ዶ/ር አብይ አህመድ …ዛሬም ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም።ግንቦት ሃያ ፳ መጣ:-ግንቦት ሰባትን ፯ አልፎ

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

የማቴዎስ ወንጌል ፮፥፳፬

 

 ግንቦት ሃያ ፳ ስለመጣ አንዱን የጉጅሌ አባል ማንነቱን ለሚጠየቀው ሰው መልሱ”አህያ ፈጅ”ከሚለኝ ይልቅ፤”ዥብ ነኝ” አለማለቱ፣ሁለታችንም በምናውቀው ምክንያት፦”…በቅሎ፥አባትኽ፡ማን፡ነው፡ቢሉት፥እናቴ፡ፈረስ፡ነች፡አለ።” እንደሚሉት ሰዎች ዓይነት ነው፤ምክንያቱስ?…

 

ለምን እንወሻሻለን ዶ/ር አብይ አህመድንስ ስለፖለቲካዊ ማንነቱን በምሳሌ”ምንድነው ሥራህ?”ስለው”አህያ ፈጅ”ከሚለኝ፤በቀላሉ”ዥብ ነኝ”ያላለኝ ምክንያቱን እኔም ሆንኩ እሱ፣ሁለታችንም እናውቀዋለን ብዬ አምናለሁ።

ምክንያቱስ ምንድን ነው?ቢባል አጋጣሚው በግንቦት ሃያ ፳ መምጣት ላይ የተሰመረ ነውና የጥያቄው መነሻ ግን እሰይ መጣልን የተባለበት ምክንያት ሲሆን፤የበዓል ቀን መባሉ ነው።ባሕላዊ ዕምነትም አይደለም፤እንደላሊበላዎቹ በሰው ተስካር እንደሚሞሸሩት።ዶ/ር አብይ አህመድም ይህንን ያውቁታል ብዬ እገምታለሁ።በዚያን ዕለት ግንቦት ሃያ ለኢትዮጵያውያን ያሳለፍነውን መከራ እየተራመድን የምንወጣ መስሎን ደስታ በተቀላቀለበት የለቅሶ ቤት ወደሓዘን መጓዛችንን ያወቅነውና እስከዛሬ ድረስ እጅግ በባሰ ሁኔታ መከራ መቀበል የጀመርንበት ዕለት መሆኑን የምናስታውስበት መራራ ትዝታ ነው።

ወደፍሬ-ነገሩ ስንመጣ “እሳት ሲነድ ለአንዱ ረመጥ ለአንዱ አመድ”እንጂ፣ሁለት እሣት ወይም ሁለት አመድ አይኖርም።እነሆ በአሁኑ ወቅት የተፈፀመው የሥልጣን መደላድል፦ምርጫም ሽግግርም ሳይሆን፣በተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሰበብ፣የጎደለውን ለመሙላት ዶ/ር አብይ አህመድ ማሟያ ሆነው ተመረጡ ተባለ እንጂ፤ሕዝብ የመረረ አመፁን ይዞ ጉሮሮአቸውን ሊያንቅ ይህችን ያህል ቀርቷቸው ከመግፋት በስተቀር የሚያውቁት ነገር አልነበረም።እናም ብዙም የተባለው በዶክተርነቱ ላይ አይደለም፣በአዲሱ ሹመት ጠቅላይ ሚኒስቴር ስለተባለው አብይ አህመድ፤ እና በጠቅላይ ሚኒስቴርነታቸው ሰበብ፣በኮነሬልነታቸው ማዕረግ የሥልጣን ርክክብ ምክንያት ስለተነሳው ነው።

