ድንቄም “Bringing Africa Togather” (መስቀሉ አየለ)

ከነጻነት ወዲህ በዚህ አየር መንገድ መሳፈር ባርነት “መቀደስ” ነው!

Ethiopian Airlines crew.

መስቀሉ አየለ

አንዳርጋቸው ጽጌ በግዮን ሆቴል ውስጥ ታስሮ እንደነበር በቃለ መጠይቁ ወቅት ካጋለጠ ወዲህ እንዲህ ያሉ “የክብር ኮከብ” ያንጠለጠሉ ሁቴሎች ብቻ ሳይሆኑ በነ ለታዬ ስም መሃል አዲስ አበባ ውስጥ የተገነቡ “መኖሪያ ቪላዎች” ሁሉ የሰው ልጅ እንደ በግ የሚበለትባቸው የአገር ውስጥ ኦሽዊትዝ ካምፖች እንደሆኑና ምን ያህል ዜጎቻችን ዋጋ እንድከፈሉባቸው የነ ሞንጆሪኖን የእግር ጥፍር ዘቅዝቆ በጉጠት የሚነቅለው ብድር መላሽ አዲስ አበባ ሲደርስ ተጽፈው የማያልቁ ህልቁ መሳፍርት የሰቆቃ ዶሴዎች ወደ ጸሃይ ብርሃን ይወጣሉ። ምስጋና ለማህበራዊ ድህረገጽ የወፎች ዝማሬ የሚሰማበት የገነት ውስጥ የአትክልት ስፍራ የሚመስለን ግዮን ከሆዱ ውስጥ የቶርቸር ቻምበር ጭምር ተገጥሞለት እምባ እንድር ጅረት የሚፈስበት ተቋምም ጭምር እንደሆነ ዜናው በብርሃን ፍጥነት አለምን ሲያዳርስ የጉዳዩ ተዋናይ የሆነው የግዮን ሆቴል አስተዳደር ዛሬ ይፋ ለወጣበት ድብቅ ማንነቱ ወደ አደባባይ ወጥቶ ትንፍሽ ያለው ነገር የለም።ወንጌል ከላይ አብረቅርቀው ውስጣቸው ግን ስለተበላሹ ነገሮች ሲናገር “የተለሰነ መቃብር” የሚል ስነ ቃል ይጠቀማል። እነ ቴዲ አፍሮ በዚህ ሆቴል ሲያዘጋጁ በኖሩት የሙዚቃ ኮንሰርት እየተዝናና፣ ሰርጉን እየደገሰና በግዮን መናፈሻ ውስጥ ፎቶውን ለታሪክ እያስቀረ ነገር ግን ማእከላዊንና ቅሊንጦ የሚል ስም ሲሰማ ሲያማትብና ሲሳቀቅ የኖረው ህዝብ ምስጋና ለፋኖ ቄሮና ዘርማ ዛሬ ህዝባችን ከደረሰብት ንቅናቄ አንጻር ይህንን ጉድ ሲያውቅ በሚወስደው የሞራል አጸፋ ሆቴሉን አስከሬን የወጣበት ቤት እንደሚያስመስለው ተስፋ እንዳደርጋለን። ቴዲ አፍሮን ጨምሮ ከእንግዲህ ዘፋኞቻችንም ሊውጡት የሚገባው መራራ እውነት ከግዮን የሙዚቃ መድረቆች ስር በአጽማቸው የሚሄዱ ብዙ ነፍሳቶች መኖራቸውንና የወደቀችው ባንዲራ ሳትነሳና መሬቱ ሳይነጻ በዚህ ቦታ ላይ ለዳንኪራ መቆም ኢሞራላዊ መሆኑንና ይህን አለመስማት ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ጭምር ነው።የደደቢት አራዊቶች ግን ምናልባት ትንሽ እድሜ ካገኙ ሆቴሉን ለግዜውም ቢሆን የሙሉ ግዜ ማእከላዊ ቢያደርጉት ስንኙ ቤት ይመታላቸዋል።

ሌላው ግን የግዮን ሆቴልን ያህል ብዙ ትኩረት ያልተሰጠበት የወንጀል ተቋም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። አቶ አንዳርጋቸው እንደተናገረው የባንዲራችንን መቀነት የታጠቀው ይህ አውሮፕላን የአለም አቀፍ የበረራ ህግን በመጣስ ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣና ያለ ታሳሪው ፈቃደኝነት እጅና እግሩ በሰንሰለት ታስሮ ፊቱ በጆንያ የታፈነን ሰው ጭኖ በመውሰዱ እንደ ግዮን ሁሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ሊዘመትበት ይገባል።

ኢትዮጵያውያን አንድ ልብ ሊሉት የሚገባው ነገር ዛሬ በብዙ የአውሮፓ አገሮች ውስጥ የስደተኛነት ማመልከቻቸው ውድቅ የተደረገባቸው አፍሪካውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ሲወሰንባቸው ፈቃደኛ ስለማይሆኑና እነሱን አስገድዶ ወይንም የእንቅልፍ መርፌ በመውጋት በዚህም አንድ አደጋ ቢፈጠር እራሱን ለማዳን በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ለመጫን ደግሞ የአየር መንገድ የበረራ ህግ ስለማይፈቅድ ብቻ ሳይሆን የራሳቸው አየር መንገዶችም ተባባሪ ስለማይሆኑላቸው እንዲህ አይነቱን የጨለማ ስራ የሚሰራላቸው “ብሪንጊንግ አፍሪካ ቱጌዘር”¡¡¡ እያለ ለራሱ የዳቦ ስም ያወጣው የኢትዮያ አየር መንገድ መሆኑን በተለይም ናይጀሪያ ጋና ሴርስሊዮን ወዘተ በመሳሰሉ አገሮች በደንብ የታወቀ የአደባባይ እውነት ነው። ገና “ሀ” ብለው አዲስ አበባ በገቡ ማግስት በወቅቱ የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢነትን የተቆናጠጠው የዋርዲያዎቹ አለቃ ሰዬ አብራሃ የተባለ እፉኝት አየር መንገዳችን የሚታወቅበትን ባለ ግርማ ሞገሱን የአንበሳ አርማ “የአማራ ሱፐርማሲ መገለጫ ነው” ብሎ እንዳስጠፋው ይታወቃል። ስንት ትውልድ ተፈራርቆና ስንት ተደክሞበት እንደ አትሌቲክሳችን ሁሉ በበጎ የምንታወቅበትን አንድያ ተቋም አዋርደው የመርዝ ሰንኮፋቸው ከረጢት ሲያደርጉት ሃዘኑን ሆድ አይችለውም።መቸም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በብዙ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ፊት እየቀረበ ይህንን ጉድ መግለጡ ለአየር መንገዱ “ጥሩ ማስታወቂያ”¡¡¡ ሆኖለታል።ነገር ግን በዚህ ሳይወሰን ትንሽ ትንፋሽ ወስዶ ደግሞ ተቋሙ በምን አይነት አራዊቶች እጅ እንደወደቀ እንዲታወቅና ዋጋም እንዲከፍልበት ይህን አየር መንገድ አለም አቀፍ የህግ ባለሙያዎችን በማቆም በእንግሊዝ አገር ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሰርትበት አደራ እንላለን።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s