“መደመሩን” ከቀኝ ጅቦች ለማዳን – ፀረ-ቅልበሳ ኃይሎችን ማደራጀት – B.K

 

1966 ዓም ተጠናክሮ የመጣው የለውጥ ማዕበል ቤተመንግስቱን ሳይቀር አንቀጠቀጠ። ንጉሡ የሕዝቡን ተቃውሞ መቋቋም አቃታቸው። በዚህን ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሃብተወልድ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ። ይህ ለመጀመርያ ጊዜ የተደረገ በሳል የፖለቲካ ርምጃ ነበር። ንጉሡ የሕዝቡን ንቅናቄ በጥገናዊ ለውጥ ለማስተካከል ሞክረው ልጅ እንዳልካቸው መኮንንን ጠቅላይ ሚኒስቴር አድርገው ሾሙ። ሕዝቡ አሁንም ተቃውሞውን ገፋበት። የንጉሡ አስተዳደርር ለፖለቲካ ፓርቲ እውቅና የማይሰጥ ስለነበር ሃገሪቱ ጠንካራ ድርጅት አልነበራትም። በወቅቱ የተደራጀውና የታጠቀው ኃይል ወታደሩ ስለነበር ሥልጣኑን በቀላሉ ቀርጨም አደረገ። ይህ ኃይል “የጊዜአዊ ወታደራዊ አስተዳደርር ደርግ” ይባላል። ወድያውኑ በአስቸኳይ የተደራጁት ኢሕአፓና መኢሶን ሥልጣኑን አንደኛው በትጥቅ ትግል ሌላኛው ደግሞ በሠላማዊ መንገድ ለመንጠቅ ትግላቸውን በየፊናው ተያያዙት። ኢሕአፓና መኢሶን በርዕዮተ ዓለም የበሰሉ ለዴሞክራሲ ሲሉ ደርግን ለማስወገድ በቆራጥነት የተሰለፉ የምሁራን ድርጅት ነበሩ። እነዚህ ቡድኖች አንዳች የግል ጥቅም አልነበራቸውም። በብስለት መራመድ ባለመቻሉ ምክንያት ኢትዮጵያ ይህ እድል ተበላሸባት።

ደርግ በራሱ ድክመት ሲገረሰስ እሚኒልክ ቤተመንግሥት መግባት የቻለው ባለጊዜው ወያኔ–ኢሕአዴግ ኢሕአፓና መኢሶንን ይቅርና የደርግ ያህል የርዕዮተ ዓለም እውቀት አልነበረውም። አውራ መሪዎቹ እንደውም አንዳች ፍንካች ኢትዮጵያዊነት አልታደሉም። ይኸው አውራ ቡድን ፍላጎቱ የቅርብ ቤተሰቦቹን ማበልጸግና ቢቻል ጨረቃ ላይ ማሳረፍ፣ ቀጥሎም አካባቢውን በልማት ጭላንጭል በመደለል ነዋሪውን የክብሩ ጠባቂ አድርጎ በተስፋ እያማለለ እድሜውን ዘላለማዊ ማድረግ ነበር። ደርግ ሲወድቅ፣ ከታማኝ በየነና ጥቂቶች በቀር፣ ሕዝቡ በቂ ተቃውሞ አላደረገም። አውራው ቡድን አንዳች ተቃውሞ ያላሳየውን ጨዋ ሕዝብ ሥነ–ልቦና እያደር መቆጣጠር በመቻሉ ለሃያ ሰባት ዓመት ደሙን ካለርኅራሄ መጠመጠ፣በርካቶችን አስደደ የሚችለውን ገደለ። ሥርዓቱ በሙስና ያባለጋቸው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ባለጌ ኃይል አለው። ችግሩ እዚህ ላይ ነው። ልብ በል።

