ቋንቋና ብሔራዊ ኵራት – ጌታቸው ኃይሌ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከየትና እንዴት መጣ? (ስዩም ተሾመ)

ሰሞኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰኘው አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መመስረቱን ተከትሎ በአንዳንድ የአማራና ኦሮሞ ልሂቃን፣ እንዲሁም የአንድነት አቀንቃኝ በሆኑ ወገኖች መካከል አላስፈላጊ እሰጣ-ገባ እየተካሄደ ነው። ራሴን ማጋነን አይሁንብኝና፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚባል ፓርቲን ስለማቋቋም ሳይነሳ፣ ኦቦ ለማ መገርሳ ወደ ባህር ዳር መሄድ ሳያሰብ፣ የኦሮማራ ጥምረትና ትብብር ሳይጀመር፣… ከሁለት አመት በፊት ከታች በምስሉ ላይ በተገለፀው መልኩ የአማራ ልሂቃን ከቀኝ ወደ ግራ ዘመም፣ የኦሮሞ ልሂቃን ደግሞ ከግራ ወደ ቀኝ ዘመም ፖለቲካ በሚያደርጉት ሽግግር በእኩልነት መርህ ላይ የተመሰረተ ጥምረት እንደሚመሰርቱ ገልጩ ነበር።

በዚህ መልኩ በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የተጀመረው የኦሮማራ ጥምረት ብአዴንና ኦህዴድ እርስ-በእርስ እንዲተባበሩ በማድረግ የህወሓት የስልጣን የበላይነት ለማስወገድ አስችሏቸዋል። አብዛኞቹ የኦሮሞ ልሂቃን ሲያራምዱት የነበረውን የኦሮሞ ብሔርተኝነት ወደ በመተው ኢትዮጲያዊ አንድነትን ማቀንቀን ጀምረዋል። በተቃራኒው ብዛት ያላቸው የአማራ ልሂቃን ሲያራምዱት የነበረውን ኢትዮጲያዊ አንድነት ወደ ጎን በመተው የአማራ ብሔርተኝነትን ማቀንቀን ጀምረዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መመስረት የዚሁ የሽግግር ሂደት ውጤት ነው። ስለዚህ የራሱን የለውጥ ሂደት ተከትሎ የመጣ ስለሆነ እንደ ልዩ ፖለቲካዊ ክስተት መታየት የለበትም። በመሆኑም “እንዴት የአማራ ብሔርተኛ ቡድን ሊፈጠር ይችላል?” ብሎ መረባረብ አያስፈልግም፣ ወይም “የአማራ ብሔርተኛ ቡድን ስለተቋቋመ የተለየ ነገር ይሰራል” ብሎ መጠበቅ አግባብ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ የአማራና ኦሮሞ ልሂቃን የፖለቲካ ንቅናቄ ከቅኝ ወደ ግራ እና ከግራ ወደ ቀኝ የተሸጋገረበትን ምክንያት መዝርዝር መረዳት ያስፈልጋል።

ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ኢትዮጲያ ውስጥ ከፍተኛ የፖለቲካ ሽኩቻ የነበረው በኦሮሞ፥ አማራና ትግራይ ልሂቃን መካከል እንደነበር ይታወቃል። ለዚህ ዋናው ምክንያት ሦስቱ የፖለቲካ ቡድኖች የሚያራምዱት የፖለቲካ አቋምና አመለካከት፣ እንዲሁም በሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ያላቸው የስልጣን ልዩነት ነው። እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የትግራይና ኦሮሞ ልሂቃን በአብዛኛው ከሀገራዊ አንድነት (ኢትዮጵያዊነት) ይልቅ በዘወግ ብሔርተኝነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት የሚያራምዱ ናቸው። በተቃራኒው አብዛኛው የአማራ ልሂቃን በአብዛኛው ከዘወግ ብሔርተኝነት ይልቅ በሀገራዊ አንድነት (ኢትዮጵያዊነት) እሳቤ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት ነበራቸው።

ይህ በተቃዋሚ ጎራ ብቻ ሳይሆን ሦስቱን ክልሎች በሚወክሉት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ላይ ጭምር ልዩነቱ በግልፅ ይታያል። ለምሳሌ ቀንደኛ የሚባሉት የህወሓትና ኦህዴድ አመራሮች የዘወግ ብሔርተኝነት አራማኞች መሆናቸው ይታወቃል። በአንፃሩ አብዛኞቹ የብአዴን ነባር አመራሮች የቀድሞ የኢህአፓ አባላት የነበሩ ሲሆን በአብዛኛው የአንድነት አቀንቃኞች ነበሩ። ከዚህ በተረፈ፣ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የዘውግ ብሔርተኝነት የሚያራምዱ የብአዴን አመራሮች ፀረ-አማራ የሆነውን የህወሓት አስተምህሮት የሚያቀነቅኑ ነበሩ።

ምንም እንኳን የሚያራምዱት የፖለቲካ አቋምና አመለካከት አንድ ዓይነት ቢሆንም ከፖለቲካና ኢኮኖሚ አንፃር መሰረታዊ ልዩነት አላቸው። የትግራይ ልሂቃን በሀገሪቱ የፖለቲካ ስልጣንና ኢኮኖሚ ላይ የበላይነት ነበራቸው። በአንፃሩ የኦሮሞ ልሂቃን ያላቸው የፖለቲካ ስልጣን የህወሓት መጠቀሚያ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ አልነበረውም። በመሆኑም የኦሮሞ ልሂቃን ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንፃር የነበራቸው ሚና በጣም ውስን ነበር። የአማራ ልሂቃን በፖለቲካና ኢኮኖሚው ረገድ የክልሉን ሕዝብ መብትና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር የነበራቸው አቅምና ስልጣን ልክ እንደ ኦሮሞ ልሂቃን ውስንና አነስተኛ ነበር።

በመንግስታዊ ስርዓቱ ውስጥና ውጪ የነበሩት የኦሮሞና አማራ ልሂቃን የትግራይ ልሂቃንን የበላይነትና ተጠቃሚነት ለማስወገድ የሚያስችል ፖለቲካዊ አቅም አልነበራቸውም። የኦሮሞ ልሂቃን ከትግራይ ልሂቃን ጋር ተመሳሳይ የሆነ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት የነበራቸው ቢሆንም የህወሓቶች መጠቀሚያ ከመሆን አልዘለሉም። የአማራ ልሂቃን ከህወሓቶች የተለየ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት የነበራቸው ቢሆንም የአማራን ሕዝብ መብትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አልቻሉም።

ህወሓት የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት ለማስቀጠል የሚከተለው ስልት፤ የአማራ ልሂቃንን አቋምና አመለካከት በትምክህት፣ የኦሮሞ ልሂቃንን ደግሞ በጠባብነት በመፈረጅ በኃይል ማፈን ነበር። ተቃዋሚዎች ከሆኑ ደግሞ ትምክህትና ጠባብነት የሚሉት ወደ ግንቦት7 እና ኦነግ አባልነት ቀይሮ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ይከስሳል፣ ያስራል፣¸ያሰቃያል።

በመሰረቱ “ጠባብ ብሔርተኛ” (ጠባብነት) – “ለጎሳው ብቻ የሚያስብና የሚያደላ፣ በሌላው ላይ ጥላቻ የሚያሳይ” ማለት ነው። “ትምክህት” (ትምክህተኛ) – “ከመጠን በላይ በራስ መመካት፥ መተማመን፣ ራስን ከፍ አድርጎ የሚያይ” ማለት ነው። በዚህ መሰረት፣ “ጠባብ ብሔርተኛ” ከሌሎች ብሔሮች ይልቅ የራሱን ብሔር ወይም ጎሳ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስቀድም ሲሆን “ትምክህተኛ” ደግሞ የራሱን ጥቅምና ፍላጎት በሌሎች ላይ ለመጫን የሚሞክር ነው።

ህወሓት በብሔርተኝነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት እንዳለው ይታወቃል። ሆኖም ግን፣ ባለፉት 25 አመታት በተግባር እንደተመለከትነው ይህ የፖለቲካ ቡድን በአንድነት ሆነ በብሔርተኝነት ጎራ ከተሰለፉ ሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ጋር አብሮ የመስራት ፍላጎት ሆነ ዓላማ የለውም። ይህ የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት ህወሓት ብሔርተኛ ብቻ ሳይሆን ትምክህተኛ ጭምር ስለሆነ ነው።

እንደ “ጠባብ ብሔርተኛ” ህወሓት ከሌሎች ብሔሮች ይልቅ የራሱን ብሔር ጥቅምና ፍላጎት ያስቀድማል፣ እንደ “ትምክህተኛ” ደግሞ የራሱን ጥቅምና ፍላጎት በሌሎች ብሔሮችና የፖለቲካ ቡድኖች ላይ ይጭናል። ስለዚህ ህወሓት “ጠባብ ብሔርተኝነት” የሚለውን አፍራሽ አገላለፅ የሚጠቀመው በዋናነት የኦሮሞ ልሂቃን የሚያነሷቸውን የመብትና ተጠቃሚነት ጥያቄዎች በኃይል ለማዳፈን ነው። በተመሳሳይ “የትምህክት አንድነት” የሚለውን የሚጠቀመው ደግሞ በዋናነት የአማራ ልሂቃን የሚያነሷቸውን የመብትና ተጠቃሚነት ጥያቄዎች በጉልበት ለማፈን ነው።

በዚህ መልኩ ህወሓት በአማራና ኦሮሞ ልሂቃን ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ የሚከተለውን ለውጥ አስከትሏል፡- አንደኛ፡- የአማራ ልሂቃን የፖለቲካ አቋምና አመለካከት ከአንድነት ወደ ብሔርተኝነት እንዲሸጋገር፣ ሁለተኛ፡- የኦሮሞ ልሂቃን የፖለቲካ አቋምና አመለካከት ከብሔርተኝነት ወደ አንድነት እንዲሸጋገር፣ ሦስተኛ፡- በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥ የኦሮሞና አማራ ልሂቃን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ጥምረት እንደሚመሰርቱ ያስችላል። ይህን የለውጥ ሂደት በ2008 ዓ.ም ባወጣሁት ፅሁፍ ላይ እንደሚከተው ገለጬ ነበር፡-

 1. “ትምክህተኛ” የሚለው እሳቤ የአማራ ብሔር ተወላጆችን በባህላቸውና በታሪካቸው ላይ ያላቸውን የራስ መተማመን ስሜት የሚሸረሽር ነው። በዚህ መልኩ የሚደረገው ተፅዕኖ በአማራ ልሂቃን ላይ የማንነት ቀውስ (identity crisis) ይፈጥራል። አንድ ሰው በአማራነቱ ብቻ “ትምክህተኛ” እየተባለ ታሪኩና ማንነቱ እንደ ጥፋት ሲቆጠር በውስጡ የብሔርተኝነት ስሜት ያቆጠቁጣል። በመሆኑም አማራን “የትምክህት አንድነት” በሚል እንደ ብሔር የሚገባውን ጥቅምና ኃላፊነት ተነፍጎ ስለነበር፣ የፖለቲካ አሰላለፉን በሂደት ከአንድነት ወደ ብሔርተኝነት እየቀየረ መጥቷል።
 2. በተመሣሣይ፣ “ጠባብ ብሔርተኛ” የሚለው እሳቤ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ ያለውን ድርሻ የሚያንኳስስ፤ በሀገሪቱ አንድነት ላይ ያለውን ሚና ከምሶሶነት ወደ ቅርጫፍነት የሚያሳንስ ነው። በሀገሪቱ የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ የሚገባውን መጠየቁ እንደ ጥፋት ተቆጥሮ “በጠባብነት” ሲፈረጅ በኃይል ሚዛኑን ውስጥ የሚገባውን ድርሻ ለመያዝ በራሱ መንቀሳቀስ ይጀምራል። በመሆኑም ኦሮሞን “ጠባብ ብሔርተኛ” በሚል በሀገሪቱ አንድነት ውስጥ የሚገባውን ጥቅምና ኃላፊነት ተነፍጎ ስለነበር፣ የፖለቲካ አሰላለፉን በሂደት ከብሔርተኝነት ወደ አንድነት እየቀየረ መጥቷል።
 3. የሁለቱ ሕዝቦች ጥያቄ በዚህ የሽግግር ሂደት መሰረት ከሁለት ተቃራኒ ጫፎች ወደ መሃል በመምጣት ያልተጠበቀ ጥምረት ተፈጥሯል። ይህ አንደ ቀድሞው በሁለት ተቃራኒ ፅንፈኞች መካከል የተፈጠረ ጥምረት አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ ሁለቱም ሕዝቦች በማንነታቸውና በሆኑት ልክ የሚገባቸውን ጥቅምና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴው የተፈጠረ የጋራ ጥምረት ነው። በመሆኑም የኦሮሞና አማራ ጥምረት በእኩልነት መርህ ላይ የተመሰረተ ጥምረት ነው።

 

