የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ 4 ቀናት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል! (የሰነድ ማስረጃ)

ከስዩም ተሾመ

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርስ ስምምነትን ለመቀበል መወሰኑን ተከትሎ ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኗል። በተለይ በአንዳንድ የትግራይ አከባቢዎች የአልጄርስ ስምምነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ፤ በተለይ ባድመ ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች መስዕዋት ሆነዋል፣ በአከባቢው የሚኖሩ የማህብረሰቦችን ለሁለት ይከፍላል፣ እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገሪቱ መሬትና ሉዓላዊነት ላይ በተናጠል የመወሰን ስልጣን የለውም እና ስምምነቱን ለመቀበል ሕዝበ ውሳኔ መደረግ አለበት የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ። ከዚህ አንፃር “የኢህአዴግ መንግስት የአልጄርስ ስምምነትን ተቀብሎ ተግባራዊ ሊያደርግ አይገባም” የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ።

ሆኖም ግን፣ “የጉድ ሀገር ጉድ እያደር ይወጣል” እንደሚባለው፣ ከአልጄርስ ስምምነት ጋር በተያያዘ ሌላ አዲስ ጉድ ወጥቷል። ይኸውም የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአልጄርስ ስምምነትን ተቀብሎ አፅድቆታል። ህዳር 29/1993 ዓ.ም በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ 7ኛ ዓመት ቁጥር 7 ታትሞ በወጣው አዋጅ ቁጥር 225/1993 መሰረት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በኤርትራ መንግስት መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በኤርትራ መንግስት መካከል በአልጄሪያ ዋና ከተማ አልጄርስ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ለማፅደቅ የወጣው አዋጅ ቁጥር 225/1993 የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55 ንዕስ አንቀፅ 1 እና 12ን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሆነ በአዋጁ ተጠቅሷል። አንቀፅ 55 (1) የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ መሰረት ለፌደራል መንግስት በተሰጠው የስልጣን ክልል ውስጥ ሕጎችን ያወጣል በማለት ይደነግጋል። አንቀፅ 55(12) ደግሞ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የህግ አስፈፃሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም-አቀፍ ስምምነቶች ያፀድቃል” ይላል።

የአልጄርስ ስምምነት በቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የኤርትራው ፕረዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፊርማ የፀደቀው ታህሳስ 03/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 12th December, 2000) መሆኑን ከላይ ካለው የስምምነቱ ሰነድ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጂ፣ የአልጄርስ ስምምነትን በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የታወጀው ህዳር 29/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 8th December, 2000) ነው። በመሆኑም የሰላም ስምምነቱ አልጄርስ ላይ ከመፈረሙ አራት (4) ቀናት በፊት የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፅድቆት ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል። የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55(4) ምክር ቤቱ “የህግ አስፈፃሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም-አቀፍ ስምምነቶች ያፀድቃል” የሚል ቢሆንም የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በምክር ቤቱ ፀድቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታውጇል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s