አውራው የማፍያ ቡድን ሃያ ሰባት አመት በስርቆት ሲገዛ ጉምሩኩን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የፍተሻ ኬላዎችን፣ ወደብ ላይ ሠራተኞችን፣ ደህንነትና ወታደራዊ እና ዘርዝሬ የማልጨርሰው ሌሎች ባለፉት መንግሥታት የተቋቋሙ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሙስና ባለሙያዎችንና ዘራፊ ባለጌዎችን አስቀምጧል። ልብ በሉ እንደ ደርግ ጊዜ አብዮቱን የሚወዱ ካድሬዎች ሳይሆን የተቀመጡት ለዝርፍያ የተዘጋጁ ቦዘኔ መሃይም ሌቦች ናቸው በየወንበሩ ፊጥ ያሉት። እነዚህን ባለጌዎች ማንም በድፍረት መናገር አይችልም። አንዱን ባለጌ መናገር ማለት ሄዶ ሄዶ ወደ ላይ አውራ ሌባውን መድፈር እንደ ማለት ነው። ይህ በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ በደሉን አምቆ ሲገዛ ኖረ። ብልግናው ከየቢሮው አልፎ አካባቢውን ሲበክል ብሶት የወለደው ቄሮ፣ ፋኖና ዘርማ የሞት የሽረት ትግል አደረጉ። የነለማ ቡድንን በሳል ሚና ጨምሮ የዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን መምጣት ይህ የሃያ ሰባቱ ዓመት ብሶት የወለደው ነባራዊ ሁኔታ ነው።

ለመሆኑ የቀኝ ጅቦች እነማን ናቸው – በዶክተር አብይ የሚመራውን የመደመሩን ፍልስፍና የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን አሉ ማለት ይከብዳል። ደርግ ሙስናን እንደ ርዕዮተ ዓለም ስለማያራምድ በጥቅማ ጥቅም የገዛቸው ኃይል አልነበሩትም። ኢሕአዴግ ግን ሙስናውንና ዝርፊያውን የሚያስፋፉ በማፍያው አውራ ቡድኖች የተሾሙ አገልጋዮች አሉት። ሥርዓቱ በንግዱም ይሁን በአስተዳደር ቢሮው በርካታ ተጠቃሚዎችን አፍርቷል። ሌላም ጉዳይ አለ። አስተሳሰብ ያድጋል በመሆኑም የሥርዓቱን አሳፋሪ ጥፋቶች ተገንዝበው ወደ መደመሩ ፍልስፍና ራሳቸውን የመለሱ የኢሕአዴግ አባላትም አይኖሩም አይባልም። ይህንን ሁኔታ ሰው በአንክሮ ሊመዘግበው ይገባል። የቀኝ ጅቦች ማለት አውራው የሙስና ኃይል በዘረጋው የዘረፋና የሌብነት ሥርዓት ተጠቃሚ የሆኑ ዛሬ ከመደመሩ ፍልስፍና ጋር መጓዝ ያቃታቸው የደነገጡ ግለሰቦች ማለት ነው። እነዚህ ፈሪ ግለሰቦች የቅልበሳ ሥራ ለማድረግ ከመሞከርና ግድያ ከመፈጸም አይቦዝኑም።