በአጠቃላይ የአማራና ኦሮሞ ልሂቃን በሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት ረገድ ያሳዩት ለውጥ አንደኛና ሁለተኛ ላይ በተገለፀው መሰረት የመጣ ነው። ሦስተኛ ላይ የተገለፀው የለውጥ ሂደት ደግሞ የዶ/ር አብይ አመራር ወደ ስልጣን እንዲመጣና ህወሓት የነበረውን የስልጣን የበላይነት እንዲያጣ አድርጎታል። “ይህ የለውጥ ሂደት በአማራና ኦሮሞ ልሂቃን መካከል ያለውን ግንኙነት ወደዬት ይወስደዋል? በቀጣይ የህወሓት ሚና ምን ይሆናል? እነዚህ ለውጦች የሚፈጥሩት ተፅዕኖ የሀገራችንን ፖለቲካ ወደዬት ሊወስደው ይችላል?” የሚሉትንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን በቀጣይ ፅሁፍ በዝርዝር ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ለአሁኑ ግን በኦቦ ለማ መገርሳ የተቀጣጠለው ኢትዮጵያዊነት ሆነ በአብን የተጀመረው ብሔርተኝነት የህወሓትን የበላይነት ለማስወገድ በሚደረግ ትግል የተቀየሱ የትግል ስልቶች ናቸው። ስለዚህ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መምጣት እንደ ልዩ ፖለቲካዊ ክስተት ተወስዶ ላለመግባባትና እሰጣ-ገባ መንስዔ ሊሆን አይገባም።

ነገረ ባድመ – የ ህውሀት Plan A ና Plan B (የሰሜኑ ቋያ የ ብአዴን አመራር)

ጀንራል ጻድቃን በባድመ ጦርነት ወቅት

ህወሃት ውስጥ የመሽገውና ከእኔ በላይ ብልጣብልጥ የለም የሚለው ተስፋፊው ቡድን በእነ ስዬና ፃድቃን ፕላን አርቃቂነት በኤርትራ ጉዳይ ፕላን A እና ፕላን B አዘጋጅቶ እንቅስቃሴ ላይ መክረሙ ይታወቃል።

ፕላን A –

በአልጀርሱ ስምምነት መስረት የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ተቀብሎ አሁን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያለውን በተለይም የኢኮኖሚ መገለል በዚህ በኩል ከሻዕቢያ ጋር ስምምነት በመድረስ ከህዝባችን የሚነሱትን ጥያቄዎች ማስተንፈስ የሚል ሲሆን ለዚህም ፕላኑ ተግባር ላይ ይውል ዘንድና በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ይወስን ዘንድ ከተናጠል ቅስቀሳ እስከ በህዝብ መድረኮች አጃንዳ እንድሆን ህወሃት ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልወጣው ተራራና ያልወረደው ቁልቁለት የለም። ባደረገውም ጥረት መስረት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ያለምንም ልዩነት ተቀባይነት አገኘ ህወሃትም ደስ አላት።

ነገር ግን ገና ከመጀመሪያውም ከእኔ በላይ ብልጥ የለም በሚል የሞኝ ሃሳብ የተጀመረው ውጥን ካልታስበውና በደስታ ብዛት ይፈነጥዛል ከተባለው ከትግራይ ህዝብ እስከ እራሱ የህወሃት አባላት ድረስ ትልቅ ተቃውሞ ሲገጥመው በአንድ ጀንበር ውስጥ ሃሳቡን ቀይሮና በእራሱ በህወሃት አርቃቂነት ያለምንም ልዩነት የተወስነን ሃሳብ ያላየና ያልስማ በመምስል ሽምጥጥ አድርጎ ክዶ ከትግራይ ክልል የምትስጥ ስንዝር መሬት አትኖርም በሚል መግለጫ ነው መላገጫ ነገር አወጣ። እኛም እኛስ እንተዋወቃለን ይህንን ባህሪ ለማያውቁት ስዎች ግን ይህንን ያህል ለትዝብት ሙውደቃችሁ እናንተ ባታፍሩም እኛ አፈርንላችሁ እናንተው አመጣችሁት እናተው አስወሰናችሁ እናንተው ተቃወማችሁ ይገርማል ብለን ዝም እንዳልን ይሄው ሞኝና ብልጣብልጥ ነኝ ባዩ ቡድን አሁን ደግሞ ሌላ አድስ ፕላን Bን ይዞ የኢህአዴግ አመራርን ውስጥ ለውስጥ ለማሳመን ቅስቀሳ ጀምሯል።

ፕላን B –

የኢትዮጵያ ህዝብ ስንዝር መሬት ከምትስጥበት ህይወቱን ቢያጣ ይሻለዋል፣ ስለዚህ ከኤርትራ መንግስት ጋር እኛ ባልነው መስረት የማይስማማ ከሆነ የህዝቡም፣ የሰራዊቱንም ስሜት ስናጠናው ለሉዓላዊነቱ መስዋዕትነት መከፈል የሚችል ስለሆነ በዲፕሎማሲው በኩል ሰፊ ስራ እንስራና ምክንያት በመፍጠር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጦርነት አድርገን የሻዕቢያን መንግስት በማስወገድ ለእኛም ለቀጠናውም ተስማሚ የሆነ ስርዓት እንድፈጠር እናድርግ ይህንንም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ውሳኔ ይስጥበትና ከወዲሁ ዝግጅቶች ይደረግ የሚል ነው።

ሃሃሃሃሃሃ……… ይህ ሃይል በፍፁም ከባለፉት ተሞክሮዎቹ የማይማር ስለሆነ ከእራሱ በስተቀር የሌላውን ስሜትና ስነ ልቦና ማወቅና መገምገም አይችልም አይወድምም በመሆኑም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፕላን Bን እፈፅማለሁ ማለት ለእኔ ከዕቃቃ ጨዋታ ለይቸ አላየውም። ምክንያቱም በእነዚህ ስግብግብ ዘረኛ፣ ሙስኛ ተስፋፊዎች ችግር ፈጣሪነት በተፈጠረው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መሻከር ምክንያት።

ስለሆነም አሁን ላይ ይህንን ቅዥታችሁን አቁሙና እስኪ መጀመሪያ የቤት ስራችሁን ጨርሱ። ከአጎራባች አገር ጋር ይቅርና ከጎረቤት ወንድም ክልልና ህዝብ ጋር የገባችሁትን የመሬት ወረራና በአገር አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆናችሁበትን የሙስናና የአድሎ ችግሮችን በይቅርታና በህግ አግባብ መፍትሄ እንዲሰጡ አድርጉ። በተለይ በተለይ በእናንተ ብቻም ሳይሆን በተከታዯቻችሁም እየታዬ ያለውን ትልቁን ቫይረሳችሁን ለጎረቤት ክልልም ሆነ ለጎረቤት አገር ያስቸገረውን በሽታችሁን “ከእኔ በላይ ብልጥ የለም ” የሚለውን ደዌ ወይ ታከሙት ወይም ተፀበሉ።

ካልሆነ በተለይ ከእናንተ በእጅጉ የሚበልጠውንና የምንሳሳለትን የትግራይን ሰፊ ወንድም ህዝብና መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ ልክ እንዳለፉት ጊዜያት በአገር ተወረረ የሞኝ ቅስቀሳ እሳት ውስጥ መክተት የሚቻልበት ሁኔታ ያለ አይመስልኝም። ደግሞም እርግጠኛ ነኝ አይሳካም አይደለም። ኢህአዴግ ሌላ ምድራዊ ሃይል ቢያጅባችሁም አይሆንም።

ዛሬን በዛሬ መነፀር እንጅ በትናንት መነፀር ማየት የመነፀሩ ችግር ሳይሆን የተጠቃሚውን የሁኔታ ግምገማ ችግርና ቁሞ ቀርነት ብቻ ነው የሚያሳየው።

አስር ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ይላል ደጉ የአገሬ ስው!!

መልካም ቀን!!

የሰሞኑ ዜና፡- (ከአምባሳደር እምሩ ዘለቀ)

ቁጥር ፪ ግንቦት ፪ ሺ ፲

አምባሳደር እምሩ ዘለቀ

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተሾመ እነሆ ሁለት ወር አለፈው፡ በዚህ ጊዜ ዉስጥ ጠ/ሚስትሩ ብዙ ተናግሯል፣ ብዙ ቦታ ባገር ዉስጥ ውጪም እየተዘዋወረ ተናግሯል። በተለይ የርትግራይን “የኢትዮጵያ ሕዝብ ፋና ሁኖ የበላይ ወርቃማ የተባረከ ልዮ መሪነት ስጦታ” እንዳለው መስክረዋል። ጎረቤት አገሮችንም ጂቡቲን ኬንያንና ሱዳንን ጎብኝተዋል፡ ጋዜጠኞችና አንድ አንድ ስማቸው የታወቀ እስረኞች ተፈተዋል። ሳዊዲ አረብያ ተጉዞ አል ሙዲንና አንድ ሺ እስረኞች ለማስፈታት ሞክርዋል። አልፎ ተርፎ ንጉሥ እንደሚሆን የገንዛ አናቱ ንግርት እንደሆነ ገልጽዋል። የባለስልጣኖች ሹም ሽር አደርግዋል፡ ብዙ የአስተዳደር ቀውሶችና ለዉጦች አሳዉቋል። ነገር ግን መሰረታዊ የሆኑ ለዉጦች አልተደረጉም። ለዚህም ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል ይባላል። የተሾሙትም አዲስ ሚኒስትሮች ቦታ ተዘዋወሩ እንጂ የቆዩ ባለስልጣን ናችው። አሁንም እዉነተኛዉ ተጨባጭ ሃይል በወያኔዎች እጅ እያለ ጠ/ሚሩ የሚናገረዉና የምያሳየዉ ሃገራዊ አስተያየት ከመረጡት ወገኖች ልማዳዊ አገዛዝና ትግባር በጣም የተለየና ተቃራኒ በመሆኑ ዉጤቱ ምን እንደሚሆን ያጠያይቃል።

በሃገር ዉስጥ የሚካሄደው ሕዝባዊ እምቢታና አመጽ የወያኔዎችን ስልጣን እንዳፈረስዉና እነሱም ተደናግጥዉ ለዉጥ ያመጡ ለመምሰል አዲስ ጠ/ሚር ሾመዉ ህዝቡን እያደናገሩ ስልጣናቸዉን ይዘው ለመቆየት መሞከራቸው ግልጽ ነው። ነገር ግን በሃገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ በተቃዋሚ በኩል የሚሰማዉ ድምጽና አስተያየት በጣም የበሰለና የሃገርን ሁኔታና ችግር የምያሰፈልገዉንም መፍተሄ አብራርቶ የሚያስገንዝብ ሆኖ ሳለ ተግባር ላይ ሊያዉለው የሚችል ሃገራዊ ሃይል እስካሁን አልተገኘም። ባሁኑ ወቅት በየፊናዉ የሚወጠነዉ ሰላማዊ እርቅና ድርድር ተመልሶ አዲስ የአምባገነኖች አገዛዝ እንጂ ለሃገሪቷ ሕዝብ መሰረታዊ መብትና ነጻነት ያመጣል ብዬ አላምንም።

በሰፊዉ ሕዝብ በኩል የማያጠራጥር የሃገር ፍቅር እንዳለና፡ ደምና ስቃይ እየተከፈለበት ያለ የሁኔታዉ ግንዛቤ መኖሩና ጠንካራ የለውጥ ፍላጎት እንደመነጨ ግልጽ ነው። ይሁንና ባለፉት አርባ አራት ዓመታት በተለይ በመጨረሻዎቹ ሃያ ሰባት ዓመት በሕዝቡ ላይ የዋለው የዘረኝነት ጭካኔ ሙስናና ስርቆት አስተዳደር በህብረስቡ ላይ ከባድ በሽታና መቃቃር እንደፈጠረ ግልጽ ነው። በአንድ አላማ ተስማምቶ ለመራመድ እንቅፋት የሆነው ይሄዉ ነው። ስለዚህ ባለፉት ዘመናት በእንደዚህ አይነት ግንዛቤ የወሰዱንን አስተሳሰቦች መመራመርና የማንነታችንን እዉነተኛዉን ፍንጭ ማግኘት አለብን።

