ላይ ነበር አሉታዊ ዘመቻው። አቃቂሩ ሲደረት የተከረመው። እነሱ ከዛ ከወያኔ ሃርነት ጋር ጉሩቦ ለጉሩቦ ተናንቀው እስረኛ ሲያስለቅቁ፤ የሥልጣን ሹም ሽር ሲያስደርጉ እንኳን የተፈቱት እንኳን ሽራፊ ዕውቅና ለመስጠት ፈቃዶኞች አይደሉም። የትሜና የተወረውሩት የነፃነት አርበኞች በክብር ከሚወዷቸው ህዝብ ጋር እንዲገናኙ ሲደረግ ምንም ነበር። የወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ ከእሳት የገባ ፕላስቲክ ሆኖ የሚይዘውን የሚጨብጠውን ሲያጣ እኛ ያ የሥነ – ልቡና ልቅና የፈጥረን አዲሱ ለውጥ ጋር ከጎኑ ልንቆም አልቻልነም። እስኪ ይነገረኝ ከዛ የሲኦል የበቀል ጉደጓድ የወጣ አንድ የነፃነት አርበኛ አብይን አይዞህ ከጎንህ ነን ያለነው በአደባባይ ያለ ካለ ይምጣ? ማን አለ? ከማሳጣት በስተቀር። ያልተገኘውን ነገር አጎልብቶ አጎልምሶ ከመግለጽ በስተቀር። ፈጠሪ ለሰጠው መልካም ነገር ምስጋና ካጣ ሊቀማም መብቱ ነው እራሱ አዶናይ። ክብር እኮ የፈጣሪ እንጂ የሰው ሥራ አይደለም። ስኬትም እንዲሁ። ይህን ዕድልስ ምነው የ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ወላጅ አባት፤ ልጆች፤ ባለቤቱ እና ቤተሰቡ ባገኘው በነበረ። እኔ ስጋት አለብኝ … የወያኔ ብቻ አቅም አይደለም ይህን አንበሳ አሳልፎ ያሰጠው፤ አሁንም ከ አንበሳ መንገጋ ስጋ የመንጠቅ አህል ነው? ይቻላልን? አዳኖይ ይመልሰው። ቀንቶት ያ ሙሉሰው ለ ዓይነ ሥጋ ቢበቃ የሆነውን ሁሉ ዝቀሹ ተመክሮው በመቻል ይችለዋል። ስለዚህም ምህረቱ በሁሉም አቅጣጫ ይሁን እንላለን እኔ እና ብዕሬ እና እኔ። ሶሻሊዝም እና እኛ እንዲህ እና እንዲያ ነው … አንዱን አስውጦ ራስን ማውጣት። ለዚህ ነው እኔ አቦ ለማ መግርሳን የምዕት ቅኔ ያላኳቸው። እናትም ዘመንም እሳቸውን የመሰለ የምህረት ሰማይ አልፈጠረችም።

 • እም!

ዶቼቨሌ እና ቪኦኤ በሁለት ጎራ ላይ ነው ቸክለው ነበር የከራረሙት። የሰከኑ የመኖራቸውን ያህል የሚያጣጥሉ፤ ምክንያት እዬፈለጉ የሚሰላቁም ተደምጠዋል። የለማ የአብይ የገዱ መንፈስ እኮ የፊናንስ፤ የጦር ሃይል አቅም እምጡ አላለም። እውነት  ለኢትዮጵያ የሚታሰብ ከሆነ፤ በቻፕተር ተደራጅታችሁ ገንዘብ አጠራቅማችሁ እርዱኝ አላለም። በመንፈስ መደገፍ ብቻ ነው የጠዬቀው። መልካም ነገርን አለመግለጽ መብቴ ነው መጠዬቅም መብቴ ነው ምን ማለት ነው ይሄ? አገር እኮ፤ ህዝብ እኮ የአሽዋ ቤት አይደለም። በያንዳንዱ ቃል ውስጥ መደርመስም ማቋጥቆጥቆጥም አለ። ቁልጭ ያለው ነገር የህዝብ ሳቅን አልናፈቅነውም። ማን በደልክ? ማን ተበደልክ? እያልን ቁርሾ እዬለቃቀምን እርስ በርስ መተላለቅ፤ የበላይ ሆኖ የኖረው መንፈስ መሬት ተነጥፎ ደግሞ ያው የተለመደው ዱላውን በዙር እንዲቀምስ ነው ፍላጎታችን። መቧከሱ እንዲቀጥል። የእልቂት ታንቡር እና መለከት መናፈቅ። በዚህ ውስጥ የበዳይም የተባዳይም እናት አለች አላዛሯ ኢትዮጵያ። ስንት ጊዜ ይቃጠል የማህጸን አንጀት። ሺዎች ሲፈቱ ደግሞ 4 ሚሊዮኑ ደግሞ መከዘን አለበት፤ ለዛውም በዘር ተነጥሎ። ዓይን ያወጣ ዓይኑ ይውጣ እንደሚለው የሃሞራቢ ህግ። አቦ ሌንጮ ለታን ተቀብልህ የወያኔ ሃርነት ፊታውራሪዎችን አስራለሁ ብትል አይሆንም። የጥገናዊ ለውጥ ባህሪም አይፈቅድም።

አንዷን ፈርኦኒት እና ሌባ በሚ/ር ደረጃ ላይ አስቀምጠህ ለዛውም ጉሮሮ ላይ ሰንቅረህ ገና ሙግት አለባቸው ከእኔ ጋር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በዚህ ጉዳይ አንላቀቅም፤ አንዷን ሌባ እና ፈርኦኒት ማግለል አይቻልም። ሁሉንም ለማግለል ደግሞ አንተ ራስህ ሞግተህ ያመጣኸው ለውጥ አይደለም። መሪዎች አልነበራቸው ህዝባዊ አብዮቶች። ዋጋ አሳጥተን ለወያኔ የበቀል ገጀሞ አሰናድተን በኮፒ ራይ ስናምሳቸው ነበር የኖረንው የራሳችን ወገኖች ግን ጥግ አስይዘን፤ ለወያኔ ሃርነትም በሥማችን የበቀል ቁርሾ ኩትኩት ያሰናዳንለት ናቸው የአማራ የህልውና ተጋድሎና የኦሮሞ ንቅናቄ አብዮት ያመጡት ለውጥ ነው። ለውጡን ማድመጥ መምራት የቻሉ ደግሞ ተፈጠሩ። እኛ ኔት ላይ ስንፋለም ሾለክን። እንዲያውም ዕድሉን በአግባቡ ስለተያዘ እንጂ ወያኔ ሃርነት ትግራይም መዳፉ ላይ ለማስቀመጥ ዕድሉ ሁሉ ነበረው። ምን አለን እኛ የምንመክትበት ሰራዊት? ምን? የህሊና አቅም እንዲህ 84% ሆ! ብሎ የሚያሰደግፍ፤ የአዲስ ሃሳብ ፍልቅት? እኮ ምን?

