አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ 771 ሰዎች ከእስር ተፈቱ

 

ይቅርታ ለማድረግና ክስ ለማቋረጥ መሥፈርቱ ምን እንደሆነ አልተገለጸም

በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ፣ 771 ተከሳሾችና ፍርደኞች በይቅርታና ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲፈቱ ተደረገ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ቅዳሜ ግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ በሽብር ወንጀል ተከሰው የነበሩ 137 ግለሰቦች፣ አቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ አቶ ዓለማየሁ ጉጆና አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤልን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተከሰሱ 31 ግለሰቦች፣ በልዩ ሁኔታ የ27 ሰዎችና የአራት ድርጅቶች ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ክስ ተመሥርቶባቸው የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸው የነበሩ 576 ሰዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸውም አቶ ብርሃኑ አስረድተዋል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 የተሰጠውን ሥልጣን መሠረት አድርጎ፣ የፍትሕ ሥርዓቱን በሚመለከት ኅብረተሰቡ ሲያነሳ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ቅሬታዎችን በመመልከት፣ ከላይ የተጠቀሱት ተከሳሾችና ፍርደኞች ክሳቸው እንዲቋረጥና በይቅርታ እንዲፈቱ መደጉን አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

ክሳቸው የተቋረጠላቸው ተከሳሾች ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት እንደሆነ፣ ፍርድ ያረፈባቸውም ለይቅርታ ቦርድ ቀርቦና በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ውሳኔ ተሰጥቶበት መሆኑንና በአዋጁም በልዩ ሁኔታ እስረኞችን መልቀቅ እንደሚቻል በመደንገጉ ተግባራዊ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ቅዳሜ ግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ክሳቸው የተቋረጠላቸውንና ይቅርታ የተደረገላቸውን ግለሰቦችና ድርጅቶች በማስመልከት መግለጫ በሰጡበት ወቅት

የግንቦት ሰባት ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ አንዳርጋቸው፣ በሽብር ወንጀል ሁለት ጊዜ ክስ ተመሥርቶባቸው በዕድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ እንደተፈረደባቸው ይታወሳል፡፡ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ከዱባይ ወደ አስመራ ለመሄድ የመን ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ በፀጥታ ሰዎች ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ በቀጥታ ወደ ፌዴራል ማረሚያ ቤት ተወስደው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታስረው ላለፉት አራት ዓመታት ያህል ቆይተዋል፡፡ ከእስር እንዲፈቱ በዓለም አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ግፊቶች የነበሩ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት ትዕዛዝና የሥራ አቅጣጫ መሠረት፣ ዓርብ ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር መፈታታቸው ታውቋል፡፡

በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው ላለፉት አምስት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኙት፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና በሕግ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ የሁሉም ተከሳሾች ክስም ተቋርጧል፡፡

በሦስት የተለያዩ የክስ መዝገቦች ክስ ተመሥርቶባቸው በሁለቱ መዝገቦች ጥቂት ተከሳሾች በነፃ ሲሰናበቱ፣ አቶ መላኩና አቶ ገብረ ዋህድን ጨምሮ አብዛኛዎቹ በአንድ፣ በሁለትና በሦስት ክሶች ጥፋተኛ ተብለው የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት፣ ፍርድ ቤቱ ለማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዞ ነበር፡፡ በሌላ አንድ መዝገብም ጥፋተኛ ለማለት ወይም በነፃ ለማሰናበትም በተመሳሳይ ቀን ቀጠሮ ተይዞ ነበር፡፡

በአዋጅ ቁጥር 943/2008 ክስ የመመሥረትና ክስ የማቋረጥ ሥልጣን የተሰጠው ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ‹‹ጉዳዩን በጥልቅ በመመርመር የክስ መዝገቡን ማቋረጥ ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ክሳቸው እንዲቋረጥ፤›› በማለት፣ ክሱን እየመረመረው ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አቅርቦ ክሱ እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡

በመሆኑም በእነ አቶ መላኩ የክስ መዝገብ የተካተቱት፣ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ነጋ፣ አቶ ከተማ ከበደ፣ ላለፉት አምስት ዓመታት ክሳቸው ሲታይ የነበሩት አቶ ጌቱ ገለቴ (በሌሉበት)፣ አቶ ገብረ ሥላሴ ገብሬ፣ አቶ ስማቸው ከበደ፣ ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋዬ (የአቶ ገብረ ዋህድ ባለቤት)፣ የኢሊሊ ሆቴልና የገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ (በሌሉበት)፣ አቶ ፍፁም ገብረ መድኅን፣ ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ጌትአስ ኩባንያ፣ ኮሜት ትሬዲንግ ሐውስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበርና ነፃ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

በሌላ መዝገብ ክስ የተመሠረተባቸውና በ2009 ዓ.ም. መጨረሻ በከባድ የሙስና ወንጀል መጠርጠራቸው በመገናኛ ብዙኃን በወቅቱ በነበሩት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ተነግሮ በቁጥጥር ሥር የዋሉትና ክስ የተመሠረተባቸው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ፣ አቶ ዋስይሁን አባተ፣ አቶ አክሎግ ደምሴ፣ አቶ ዘርፉ ተሰማ፣ አቶ መስፍን ወርቅነህ፣ ወ/ሮ ስህን ጎበና፣ አቶ ጌታቸው ነገሪ፣ አቶ ነጋ መንግሥቱ፣ አቶ ሙሳ ሙሐመድ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል፣ አቶ ሲራጅ አብዱላሂ (ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት)፣ ኮሎኔል መላኩ ደግፌ፣ ትርሲት  ከበደ፣ አቶ ገዛኸን ኢጀራ፣ ቤዛዓለም አክሊሉ፣ አቶ ወንድሙ መንግሥቱ፣ አቶ ቢልልኝ ጣሰውና ማኅደር ገብረሃና ክስም እንዲቋረጥ ተጠይቆ ተቋርጧል፡፡

ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ስለተቋማቸው የሥራ ተግባርና ክስን ለማቋረጥ በአዋጅ ሥልጣን እንደተሰጠው ጠቁመው፣ ከላይ የተጠቀሱት 771 ግለሰቦችና አራት ድርጅቶች ክስ እንደተቋረጠና በይቅርታ እንደተፈቱ ከገለጹ በኋላ፣ ማስተናገድ የሚችሉት አንድ ሦስት ጥያቄዎችን ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ሰዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑን በመጠቆም፣ 31 ግለሰቦችን ብቻ ለይቶ መፍታትና በቅርቡ በ2009 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኃላፊነት ላይ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ምዝበራ ተጠርጥረው ክሳቸው እየተካሄደ ቢሆንም፣ የተወሰኑ ከሁለት ተቋማት ብቻ የተመረጡ ሰዎች በክስ ማቋረጥ ውስጥ እንዲካተቱ የተደረገው እንዴት እንደሆነና የመለያ መሥፈርቱ ምን እንደሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡

አቶ ብርሃኑ በሰጡት ምላሽ እንደተናገሩት፣ መፍትሔው ማሰርና መቅጣት ሳይሆን መፍትሔ የሚመጣበትን መሥራት ነው፡፡ ‹‹በሙስና ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው የተከሰሱት? ከ90 በላይ ክስ ተመሥርቶ በአንድና በሁለት ጉዳዮች ብቻ ክርክር ይካሄዱባቸው የነበሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ወደፊት ሙስና እንዳይፈጸም መከላከል፣ ድርጊቱ ከተፈጸመም ከመታሰራቸው በፊት በሚስጥርም ይሁን በሌላ መንገድ ማስረጃ ሰብስቦ ከተረጋገጠ በኋላ መጠየቅ ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡ እየያዙ ማሰር ብቻ ለውጥ እንደማያመጣ፣ በትልልቁ ላይ ትኩረት ተደርጎ ካልተሠራ በሽርፍራፊው ላይ ብቻ ትኩረት መስጠት ጥቅም እንደሌለው አክለዋል፡፡

የሽብር ተግባር ወንጀል ተከሳሾችን በሚመለከት በአንድም በሌላ ከፖለቲካ ጋር የተገናኘ መሆኑን ጠቁመው፣ የፖለቲካ ምኅዳሩን በማስፋት ሕግና ሕግን ተከትለው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ይቅርታው ቀጣይነት እንዳለውና እንደሌለው ተጠይቀው ‹‹ይቀጥላል፣ ግን መብት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ ክስ ተቋረጠ ማለት ወንጀል ወይም ጥፋት የለም ማለት አለመሆኑን አቶ ብርሃኑ ጠቁመው፣ የተቋረጠ ክስ ሊንቀሳቀስ እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡

በመገናኛ ብዙኃን ተጠርጣሪዎቹን ጭምር በማሳየት የመንግሥትንና የሕዝብን ሀብትና ገንዘብ መውሰዳቸውን የገንዘቦቹ ዓይነትና መጠን ተገልጾ፣ በርካታ ይዞታዎችም መኖራቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶች ታይተው በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የፕሮጀክቶቹ ስም እየተጠቀሰ ለግለሰቦች ጥቅም መዋሉና ሌሎችም ማስረጃዎች ቀርበው እያለ፣ ክስን ማቋረጥ በቀጣይ ለኅብረተሰቡ የሚያስተላልፈው መልዕክት ምንድነው? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ብርሃኑ፣ ምላሽ ሳይሰጡበት መግለጫቸውን አጠናቀዋል፡፡

ስርዓቱ ፀረ አማራ ነው! (ጌታቸው ሺፈራው)

አበበ ካሴ

የመጀመርያው አበበ ካሴ ይባላል! 20 ጥፍሮቹ ተነቅለው፣ ዘሩን እንዳይተካ ተደርጓል። ማዕከላዊ ተዘግቷል ተብሎ በማዕከላዊ ሰቆቃ የደረሰበት አበበ ካሴ ቃሊቲ በስቃይ ላይ ነው። የተቀየረለት በትህነግ ታጋዮች የሚተዳደር ሌላ አሰቃቂ እስር ቤት ነው!

ዮናስ ጋሻው

ሁለተኛው ዮናስ ጋሻው ነው። ግራ ጎኑ ሽባ ሆኗል። ዘሩን እንዳይተካ ተደርጓል። ማዕከላዊ ውስጥ ይህን የመሰለ ሰቅጣጭ ወንጀል ደርሶበት፣ ማዕከላዊ ተዘጋ ተብሎም ዮናስ አልተፈታም። ክሱ አልተቋረጠም!

ፈረደ ክንድሻቶ

ሶስተኛው ፈረደ ክንድሻቶ ይባላል። መቀሌ ወስደው ዘሩን እንዳይተካ አድርገውታል። አሁንም በእስር ላይ ነው!

አስቻለው ደሴ

አራተኛው አስቻለው ደሴ ነው። ዘሩን እንዳይተካ ተደርጓል። የተሰቃየበት ማዕከላዊ ተዘጋ ከተባለ በኋላ እንኳን እሱ በቂሊንጦ ብዙ ስቃይ ደርሶበታል። አሁንም በእስር ላይ ይገኛል።

አራቱም በአርበኞች ግንቦት 7 ስም የታሰሩ ናቸው። ይህ ፀረ አማራ ስርዓት ዘራቸውን እንዳይተኩ አድርጓል። በቁማቸው ገድሏቸዋል። የትህነግ ዘረኛ ታጋዮች ከሚመሩት ማዕከላዊ ወጥተው እነዚህ ዘረኞች የሚያስተዳድሩት ሌላ የሰቆቃ እስር ቤት ይገኛሉ!

ዶ/ር አብይ ከተመረጡ በኋላ እስረኞች እየተፈቱ ነው። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ክስ ተቋርጧል። አባል ናችሁ ተብለው የታሰሩት የአማራ ወጣቶች ግን መስለቢያው ማዕከላዊ ተዘጋ ከተባለ በኋላም፣ የተቀየረላቸው ሌላ የስቃይ እስር ቤት ነው። ክስ ተቋረጠ እየተባለ እንኳን በሕዝብ ላይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመባቸው ወጣቶች አልተፈቱም።

የሀገሪቱን ዶላርና ዩሮ በታንከር አጭቆ የተገኘ ሌባ ሲፈታ፣ የደሕንነት መስርያ ቤቱ ታወቂ ገዳይ ሲፈታ፣ ስም ስላላቸው በርካታ የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ሲፈቱ ለሕሊና የሚሰቀጥጥ መንግስታዊ ወንጀል የተፈፀመባቸው ወጣቶች ግን የስቃይ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ!

አራቱ የሰቆቃ ሰለባዎች በሌሎች ወንድምና እህቶቻቸው ላይ ለሚፈፀመው ማሳያ እንጅ ብቸኞቹ አይደሉም። አሁንም። በርካታ ንፁሃን በስቃይ እስር ቤት ይገኛሉ። በመንግስት በጀትና ፖሊሲ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፀምበት ማዕከላዊ ተዘግቶም በእስር ላይ ናቸው። ክስ ለ5ኛ ዙር ሲቋረጥም እነሱን የሚያካትት አልሆነም። ይህ ስርዓቱ ፀረ አማራ ስለመሆኑ ዋና ማሳያ ነው! ስርዓቱ ፀረ አማራ ነበር! አሁንም ፀረ አማራ ነው!