ሥልጣንን ተገን ያደረጉ ግለሰቦችና አብረዋቸው የሚሠሩት ነጋዴና ሸሪኮች ካላንዳች እፍረት በከፍተኛ ፍጥነት ዝርፊያና ሌብነት ሲፈጽሙ የቆዩት – ሥርዓቱ አንድ ቀን እንደሚወድቅ ያውቁ ስለነበር ነው። አውራ ሌቦቹ ቤተሰቦቻቸውን ወርቅ አልብሰው ወርቅ መኪና ይነዳሉ። በየመሥሪያ ቤቱ የተጎለቱ ባለጌዎች ዘመዶቻቸውን ሳይቀር አውሮፓና አሜሪካ ልከዋል። አንዳንዱ በህገ ወጥ ዶላር እያሸሸ ለዘመዱ አሜሪካ ውስጥ ቪላ ገዝቷል። ይህን ያህል ነው ኢትዮጵያ የተመዘበረችው። የዝርፍያው ፖለቲካ በፈጠረው ችግር ምክንያት ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ መብላት፣ መጠጣት እማይችልበት ደረጃ ደርሰው ሳለ ነው የብዙ ታጋዮች ውጤት የሆነው የመደመሩ ፍልስፍና ድንገት የበራው። ብርሃኑ ባለጌዎችን አሳውሯል። አውራ ሌቦቹም ከፍርሃት የተነሳ በተወሰነ አካባቢ ለመመሽግ ተገደዱ።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ “የቀን ጅቦች” ያሏቸው ቀልባሾች አስቀድመው የተደራጁ የማፍያ ቡድኖች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ሌቦች በርካታ ገንዘቦች፣ ትጥቆች፣ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎችና በየቦታው በጥቅም የገዟቸው አጋዥ ባለጌዎችን አቅፈዋል። ይህ የቅልበሳ ቡድን በወታደራዊ ሙያ የሠለጠኑ ግለሰቦችንና መቺ ኃይሎችንም አደራጅቷል። ዛሬ አይደለም የተደራጀው ገና አስቀድሞ “ነገም ሌላ ቀን ነው – ሳንቀደም እንቀድማለን” ብሎ ነው የተሰባሰበው። ፈላስፋው ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይላቸው በመደመሩ ዙርያ የተሰለፈው ሕዝብና ፍቅር ነው። ታላቁ መሪያችን ፍርሃታቸው ደግሞ ሕዝቡ የቀመሰው ፍቅርና ሕብረት እንዳይዛነፍ ከሁሉም በላይ ደግሞ ከፍ ያለችው ኢትዮጵያ ዳግም እንዳትቆዝም ነው። ትላንት መስቀል አደባባይ ላይ ቦንብ ያፈነዱ ዛሬ ደግሞ የሕዝብ ኃብት የሆኑትን ታላቁን ምሁር ኢንጂነር ስመኘው በቀለን የገደሉት የቀን ጅቦች ጥቃታቸውን በዚህ ያቆማሉ ማለት አይደለም። ስለሆነም፤

፩. ዶክተር አብይ በሂደት በየቢሮው የተሰገሰጉትን ሌቦች ማጥራት አለባቸው። በርካታ የተማረ ኃይል ስለሚኖር ሌቦቹ መሥፈርቱን ጠብቆ በሚቀጠሩ የሠራተኛ ኃይሎች ሊተኩ ይገባል። ይህ ድልድል እላይ በየደረጃው እስከተቀመጡት ባለስልጣኖች ዘንድ ሊደርስ ይገባል። እርሳቸው ይህን ሲያደርጉ የቀኝ ጅቦቹ በአስተዳደሩ ላይ ጥፋቶችን ሊፈጽሙ ስለሚችሉ በየቢሮው ያሉት አገልጋዮች ይህን ክፋት ሊቆጣጠሩ ይገባል።

፪. ሌላው ትልቁ ሥራ የሕዝብ ነው። ሕዝቡ በየቀበሌው በአዋቂዎች የሚመራ “የቀኝ ጅቦችን ውር ውር የሚቆጣጠር፣ “የመደመሩ ፍልስፍና አራማጆችና ፀረ–ቅልበሳ ኮሚቴ” ሊያቋቁሙ ይገባል። ይህ ትልቅ ጉዳይ እንደውም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቢታገዝ አባላቱ ከወንበሩ ይልቅ ለሃገር ደህንነት ቅድሚያ መስጠታቸውን ያሳያል። ሁሉም ነገር በስሜት ሳይሆን በጥበብ የሚራመድ ሊሆን ይገባል። ስሜት ብቻዋን ተሸናፊ ታደርጋለች። ሕዝቡ በጥበብ ከተደራጀ ዶክተር አብይ እንዳሉት ጸጉረ ለውጦችን መለየትና እንቅስቃሴአቸውን በአንክሮ መከታተል ይችላል። ፖሊስ በሕዝብ ተሳትፎ እየታገዘ እንደ መርካቶና ፒያሳ ያሉትን ሕዝብ የሚበዛባቸውን ቦታዎች ሠላም ለመጠበቅ በሙያ የታገዘ ሥራ ሊከውን ይችላል።

