የ “ESFNA” ቦርድ ህዉሃት/ኢህአዴግን እና የአግ7 መሪዎችን የማደራደር ሂደቱን ጥሩ አድርጎ አቀላጠፈዉ

ሸንቁጥ አየለ
============
ESFNA  ቦርድ  5 ሰዓታት የፈጀ ዉይይት አድርጎ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተጋበዙ ከተቃዋሚ ድርጅቶችም ሰው ይጋበዝ:: እናም ተቃዋሚዎችም አንድ ሰው ወክለው ይቅረቡ” የሚለው የውሳኔ ሃሳብ አሳልፏል የሚል ዜና አሁን ዘሀሻ አስነበበን::
እኔም ይሄን አይነት ዉሳኔ እንደሚሆን ገምቼ ነበር:: የቦርዱ ዉሳኔ ልክ ብዙ የተደከመበት እንዲመስል ብዙ ተራገበ::ስሌቱ ግን ቀላል ነዉ::እነ ሌንጮ ለታ የጀመሩትን የማደራደር እቅድ በተፋጠነ መልኩ መስመር የማሲያስይዝ አሰራር ነዉ::ወያኔ አቢይን ከፊት አሰልፋ ኦህዴድ እና ብአዴን ከህዉሃት ተጣልተዋል የሚለዉን የህጻን ትርክት ለኢትዮጵያ ህዝብ እየተረከች ህዝቡን ለማጃጃል ከፍተኛ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ዉጤታማ ሆናለች እና ቦርዱም ልክ አንዳች የዉሳኔ አጣብቂኝ ዉስጥ የገባ ለማስመሰል ስንት ብዙ ፕሮፖጋንዳ ሲያስነፋ ከረመሳ::
አቢይ ጥያቄዉን ያቀረበዉ እራሱ አለ ቦርዱ ፈቃድ አይደለም::ከቦርዱ ጋር ቀደም ያለ ንግግር ተደርጎበት ነዉ:: ቦርዱ ህዉሃት/ኢህአዴግን እና የአግ7 መሪዎችን የማደራደር ሂደቱን ጥሩ አድርጎ አቀላጠፈዉ እሳ ጃል…::
መልካም ድርድር:: ህዉሃት አድፍጣ ልክ 1997 ዓም የቅንጅት መሪዎችን በድርድር ስም አዋዝታ አፈር እንዳስጋጠቻቸዉ የአሁኑን ሂደት በምን መልክ በታላቅ የተቀናበረ ድል ወደራሷ የበላይነት ቋት ዉስጥ እንደምትከተዉ እህኔ ስንት ጥናት አስጠንታ: ስንት አማካሪ አሰልፋ ይሆን?
ቦርዱም ጥሩ ቼዝ ተጫዉቷል::
የሆኖ ሆኖ ከወያኔ/ኢህአዴግ ጋር የሚደረግ ድርድር ሁሉ ዉጤቱ ዉሃ ወቀጣ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነዉ::
በድርድር ስም ዉይይት በመጀመሩ ብቻ ግን ህዉሃት/ኢህአዴግ ብዙ ድሎችን ታተርፋለች::
1. በአሜሪካኖቹ ዘንድ ሊጣልባት ያለዉ  ህግ ዉድቅ ይሆናል::በዚህም እንደገና ምዕራባዉያን ጉያ ተደላድላ ገባች ማለት ነዉ::
2. ዋላላ ተቃዋሚዎችን ወደ ጉያዋ የማስገባት እና አብራ የማሰለፍ እድሏ ሰፋ ማለት ነዉ
3. የሚቀጥለዉን ምርጫ ክፍት አደርጋለሁ በማለት በተወሰነ ደረጃ ምርጫዉን ከፍታ እንዲሁም በተወሰነ ደረጃ ምርጫዉን አጭበርብራ የተዋጣለት ጨዋታ ትጫወታለች ማለት ነዉ::አንዳንድ የሚነሱባትንም ወቀሳዎች ያልዳበረ የዲሞክራሲ ሂደት ስላለ ነዉ  በማለት እና ለወደፊቱ ቃል በመግባት ሁኔታዉን በቁጥጥር ስር ታደርጋለች ማለት ነዉ
4. አክራሪ እና እዉነተኛ ተቃዋሚ የሚባሉትን በጥንቃቄ በማጥናት ዉስጥ ዉስጡን ቀስ ብላ እምሽክ አድርጋ ከእስተዛሬዉ በተሻለ ትበላቸዋለች ማለት ነዉ
5. ተቃዋሚዎች ተሰባስበዉ እና ተጠናክረዉ ሲመጡ ህዝባዊዉ አመጽ በሂደት እየበረደ ስለሚመጣ የአዉራ ፓርቲ ፖሊሲዋን እንደገና ጎትታ ይዛ በመምጣት ከተወሰነ አመታት ብኋላ ተቃዋሚዉን አከርካሪዉን ትመታዋለች ማለት ነዉ::
አሁንም የመለስ ፍልስፍና እየሰራ ነዉ::መለስ ባንድ ወቅት እንዲህ ነበር የተናገረዉ::”እኛ ተቃዋሚዎች እንዲደራጁ እናበረታታለን::እግር ሲያወጡ ግን እግራቸዉን እንቆርጥላቸዋለን:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s