አሁን እንደሚታየው የወያኔዎች የፖሊቲካ መሰረት ፈርሷል። ስልጣን ከጨበጡ ከሃያ ስምንት ዓመት ያተረፉት የመላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥላቻና ንቀት ነው። በሕዝቡ ላይ የሰሩት ግፍ፣ ግድያ፣ ጭካኔ አስከመቼም የማይረሳና ለወደፊትም የሚጠየቁበት ነው። ከወልቃይት ጠገዴ ከሰሜን ጎንደር ከአርማጮሆ፣ ከራያ አዘቦት ከወሎ፣ ከቤኒሻንጉል የተወሰድው መሬትና የተፈናቀለው ሕዝብ ከተወለደበት እና ከኖረበት ተመልሶ ሃብቱን መልሶ መያዝ አለበት። ለሱዳን የተለቀቀው የሃገር መሬት መመለስ አለበት። ሕዝቡም ለተዘረፈው ለተቀማው ሃብት ካሳ ማግኘት አለበት። የዘረፉትም የሰረቁትም ገንዘብ ተመላሽ ይሆናል። የሚገድፏችውም የዉጪ መንግሥታት ይህንን አዉቀው ሌሎች ወገኖች እያባበሉ ነው። ወገናችን ብለው የሚመኩበት ሰፊዉ የትግራይ ሕዝብ ራሱ አይከተላቸዉም። ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተገንጥሎ ለመኖር እንደማይችል ያዉቃል። ስለዚህ የወያኔዎቹ አገዛዝ አልቆለታል ለማለት ይቻላል። አጥብቆ ማሰብ ያለብን ወደፊት ስለሚሆነው ነው።

በአሁን ወቅት ተዘርግቶ በምናየው የፖሊቲካ ሰንጠረጅ ላይ ተሰልፈዉ የሚገኙት ዋና ቡድኖች የኦሮሞ ድርጅቶችና የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሾሙት አዲሱ ጠ/ሚ ናቸዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከአንድ ሲሶ (ከሰላሳ ሚልዮን) ይበልጥ የሆነው የአማራው ሕዝብ ስሙ እንኳ አይነሳም። እንድያዉም በአማራው ላይ የሚካሄደው የግፍ ዘመቻ እየባሰና ጦር እየዘመተበት እየተገደለና እየተሰቃየ፣ ከተወለደበትና ከኖረበት ከየቦታዉ እየተፈናቀለ፣ እየተሰደደ፣ ሃብቱን እየተቀማ ነው።

ይህ የሆነበት ምክንያት አማራው በራሱ ላይ በፈጠረው ደካማነትና መተማነን ማጣትና ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለመጪዉ ትውልድ ያለበትን ታሪካዊ ግዴታና ሃላፊነት ባለማክበርና በመሸሹ ነው። አለዝያ ከሰላሳ ሚልዮን በላይ የሚሆን የአማራ ሕዝብ በአንድ የወመኔ ሽፍቶች ሰብአዊ መብቱ ተገፎ፣ እንደ እንሰሳ የሚነዳበት ምክንያት አይኖርም ነበር። ያሳፍራል፣ ያሳዝናል!! ከአምስት ዓመት በፊት አማራዉ መደረጃት አለበት ብዬ ሳስታዉቅ ይህንኑ በማሰብ ነበር።

ያለፈው አልፏል። ከአሁን ወዲህ የአማራዉ ሕዝብ ራሱንና አገሩን ኢትዮጵያን ከጥፋት ለማዳን ታጥቆ በአንድነት የመጣዉን አደጋ መመከት አለበት። አማራጭ የሌለው ሁኔታ ነው። በአገር ቤት ያለው ሕዝብ ይህንን ተረድቷል። እንቅፋት የሆኑት የፖሊቲካ ድርጅቶችና ነጋዴዎች ናቸው። ፍሬቢስ የሆነ ገበያቸዉን ትተው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንዲሰለፉ እጠይቃለሁ።

የአማራው ሕዝብ በተለይ ወጣቱ ትውልድ “የነገው ሰው” የሆነው አሁን የሚካሄደው የፖሊቲካ ድርድር በእርሱ ዕድል ላይ መሆኑን አጥብቆ መገንዘብ አለበት። ደጉንም ክፉንም የሚሸከመው እርሱ ነው። በቅርቡ ካለፈው የወረስው መለያየት ዘረኝነትና ጥላቻ ስለሆነ ይህኑን አዉቆ ጥሎ፣ በአዲስ ጤናማ መንፈስንና እዉቀት ኢትዮጵያን መገንባት አለበት።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
እዘ፡

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ

I. መግብያ፡-
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 3-5 ያካሄደዉን ኣስቸኳይ ሰብሰባ ኣጠናቋል። ህወሓት/ኢህወዴግ በ17 ዓመቱ የትጥቅ ትዓልም ሆነ ሩብ ክፍለ ዘመን ባለቆጠረው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ትግል ምዕራፎች ሁሉ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረግነው ትግል በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፈን እዚህ ላይ መድረስ ችለናል። የ43 ዓመታት የድልና የፅናት ጉዞአችን ስኬት ምንጭ የጠራና ብቁ አብዮታዊ መስመር ይዞን የዘለቅን መሆኑ ነው። ይኸንን መስመር በፅናት ጨብጦ በፅናት ታግሎ የሚያታግል ድርጅት ባለቤት ስለሆንን ነው። ባለፉት 27 ዓመታት ባጠቃላይ፣ ባለፉት የ17 የተሐድሶ ዓመታት ደግሞ በተለይ ዙርያ መለስ መሰረታዊ ለውጥ መስመዝገብ ችለናል። ሃገራችን ኢትዮዽያ የነበረችበት እጅግ ኣስፈሪ የመበታተንና የማሽቆልቆል ጉዞ ተገቶ ወደ ኣዲስ ምዕራፍ እንድትሸጋገርና ስሚና ክብር ከፍ ብሎ እንዲጠራ ኢህኣዲግ እልህ አስጨራሸ ትግል ኣካሂዷል። በተደረገዉ ትግል የሃገራችን ህዝቦች የመልማት እኩል ዕድል ያረጋገጠ ስርዓት ተገንብቶ ህዝቦችን በኢኮኖሚና በማሕበራዊ ረገድ ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ዉጤት ለማረጋገጥ ተችሏል። በእርግጥም አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን ሃገራችንን ከጥፋት የታደገ፣ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠበት አዲሲቷ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮዽያ እንድትፈጠር ያደረገና ለወዲፊትም የሃገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ መሆኑ የአስከኣሁኑ ትግላችን ያረጋገጠው እውነት ነው።
ይኸ ተኣምር የፈጠረና የሃገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ የሚያስችል ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኣደጋ ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ እንዲፈጠር ከምንም በላይ የመሪ ድርጅታችን ኢህኣዴግ አመራር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ባህርይው እየተሸረሸረ በከፋ የጥገኛ ዝቅተት ኣረንቋ ውስጥ በመዘፈቁ መሆኑን ድርጅታችን ኢህአዴግ በሚገባ የተነተነዉ ጉዳይ ነዉ። ይሁን እንጂ ይኸንን ፈተና በሚገባ ለማለፍ ሲባል በድርጅታችን የተጀመረዉ በጥልቅ የመታደስ እንቅስቓሴ ኣሁንም ቢሆን በሚፈለገዉ ደረጃ ሊሳካ ኣልቻለም።
ይህንን መነሻ በማድረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በወሰናቸዉ ዉሳኔዎች በሃገራችንና ክልላችን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ የትግል አቅጣዎቻችን ላይ በዝርዝር በመውያየት ውሳኔዎች አስልፏል።
II. ውሳነዎች
ሀ. የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ግንቦት 28/2010 ዓ.ም ባካሄደዉ አስቸኳይ ሰብሰባ የኢትዮ-ኤርትራን ግጭት በሰለማዊ መንገድ ለመፍታትና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን አስመልክቶ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ የቀረበለት ሪፖርት በዝርዝር በማየት የሚቀጥሉትን ውሳኔዎች አሰልፏል።
1. ከምንም ነገር አስቀድሞ የኢህአዴግ ስራ ኣስፈፃሚ ሊያየው ይገባ የነበረዉ ጉዳይ የኢህአዴግ ምክርቤት በመጋቢት /2010 ዓ.ም ያስቀመጠዉን ወሳኔና ግምገማ መሰረት በማድረግ በድርጅታችን በግልጥ እየታየ የመጠዉን መሰረታዊ የአመራር ብልሽትና ያስከተለዉን ጉዳት፣ እንዲሁም ባለፈዉ የተጀመረዉ የጥልቀት መታደስ የደረሰበት ደረጃን በጥልቀት በመገምገም በሃገራችን ዋነኛ ችግር ላይ ትኩረት ኣድርጎ ማየት አለመቻሉ አንድ መሰረታዊ ጉድለት ነው።
2. የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ማየት የነበረበት ሌላ መሰረታዊ ጉዳይ አሁን ገጥሞን ላለው መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ ላይ ትኩረት ኣድርጎ መውያየት መሆን ሲገባዉ የችግሩ ባስከተላቸው ውጤቶችና ለጊዚያዊ መፍትሔዎች ቅድሚያ መስጠቱ አንድ ሌላ ጉድለት እንደ ሆነና፣ ዘለቂው መፍትሔ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመራችን በግልፅ የለያቸውን የልማት አቅምቻችን ማለትም መላው ህዝባችን፣ መንግስትና የግል ባለሃብቱን በማደራጀት ርብርብ እንዲያደርጉ መቻል ላይ ያለብን ችግር ላይ ትኩረት ስጥቶ መውያየት ኣልቻለም።
3. እነዚህ እላይ የጠቀስናቸው ጉድላቶች እንደ ተጠበቁ ሆነው ስራ ኣስፈፃሚው የኢትዮዽያና የኤርትራን ጉዳይ ኣስመልክቶ የወሰነው ውሳኔ በመሰረቱ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ በኢህአዴግ የሚመራዉ መንግስት ለኣፍሪካ ቀንድ ሰላም በጠቃላይ ለሁለቱ ሃገራት ወንድማሞች ህዝቦች በተለይ ሲባል ስምምነቱን ያለቅድመ ሁኔታ በመቀበል ህዝባችንና መላዉ ኣበላችንን በማወያየትና በማሳመን እንድሁም ዓለም ኣቀፉን ማሕበረሰብ ከጎኑ በማሳለፍ ለተግባራዊነቱ ያላሰለሰ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት 18 ዓመታት ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ አልተቻለም። ስለሆነም የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሳለፈዉ ዉሳኔ በመሰረቱ ከሰላም ፖሊስያችን ጋር የተጣጣመ መሆኑን በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ዉሳኔ መተላለፉ ተገቢና ዉቅታዊ መሆኑን የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ደምድሟል።
ኣፈፃፀሙን በሚመለከት ግን ሃገራችን ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ጋር ከሏት የአዋሳኝ ድንበር ጉዳዮች አንፃር ጭምር እጅግ ከፍ ያለ ትርጉም ያለዉ በመሆኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባዉ አፅንኦት ሰጥቶ ተውያይቷል። ከዚህ ጋር በተያየዘ በኢትዮ-ኤርትራ አዋሳኝ አከባቢዎች የሚኖረዉ ህዝብና ሚሊሻ ላለፉት 20 ዓመታት ከኑሮኣቸዉና ከሥራቸው ተፈነቅለዉ የሃገራችንን ልዓላዊነትና ህገ-መንግስታችን ለማሰከበር ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም ለሳዩት ቆረጥነትና ከከፈሉት የማይታመን መስዋዕትነት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ያለዉን ክብርና ኣድናቆት እየገለፀ ድርጅታችን ኢህአዴግና ከፌደራል መንግስት ጋር በመሆን በቂ ድጋፍ ሊያገኙ እንዲሚገባ ወስኗል።
4. የኢህኣዴግ ስራ ኣሰፈፃሚ ኮሚቴ አሁን የገጠመንን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል ከመንግስት የልማት ድርጅቶችን መካከል ቴሌ፣ ኤለክትሪክ ማመንጨዎች፣ ሎጀስቲክስና የኢትዮዽያ ኣየር መንገድ ከፍተኛዉ ድርሻ በመያዝ የግል ባለሃበቶችን ለማሳተፍ እንዲሁም የቀሩትን የልማት ድርጅቶች በከፊል ወይም በሙሉ ወደ ግል ይዞታ ለማስተላለፍ የወሰነዉ ውሳኔ ከፕሮግራማችንና ፖሊስዎቻችን ጋር የማይጋጭ፣ ባለፉት ጉባኤዎቻችን እየተወሰነ የመጣና ወቅታዊ መሆኑን በማረጋገጥ ተቀብሎታል። ይሁን እንጂ ኣፈፃፀሙ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲዳረግና ልማታዊ ዴሞከራሲያዊ መስመራችንንም ሆነ የኢትዮዽያ ህዝቦችን ጥቅም በማይጎዳ መልኩ መከናወን እንዳለበት አፅንኦት ሰጥቶበታል።
5. በኢትዮ-ኤርትራ ዘላቂ ሰላም ጉዳይም ሆነ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር በተያየዘ የተወሰኑ ውሳኔዎች ወደ ኢህአዴግ ምክርቤት ሳይቀርቡ፣ አጋር ድርጅቶች ሳይሳተፉበት እና የሚመልከታቸው አካላት በዝርዝር ሳይወያይበት እንደመጨረሻ ውሳኔ ተወስዶ ለህዝብ ይፋ መደረጉ አንድ ጉድለት እንደሆነ ማእከላዊ ኮሚቴዉ ደምድሟል።
6. የኢትዮዽያ በሔር፣ በሄረሰቦችና ህዝቦች ከዳር እስከዳር በከፍተኛ ሃገር ፍቅር የተሳተፉበት እና መስዋእት የከፈሉበት ጉዳይ በዝርዝር ሳይወያዩበት እና በቂ መተማመን ሳይደረስበት በሚድያ ይፋ መግለጫ መሰጠቱ ህዝባችን ላይ ቅሬታ፣ ቁጣና መደነጋገር የፈጠረ በመሆኑ አንድ ሌላ ጉድለት ነው።
ለ. የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በጥልቀት ከተወያየባቸው ጉዳዮች አንዱ አሁን ያለንበት ክልላዊ እና ሃገራዊ ሁኔታ እንዲሁም ቀጣይ የትግል አቅጫጫዎች የሚሚለከት ነው። በኢህኣዴግ ደረጃም ሆነ በህወሓት ካለፉት አመታት ጀምሮ ልማታዊ መስመራችን እና በህገመንግስታችን ላይ ያጋጠመ ያለዉን ችግር ሲገምግም ቆይቷል። ይሁን እንጂ የችግሮቹ ስፋትና ትርጉም በኢህአዴግ ደረጃ በጥልቀት መገምገም እንዳለበት በመግባባት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።
1. የኢህአዴግ ምክርቤት በመጋቢት 2010 ባስቀመጣቸው ውሳኔዎች ድርጅታችንን ከአደጋ ለማዳን እንዲቻል የለየናቸው ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው በጥብቅ ድስፕሊን እና ተጠያቅነት እንዲተገበሩት ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጧል። በዚ ረገድ በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴው የደረሰበት ደረጃ በኢህአዴግ እንዲገምገም የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ይጠይቃል።
2. በዴሞክራሲ ሓይሎች እና በጥገኝነት መካከል የሚደረገው ቀጣዩ የትግል ምእራፍ በዋናነት በዴሞክራሲ እና በልማት ዙርያ በሚለኮስ ንቅናቄ ማሕበራዊ መሰረታችን እና ከልማታችን ተጠቃሚ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሚያደርጉት የተደራጃ ትግል ነው። ይህን ለማድረግ እንዲቻል መላው ህዝባችን እና አባላችን የምንገኝበትን መድረክ ባህሪ መነሻ በማድረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በሃገር ደረጃ በሚደረገው ሁሉንአቀፍ ትግል በቁርጠኝነት እንዲረባረብ ወስኗል።
3. በአሁኑ ወቅት በኢህአዴግ ደረጃ እየተደረጉ ያሉ የኢህአዴግን ህገ-ደንብ እና ተቋማዊ አስራር ያልተከተሉ የአመራር ምዳባዎች እንዲታረሙ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ይጠይቃል።
4. ለደርጅታችን ነባር አመራሮች እውቅና እንዲሰጥ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ወስኗል።
5. በሃገራችን ህገ መንግስት በሚገባ መልስ የሰጠባቸው የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎችን ፈደራላዊ ስርዓታችን በመፃረር እና የህዝባችን ክብር በሚነካ መልኩ በሓይል እና በተፅእኖ የትግራይ እና ህዝብ አድነት እና ሰላም ለመረበሽ የተደረጉ ያሉት ፀረ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሶች ህወሓት ከህዝቡ ጋር በመሆን በፅናት ለመታገል ወስኗል።
6. የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት እንደለፈው ግዜ ሁሉ የአብያታዊ ዴሞከራሲያዊ መስመራችን አስተማማኝ ደጀን በመሆን ትግላችንን የሚጠናክር እና እንደ ካሁን ቀደሙ በመሰመራችን ዙርያ ጠንካራ ርብርብ እንዲደረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ወስኗል።
7. ከህዝባችን ጋር ባለፉት ጥቅት ወራት ባካሄድናቸው መድረኮች በርካታ ችግሮች እንዳሉ ተገንዝበናል። ድርጅታችን የነዚህ ችግሮች መነሻ እንዲሁም የመፍትሔ ኣቅጫጫ በግልፅ ኣስቀምጦ በተግባር ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሌትተቀን ርብርብ ለማድረግ ወስኗል።
8. ህዝባችን መሪ ድርጅቱ እንዲታደስ በተለያዩ መድረኮች ያደረገዉ ተሳትፎ እና ትግል ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ባህሪውን ጠብቆ እንዲሄድ ላረገው አስተዋፅኦ ማእከላዊ ኮሚቴው አድናቆቱን እየገለፀ፤ በቀጣይም ቢሆን ትግሉን በተደራጀ መልኩ እንዲ ቀጥል ጥሪውን ያቀርባል። በዚህ አጋጣሚ ሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ ተከትለው ኣማራጭ ሃሳብ ከሚያራምዱ ሓይሎች ጋር ኣብሮ ለመስራት ያለው ዝግጅነት መግለፅ ይወዳል። ይሁን እንጂ ህወሓት እና የትግራይን ህዝብ ለማዳከም እና ለመምታት በተለያዩ መንገዶች ፀረ ትግራይ ህዝብ እና ፀረ ህወሓት እንቅስቃሴ የሚያድርጉ የውስጥም የውጭም ሓይሎች ህዝቡ ኣምሮ እንዲታግላቸው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል።
9. ወቅታዊ ሁኔታዉን በፍጥነት ለማየት እና ለመገምገም የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ እና ምክርቤት አስቸኳይ ሰብሰባ እንዲጠራ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ይጠይቃል።

