ብአዴን አዉራዉ እንደጠፋበት ንብ ወዲያ እና ወዲህ እየተንገዋለለ ነዉ! (ሚኪ አማራ)

ብአዴን እስከ 2012 እንኳን የሚቆይ አይመስለም፡፡ ምኑን ይዞ ምኑን እንደሚጨብጥ ግራ ገብቶታል፡፡ ተከፋፍሎና ተኮራርፎ መግለጫ እንኳን ለመስጠት ወኔ አጥቶ አይተነዋል፡፡ መቀሌ ላይ የተገኘዉ የብአዴኑ ቁንጮ ህላዊ ዮሴፍ «ብአዴን በስብሷል፣ የኛ ያልሆነ የዘቀጠ አስተሳሰብ ግብቶበታል፣ ትምክተኛ እና ነፍጠኛ ማለት እንኳን ማለት አልቻለንም» ብሎ በቴሌቪዠን የራሱን ድርጅት መቀሌ ላይ አንበላዉሶታል፡፡ እኔ ብአዴንን ብሆን እንደዚህ ዝቃጩ ነዉ የተጠራቀመበት ብሎ እየተሳደበ እዛዉ መቀሌ ሳይወጣ ሁለት መስመር ደብዳቤ ከድርጅቱ የሚያሰናብት ፋክስ አደርግለት ነበር፡፡ ግን ማን ያደርጋታል፡፡ እንደዚህ እየተባሉ ብአዴን ከመሆን እዉነት ወደ ነበሩበት የዲኤ ስራ መመለስ ይሻላል፡፡

ለማንኛዉም ብአዴን ህወሃትን ቢንከባከበዉም ከዉግዘት አልተረፈም፡፡ መቀሌ ላይ እንዲሰማ ተብሎ በአማረኛ ስብሰባ ተዘጋጅቶለት «ብአዴን የሚባል ቡድን ቢስተካከል ይሻለዋል» አይነት ዛቻ ተላልፎለታል፡፡ እኔ ግን የሚገርመኝ ብአዴን እንዲህ ለህወሃት እያሽቋለጠ ህወሃት ግን ሁሌም ይከሰዋል፡፡ ነገ አዲሱ የአማራ ፓርቲ ወደ ስልጣን ሲመጣ ህወሃት ምን ሊዉጠዉ ነዉ፡፡

ህወሃት በነገራችን ላይ ኦህዴድንና ደህዴንን ሲናገር ሰምቼ አላዉቀም፡፡ ብአዴንን እንደ ዉሽማዉ ስለሚያየዉ እንደፈለገ ነዉ የሚጫወትበት፡፡

ለማንኛዉም አዉራዉ እንደጠፋበት ንብ ብአዴን ወዲያ እና ወዲህ እየተንገዋለለ ነዉ፡፡ በተለይም ሰሞኑን ገዱ አንዳርጋቸዉ በጉብኝት፣ እንዲሁም የባልተቤቱን ህክምና ለመከታተል ከባህርዳር አካባቢ በመጥፋቱ ብአዴን አባት እና እናት እንደሌለዉ ልጅ ተበታትኖ የት እንደሰነበተ አልታወቀም፡፡

ባጠቃላይ መቀሌ፣ አዳማ እና አዲስ አበባ ላይ እየተወራ ያለዉ የፖለቲካ ልዩነት እና ባህርዳር ላይ ያለዉን ጉምጉምታ ስናየዉ በዚህ ድርጅት ዉስጥ ያለዉ ጦርነት ገና እየተፏፏመ እንጅ እየቀነሰ አይመስልም፡፡ በዚህም ምክንያት ሃምሌ ላይ ኢህአዴግ ወደ አንድ ግንባር ያድጋል የሚለዉ ሃሳብ ዜሮ ነዉ፡፡ ህወሃት በዚህ እርግጠኝነት በሌለበት ሁኔታ ወደዚህ ዉሳኔ ደፍሮ ይሄዳል ተብሎ አይታሰብም፡፡