በዚህ ላይ አቤቶ ኤርትራም አለች። ኤርትራ አጀንዳ አይደለችም። በታሪኳ ገብታ የማታምስበት ድርጅት ቢኖር ኦህዴድ ብቻ ነው፤ አሁን ባለው ሁኔታ ነገ አይታወቅም። ይህ የሰማይ ስጦታ ነው ልብ ላለው በዚህ አዬር ከቀጠለ። ጤና ስለማትሰጥው አገር አይታሰብም። ሌላ ሥራ የላትም ኤርትራ። ይህ ዕድል ልብ ላለው የሱባኤ ውጤትም ነበር። የኢትዮጵያ ቀና ማለት መቼውንም ስለማትሻ – እትጌ ኤርትራ። ኢትዮጵያ በሙሉ ሪሶርሷ አቅም ካገኘች ኤርትራን ማን ሲያስታውሳት። የተንጣለለ ወደብ ብቻውን አራጣ ይዛ አይታዋለች። ፈጣሪ ካልተጨመረበት የፈለገ ዓይነት ትምክህት አሽዋ ነው።

 • ለውጥ ተፈልጎ ለውጥ ተሸሽቶ።

በፍጹም ሁኔታ እንደ ሰው ቁጭ አድርገን ልገምግምህ ብንል የምንችለው አንድ አይደለም ሁለት አይደለም 43 ዓመት ሙሉ ራሱን በሁሉም መልክ ካደራጀ 666 ቡድን ጋር ተጋድሎ እዬተደረገ እኛ የገበርዲን ሽርሽር ላይ ነበር የከራረምነው። ወይ እኛ አቅም የለን፤ የሚችሉትን ሊያደርጉ የፈቀዱ ሲፈጠሩ ደግሞ ቀስቱን አነጣጠርን እንደ ለመደብን ውጊያ ላይ። ተጨማሪ ደም፤ ተጨማሪ ብጥብጥ ናፈቀን። ቀድሞ ነገር ዶር አብይ አህመድን ኢትዮጵያዊ አድርገን የራሳችን ወገን አድርገን ተቀብለናቸዋልን? ለመሆኑ ወገናችን ናቸው ብለናልን? ከውጭ አገር የሄዱ የሌላ አገር ዜጋ እኮ ነው ያደረግናቸው ልክ እንደ ደንቢ ዶሎ። ስለምን? ስለሚበልጡ ሙሉ እዮራዊ አቅም ስላላቸው። በቃ ይሄው ነው። ህዝብ አታነጋግር እንደ ድንጊያ ቢሮህን ዘግተህ ተቀመጥ እኮ ነው ጉዳዩ። ችለታህን ሰው አይወቅ የጋን ውስጥ መብራት ሁን ነበር ዘመቻው። በቅናት ሲያሳብድን የከረመው ይሄው ነው። አሁን ፖለቲካኛ ያልነበረው ሰው ነው በመደበኛ ንግግራቸውን ቃል በቃል እያደማጠው ያለው። ምክንያቱም ህሊናን በሁለገብ ዕወቀት የሚያበለጽግ ነፃ የአየር ላይ ት/ ቤት ስለሆነ። ስብከተ ወንጌል ነው።

 • ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ!

ኢትዮጵውያን ወገኖቼን በቀዬው እያገኘሁዋቸው ነው። አሁን ደግሞ ውጪ ያለችሁትን ላይ እፍልጋለሁኝ እከሌ ተከሌ ሳይባል፤ ከፈቀዳችሁልኝ ከእናንተ በላይ የሚበልጥ ጉዳይ የለም እና ልያቻሁ ነው የአሁን ጥያቄ። ለዛውም „ አታብዙት ይህን የነፍጠኝ ሰንደቅዓላማ“ የሚበላውን የጣሰ በዛ በልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ብሄራዊ ሸማችን በሚያሸበረቀው ትዕይነት የዬዓመቱ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ለማዬት የናፈቀ መንፈስ ነው። ፍቅርን መሻት መልካምነት ነው። ይህን ዕድል ልጠብቅ ብል አንድ ዓመት ይቃጠላል። አጋጣሚው ተገጣጥሟል መጋቢት እና ነሃሴ ነው ነገርዬው። በማህልም ሳንገናኝ የሚሆነው አይታወቅም ነው ጉዳዩ። ከሳውዲ ሲመለሱ በቀጥታ የሄዱት ዶር ምህረት ደበበ ከሰበሰቡት መንፈሳዊ የህሊና የንጥህና ማስጠበቂያ አዳራሽ ነበር። „ሳላገኛችሁ ትሄዳላችሁ ብዬ፤ ታመልጡኝ አላችሁ ብዬ ነበር። ቆኛችሁኝ እግዚአብሄር ያክበርልኝ!“ ነበር ያሉት ድካማቸውን ገፍተው ፈገግታ ለግሰው። ያ ቅን ማህበረሰብ ደግሞ ልቡን፤ ህሊናውን ሸልሟቸዋል። „ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል የሚሉት አቮውም ለዚህ ነው። በዛ ዓራትዓይናማ የንግግር ጥበባቸው ተስፋን የሰነቀ የልብ መንገድ ነበር የከፈቱት። ዕድሉን ለመጠቀም ማሰብ ብልህነት ነው። ሰው የህይወቱ ቀጣይነት በመዳፉ የለም። ግራ ቀኝ ሴራ በጣምራ አስፍስፎ ጦሩን መዞም እዬጠበቀ ነው። በፆም በጸሎት እባክህን ይህን ሰው እንደሚሆን አድርግልን … የሚል አቅሙ ሽውህራር የበላውም አይጠፋም። መመጠን ካልተቻለ ይሄው ነው ጥቃት ማቀድ። በዛ ላይ ውጪ አገር እኮ ተለያይተናል። ማን ማንን ያምናል ዛሬ? ማን ሞኝ አለ ቤቱንም ልቡንም ከፍቶ የሚያስረክብ።

በስልክ እኮ ልብ ለልብ ከቀረ ስንት ጊዜው ነው። መቅጃ አዛጋጅተው ነው የሚደውሉት። ፈጣሪ በዬግላችን የሰጠን ነፃነት በዬፌርማታው ቀማኛው ብዙ ነው። ሰው በኢሜል ሲገናኝ አይተማመንም። ያ የመንፈስ የህሊና የቃል ዕዳ ነው። ሰው ሌላውን ሲያምነው ነው የውስጡን የሚነግረው ይሄ ይተብሃል ቀርቷል ዛሬ። አጋጣሚ ተጠብቆ ማጥቂያ እና ማስጠቂያ ነው። በተለይ ያ ሰው ጥሩ አጋጣሚ ከኖረው ያችን መዘዝ ተደርጋ ይከሰስበታል፤ ይወገዘብታል፤ ይገለልበታል። የተሰጠው ከበሬታንም ሙጃ እንዲውጠው ይደረጋል። በስውሩ መረብ ያለውንማ አማኑኤል ብቻ ነው የሚያውቀው ስንት ዜጋ ማህበራዊ ህይወቱ እንደ ከሰለ። ፍርዱን ይጠብቅ እያንዳንዱ እስተ ልጅ ልጁ ድረስ።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ኢትዮጵያ ከብራ በምትንግሥበት ጃኗዋ ዕስር ባላታወጀበት፤ ድምፆዋ ከፍ ብሎ በዜማ በሚደመጥበት አገር የጠማኝን ፍቅር መጥቼ ላጣጥመው ከወገኖቼ ጋር ነው። ለእኔ እናንተ „አሸባሬ“ ምንትሶ ቅብጥሮስ አይደላችሁም ናፍቆቶቼ ናችሁ ነው አብዩ ጉዳይ። ሲያሰኛቸሁም ውቁኝ ዱላውን የምችልበት ትክሻ አመቻችቼ እመጣለሁ ከፈቀዳችሁልኝ፤ ራስን ዝቅ ያደረገ ትህትናዊ ጥያቄ ነው። ክፋት የለውም።