ህገ መንግስታችና ህገ መንግስታዊ ስርአታችን ለማጠናከር እንረባረብ!!
ዘለአለማዊ ክብርና ሞጎስ ለትጉሉ ሰማእታት!!
የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ
ሰነ 06/2010 ዓ.ም
መቐለ፤

የሽግግር መንግስት አስፈላጊነት (ሰማሃኝ ጋሹ)

ሰማሃኝ ጋሹ (ዶ/ር)

Abiy Ahmed Ali is an Ethiopian politician. He is the 12th Prime Minister of Ethiopia.

አሁን በኢትዮጵያ እየተካሄደ በሚገኘዉ የለዉጥ ሂደት በተቃዋሚዉ ሃይል በኩል ሊወሰዱ ስለሚገባቸዉ እርምጃዎች የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ። በአንድ በኩል ዶ/ር አብይ እየወሰዳቸዉ የሚገኙት እርምጃዎች አበረታች በመሆናቸዉ እሱን እየደገፍን የተሻለ ለዉጦች እንዲደረጉ ግፊት እናድርግ የሚል ነዉ። የእነዚህ ወገኖች መከራከርያ በኢትዮጵያ ያሉት የፖለቲካ ሃይሎች ያላቸዉ የፖለቲካ ፕሮግራም የተለያየ በመሆኑ የሽግግር መንግስት ይመስረት ቢባል አብረዉ መስራት አይችሉም የሚል ነዉ። በሌላ በኩል አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ታዋቂ የሰበአዊ መብት ታጋዮች የሽግግር ፥ የጥምር ወይም ባለ አደራ መንግስት መመስረት አለበት የሚል አቋማቸዉን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህም መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፥ መድረክና በቅርቡ የተመሰረተዉ የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ንቅናቄ ይገኙበታል። ለዚህም ዋናው መከራከርያቸዉ ላለፉት 27 አመታት ስልጣን ላይ የቆየዉ መንግስት በራሱ መንገድ የሚያደርጋቸዉ የለዉጥ እርምጃዎች አስተማማኝና ዘላቂነት ሊኖራቸዉ ስለማይችል ዋና ዋና የፖለቲካ ሃይሎች የተሳተፉበት የለዉጥ ሂደት ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት የሚያግዝና ለዉጡንም ዘላቂና አስተማማኝ ያደርገዋል በሚል ነዉ። እኔም የሽግግር መንግስት ማቋቋም ያስፈልጋል ከሚሉት ወገን ስሆን መከራከርያየንም እንደሚከተለዉ አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ ላለፉት 45 አመታት አስቸጋሪ በሆነ የፖለቲካ ቀዉስ ዉስጥ አልፋለች። በተማሪዎች እንቅስቃሴ የተጀመረዉ ‘ የብሄር ጭቆና’ ትርክት በርካታ ብሄር ተኮር የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲመሰረቱ ምክንያት ሆኑዋል። በተለይ ህወሃት የተከተለዉ የአማራዉን ብሄር እንደ ጨቋኝና ጠላት አድርጎ ያቀረበበት መንገድ አሁን ላለዉ የፌዴራል ስርአት ምስረታ እንደ ዋነኛ ግብአት አገልግሎአል። አማራዉ ጨቋኝ ሌሎች ተጨቋኝ ተደርገዉ የቀረቡበት መንገድ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ብሄሩ በጥርጣሬ እንዲታይና በሌሎች ክልሎች እንደ አገሩ በነፃነት እንዳይኖር የተደረገበትን ሁኔታን ፈጥሮአል። ህወሃት በ 1983 ዓም ባደረገዉ የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደትም ሆነ ቀጥሎ በመጣዉ ህገ መንግስት የማርቀቅና ማይደቅ ሂደት ህብረ ብሄራዊ የፖለቲካ ሃይሎች እንዳይካፈሉ የተከለከሉ ሲሆን ሁሉም ብሄሮች በተለያየ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲወከሉ አማራዉ ግን በሂደቱ እንዳይወከል ተደርጓል።

ይህ ህገ መንግስትም ሆነ እሱን መሰረት አድርገዉ የተቋቋሙት የፖለቲካ ተቋማትና ክልሎች በህብረ ብሄራዊነትንና በግለሰብ መብት ላይ የሚያምነዉን ማህበረሰብና የአማራዉን ህዝብ ጥቅም የጎዳ ነው። እነዚህ የህብረተስብ ክፍሎች ሳይወከሉ የፀደቀዉን ህገ መንግስት ብትወዱም ባትወዱም ተቀብላችሁ ቀጥሉ የሚል ለዴሞክራሲ እታገላለሁ የሚል የፖለቲካ ሃይል መኖሩ አሳሳቢ ጉዳይ ነዉ። አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች የሽግግር መንግስት ተመስርቶ መሰረታዊ የህገ መንግስት ለዉጥ እንዳይደረግ የሚፈገልጉት የብሄር የፖለቲካ ሃይሎች ብቻቸዉን የመሰረቱት ስርአት የብሄሬን መብት ከጠበኩት በላይ ያስከበረልኝ ስለሆነ እንዲነካብኝ አልፈልግም ከሚል የመነጨ ነዉ። እነዚህ የፖለቲካ ሃይሎች መረዳት ያለባቸዉ በጣም ከፍተኛ የህበረተስብ ክፍልን በማግለል የተመሰረተ ስርአት ዘለቅታዊ ሰላምና መረጋጋትን የማያመጣና ዉሎ አድሮ አገሪቱን ቀዉስ ዉስጥ የሚከት መሆኑን ነዉ። የአገሪቱን አጣብቂኝ የፖለቲካ ሁኔታ ለመቀየር አንዱና ወነኛዉ መንገድ በዚህ ስርአት ምስረታና ሂደት የተገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሂደቱ በማሳተፍ ነዉ። ስለዚህ ከላይ የተገለፁትን የህብረተሰብ ክፍሎች መሰረታዊ መብቶች ለማስጠበቅ አሁን ያለዉን ህገ መንግስትን የማሻሻል ወይም የመለወጥ እርምጃ የግድ አስፈላጊ ነዉ። ይህንን አይነት መሰረታዊ ለዉጥ ለማካሄድ ደግሞ የግድ ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎችን ያሳተፈ ውይይትና ድርግር መደረጉ የግድ ስለሚል የሽግግር መንግስት ምስረታ አስፈላጊነትን ያጎላዋል።

እንደዚሁም የህገ መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን፥ የህገ መንግስት ጉባኤ አባላት የተመረጡበት መንገድና ህገ መንግስቱ የፀደቀበት መንገድ የተጭበረበረና ህዝብን ያላሳተፈ ነበር። የአንድን ህገ መንግስታዊ ስርአት ቅቡልነት የሚወስነዉ ዋነኛዉ መርህ ህዝብን ያሳተፈ መሆኑና የፀደቀበትም መንገድ ህጋው ሲሆን ነዉ። አሁን ያለዉ ህገ መንግስት ህዝቡን ያሳተፈ እንዳልነበር በመግለፅ የህገ መንግስቱ ጉባኤ ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ህዝቡን ይቅርታ መጠየቃቸዉ አይዘነጋም። ይህንን በህገ ወጥ መልኩ የፀደቀ ህገ መንግስት ተቀብላችሁ ለሚቀጥለዉ ምርጫ ተዘጋጁ ማለት ቀልድ ነዉ። ስለዚህ ህገ መንግስቱን በማርቀቅና ማፅደቅ ሂደት ህዝቡ የሚሳተፍበትና በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ህገ መንግስት እንዲኖር ሁሉንም የፖለቲካ ሃይሎች ያሳተፈ የሽግግር ሂደት መኖሩን ግድ ይላል።