ዶ/ር አብይ ለምን አዜብን ሾመ? (ጌታቸው ሺፈራው)

ጌታቸው ሺፈራው

Azeb Mesfin on Zami Radio

ትህነግ/ህወሓት ባለፈው 27 አመት ያሳየን “ብቃት” ችግር ያለባቸውን፣ ሕዝብም ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች “አክ እንትፍ” ያሏቸውን እሱ ጋር በማስጠጋት ደካሞችን መጠቀሙ ነው። ለዚህ በምሳሌነት መቀሌ ሄደው “ነፍጠኛ እና ትምክተኛ ብለን የመሳደብ መብታችን ተነፈግን” እያሉ የሚያለቅሱትን የብአዴን ጡረተኞች መጥቀስ ይቻላል። እነ ህላዊ ዮሴፍ በትህነግ የተመረጡት ከሕዝብ የተጣሉ በመሆናቸው ነው። ይሰጡት የነበረው አገልግሎት ሕዝብን መዝለፍ፣ ለህዝብ የቆመውን ማስጠቃት ነበር።

– ዶ/ር አብይ አህመድ አዜብ መስፍንን የሜቴክ ቦርድ አባል አድርጎ ሾመ ሲባል ብዙ ደጋፊዎቹም ቅር ሳይሰኙበት አልቀሩም። ተቃዋሚዎቹም “ብለናችሁ ነበር” ብለዋል። አዜብን በእውቀቷ ሾማት የሚል አይገኝም። አዜም ከሰራተኞች ጋር ተግባብታ ትሰራለች ማለት አይቻልም። መለስ ዜናዊ በመተ ማግስት አንድ የውጭ ጋዜጠኛ የመለስ ዜናዊ አድናቂ መሆኑን ፅፎ ነበር። መለስን የሚያደንቀው ለኢትዮጵያ በሰራው መልካም አይደለም። በጎ አሰራም ብሎ ይመሰክራል። መለስ ዜናዊ ለጉብኝት ወደ ውጭ ሀገር በሄደበት ወቅት ጋዜጠኛው ለቃለመጠይቅ ቀጠሮ አስይዞ እየጠበቀ ነው። አንደኛው ክፍል ውስጥ። በወቅቱ ባልና ሚስቱ ይጨቃጨቃሉ። በአብዛኛው የሚሰማው የአዜብ ድምፅ ነበር። በመጨረሻ በሩን መለስ ጆሮ ላይ ጠርቅማበት ወጣች ይላል ጋዜጠኛው። እናም ጋዜጠኛው መለስ ዜናዊ ይችን ሴት ችሎ በመኖሩ ብቻ ጀግና ነው ይላል። በአጭሩ አዜብ ፀባይ የራቃት ሴት ነች። ለባሏ እንኳ ክፉ ናት።

– አዜብ የባሏን ስልጣን ተጠቅማ ብዙውን ባለስልጣን ከፍ ዝቅ አድርጋለች። በባሏ ስልጣን ተመክታ ብዙውን አዝዛለች። ሀብት አካብታለች። ባለስልጣናቱን ለባሏ ከማሳጣት ባሻገር ስልጣንና ገንዘብ የመስጠትና የመቀማቱ ስራ ላይ እንደነበረችበት ብዙዎቹ ይናገራሉ። አዛዥ ናዛዥ ነበረች። በመለስ ሞት ማግስት ግን ያ ሁሉ የአዜብ አቅም ተናደ።

– ከመለስ ሞት በኋላ ስለ አዜብ ብዙ ነገር ተብሏል። በሙስና ለማባረር ለማሰር አስፈራርተዋታል። በየ ግምገማው አብጠልጥለዋታል። በብሔራዊ ቴሌቪዥኑ ከማዕከላዊ ኮሚቴ መባረሯን አስወርተውላታል።

– ከቤተ መንግስት እንኳን አልወጣም የሚያስብል የገገረ አመል ያላት አዜብ ከመለስ በኋላ የገፋችው፣ የጎነተለችው ሁሉ ዝቅ አድርጎ ሲያያት፣ ባገኘው አጋጣሚ ሲበቀላት፣ የለመደችውን ለማዘዝ ስትጥር ሲያፌዝባትና ሲያዋርዳት እንደተሸነፈች ሴት በር ዘግታ ከማልቀስ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራትም። “መለስ ማረኝ” ብትለው፣ መለስ አይመጣም።

– ከእነ ገብረዋህድ ጋር በሌብነት ቂሊንጦ ታስረው የነበሩት የትህነግ ባለሀብቶች አዜብ ከማዕካላዊ ኮሚቴ ተባረረች ተብሎ በኢቲቪ በመነገሩ ሲጨፍሩ አድረዋል። አዜብ ያስቀየመችው ብዙ ነው። በእሷ ውድቀት የሚደሰተው በርካታ ነው። በአገኘው አጋጣሚ የሚያዋርዳት ሞልቷል። ከትህነግ/ህወሓት ሰፈር! በቀኗ ያደረገችው፣ ቀን ሲጥላት አግኝቷታል!

– ትህነግ በወልቃይት ጉዳይ ላይ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ አዜብ መስፍን “እኔ የወልቃይት ተወላጅ ነኝ። ወልቃይት የትግራይ ነው።” የሚል ሰፊ መግለጫ እንድትሰጥ ጠይቋት እንደነበር ተገልፆአል። በባሏ ስልጣን ተመክታ ስታዛቸው፣ ስታሾከሹክባቸው፣ ስትነጥቃቸው ከነበሩት የትህነግ ካድሬዎች ጋር በገባችው የከረረ ጠብ ምክንያት መግለጫውን አልሰጥም ብላለች። አዜብ መግለጫውን አልሰጥም ያለችው ለትህነግ አስተሳሰብ ወጥታ፣ ለእውነት ቆማ አይደለም። ነገም ከተመቻት መግለጫ ትሰጣለች። ነገር ግን ስታዝዛቸው የነበሩት ካድሬዎች ጋር በተፈጠረ አምባጓሮ መግለጫ ለመስጠት አይኗን በማታሽበት ጉዳይ ላይም አሻፈረኝ እንዳለች ተሰምቷል።

ታዲያ ይችን ሴት ዶ/ር አብይ ለምን ፈለጋት?

– አዜብ አቅም የላትም፣ ፀባይ የላትም። ሙሰኝነቷ የታወቀ ነው። በትህነግ ሰዎች ተጥላለች። “መለስ ማረኝ” ስትል ታመጭቀው የነበረው ባሏ ባይደርስላትም፣ ዶ/ር አብይ አህመድ ደርሶላታል። ዶ/ር አብይም የደረሰላት ደካማነቷን ፈልጎ ነው። በዚህ ወቅት ስታዛቸው፣ስልጣን ስትሰጥ፣ ስትነጥቃቸው በነበሩት የትህነግ ካድሬዎች የተናቀችውን አዜም መስፍንን ያክል ከትህነግ ሰፈር ታማኝ ሰው አያገኝም።

– ለአዜብ ዶ/ር አብይ ደም መላሽ ነው። ከስልጣን ያባረሯትን፣ በባሏ ተመክታ ስታሳጣቸው ስለነበር፣ ከመለስ ሞት በኋላ ያስለቀሷትን የትህነግ ጉምቱዎች ከስልጣን ገፍቷቸዋል። የተጣለችውን አዜብን እንደገና “ሹመት” ሰጥቷታል። ባትሰራበትም ባጇንም ለእነ ስብሃት ነጋ በማሳየት ትልቅ ደስታ ታገኛለች።

– ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን እንደመጣ “አብይ አያዘንም” ብለው ስልጣን የለቀቁት የሜቴክና የኢንሳ ኃላፊዎች ናቸው። ኢንሳ ላይ ተመስገን የሚባል አብይ እንደልቡ የሚያዘውን የብአዴን ካድሬ ተክቷል። ክንፈ ዳኘው አዜብ ቀን ሲጥላት ሲገላምጧት ከነበሩት መካከል መሆኑ ነው። ክንፈ ዳኘው ቢለቅም መስርያ ቤቱ በትህነግ ካድሬዎች የተሞላ ነው። እነዚህ ካድሬዎች የብአዴኑ አዲስ ሹመኛ አምባቸው መኮንን ደፍሮ አይናገራቸውም። ድክመታቸውን የምታውቀው፣ እንደገና ቀን ወጣልኝ የምትለው አዜብ ግን ልክ ልካቸውን ለመንገር፣ እንደፈለገችው ለማሳጣት፣ አስፈላጊ ከሆነም ከስልጣን እንዲባረሩ ለማድረግ ወደኋላ አትልም። ይህን ደግሞ አብይ ቃል ገብቶላት እንደሚሆን ግልፅ ነው። በመሆኑም አዜብ ወደ ሜቴክ የተላከችው በአምባቸው ጀርባ ሆነ እነ ክንፈ በሰገሰጓቸው ካድሬዎች ቀስት እንድትወረውር ነው። ሜቴክ ደግሞ ሰፊ ነው፣ ሀብታም ነው። ብዙ ቦታ ያደርሳል።

– ዶ/ር አብይ ለተጣለችው አዜብ ሲደርስላት፣ በሜቴክ የምታደርግለት ውለታ ብቻ በቂ አይደለም። አዜብ የትህነግ ሰዎችን ድክመት ታውቃለች። ማህበራዊ ህይወታቸውን ታውቃለች። ባሏ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የድብቁን ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ የትህነግን ካድሬዎች ውስጠ ሚስጥር ታውቃለች። የሜቴክ የቦርድ አባል አድርጎ ሲሾማት ብዙ ቅሬታ የደረሰበት አብይ፣ ሌላ ስልጣን ሊሰጣት አይደፍርም። ከዚሁ ተሸጉጣ ግን የትህነግን ሰዎች ውስጠ ሚስጥር ለእሱ በማቀበል፣ በአጭሩ በማሾክሾክ ቀላል የማይባል አበርክቶ ታደርጋለች። አዜብ መስፍን ዶ/ር አብይ ካደረገላት ውለታ፣ ያዋረዷትን የትህነግ ሰዎች በማሳጣት፣ አጋጣሚውን ሁሉ ተጠቅማ ለአብይ የተቻላትን በማድረግ ወደ ኋላ አትልም። አብይ አሁን ላደረገላት “ከአሁን በኋላ ብሞትም አይቆጨኝ” እንደምትል ግልፅ ነው። አብይም በቦርድ አባልነት ብቻ ደንበኛ መረጃ አቀባይ አግኝቷል። ዶ/ር አብይ የአዜብ ባል የሚታወቅበትን በደካሞች መጠቀም ስልት በአዜብ ጀምሮታል። ነገሩ በሰፈሩት ቁና ነው! የመለስ በደካማ የመጫወት ግፍ በሚስቱ ደርሷል! ጠንካራ በሬ፣ ከሞተ በሬ ቆዳ በተገኘ ጠፍር ተጠልፎ ይወድቃል። ዶ/ር አብይም የትህነግ ሰዎች ባሏ ሲሞት ጠብቀው በገደሏት አዜብ የምትባልት ጠፍር የበሬዎቹን የትህነግ/ህወሓት ፖለቲከኞች ለመጥለፍ የቻለውን ሁሉ ያደርጋል። አዜብ በሜቴክ የቦርድ አባልነት የተሾመችው ትህነግን በመጥለፊያ ጠፍርነት ነው!

አሜሪካዊው ፕሮፌሰር ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያላቸው ምልከታ

– blind –
Click Here to Continue to blind

ፕሮፌሰር ታይለር ኮዌን (ዶ/ር) ካስተናገዷቸው በርካታ ጥያቄዎች ውስጥ ስለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ስለ ብድር ዕዳ፣ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ የመፍቀድ ጥቅሙና ጉዳቱ፣ ወዘተ ተጠይቀዋል፡፡

በኢኮኖሚስቱ ዕይታ መሠረት ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ይልቅ ተስፋ የሚጣልባት ሆናለች፡፡ ይኸውም በሌሎች አገሮች ዘንድ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሲቀዛቀዙ በኢትዮጵያ ግን እያቆጠቆጡ መገኘታቸው፣ ላለፉት አሥር ዓመታት በአማካይ የአሥር በመቶ ዕድገት እያስመዘገበች የቆየች አገር መሆኗ ብቻም ሳይሆን፣ የአገሪቱ ሰፊ የሰው ሀብት ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ትልቅ የለውጥ ተስፋ ያለው በመሆኑ ጭምር ኢትዮጵያ ከተቀረው አፍሪካ ይልቅ የተሻለ መንገድ ላይ የምትገኝ አገር ስለመሆኗ ፕሮፌሰር ታይለር አስረድተዋል፡፡

ይህም ሆኖ አገሪቱ ወሳኝ የሚባሉ ችግሮች ተደቅነውባታል፡፡ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚመራው የመገበያያ ገንዘቦች የምንዛሪ ተመን፣ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የሚሆኑ የግብይት መድረኮች እንዳይበራከቱ እንቅፋት ይሆናል ይላሉ፡፡ መንግሥት በውጭ ምንዛሪ ተመንና በወለድ ምጣኔ ላይ የሚከተለው አሠራር ገበያ መር መሆን እስካልቻለ ድረስ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት አጋዥ የሆኑ ገበያዎችን የማስፋፋት እንቅስቃሴዎች እንደሚገቱ ጠቅሰዋል፡፡

ይኼንን ሲያብራሩም፣ በመንግሥት ለወለድ የሚቀመጠው ምጣኔ ገበያው ከሚሰጠው መጠን ይልቅ ከ30 እስከ 33 በመቶ ቅናሽ ያለበት በመሆኑ የገበያውን መዛባት ያስከትላል፡፡ ይህ በሆነበት ወቅት ደግሞ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱን መፍታት ከባድ እንደሚሆን አሳስበዋል፡፡ ምንም እንኳ የሚያስከትላቸው ከባድ ጫናዎች ቢኖሩም፣ እነዚህ ጫናዎች ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆዩ በመሆናቸው መንግሥት የምንዛሪ ተመን ላይ የሚያስቀምጠውን ምጣኔ እንዲያነሳ ጠይቀዋል፡፡ የወለድ ምጣኔውን ማንሳት ቢያንስ ለሁለትና ሦስት ዓመታት መንግሥትን ችግር ውስጥ ቢከተው ነው ያሉት የኢኮኖሚክስ ምሁሩ፣ ይህ ዕርምጃ ግን ለኢኮኖሚው የረዥም ጊዜ ዕፎይታ እንደሚያስገኝ ይሞግታሉ፡፡

በቴክኖሎጂ መስክ የኢትዮጵያ አዝማሚያ ብዙም የሚባልለት ባለመሆኑ፣ ይህም ትኩረት ይሻል ብለዋል፡፡ በቴክኖሎጂ መስክ ከፍተኛ የሰው ኃይል ማሰማራት ስላለው ጠቀሜታ በመተንተን ሐሳባቸውን አካፍለዋል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ምርት ሰጪ እንዲሆን የማድረግ ሥራ መንግሥትን እንደሚጠብቀውም አክለዋል፡፡

የውጭ ባንኮች እንዲገቡ ቢፈቀድ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ይቀረፍ እንደሆነ ለተጠየቁት ሲመልሱ፣ አይቀረፍም የሚል ፈርጣማ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ለዚህ ምላሻቸው ማብራሪያቸው አሁንም አገሪቱ የምትከተለው የተዛባ የምንዛሪ ተመንና የወለድ ዋጋ አቅርቦትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ የውጭ ባንኮች ቢገቡም የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ሊፈታ አይችልም የሚል መከራከሪያ ያዘለ ምላሽ አቅርበዋል፡፡ የውጭ ባንኮች ቢገቡ፣ አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ የፋይናንስ ሥርዓት ይዘው እንደሚመጡ እንደሚጠበቅ፣ ልዩ ልዩ የፋይናንስ አገልግሎቶችና ምርቶችም እንደሚመጡ፣ የውጭዎቹ አዎንታዊ ተፅዕኖ የአገር ውስጥ ባንኮችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ይገልጻሉ፡፡ ይሁንና ብር ከውጭ ገንዘቦች አኳያ የተሰጠው የመገበያያ ዋጋ እስካልተስተካከለ ድረስ አገሪቱ የካፒታል መዛባት ውስጥ እንደምትዋልል ይጠበቃል፡፡