ለእኛ ሰውና ሰው፤ መንግሥትና ህዝብ ሲገናኝ ያመናል። ወያኔም በዘጠኝ መንግሥት የሸነሸናት ኢትዮጵን፤ በ100 ሚሊዮን አሉታዊ ኢጎ የከዘነን ለዚህ ነበር። እኛ ግን ይህ ቀን አስበን በዬዓመቱ ስብሰባ እያዘጋጅን ኖረንበታል። ለእኛ የሚፈቀደው መንፈስ ለሌለው ባዕድ ይሁን ነው። ግን እኛ ምኖች ነን? የቅናትም አለው ዓይነት። የምቀኝነትም አለው ዓይነት። ይሄ እኮ እኛ ያደራጀነው፤ የደከምንበት፤ በእኛ ማንፌስቶ የሚመራ አይደለም። እኛ ሳንፈጠር የተፈጠረ የራሱ መርህ ያለው ስፖርታዊ ድርጅት ነው። ስፖርት ደግሞ ፍቅር ነው ተልዕኮው።፡ሌላ ቦታ መርኽ ይጠበቅ ከሆነም ይሄም አያስኬድም። ለእኛ ሲሆን አይሰራም ለሌላ ሲሆን መርህ ይሰራል። „አማራ ተጋድሎ“ ብሎ የወጣው እኮ ህዝብ ነው። ያ የሚሊዮኖች ድምጽ መርሁ ይከበር የለም። ከሚሊዮኖች ፈቃድ የአንድ ሰው ቀንጣ ትዕዛዝ ለእኛ ህሊና ገዢያችን ዳዊታችን ነው። መብት እንጂ የግዴታ ህግጋት እንዲያስተዳደረን አያሻንም። ሰው ይታዘባል አለማለት።

ምን አለ ሰው እና ሰው ቢገናኝ። ምን አለ መሪ እና ህዝብ ቢገናኝ። አማራ እና ኦሮሞ በባህርዳር ላይ ሲገናኙ የካድሬ ስብሰባ ነው ነበር የተባለው። ያ እኮ ነው ለዛሬ የመተንፈሻ ቧንቧ የሆነው። ከቅንጅት በኋዋላ እኮ የማናውቀው ዕዳ ተሸክመን ቀበሪ አልባ እኮ ነው ያለነው። ልጆች እኮ የአገራችን ሰዎች የሚሏቸው በዬጓራው ያሉትን እንደ አቅሪያባቸው ነው። ያን ጊዜ ልጅ የነበሩት ዛሬ አድገዋል፤ ከዛ በኋዋላ ተወልደው ያደጉትን እኔ አላውቃቸውም። ተበትነናል እኮ። በሦስት መሪዎች ከሦስት ተሰነጣጥቀን እንደ ጠላት ነው የምንተያዬው። በሃይማኖቱም ይሄው ነው። የውጪዉ፤ የአገር ውስጡ፤ የማህሉ ሦስት። እኔ አሁን ከሁሉም አልሄድም። ለዛውም ወንድሜ ሙሉ አቅሙን የሚያፈስበት የውጩ ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ። ስለምን? እማውቃት ቤተክርስትያን አንድ ብቻ ናት። አንዲት ትንሽ አገር ሲዊዝ ሦስት የሰባካ ጉባኤ ነው ያለው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። እና ሥርጉተ የት ትሁን? ሦስት አካል የለኝም ያለኝ አንድ አካል፤ አንድ ገጽ ነው። ከ አንዱ ሂዳ ከሌላው ብትቀር ደመ መራራ ናት። ስለዚህ እኔ ከውጪ አገር የተዋህዶ ቤተክርስትያን አንድ በመሆነቸው አንድነታቸውም ታምር ከሰራው የሌላ አገር ተዋህዶዎች እሄዳለሁኝ ዓውደ ዓመት ሲሆን አቅም ሲኖረኝ። በቃ። ገዳማት በተወሰነ ጊዜ እሄዳለሁኝ። ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰብሳቢ አልባ እንደተበተነ እኮ ነው ያለው።

 • የክብር ሙቀት።

ዛሬ ያ አቧራ ላይ የወደቀው የፓን አፍሪካ የዓለም ማህበር መሥራች አቅሟ ወግ ደርሶት ኬንያ ላይ ኢትዮጵያ እንደዛ ስትከብር፤ ስትንገሥ ለነፃነት ራህብተኞች እሾኽችን ነው። ያን ያህል በግርማ እና በሞገስ አፈር ላይ የተጠቀጠቀው ኢትዮጵያ ኬንያ ላይ ትንሳኤዊ ከብረ ልዕልናዋ ሲታወጅ ባዕዳችን ነው። አጀንዳችን አልሆነም። ስለምን? የአማራ እና የኦሮሞ ተጋድሎዎችን ውጤትን ማድመጥም፤ ማዬትም ስለማንፈቅድ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ የራሴ ድል ነው ብሎ ካድሬዎቹን አሰማርቶ በአፈረሳት ኢትዮጵያ ላይ የከንቱነት ሸቀጥ ቤት ከፍቶ፤ ዓይኑን በጥሬጨው አሽቶ ፊት ለፊት ሲሟገት፤ እኛ በተለያዬ ሁኔታ የተሳደድንበት ኢትጵያዊነት ከፍ ብሎ ሲልቅ የድላችን፤ የድካማችን አካል ልናደርገው አልፈቀድንም።  አላዛሯ ኢትዮጵያ ክብርት ኢትዮጵያ ስትሆነ ፍሳሃችን ሊሆን ሲገባ ሌላ ስንጠቃ እናመርታለን።

ስንት ሰው ነው ከሲኦል ጉድጓድ ኑሮ ወጥቶ ከቤተሰቡ ጋር የተቀላቀለው? ስንት ወገን ነው ስደት ላይ ታስሮ የነበረው ተፈቶ ለአገሩ መሬት የበቃው፤ ያ ዝም ብሎ ከመሬት የታፈስ፤ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ገዢዎች በደጋፊዎቻቸው ፈቃድ የተከወነ ድል ነውን? ኤርትራ ላይ በዘመነ ደርግ ጊዜ የታሰሩት እንኳን ከዛው ነው ያሉት፤ ከዛም በኋዋላ ትክ የሌላቸው መኮንነኖች ሁሉ ነፃነት እናመጣልን ብለው  የኤርትራ የሴራ ዋሻ ብልቷቻውል ግን የኤርትራ መንግሥት ተጠይቆ ያውቃልን? አጀንዳ ሆነው ወገኖቻችን ያውቃሉን? ዛሬ ሱዳን፤ ኬንያ፤ ሳውዲ አርብያ በተገኙበት ሁሉ እርዳታችሁን ሳይሆን ክብራችን መልሱ ብለው የሰማይ ታምር ባለቅኔው ጠ/ ሚር ለውጤት ሲበቁ የእኛ አይደለም። የአንድ ሰው ነፍስ እኮ አንድ ቀን አይመረትም።