*****

አቶ በረከት ስምዖን አምባሳደር ሆኖ እንዲሾም ቢጠየቅም እምቢ ማለቱ ተሰማ

(ዘ-ሐበሻ) ከንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀንበርነቱን ከ6 ወር በፊት ራሱን ያነሳው አቶ በረከት ስምዖን አምባሳደር ሆኖ እንዲሾም ቢጠየቅም እምቢ ማለቱ ተሰማ::

እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በረከት ስምዖን እንዲሾም የተፈለገው በብራሰልስ ቤልጂየም. ነበር:: ሆኖም ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በርከት ጥያቄውን እንዳልተቀበለው ነው የተገለጸው::

በርከት በድርጅቱ ውስጥ የመገፋት ስሜት እንደሚሰማው የሚገልጹት ምንጮች በተለይ ከዚህ በፊት አሰናብቱኝ ብሎ የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገባ በኋላ እንደገና በድርጅቱ ውስጥ መታየቱ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል:: አሁንም የቤልጂየሙን የአምባሳደርነት ጥያቄ ያልተቀበለው በሃፍረት አልያም በጤና ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል::

አቶ በረከት ከኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስተርነቱና ከንግድ ባንክ የቦርድ አባልነቱ ራሱን ማንሳቱ አይዘነጋም::

አቶ በረከት ስምዖን፣ ከህወሃት ጋር በመሆን የእነ ዶ/ር አብይንና ለማን ቡድን ለመምታት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝና በኢህዴግ ውስጥ ያለው ተቀባይነት እየተመናመነ የመጣው አቶ በረከት፣ ከብአዴን ይልቅ ከህወሃት ጋር ጥምረት በመፍጠር እርሱና በህወሃት ዙሪያ የሚገኙ ጓደኞቹ የሚቆጣጠሩትን ስርዓት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ይህም እየከሸፈበት መሆኑ መዘገቡ አይዘነጋም::

****

የበረከት ስምኦን ሴራ እና የሁለቱ ብአዴኖች ፍጥጫ!

ጌታቸው አምባዬን የብአዴን ሊቀ መንበር፣ ቀድሞ አባዱላን ኋላ ደግሞ ሽፈራው ሽጉጤን ጠቅላይ ሚኒስትር ለማደረግ የእነ በረከት ሴራ፤

(አንጀቱ ያረረው ሞረሽ ነኝ፣ ከብአዴን ቤት)

፩. የሁለቱ ብአዴኖች ፍጥጫ፤
———————————
የስምኦን ልጅ በረከት አማራ ላይ ከሚሸርበው ተንኮል መቼም ተዘናግቶ አያውቅም፡፡ አጋዦች ሞልተውታል፡፡ ሲያስፈልገው ከህወሃት መንደር ይመዝዛል፡፡ ወደ ህወሃት መንደር ከመጓዙ በፊት ግን በብአዴን ቤት ያሉትን አጋሮቹን ይጠቀማል፡፡ ዋነኛ አጋሮቹ ደግሞ ሽማግሌዎቹና ባልቴቶቹ (በረከት፣ አዲሱ፣ ህላዌ፣ ታደሰ፣ ሁለቱ ገነቶች፣ ዝማም…።) ብአዴኖች ናቸው፡፡ ግቡን ለማሳካት ደግሞ አንዳንድ በብሔር አማራ፣ በተግባር ግን ጸረ አማራዊ ድረጊት ውሥጥ የተነከሩ ባንዳዎችን (እንደ ጌታቸው አምባየና አለምነው ዓይነቶቹን) ይጠቀማል፡፡

በብአዴን ቤት የመረረ የውስጥ ትግል ከተጀመረ ሁለትና ሦስት ዓመታት ሞልቶታል፡፡ ትግሉ በአማራነት ዙሪያ ነው፡፡ የነ በረከት ቡድን፣ “ትምክህት”እና “ነፍጠኝነት” የሚሉ ቃላትን በዱላነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ይወዷቸዋል፡፡ በእነዚህ ቃላት አማካይነት አማራን ሲሰድቡና ሲያዋርዱ ኖረዋል፡፡