መንግሥት የአገሪቱ ባንኮች ያላቸው አቅም፣ የካፒታል መጠንና የቴክኖሎጂ ብቃት ከውጭ ተፎካካሪዎች ጋር የሚያወዳድራቸው አይደለም በሚል ምክንያት የውጭ ባንኮች እንዳይመጡ መከልከሉ ይታወቃል፡፡ ይህ ግን የአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገትና መስፋፋት በጊዜ ሒደት አንዱ ባንክ በሌላው እንዲጠቃለል የሚያስገድድበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆንም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ በዚህ ሒደት ትንንሾቹ ባንኮች እየከሰሙ ትልልቅ ባንኮች እንደሚወለዱ ይጠበቃል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የተከማቸው የውጭ ብድር አገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚገዳደርበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም እንደተለመደው ማደጉን እየገታ፣ ለልማት ይውል የነበረው ገንዘብ ለዕዳ ክፍያ እየዋለ የኢኮኖሚውን የሙቀት መጠን እያቀዛቀዘው እንደሚሄድ ሥጋት አጭሯል፡፡ በአንድ ወቅት ቻይናም በከፍተኛ የዕዳ መጠን ተዘፍቃ እንደነበር ያስታወሱት ፕሮፌሰር ኮዌን፣ ኢትዮጵያ ያለባት የዕዳ መጠን የኢኮኖሚ ዕድገቷን የሚፈታተነው ከሆነ አሸንፎት ካቀዛቀዘው ከባድ ሁኔታዎች እንደሚፈጠሩ አሳስበው ይህም ሆኖ የአገሪቱ የወደፊት ዕድል ጨለምተኝነት እንደማይታበት ይናገራሉ፡፡

በውጭ ኢንቨስትመንት ረገድ፣ ኢትዮጵያ በከባድ የገጽታ ድርቅ ስትመታ መቆየቷን ገልጸው ልሂቃኑና ጉምቱዎቹ የአሜሪካ ኢኮኖሚስቶች ሳይቀር በኢትዮጵያ እየታየ ስላለው መልካም ነገር፣ እየተከናወነ ስላለው ጉዳይ ብዙም ዕውቀቱ እንደሌላቸው ጠቅሰዋል፡፡ በየወቅቱ በስዊዘርላንዷ ዳቮስ ከተማ እየተገናኙ የሚመክሩት የዓለም ጠበብቶቹ ኢትዮጵያን እንዲያውቋት ለማድረግና አገሪቱም ከውጭ ኢንቨስትመንት በብዛት ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያግዙ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች እንደሚያስፈልጓት ፕሮፌሰር ኮዌን ይመክራሉ፡፡ የሕዝብ ግንኙነት ዘመቻውን ራሷ አገሪቱ በቀጥታ የምታከናውነው ከሚሆን ይልቅ፣ ለአገሪቱ ቅኑዓን የሆኑ ጸሐፍት ስለአገሪቱ ገጽታ እንዲያስተጋቡ ማድረግ እንደሚበጅ መክረዋል፡፡

አዲስ አበባ እንደ ህንድና ናይጄሪያ ከተሞች መጨናነቅ እንደጀመረች ማየታቸውን የገለጹት ፕሮፌሰር ኮዌን፣ የከተማይቱ ገጽታ የህንድ ከተሞች ከ25 ዓመታት በፊት ያለፉበት ሁኔታ እንደሚያስታውስ ዘክረዋል፡፡ በመሆኑም በከተማይቱ የሚታየው የመኪና ጭስ የሰዎችን ጤና የሚፈታተንበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ስለመሆኑ አመላካች እንደሆነ፣ የትራፊክ መጨናነቁም ለከተማ ገጽታ አስቸጋሪ እንደሚሆን አሳስበው፣ ይህ በቶሎ መለወጥ ካልቻለ ከተማዋ ከማትወጣበት አስቀያሚ ሁኔታ ውስጥ እንደምትወድቅ ገልጸዋል፡፡

ስለ ዓለም ባንክ፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም የንግድ ድርጅት ወቅታዊ ጉዳይ ሕዝብ ዘመም አቀንቃኝነት ወይም ፖፑሊስት አራማጆች በምዕራቡ ዓለም ከመምጣታቸው አኳያ ለወደፊቱ ኢትዮጵያ ምን ይጠብቃታል? ምንስ ልትጠቀም ትችላለች? ለሚለው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ፀረ የዓለም ባንክ አቋም እንዳለው ሰው አትመልከቱኝ እንጂ የዓለም ባንክ ባይኖር እንኳ ኢትዮጵያ ምንም የምታጣው ነገር የለም፤›› ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ እነዚህ ተቋማት የነበራቸውን አስፈላጊነት በአሁኑ ወቅት እንዳጡት፣ ምናልባትም በቀውስ ውስጥ የሚገኙ እንደ አርጀንቲና ያሉ ጥቂት አገሮች አሁንም ድረስ የዓለም ባንክ አሊያም የዓለም የገንዘብ ድርጅት ትልቅ ጠቀሜታ ሊሰጧቸው እንደሚችሉ አብራርተዋል፡፡ ‹‹የዓለም የገንዘብ ድርጅት ቀውስ ላይ አተኩሮ የሚሠራ ተቋም ነው፡፡ ከእሱ ጋር አለመሥራት ግን አሳዛኝ ክስተት አይሆንም፤›› ብለውታል፡፡

ስለ ድሬዳዋ ዝም አንልም! – በሓይላይ ብርሃነ


ስለ ድሬዳዋ የምንጮኽው ስለተወለድንባት ስለአድግንባት ወይም ስለ ኖርንባት ብቻ አይደለም:: ስለ ድሬዳዋ የሚገደን ከተቆረቆረችበት ጊዜ ጀምሮ አብሯት የኖረው የአብሮነት እሴት :የኢትዮጵያውያን ሁሉ የማንነት አሻራ: የፍቅር ከተማነቷ: ኗሪዎቿን ሁሉ ሳትለያይና በጎሳ በሃይማኖት ሳትነጣጥል አቅፋ ና ደግፋ የመያዝ ባህሏ እየተሸረሸረ በምአስመሳይነት እየተታካ ስለሆነ ጭምር ነው::

ተወልደህ አድገህ መኖር የማትችልባት ከተማ!

ድሬዳዋ በአሁን ሰአት እንኳን በቅርብ ለሚመጡ ተወልደውና አድገው በተለያየ ሙያ ተመርቀው ስራ ማግኘት የማይችሉባት ከተማ ሆናለች::የድሬዳዋ ቻርተር በግልፅ አማረኛ ቋንቋ የስራ ቋንቋ እንደሆነ ቢደነግግም ነገር ግን በስራ ላይ ሊተገበር አልቻለም በዚህ የተነሳ በተለያዬ ሙያ በተለይም በግብርና : በጤና ት በመምህርነት ( የመጀመርያ ደረጃ) ተመርቀው ሶማሊኛ ወይም ኦሮምኛ ቋንቋ ባለመቻላቸው ስራ መያዝ ያልቻሉ ብዙ ናቸው:: ይሄን መስፈርት ባለሟሟላታቸው በቢፒአር ስበብ ስራቸውን ያጡ በርካቶች ናቸው:: በዚህ ምክንያት በትምህርት ደረጃቸውና በአገልግሎታቸው የሚገባቸውን እድገት ማግኘት ያልቻሉ ብዙ ናቸው:: በአጠቃላይ በዚህ ምክንያት ድሬዳዋ ለተወላጆቿ ና ለኗሪዎቿ ምቹ ባለመሆኗ ብዙዎችልስደት ለመዳረግ ተገደዋል::

የ40:40:20 ፖለቲካ!

የምርጫ 97 ድሬዳዋ ላይ ቅንጅት ማሸነፉን ተከትሎ በ1999 ዓ.ም የኢህአዴግ ፅ/ቤት ለመጀመርያ ጊዜ ተከፈተ:: የፅሕፈት ቤቱን መከፈት ተከትሎ ፈፅሞ ምንም አይነት ህጋዊ ድጋፍና ማእቀፍ የሌለው በቻርተሩም የማይታወቅ 40:40:20 የሚባል ፖለቲካ መተግበር ጀመረ:: የዚህ ፖለቲካ ውሳኔ በኦሮሞ ና በ ሱማሌዎች መካከል ያለውን የይገባኛል ውዝግብ ማርገብ አላማው ያደረገ ቢሆንም ነገር ግን አንደኛ የአብላጫውን ህዝብ ከግምት ያላስገባ መሆኑ እና የህዝብ ይሁኝታ ያላገኘ በአናቱም የከተማውን መተዳደርያ ያላገናዘበ ህገ-ወጥ ነበር:: ይሄ ውሳኔ የህዝብን ቁጥር መሰረት ያደረገ ቢሆንም ነገር ግን ከእውነታውና ከራሱ ከመንግስት የቤት ቆጠራ ዳታ ጋር የማይገናኝ ነበር::በነገራችን ላይ በወቅቱ በነበረው የህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ መሰረት ከአጠቃላዩ ህዝብ ውስጥ ሶማሌ 13.9% ኦሮሞ 48% አማራ 27.7% ነበር:: ነገር ግን በአባይ ፀሃዬ የወቅቱ ውሳኔ መሰረት 40% የምክር ቤት ወንበርና የሃላፊነት ቦታዎችን ሱማሌ እንዲይዝ 40% ደግሞ ኦሮሞ እንዲይዝና ምንም እንኳን ከኦሮሞ ቀጥሎ በህዝብ ብዛት አብላጫውን የሚይዘው አማራው ቢሆንም 20% ከሌሎች( ትግሬ እና ደቡብ) ጋር ተጋርቶ እንዲይዝ ተወሰነ:: ይሄ የ40:40:20 ፖለቲካ ለብዙዎች ስደትና በተወለዱበት ከተማ መኖር እንዳይችሉ ምክንያት ሆኗል::

የፈረቃ አገዛዝ!

ከላይ ያለው እንደተጠበቀ ሆኖ ድሬዳዋን ከሌላው ልዩ የሚያደርጋት በፈረቃ የምትተዳደር መሆኗ ነው:: የቁጥሩ ፖለቲካ እንደተጠበቀ ሆኖ ድሬዳዋ ስትነሳ በብዙዎች ዘንድ ስማቸው በክፉ የሚነሳው አባይ ፀሃዬ ውሳኔ መሰረት ሁለት አመት ኦሮሞ ሁለት አመት ሶማሌ እየየኦሮሞው እንዲመሯት ተወሰነ:: በዚህ መሰረት አንዳንዶቹ እንደሚሉት “በፈረቃ እንዲዘርፏት” ተደረግ:: ከሁሉ በላይ ግን አንዱ የኦሮሞው ከንቲባ ያቀደውን ሳይጨርስ ስልጣኑን እንዲያስረክብ ስለሚደረግ የሶማሌውም ያቀደውን ሳይተገብር ስልጣኑን ለማስረከብ ስለሚገደድ የድሬዳዋ የልማት ነገር ” የውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ” እንዲሆን ተገዷል::

አፍንጫችሁን ተይዛችሁ!

አቶ አባይ ፀሃዬ ከላይ የተገለፀውን የቁጥር ና የፈረቃ ፖለቲካ ለማስተዋወቅ በጠሩት የሁሉም ብሄሮች ሽማግሌዎች እና ካድሬዎች ስብሰባ ላይ ከሁሉም ብሄሮች ሽማግሌዎች ና ካድሬዎቹ ጭምር ከፍተኛ ተቃውሞ ቢገጥመውም ማሰመኛቸው ዱላ ና ማስፈራሪያ የሆኑት አባይ ፀሃዬ ግን “ወደዳችሁም ጠላችሁም አፍንጫችሁን ተይዛችሁ ትቀበላላችሁ” በማለት የአንባገነናዊነታቸውን ጫፍ ለማሳየት የሞከሩ ሲሆን የከዚራ አድባሮች ወ/ሮ ከበቡሽ እና ወ/ሮ ሩቅያ ” ደርግም አፍንጫችንን ይዞ አልገዛንም” በማለት የእንባገነኑን መድረክ ረግጦ በመውጣት የድሬዳዋ የብእሴት እናትነታቸውን ና ያለመነጣጠል እሴትን በተግባር ማሳየት ችለው ነበር::

በኣጠቃላይ ድሬዳዋ ህጋዊነት ቦታ ያጣበት : ለሌላው የሚተርፈው ይአብሮነት እሴት የጠፋበት ሰዎች በኦሮሞነታቸው : በሱማሌነታቸው : በአማራነታቸው ብቻ ባይወራም ከፍተኛ ግፍ የሚፈፀምባቸው: ህዝቡ በመልካም አስተዳደር በሙስና በዴሞክራሲና በሰብአዊ መብቶች እጦት የሚሰቃይባት ከሀሩሩ ጋር የምድር ሲኦል እየሆነች የመጣች ከተማ ሆናለች::

ቸር ይግጠመን!

ዶ/ር አብይ አህመድ ለፌዴሬሽኑ ያቀረቡት ጥያቄ እና ድምጸ ውሳኔው! (ዳዊት ከበደ ወየሳ)

Dr. Abiy Ahmed newly elected Ethiopian PM..