ያ ጀግና ኮ/ ደመቀ ዘውዴ ክብሩ ሳይደፈር ከእስር መውጣቱ ሳይሆን በስብሰባ ጥሪ አልደረሰውም ሌላው ሙግት ነበር በጎንደሩ ጉባኤ ያዳመጥኩት። ትልቁን ነገር ትተን። ከቁም እስር ይፈታ ነው መሰረታዊ ጉዳይ ሊሆን የሚገባው። ሺህ ሌባ ይፈታ አርበኛ አንዳርጋቸው ለልጆቹ ነፍሱ ይትረፍ። መከራውን ለተጋራች ለትዳሩ ይኑርላት። የሺብሬ እናት ምን ተጠቀመች? ማን ያስታውሳታል? የእኔ ስጋት ሌላ ነው ከእነ ሙሉ አካሉ መንፈሱ ያስረክቡን ይሆን? ወይንስ የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ቀደም ብዬ እንደ ፈራሁት ይሆን ነው የሚስጨንቀኝ። በእሱ እሰር ዙሪያ ብዙ ትብትቦች አሉ። ይህ ነው እንጂ ለእኔ ቁም ነገሬ የሌባ መፈታት፤ መሾም መሸለም አይደለም። አርበኛ አንዳርጋቸው እኮ መንፈሱ ጊዜ እና ሁኔታ አላገዛውም ከእኛ ተፈጥሮ እንጂ ከልቡ ብቁ ሰው ነበር ለዬትኛውም ሃላፊነት። መከራን የሚደፈር በመከራ የኖረ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነው ለቂም ማወራረጃ …. እ.

ሌቦች ተፈቱ የግድ ነው። አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ነፍሱን ለማግኘት የእነሱን ሰዎች መፍታት ግድ ይላል። ለዛውም አንድ አጋዚ ምን ሊያደርገው እንደሚችል አይታወቅም። አንድ ሰው በቂ ነው። ባህርዳር ላይ አንድ አጋዚ እኮ ነው 50 ነፍስን የጨፈጨፈው። አንድ ሰው ነው ደራሲ ምስባእከ ወርቁን ቀፎውን ያስረከበን። የጨዋታው ሜዳ እኮ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መዳፍ ውስጥ ነው። አረበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን እስኪ እኔ እተካለሁ የሚል አንድ የፖለቲካ ሊሂቅ ውጪ አገር የሚኖር ይምጣ እና እኔን ይሞግተኝ። ኤርትራ እያለ ነው እኔ አንዳርጋቸው ጽጌ ሽልማታችን ነው ብዬ የጻፍኩት። ዛሬ የሚታዩት ፎቶዎች ሁሉ እኔ ያሳባሰብኳቸው ፎቶዎች የነበሩ ናቸው። ሁለት ቀን ነበር ያገኘሁት ያን ታላቅ ኢትዮጵያዊ በቅንጅት ምሥራታ በሲዊዝ እሱም እኔም ገላጭ ሆነን፤ በፍራንክፈርቱ ስብሰባ እሱ ገላጭ እኔ ሰብሳቢ ሆኜ። ኢሜል /ስልክ ቀጣይ ግንኙነት አላስፈለገኝም። ሥሜን አያውቀውም። ሥሜን ሳልገልጥ ነበር ስብሰባውን የመራሁት። በዛ በሁለት ቀን አቅሙን ሳዬው ልክ እኔን አንደ ፈጠረኝ እንደ ጓድ ገ/ መድህን በርጋ ያለ የድርጅት ብቃት ነበር ያዬሁበት። እኔ ወስጥን ነው ማዬት እምወደው።

ስለሆነም አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ህይወት ለማግኘት ሌባው ሁሉ ቢፈታ ለእኔ ቅጭጭ አይለኝም። ሴራም አለበት የእሱ እስር ዘመን የሚፈትሽው። ይህንንም በተለያዬ ሁኔታ ጽፌበታለሁኝ። ብቻ ያ መከራን የፈቀደ አፈር በልቶ፤ አፈር ለብሶ እንደ ልዑል አለማዬሁ ቴወድሮስ እንደ ወጣ እንዲቀር የተበዬነበት ቅን ዜጋ፤ ብቁ ዜጋ፤ ከበለሃሳቦች እጅ ወጥቶ መከራውን ለተሸከመች የትዳር አጋሩ እና ልጆቹ ለእኔያ ዘመን እንዳሰራቸው ለኖረ አርበኛ አባቱ ይኑርላቸው። እኛማ ወርቃችን መቼ አውቅንበት። እኔ አንዳርጋቸው ጽጌ ሽልማቴ ብዬ የጻፍኩትን ጹሁፍ የሚለጥፍ ድህረ ገጽ እንኳን በወቅቱ አላገኘሁም ነበር። የላኩበትም መድርሱም የተረጋገጠብት የመልሱ ኢሜል በእጄ አለ። ግን ደፍሮ ፖስት ማድረግ አልተቻለም። ለምን? ድንብልብል። ይልቅ ለእስር ከታደረገ በኋዋላ መኖሩን ዘሃበሻ ሳያግደኝ መንፈሱን ሙሉ አስተናግዶልኛል እና አመሰግነዋለሁ በዚኸው አጋጣሚ። ታሪኩም ነው ለድህረ ገጹ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በቀላል የፖለቲካ ትንተና ሰብዕናውን ሆነ ብቃቱን መግለጽ አይቻልም። ውስጡ የሚያበራ ዕንቁ የነበረ ሰው ነው። ከእስር ቢፈታ ይህ ታላቅ ሰው ደስታውም ፍሰሃውም ሁነቱም የተከዱኑ ጠጠርማ ጉዳዮች አሉበት። ስለዚህ እኔ እርግጠኛ የምሆንበት ነገር የለም። ተቀላቅለናል። ማን ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም። የሚያዋጣው ዘግቶ ገዳማዊ ህይወትን አህዱ፤ ክለቱ፤ ሦስቱ … አርባዕቱ … ማለት … ኑ እስክንባል በተፈቀደው ሁኔታ።

 • በለውጡ አራማጆች የተደራጀ የሥነ – ልቦና የጥቃት በረዶ።

ሌላ ይህ ለውጥ ከተጀመረ ጀምሮ ያወረድነው ማዕት በሥነ – ልቦና ላይ ያደረሰው ጫና ግምት ውስጥ አልገባም፤ ለለውጡ አራማጆች በለማ አብይ ገዱ አንባቸው። እነሱን እኮ ሰላማዊ ህይወታቸውን ነበር ያወከነው። ጊዜያቸውን ተሻምተናል። አትኩሮታቸውን በትነነዋል። ተረጋግተው ከአውሬው ሴራ ጋር እንዳይጋፈጡ ተጨማሪ ጫና ፈጥርንባቸውል፤ ለዚህም ታሪክ እንደሚጠይቀን ልብ ልክ ነው። ዳኛው ፈጣሪም አዘቅዝቆ ይመለካታል። ልክ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ኢትዮጵያ ሱማሌ፤ ጨለንቆ፤ ሞያሌ፤ ወልድያ፤ ቤንሻንጉል ላይ እንደ ከፈተው ጣምራ ዘመቻ እኛም በኔት ሞጥረን ማጣጣሉን፤ ማቃለሉን ነበር ተያዬዝነው። አዲሱ ለውጥ ለግብ እንዳይደርስ ታገልነው። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ደግሞ ከ27 ዓመቱ ከነፃነት አርበኛው ሲደርስበት የነበረው ዱላ ተግ ብሎ ካሳ ነው የተሸለመው። የተሰነጠቀው ተገጠም። በስክንት ወቅቱን መከሩበት። ከልባቸው ሆነው ዘከሩ። አቅማቸውን እንደ ገና አሳምረው አደራጁ። አሁን መልሰው በመቋቋም ላይ ናቸው። መቀልበስም ሊኖር እንደሚችል ማሰብም ብልህነት ነው። ሌላ ያልተጠበቁ የጥቃት አደጋዎችም ባልታሰበ መንገድ ሊኖር ይችላል በግልም በጋራም ሽብር።