የቀዝቃዛዉ ጦርነት በማብቃቱ ምክንያት ህወሃት ለይስሙላ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን የተቀበለ ቢሆንም በመሰረታዊ ደረጃ ይህ ህገ መንግስት የህወሃት የፖለቲካ ፕሮግራም ቅጂ ነዉ። በዚህም ምክንያት ህወሃት አገሪቱን ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸዉ የተጠቀመበት ሲሆን በዚህም የተነሳ ለረጅም ዘመን ተሳስበዉና ተዋደዉ ይኖሩ የነበር የህብረተሰብ ክፍሎች የጎሪጥ እንዲተያዩ በማድረግ የብሄር ግጭት እንዲባባስና የገሪቱንም አንድነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አድርጓል። በዚህም የተነሳ በፖለቲካ ሃይሎች መካከል የግለሰብና የብሄረሰብ መብት ማስከበርን፥ ኢትዮጵያዊ ማንነትና የብሄረሰብ ማንነትን፥ የክልሎች አወቃቀርን ፥ የብሄረሰብ ማንነት በፖለቲካ ተስትፎ ዉስጥ ያለዉን ሚናን አስመልክቶ ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሮአል። እነዚህን ወሳኝ የፖለቲካ ጉዳዮች ተነጋግሮ እልባት መስጠት ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም። ለዚህም ነዉ የሽግግር መንግስት መመስረቱ በአገሪቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት ከፍተኛ እድል የሚሰጠዉ።

ሌላዉ የሽግግር መንግስት ማቋቋም አስፈላጊ የሚሆነዉ ስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት የሚያደርገዉ ለውጥ በአመዛኙ ጥገናዊ ለዉጥ በመሆኑ ነዉ። እስካሁን በዶ/ር አብይ የሚመራዉ ቡድን ያደረጋቸዉ ለዉጦች ላለፉት 3 አመታት ከነበርንበት ቀዉስ እንድናገግም የረዳና አንፃራዊ መረጋጋትን ያመጣ ነዉ። በጠ/ሚኒስትሩ የሚወስዱት እርምጃዎች አበረታች ቢሆኑም ጥልቀት ያለዉ ለዉጥ ያመጣሉ ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ዶ/ር አብይ አስቀድመው የለዉጥ ፍኖተ ካርታቸዉን ያላሳወቁ በመሆኑ አገዛዙ ስር ነቀል ለሆነ ለዉጥ መዘጋጀቱን የሚሳይ ማስረጃ የለም። አገዛዙ ስር ነቀል ለዉጥ አመጣለሁ ቢል ስልጣን ላይ የመቆየት እድሉን ስለሚያመነምነዉ ስር ነቀል ለዉጥን በራሱ ተነሳሽነት ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም። ይህ ስር ነቀል ለዉጥ ህገ መንግስቱን የማሻሻል፥ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንቅፋት የሆኑትን እንደ አብዮያዊ ዴሞክራሲና ልማታዊ መንግስት የሚባሉትን የአገዛዙን ዋና ዋና ርዮታለማዊ መሰረቶች የመለወጥን፥ ላለፉት 27 አምታት የተፈፀሙትን ወንጀሎችና ዝርፊያዎች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩ ማድረግን የመሳሰሉትን ስለሚያጠቃልል አገዛዙ ስር ነቀል ለዉጥን በራሱ ፈቃድ ያደርጋል ተብሎ አይታሰብም። ለዚህም ነዉ እውነተኛና መሰረታዊ ለዉጦችን ለማካሄድ የሽግግር መንግስት መመስረቱ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚኖረዉ።

ሌላዉ የሽግግር መንግስት መኖርን አስፈላጊ የሚያደርገዉ የሽግግር ፍትህ ( transitional justice) ለማካሄድ የተሻለ እድል መፍጠሩ ነዉ። አንድ በግጭትና ጭቆና ዉስጥ ያላፈች አገር በአለፈዉ ስርአት የተፈፀሙ ወንጀሎችን በማጣራት ተጠያቂዎችን ለፍርድ በማቅረብ ወይም በምህረትና ይቅርታ ያለፈዉን ታሪክ በመዝጋትና ያ ሁኔታ እንዳይደገም ቃል በመግባት አዲስ ጅማሮን ማድረግ ይኖርባታል። ይህንን መሰረታዊ ሂደት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማካሄድ የግድ ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎች በሂደቱ ሊሳተፉ ይገባል። ለዚህም የሽግግር መንግስት ምስረታ በጣም ጠቃሚ ነዉ። በአጠቃላይ ከላይ በዝረዘርኳቸዉ ዋና ዋና ምክንያቶች ስርአቱ መሰረታዊ ለዉጦችን ያደርጋል ብሎ ከመጠበቅ ይልቅ ሂደቱ ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎች የተሳተፉበት እንዲሆን የሽግግር መንግስት ምስረታ እንዲደረግ ግፊቱ መቀጠሉ አስፈላጊ ይሆናል።

በየቦታው ግጭትና ሁከት እየተካሄደ ነው (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Ethiopian government sending soldiers to the town of Welkite.

በየቦታው ግጭትና ሁከት እየተካሄደ ነው። የፍቼ ጨምበላላ በዓል ዛሬም በከፍተኛ ዘረፋና ጥቃት ምክንያት የበዓል ደባቡ ጠፍቶ ውሏል። በተለያዩ የሀዋሳ ከተማ መንደሮች መደብሮች ሲዘርፉ ውለዋል። በሰው ህይወት ላይም የሞት አደጋ መከሰቱን የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተዋል። ስርዓት አልበኝነት ሀዋሳ ላይ ሰፍኗል። ወልቂጤ ታስፈራለች። ህዝቡ ተረብሿል። ንብረት እየወደመ ነው። የሰው ህይወት ጠፍቷል። የአገዛዙ ሃይሎች የጥፋቱ አካል ሆነው ተሰማርተዋል።

ባህርዳር የአገዛዙ ታጣቂዎች ተማሪውን ሲደበድቡ መዋላቸውን በቪዲዮ ጭምር ተደግፎ በወጣ መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ልዩ ሃይል በየመንገዱ ያገኙትን ሰው በቆመጥ ሲያገላብጡ ታይተዋል። ከተማሪውና ከነዋሪው በርካታ ሰው ጉዳት ደርሶበታል። የወልቃይት ጉዳይ ሊፈነዳ የደረሰ ፈንጂ መሆኑ እርግጥ ነው። የአማራው መፈናቀል በቀጠለበት፡ ጥቃቱም ባልተቋረጠበት ሁኔታ ተቃውሞዎች ከባህርዳር ሌላ በሌሎች የአማራ አከባቢዎችም ሊከሰቱ እንደሚችሉ ምልክቶች እየታዩ ነው።

የጉጂና ጌዲዮ፡ የጉጂና አማሮ ግጭት አስከፊ መስመር ላይ ወጥቶ ቀጥሏል። ሁለቱ ወገኖች የሚዋሰኑባቸው አከባቢዎች ከግጭት ጋር መላቀቅ አልቻሉም። ዛሬም የሚፈናቀሉ ሰዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። ቤቶች ይቃጠላሉ። ሰላም የሰማይን ያህል ርቋል። አማሮ ኬሌ ዛሬም የሰው ህይወጥ የጠፋበት ግጭት እንደነበረ ሰምተናል። በጉጂና በኮሬ ወገኖች መከካል የተጀመረውና ለአንድ አመት የዘለቀው ግጭት ደም አፋሳሽ ሆኖ እንደቀጠለ ነው።

ድሬዳዋ ተወጥራለች። የብሄር ፌደረራሊዝሙ አፍኖ ሊገላት ከጫፍ ደርሷል። የከተማው ነዋሪ የሀገር ውስጥ ሰደት ብቸኛው አማራጭ ሆኖበት በአጎራባችና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች እየተሰደደ መሆኑም ታውቋል። ሀረር መረጋጋት አልቻለችም። ባለፈው ቅዳሜ የተከሰተባት ግጭት አሁንም ዳር ዳር እያለባት ነው። ከተማዋ በሀረሪና በኦሮሚያ ክልሎች ፍጥጫ እንደቆዳ ተወጥራ ልትቀደድ ከአፋፉ ተጠግታለች።

ሶማሌ ክልል በ11ዱም ዞኖች ለአንድ ወር ሲካሄድ የዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ በተለይ በሽንሌ ዞን ቀጥሏል። ከዕውቀትም ከብስለትም ነጻ የሆነው የክልሉ ፕሬዝዳንት የጥፋት እጁን በመወልወል ለሌላ ዙር ዕልቂት እየተዘጋጀ ለመሆኑ እየተነገረ ነው። ወደ ኦሮሚያ ክልል የላካቸው የጥፋት ሃይሎቹ በጭናክሰን የሰው ህይወት ማጥፋታቸውን ቀጥለዋል። ጅጅጋ ስጋት ይንጣታል። ወደ አዲስ አበባ ለአቤቱታ የሄዱት ሽማግሌዎች በአብዲ ዒሌና በህወሀት ወረበሎች እየታደኑ መሆኑም ታውቋል።

አፋሮች ባልተለመደ መልኩ ለተቃውሞ አደባባይ መውጣት ጀምረዋል። አሳይታ፡ ሰመራ፡ ኮልነባ ሌሎች የአፋር ከተሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጎልቶ እየወጣ ነው። ግጭትም ተከስቷል። በወሎ በኩል በአፋርና አማራ ክልል መገናኛ ላይ የሚገኙ አከባቢዎች ሰላም ካጡ ሰንብተዋል። የሰው ልጅ ህይወት እየተገበረ መሆኑ ቀጥሏል የሚል መረጃ ሳይቋረጥ እየመጣ ነው።

ትግራይም ከሰሞኑ የተቃውሞ ሰልፍ እያስተናገደች ናት። የባድመ ጉዳይ የትግራይን ህዝብ አደባባይ ለተቃውሞ እንዲወጣ አድርጎታል። ኢሮብ የጀመረ ባድመ ከተማን ያዳረሰ፡ ወደ ሌሎች አከባቢዎችም እየገባ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታም አያምርም። ከፋን ይዞ እስከጂማ ኢሉባቡር ጥሩ ነገር አይሰማም። ጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን በሚፈሰው ስደተኛ ምክንያት ተወጥራ ልትፈነዳ ደርሳለች። አስጠጉን ብለው እየገቡ ያሉት ደቡብ ሱዳኖች በቁጥር ኢትዮጵያውያኑን ሊበልጡ መሆናቸው ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል። ደግሞም እንግዳ ነን ብለው አርፈው መቀመጥ ያልቻሉት ደቡብ ሱዳኖቹ ቤተኛውን ኢትዮጵያዊ እያጠቁት መሆኑም ይሰማል። በቤንሻንጉል ጉምዝ ያለውም ነገር የተለየ አይደለም። ያስጨንቃል።

በአጠቃላይ ሀገሪቱ ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ በአራቱም አቅጣጫዎች የሚሰማው ነገር ያስፈራል። የብሄር ፌደራሊዝሙ ዋጋ እያስከፈለን ነው። ”ኢትዮጵያን በብሄር ሸንሽነን፡ በቋንቋ ፌደራሊዝም አጥረን ካልሆነ በቀር በስልጣን መቆየት አንችልም” በማለት በግልጽ የተናገሩት አቶ መለስ እሳቸው በህይወት ኖረው ማየት ባይችሉም የዘሩት እህል እየጎመራ፡ ፍሬ እያፈራላቸው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በአዲሱ አስተዳደር ተስፋ አይቶ፡ ደስታውን በሚገልጽበት በዚህን ወቅት በአንድ ላይ እዚህም እዚያም የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት ማን የጫረው፡ ማን ያቀጣጠለው እንደሆነ ሚስጢር አይደለም።

በአጭሩ የብሄር ፌደራሊዝም ኢትዮጵያን ከገደል አፋፍ አስጠግቷታል። ህወሀት የሚሾፍረው የጥፋት መኪና በፍጥነት ጭው ወዳለ ገደል እየበረረ ነው።

የወርቅ ዕንቁላል የምጥለውን ዶሮህን አትረዳት (ወንድሙ መኰንን)

ወንድሙ መኰንን፣ ሰኔ 5 ቀን 2ሺ10 ዓም (12 June 2018) ኢንግላድ

Ethiopian Airlines before and after.