ከአርባ አመታት በፊት በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያውያን፤ የመጀመሪያ ጠቅላላ ስብሰባቸውን ቦሰተን ከተማ ላይ ሲያደርጉ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ፤ የስብሰባውን አላማ አድንቀው ለተማሪዎቹ ደብዳቤ ልከውላቸው ነበር (ሙሉውን ደብዳቤ ከዚህ በፊት ለህትመት አብቅተነዋል)። በወቅቱ የነበሩት የተማሪዎቹ መሪዎች ግን፤ የቀዳማዊ ኃይለስላሴን መንግስት የሚቃወሙ በመሆናቸው፤ ይህንን የንጉሠ ነገሥቱን አክብሮት የተሞላበት ደብዳቤ ለመላው ተማሪ ሳያስነብቡ ቀሩ። ይልቁንም የወቅቱ ተማሪዎች ንጉሠ ነገሥታቸውን ንቀው እና ጠልተው፤ ስብስባቸውን እያጠናከሩ ሄደው እራሳቸውን ወደ ፖለቲካ ድርጅት ቀየሩ። ኢህአፓ እና መኢሶን የዚያ ትውልድ የተማሪዎች ንቅናቄ ውልዶች ናቸው። መጨረሻቸውም እርስ በርስ መገዳደል እና መጨራረስ መሆኑን ታሪክ ይነግረናል። ምናልባት የቀዳማዊ ኃይለስላሴን መልዕክት በጥላቻ ከማየት ይልቅ፤ ትንሽም ቢሆን ቅንጣት ያህል ስፍራ ሰጥተው ቢሆን ኖሮ እርስ በርስ ከመጨራረስ ይልቅ ኢትዮጵያን ዛሬ ከደረሰችበት በላይ በእጥፍ ሊያሳድጓት ይችሉ ነበር። …አሁን ሌላ ዘመን ላይ ነን። የዶ/ር አብይ አህመድ የፍቃድ ደብዳቤ ለአባላቱ እንዳይደርስ ተደርጎ አልተደበቀም። ለአባላቱ ይፋ ሆኖ ግልጽ ውይይት እና ውሳኔ ይሰጥበታል። ውሳኔው ምንም ሆነ ምን የሳቸው ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ እራሳቸው ዶ/ር አብይም ጭምር ውሳኔውን በኩርፊያ ሳይሆን በጸጋ ለመቀበል መዘጋጀት አለባቸው። ይህ ሲሆን… በሃሳብ ሳንለያይ ነገን በተስፋ ማየት እንጀምራለን።

ዳዊት ከበደ ወየሳ

ዶ/ር አብይ አህመድ በመጪው የጁላይ ወር፤ ዳላስ ቴክሳስ በሚደረገው የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ላይ ለመገኘት ጥያቄ አቅርበዋል። ዶ/ር አብይ እንደማንኛውም ሰው መገኘት የሚችሉ ቢሆንም፤ በደብዳቤያቸው ላይ ያቀረቡት ሃሳብ ግን… በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ በደብዳቤያቸው ላይ፤ የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን በየአመቱ ለሚያደርገው ዝግጅት ያላቸውን አድናቆት አልሸሸጉም፤ ኢትዮጵያውያንን በኢትዮያዊነት መንፈስ ለረዥም አመታት በአንድነት በማሰባሰቡ ለፌዴሬሽኑ አክብሮታቸውን በትህትና ገልጸዋል። እሳቸውም በእንዲህ አይነቱ ዝግጅት ላይ፤ በተለይም አርብ ጁላይ 6 ቀን በሚከበረው የ”ኢትዮጵያ ቀን” ላይ በመገኘት፤ የኢትዮጵያዊነት ስሜትን የሚያነቃቃ ንግግር ለማድረግ ነው ጥያቄ ያቀረቡት። ይህ ጥያቄ ሰፋ እና ሞቅ ያለ ውይይት አስከትሏል።

እንደሚታወቀው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን እንደዚህ አይነት ሃይለኝ ክርክር ውስጥ የገባው፤ ከጥቂት አመታት በፊት በአትላንታው ዝግጅት ላይ፤ “ብርቱካን ሚዴቅሳ በክብር እንግድነት ትገኝ ወይስ አትገኝ?” በሚለው ሃሳብ ላይ ነው። በወቅቱ ፌዴሬሽኑ ለሁለት እስከመከፈል የደረሰው የአብላጫውን ውሳኔ ከመቀበል ይልቅ፤ “እኔ ያልኩት ካልሆነ…” የሚል ማገንገን በመበርከቱ ነው። ያን ግዜ የፌዴሬሽኑ አባላት በጋራ ለወሰኑት ውሳኔ ተገዥ የሆኑት ክፍሎች አሸናፊ ሆነው ዛሬም ድረስ ዘልቀው፤ 35ኛ አመታችንን እንድናከብር ምክንያት ሆነውናል። አሁንም የዶ/ር አብይን መገኘት አስመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል። ውሳኔው “እሺ” ወይም “እምቢ” ሊሆን ይችላል። ዋናው ቁምነገር ውሳኔው ምንም ሆነ ምን፤ ሁላችንም ለውሳኔው ተገዥ ለመሆን እራሳችንን ማዘጋጀታችን ላይ ነው።

አሁን ያለንበትን ሁኔታ መሰረት አድርገን ለግዜው ሃሳቦችን ለሶስት ከፍለን ማየት የግድ ነው። አንደኛው ወገን የዶ/ር አብይ አህመድን ጥያቄ የሚቀበል ነው። ሁለተኛው ወገን የዚያ ተቃራኒ ሲሆን፤ ሶስተኛው አካል ደግሞ የአስታራቂነት ሚና የሚጫወተው ክፍል ነው። እኛም የራሳችንን ውሳኔ ከመስጠታችን በፊት እነዚህም ሶስት ክፍሎች በአንክሮ እንመልከታቸው።

1ኛ – የዶ/ር አብይ አህመድን መገኘት የሚደግፉት ክፍሎች የሚከተሉትን ሃሳቦች ይሰነዝራሉ።

1-1/ “እንኳንስ ዶ/ር አብይ ጥያቄ አቅርቦልን ቀርቶ፤ እኛው ራሳችን ጠይቀነውም ቢሆን እንዲገኝ ማድረግ ነበረብን። ስለዚህ መገኘት አለበት።” ይላሉ።

1-2/ “አሁን ባለው ሁኔታ ዶ/ር አብይን ለማየት እና ለማግኘት የሚፈልገው ኢትዮያዊ ቁጥር በርካታ ነው። ስለሆነም በእለቱ መገኘቱ ለፌዴሬሽኑ ጥቅም እንጂ ጉዳት ስለሌው ቢገኝ ይመረጣል።” የሚሉ ወገኖችም አሉ።

1-3/ “በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው፤ ዶ/ር አብይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊነትን ለመስበክ ከሆነ በእለቱ መጋበዙ ምንም ክፋት የለውም።” በማለት የሚከራከሩም አሉ።

2ኛ – የዶ/ር አብይ አህመድን መገኘት የማይደግፉት ደግሞ ይህንን ይላሉ።

2-1/ “ፌዴሬሽኑ በእለቱ ዋና ተናጋሪ አድርጎ የሰየመው፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ነው። በዚህ ላይ ሌላ ተደራቢ ሰው አድርገን መጋበዝ ትክክል አይደለም። ስለዚህ ሌላ ተናጋሪ መጋበዝ አግባብ አይደለም።” ብለዋል።

2-2/ “ምንም ሆነ ምን ዶ/ር አብይ በዚህ ዝግጅት ላይ፤ የሚያስተላልፈው የፖለቲካ መልዕክት ስለሆነ መገኘት የለበትም።” የሚሉም አሉ።

2-3/ “ሲጀመር በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ እንዲገኝ ጥያቄ መቅረቡ አግባብ አይደለም። ሲቀጥል ደግሞ ዶ/ር አብይ እስካሁን ሲናገር ከነበረው የተለየ ነገር አይናገርም። አመጣጡ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ስለሆነ፤ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም።” በማለት የዶ/ር አብይ አህመድን መገኘት አይቀበሉትም።

3ኛ – ከላይ የተገለጹትን ሁለት የተለያዩ ወገኖች ለማቀራረብ የሚጥሩ 3ኛ ወገኖች ደግሞ ይሄንን ይላሉ።

3-1/ ዶ/ር አብይ በፌዴሬሽኑ ዝግጅት ላይ የሚገኝ ከሆነ፤ ተመጣጣኝ የሆነ ግብረ መልስ የሚሰጡ እንደታማኝ በየነ አይነት ሰዎችም ተገኝተው ንግግር ማድረግ አለባቸው።

3-2/ ዶ/ር አብይ በፌዴሬሽኑ የመክፈቻ ወይም የመዝጊያ ዝግጅት ላይ መገኘት ይችላል። በኢትዮጵያ ቀን ላይ ተገኝቶ ንግግር ማድረጉ ግን ተቀባይነት የለውም።

3-3/ ዶ/ር አብይ ስራውን ገና መጀመሩ ነው። ባይሆን እስከሚቀጥለው አመት ድረስ ጠቅላላ ስራውን እንገምግመው። ከዚያም እኛ ራሳችን ልንጋብዘው እንችላለን። የዘንድሮን ግን ይለፈን… በማለት አስታራቂ የሚመስሉ ሃሳቦችን ሰንዝረዋል።

እንግዲህ እነዚህ ሃሳብ እና አስተያየቶች በቅርበት ከፌዴሬሽኑ ሰዎች ጋር ስንነጋገር የተሰጡን ሃሳቦች ናቸው። በዛሬው እለት በፌዴሬሽኑ አባላት መካከል የሚደረገው ስብሰባም እነዚህን መሰረታዊ ነጥቦች እንደሚያንሸራሽር ይጠበቃል። የፌዴሬሽኑ ተወካዮች አባሎቻቸውን በማማከር የሚሰጡትን ሃሳብ እና ውሳኔ ይዘው፤ እነሱም ዛሬ ምሽት ድምጻችወን ይሰጣሉ፤ ይህ ውሳኔም የመጨረሻ ይሆናል።

ከኛ የሚጠበቀው ውሳኔው ምንም ሆነ ምን፤ ለውሳኔው አክብሮት መስጠት ይኖርብናል። ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ቀን ላይ እንዲገኙ የሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ፤ ኢህአዴግ ያደረሰባቸው ጉዳት ያላጠገገላቸው ኢትዮጵያውያን ደግሞ የዶ/ር አብይ አህመድን በዚህ አይነቱ ዝግጅት ላይ መገኘትን አይቀበሉትም። ምንም ሆነ ምን ግን የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ለመቀበል ራሳችንን እናዘጋጅ። ውሳኔውን ብንቀበለውም ሆነ ባንቀበለው ተቃውሞ እና ድጋፋችንን በሰለጠነ መንገድ መግለጽ ይኖርብናል።

ልብ ይበሉ። በስፖርት ውድድር ጨዋታ ላይ ሁለት ተቃራኒ ቡድኖች ይጋጠማሉ። ፍልሚያው እልህ አስጨራሽ ሊሆን ይችላል። ዳኝነቱም ቢሆን ከበድ ይላል። በመጨረሻ ግን አንደኛው አሸናፊ ሌላኛው ተሸናፊ ይሆንንና የጨዋታው ግዜ ያበቃል። በውድድሩ መጨረሻ ላይ የሁለቱም ቡድን አባላት እጅ ለእጅ ተጨባብጠው፤ አንዳንዴም ማልያ ተቀያይረው በፍቅር እና በሰላም ይለያያሉ። ይህን የተመለከተው የሁለቱ ቡድኖች ቲፎዞም የተፋላሚዎቹን ፍቅር ተመልክቶ ሽንፈቱን ውጦ ለሚቀጥለው አመት ፍልሚያ፤ ተስፋ ሰንቆ ይለያያል።

አሁን ባለው ሁኔታ የዶ/ር አብይ ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ ፌዴሬሽኑ የደረሰህበትን ድምጸ ውሳኔ፤ ለህዝቡ ባስቸኳይ ይፋ ማድረግ አለበት። ይህ ከሆነ የዶ/ር አብይ አህመድ ተቃዋሚዎች አጋጣሚውን በመጠቀም በትልቁ ስቴድየም ውስጥ ትልቅ እና የሰለጠነ ተቃውሞ ለማቅረብ ነገሩን ወደ ጥሩ አጋጣሚ መቀየር አለባቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ ውድቅ ከሆነ፤ ፌዴሬሽኑ በደብዳቤ የአክብሮት ምላሽ ሊሰጥ ይገባዋል። በዚያው መጠን ዶ/ር አብይም ውሳኔውን አክብረው በመቀበል፤ አዎንታዊ የአጸፋ ምላሽ ሊሰጡ ይገባል። ይህን የተመለከተው ህዝብም በተመሳሳይ መልኩ ሰላም ሊያወርድ ይችላል። ከዚህ ሁሉ ተቃራኒ በመሆን፤ “እኔ ያልኩት ካልሆነ…” የሚል ወገን ካለ ግን ከራሱ ጋር ለአንድ አፍታም ቢሆን ሊመክር ይገባዋል። በጥላቻ ከመለያየት ይልቅ፤ በፍቅር መለያየት እንደሚቻል ነጋሪ እና መካሪ የሚያስፈልገን ግዜ ላይ አይደለንምና… ልብ ያለው ልብ ይበል።

ለኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ – ከአለምአቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረሀይል

አለምአቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረሀይል
ለኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ

ጉዳዩ፦ በስፖርት ፌዴሬሽኑ አመታዊ በአል ላይ የሚጋበዙ እንግዶችን በተመለከተ

ክቡራት እና ክቡራን፣

በቅድሚያ ፣ እንኳን ለ35ኛው ክብረ-በአል አደረሳችሁ እያለ በልዩ ልዩ ከተሞች የተዋቀሩትን ግብረሀይሎች በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያስተባብረው አለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረሀይል መልካም ምኞቱን ይገልጻል። ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 የስፖርት ፌዴሬሽኑ አመታዊ በአሉን በዳላስ፣ ቴክሳስ እንደሚያከብር ይታወቃል። ከዚህ በአል ጋር ተያይዞ በጁላይ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቀን የሚከበር ሲሆን በዚህ እለት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሲወደሱ ይውላሉ። ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያደረጉ ዜጎች በክብር እንግድነት በመገኘት በእለቱ መልክታቸውን እንደሚያስተላልፉም ይታወቃል። በዚህ ረገድ፣ በርካታ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ክብረ-በአሉን በመጠቀም መልክታቸውን ሲያስተላልፉ ኑረዋል።The Ethiopian Sports Federation in North America (ESFNA 2017),

ዘንድሮ በሚከበረው የኢትዮጵያ ቀን ላይ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ተገኝተው መልክታቸውን ማስተላለፍ እንደፈለጉ በተለያዩ ወገኖች እየተነገረ ይገኛል። ይህንን ሁኔታ በተመለከተ ፌዴሬሽኑ ተመካክሮ ውሳኔ ላይ እንደሚደርስም ይጠበቃል። ይሁን እና፣ የዶ/ር አብይ አስተዳደር ያቀረበው የተጋባዥነት ጥያቄ እና ፌዴረሽኑ የሚያሳልፈው ውሳኔ በዲያስፖራው ማህበረሰብ መካከል ከፍተኛ የሆነ የሀሳብ እና የአንድነት መከፋፈል ያስከትላል የሚል ትልቅ ስጋት አለ። ይህ
ፌዴሬሽን በርካታ ውጣ ወረዶች ቢያጋጥሙትም ኢትዮጵያዊያንን በጋራ አሰባስቦ ዘመናትን መሻገር የቻለ የኢትዮጵያዊያን ተቋም ነው ብሎ ማለት ይቻላል። አሁንም ቢሆን፣ ይህ ፌዴሬሽን የራሱ የተቋሙን እና የሚያገለግለውን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ አንድነት የሚያስጠብቅ አርቆ አሳቢ እና ብልህነት የተሞላበት ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ፌደሬሽኑ የክብር እንግዶችን እና ተናጋሪዎችን የሚመርጥበት ህገ-ደንብ እንዳለው ይታወቃል። በዶ/ር አብይ አስተዳደር የቀረበውን ጥያቄ በህገ-ደንቡ መሰረት ያስተናግደዋል የሚል እምነት በብዙዎች ዘንድ አለ። የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ ዶ/ር አብይን ጨምሮ፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዳይሆኑ የሚከለክል ህገ-ደንብ ካለ፣ የፌደሬሽኑ ውሳኔ ይህንን ህገ-ደንብ የተከተለ ይሆናል ብለን እናምናለን። ነገር ግን፣ የህገ-ደንብ ክፍተት ካለ እና በሌሎቹ ልዩ ሁኔታዎች የተነሳ፣ ዶ/ር አብይ የሚጋበዙ ከሆነ፣ በፌደሬሽኑ እና በዲያስፖራው ማህበረሰብ ላይ የተለያዩ ችግሮች ይከሰታሉ የሚል ስጋት አለን።

