ዶ/ር ዓብይ አህመድ አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች አምስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በጡረታ ሰበብ አሰናበቱ

(ዘ-ሐበሻ) ወደ 50ኛው ቀን የስልጣን ቀናቸው እየተቃረቡ የመጡት ዶ/ር ዓብይ አህመድ በአምስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ ወሰዱ::

አማራን እና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አከርካሪውን መትተነዋል; የኦሮሞና የአማራ ግንኙነት መርህ አክባ ጉድኝት ነው የሚሉትና በየ ስብሰባው በ እርጅና ብዛት እንቅልፍ የሚወስዳቸው አቶ ስብሃት ነጋ በጡረታ ከተገለሉ ባለስልጣናት መካከል አንደኛው ሆነዋል::

የጠቅላይ ሚኒስተሩ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ “አገራችን እያካሄደች ያለችው ሪፎርም የተሳካ እንዲሆን የማድረጉ ሥራ እንዲሁም ለሕዝቡ የልማትና ለውጥ ፍላጎት ተገቢ ምላሽ የመስጠቱ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያግዙ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እያካሄዱት ያለው የካቢኔ ለውጥ ይገኝበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በአዳዲስ ኃላፊዎች እንዲመሩ በማድረግ ላይም ይገኛሉ፡፡” ካለ በኋላ “ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለበርካታ ዓመታት በመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም በጡረታ እንዲያርፉ እየተደረገ ነው፡፡” ብሏል::

አቶ ስብሃት ነጋ በአሁኑ ወቅት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል በመሆን ሲያገለግሉ የነበረ መሆኑ ይታወሳል::

ሌላው ተሰናባች የቀድሞ የደህዴን ሊቀመንበር ዶ/ር ካሱ እላላ ከፖለሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ አቶ በለጠ ታፈረ ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም፣ ዕቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት፣ አቶ ታደሰ ኃይሌ ከንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሲ ዕቅድ አፈጻጸምና ክትትል፣ እና አቶ መኮንን ማን ያዘዋል ከፖሊሲ ምርምር ማዕከል ናቸው::

እነዚህ ዛሬ በጡረታ የተገለሉ የተባሉት ባለስልጣናት ከከፍተኛ ሙስና ጋር ስማቸው የሚነሳ ቢሆንም በዚህ ጉዳይ ይጠየቁ አይጠየቁ የሚታወቅ ነገር የለም::

የዶ/ር ዓብይ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆዩትን በጡረታ የማሰናበቱ ጉዳይ ይቀጥላል ብሏል::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s