፫. የቀኝ ጅቦቹን ማንነት መለየት ዋናው ትኩረት መሆን ይገባል። ይህ በሙያዊ ክህሎት መመራት አለበት። ፖለቲካው ከብርሃን ፍጥነት ቀድሞ ኃብታም ያደረጋቸው ሰዎች ለቀኝ ጅቦቹ ድጋፍ ሊያደርጉ ይችላሉ። የቀኝ ጅቦች የዝርፊያው መቋረጥ ባስደነገጠው ባለሥልጣንም ሊታገዙ ይችላሉ። ይህን ሁኔታ እንደምን መቆጣጠር እንደሚቻል ምክክር ማድረግ ያስፈልጋል። የቀኝ ጅቦቹ በቂ ገንዘብ፣ ተሽከርካሪዎችና የጦር መሳርያዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ መገልገያዎች ስለሚኖሯቸው ከከተማ ከተማ መዞር ብቻ ሳይሆን በከፍተኛና ትናንሽ ሆቴሎች ውስጥም ሆነ ምስጢራዊ ቦታዎች እያደሩ ደብዛቸውን መሰወር ይችላሉ። የቀኝ ጅቦቹ የጦር መሳርያዎችንና ቦንቦችን ሊደብቁ ይችላሉ። ሕዝቡ በቡድን በቡድን ተደራጅቶ ፎቶግራፎችን ከማንሳት ጀምሮ የጠረጠርውን በጨዋ ሥርዓት አቁሞ መጥየቅ ይገባል። የቀን ጅቦቹ የሚፈልጉትን እቅድ እምሽት ላይ ሊነድፉ ስለሚችሉ ይህን የመከታተል ልዩ አቅምም ሊገነባ ይገባል። ሕዝቡን መደመሩን ከቅልበሳ ለማዳን ጥበባዊ እቅዶችን ከነደፈና በአመክኖዖ ከተመራ የቀኝ ጅቦቹ ሊጋለጡ ይችላሉ።

፬. ሕዝብ ዘራፊዎቹና ሌቦቹ የቀደዱትን የተንኮል ቦይ ተከትሎ አብሮ መፍሰስ የለበትም። ተንኮስ አድርገው ሕዝብ በስሜት ተነሳስቶ ጎጂ ነገሮች እንዲፈጽም ነው ፍላጎታቸው። የመደመሩ ፍልስፍና እንዲቀለበስ የቀኝ ጅቦቹ ሠላምን ለማደፍረስ በርካታ መላዎችን መንደፍ ይችላሉ። ልምላሜን ለማምጣት እውቀት ባይኖራቸውም እንኳን ድርቀትን ለማስፈን መላን አያጡም። የቀኝ ጅቦቹ አውራ አለቆች አንዳንዶቹ በልዋጭ ልዋጭና የልመና የሠፈር ስለላ ረገድ በቂ ሙያን ያካባቱ አልፎ ተርፎም በባለስልጣን ቤት ዘበኛ ሆኖ ተቀጥሮ በመስራትና ምስጢር በመጥለፍ ሥራ ከማንም በላይ የተካኑ ኋላም ለሃ ሰባት ዓመት “አንድ ላምስት በሚለው ጥርነፋና ከፋፋይ የክልል ፖለቲካ ታግዘው በማጋጨትና በማናቆር ሙያ ህዝብን ምን ያህል እንዳስጨነቁ የሚረሳ አይደለም። እነዚህ አውራ ሌቦች የመደመሩን ፍልስፍና ለማደናቀፍ የክፋት መላ በማውጠንጠን ረገድ አሁንም ቢሆን የማይናቅ እምቅ ችሎታ እንዳላቸው መዘንጋት አያስፈልግም።