አዲሶቹ ብአዴኖች ትምክህተኛና ነፍጠኛ የሚሉትን ቃላት ጠልተዋል፡፡ በእነዚህ መለኪያ የሚደረግ ፍረጃን አይቀበሉም፡፡ እንደውም ነውር (ታቡ) መሆን አለባቸው ይላሉ፡፡ እነ በረከት ግን የአማራን ሕዝብ ጥቅም ለማስከበር የሚንቀሳቀሱትን አዲሶቹን ትምህተኛና ነፍጠኛ በማለት ለማሸማቀቅ ይጥራሉ፡፡ በየስብሰባው በነጋ በጠባ ቁጥር መገምገሚያቸው ትምክህተኛና ነፍጠኛ የሚሉት ቃላት ናቸው፡፡ አዲሱ ብአዴን እነዚህን ጸረ አማራ አንድምታ ያላቸው ቃላቶች አይቀበልም፡፡

የነባሩ ብአዴን አቋም ያው የድሮውንና የነበረውን ማስቀጠል ነው፡፡ ለእነ በረከት አዲሱ ትውልድ አማራን የመምራት ብቃት የለውም፡፡ የለውም ብሎ ማመን ብቻ ሳይሆን በየቦታው ማጣጣል የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡

፪. ንጉሡ፣ ላቀ፣ አምባቸው፣ ለገሰና ተስፋዬ
———————————————
በተለይ ከአዲሱ የብአዴን አመራሮች ውስጥ ንጉሡ ጥላሁን፣ዶ/ር አምባቸው መኮነን፣ ላቀ አያሌው (የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ የነበረው) እና ለገሰ ቱሉ ከአሁን በኋላ አሮጌው ብአዴን የአዲሱን አመራር እጅ መጠምዘዝ እንደማይችል በግልጽ አማርኛ ነገረዋቸዋል፡፡ እጅን ጠምዝዞ ያሻውን ማስፈጸም ቀርቷል፣ የፈለጋችሁትን ማስፈጸም ከእንግዲህ የለም አሏቸው፡፡ እነ ንጉሡ (የገዱ ቡድኖችና ደጋፊዎች) ከዚህ በታች የተገለጹትንና ሌሎች ሐሳቦችን አንስተዋል፡፡ እንዲህ አሉ፣

• ከውስን አመራሮች ውጭ ብአዴን ተላላኪ ነው፡፡

• የሕወሃት የበላይነት አለ፣ ብአዴን አማራን እንዳይመራ ነጻነቱን ተነፍጓል፡፡

• አማራ ሲፈናቀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምበት ብአዴን ከአማራ ጋር አልቆመም፤ አሁንም እየተፈጸመበት ነው፡፡

• በፌደራል ሥርኣቱ አማራ ተጠቃሚ አልሆነም፣ አይደለምም፡፡

• የመብት ጥያቄ ስናነሳ እስራትና ግርፋት ይደርስባናል፣ ግንቦት ሰባት እንባላለን፣ የሱዳን ታርጋ ባለው መኪና በርካታ የበታች አመራሮች ተወስደው ተገርፈዋል፡፡

• ክልሉ ከየትኛውም ክልል በባሰ ሁኔታ ወደ ኋላ ቀርቷል፡፡

• የደህንነት እና የመካላከያ አመራሩ በአንድ ብሔር የተጥለቀለቀ ነው፡፡

• የተባረሩ የአማራ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ ሥራቸው ይመለሱ፡፡

• መላኩ ፈንታ ይፈታ ወዘተ…

በነገራችን ላይ ንጉሡ ጥላሁንን እና ላቀ አያሌውን ለመገሰጽ ከሞከሩት ውስጥ አንዱ ጌታቸው አምባዬ ነበር፡፡ ገነት ገብረ እግዚአብሔር የምትባለው ሕወሃት ደግሞ ስለ መላኩ ፈንታ ሲነሳ ስለምን ገብረዋህድስ እንዲፈታ አትጠይቁም አለች፤ ያው ዘር ከልጓም ይስብ የለ!