ቀን ተመልሷል ብሎ ሃሳቡን የገለጠው ሁሉ በተጠና ስልት ከምድረ ገጽ ይጠፋል ለውጡ ካልቀጠለ። እዬተመዘገበ ሊስቱ ተይዟል። በዚህ ማህል ለመጀመሪያ ጊዜ በትረ የቁጥጥጥር ሴል አከረክሪዋ ባልታሰበ ሁኔታ የደቀቀው ኤርትራም የሰላ የደህንነት ስራውን በስንጥቁ ውስጥ ገብቶ ያሻውን ይከውናል። የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ጸሐፊ ማህበረ አቦይ ስብሃት እኮ ናቸው። አቦይ ከሁሉም ለሁሉም ሴራ የተዳራጀ ፖሊሲ ቀማሪ ናቸው። ዘረ ብዙ መረበ ብዙ። ሳጅን በረከት ስምዖን ደግሞ ከሰሞናቱ አንድ ሹመት ጀባ እንዲልላቸው ሌላም ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። ይህም መጠበቅ ድንቅ ነው … አዲስ ነገር ሲፈጠር ያዙኝ ልቀቀኙ ከመንል … ሰከን ያለ ጉዞ፤ የሃይል አሰላላፍን ጥበብ መኖር ለፖለቲካ እርካብ ጠቀሚ ስለሆኑ ፊደል ገበታ እንግዛ … መምራት እንደሚናፍቅ ሁሉ ለመመራትም ናፍቆተኝ መሆን ያስፈልጋል። ልክ እንደ ቀድሞ ጠ/ ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ።

 • የሰው ብርንዶ … ናፋቂነት።

ቀድሞ ነገር መቼ ነፃነት እርቦን? መቼ የህዝብ ዕንባ አንገብግቦን? መቼስ የኢትዮጵያ እናቶች የ43 ዓመት የሰው ብርንዶ ማቀርብ እንገፍግፎን? እኛ ቀይ ምንጣፍ፤ ሥም፤ ዝና በቃ። ኤርትራም እንዳይከፋት ጥብቅናው አለ። አሁን ይህም በሽታሽቶሽ አሹልከን ሁሉንም አጥተን ድንኳናችን ጥለን ከዜሮ ጀምረን እንደ ዘመነ ቅንጅት በረድ ደግሙ ታቱ በበረደው ቁርጭምጭሚት ይቀጥል ነው። አቅም ስለሚባለው ነገር የትርጉም ንጠት አለብን። ይልቅ ሌላም ዱብ ዕዳም ይጠበቅ። ከዚህ የሌቦች ማህበር በላይ … ውጪ ያሉ የትግራይ ሊሂቃንም እርቀ ሰላም አውርደው አዲስ መሪ ይዘን መጣን በማለት ብቅ ብለው የአብይን መንፈስ የሚሞግት አከርካሪ የሚሰብር የ100 ዓመትን ዕውን የሚያደርግ ስልት እና ስትራቴጂ ይጠበቅ። አቶ ሰዬ አብርሃም ወደ አገር ቢመለሱ ምን ሊባል ነው? ወይንም ቋፍ ላይ ያለው መንፈስ ፈንድቶ ወደ አልታወቀ አቅጣጫ ለውጡ እንደ ግብጽ መጪ ቢልስ …

ለመሆኑ የደንቢደሎውን ህዝባዊ ስብሳባ በአደብ አዳምጣችሁታልን? ዶር መራራ ጉዲናም ቢመረጡም አይፈልጉትም። ሌላ ሦስተኛ መንገድ የያዘ መንፈስ ነው። ማቀራረብ አይደለም ማጠጋጋት አይቻልም። አክቲቢስቱም የኦሮሞ ማለቴ ነው፤ ፈርስቶችን ጨምሮ፤ ሊሂቃኑም ከሚሉት ውጪ ያለ ደሴት ነው …

 • አላዛሯ ኢትዮጵያ … የሥም ትንስዔዋ!

እነሱ በህይወት እያሉ እኮ ነው ሥሟ ሞት የተፈረደባት ኢትዮጵያ ዛሬ ሺህ ሚሊዮን ጊዜ የምትነሳው። ከመጋቢት 10 ቀን ከ2010 ጀምሮ ሲቆጠር ሳትነሳ ውላ አታውቅም። ለዛውም በክብር፣ በልቅና በጥበብ ልክ እንደ ጥንቱ እንደ ጥዋቱ። „ከንባታነት፤ ዳውሮነት፤ ሃመርነት፤ ሲዳማነት ውብ ነው ግን ኢትዮጵያዊነት ከሁሉም ይበልጣል፤ ከሁሉም ያድምቃል፤ ከሁሉም ይጥማል።“ ማህበረ ደራጎን እና የኤርትራ መንግሥት ይህን ከሚሰሙ፤ ይህን ከሚያዳምጡ ቀብራቸውን ይምርጣሉ። ሌላው ደግሞ ኢትዮጵያ አታሳፍልግም ከሚለው ጋር ጊዜያዊ የሃሳብ እርቀ ሰላም ፈጥሮ የኢትዮጵያን የክብር ጉዞ መንገድን ለመጥለፍ ቋንጃ ሲከተክት ውሎ ያድራል። አብይን ከከተከተ ዘመድ ነው ሁሉም። ተዛመደ በአሉታዊ ሐረግ። ለመሆኑ የት ነው ያለነው? ግን ገብቶናል ኢትዮጵያን በሙሉ ቁመና ማቆዬት ማለት ምን ማለት እንደሆነ? ቀን ጥሩ ነው። ላለመደገፍ መብት አለኝ፤ „ለመጠዬቅ መብት አለኝ ግን ግዴታ የለብኝ።“ ሆኖ አያውቅም። በዬትም ሁኔታ ካለግዴታ የተፈጠረ መብት ከለመብት የተፈጠረ ግዴታ የለም። የትም አገር። ሁሉንም ጠልቶ የሚኖር ዴያቢሎስ ብቻ ነው።