የምታውቁትን ተረት ልድገምላችሁ። አንድ በዶሮ ዕርባታ ብቻ የሚተዳደር ድሀ ገበሬ ነበረ። ጫቹቶቹን እያስፈለፈለ አውራዎቹን እየሸጠ፣ እንስቶቹን ግን እያኖረ አንዳንዴም ዕንቁላላቸውን እየለቀመ ሽጦ ኑሮውን ያሸንፍ ነበር። አንዴት የምትገርም እንስት ዶሮ ተፈለፈለች። ገና ከጫጩትነቷ ጀምራ የተለየች (unique), እንደአውራዎቹ የሚያብረቀርቅ የላባ ቀለም ነበራት። አንዳንዴም እንደ ቆቅም ያደርጋታል። ለየት ያለች ስለሆነች ገበሬው ከሌሎቹ አብልጦ ይወዳት ነበር። ለአቅመ ዶሮ ከደረሰች በኋላ ብዙ ጊዜ ዕንቁላል ሳትጥል ዘገየች። ቢጠብቅ፣ ቢጥብቅ ዕንቁላል አልጥል ስላለች፣ “ይኽቺ መልኳን አሳምራ የማትረባ ዶሮ!” ብሎ ከአውራዎቹ ጋር ሊሸጣት ሲያቅማማ፣ አንድ ቀን ሳይታሰብ አሽካክታ የሚያብረቀርቅ ዕንቁላል ጣለች። ገርሞት ዕንቁላሉን ሲያነሳው ለየት ባለ ሁኔት እንደ ድንጋይ ከበደው። እንዲያው እያፈረ፣ እየፈራ እየተሸበረና እየተሸማቀቀ፣ ወደ ወርቅ ቤት ወስዶ ባለሙያዎቹ እንዲመረምሩለት ጠይቃቸው። የወርቅ ቤቱ ባለሙያ ሙሉ በሙሉ ዕንቋላሉ የወርቅ ትልቅ እንክብል መሆኑን አረጋገጠለት። ከዚያም ያንን የወርቅ ዕንቁላል ወስዶ በብዙ ሺ ብር ሽጦ ከድህነቱ ተላቀቀ። ላሞች ገዛ፣ በሬዎች ገዛ፣ ፈረሶች ገዛ፣ በቅሎዎች ገዛ ….። ያችን ባለውለታ ዶሮ በእንክብካቤ ያዛት። “ዕንቋላል ብትጥል ባትጥል ምን ቸገረኝ? በአንድ ጊዜ በጣም ሀብታም አድርጋኛለች፣ ባለውለታዬ ናት!” ብሎ ከእጁ እይበላች ለማዳ (pet) ሆነች። ኑራ ኑራ፣ ቆይታ ቆይታ፣ አንድ ቀን አሽካክታ ሌላ የወርቅ ዕንቋላል ጣለችለት። አሁንም ወስዶ ያንን ከባድ ሚዛን ንጹህ ወርቅ ሽጦ ሀብት በሀብት ሆነ። ቤቱን በዕብነ በረድ ሠራ። ዉድ መኪና ገዛ። በሰፈሩ እሱን የሚያክል ሀብታም አልነበረም። ታዲያ ምንም ሳይጎድለው አንድ ቀን አንድ ሰይጣናዊ ሀሳብ ብልጭ አለበት። “ለምን እኔ ወቅቷን ጠብቃ አንድ የወርቅ ዕንቁላል እስክትጥል አስጠበቀኝ። አርጄአት በውስጧ ያለውን ወርቅ በሙሉ ሙልጭ አድርጌ ወስጄ ለምን በበለጠ በአንዴ የናጠጠ ኃብታም አለሆንም?” ብሎ ተሰገበገበ። ወሰነም። ምንም ያልጠረጠርችው ዶሮ እንደልማዷ ከእጁ ልትበላ ስትቀርበው ምንም ሳታሰበው ይዞ አረዳት። በጉጉት ሆዷን ሰንጥቆ ሲከፍታት በውስጧ ምንም ወርቅ አልነበረም። ከዚያ በኋላ የሚሆነውን አንባቢ ይገምተው።

ይኸን ታሪክ እዚህ ለመድገም ያነሳሳኝ የሰሞኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመሸጥ የኢትዮጵያ ገዢዎች የወሰዱት እርምጃ አስደንግጦኝ እና አሳስቦኝ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 30 December 1945 (ታኅሣስ 21 ቀን 1938) ዓ.ም፣ ልክ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንዳለቀ፣ ትራንስወርልድ ኤር ላየንስ በተባለ የአሜሪካ አየር መንገድና በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግስት የጋራ የሽርክና ንግድ ተመሠረተ። በዚያን ጊዜ አምስት DC-3 በተባሉ ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት የተረፉ የአሜሪካ የጦር ማጓጓዣ አይሮፕላኖች የጀመረው ድርጅት፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ልጆች ጥረት ከውስጥ በራሱ አድጎ (organic growth) እና ተመንድጎ፣ የ22 ቦይንግ ድሪምላይነር (Boeing 787 Dreamliner))፣ 16 ቦይንግ 777 (Boeing 777)፣ 6 ቦይንግ 767 (Boeing 767)፣ 2 ቦይንግ 757 (Boeing 757)፣ 23 ቦይንግ 737 (Boeing 737)፣ 9 ኤርባስ (Airbus A350)፣ እና የ22 ዲሀቫላንድ ካናዳ ዲኤችሲ-8-400 (De Havilland Canada DHC-8-400)፣ በጠቅላላው የ100 ዘመናዊ በራሪ አይሮፕላኖች ባለቤት ሁኗል። ዛሬ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማይበርበት የዓለም ክፍል የለም። አንዲት አውስትራሊያ ብቻ ነበረች የቀረችው፣ እሷም ባለፈው ሳምንት በውል ተጠናቀቀች።

አየር መንገዱ፣ ከማንኛውም ከበለጸጉት አገራት ባላነሰ፣ ደረጃውንና ጥራቱን የጠበቀ ቴክኒካል ሰርቪስ አለው። ከራሱ አልፎ ተርፎም ቴኪኒካል ሰርቪሱ የሌሎች አገሮች አይሮፕላኖች እየጠገነ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል። ከብዙ አገሮችም ወጣቶች እየመጡ የቴክኒካል ሙያን ይማሩበታል። ያም ሌላው የወጪ ምንዛሪ የገቢ ምንጭ ነው። የራሱ የፓይሌቶች ወይም አብራሪዎች ማሰልጠኛ አለው። እጹብ ድንቅ የተባሉ አብራሪዎቻችን ከዚያ ነው የሚመረቁት። የኔልሰን ማንዴላን መጽሐፍ ያነበበ ኢትዮጵያውያን ፓይሌቶች የመጀመሪያዎቹ አፍሪካውያን አውሮፕላን አብራሪዎች መሆናቸውን መገንዘብ ይችላል። ይኸ ሁሉ ሲኬታማነት የተገኘው በኢትዮጵያ ልጆች ወዝና ላብ ነው። ሌላ ሲከስር አየር መንገዳችን የሚያተርፈው ከሌሎች ሲወዳደር ሠራቶኞቹ ከሌሎች አገሮች ባነሰ ደሞዝ ድንቅ ሥራን ሲሊሚሠሩ ነው። ያ ምንጊዜ መካድ የለበትም።

ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶርህን በቆቅ ለውጥ አለ ያገሬ ሰው!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ብቸኛው ተውዳዳሪ የማይገኝለት አትራፊ አየር መንግድ ነው። በየጊዜው የተፈጠሩ፣ እንደ ኢስት አፍሪካን ኤርዌይስ ያሉ አየር መንገዶች ከሥረው ከገቢያ ሲወጡ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያተረፈ ለአገሪቱም የማይደርቅና የማያቋርጥ የውጭ ምንዛሪ የሚያመጥላት ብቸኛው የተሳካለት ድረጅት ነው። እንዲያው በአጠቃላይ ሲነገር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየጊዜው ወርቅ ዕንቁላል የምትጥለውን ዶሮ ነው የሚመስለው። ሥራ “ሀ” ብዬ የጀመርኩት በዚህ ድርጅት ውስጥ ስለሆነ፣ ዛሬም ቢሆን ወገንተኝነት ይሰማኛልና አትፍረዱብኝ።

የኢትዮጵያ ገዢዎች እንደሆኑ የውጪ ምንዛሪ ሁሌ እንዳጠራቸው ነው። በሚሊዮን የሚቆጠር የውጪ ዕርዳታ ቢጎርፍላቸውም፣ ቋታቸው ምንም ጠብ አትልም። ምነው ቢባል፣ ከዚህ በፊት 11 ቢሊዮን ዶላር ገብቶላቸው፣ አስራ አንዱም ቢሊዮን እንዳወጡ አንብበን ጉድ ብለናል። ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከዛሬ ዩኤስ አሜሪካ ብቻ $30 ቢልዮን እንደሰጠች ይታወቃል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን አንዳት ቤሳ ቢሲት አልደረሰውም። ለሕዝባችን “40 ቢታለብ ያው በገሌ” ያለችው ድመት ብጤ ነው። እንዳልኳችሁ የኢትዮጵያ ገዢዎች ቋት ጠብ አትልም። በየጊዜው ያው የውጪ ምንዛሬ እጥረት እዬዬ እንደቀጠለ ነው። ማቆሚያ የለውም። ታዲያ ያንን የውጪ ምንዛሪ ጥማት ለመቁረጥ  የኢትዮጵያ ቅርሶች እይተቸበቸቡ አልቀዋል። የዚህ የውጭ ምንዛሪ ጥም የኢትዮጵያ ገዢዎችን ያላስቧጠጣቸው ግድግዳ የለም። Daily Mail የተባለው ጋዜጣ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍሮ ነበር፡

“… a corrupt London Police stood to gain 2 million ($3.13 million) by brokering the sale of Ethiopian embassy in London for £24 million ($37.5 million).”

የንጉሠ ነገሥቱ ነፍስ በሰማይ ቤት ይማርና፣ ሕንጻው የምይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ አንጡራ ሀብት (Heritage) አድርገው በፍርድ ቤት አስወስነው ስለነበር ሺያጩ ሳይሳካላቸው ቀረ እንጂ ዛሬ የሎንደኑ ኤምባሲአችን 17 Pricess Gate መሆኑ ቀርቶ የሆነች ጭርንቁስ ስቶክዌል ውስጥ የኪራይ ቤት ውስጥ ተወሽቆ በተገኘ ነበር።

ይኸው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ነበር መሬትን ከገበሬ ቀምቶ ለውጪ ባለሀብቶች በውጪ ገንዘብ (hard currency) መቸብቸብን ያመጣውና መንግሥት ተቢዬውን ከሕዝብ ያጋጨው። የውጪውን ምንዛሪ ቢሰበሰብ ቋቱ እንደሆን ጠብ አይል፣ እንዲያው ምን አለፋቸው!

እስቲ በውጪ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽ፣ የኢትዮጵያ የንግድ መርከቦች … ወዘተ ተሸጡ እንበል። የውጪ ምንዛሬዋንም አገኟት። ወያኔ እጅ የገባ የውጭ ምንዛሪና እሳት ውስጥ የወደቀ ቅቤ አንድ ነው። እንደገባ ነው የሚወጣው። ነገም እኮ ያው ነው! ያቺ ስትሟጠጥስ ምን ሊሸጡ ነው? ያች የውጭ ምንዛሬ እንቁላል የምትጥል ዶሮ እንደሆነች የለች። አየርመንገድ ከሌለ ወርቁ ከየት ሊመጣ ነው?

ሌላም የማይታይ ጣጣ አለ። አንድ ያስተዋልኩትን ምሳሌ ልጥቀስላችሁ። ሪያል ማድሪድ የተባለው የእስፓኒሽ የፉትቦል ቲም የማያውቅ አለ? ሲብዛ ሀብታም ነው። ብዙም ያሸንፋል። የሚገርመው የትም አገር ይሁን፣ የትም ቡድን ውስጥ ኮከብ የተባሉ ተጫዋቾች ሲፈጠሩ፣ እያሳደደ ይገዛቸዋል። ኮከብ በኳክብት የተሞላ ቡድን ነው። አንዱ ዓላማው በነዚህ ኮከብ ተጫዋቾች ተጫውቶ ዋንጫ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን፣ እነዚህ ኮከብ ተጫዋቾች ለሌላ ክለብ ተጫውተው ድል እንዳይነሱት፣ በብዙ ሚሊዮን ዶላር ገዝቶ ከጨዋት ውጪ ማድረግ ነው። ለወራት፣ለዓመታት ቤንች ላይ ያስቀምጣቸዋል። የማንቸስተሩ ዩናይትዱ ኮከብ ተጫዋች ዴቪድ ቤካም ወደ ማድሪድ ተዛውሮ ነው የጨዋታ አኪሩ የጠፋው። የሊቨርፑሉ ማይክል ኦዌን በማድሪድ ተገዝቶ ቤንች ሲያሞቅ ኑሮ ነው ኮከብነቱ የደበዘዘው። ተምልሶም ሰው አልሆነ። በተመሳሳይ ዓላማም ታዲያ ሌሎች የታወቁ አየር መንገዶች፣ እንደሉፍታንዛ፣ ብሪቲሽ ኤርዋይስ፣ አሊታሊያ ያሉት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ገዝተው የራሳቸው ካደረጉ በኋላ፣ የአይር መንገዱን መሥመሮች በሙሉ እጃቸው አስገብተው ከጨዋታ ውጪ ሊያድርጉት እንደሚችሉ ታስቦበት ይሆን? ዶሮ ባትበላ ጭራ ታፈሳለች አሉ አበው።

የኢትዮጵያ መንግስት ልብ ግዛ። የወርቅ ዕንቁላል የምትጠለውን ዶሮህን አትረድ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ  አንድ በድሀ አገር ብቻውን ተመዞ የወጣና በእግሩ የቆመ ድርጅት ብቻ ሳይሆን፣ እንደአትሎቶቻችን ስማችንን በጥሩ ገጽ ያስጠራ ድርጅት ነው። ስኬታማ መሆኑ ሊያስሸጠው ከሆነ ያቺን ያለችንን አንድ ዓይን እንድማጥፋት ነው። በድንብ በጥንቃቄ ይታሰብበት እላለሁ። ባይሆን የአንበሳውን ድርሻ፣ ይኸ በዶክተር ዓቢይ የሚመራው ቡድን ለኢትዮጵያ የሚያስብ የምስላልና፣ መንግሥት ያስቀረው።

ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልም። ሀሳቤን ወርውሬአለሁ!