1. የፌደሬሽኑ ዋነኛ ተገልጋይ እና ደጋፊ የሆነውን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ይከፋፍለዋል፣
2. እራሱ ፌደሬሽኑን ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሊከፋፍለው ይችላል፣
3. በመጭው ጁላይ ወር የሚደረገውን ክብረ-በአል የሚያሰናክሉ እና የሚያስተጓጉሉ የተቃውሞ ሂደቶች እና የደህንነት ስጋቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ።

ከላይ እንደተገለጸው፣ የህገ-ደንብ ክፍተት ካለ ወይም በልዩ ሁኔታ ዶ/ር አብይ አህመድ ተጋባዥ የሚሆኑ ከሆነ፣ ፌደሬሽኑ እና ማህበረሰቡ ፈተና ላይ እንደሚወድቁ ከበቂ በላይ ምልክቶች እየታዩ ይገኛሉ። ይሄንን ሁኔታ ለማለዘብ እና ፈተናውን ቀለል ለማድረግ፣ ፌደሬሽኑ የማመጣጠን ሥራ ሊሰራ ይገባል ብለን እናምናለን። ይህም ማለት፣ በተቀዋሚውም ወገን ያሉ ታዋቂ ሰዎች በኢትዮጵያ ቀን በክብር እንግድነት እንዲገኙ እና መልክታቸውን እንዲያስተላልፉ መፈቀደ አለበት። ከዚህ አኳያ፣ ከታች ስማቸው የተጠቀሰው መሪዎች ተጋባዥ እንግዶች ቢሆኑ፣ ሁኔታውን ለማለዘብ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለን ከልብ እናምናለን።

1. ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ
2. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
3. አቶ አንዷለም አራጌ

የሚቻል ከሆነ ፌደሬሽኑ ህገ-ደንቡን በመከተል፣ ካልሆነም ከላይ የተገለጹትን ኢትዮጵያዊያንን በሂደቱ በማሳተፍ ለተቋሙም እንዲሁም ለዲያስፖራ ማህበረሰቡም የሚበጅ እና አንድነታችንን የሚያጸና ውሳኔ ቦርዱ እንዲወስን ጥሪያችንን እናቀርባለን። ይህ ደብዳቤ ለቦርዱ ውይይት ግብአት ይሆናል ብለን ከልብ እናምናለን። ለደብዳቤያችን መልስ በተቻለ ፍጥነት እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያ በነጻነት፣ በእኩልነት እና በፍትህ ለዘላለም ትኑር!!

አለምአቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረሀይል

ግልባጭ፦ ለኢሳት፣ ለኦኤምኤን፣ ለቮይስ ኦፍ አሜሪካ፣ ለዶቸቬሌ እና ሌሎች የሚዲያ ተቋማት

የቤተ ክርስቲያንን ነጻነትና ተደማጭነት ለመመለስ ያለመ የማኅበረ ካህናት አንድነት ተመሠረተ

  • ጅምሩን በአሜሪካ ቢያደርግም በመላው ዓለም ኦርቶዶክሳውያን ካህናትን ለማቀፍ ይንቀሳቀሳል
  • ቤተ ክርስቲያን በሚገባት ክብርና ልዕልና እንዳትገኝ የካህናት ግድየለሽነት አስተዋፅኦ አድርጓል
  • በጎሠኝነትና ምንደኝነት፥ ከዓለም በከፋ ኹኔታ ተከፋፍለን፤ መተማመን ጎድሎናል፤ ተራርቀናል
  • ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ ጎድቷታል፤ መከራዋንም አብዝቶታል፤ በአንድነት ልንፈታው ይገባል
  • አባላቱ፣ ከግለኝነት እና ጎሠኝነት የጸዱ ሊኾኑ ይገባል፤ የአስተዳደር ልዩነቱ አይገድበውም፤

†††

  • አንድነት ሲኖረን እግዚአብሔር ይሰማናል፤ምእመናኑን ወደ አንድነት ማምጣቱም አይከብድም
  • ቅ/ሲኖዶሱ ሚናውን በነጻነት እንዲወጣ፤ ፓትርያርኩ ሓላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲተገብሩ…
  • የቤተ ክህነት ሓላፊዎች ለሁለት ጌቶች ሳይገዙ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ብቻ እንዲፈጽሙ…
  • መንግሥት ተገዶም ቢኾን ያደምጠናል፤ ተቋማት ያከብሩናል፤ሉዓላዊነትና ነጻነት ይመለሳል፤
  • “እንችላለን” በሚል እምነት የሌሎችንም ችግር የሚቀርፍ ሙሉ አቅም ለመፍጠር ያስችላል፤

†††

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ከየትኛውም አካል የሚደርስባትን ትንኮሳና ጥቃት በመመከትና በመከላከል ዘርፈ ብዙ ፈተናዎቿን በጋራ የመፍታት ዓላማን ያነገበ የካህናት አንድነት ማኅበር በሰሜን አሜሪካ ተመሠረተ፡፡

የአንድነት ማኅበሩ የተመሠረተው፣ ከአሜሪካ እና ከካናዳ አህጉረ ዓለም የተሰበሰቡ ሊቃውንት፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደግበሚል መሪ ቃል ለሦስት ቀናት በሲያትል ከተማ ባደረጉት ጉባዔ ነው፡፡

ከመላው የአሜሪካ ግዛትና ከካናዳ የመጡ በቁጥር ከ70 በላይ የኾኑ ልኡካን፣ ከሚያዝያ 25 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. (May 3 – 5, 2018) በዋሽንግተን ሲያትል ከተማ ያካሔዱት ይኸው የካህናት አንድነት ማኅበር ምሥረታ ጉባዔ፣ታሪካዊ እንደኾነና ፍጹም መንፈሳዊነት ባልተለየው ኹኔታ በጸሎት፣ በፍቅርና በእንባ ጭምር እንደተከናወነ፣ በመርሐ ግብሩ ፍጻሜ የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

በምሥረታ ጉባኤው፣ ቤተ ክርስቲያናችን በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትገኝበትን ወቅታዊ ኹኔታ የዳሰሰ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደቀረበና ጥልቅ ውይይት እንደተደረገ ተገልጿል፡፡ እውነትን የያዘችው ቤተ ክርስቲያናችን በሐሰተኛው ዓለም ውስጥ የምትጓዘው በእሳት መካከል እንደኾነ የጠቀሰው መግለጫው፣ ከፖሊቲካ ኃይሎች የሚደርስባት ፈተና ግንባር ቀደሙ ነው፤ ብሏል፡፡

መንግሥታት ሥልጣናቸውን ለማደላደል ተቋማዊ ነጻነቷን በዓምባገነንት እየተጋፉ፣ አስተዳደራዊ መዋቅሯን በመቆጣጠር በሥርዐቷና በሕጓ እንዳትመራ፤ በሀብቷና በንብረቷ በአግባቡ እንዳትጠቀም ያደረሱባትን በደሎች አብራርቷል፡፡ ተጽዕኖው በፈጠረው ተጋላጭነት ተጠቅመው በውስጧ የተሰገሰጉ ግለሰቦችም፣ አስከፊ ምዝበራ እየፈጸሙባት እንደቆዩና በአሁኑ ወቅት ሌብነቱን ነውር አልቦ ልማድ በማድረግ ያለኀፍረት እያንሰራፉት እንደሚገኙ አስፍሯል፡፡

በውጤቱም፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ የምታምንበትን እንዳትናገር፣ እውነቱን በዐደባባይ እንዳትመሰክር፣ አጥፊዎችን እንዳትገሥጽና እንዳትመክር፣ መተኪያ የሌለው የሸምጋይነት ሚናዋንም እንዳትወጣ ከማሳነስም በላይ አስተዳደሯ እንዲዳከም፣ ተደማጭነቷ እንዲጠፋ፣ ከዚህ አልፎ ያለስሟ ስም፣ ያለግብሯ ግብር እየተሰጣት ጥቂት በማይባሉ የሀገራችን ኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ በጠላትነት እንድትፈረጅ እንዳደረጋት አትቷል።

የውስጥ ችግሩንና የውጭ ተግዳሮቱን በዋናነት መከላከልና ማስወገድ የሚገባቸው፣ የኖላዊነቱ ሓላፊነት የተሰጣቸው አዕይንተ እግዚአብሔር ካህናትቢኾኑም፣ ለዓመታት አንቀላፍተው በመቆየታቸው ከዚያም አልፎ ከዓለማውያን በከፋ መልኩ በጥቅመኝነትና ጎሠኝነት መከፋፈላቸውና መራራቃቸው፣ ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ እንደጎዳትና መከራዋን እንዳበዛው መግለጫው ተችቷል፡፡

“በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተለያየ ጊዜ የመከራ ዶፍ ሲወርድ እጃችንን አጣጥፈን በመቀመጥ፣ ለፖለቲካ ኃይሎች በማጎብደድና በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ እንዲገቡ በመጋበዝ፣ በመፍቀድና በመተባበር፣ በጎሠኝነት በመከፋፈል፣ በጉቦ ቅብብል፣ በምዝበራውና በዘረፋው በመሳተፍ፣…ወዘተ የብዙዎቻችን እጅ እንዳለበት መካድ አንችልም፤” ያለው መግለጫው፣ ለችግሩ መባባስ በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ የእያንዳንዳችን አስተዋፅኦ እንዳለበትና ለዓመታት ማንቀላፋታችንን ከማመን መነሣት እንደሚገባ አስገንዝቧል፡፡

31958247_1818206608475844_7227731421392011264_n

መፍትሔው፣ ችግሩን በግልጽ ተነጋግሮ በመተማመን እንደሚገኝ የጠቆመው መግለጫው፣ ለዚህም ካህናት ከግዴለሽነት፣ አድርባይነት፣ ምንደኝነትና ጎሠኝነት ክፉ ልማድ ርቀው ለሌላው የሚያስተምሩትን ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት በራሳቸው በመተግበር ለውጥ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል፡፡ ጥቂት አባቶችና ወንድሞች፣ምእመናን በተለይም ወጣቶች፣ በተለያየ ጊዜ በተናጠል የሚያደርጉት ተጋድሎ በቂ እንዳልኾነና በኖላዊነት የሚመሩት ካህናት አንድነት በእጅጉ አስፈላጊ እንደኾነ አሥምሮበታል፡፡

በአንድነት መንቀሳቀስ ከቻልን፥ እግዚአብሔር ይሰማናል፤ የምንመራቸውን ምእመናን ወደ አንድነት ማምጣቱ ከባድ አይኾንም፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሲኖዶስነት ሚናውን በነጻነት እንዲወጣ፤ ፓትርያርኩ የፓትርያርክነት ሓላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲተገብሩ፤ በየደረጃው ያሉ የቤተ ክህነት ሓላፊዎች ለሁለት ጌቶች ከመገዛት ተላቅቀው የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልእኮ ብቻ የሚፈጽሙ እንዲኾኑ ቀላል የማይባል ተጽዕኖ መፍጠር እንችላለን፤ መንግሥትም ቢኾን ተገዶ ያደምጠናል፤ ተቋማትም ያከብሩናል፤ ብሏል፡፡

“የቤተ ክርስቲያንን ችግር መፍታት አይቻልም፤” የሚል የቀቢጸ ተስፋ ድምዳሜ፣ የዓለም ብርሃን መኾን የሚገባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በድቅድቅ ጨለማ እንድትጓዝ ከመፍረድ ተለይቶ እንደማይታይና በምትኩ “እንችላለን” የሚለውን እምነት በመያዝ ከራሳችን አልፈን የሌሎችን ችግር የምንቀርፍበት ሙሉ አቅም ለመፍጠር፣ ከራስ ክብርና የግል ጥቅም ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን ህልውናና ክብር ቅድሚያ ሰጥቶ መቀናጀት እንደሚያስፈልግ ጠቁሟል፡፡

32073061_1818207351809103_4640285862054068224_n

በመንፈሳዊውም በዓለማዊውም ዕውቀት የተራቀቁና የመጠቁ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ካህናትና ምእመናን፣ በትክክለኛው መንገድ የሚመራቸው እስካገኙ ድረስ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውን ብቻ ሳይኾን ሕይወታቸውንም ለመስጠት የማይሰስቱ ወጣቶች እንዲሁም እምቅ አቅምና ሀብት ያላት ታላቅ ቤተ ክርስቲያን፣ ምንም እንደሌላትና ምንም ማድረግ እንደማትችል ሁሉ የማንም መፈንጫና መዘባበቻ የኾነችበትን የዘመናችንን ክፉ ታሪክ በመቀየር በቀላሉ የማይተነኩሷትና የማይገዳደሯት ሉዓላዊ፣ የተከበረች፣ ነጻና ተደማጭ ለማድረግ፣ በአንድነትና በቁጭት ከመንቀሳቀስ በቀር አማራጭ አለመኖሩን አሳስቧል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚመሠረተው ይኸው የማኅበረ ካህናት አንድነት፣ በሲኖዶሳዊ አስተዳደር የተፈጠረው ልዩነት እንደማይገድበው መግለጫው ጠቅሶ፣አባል የሚኾኑ ካህናትም፦ የሃይማኖት ሕጸጽ የሌለባቸው፣ ጎሠኝነት ያልተጠናወታቸው፣ ከግለኝነት ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ የሚያስቀድሙ፣ አቅም በፈቀደ ሁሉ ሃይማኖታዊ ተጋድሎ ለማድረግና መሥዋዕት ለመክፈል ቁርጠኝነት ያላቸው ሊቃውንት፣ መነኰሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል ሁሉ እንደኾኑ ገልጿል፡፡

የማኅበሩን ዓላማና ጥቅም የተገነዘቡ ሁሉ በየአጥቢያው ለሚያውቋቸው ካህናት በትጋት በማስረዳት፣ በቀላሉና በአጭር ጊዜ ዓለም አቀፍ አንድነቱን ማምጣት እንደሚቻል ያመለከተው መግለጫው፣ የማኅበራዊ መገናኛው ለቅስቀሳው ያለውን አመቺነት በአማራጭነት ጠቁሟል፡፡

የካህናት አንድነቱ፣ ጅምሩን በሰሜን አሜሪካ ያድርግ እንጅ፣ በሒደት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን ሁሉ በአባልነት ለማካተት ዕቅድ ይዞ በከፍተኛ ኹኔታ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታውቋል – ቆጭቶናል ብለን ከተነሣን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን የቤተክርስቲያናችንን ጉዳይ ማስቀደም ይገባናል። ሁሉም ካህናት ወደዚህ አንድነት ይመጣሉ። የሚመጡበት ጊዜ ግን የተለያየ መኾኑ የሚጠበቅ ነው።

በመጨረሻም ጉባዔው፣ ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትና የሚቀጥለውን ዓመት ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ለማድረግ በመወሰን ተጠናቋል!

‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡

ሙሉ የአቋም መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል::

ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ

መግቢያ

የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። /2ኛቆሮ.11፥28

ቅዱስ ጳውሎስ ከላይ በተጠቀሰው መልእክቱ፣ ክርስቶስን በመስበኩ ምክንያት ብዙ ጊዜ እንደታሰረ፣ እንደተገረፈ፣ በየብስም በባሕርም፣ በከተማም በበረሓም ለሞት እስኪደርስ ድረስ ብዙ መከራና ሥቃይ እንደጸናበት፣ ረኀቡና ጥማቱ፣ ቍሩና ዋዕዩ እንደተፈራረቀበት ከዘረዘረ በኋላ ነው፣የቀረውንም ነገርሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው፤ የሚለው፡፡

በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ደም ተመሥርታ በየዘመናቱ በተነሡ ቅዱሳን ተጋድሎና ጥብዓት ዘመናትን ተሻግራ ወደኛ የደረሰችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የተከፈለላት መሥዋዕት የቱን ያህል እንደኾነ ከላይ የተጠቀሰው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ትልቅ ማሳያ ነው። ተጋድሎ የሚያስፈልገው መከራ ስላለ እንደኾነ እሙን ነው። እውነትን የያዘችው ቤተ ክርስቲያናችን ደግሞ በሐሰተኛው ዓለም ውስጥ ጉዞዋ በእሳት መካከል እንደኾነ ጥርጥር የለውም።

መሪ ቃል፦ ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደግ

የአንድነት ምሥረታው የመነሻ ሐሳብ አሁን ያለበት ደረጃ፤

በክርስትና ታሪክ ጥንታውያት ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት አንዷና ዋነኛዋ የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በረዥም ጊዜ ታሪኳ፣ በቅድስናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር ተቀባይነትና ዕውቅና ያገኙ ብዙ ቅዱሳንን ያፈራች፣ በዓለማችን ላይ ከሚገኙት የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትና በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት እምነቶች በአማኞች ብዛት ግንባር ቀደም የኾነች ስመ ጥርና ገናና ቤተ ክርስቲያን ናት።

የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ ጠብቃ ከትውልድ ወደ ትውልድ ያሸጋገረች የሀገር ባለውለታ ቤተ ክርስቲያን ናት። ስለሀገር ሰላምና ደኅንነት፣ ስለሕዝብ አንድነት ስትጸልይና ስታስተምር ከመኖሯም በላይ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን፣ ክብርንና ነጻነትን የሚያሳጣ፣ ሃይማኖትንና ማንነትን የሚያጠፋ የውጭ ወራሪ ሲመጣ በግንባር ቀደም እየተሰለፈች መሥዋዕትነት የከፈለች፣ የውስጥ ዓምባገነን ሲነሣ ደግሞ በግልጽ የሚገሥጹና የሚያወግዙ ቆራጦችና ጥቡዓን አባቶች የነበሯት በብዙዎች ዘንድ የምትወደድ፣ የምትከበርና የምትፈራ ባለግርማ ሞገስ ቤተ ክርስቲያን ናት።

ይኹንና ከጊዜ በኋላ ክብሯና ልዕልናዋ እየኮሰሰ፣ ተደማጭነቷና ተፈሪነቷ እየቀነሰ ዛሬ መሸምገል እንኳን የማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።አሁን አሁን ከዚህም አልፎ የትንሹም የትልቁም መዘባበቻና መሣለቂያ ወደ መኾን እየተሸጋገረች ትገኛለች። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ዘመን ብዙ ዓይነት ፈተናዎችና በርካታ ውስብስብ ችግሮች ያሉባት ብትኾንም ጥቂቶቹን ብቻ ለመጥቀስ እንሞክራለን።

1ከፖለቲካ ኃይሎች የሚደርስባት ተጽዕኖ፤

ይህ ችግር በአሁኑ ጊዜ በግንባር ቀደም የሚጠቀስና ለአብዛኞቹ ችግሮችም እንደ ዋና መንሥኤ የሚጠቀስ ነው። ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ ያለውን ብቻ እንኳን ብንመለከት፣ ለዓምባገነናዊ አገዛዙ እንደማትመች አስቀድሞ የተረዳው የደርግ መንግሥት፣ የፖለቲካ ሥልጣን በያዘ ማግሥት፥ ፓትርያርኳን ገድሎ፣ ጳጳሳቷን አስሮ፣ ሀብት ንብረቷን በግፍ ወርሶ፣ ነጻነቷን ቀምቶ እስረኛ በማድረግ ነው ሥልጣኑን ያደላደለው።

በእሳት ውስጥ ማለፍ የምትችልና የማትሞት ቤተ ክርስቲያን ስለኾነች ነው እንጅ፣ ደርግ እንዳደረሰባት በደልና እንደሚከተለው ርእዮተ ዓለም/ኮሚኒዝም/ ቢኾን ኑሮ አሁን የደረሰችበት ደረጃም ባልደረሰች ነበር። ኾኖም ግን በቀላሉ የማይተኩትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ከማጣቷና የዕድገት ግሥጋሴዋ ከመገታቱ በተጨማሪ፣ ሥርዓቱ በርካታ አማኞቿ ከሃይማኖት እንዲወጡ ወይም ለሃይማኖታቸው ግዴለሽ እንዲኾኑ ስላደረጋቸው የደረሰባት ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም።

አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥትም ቢኾን ገና ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ነበር ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለማዳከም ዓላማ አንግቦ፣ ዕቅድ አውጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረው። /የዶክተር አረጋዊ በርሄን መጽሐፍና የሌሎች ግለሰቦችን ምስክርነት መጥቀስ ይቻላል/ ሀገሪቱን እንደተቆጣጠረም፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን በጀት በማገድና በወቅቱ የነበሩትን ፓትርያርክ ከመቀየር ጀምሮ ቁልፍና ወሳኝ የኾኑትን የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅሮች በራሱ ካድሬዎች በማስያዝ ነበር ቤተ ክርስቲያኒቱን በመዳፉ ውስጥ ያስገባት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኒቱ የምታምንበትን እንዳትናገር፣ እውነቱን በዐደባባይ እንዳትመሰክር፣ አጥፊዎችን እንዳትገሥጽና እንዳትመክር፣መተኪያ የሌለው የሸምጋይነት ሚናዋንም እንዳትወጣ ከመደረጓም በላይ አስተዳደሯ እንዲዳከም፣ ተደማጭነቷ እንዲጠፋ እንዲያውም ከዚህ አልፎ ያለስሟ ስም፣ ያለግብሯ ግብር እየተሰጣት ጥቂት በማይባሉ የሀገሪቱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ በጠላትነት እንድትፈረጅ አድርጓታል።

ይህ ዘመን በፓትርያርክና በጠቅላይ ሚኒስትር፣ በቀበሌና በደብር ጽ/ቤት ያለው ልዩነት እስኪጠፋብን ድረስ መደበላለቅ የተፈጠረበት ዘመን ነው። “ፖሊስ ጠርቼ አሳስርሃለሁ፤ ደኅንነት አምጥቼ አስገርፍሃለሁ” የሚሉና ራሳቸውም የጦር መሣሪያ የታጠቁ የቤተ ክህነት ሓላፊዎች፣ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች የተፈጠሩበት፣ የቤተ ክህነቱ ቅልብ ወንበዴዎች የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን የመኖሪያ ቤት በሮች እየገነጠሉ፣ መስኮቶችን እየሰበሩ ጳጳሳትን የመደብደብ ሙከራ ሲያደርጉ ከልካይ እንደሌላቸውና ወንጀል ኾኖ እንደማይቆጠርባቸው የታየው በዚሁ ዘመን ነው። ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤዎች እየተገኙ መመሪያ እስኪሰጡ ድረስ፣ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ዐይን ያወጣና ቅጥ ያጣ ጣልቃ ገብነት የተፈጸመውም በዚሁ በእኛው ዘመን ነው።

2ኛ. የአስተዳደር ችግር

ከላይ ከተገለጸው ጋራ ተያይዞ የቤተ ክርስቲያናችን የአስተዳደር ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። በአሁኑ ጊዜ፥ ጉቦኝነት፣ ዘረፋ፣ምዝበራ፣ ዘረኝነት/ጎጠኝነት፣ አድሏዊነት፣ የአስተዳደሩ ዋና ዋና መገለጫዎቹ ኾነዋል። እነዚህ አስጸያፊ ተግባራት እንደነውር የማይቆጠሩበት ደረጃም ተደርሷል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ልዩ ልዩ መዋቅሮች የተሠገሠጉ አምባገነኖች ለሚፈጽሙት ግፍና ጭቆና ጠያቂ የላቸውም።

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ችግራቸውን በአግባቡ የሚፈታ የአስተዳደር አካል በማጣታቸው ምክንያት በተረጋጋ መንፈስ አገልግሎት ለመስጠት ካለመቻላቸውም በላይ ለከፍተኛ መጉላላት፣ እንግልትና መከራ ተዳርገዋል። የሕግና የሥርዓት መሠረት የኾነችው ታላቋ ቤተ ክርስቲያን፥ሕገ ወጥነትና ሥርዓት አልበኝነት የነገሠባት፣ ፍትሕ ርትዕ የተጓደለባት ኾናለች፤ ምእመናኗም በመሪዎቻቸው አባቶች ጳጳሳትና ካህናት እንደዚህ ዘመን ያፈሩበትና የተሸማቀቁበት ጊዜ ታይቶ አይታወቅም፤ በርካቶችም ተስፋ እየቆረጡ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እየተቅበዘበዙ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት ከበረቱ ብዙዎች እንደወጡ መረጃዎች እያመላከቱ ነው።

በመሠረቱ አሁን በቤተ ክርስቲያናችን እየታየ ያለው ትርምስ፣ድንገት ዛሬ የተፈጠረ አይደለም። በአጋጣሚ የኾነም አይደለም። ከ30 እና 40 ዓመታት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዳከም በዕቅድ የተነደፈ ነው እንጅ። ለዓመታት የተዘራው ክፉ ዘር አሁን ለፍሬ ደርሶ ቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አደጋ እንዲያንዣብባት አድርጓል።

ክፉዉ ዘር ዛሬም እየተዘራ ነው። እጃችንን አጣጥፈን ከተቀመጥን ደግሞ ከ20 እና 30 ዓመታት በኋላ ቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ብቻ ወደ መኾን የማትሸጋገርበት ምክንያት አይኖርም። አንዳንዶቻችን፣ “ቤተ ክርስቲያን እስከ ዓለም ፍጻሜ ትኖራለች፤” ሲባል እንዲሁ በረድኤተ እግዚአብሔር ተጠብቃ ብቻ ይመስለናል። እውነቱ ግን ይህ ብቻ አይደለም። ጉዞዋ በእሳት መካከል ነው። ከሐዋርያት ጅምሮ ብዙ ቅዱሳን ተጋድለውላታል፤ ተሠውተውላታል። ዛሬም ወደፊትም የሚጋደሉላት የሚሠዉላት ያስፈልጓታል። የትላንቶቹ በተጋድሎአቸው ለእኛ አስረክበዋል። ዛሬ ተራው የኛ ነው። ነገ ደግሞ እኛ የምናስረክባቸው ይኾናል። ምንድን ነው የምናስረክባቸው? የሚለው ጥያቄ ግን መመለስ ይኖርበታል – ቁጭት!!

በአሁኑ ጊዜ ወደ 195 ገደማ ከሚኾኑት የዓለም ሀገሮች ወስጥ ከ45 ሚሊዮን በላይ የሕዝብ ብዛት ያላቸው ሀገሮች ከ30 አይበልጡም፡፡ ከ45 ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ አማኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ከቀሪዎቹ 165 ሀገሮች የበለጠ የሕዝብ ብዛት ያላት ተቋም ናት ማለት ነው፡፡ ከእኒህም ውስጥ፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ካህናት፣ በመንፈሳዊውም በዓለማዊውም ዕውቀት የተራቀቁና የመጠቁ ካህናትና ምእመናን፣ በትክክለኛው መንገድ የሚመራቸው እስካገኙ ድረስ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውን ብቻ ሳይኾን ሕይወታቸውን ጭምር ለመስጠት የማይሰስቱ ወጣቶች እንዲሁም ዘርዝረን የማንጨርሰው እምቅ አቅምና ሀብት ያላት ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ኾኖም ምንም እንደሌላትና ምንም ማድረግ እንደማትችል ተቆጥራ ማንም እንደፈለገ የሚፈነጭባት፣ የትንሹም የትልቁም መዘባበቻ ኾና ከማየት የበለጠ ምን የሚያንገበግብ ነገር ይኖራል?

በስደት በምንኖርበት ሀገር እንኳን፣ አውራ ጎዳናዎች እየተዘጉ በሞተረኛ ፖሊሶች እየታጀብን ሃይማኖታዊ በዓላትን በነጻነት ለማክበር መቻላችንን አስበን፣ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶቻችን በገዛ ሀገራቸው በየከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በሃይማኖታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ወከባና እንግልት ስንሰማ ካልተቆጨን ምን ሊያስቆጨን ይችላል?በማይመች ኹኔታ ውስጥ እያለፍን እንድናንቀላፋ አዚም ያደረገብን ማን ነው? ለመሆኑ እኛ የዚህ ዘመን ካህናት የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ምን ያህል ያሳስበናል?ካሳሰበን በተግባር ምን አድርገናል? ስለ ቤተ ክርስቲያን ስንል ምን ያህል መከራ ተቀብለናል? ስንት ጊዜስ ታግሠናል?