እንደሚባለው ሲያዩት ደግ መሳይ ክፉ፣ገንቢ አፍራሽ፣ምሥጉን ርጉም፣ምንም ያላሉም አሉም፤ባመዛኙ ግን ዶ/ር አብይ አህመድን እስኪ እንያቸው ብለዋል። ፕሮፌሰሮች፣ ዶክተሮች፣የኪነጥበብ ባለሙያተኛ፣ሕዝብ፣ ጋዜጠኞች፣ ባለሙያተኞች በሙሉ፣ወንጀለኞች እና ነብሰገዳዮች፣አካለ ስንኩላን፣ከሁለቱ ፆታዎች በተጨማሪ ባለሦስተኛ የፆታ ረድፈኞች(ፍናፍንቶች)ነን የሚሉትንም ጨምሮ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሔር-ብሔረ-ሰቦች እኩል ነን በማለታቸው ውስጥ አልቀሩም።

ያለፍንበት የኢትዮጵያ ታሪክና ለወደፊቷ የምንመኝላት ተስፋ ተዳምረው፣አሁን ስለአለንባት አገር እንድንስማማ ትግል በመጀመሩ ነው፣ማን እንደሆነ ትውልድ ገዳይ ብለን በሰከነ ሁኔታ የበሰበሰውን አይነት ብርቱካን እንደመለየት ጉዞውን የምንያያዘው።ይህ ጉዞ እንዳለፉት አርባ አራት ዓመታት ዓይነት፣በደም የተጨማለቀ፣በሰቆቃ የታጨቀ፣በግፍ የተለቃለቀ፣በውሸት የተደበቀ፣በሚገድል እያነቀ፣ጭካኔን የሰነቀ፣ደግነትን ያራቀ፣የሚያስገድል እያሳቀ፣በለሰለሰ ልሣን ውስጥ ውስጡን የማያሳጣን፣ዕውነትን ያልሆነ ዳሩግን የሚያስመስል፣በብልጭልጭ ያልተንቆጠቆጠ፣ወርቅም ያልሆነ፣በፍፁም መሆንም የለበትም፤ይህ የጉዞአችን አቅጣጫ ነውና።በተቻለ መጠን ከአስርቱ ትዕዛዛት ቢያንስ አምስቱን የሚያከብር ቢሆን ይመረጣል።

እናም”ቃል”ነበር መጀመሪያ በፊደላት ውስጥ ተፀንሶ፤እንደ”ዥብ”ቃል።ጅማቱ እንኳ ሳይቀር”ልብላው…ልብላው”እንደሚልና ቆዳው ደግሞ ብሶ”ምን እንደሚሆን እናውቀዋለን።ሥምና ተግባራቸው የተለያየ ከሆኑ በዛም አነሰም በመንገድ ላይ የውርደት ሐቁ እንደ ኣያጅቦ ቅልብጭ ብሎ ባደባባይ ይታያል።ኣያጅቦ ደግሞ አስቀያሚ ጥርሶቹ ብቻ ሳይሆኑ፣አንካሳ እግሮቹም ያጋልጡታል፤ከዚያም በላይ”ያ ሆዳሙ ቆሻሻው “አያ ዥቦ”ነው ይባላል።

ከዚህ አንፃር ቀጭኗ የፈተና መንገድ መጣች፦ግንቦት ሃያ ፳ የተባለችው ቀን “ለአንዱ እሣት ላንዱ አመድ”የሆነው ዕለት እየመጣ ነው፤ዶ/ር አብይ አህመድ እሣት እና አመድም መሆን አይቻላቸውም። ምክንያቱም ግንቦት ስባት ፯ የታወቀ የኢትዮጵያውያን የድል ቀን እና መቶዎች በጅምላ በአንዴ በምርጫ ድል ሰበብ እና በነፃነት ትግል ምክንያት የተገደሉበት የሰማዕታት ዕለት ሆኖ የሚከበርበት በመሆኑ፣የዚያ ግንቦት ሃያ ፳ ግድያ ሰበብ መነሻ  በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሃያ ሰባት ዓመታት መከራ እና ሰቆቃ ምክንያት መሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።ይህቺ ግንቦት ሃያ ፳ የተባለች ርጉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራዋን ፅዋ መጋት የጀመረችበት ቀን ስለሆነ ማቅ የመልበሻችን መጀመሪያዋ ዕለት ግንቦት ሃያ ፳ ሆናለች።የ”ወያኔ ኢሐድግ”ብለው የ”ባንዳዎችን ቡድን” የሚያንቆላጰላጥሱትም ሆኑ፣የጉጅሌን መሰሪ ተግባሮች ጠንቅቃችሁ የምታውቁ ሁሉ፤ብታምኑም ባታምኑም በኢትዮጵያ ሐገራችን ዜጎች በትዕቢት፣በግዴለሽነት፣በማንለብኝነት፣እና ያለምንም ምክንያት በየቀኑ ኢትዮጵያውያንን ይገድላሉ።ግንቦት ሃያ ፳ መጣ:-ግንቦት ሰባትን ፯ አልፎ፤ታዲያ ዛሬም ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም።