አቶ ስዩም መስፍን “ባድመ” የኢትዮጲያ አካል መሆኗን የሚያሳይ ማስረጃ አለማቅረባቸውን የድንበር ኮሚሽኑ ሪፖርት አረጋገጠ!

ከስዩም ተሾመ

የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን ሪፖርትና ሌሎች ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚጠቁሙት የባድመ አከባቢ ለረጅም አመታት ሰው-አልባ ነበር፡፡ በአከባቢው ሰዎች መስፈር የጀመሩት ከ1950ዎቹ ጀምሮ ነው፡፡ የባድመ ከተማ በራሷ የተቆረቆረችው በወቅቱ የትግራይ አውራጃ አስተዳዳሪ በነበሩት በራስ ስዩም መንገሻ ድጋፍ ነው፡፡ ከ1950ዎቹ ጀምሮ አከባቢው በኢትዮጲያ ስር ሲተዳደር እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ይህንንም የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን በዝርዝር ገልጿል፡፡ ከ1950ዎቹ በፊት በነበረው ግዜ በአከባቢው በቋሚነት የሚኖሩ ሰዎች ባለመኖራቸው ምክንያት ባድመ የኢትዮጲያ ይሁን የኤርትራ በግልፅ መለየት አስቸጋሪ ነበር፡፡ ከ1950ዎቹ በኋላ ግን የባድመ አከባቢ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጲያ ስር እንደነበረች ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል፡፡ እ.አ.አ እስከ 1970ዎቹ ድረስ አከባቢው በኢትዮጲያ ሲተዳደር እንደነበረ የሚያሳዩ መረጃዎች እንዳሉ በድንበር ኮሚሽኑ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡ በአጠቃላይ ከ1984 በፊት ሆነ በኋላ የባድመ መሬት የኤርትራ አካል ሆኖ አያውቅም!

 

ኤርትራ ከተገነጠለች በኋላም ባድመ በትግራይ ክልል የተሓታይ-ዓዲኣቦ ወረዳ (Tahtay-Adiabo Woreda) አካል ሆና ቀጥላለች፡፡ ለዚህ ደግሞ በ1987 (እ.አ.አ በ1994) ዓ.ም በተካሄደው ሀገር-አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ የባድመ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ተካትተዋል፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት እንደሚያሳየው በ1987 (1994) ዓ.ም አጠቃላይ የተሓታይ-ዓዲኣቦ ወረዳ ነዋሪዎች ብዛት 79,832 ሲሆን ከእነዚህ 77246 ትግሬዎች (ተጋሩዎች)፣ 1928 ኤርትራዊያን፣ 1144 ኩናማዎች ናቸው፡፡ በባድመና አከባቢዋ የሚኖሩ ሰዎች 1,089 ናቸው፡፡ የባድመ ከተማ ነዋሪዎች 892 የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 734 ትግሬዎች፣ 157 ኤርትራዊያን እና 1 አማራ ነበሩ፡፡

“BADME AND THE ETHIO-ERITREAN BORDER: THE CHALLENGE OF DEMARCATION IN THE POST-WAR PERIOD” በሚል ርዕስ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ እ.አ.አ ባድመ የኤርትራ አካል ሆና እንደማታውቅ ከ1900 ጀምሮ በኢትዮጲያና በቅኝ-ገዢዎች መካከል የተፈረሙ የድንበር ስምምነቶችን ዋቢ በማድረግ ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ በ1987 ዓ.ም በኢትዮጲያ የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የባድመ አከባቢ ነዋሪዎች ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ ስለዚህ የባድመ አከባቢ ነዋሪዎች በተሓታይ-ዓዲኣቦ ወረዳ (Tahtay-Adiabo Woreda) ተመራጭ አማካኝነት በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወክለዋል፡፡

ስለዚህ ሁለቱ ሀገራት “በድንበር ይገባኛል” በሚያደርጉት ክርክር መቅረብ ያለበት ማስረጃ ከ1950ዎቹ ወዲህ ያለው እውነታ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የአፄ ሃይለስላሴ መንግስት እ.አ.አ በ1947 ከኢጣሊያ ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት፣ እንዲሁም ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት ስር በነበረችበት ወቅት የተላለፉ ውሳኔዎች፣ እንዲሁም በተጨባጭ መሬት ያሉ ማስረጃዎች በዋቢነት ሊጠቀሱ ይገባል፡፡ በአጠቃላይ ከ1950ዎቹ በፊት በነበረው ግዜ አከባቢው ሰው አልባ ምድረ በዳ ስለነበር የኤርትራ ይሁን የኢትዮጲያ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም፡፡ ነገር ግን፣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን የሚመራው ልዑካን ቡድን የአልጄርስ ስምምነትን ተከትሎ ለተቋቋመው የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ያቀረበው የድንበር ይገባኛል መከራከሪያና ማስረጃ እ.አ.አ በ1900, 1902, እና 1908 ዓ.ም በአፄ ሚኒሊክ ዘመን የተፈረሙ የድንበር ስምምነቶችን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ከ1950ዎቹ ጀምር ባድመና አከባቢዋ በኢትዮጲያ መንግስት አስተዳደር ስር እንደነበር የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ በተካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ የባድመ ከተማና አከባቢው ህዝብ በኢትዮጲያ ስር የተቆጠረ መሆኑን ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የባድመና አከባቢው ነዋሪዎች በ1987 ዓ.ም በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ተሳታፊ እንደነበሩ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን ሪፖርት እንደሚያሳየው በአቶ ስዩም መስፍን የሚመራው የኢትዮጲያ ልዑካን ቡድን ባድመ የኢትዮጲያ አካል መሆኗን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ለኤርትራ እንድትሰጥ ተደርጏል፡፡ ሌላው ቢቀር ከኤርትራ መገንጠል በኋላ የባድመ አከባቢ ህዝብ በኢትዮጲያ ሀገር አቀፍ ምርጫና ህዝብ ቆጠራ ተሳታፊ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲና ከምርጫ ቦርድ ማቅረብ በፍፁም አዳጋች ሊሆን አይችልም፡፡ ከዚያ ይልቅ፣ ባድመን ለኤርትራ አሳልፎ የሰጠው አቶ ስዩም መስፍንና ሌሎች የህወሓት ባለስልጣናት ናቸው፡፡ እነዚህ ባለስልጣናት በሀገር ክህደት ወንጀል መጠየቅ አለባቸው፡፡

የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን ጉዳዩን በሚያጣራበት ወቅት የኤርትራና ኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያቀረቡትን መከራከሪያና ማስረጃዎች፣ እንዲሁም ይህን መሠረት አድርጎ ውሳኔ ያሳለፈበትን ሂደት ለማሳየት ከኮሚሽኑ ሪፖርት ውስጥ የሚከተለውን ቀንጭበን ወስደናል፡፡ በዚህ መሠረት ኮሚሽኑ አቶ ስዩም መስፍን ባድመ ከ1950ዎቹ በኋላ የኢትዮጲያ አካል እንደነበረች የሚያሳይ ማስረጃ እንዳላቀረቡ በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ባድመን የሸጣት ስዩም መስፍን መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡

****–

1.19 Hearings were held at the Peace Palace in The Hague from 10 through 21 December 2001, during which oral arguments and replies were heard from the following:

 • For Eritrea: His Excellency Ali Said Abdella, Foreign Minister of Eritrea, Agent
 • Professor Lea Brilmayer, Co-Agent
 • Mr. O. Thomas Johnson
 • Professor James Crawford, SC
 • For Ethiopia: His Excellency Seyoum Mesfin, Minister of Foreign Affairs of Ethiopia, Agent
 • Mr. B. Donovan Picard
 • Mr. Ian Brownlie, CBE, QC
 • Mr. Rodman R. Bundy
 • Ms. Loretta Malintoppi
 • Mr. Dylan D. Cor

1.20 In the course of the written proceedings, the following submissions were presented by the Parties:
On behalf of Eritrea,
in the Memorial:
For the reasons set out in this Memorial, which Eritrea reserves the right to supplement and develop further in subsequent pleadings and oral argument, it is respectfully submitted that the boundary between the two parties is that depicted in Figure 2.1 above and in Map 1 in Eritrea’s Atlas.

in the Counter-Memorial:
For the reasons set out in this Counter-Memorial, which Eritrea reserves the right to supplement and develop further in subsequent pleadings and oral argument, it is respectfully submitted that the boundary between the two parties is that depicted in Figure 2.01 in Eritrea’s Memorial and in Map 1 in Eritrea’s Memorial Atlas.

in the Reply:
For the reasons set out in this Reply, which Eritrea reserves the right to
supplement and develop further in subsequent pleadings and oral
argument, it is respectfully submitted that the boundary between the two
parties is that depicted in Figure 2.01 in Eritrea’s Memorial and in Map 1 in Eritrea’s Memorial Atlas.

On behalf of Ethiopia,

in the Memorial:

On the basis of the facts and legal arguments presented in this Memorial; and Considering that Article 4 of the 12 December 2000
Agreement provides in the relevant part of paragraph 2 that

The parties agree that a neutral Boundary Commission composed of five members shall be established with a mandate to delimit and demarcate the colonial treaty border based on pertinent colonial treaties (1900, 1902 and 1908) and applicable international law;

and in paragraph 10 that –

With regard to those portions of the border about which there appears to be controversy, as well as any portions of the border identified pursuant to paragraph 9 with respect to which either party believes there to be controversy, the parties shall present their

written and oral submissions and any additional evidence directly to the Commission, in accordance with its procedures;
The Federal Democratic Republic of Ethiopia, while reserving the right
to supplement or amend these Submissions in the light of further
pleadings in the case, respectfully requests the Commission to adjudge
and declare:

– That the boundary in accordance with the Treaty of 1900 is constituted by the line described in Chapter 4, paragraph 4.7 above;
– That the boundary in accordance with the Treaty of 1902 is constituted by the line described in Chapter 4, paragraph 4.8 above;
– That the boundary in accordance with the Treaty of 1908 is to be delimited and demarcated on the basis of the modus operandi described in Chapter 3, paragraphs 3.216 to 3.223 and Chapter 4, paragraph 4.9 above.

in the Counter-Memorial:
On the basis of the facts and legal arguments presented in Ethiopia’s
Memorial and Counter-Memorial; and
Rejecting the Submissions of Eritrea set forth in her Memorial;

The Federal Democratic Republic of Ethiopia, while reserving its right to supplement or amend these Submissions in the light of further pleadings in the case, respectfully requests the Commission to adjudge
and declare:

– That the boundary in accordance with the Treaty of 1900 is
constituted by the line described and illustrated in Chapter 2 of
this Counter-Memorial;
– That the boundary in accordance with the Treaty of 1902 is
constituted by the line described and illustrated in Chapter 3 of
this Counter-Memorial; and
– That the boundary in accordance with the Treaty of 1908 is
constituted in accordance with the methodology and consid￾erations described and illustrated in Chapter 4 of this Counter￾Memorial.

in the Reply:
On the basis of the foregoing, and rejecting Eritrea’s contentions to the
contrary, Ethiopia confirms the Submissions as set out at the end of her Counter-Memorial.

In the oral proceedings, the following submissions were presented by the Parties:
On behalf of Eritrea,
at the hearing of 20 December 2001:
It is respectfully submitted that the boundary between the two parties is
that depicted in map 1 of Eritrea’s memorial atlas, the coordinates of
which are more fully described in the 1:50,000 map that Eritrea has
deposited with the Secretary.