 • ጥሩ መንፈስ።

ኢህአድግ በ27 ዓመት ያልሰራው የለውጥ ዓይነት አቅጣጫ አለ ለዛውም ዘራፊውንም፤ ሌባውንም፤ ወራሪውም፤ ደም ሲጨልጥ የኖረውን፤ በሰው ልጆች የስቃይ ጩኽት ሙዚቃ ሲዝናና የኖረውም፤ አርዮሱንም፤ ደራጎኑንም፤ ሳኦልንም ሁሉም ተቻችለህ ኑር ተብሎ ተፈቀዶለታል። ለማን ሲባል? ትውልዱን ለማስቀጠል ሲባል። ስንቱ ሌባ፤ ስንቱ ዘራፊ፤ ስንቱ አሳሪ፤ ስንቱ አክራሪ፤ ስንቱ ገዳይ፤ ስንቱ ዳብዳቢ ስንቱ ረ ስንቱ ታስሮ ይዘለቃል? ስንቱ? ቁንጮው ላይ ሆኖ፣ ዳኛ ሆኖ፣ አቃቢ ህግ ሆኖ፤ ፈራጅ ቀዳጅ ሆኖ፤ አሳሪ ሆኖ፣ ደብዳቢ ሆኖ፤ ታች ያለው ሌባ ደግሞ ተሳዳጅ? አዛውነቱ ሌባ፤ ከእሱ የሚያንስውን ድርጁውን ሌባ ሲያሳድድ፤ ተሳዳጁም ሌባ አሳዳጁም ሌባ? በዚህ ቅጥመጠኑ በጠፋበት ውል የለሽ ጉዞ ነው እኒህ መሪ የመጡት። እኛም አላስጠጋናቸውም፤ እነሱ አላስጠጓቸውም የሁለት አገር ስደተኛ ነው የሆኑት። ብቻ ፈጣሪ አይረሳቸውም። ጊዜው አልበቃ ስላለ ነው እንጂ እኮ በእያንዳንዱ ንግግራቸው ውስጥ ያለው የተስፋ ዘር ሌላ ኢትዮጵያን አምጦ ለመወለድ የታለመ ስለመሆኑ እግር እግር እየተሄደ ቢሰራበት ስንት ፍሬ በኖረው። ለብዙ ዘመን የሚያገለግሎ መጠነ ሰፊ ልቅም ያሉ አዳዲስ የፖሊሲ ሃሳቦች አሉበት። ብዙ መጸሐፍም ይወጣዋል – ለቅኖች በዚህች በተወሰነ ጊዜ ብቻ ባለቅኔው ጠ/ ሚር  ያቀኑት ቅንነት ዘመንንም ይካሳል ታሪክንም ያወርሳል።

ጥያቄ ሁላችንም አለን። እኔም አለኝ። በልቤ እዬመዘገብኩ እያስቀመጥኩኝ። ቀጣይም ነው ሙግቱ። ግን ኢትዮጵያ መንግሥት አሁን አላት፤ በዚህ ዘርፍም ጉድለት አለ፤ ይህ ላይ ስስ ነው፤ ይህ ደግሞ ጭራሹንም አልተሰበበትም ተዘሏል፤ ባለፉት ቀናት ሚዛኑን ያላጠቡቁ ክፍተቶች አሉ፤ ሚዛኑ ካልተጠበቀ ለጥገናዊ ለውጠም ቢሆን አደጋ አለው የሚል። ከዚህም አለፍ ያሉም ምኞቶች አሉኝ። አቤቱታዬ ይቀጥላል። ግን ዛሬ የተገኘውን ከቶውንም ያላሰብኳቸውን የመንፈስ መረጋጋቶቼን ጠቅጥቄ አይደለም። እጅግ ወርቅ የሆኑ ተገባሮች ከመጋቢት 24 / 2010 ቀን ጀምሮ እስከ አሁን በተከወኑት ላይ የእኔ ብዬ አስጠግቼ አክብሬ ነው።

መሪ ሰው ነው እንጂ መሪ ማሽን አይደለም። መሪ ሰው እንጂ ባለክንፍ መሪ የለም። መሪ ሰው እንጂ አስማት አይደለም። መሪ ሰው እንጂ ቁማር አይደለም። በሌላ በኩል መሪ አጋዥ ሲያገኝ እንጂ ብቻውን ከሆነ የፈለገ ዕንቁ ይሁን ይወድቃል። የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ አቅም የባከነው በዚህ መልክ ነው። እሱ ያደራጃቸው የመንፈስ ሃብቶች ዛሬ የሉም ፈልሰዋል። መሪ ማሽን አይደለም ወይንም ማጅክ። ለ6 ኣውሮፓ አገር ሦስት ወር ነው ለመሸፈን፤ አሁን ደግሞ በቀን ሁለት ቦታ ለዛውም ውጪ አገር እና አገር ቤት መባተል ነው የሚታዬው።

በመንግሥት ሚደያ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሲመሰገን አዳምጫለሁኝ። ጥረቱ ዕውቅና አግኝቶ። እነ አቦ በቀለ ገርባ ሲፈቱ ገንቦ እንኳን ጆሮ አለው፤ የመንግሥት ሚዲያ ተብዬው አንጠልጥሎ ነበር የጠራቸው። ሎቱ ስብሃት ስለ ሃጢያተኞች፤ አሁን ግን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሽብር ተጠርጥረው ነው የሚል ነው የተደመጠው። ይህ ለውጥ ነው። „አቶ“ ብሎ መነሳቱ በራሱ ዕወቅናው ቃል ጠባቂ ነው። የሰው ልጅን ክብር መጠበቅ። ከሰው የተነሳ ራዕይ እንደአለ ስለመኖሩ ያመለክታል። ግርዶሽ ከተሰራለት ግን አይታዬንም።

ለእኔ የአሜሪካኑ ጉዞ ተሳካም አልተሳከም እምታተርፈውም እምትከስረውም ኢትዮጵያ ናት። ቢቀሩም ለመልካም ነው ቢገኙም ለመልካም ነው። ፈጣሪ የወደደው ይከወን። ጠቃሚ ከሆነ ያሳካላቸው የማይጠቅም ከሆነ ምክንያት ፈጠሮ ይዝለልላቸው። ይህም አጀንዳ ሆነ መታመስ ግን ቅናት እና ምቀኝነት ብቻ ነው። አቅማቸው ስለሚታወቅ የቀረው መንፈስ ደግሞ ከእኛ እጅ ይወጣል ነው። አቻውን ለመከወን መትጋት እንጂ ሃሳብ ያለውን ትልም እዬተከተሉ መባትል የአቅም ብከነት በዛ ላይ ትዝብት ነው። ስንቱን ነው መቃወም ይቻላል? እግዚብሄር የወደደው የቀባው የፈለገ መጋረጃ ቢሰራ አይቀሬ ነው። ሳጅን በረከትን ያህል የመከራ ሌሊት፤ አቦይ ስብሃትን የመሰለ የበረዶ ሌሊት የተሻገረ መንፈስ አሁንም አዶናይ አለው። ቅኖችም በጸሎት ይተጉለታል። የአረብ አገር እህቶቻችን ግፍ በመቃወም በተደረገው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የተገኘ የኢትዮጵያ ኢንባሲ የለም። መቼም ያ ሰው መሆንን ብቻ ነበር የሚጠይቀው። ለነገሩ ያነን ሰልፍ የተቃዎሙት እኮ ናቸው ዛሬ ተነጥፎ ተጎዝጉዞ ንጉሣዊ አቀባበል የተደረጋላቸው እነ አቦ ሌንጮ ለታ። አሁን ደግሞ እስኪ እንገናኝ እንተያይ ነው …

 • የብዕር መርኽ ክወና።

ለሰው መልካም ሲታሰብ መልካምነት በገፍ ያተርፋል። ክፉ ሲታሰብ ደግሞ ባላሰብነው ሁኔታ ቅጣቱ የእዮር ይሆናል። አለመርካት መብት ነው። ያረካ ደግሞ ድርጅትን በፖለቲካዊ ፍልስፍናዊ አቅሙ እና መርሁን መካች አድርጎ፤ አብቅቶ ሌት ተቀን ባትሎ፤ ወጥቶ ወርዶ ራስን ማስከበር ከልካይ የለበትም። ሜዳውም ፈረሱም … ይብቃኝ ተዚህ ላይ … ቀጣዩ ከጠ/ ሚር አብይ አህምድ ቢሮ ጋር ጠንከረ ያል ሙግት ይኖረኛል፤ ምኞት እና የተስፋ አቤቱታ ይሆናል። ከተሰነበተ።

 • የእኔ ቅኖች ጊዜው ሲኖር እንዲህ ቢሆንስ?