እንግዲህ ዶ/ር ኮነሬል አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስቴር፣የጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አማካኝነት ለግንቦት ሃያ ፳ በመቆም ባለፉበት ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ የነብስ ማጥፋትና የንብረት ዝርፊያ መፈፀሙን ይሁንታ መስጠት፤ካሻቸውም ማስቀጠል:-አሊያም ከዚህ ማቅ ለመውጣት ግንቦት ፯ በተገኘው የሕዝብ ድምፅ ማሸነፍ እና ከሁለት መቶ ሰላማዊ ሰዎች በላይ በጅምላ ከተገደሉበት የድል ቀን ጋር በመቆም ሕዝብን መደገፍ ምርጫቸውን መለየት ይኖርባቸዋል።

 

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።  የሉቃስ ወንጌል ም-፲፮፥ቁ-፲፫

ጉድ በል ኢትዮጵያዊ፤ብሊዮን ሲሲ ደም-ተመጥጧል።
ኢትዮጵያን ያመሳት ወቸገል ዜናዊ፤
አምስት ብሊዮን ዘርፏል፣
ጉድ በል ኢትዮጵያዊ።
በትግሬነት ጨምበል ወልቃትነቷን፤
የከዳችው አዜብ ሳታውቅ ማንነቷን፤
በሸበጧ ገብታ ባሏ የዘረፈውን፤
እሷም በተራዋ ዘርፋናለች አሁን።
ምንቀራት እንጀራ ከሕዝቡ አፍ ነጥቃ፤
ቡና እና ሌጦውን ሳትታይ ደብቃ፤
በሁሉም አቅጣጫ በሚስትነት ሥሟ፤
በፍርፋሪ ሥልጣን በሴትነት አቅሟ፤
እያሞጠሞጠች፣ታጋይ ነኝ እያለች፤
በካድሬዎች ወጥ-ቤት ያኔ እንዳልታገለች፤
ይህንን ሐቅ ታሪክ አድርጋለት ጭምብል፤
ታጭበረብራለች ዛሬም ልታባብል። 
ሚስቱ የነበረችው የወቸገል ዜናዊ፤  
ቢሊዮን ዘርፋለች፣
ጉድ በል ኢትዮጵያዊ።
ዶክተር-አብይ አንተም ወንጀለኞች ለቀህ፤
ሲዘርፉ እንዳላየህ ትሆናለህ አውቀህ።
ይሄንን ልብ በል አይተህ ዝም አትበል፤
መራራ ነው ትግል ተዘጋጅ ለመክፈል።
በፈለግነው ሒሳብ ደሞዙ ቢሰላ፤
ልዩ ገቢ ቢኖር ቢፈለግም መላ፤
በፍፁም ይህ ንብረት የኢትዮጵያችን ነው፤
ዛሬ ካልተመለሰ ለመቼም አናምነው።
እናም ባለሥልጣን ሁሉም የነበሩ፤
እንደወቸገሉ በሕዝብ ይመርምሩ።
ኢትዮጵያን ያመሳት ወቸገል ዜናዊ፤
አምስት ብሊዮን ዘርፏል፣
ጉድ በል ኢትዮጵያዊ።   
ዓቢይ ኢትዮጵያዊ
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s