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ ጥቂት አባቶችና ወንድሞች፣ በተናጠል ከሚያደርጉት ትግል እንዲሁም አልፎ አልፎ ምእመናን በተለይም ወጣቶች በተለያየ ጊዜ ለሃይማኖታቸው ካደረጓቸው ተጋድሎዎች ውጭ፣ እኛ ካህናቱ ለብዙ ዓመታት አንቀላፍተናል። የእኛ ማንቀላፋት ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ጎድቷታል፤ መከራዋንም አብዝቶታል። መነሣት ያለብን ማንቀላፋታችንን በማመን ነው። ለችግሩ መባባስ በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ የእያንዳንዳችን አስተዋፅኦ አለበት። በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተለያየ ጊዜ የመከራ ዶፍ ሲወርድ እጃችንን አጣጥፈን በመቀመጥ፣ ለፖለቲካ ኃይሎች በማጎብደድ፣ መንግሥት በቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ በመጋበዝ፣ በመፍቀድና በመተባበር፣ በጎጥ በመከፋፈል፣ በጉቦ ቅብብል፣ በምዝበራውና በዘረፋው  በመሳተፍ፣…ወዘተ የብዙዎቻችን እጅ እንዳለበት መካድ አንችልም።

ታላቋ ቤተ ክርስቲያናችን፣ በዚህ ዘመን መገኘት በሚገባት ክብርና ልዕልና እንድትገኝ እኛ ካህናቱ ምን እናድርግ? ያልሠራነው ነገር ከመብዛቱ የተነሣ ለዚህ ጥያቄ የሚኖረን መልስ ብዙ እንደሚኾን አያጠራጥርም። ነገር ግን በእኛ አሳብ፣ ከዚህ በታች የተቀመጡትን ሁለት ጉዳዮች ማከናወን ከቻልን፣ ከእግዚአብሔር ፍርድና ከታሪክ ወቀሳ እንድናለን ብለን እናምናለን።

የካህናት አንድነቱ ዓላማዎች፤

1ኛ. ቤተ ክርስቲያናችንን ከፖለቲካ ኃይሎችና ከማንኛውም አካል ተጽዕኖ ነጻ እንድትወጣ፣ ወደ ቀደመ ክብሯና ልዕልናዋ እንድትመለስ፣ ሃይማኖቷንም በነጻነት እንድታስፋፋ ማስቻል፤ እንዲሁም ከፍተኛውን የሀገሪቱን የሕዝብ ቁጥር በሃይማኖት የምትመራ እንደመኾኗ መጠን በሀገር ጉዳይ ላይ ሊኖራት የሚገባው ተደማጭነት እንዲመለስ፣ የሰላም የፍቅር የአንድነት ሰባኪነትዋ፣ ሸምጋይነትዋና አስታራቂነትዋ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መታገል፤

2ኛ. አስተዳደሯን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሷ ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎችና ቀኖናዎች ብቻ እንድትመራ፤ ሀብቷን፣ ንብረቷንና ቅርሷን ከምዝበራ እንድትጠብቅ እገዛ ማድረግ፤

3ኛ. ለወደፊቱም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ከማንኛውም አካል የሚመጣውን ጫና እና በደል በመመከት ለነጻነቷ፣ ለመብቷና ለጥቅሟ ጥብቅና መቆም ናቸው፡፡

አባልነት፦ የሃይማኖት ሕጸጽ የሌለባቸው፣ የዘረኝነት/የጎጠኝነት በሽታ ያልተጠናወታቸው ወይም ከበሽታው የተፈወሱ፣ ከግል ጥቅማቸው ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ የሚያስቀድሙ፣ አቅማቸው በሚፈቅደው ሁሉ ሃይማኖታዊ ተጋድሎ ለማድረግና መሥዋዕት ለመክፈል ቁርጠኝነት ያላቸው፤ በአሁኑ ወቅት ያለው የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መለያየት ሳይገድባቸው በመላው ዓለም የሚገኙ ሊቃውንት፣ መነኮሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል ሁሉ የማኅበረ ካህናቱ አባል መኾን ይችላሉ።

አንድነቱ ለምን ያስፈልገናል

ወደ መፍትሔው መድረስ የምንችለው ችግሩን በግልጽ ተነጋግረን ስንተማመን ብቻ ነው። በተለይ ባለፉት ጥቂት ዐሠርት ዓመታት ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በጎጥና በሌሎች ምክንያቶች ከዓለማውያን በከፋ ኹኔታ ተከፋፍለን ብዙ ሽኩቻ አሳልፈናል።መተማመን ጎድሎናል፤ ተራርቀናል፤ ተገፋፍተናል፤ ተቆሳስለናል፤ የኛ ፍቅር መጉደል እኛን ራሳችንንም ጎድቶናል፤ ቤተ ክርስቲያናችንንም ብዙ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል። ከሃይማኖት ቤተሰቦች የማይጠበቅ ይህን ክፉ ባህል በመተው አንድ ኾነን ለቤተ ክርስቲያናችን በጋራ የምንቆምበት፣ ለሌሎች የምናስተምረውን ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት እኛም የምንተገብርበትና አስደናቂ ለውጥ የምናመጣበት ወሳኝ ጊዜ ላይ በመድረሳችን አንድነቱ ለነገ የማይባል አንገብጋቢ ጉዳይ ኾኗል።

ብዙዎቻችን የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር ሌላ አካል እንዲፈታልን እንጠብቃለን። እውነታው ግን ከእኛ ውጭ ማንም ሊፈታልን የማይችል መኾኑ ነው። እኛም ብንኾን አንድነት ከሌለን ልንፈታው አንችልም። አንድነት ሲኖረን እግዚአብሔር ይሰማናል፤ መንግሥት ተገዶም ቢኾን ያደምጠናል፤ ተቋማት ያከብሩናል። ካህናት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንት/ከእኛ በላይ ላሉት ሊቃነ ጳጳሳት ጉልበት፣ ከእኛ በታች ላሉት ምእመናን መሪ/ እንደመኾናችን መጠን እኛ በአንድነት መንቀሳቀስ ከቻልን፥ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሲኖዶስነት ሚናውን በነጻነት እንዲወጣ፣ ፓትርያርኩ የፓትርያርክነት ሓላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲተገብሩ፣ በየደረጃው ያሉ የቤተ ክህነት ሓላፊዎች ለሁለት ጌቶች ከመገዛት ተላቅቀው የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልእኮ ብቻ የሚፈጽሙ እንዲኾኑ ቀላል የማይባል ተጽዕኖ መፍጠር እንችላለን።

እኛ አንድ መኾን ከቻልን በአባትነት፣ በእረኝነት የምንመራቸውን ምእመናንን ወደ አንድነት ማምጣቱ ከባድ አይኾንም። የካህናቱና የምእመናኑ አንድነት ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋራ ተደምሮ የቤተ ክርስቲያናችንን ሉዓላዊነትና ነጻነት ይመልሳል፤ ያስከብራል።መንግሥት አሉታዊ ተጽዕኖ ከማሳደር እንዲታቀብና ከቤተ ክርስቲያናችን ላይ እጁን እንዲያነሣ ይገደዳል። ካህናቱ ጥቃቅን የልዩነት ምክንያቶችን አስወግደን፣ ከእንቅልፋችን ነቅተን፣ ግዴለሽነታችንንና ምንደኝነታችንን አሽቀንጥረን ጥለን በአንድነት መንቀሳቀስ ከቻልን ይህችን ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ማንም በቀላሉ ሊተነኩሳትና ሊገዳደራት ወደማይችልበት ደረጃ እናደርሳታለን።

መቼም ቢኾን መዘንጋት የሌለብን ነገር ቢኖር፣ በዚህ ዘመን የምንፈራው፣ የምንከበረው፣ የምንደመጠው፣ ሃይማኖታዊ መብታችንን ማስጠበቅና የምንፈልገውን ለውጥ ለማምጣት የምንችለው ብዙ ኾነን አንድ ስንኾን ብቻ መኾኑን ነው።

እንዴት ወደ አንድነት መምጣት እንችላለን

ይህ የካህናት አንድነት ጅምሩን በሰሜን አሜሪካ ያድርግ እንጅ በሒደት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን ሁሉ በአባልነት ለማካተት ዕቅድ ይዞ በከፍተኛ ኹኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በሺሕ የሚቆጠሩ ካህናትን እንዴት አድርጎ ወደ አንድነት ማምጣት ይቻላል? በማለት የሚተይቁ አሉ፡፡ ጉዳዩ ከባድ ቢመስልም በቀላሉና በአጭር ጊዜ ሊተገበር የሚችል መኾኑን በምሳሌ ማሳየት እንችላለን።

ለምሳሌ፦ ከኢትዮጵያ ውጭ 200 የሚኾኑ አጥቢያዎች አሉ ብንልና በእያንዳንዱ አጥቢያ በትንሹ በአማካይ 3 አገልጋዮችን መመልመል ቢቻል ከኢትዮጵያ ውጭ በአንድ ጊዜ ከ600 በላይ ካህናትን የዚህ ማኅበር አባላት ማድረግ ይቻላል ማለት ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ ለምሳሌ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ወደ 130 ገደማ የሚኾኑ አጥቢያዎች አሉ። በእያንዳንዱ አጥቢያ በትንሹ 10 ካህናትን መመልመል ቢቻል በአንድ ጊዜ 1300 ካህናትን ወደ አንድነቱ ማምጣት ይቻላል ማለት ነው። ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ አጥቢያዎችንም በተመሳሳይ መንገድ በመሔድ በሺሕ የሚቆጠሩ ካህናትን ወደዚህ አንድነት ማምጣት ይቻላል ብለን በጽኑዕ እናምናለን። ዘመኑ ደግሞ ለዚህ የተመቸ ነው። ማኅበራዊ መገናኛዎቹ በአንድ ጊዜ ብዙዎችን መድረስ ያስችላሉ።

ይህ ማኅበረ ካህናት ነገ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የማኅበራዊ መገናኛ ተከታዮች እንደሚኖሩት አንጠራጠርም። ይህ ስሌት ተግባራዊ መኾን የሚችለው ግን የካህናት አንድነቱን ዓላማና ጥቅም የተረዳን ሁላችንም በመላው ዓለም ለሚገኙ፣ ለምናውቃቸውና ለምንቀርባቸው ካህናት ሁሉ በትጋት ማስረዳትና መቀስቀስ ስንችል ብቻ ነው። ቆጭቶናል ብለን ከተነሣን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ ማስቀደም ይገባናል። ሁሉም ካህናት ወደዚህ አንድነት ይመጣሉ። የሚመጡበት ጊዜ ግን የተለያየ መኾኑ የሚጠበቅ ነው።

እንችላለን የሚለው እምነት ጎድሎናል፡፡ ብዙዎቻችን፣ የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር፥ የማይገፋ ተራራ፣ የማይሻገሩት ጎርፍ፣ የማይነጋ ጨለማ አድርገን ወስደነዋል። ሊፈታ የማይችል ነው ብለን ደምድመናል። በእኛ አቅም ልናደርገው የምንችለው ምንም ነገር የለም ብለን ተስፋ ቆርጠናል። የቅዱስ ሲኖዶስ ሰብሳቢና የቤተ ክርስቲያናችን ርእሰ አበው የኾኑት ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሮች አንዱ ስለኾነው አስተዳደራዊ ብልሽት፣ ስለተንሰራፋው ግልጽ ዘረፋ፣ ጉቦኝነትና ሌብነት ተጠይቀው ሲመልሱ፣ “ከአንበሳ መንጋጋ ሥጋ የማውጣት ያህል ነው”፤ “ምናልባት ቀጣዩ ትውልድ ይቀርፈው ይኾናል“ …ወዘተ በማለት ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል አስከፊ ኹኔታ ውስጥ እንዳለች ብቻ ሳይኾን ከአዘቅቱ መውጣት የማትችል መኾኗንም ጭምር ሊያሳዩን ሞክረዋል።

በርግጥ ይህ ለብዞዎች ተስፋ አስቆራጭ ቢኾን ሊያስደንቅ አይችልም፤ ምክንያቱም ቅዱስ ወንጌል እንዲህ ብሏልና፤ የሰውነትህ መብራቱ ዐይንህ ነው፥ዐይንህ ብሩህ ቢኾን ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይኾናል። ዐይንህ ግን ታማሚ ቢኾን ሰውነትህ ሁሉ ጨለማ ይኾናል። በአንተ ላይ ያለው ብርሃን ጨለማ ከኾነጨለማህ እንዴት ይበዛ!” /ማቴ.6፥22/

እንግዲህ እናስተውል፤ ዐይን ማለት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጅምሮ በየደረጃው የምንገኝ ውሉደ ክህነት ነን። አዕይንተ እግዚአብሔር ተብለን የምንጠራ መኾናችንን ልብ ይሏል። እኛ፣ ችግር መፍታት አንችልም፤ ብለን ተቀመጥን ማለት፣ የዓለም ብርሃን መኾን የሚገባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድቅድቅ ጨለማ እንድትጓዝ ፈረድንባት ማለት ነው። አሁን ጥያቄው፣ሁላችንም ከዚህ ጨለማ እንዴት እንውጣ የሚለው ነው።

መፍትሔው፣ የጎደለንን “እንችላለን” የሚለውን እምነት ማምጣት ነው። ችግራችንን ራሳችን እንፈታዋለን፤ በዘመናችን የሚታየውን ክፉ ታሪክ መለወጥ ይገባናል ደግሞም መለወጥ እንችላለን ብለን ማመን ነው። እንኳን እኛ፣ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ የምናደርገው ሃይማኖተኞቹ አይደለንም፣ ዓለማውያን እንኳን፣ “እንችላለን” ብለው በአንድነት በመነሣታቸው ብዙ ነገር ለመለወጥ እንደ ቻሉ በርካታ ታሪኮችን መጥቀስ ይቻላል። በቅርቡ እንኳን የሀገራችን ርእሰ መንግሥት ከሥልጣን እንዲወርዱ ያስገደዳቸው፣ “እንችላለን” ብለው የተነሡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተቀናጅተው ባደረጉት ትግል እንደኾነ መዘንጋት አይገባንም። ስለዚህ ከእኛ አቅም በላይ የኾነ ችግር የለንም።እንዲያውም ሙሉ አቅማችንን መጠቀም ከቻልን የእኛን ብቻ ሳይኾን የሌሎችን ችግር መፍታት እንደምንችል ማመን ይገባናል።