On behalf of Ethiopia,

at the hearing of 21 December 2001: The Federal Democratic Republic of Ethiopia respectfully requests the
Commission to adjudge and declare, first, that the boundary, in accordance with the treaty of 1900, is constituted by the line described and illustrated in chapter 2 of the counter-memorial; secondly, that the boundary in accordance with the treaty of 1902 is constituted by the line described and illustrated in chapter 3 of the counter-memorial; and, thirdly, and finally, that the boundary, in accordance with the treaty of 1908, is constituted in accordance with the methodology and considerations described and illustrated in the oral hearing

4) The Position after 1935

5.91 The Commission has examined the major elements in the course of events since 1935: the Italian invasion of Ethiopia; the outbreak of the Second World War; the British military occupation of Eritrea; the post-war developments including the treatment of the political future of Eritrea; the creation of the federation between Ethiopia and Eritrea; and the eventual termination of that federation. However, the Commission can perceive nothing in that chain of developments that has had the effect of altering the boundary between the Parties. The boundary of 1935 remains the boundary of today.

5.92 However, there is one specific body of material to which the Commission has given careful consideration, namely, the Ethiopian evidence of its activities in the area west of Eritrea’s claim line. The Commission notes that no evidence of such activities was introduced in the Ethiopian Memorial. The evidence to be examined appeared only in the Ethiopian Counter-Memorial. It was not added to or developed in the Ethiopian Reply.

5.93 The places in which Ethiopia claimed to have exercised authority west of the Eritrean claim line are all, with two exceptions, clustered in the northeast corner of the disputed triangle of territory. The most westerly location is Shelalo. The Commission observes that the area of claimed Ethiopian administrative activity comprises, at the most, one-fifth of the disputed area. The area of claimed administration does not extend in any significant way towards the Ethiopian claim line.

5.94 The Commission observes, secondly, that the dates of Ethiopian conduct relate to only a small part of the period that has elapsed since the 1902 Treaty. There are some references to sporadic friction in 1929-1932 at Acqua Morchiti. Apart from those, the material introduced by Ethiopia dates no further back than, at the earliest, 1951 – a grant of a local chieftaincy to an Ethiopian general. Even this grant, in specifying the places sought by the general, namely, Afra, Sheshebit, Shelalo, from Jerba up to Tokomlia, Dembe Dina and Dembe Guangul, described them as “uninhabited places” which the general wanted to develop. The evidence of collection of taxes is limited to 1958 and 1968. In 1969 there is a reference to a table of statistics about the Adiabo area, but of the places mentioned in the table only two appear to be marked on the Ethiopian illustrative figure of the claimed region. One item dating from 1970 refers to the destruction of incense trees. There is some evidence of policing activities in the Badme Wereda in 1972-1973 and of the evaluation of an elementary school at Badme town. There are, in addition, a few items dating from 1991 and 1994.

5.95 These references represent the bulk of the items adduced by Ethiopia in support of its claim to have exercised administrative authority west of the Eritrean claim line. The Commission does not find in them evidence of administration of the area sufficiently clear in location, substantial in scope or extensive in time to displace the title of Eritrea that had crystallized as of 1935.

5.96 The Commission’s conclusions regarding the 1902 Treaty line as a whole will be found in Chapter VIII, paragraph 8.1, sub-paragraph A.


CHAPTER VIII –DECISION

8.1 For the reasons set out above, the Commission unanimously decides that the line of the boundary between Eritrea and Ethiopia is as follows:

A. In the Western Sector

(i) The boundary begins at the tripoint between Eritrea, Ethiopia and the Sudan and then runs into the centre of the Setit opposite that point (Point 1)
(ii) The boundary then follows the Setit eastwards to its confluence with the Tomsa (Point 6)
(iii) At that point, the boundary turns to the northeast and runs in a straight line to the confluence of the Mareb and the Mai Ambessa (Point 9).

 

ኦፌኮ በምርጫ ኦህዴድን ለመዘረር የሚያደርገው ሩጫ አሳሰቦኛል (ያሬድ ጥበቡ)

ቢሳካለት አንድምታው ምንድን ነው? የአትላንቲክ ካውንስል ስብሰባ ላይ የተገኙ ወገኖች እንዳጫወቱኝ በበቀለ ገርባና እስክንድር ነጋ መካከል ልዩነቱ እጅግ ጎልቶ የወጣበት አንድ ጉዳይ ቢኖር የቀጣዩ ምርጫ ጥያቄ ነው። በቀለ ምርጫው የጊዜ ሰሌዳውን ጠብቆ እንዲካሄድ ግፊት ሲያደርግ የእስክንድር ትኩረት ደግሞ ሁሉን አቀፍ ጉባኤ እንዲጠራ ነው። ጥያቄው፣ ለምን እነበቀለና ኦፌኮ ለምርጫ መጣደፉን መረጡ የሚል ይመስለኛል።

ፍርሃታቸው፣ ሁሉን አቀፍ ጉባኤ ከተካሄደ መሠረታዊ ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ተነስተው ወደ ድሮዊንግ ቦርዱ ወይም ሰኔ 1983 የሽግግር ጉባኤ ይመልሰናል የሚል ፍርሃት ስለሚሰማቸው ይሆን? ወደ ሽግግር መሰል ሁኔታ ብንመለስ ለምን ይፈራሉ? ህገመንግስቱን አሻሽሎ፣ አርሞ፣ አስተካክሎ ወደ ምርጫ መሄድ ለምን ያስፈራቸዋል? ይህስ ፍርሃታቸው የወያኔ እቅፍ ውስጥ እንደማይጥላቸው ምን መተማመኛ አለ?

blinds
Secret Offers Expire Soon! Click Here Now To Find!

ለማስተዳደር አስቸጋሪ ከሆኑ ዘጠኝ ክልሎች ይልቅ የባህልና ቋንቋ ፍላጎታቸውን ሳያዳክም እንደ አዲስ አነስ አነስ አድርጎ የአውራጃ ፌዴራል አስተዳደሮችን በማቆም በተሻለ መንገድ ማዋቀር ለእድገት ሊያመች ይችላል። ለምን በወያኔ ጥብቆ ልክ በተሰፋ የክልል አጣብቂኝ ውስጥ መኖር መገደድ አለብን? ዛሬ ያለው ክልል እኮ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ያለውን ትግራይና 28 ሚሊዮን ህዝብ ያለውን አማራ ወይም 34 ሚሊዮን ህዝብ ያለውን ኦሮሚያ እንደ እኩል ነው የሚያየው። ለአማራ ክልል ዋና ከተማ የሚደረገውን ያህል ለመቀሌም ይደረጋል። ይህ ሊቀጥል አይችልም። የአማራ ክልል ለትግራይ የሚደረገውን ስድስት እጅ የበለጠ ሲደረግለት ብቻ ነው ሥርአቱ ፍትሃዊ ነው የሚባለው። ይህ እንዲሆን ደግሞ የአማራው ክልል ለማስተዳደር ምቹ ወደሆኑ ፌዴራል አውራጃዎች ሲከፋፈል ለፍትሃዊ አስተዳደር በር ይከፍታል። ለምሳሌ አንድ ፌዴራል አውራጃ በአማካይ ሁለት ሚሊዮን ህዝብ ቢኖረው ትግራይ ሶስት ፌዴራል አውራጃዎች (ምሥራቅ፣ ምዕራብና ማእከላዊ)፣ አማራ 14 አውራጃዎች (ምናልባት የኃይለሥላሴ ዘመንን አውራጃዎች ተከትሎ)፣ ኦሮሚያ 17 ፌዴራል አውራጃዎች (ምናልባት የቀድሞ የጎሳ አደረጃጀቱን ይዞ ኢቱ፣ ቦረና፣ ከረዩ ወዘተ አያለ) እንደገና ሊዋቀር ይችላል።

አዲስአበባም ለ27 ዓመታት ተነፍጎ የቆየውን የፌዴራል መንግስቱ አባልነት መብቱን አስከብሮ፣ አንገቱ ላይ የተንጠለጠለበትንም የኦሮሞ ብሄርተኝነት ሰይፍ አስወግዶ፣ በመቶ ስንትስ ዓመታት ታሪኩ የሁሉም ብሄረሰቦች የገንዘብ፣ የጉልበት፣ የፍቅር፣ የእንባ ሃብት ፈሶበት የተሠራ የኢትዮጵያችን መዲና በመሆኑ የኢትዪጵያ ብሄርተኝነት መፈልፈያ የችግኝ እርሻ ሆኖ መተው ይኖርበታል። ይህም ከኦሮሞ ብሄርተኝነት ጋር በየጊዜው እንዳያላትመውና የቁርሾ መንስኤ እንዳይሆን፣ አዲስአበባ አሁን ካለውም የመሬት ይዞታ ሰፋ ብሎ መከለል ይኖርበት ይሆናል። የማእከላዊ ኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ተብሎ። በአማርኛም ላይ አፋን ኦሮሞን ተጨማሪ ቋንቋው አድርጎ ሊቀበል ይችላል፣ የኦሮሞ ብሄርተኞች የላቲኑን ቁቤ ትተው የግእዙን ኢትዮጲስ ፊደል ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ።

የኦሮሞ ብሄርተኞች በአንድ ሃገር ሁለት ፊደል መጠቀም አዳጋች መሆኑን መቀበልና፣ ላቲኑን አስር ጊዜ የሚያስከነዳው የግእዝ ፊደል አፋን ኦሮሞን ለመግለፅ የበለጠ አቅምና ክህሎት እንዳለው ሊቀበሉ ይገባል ። የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዢ ስለሆንን የተለየ ፊደል ያስፈልገናል ተብሎ የገባው የላቲን ቁቤ ዛሬ ኢትዮጵያዊነቱን ብቻ ሳይሆን የማእከላዊ መንግስት አስተዳደሩን ለተረከበው ኦሮሞ ቁቤ አይመጥንም። አውሮፓውያን ለጥቁር ህዝቦች ዝቅተኝነት ዓይነተኛ መከራከሪያቸው “ተመልከቷቸው ፊደል ያለው ቋንቋ እንኳ የላቸውም” የሚል በመሆኑ፣ የግእዝ ፊደልን ወደተቀረው አፍሪካ ይዘን መሄድ ሲገባን ኢትዮጵያ ውስጥ መቀበል ቢያቅተን ራስን ሰድቦ ለሰዳቢ የመስጠት ያህል ነውር ነው።

የኦሮሞ ብሄርተኝነት አፋን ኦሮሞን የኢትዮጵያ ተጨማሪ የሥራ ቋንቋ ማድረግ ከፈለገ፣ ኢትዮጵያዊ ለሆነው ግእዝ ያለውን ጥላቻ ማቆም አለበት። ሥልጣን ይዘናል የፈለግነውን ማድረግ እንችላለን ብሎ የሚያስብም ከሆነ ወያኔ ለ27 ዓመታት ከሄደበት የጡንቸኝነትና የህዝብ ጥያቄ እምቢተኝነት ጋ ተመሳሳይ ስለሚሆን ሄዶ ሄዶ የወያኔ እጣ ነው የሚደርሰው። ወያኔ የወደቀው ከአነስተኛ ብሄረሰብ የወጣ ስለሆነ አይደለም፣ አስተሳሰቡ ጠባብና እብሪተኛ ስለነበር እንጂ። ወያኔ ባለፉት ሁለት ወራት ዶክተር አቢይ ያሰማቸውን የፍቅር መልእክቶች እያሰማና የህዝብን የልብ ትርታ እያደመጠ ቢሄድ ኖሮ ትግሬነቱም ሆነ አናሳነቱ ችግር ባልሆነ፣ በአጋዚ ሳይሆን በቄጠማ መግዛት በተቻለው ነበር። የኦሮሞ ብሄርተኝነት ከዚህ የወያኔ አካሄድና አወዳደቅ ሊማር ይገባዋል።

ወደጀመርንበት ወደ የፌቡ ወዳጄ ዶክተር ገረፋ ቱሉ ወዳነሳው የኦፌኮ የምርጫ ዝግጅት ጉዳይ ስንመለስ፣ ዛሬ ኢትዮጵያችን ለምርጫ ፖለቲካ ዝግጁ አትመስለኝም። የማገገሚያ ወቅት ያስፈልጋት ይመስለኛል። ምናልባት የምርጫውን ወቅት ተጨማሪ ሁለት አመታት ሰጥቶ የዶክተር አቢይን አስተዳደር እንደ ሽግግር ዘመን ሥልጣን ለማየት መነጋገር ይኖርብን ይሆናል። ምናልባትም በጎማ ማህተሙ ፓርላም ምትክ ልክ በሰኔ 1983 አቶ መለስ ይመሩት የነበረውን ዓይነት የሽግግር ምክርቤት ያስፈልገን ይሆናል። የኢህአዴግ አስተዳደርና የሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ምክርቤት ቅይጥ ። እንዲህ ዓይነት እሳቤ ለፈረንጆቹም ሆነ የነርሱን ቃል እንደ አስርቱ ትእዛዝ ለሚያንበለብለው ምሁር ባእድ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ከኢትዮጵያ አፈር የሚነሳ ለአለም የምናበረክተው የፖለቲካ ሳይንስ አበርክቶም ሊሆን ይችል ይሆናል። በህዝብ መድረክ ላይ እያሰብኩ ነው። አዲስም ነው። አታውግዙት፣ ተወያዩበት። ተጨንቀን፣ አምጠን እኛነታችንን እስቲ እናግኝ። አይዞን!