„kenebete (ቀንበጥ)“ ብሎግን እንዲሁም „Sergute Selassie Youtube“ ብትጎበኙስ ምን ይመስላችሁዋል።

የፍቅራዊነት የቃላት ፖስተራዊ ቻናልን ይጎብኙልኝ። እስቲ ኑልኝ!

„መሪ ማለት መሪ እንጂ ነጂ ማለት አይደለም።“

(ከባለ ቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ።)

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

የ “ESFNA” ቦርድ ህዉሃት/ኢህአዴግን እና የአግ7 መሪዎችን የማደራደር ሂደቱን ጥሩ አድርጎ አቀላጠፈዉ

ሸንቁጥ አየለ
============
ESFNA  ቦርድ  5 ሰዓታት የፈጀ ዉይይት አድርጎ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተጋበዙ ከተቃዋሚ ድርጅቶችም ሰው ይጋበዝ:: እናም ተቃዋሚዎችም አንድ ሰው ወክለው ይቅረቡ” የሚለው የውሳኔ ሃሳብ አሳልፏል የሚል ዜና አሁን ዘሀሻ አስነበበን::
እኔም ይሄን አይነት ዉሳኔ እንደሚሆን ገምቼ ነበር:: የቦርዱ ዉሳኔ ልክ ብዙ የተደከመበት እንዲመስል ብዙ ተራገበ::ስሌቱ ግን ቀላል ነዉ::እነ ሌንጮ ለታ የጀመሩትን የማደራደር እቅድ በተፋጠነ መልኩ መስመር የማሲያስይዝ አሰራር ነዉ::ወያኔ አቢይን ከፊት አሰልፋ ኦህዴድ እና ብአዴን ከህዉሃት ተጣልተዋል የሚለዉን የህጻን ትርክት ለኢትዮጵያ ህዝብ እየተረከች ህዝቡን ለማጃጃል ከፍተኛ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ዉጤታማ ሆናለች እና ቦርዱም ልክ አንዳች የዉሳኔ አጣብቂኝ ዉስጥ የገባ ለማስመሰል ስንት ብዙ ፕሮፖጋንዳ ሲያስነፋ ከረመሳ::
አቢይ ጥያቄዉን ያቀረበዉ እራሱ አለ ቦርዱ ፈቃድ አይደለም::ከቦርዱ ጋር ቀደም ያለ ንግግር ተደርጎበት ነዉ:: ቦርዱ ህዉሃት/ኢህአዴግን እና የአግ7 መሪዎችን የማደራደር ሂደቱን ጥሩ አድርጎ አቀላጠፈዉ እሳ ጃል…::
መልካም ድርድር:: ህዉሃት አድፍጣ ልክ 1997 ዓም የቅንጅት መሪዎችን በድርድር ስም አዋዝታ አፈር እንዳስጋጠቻቸዉ የአሁኑን ሂደት በምን መልክ በታላቅ የተቀናበረ ድል ወደራሷ የበላይነት ቋት ዉስጥ እንደምትከተዉ እህኔ ስንት ጥናት አስጠንታ: ስንት አማካሪ አሰልፋ ይሆን?
ቦርዱም ጥሩ ቼዝ ተጫዉቷል::
የሆኖ ሆኖ ከወያኔ/ኢህአዴግ ጋር የሚደረግ ድርድር ሁሉ ዉጤቱ ዉሃ ወቀጣ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነዉ::
በድርድር ስም ዉይይት በመጀመሩ ብቻ ግን ህዉሃት/ኢህአዴግ ብዙ ድሎችን ታተርፋለች::
1. በአሜሪካኖቹ ዘንድ ሊጣልባት ያለዉ  ህግ ዉድቅ ይሆናል::በዚህም እንደገና ምዕራባዉያን ጉያ ተደላድላ ገባች ማለት ነዉ::
2. ዋላላ ተቃዋሚዎችን ወደ ጉያዋ የማስገባት እና አብራ የማሰለፍ እድሏ ሰፋ ማለት ነዉ
3. የሚቀጥለዉን ምርጫ ክፍት አደርጋለሁ በማለት በተወሰነ ደረጃ ምርጫዉን ከፍታ እንዲሁም በተወሰነ ደረጃ ምርጫዉን አጭበርብራ የተዋጣለት ጨዋታ ትጫወታለች ማለት ነዉ::አንዳንድ የሚነሱባትንም ወቀሳዎች ያልዳበረ የዲሞክራሲ ሂደት ስላለ ነዉ  በማለት እና ለወደፊቱ ቃል በመግባት ሁኔታዉን በቁጥጥር ስር ታደርጋለች ማለት ነዉ
4. አክራሪ እና እዉነተኛ ተቃዋሚ የሚባሉትን በጥንቃቄ በማጥናት ዉስጥ ዉስጡን ቀስ ብላ እምሽክ አድርጋ ከእስተዛሬዉ በተሻለ ትበላቸዋለች ማለት ነዉ
5. ተቃዋሚዎች ተሰባስበዉ እና ተጠናክረዉ ሲመጡ ህዝባዊዉ አመጽ በሂደት እየበረደ ስለሚመጣ የአዉራ ፓርቲ ፖሊሲዋን እንደገና ጎትታ ይዛ በመምጣት ከተወሰነ አመታት ብኋላ ተቃዋሚዉን አከርካሪዉን ትመታዋለች ማለት ነዉ::
አሁንም የመለስ ፍልስፍና እየሰራ ነዉ::መለስ ባንድ ወቅት እንዲህ ነበር የተናገረዉ::”እኛ ተቃዋሚዎች እንዲደራጁ እናበረታታለን::እግር ሲያወጡ ግን እግራቸዉን እንቆርጥላቸዋለን:

“ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው” አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ

BBC Amharic:  በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በልዩ ይቅርታ እንደሚፈቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቅዳሜ እለት መግለፁን ተከትሎ ከትንናት ሰኞ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መፈታታቸውን ሲጠብቁ ቆይተው ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ተለቀዋል።

በቤተሰባቸው ቤት ከቅዳሜ ጀምረው ሲጠባበቁ ለነበሩት ወዳጆቻቸው ባደረጉት ንግግር አቶ አንዳርጋቸው ”እኔ ተፈትቻለሁ ኢትዮጵያ ግን ያልተፈቱ ብዙ ችግሮች አሉባት” ብለዋል።

ከእስር ተፈተው ቤታቸው ሲደርሱ የተመለከቱት ነገር ያልጠበቁት እንደሆነ የተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው። “ምንም መረጃ ባይኖረኝም ኢትዮጵያዊያን እኔን ለማስፈታት ጥረት እንደሚያደርጉ ይሰማኝ ነበር” ብለዋል።

ለዚህ ቀን መምጣት ለደከሙ ለሁሉም ሰዎች ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ገብቶበት ካለው አስቸጋሪ ሁኔታ አንፃር፤ እንዲህ አይነት ሃገር ከማየት ፍርድ ቤታችሁ የወሰነውን የሞት ቅጣት ተግባራዊ አድርጉ” በማለት ለመርማሪዎች መናገራቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት በቴሌቪዥን ተቆራርጦ ነው የቀረበው ያሉትን ምስል እንዳዩት የተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው “ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው፤ ነገር ግን ቆራርጠው ነው ያቀረቡት።”

