የመሐል ሐገሩን ማእከላዊን በእጅጉ የሚያስንቁ ማሰቃያ ቤቶች በትግራይ አሉ።

ሐጫሉ አበበ ይባላል። የአምቦ ልጅ ሲሆን በ2008 በባህርዳር ዩንቨርስቲ 2ኛ ዓመት ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበር።

በ2008 በባህርዳር ከተማ በነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ታስሮ ትግራይ ክልል (ሽሬ?) የሚገኝ የወታደር ካምፕ ለሁለት አመት ከቆየ በኋላ ከሳምንት በፊት ነው ከሌሎች ሰላሳ የሚሆኑ አብረውት በካምፑ ታስረው ከነበሩ ተማሪዎች ጋር በሲኖትራክ በለሊት አምጥተው ባህርዳር የተጣሉት።

ተማሪዎቹ መጀመሪያ ሲታሰሩ 600 እንደነበሩ እና በኋላ ላይ ግን 80ዎቹ ብቻ ታስረው እንዲቆዩ መደረጋቸውን አበበ ይናገራል። በካምፑ ቆይታቸውም የሚሰጣቸው ምግብ ዳቦ በሻይ እና ኮቾሮ በውሃ ብቻ ነበር። ፍርድ ቤት የሚባልም ቀርበው አያውቁም። ብልት ላይ ውሃ ተንጠልጥሎባቸውም የተኮላሹ አሉ። ቤተሰቦቻቸው ሊጠይቋቸው ቀርቶ የት እንዳሉም አይታወቅም ነበር።

እዛው ካምፕ ከ20 ዓመት በላይ የቆዩ ፍርድ ቤት ቀርበው የማያውቁ እንዲሁም ከእነ አበበ ጋር በ2008 ታስረው ያልተፈቱ (አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ) በርካታ እስረኞች አሉ።

ማእከላዊ ብቻ ሳይሆን ማእከላዊን በእጅጉ የሚያስንቁ ማሰቃያ ቤቶችም ይዘጉ!”

ማህሌት ፋንታሁን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s