የቀን ጅቦቹን ሻጥርና የግድያ ሤራ ማክሸፍ የሚቻለው የእነርሱን የክፋት ሥራዎች ተረድቶ ብሎም በጥበብ በልጦ በመገኘት ንቃትና በጠነከረ ህብረት ብቻ ነው። የቀኝ ጅቦች የሙስናውና ብልግናው ሥርዓት ልጆች ናቸው። ሥርዓቱን ለመመለሰ ቅልበሳ ማድረግ የሞት የሽረት ትግላቸው ነው። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የሚከወነው ኢትዮጵያን የማንሳትና ፍቅርን የማጎልበት ቅን ሥራ ለቀኝ ጅቦቹ ምን ያህል ውርደትና እፍረት መሆኑን ለማወቅ አንዳች ምርምር አያስፈልግም። የመደመሩ ፍልስፍና ለቀኝ ጅቦቹም ሆነ ለአውራ ሌቦቹ – በህይወት ሳሉ ሺህ ጊዜ መሞት – ማለት ነው። የቀኝ ጅቦቹ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለሱም። ይሁንና ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ አሸንፈው ዳግም የጨለማውን ዘመን መመለስ ከቶ አይችሉም። አርፈው ቢቀመጡ ለነሱም ሆነ ቤተሰቦቻቸው መልካም ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ግድያው በሕወሓት ደህንነት ተቋም የተቀናበረ ነው ፤ ኢንጂነር ስመኘው መገደሉን ተከትሎ የአማራ ተወላጆች ከግድቡ ስራ እየተባረሩ ነው። ሚኪ አምሐራ

1. ኢንጅነር ስመኘዉ ከመሞቱ አንድ ቀን በፊት ወይም አብይ ወደ አሜሪካ ከሚመጣበት አንድ ቀን በፊት ቤተመንግስት ከአብይ ጋር አንደነበር፡፡ በዚህም መቸም ሪፖርት ሲያቀርብ ያለበትን የደህንነት ወይም ከስራ ጋር በተያያዘ ከሰወች ጋር ያሉትን ግንኙነቶች አቅርቦ ይሆናል ተብሎ ይገመታል

2. አጠቃላይ ቤተሰቡ የደህንነት ችግር እንደነበረበት፡፡ ሚስቱ በደህንነቶች ግፊት እንደወጣች እና ልጆቹም በዛዉ ችግር ዉስጥ እንደነበሩ መረጃዉ ያሳያል፡፡ ሚስቱ አልደረሰችም ለማለት በነገዉ እንዲቀበር ተፈልጎ የነበረ ቢሆንም ቀብሩ ከተራዘመ በኋላ ካናዳ ያለዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዲስ ላይ እንድትገኝ ብዙ ሙከራወች አድርጎ እንዳልተሳካለት የሚሉ መረጃወች ደርሰዉኛል፡፡ ሰዉየዉ እና ቤተሰቡ ለምን በደህንነቱ ጫና ስር እንደወደቁም መጠየቅ አለበት፡፡ኢንጅነሩም ህይወቱ ላይ ችግር ሊደርስ እንደሚችል እና ልጆቹ ያለወላጅ ቢቀሩ ጠንካራ እንዲሆኑ እና ትምህርታቸዉ እንዳይስተጓጎል ይመክራቸዉ እንደነበር ተሰምቷል፡፡