እንደውም ተስፋዬ ጌታቸውማ (በአለምነው የተተካው አዲሱ ብአዴን) አመራሩን ለማፍረስ በብአዴን ውስጥ የቀለም አብዮት እያካሔዳችሁ ነው አለ፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ የብአዴን የቀለም አብዮት በማለት ተስፋዬ የገለጸው ግቡ ደመቀ እና ገዱን በማንሳት የብአዴንን ሊቀመንበር ጌታቸው አምባዬን በማድረግ አመራሩን መበታተን ነው፡፡ በታትኖ ዳግም ሙቅረት (reconfiguration) በመሥራት በእነ በረከት “ክሊኮች” ብአዴንን ማጥለቅለቅ፤ ያው ይህም ከሸፈባቸው፡፡

፫. ደመቀ መኮንን
——————
ደመቀ መበርታት ከጀመረ ዋል አደር ብሏል፡፡ የደመቀን ቃል በመጠቀም “ብአዴን የራሱ ወርድና ስፋት ያለው ድርጅት እንጂ የማንም ተላላኪ አይደለም፡፡ ብአዴን ሌላ አንጋሽ አያስፈለገውም ፤ ብአዴን የሚታገለው የሚታመነው ለራሱና ለህዝቡ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ‘ኦን አወር ዴድ ቦድይ’ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ሊሆን አይፈቀድም” አለ፡፡ የስምኦን ልጅ በረከት እና አጋሮቹ እንደ ድሮው በብአዴን ቤት በማዳከር ወደ ፈለጉት መንገድ ለመጎተትም ለመጠምዘዝም ያደረጉት ፍልሚያ ከሸፈ፡፡ መክሸፍ እንደ እነ በረከት ሴራና ተንኮል!

፬. እነ በረከት አባዱላን ጠቅላይ ሚኒስትር ለማድረግ፤
———————————————————-
በረከት የብአዴንን ብሩህ ልጆች በልቷል፤ አስበልቷል፤ አቁስሏል፤ አስቆስሏል፤ አስሯል፤ አሳስሯል፡፡ በጣት የሚቆጠሩት ብቻ በማገገም ላይ ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ አድርጎም የበረከት ሆድ አይጠረቃም፡፡ በመሆኑም ሌላ ሴራ ጎነጎነ፡፡ በረከትና አሮጌዎቹ፣ ጌታቸው አምባዬን የብአዴን ሊቀመንበር ለማድረግ ደፋ ቀና አሉ… በዚህ ልፋታቸው ተደፍተው ቢቀሩም፡፡ ጌታቸው አምባዬ ሳይልኩት ወዴት፣ ሳይጠሩት አቤት ባይ ነው፡ ለነበረከትና ለህወሃት፡፡

ለበረከትና ለጌታቸው አምባዬ ሕወሃታዊ ጥምረት ምሳሌው መላኩ ፈንታ ላይ የሰሩት ደባ ነው፡፡ መላኩ ፈንታን ለማሳሰር የክስ መረጃዎችን ለበረከት ስምኦን የሰጠው ቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቤ ሕግ የነበረው ሳሙኤል ታደሰ ሲሆን መረጃ በመስጠት ለአደረገው አስተዋጽኦ ወሮታውን ለመመለስ ሲባል እንዲሁም የአቶ በረከትም ሚስት ጋር ወዳጅ ስለሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ሲለቅ በረከት የቦርድ ሰብሳቢ የነበረበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕግ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ተሹሟል፡፡ ንግድ ባንክ ሠርቶ ያማያውቅ የንግድ ባንክ የሕግ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ቪላ ቤት ቪ8 መኪና ጋር ተሰጠው፡፡ አማራን ማሳሰር እንዲህ ያሸልማል፤ ሸላሚዎቹም እነ በረከት ናቸው፡፡