ምስጋና

በመጨረሻም፣ በተለያዩ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች የምትኖሩ ካህናት፣ ከቤተ ክርስቲያናችን በላይ የሚበልጥብን ምንም ነገር የለም፤ በማለት ከቤተሰዎቻችሁ ተለይታችሁ፣ ሥራችሁን ትታችሁ፣ ብዙ ገንዘብ አውጥታችሁ፣ እስከ ግማሽ ቀን የሚደርስ የአየር ላይ ጉዞ አድርጋችሁ ወደ ሲያትል ከተማ መምጣታችሁ ለሃይማኖት መቅናት ማለት እንዴት እንደኾነ፣ለቤተ ክርስቲያን መጨነቅ ማለት ምን ማለት እንደኾነ፣ ቆራጥነታችሁንና መንፈሳዊ ወኔያችሁን በቃል ሳይኾን በተግባር ስላሳያችሁን፣ መሥዋዕትነት እንዴት እንደሚከፈል ስላስተማራችሁን ደግመን ደጋግመን እናመሰግናችኋለን! ይህ ቁርጠኝነታችሁ ለሃይማኖታችሁ ስትሉ ወደ የትኛውም ቦታ ለመሔድና ማንኛውንም መሥዋዕት ለመክፈል የተዘጋጃችሁ መንፈሳውያን አርበኞች መኾናችሁን የሚመሰክር፣ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች መኾናችሁን የሚያረጋግጥና በዓለም ላይ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ሁሉ በመልካም አርኣያነቱ የሚጠቀስ በመኾኑ መንፈሳዊ ኩራትና ደስታ ሊሰማችሁ ይገባል።

በሲያትል ከተማ የምትገኙ ካህናትም፣ ዓላማውን ከማመንጨት ጀምሮ ጉባኤው የተሳካ እንዲኾን ከአንድ ወር በላይ ለሚኾን ጊዜ ሥራችሁንና ትምህርታችሁን ሳይቀር እየተዋችሁ የስልክና የአካል ስብሰባዎችን በማድረግ፣ ሓላፊነቶችን በመከፋፈል፣ ገንዘባችሁን፣ ጉልበታችሁንና ጊዜያችሁን መሥዋዕት አድርጋችሁ ያማረ የሠመረ የምሥረታ ጉባኤ ስላዘጋጃችሁ ምስጋና ይገባችኋል።

በአጠቃላይ ይህ ጉባኤ የተሳካ እንዲኾን በሩቅም በቅርብም ኾናችሁ ለተባበራችሁ፣ በጎ አሳባችሁን ለገለጻችሁ፣ ለጸለያችሁ ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር                                   

ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም.(May 03, 2018)

የሲያትል ማኅበረ ካህናት

ሲያትል ዋሽንግተን

“የልጄን ዐይን አይቼ ብሞት ጥሩ ነበር” – ልጃቸው የታሰረባቸው የ82 ዓመት አባት

በእስር ላይ የሚገኘው የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምሕር ጌታ አስራደ

በሽብር ወንጀል ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምሕር ጌታ አስራደ ከእስር እንዲፈታ ቤተሰቦቹ ተማፀኑ።  ሌሎች እስረኞች በይቅርታና በምሕረት እየተለቀቁ በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ እስረኞች ግን አሁንም ድረስ ጭለማ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው ይገኛሉ ብለዋል።

የመምሕር ጌታ አስራደ ጠበቃ አቶ አለልኝ ምሕረቱ ይቅርታና ምሕረቱ ለሁሉም እኩል ሊሰጥ ይገባል ብለው ለፍርድ ቤትና ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቤቱቱታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)
https://amharic.voanews.com/embed/player/0/4408658.html?type=audio
ጽዮን ግርማ – VOA

ዶ/ር አብይ አህመድ …ዛሬም ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም።ግንቦት ሃያ ፳ መጣ:-ግንቦት ሰባትን ፯ አልፎ

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

የማቴዎስ ወንጌል ፮፥፳፬

 

 ግንቦት ሃያ ፳ ስለመጣ አንዱን የጉጅሌ አባል ማንነቱን ለሚጠየቀው ሰው መልሱ”አህያ ፈጅ”ከሚለኝ ይልቅ፤”ዥብ ነኝ” አለማለቱ፣ሁለታችንም በምናውቀው ምክንያት፦”…በቅሎ፥አባትኽ፡ማን፡ነው፡ቢሉት፥እናቴ፡ፈረስ፡ነች፡አለ።” እንደሚሉት ሰዎች ዓይነት ነው፤ምክንያቱስ?…

 

ለምን እንወሻሻለን ዶ/ር አብይ አህመድንስ ስለፖለቲካዊ ማንነቱን በምሳሌ”ምንድነው ሥራህ?”ስለው”አህያ ፈጅ”ከሚለኝ፤በቀላሉ”ዥብ ነኝ”ያላለኝ ምክንያቱን እኔም ሆንኩ እሱ፣ሁለታችንም እናውቀዋለን ብዬ አምናለሁ።

ምክንያቱስ ምንድን ነው?ቢባል አጋጣሚው በግንቦት ሃያ ፳ መምጣት ላይ የተሰመረ ነውና የጥያቄው መነሻ ግን እሰይ መጣልን የተባለበት ምክንያት ሲሆን፤የበዓል ቀን መባሉ ነው።ባሕላዊ ዕምነትም አይደለም፤እንደላሊበላዎቹ በሰው ተስካር እንደሚሞሸሩት።ዶ/ር አብይ አህመድም ይህንን ያውቁታል ብዬ እገምታለሁ።በዚያን ዕለት ግንቦት ሃያ ለኢትዮጵያውያን ያሳለፍነውን መከራ እየተራመድን የምንወጣ መስሎን ደስታ በተቀላቀለበት የለቅሶ ቤት ወደሓዘን መጓዛችንን ያወቅነውና እስከዛሬ ድረስ እጅግ በባሰ ሁኔታ መከራ መቀበል የጀመርንበት ዕለት መሆኑን የምናስታውስበት መራራ ትዝታ ነው።

ወደፍሬ-ነገሩ ስንመጣ “እሳት ሲነድ ለአንዱ ረመጥ ለአንዱ አመድ”እንጂ፣ሁለት እሣት ወይም ሁለት አመድ አይኖርም።እነሆ በአሁኑ ወቅት የተፈፀመው የሥልጣን መደላድል፦ምርጫም ሽግግርም ሳይሆን፣በተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሰበብ፣የጎደለውን ለመሙላት ዶ/ር አብይ አህመድ ማሟያ ሆነው ተመረጡ ተባለ እንጂ፤ሕዝብ የመረረ አመፁን ይዞ ጉሮሮአቸውን ሊያንቅ ይህችን ያህል ቀርቷቸው ከመግፋት በስተቀር የሚያውቁት ነገር አልነበረም።እናም ብዙም የተባለው በዶክተርነቱ ላይ አይደለም፣በአዲሱ ሹመት ጠቅላይ ሚኒስቴር ስለተባለው አብይ አህመድ፤ እና በጠቅላይ ሚኒስቴርነታቸው ሰበብ፣በኮነሬልነታቸው ማዕረግ የሥልጣን ርክክብ ምክንያት ስለተነሳው ነው።

እንደሚባለው ሲያዩት ደግ መሳይ ክፉ፣ገንቢ አፍራሽ፣ምሥጉን ርጉም፣ምንም ያላሉም አሉም፤ባመዛኙ ግን ዶ/ር አብይ አህመድን እስኪ እንያቸው ብለዋል። ፕሮፌሰሮች፣ ዶክተሮች፣የኪነጥበብ ባለሙያተኛ፣ሕዝብ፣ ጋዜጠኞች፣ ባለሙያተኞች በሙሉ፣ወንጀለኞች እና ነብሰገዳዮች፣አካለ ስንኩላን፣ከሁለቱ ፆታዎች በተጨማሪ ባለሦስተኛ የፆታ ረድፈኞች(ፍናፍንቶች)ነን የሚሉትንም ጨምሮ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሔር-ብሔረ-ሰቦች እኩል ነን በማለታቸው ውስጥ አልቀሩም።

ያለፍንበት የኢትዮጵያ ታሪክና ለወደፊቷ የምንመኝላት ተስፋ ተዳምረው፣አሁን ስለአለንባት አገር እንድንስማማ ትግል በመጀመሩ ነው፣ማን እንደሆነ ትውልድ ገዳይ ብለን በሰከነ ሁኔታ የበሰበሰውን አይነት ብርቱካን እንደመለየት ጉዞውን የምንያያዘው።ይህ ጉዞ እንዳለፉት አርባ አራት ዓመታት ዓይነት፣በደም የተጨማለቀ፣በሰቆቃ የታጨቀ፣በግፍ የተለቃለቀ፣በውሸት የተደበቀ፣በሚገድል እያነቀ፣ጭካኔን የሰነቀ፣ደግነትን ያራቀ፣የሚያስገድል እያሳቀ፣በለሰለሰ ልሣን ውስጥ ውስጡን የማያሳጣን፣ዕውነትን ያልሆነ ዳሩግን የሚያስመስል፣በብልጭልጭ ያልተንቆጠቆጠ፣ወርቅም ያልሆነ፣በፍፁም መሆንም የለበትም፤ይህ የጉዞአችን አቅጣጫ ነውና።በተቻለ መጠን ከአስርቱ ትዕዛዛት ቢያንስ አምስቱን የሚያከብር ቢሆን ይመረጣል።

እናም”ቃል”ነበር መጀመሪያ በፊደላት ውስጥ ተፀንሶ፤እንደ”ዥብ”ቃል።ጅማቱ እንኳ ሳይቀር”ልብላው…ልብላው”እንደሚልና ቆዳው ደግሞ ብሶ”ምን እንደሚሆን እናውቀዋለን።ሥምና ተግባራቸው የተለያየ ከሆኑ በዛም አነሰም በመንገድ ላይ የውርደት ሐቁ እንደ ኣያጅቦ ቅልብጭ ብሎ ባደባባይ ይታያል።ኣያጅቦ ደግሞ አስቀያሚ ጥርሶቹ ብቻ ሳይሆኑ፣አንካሳ እግሮቹም ያጋልጡታል፤ከዚያም በላይ”ያ ሆዳሙ ቆሻሻው “አያ ዥቦ”ነው ይባላል።

ከዚህ አንፃር ቀጭኗ የፈተና መንገድ መጣች፦ግንቦት ሃያ ፳ የተባለችው ቀን “ለአንዱ እሣት ላንዱ አመድ”የሆነው ዕለት እየመጣ ነው፤ዶ/ር አብይ አህመድ እሣት እና አመድም መሆን አይቻላቸውም። ምክንያቱም ግንቦት ስባት ፯ የታወቀ የኢትዮጵያውያን የድል ቀን እና መቶዎች በጅምላ በአንዴ በምርጫ ድል ሰበብ እና በነፃነት ትግል ምክንያት የተገደሉበት የሰማዕታት ዕለት ሆኖ የሚከበርበት በመሆኑ፣የዚያ ግንቦት ሃያ ፳ ግድያ ሰበብ መነሻ  በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሃያ ሰባት ዓመታት መከራ እና ሰቆቃ ምክንያት መሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።ይህቺ ግንቦት ሃያ ፳ የተባለች ርጉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራዋን ፅዋ መጋት የጀመረችበት ቀን ስለሆነ ማቅ የመልበሻችን መጀመሪያዋ ዕለት ግንቦት ሃያ ፳ ሆናለች።የ”ወያኔ ኢሐድግ”ብለው የ”ባንዳዎችን ቡድን” የሚያንቆላጰላጥሱትም ሆኑ፣የጉጅሌን መሰሪ ተግባሮች ጠንቅቃችሁ የምታውቁ ሁሉ፤ብታምኑም ባታምኑም በኢትዮጵያ ሐገራችን ዜጎች በትዕቢት፣በግዴለሽነት፣በማንለብኝነት፣እና ያለምንም ምክንያት በየቀኑ ኢትዮጵያውያንን ይገድላሉ።ግንቦት ሃያ ፳ መጣ:-ግንቦት ሰባትን ፯ አልፎ፤ታዲያ ዛሬም ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም።

እንግዲህ ዶ/ር ኮነሬል አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስቴር፣የጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አማካኝነት ለግንቦት ሃያ ፳ በመቆም ባለፉበት ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ የነብስ ማጥፋትና የንብረት ዝርፊያ መፈፀሙን ይሁንታ መስጠት፤ካሻቸውም ማስቀጠል:-አሊያም ከዚህ ማቅ ለመውጣት ግንቦት ፯ በተገኘው የሕዝብ ድምፅ ማሸነፍ እና ከሁለት መቶ ሰላማዊ ሰዎች በላይ በጅምላ ከተገደሉበት የድል ቀን ጋር በመቆም ሕዝብን መደገፍ ምርጫቸውን መለየት ይኖርባቸዋል።

 

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።  የሉቃስ ወንጌል ም-፲፮፥ቁ-፲፫

ጉድ በል ኢትዮጵያዊ፤ብሊዮን ሲሲ ደም-ተመጥጧል።
ኢትዮጵያን ያመሳት ወቸገል ዜናዊ፤
አምስት ብሊዮን ዘርፏል፣
ጉድ በል ኢትዮጵያዊ።
በትግሬነት ጨምበል ወልቃትነቷን፤
የከዳችው አዜብ ሳታውቅ ማንነቷን፤
በሸበጧ ገብታ ባሏ የዘረፈውን፤
እሷም በተራዋ ዘርፋናለች አሁን።
ምንቀራት እንጀራ ከሕዝቡ አፍ ነጥቃ፤
ቡና እና ሌጦውን ሳትታይ ደብቃ፤
በሁሉም አቅጣጫ በሚስትነት ሥሟ፤
በፍርፋሪ ሥልጣን በሴትነት አቅሟ፤
እያሞጠሞጠች፣ታጋይ ነኝ እያለች፤
በካድሬዎች ወጥ-ቤት ያኔ እንዳልታገለች፤
ይህንን ሐቅ ታሪክ አድርጋለት ጭምብል፤
ታጭበረብራለች ዛሬም ልታባብል። 
ሚስቱ የነበረችው የወቸገል ዜናዊ፤  
ቢሊዮን ዘርፋለች፣
ጉድ በል ኢትዮጵያዊ።
ዶክተር-አብይ አንተም ወንጀለኞች ለቀህ፤
ሲዘርፉ እንዳላየህ ትሆናለህ አውቀህ።
ይሄንን ልብ በል አይተህ ዝም አትበል፤
መራራ ነው ትግል ተዘጋጅ ለመክፈል።
በፈለግነው ሒሳብ ደሞዙ ቢሰላ፤
ልዩ ገቢ ቢኖር ቢፈለግም መላ፤
በፍፁም ይህ ንብረት የኢትዮጵያችን ነው፤
ዛሬ ካልተመለሰ ለመቼም አናምነው።
እናም ባለሥልጣን ሁሉም የነበሩ፤
እንደወቸገሉ በሕዝብ ይመርምሩ።
ኢትዮጵያን ያመሳት ወቸገል ዜናዊ፤
አምስት ብሊዮን ዘርፏል፣
ጉድ በል ኢትዮጵያዊ።   
ዓቢይ ኢትዮጵያዊ