3. ኢንጅነሩን ካስወገዱ በኋላ አባይ ላይ ያሉ ሰራተኞችን በገፍ እየቀነሱ ነዉ፡፡ ቅነሳዉ ደግሞ አማራ ላይ ያነጣጠረ ነዉ፡፡ በዚህ ሶስት ቀን ከ 50 በላይ አማራ በተለያዩ ዲፓርትመንቶች ከግድቡ ስራ እየተመረጡ ተቀንሰዋል፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉት 10 የኮኮት ሹፌሮች ሰሞኑን ከስራ ተቀንሰዋል፡፡ የሚገርማዉ በትጉህ ሰራተኝነት በቅርቡ የተሸለሙ ነበሩ፡፡ ከስሚንቶ እና ሌሎች የሃብት አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች መረጃወችን ሊያወጡ ይችላሉ የተባሉ አማሮች እየተለቀሙ እየወጡ ነዉ፡፡
1 ደጀኔ ማሞ የእንጅባራ ልጅ
2ንጉሴ አበበ የቡሬ ልጅ
3 መሀሪ ወርቅነህ የቻግኒ ልጅ
4 ይደግ ፈንቴ የቻግኒ ልጅ
5 አምደ ወርቅ የባህር ዳር ልጅ
6 አናጋዉ ይታየዉ የደምበጫ ልጅ
7 ባበይ ዋለልኝ የማርቆስ ልጅ
8 አህመድ አደም. የማርቆስ ልጅ
9. ዮሴፍ ፈንታሁን የአዴት ልጅ
10. ደምሳቸዉ ዘዉዴ የባህር ዳር ልጅ
በሌላዉ የስራ ክፍል ዉስጥ ያሉትን ይዠ እመጣለዉ ሚኪ አምሐራ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚዲያ ቢሮ ከፈተ!

እስክንድር ነጋ የሚዲያ ቢሮ ከፈተ!

ላለፉት 12 አመታት በህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ። በቅርቡም በተለያዩ የሚዲያ ውጤቶች ከህዝቡ ጋር ለመገናኘት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል…..ጋዜጠኞች ተሰባስበውም ኬክ በመቁረስ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል….ነፃው ፕሬስ ታፍኖ አይቀርም….የህዝብ አደራ አለብን!
ድል ለዲሞክራሲ!!

የለውጡ ማነቆዎች

ኢትዮጲያ የንጉሱን ስርአት አልፈልግም ብላ ከጣለች በሁዋላ በርካታ የፖለቲካ አመለካከቶችን እና ታሪካዊ ኩነቶችን አስተናግዳለች፡ ከያኔው ሶሻሊዝም እስከአሁኑ ግራ የገባው አቢዮታዊ ዲሞክራሲአዊ አስተዳደር ድረስ፡፡ ከንጉሱ ከዙፋን መውረድ ጀምሮ ሀገራችን በርካታ መልካም አጋጣሚዎችን ብታገኝም በተለያየ ሰአት ሀይልን ይዘው የነበሩ አካላት እንዲሁም ህዝቡ ሊወጡ የሚገባቸውን ሃላፊነት መወጣት ባለመቻላቸው ዛሬ ለደረስንበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ እንዲሁም ማህበራዊ ቀውስ ተዳርገናል፡፡ሆኖም ግን ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆናጠጠ ከ27 አመታት በኋላ በኢትዮጲያ ሰማይ ላይ የተሻለ የሚመስል የፖለቲካ ለውጥ እንቅስቃሴ በመታየት ላይ ነው፡፡ ጥያቄው ይህን መልካም አጋጣሚ እንደከዚህ በፊቶቹ ይባክናል ወይስ አንጠቀምበታለን ? ለውጡን ሊያደናቅፉ የሚችሉ ክስተቶች ከኢህአዴግ ከራሱ ውስጥ ወይስ ከውጪ የሚመጡ ናቸው የሚለው ነው፡፡