ጨምረውም “ፍቱኝ ብዬ አልጠይቃችሁም አብሬያችሁ የሰራሁበትን ጊዜ እንደውለታ ቆጥራችሁ የሞት ፍርዱን ተግባራዊ አድርጉ ብዬ ጠይቄያቸዋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርግ የቆየው ሪፕሪቭ የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም እንዳለው አቶ አንዳርጋቸው ለንደን ከሚገኙት የህይወት አጋራቸው የሚ ኃይለማሪያም ጋር ከአራት ዓመት በኋላ ለአጭር ጊዜ በስልክ ተነጋግረዋል።

የሪፕራይቭ ዳይሬክተር ማያ ፎአ ስለአንዳርጋቸው መፈታት በሰጡት አስተያየት “ቤተሰቡ፣ ልጆቹና ደጋፊዎቹ የሚደሰቱበት አስደሳች ዜና ነው። በቅርቡም ወደ ለንደን መጥቶ ለረጅም ጊዜ ተለይቷቸው የቆዩትን ልጆቹን ያገኛቸዋል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ” ብለዋል።

ሰኞ ጠዋት የእንግሊዝ ኤምባሲ መኪኖች በማረሚያ ቤት አካባቢ ተገኝተው ነበር፤ የአቶ አንዳርጋቸው እህት በስፍራው ከኤምባሲ ሰዎች ጋር የነበረች ሲሆን ለቤተሰቦቿ ደውላ ማለዳ እንዳገኘችውና ወደቤት እንደሚመጣ ነግራቸው ነበር።

ከሰኞ እለት ጀምሮ አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቹ ቤትና አካባቢው በመፈታቱ የተሰማቸውን ደስታ በሚገልጡ መልዕክቶችና በፎቶዎቹ አሸብርቆ ውሏል።

የአንዳርጋቸው ደጋፊዎች የእርሱን ምስል የታተመበት ቲሸርት ለብሰው በአካባቢው ተገኝተው ሲጨፍሩ እና ደስታቸውን ሲገልጡ እንደነበር ተመልክተናል።

በለንደን የምትኖረው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህይወት አጋር ወ/ሮ የምስራች ኃይለማርያም (የሚ) በባለቤቷ ሊፈታ በመሆኑ እጅግ መደሰቷን እና እስካሁንም የተፈጠረውን እንዳላመነች ለቢቢሲ ተናግራለች።

”ከአንድ ሰው ህይወት 4 አመት የሚሆነውን በእስር ማሳለፍ ምን አይነት ተጽዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ይከብዳል። ነገር ግን ባለቤቴ ከዚህ በኋላ ወደ ፀሃፊነት ያዘነብላል ብዬ አስባለሁ” ትላለች ወ/ሮ የሚ።

ለልጆቼ ዜናውን ስትነግራቸው በደስታ አልቅሰው ነበር የምትለው የሚ፤ እስካሁን አንዳርጋቸውን ለማነጋገር እየጠበቁ እንደሆነ ገልጻለች።

ባለቤቷ በሽብርተኝነት በተፈረጀው ግንቦት ሰባት ድርጅት ስለነበረው ኃላፊነት እና ስለቤተሰቡ ሁኔታ የተጠየቀችው የሚ፤ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ሰዎች ከመንግሥት ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ይታወቃል፤ ስለዚህ ሁሌም ቢሆን የሆነ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል እገምት ነበር ብላለች።

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ቀን ጀምሮ እንዲለቀቁ ሲወተውት የነበረው ሪፕራይቭ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ዋና ኮሚሽን የሆኑት አዳም ስሚዝ እስካሁን ድረስ አለመለቀቃቸውን ገልጾ ዛሬ ብሔራዊ በዓል ስለሆነ ላይለቀቁ ይችላሉ ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

አክለውም የእንግሊዝ ኤምባሲ አስቸኳይ የጉዞ ሰነዶችን ሊያዘጋጅ ይገባል፤ አንዳርጋቸውም አባቱን ማየት ሊፈልግ ይችላል ብለዋል።

የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ አንዳርጋቸው፣ በሽብር ወንጀል ሁለት ጊዜ ክስ ተመሥርቶባቸው በዕድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ እንደተፈረደባቸው ይታወሳል።

Grey line
 • አቶ አንዳርጋቸው የተወለዱትና ያደጉት አዲስ አበባ ነው። የቀለም ትምህርት ከቀመሱበት ተፈሪ መኮንን ሲወጡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ማጥናት ጀመሩ። በዩኒቨርስቲ ቆይታቸውም በተማሪዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ነበሩ።
 • የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ወድቆ ደርግ ስልጣኑን ሲይዝ ኢህአፓን ተቀላቀሉ። በወቅቱ የኢህአፓ አባል የነበሩ ወጣቶች እንደሚያደርጉት በፓርቲው በህብዕ አደረጃጀት ውስጥ በመሆን የደርግ መንግሥትን መታገል ጀመሩ።
 • አቶ አንዳርጋቸው የደርግ መንግሥት የቀይ ሽብር አውጆ በርካታ ወጣቶች ላይ እርምጃ ሲወስድ ወንድማቸውን አጥተዋል። ያኔ አንዳርጋቸው ሀገር ጥለው ተሰደዱ። በወቅቱ ከኢህአፓ ጋርም በነበራቸው የርዕዮተ ዓለም ልዩነትም ከፓርቲው ተለይተው በሱዳን በኩል እንግሊዝ በመግባት ጥገኝነት ጠየቁ። በኋላም ዜግነት አግኝተዋል።
 • በ1983 የደርግ ከስልጣን ሲወገድ አዲስ የተመሰረተውን መንግሥት ለማገዝ ወደ ሀገር ተመለሱ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆዩ ተመልሰው ወደ እንግሊዝ ሄዱ።
 • በጥር ወር 1997 ዓ.ም እንደገና አንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ አበባ ገቡ። የመጡት በምርጫው ቅንጅትን ለመርዳት ነበር፤ ወዲያውኑም የቀስተ ዳመና አባል ኾነው የፓርቲ ሥራ ጀመሩ።
 • 1997 ሰኔ ወር ላይ አቶ አንዳርጋቸው በዝዋይ እስር ቤት በሺህዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ታስረው ለሁለት ሳምንታት ቆዩ። ከእስር ቤት እንደወጡ ሐምሌ 1997 ወደ እንግሊዝ ተመለሱ።
 • በግንቦት 2000 ዓ.ም ከዶክተር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመሆን ግንቦት ሰባት ንቅናቄን መሰረቱ። አንዳርጋቸው የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ሆነው ተመርጠው ነበር።
 • ሚያዚያ 2001 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግሥት “በግንቦት ሰባት የተቀነባበረ መፈንቅለ መንግሥት አከሸፍኩ” ሲል ገለጸ። ግንቦት ሰባትንም አሸባሪ ሲል ፈረጀ። በዛው ዓመት አቶ አንዳርጋአው ጽጌ በሌሉበት የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው።
 • ሰኔ 2006 ዓ.ም አንዳርጋቸው የግንቦት ሰባትን ሥራ ለማካሄድ ዱባይ ገቡ። ከዱባይ ተነስቶ በየመን በኩል ወደ ኤርትራ ሊጓዙ ሲሉ ሰንዓ ላይ በየመን የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው ተሰጡ።
 • በ2007 የእንግሊዝ መንግሥት አንዳርጋቸው ከእስር እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግሥትን መጠየቅ ጀመረ።