ደህንነቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በ24 ሰዓታት ውስጥ ከሃገር ለማስወጣት ቢዘጋጅም ዶ/ር ዓብይ ይህን ማስቆማቸው ተገለጸ | አንዳርጋቸውን ጥየቃ የአባቱ ቤት ዛሬም ተጨናንቋል

 

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ከ እስር ቤት ተፈትተው በአባታቸው ቤት ያልጠበቁት የሕዝብ አቀባበል የተደረገላቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከቤተሰብም ከደጋፊዎቻቸውም ጋር ሳይገናኙ በ24 ሰዓታት ውስጥ ደህነንቱ ከሃገር ሊያስወጣቸው ሲል ያስቆሙት ዶ/ር ዓብይ አህመድ መሆናቸው ተነገረ::

በደህነቱ ውሳኔ ውስጥ ጣልቃ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገ መቆየት እንደሚችል ማረጋገጫ ለቤተሰቡና ለ እንግሊዝ መንግስት እንደሰጠ ታውቋል::

በሃገር ውስጥ ሲቆይም የአንዳርጋቸው ደህንነት እንዲጠበቅ መንግስታቸው እንደሚሰራ ለ እንግሊዝ መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በኩል ማረጋገጫ እንደሰጡ ነው የተዘገበው::

የአቶ አንዳርጋቸው መለቀቅ ጉዳይ የህወሓት ተከፋይ ብሎገሮችን እጅጉን እያንገበገበ መሆኑ እየታየ ነው:: ዳን ኤል ብርሃኔ የተባለው የሕወሃት ብሎገር አንዳርጋቸው  በቀጥታ አለመሸኘቱ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያለውን ትርምስ የሚያሳይ ነው ሲል በአደባባይ ጽፏል::  አንዳርጋቸው ጽጌ ካለ ቭዛ ሃገር ውስጥ ያለ የውጭ ሃገር ዜጋ በመሆኑ ወዲያውኑ ዲፖርት ሊደረግ የገባው ነበር በሚል ተቃውሞውን አሰምቷል:: ትግራይ ኦላይን የተባለው ድረገጽም የአንዳርጋቸው ጽጌን መፈታት ኮንኖ ጽፏል::

በሌላ ዜና አዲስ አበባ ከጌቱ ኮመርሽያል ሴንተር ጀርባ (በኦሮሚያ ኢንተርናሽል ባንክ ጎን ባለው የውስጥ መንገድ) ቀጥታ ተሄዶ በሚገኘው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ቤት ሕዝብ ዛሬም እየጎረፈ መሆኑ ታውቋል:: ከአዲስ አበባ መረጃውን ያደረሱን ወገኖች እንደነገሩን “እንኳን ተፈታህ, ጀግናችን ነህ” የሚሉ ሰዎች አንዳርጋቸው ቤት በመምጣት ደስታቸውን ሲገልጹ ውለዋል::

አንዳርጋቸው አሁንም ለምን ያህል ጊዜ ኢትዮጵያ እንደሚቆይ ባታወቅም በትናንትናው ዕለት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ደስታቸውን ተሰብስበው ሲገልጹ አምሽተዋል:: በዋሽንተን ዲሲ, በቴክሳስ, በካሊፎርኒያ, በ እንግሊዝ, በስዊድን, በስዊዘርላንድ, በኖርዌይ, በደቡብ አፍሪካ እና በተለያዩ ከተሞች ሕዝብ በአጭር ጊዜ በመሰባሰብ ደስታውን ሲገልጽ ያመሸ ሲሆን በተለይ በካናዳ ቶርንቶ ከተማ ሕዝቡ በመኪና ተጭኖ በአደባባይ እየተዟዟረ ደስታው ሲገልጽ እንዳመሸ ብርሃን ቲቭ ከስፍራው በምስል አስደግፎ ካሰራጨው መረጃ ለመረዳት ተችሏል::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s