ጌታቸው አምባዬ ብአዴንን ከተቀላቀለበት ጊዜ አንጻር ሲታይ መሆን የነበረበት ከአዲሶቹ ብአዴኖች ጋር ነበር፡፡ ያው እንደ አለምነው መኮንን አማራን የሚዋጋ ባንዳ ሆነ እንጂ፡፡ ይህ ሰው ክፍለ ሕዝብ ከመሆኑ በፊት የችግኝ ጣቢያ ውሃ አጠጪ ከዚያም የኅብረት ሱቅ ሠራተኛ ነበር፡፡ ጌታቸው የጤና እክል እንዳለበት (ኤች አይ ቪ፣ ኤድስ እንዳለበት) የታወቀ ነው፡፡ መጠጥና ሴት ነፍሱ ነው፡፡ የፍትህ ሚኒስትር ሆኖ የተሰጠውን ቪ8 ታርጋውን ቀይሮ ከቺቺኒያ ቦሌ፣ከቦሌ ቺቺኒያ ማታ ማታ ሲዘል አንድት ሴተኛ አዳሪን ባለጥቁር መስታዋት መኪና ውስጥ አስገብቶ ያለ ኮንዶም ካለደረግን በማለቱ ጩኸትና እሪታ በመፈጠሩ በፖሊስ ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ አድሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ ኮማንደር ግርማ ነው ያስፈታው፡፡ ያሠሩት ፖሊሶችም ከሥራ ተባረዋል፡፡ በተለይ ይቺ ታሪኩ በእነ እንቶኔ ቤት ስለምትታወቅ ያሻቸውን ያስደርጉታል፡፡ እሱም ተመችቷቸዋል፡፡ እንደውም ባልተቤቱ እሱን በያዘው በሽታ ስትሞት ሌላ አገባ፡፡ እሷን በመፍታት ከሕወሃት ሰፈር ትግሬ አገባ፡፡ ያው ተጠቃሎ ወደ ሕወሃት ዘንድ ገባ ማለት ይቻላል፡፡

እነ በረከት በብአዴን ቤት ያልተሳካላቸውን ሴራ ወደ ኢሕአዴግ ዘንድ ይዘው በሌላ ሴራ መጡ፡፡ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫንም ልክ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ እንደወጣ ሁሉ ሰው መመልመል ጀመሩ፡፡

በምልመላው አባዱላን ለጠቅላይ ሚንስትርነት አጩት፡፡ ሽፈራውን (ሞሪንጋን) ደግሞ ምክትል ለማድረግ ደፋ ቀና አሉ፡፡ አባዱላን ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ ረገድ አሁንም ድፍት አሉ፣ ይህ ሁሉ የሚሆነው በነበረከት ነው፡፡

ከተደፉበት ቀና ለማለት ፕላን B ያሉትን ካርታ መዘዙ፡፡ ሽፈራው ሽጉጤን ጠቅላይ ሚንስትር ማድረግ፡፡ እንግዲህ ይህ ሴራ ታወቀ፡፡ ሽፈራው ሽጉጤን ለማስሾም ደፋ ቀና ቢሉም አሁንም ተደፍተው ቀሩ፡፡ ደመቀ መኮንንም ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እራሱን አገለለ፡፡ ሌላ ተቀያሪ ፕላን አመጡ፤ ምክንያቱም በሁሉም ተደፉ፡፡ ያመጡትም የሊቀ መንበር ምርጫው እስከ ጉባኤ ደረስ እንዲራዘም ነበር፡፡

በዚህ ሁለትና ሦስት ዓመት በነበረው የብአዴን የውስጥ ትግል፣ በአዲሶቹ ቆራጥነት ድርጅቱ ከመፍረስ ድኗል፡፡ እነ በረከትን በከፍተኛ ሁኔታ ተገዳድረዋል፣ አማራን ለመወከል ጥረዋል፣ ይብላኝ ለእነ በረከት፡፡

“የኃጢአተኞች መንገድ ትጥፋ”፣ እንዲል ዳዊት በመጀመሪያው መዝመሩ፣ የእነ በረከትና የነጌታቸው አምባዬ መንገድ ትጥፋ፤ ፀረ-አማራ ናትና::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s