የማለዳ ወግ…. ለእስኬው ብርታት ለሰርኬ ጽናት ክብር ሲሰጥ!(ነቢዩ ሲራክ)

* ጋዜጠኛ እስክንድር ብርቱና አይበገሬ ብዕረኛ
* ጋዜጠኛ ሰርካለም ታማኝና ጽኑ ታጋይ 
* ሰርታችኋልና ትመሰገናላችሁ ፣ ትከበራላችሁ
* ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ !

ክብር ለሚገባቸው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ብርታት ለውድ ባለቤቱ ለጋዜጠኛ ሰርካለም ታማኝነትና ጽናት ከፍ ያለ አድናቆት አለኝ !ጋዜጠኛ እስክንድር ብርቱና አይበገሬ ብዕረኛ መሆኑን የማውቀው ሀገር ቤት በነጻው ፕሬስ እሰራ በነበረበት ጊዜ ጀምሮ ነው ። ጋዜጠኛ ሰርካለም እንዲሁ ቀደም ብየ የማውቃት ቢሆንም Nafkot Eskind በሚለው የፊስ ቡክ ገጿ ከእስክንድር መታሰር በኋላም ዘር ሀይማኖት ሳትለይ በምታደርገው የፍትህ ዲሞክራሲ አቀንቃኝነቷ አከብራታለሁ። ብርቱዋ ሰርኬ ታማኝነትና ጽናት የተላበሰች ስሜቷን የማትደብቅ በሰላማዊ ታጋይ መንፈሷ የማደንቅ የማከንራት እህቴ ናት ። ሁለቱ ኮከቦች ስለኢትዮጵያ ብዙ ሆነዋል ። ተስረዋል ፣ ተገርፈዋል ፣ በእስር ላይ ናፍቆትን ወልደዋል ፣ ተሰቃይተዋል ፣ ጨካኞች አባት እስክንድርን ከብላቴና ልጁ ከናፍቆት መንጭቀው ወስደው ፊት ለፊቱ በብረት ካቴና አስረው ወስደውታል …ብዙ ፈተና ያዩ ጥንዶች ብቻ አይደሉም

በትክሉ መካከል የተወለደው ናፍቆት ሳይቀር የግፉ ሰለባ ሆኗል 

ጋዜጠኛ እስክንድር ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካልም በቨርጅኒያ ተሞሽረው ስላመሹበት ምሽት ወዳጃችን ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማሪያም ” የቨርጂኒያ ምሽት ” በሚል ርዕስ ስር ያሰራጨው መረጃ እንዲህ ይላል ” …በርካታ ኢትዮጵያውያን በሂልተን ሆቴል በታደሙበት ስብሰባ አዳራሹ ሞልቶ ኮሪደር ላይ የነበረውና ሞልቶ የተመለሰው በርካታ ነበር። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለማመስገን በተዘጋጀው ስብሰባ የተለያዩ ታዋቂ ሰዋች ንግግር አድርገዋል። ጋዜጠ ኛ ሰርካለም ፋሲል የምስጋና መልእክት አስተላልፋለች። እስክንድር ያቀረበው ጥልቅና በሳል የዳሰሳ ፅሁፍ መሳጭ ነበር! ከግማሽ ሰአት በላይ በፈጀው ዳሰሳው ከንጉሱ ዘመን አንስቶ እስከ ጠ/ሚ/ር አብይ ድረስ ያለውን በማብራራት.. መጭው የአገራችን የዴሞክራሲ ሂደት ምን መሆን እንዳለበት በፅሁፉ አመላክቷል። … እስክንድር በመጨረሻም እስር ቤት አብረውት የታሰሩት “ምስጋና አድርስልን” እንዳሉት ጠቅሶ ይህንኑ አስተላልፏል። ..”

በእርግጥም እስኬውና ሰርኬ ከዚያ ሁሉ መገፋት በኋላ ቀኑ ነገቶ በደስታ ፊስታ ስላየናቸው ደስ ብሎናል ። በተወሰነ ደረጃ ለሁለቱ ብርቱ ጥንዶች ለወዳጄ ለእስኬውና ለሰርኬ ክብር ሲሰጣቸው የማየቴን የተሰማኝን ደስታ መግለጽ አይቻለኝም ። የሰራ መምስገን ይገባዋል ። በዝግጅቱ መልካም የሰሩት ሁሉ መመስገናቸውን በጎ ልምድ ነገር ነው ። በጎነቱ መልካም ስራቸው ጎልቶ ሲወጣ ሌሎችም መልካም እንዲሰሩ አርአያ ይሆናሉና ነው ።

በጎ ለመስራት የተነሳ ሰው መጀመሪያ የሚያየው በመልካም ስራው የሚያገኘውን ክብርና ሙገሳ ነው ብየ አላምንም ። ብዙዎች የኑሮ ትርጉሙ የገባን ለህሊና እርካታ እና ከጸጸት ላለመውደቅ አንጅ ለክብርና ሙገሳው ብለን እንሰራለን አልልም ። ይህን ብናደግም የፈለግነው ክብርና ሞገስ አይገኝም ። እስክንድርና ሰርኬም ያደረጉት ይህን ይመስለኛል ። ኢትዮጵያን ይወዳሉ ፣ ለሚወዷት ሀገር መስዋዕት ከፍለዋል እየከፈሉ ነው ። ይህን ሲያደርጉ አክብሩ አወድሱን ብለው አይደለም ። መስራት ያለባቸውን ስራ ለህሊናቸው ነጻነትና ለሀገራቸው ሰሩና ተከበሩ ! የሆነው ይህ ነው ! ከአድማስ ባሻገር ስለ ኢትዮጵያ ለከፈሉት መስዋዕትነት መተኪያና ማካካሻ ባይሆንም ድካማቸውን አገናዝቦ ክብር ሲሰጣቸው ስመለከት ደስ አለኝና እግዚአብሔርን ስሙን ከፍ አድርጌ በመጥራት አመሰግንኩ

ዶር አብይንም እጅ ነሳሁ !

ወዳጄ ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማሪያም ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ በሚል በዝግጅቱ ዙሪያ ባቀረበው መረጃ ላይ ስደተኛ የሙያ አጋር ጋዜጠኞች ስላስታወሰን ከልብ አመሰግናለሁ ! ብርቱ ወዳጆቸ ጋዜጠኛ እስክንድር ፣ ውድ ባለቤቱ ወዳጄ ጋዜጠኛ ሰርካለም እና ልጅ ናፍቆት እስክንድር እንኳን ደስ አላችሁ

ክብር ከሚገባው ክብር እሰጣለሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓም

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s