በእርግጥ የአሁኑ የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስደናቂ በሆነ መልኩ ህዝቡን ማነቀሳቀስ (መደመር) ችለዋል፡፡ ግን ግን ይህ የመደመር ፖሊሲ ወይም አስተሳሰብ ሀገሪቱን ከፍ ወዳለ ደረጃ ያደርሳታል ወይስ ግዜያዊ ስሜታዊነት ነው? የሚለው ሌላኛው መነሳት ያለበት ሀሳብ ነው፡፡እንደሚታወቀው የኢትዮጲያ ህዝብ በአብዛኛው በተለያዩ ከተሞች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን መቆሙን እና ለመደመርም ያለውን ፍላጎት በግልፅ አሳይቷል ነገር ግን እነዚህ የመደመር እና የድጋፍ ሰልፎች በሚያስደንቅ መልኩ ተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸው ማህበረሰቦች ያደረጉት ሰልፍ እንደሆነ እና ከኢትዮጲያዊነት ይልቅ ሁሉም የየራሱን የፖለቲካ እምነት ያራመደበት መሆኑን ለማወቅ ይዘውት የወጡትን ሰንደቅ አላማ መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡ ኢትዮጲያን እና ኢትዮጲያዊነትን የሚወክለው የትኛው እንደሆነ፤ ይህንን የተራራቀ አስተሳሰብ እንዴት ማስታረቅ ይቻላል የሚለው የአዲሱ ተቅላይ ሚኒስትር ዋነኛው የቤት ስራ እንደሆነ ለመገመት ምንም አይነት ቀመር አያስፈልግም፡፡ ሌላኛው እና ዋነኛው ጉዳይ እነዚህ ሰልፎች ላይ ታርጌት የተደረጉ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ እንዲሁም ብሄር ተኮር የሆነ ጥላቻን ያዘሉ መፈክሮች እና ንግግሮች ሌላኛው የሀገሪቱ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈተና ምንጮች እንደሚሆኑ ኣያጠራጥርም፡፡

የሆነው ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይዘውት የመጡት አዲስ አስተሳሰብ የሚደነቅ እና የሚበረታታ ነው፡፡ ሆኖም ግን የሚፈለገውን ሀገራዊ መግባባት እና ለውጥ ለማምጣት ከባድ ጫና እንደሚገጥማቸው ኣያጠራጥርም፡ ይኸውም፡-

1. አሁን ያለው የፌደራል መንግስት አደረጃጀት ብሄርን እና ቋንቋን መሰረት ያደረገ መሆኑ እና በዚህም ምክንያት በርካታ ኢትዮጲያዊያን በዘራቸው ምክንያት ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ እተፈናቀሉ መሆኑ፤ ለዚህም እንደማሳያ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ አማሮች፤ ከሶማሊ ክልል የተፈናቀሉ ኦሮሞዎች፤ከሲዳማ የተፈናቀሉ የወላይታ ተወላጆች፣ በጉጂ ህዝብ እና በጌዲኦ ህዝቦች፤ በጉራጌ እና ቀቤና ህዝቦች አጎራባች ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች የተከሰተው የህዝቦች መፈናቀል፡፡ ምንም እንኩዋን ይህ አደረጃጀት ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች መንስኤ ቢሆንም፤ በሀገሪቱ የሚገኙ አንድ አንድ ብሄረሰቦች ከዚህ የተሻለ የፌደራል ስርአት ሊኖር የችላል ብለው አለማመናቸው እና ለመቀበልም ዝግት የሌላቸው መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጀመሩት ለውጥ ትልቅ እንቅፋት ሊሆን መቻሉ አያጠራጥርም፡፡

2. የተጀመረው የመደመር እና የአንድነት ጉዞ አግላይ መሆኑ (ተገልያለው ብሎ የሚያምኑ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ብሎም ከኣንድ ብሄርተውጣጡ ልሂቃን መኖራቸው)፣ ወደፊት ከባድ መዘዝ ሊኖረው መቻሉ ሌላኛው የአዲሱ ለውጥ ማነቆ ሊሆን የመቻል እድሉ ቀላል አይሆንም፡፡

3. ሌላኛው እና ተጨማሪው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር፣ የፍቅር፣ እና የአንድነት ስብከት ውጪ እስከ አሁን ወደፊት ሊከተሉት አና ሊያራምዱት ሰለፈለጉት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ ለውጥ አቅጣጫ በግልፅ አለማስቀመጣቸው ቀጣይ የሀገሪትዋ እጣፈንታ ምን ሊመስል አንደሚችል መገመት አለመቻልም ተያይዞ ሊነሳ የሚችል ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡

4. አራተኛው እና ዋነኛው በስረዐቱ ውስጥ በተለያዩ የስልጣን እርከን ላይ ያሉ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ለውጡን ለመቀበል እና ለማቀላጠፍ ያላቸው ፍላጎት ሌላው እና ዋነኛው ማነቆ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ ባለፉተ 27 አመታት ለስልጣን መደላድል ያመቸው ዘንድ በምርጫ ቦርድ፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በክፍለ ከተማዎች፣ በቀበሌዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ውስጥ ዜጎች ባላቸው የትምህርት ዝግጅት እና ብቃት ሳይሆን ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት እና ወገንተኝነት ይኸውም የገዢው ፓርቲ አባል እና ደጋፊ መሆን እንደዋና መመዘኛ እየተቆጠረ ከመንግስት ስራ ይልቅ የፖለቲካ ተልእኮን እንዲያስፈፅሙ እና የአንድ ለአምስት የስለላ መዋቅርን እንዲያስፈፅሙ የተመደቡ ከመሆኑም በዘለለ ለእነዚህ የስርአቱ ደጋፊዎች ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማዘጋጀት ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሀብት ብክነትን አስከትለዋል እያሰከተሉም ነው፡፡

ነገር ግን ከአንድ አመት ከስድሰት ወር በዃላ ሀገራችን ቀጣዩን ምርጫ እንደማስተናገዷ መጠን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነፃ እና ፍትሀዊ ምርጫ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች ቢናገሩም፤ ከላይ የተጠቀሱት በተለየዩ የመንግስት ሀላፊነት ላይ ያሉት ግለሰቦች ለነፃ እና ፍትሀዊ ምርጫ ዝግጁ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ እና መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ ምክንያቱም የምርጫው ውጤት የመንግስትን ለውጥ የሚያስከትል ከሆነ ጥገኛ ባለስልጣናት እና አስፈፃሚ አካላት በትምህርት ዝግጅታቸው እና ባላቸው ልምድ የተሻሉ ለሆኑ ዜጎች ቦታቸውን ለመልቀቅ የገደዳሉ፡፡ በመሆኑም እነዚህ አካላት በአሁኑ ሰአት በትልቅ ስጋት አና ውጥረት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ አነዚህ ሰወች እስካሉ ድረስ በኢትዮጲያ ውስጥ ነፃ እና ፍትሀዊ ምርጫን መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዙሪያቸው ከፍተኛ ባለስልጣናትን የደህንነት ሀላፊውንም ጨምረው በሌሎች ቢቀይሩም በደህንነት እና በሰራዊቱ መዋቅር ውስጥ በግልፅ የሚታይ ለውጥን መፍጠር አልተቻለም ይህም ቀጣዩን ምርጫ ከባድ ከሚያደርጉ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውንም የመድብለ ፓርቲ ስርአት ከሚያዳክሙ ጉዳዮች ውስጥ በዋነኛነት ሊነሳ የሚችል ነው፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን የታየው የለውጥ ጭላንጭል እና ተስፋ ከባድ ፈተናዎች እንደሚጠብቁት መገመት ጨለምተኝነት አያሰኝም ይልቁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በዙሪያቸው የሚገኙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሊያስቡበት እና ትኩረት ሰተው ሊሰሩት የሚገባ የቤት ስራቸው መሆን አለበት፡፡
ቸር ያሰማን!!!
T. Feyissa Bedane, July 2018, Toronto

የ“ሲርት” ፖለቲከኞች (በመስከረም አበራ)

በመስከረም አበራ

Azeb Mesfin and TPLF

አስራ ሰባት አመት በዱር በገደል የታገሉት ህወሃቶች ደርግን የጣለው የእነሱ ጠመንጃ ብቻውን ይመስላቸዋል፡፡ይሄው ግማሽ እውነት ደግሞ ራሳቸውን ሁሌ ስልጣን ላይ መኖር የተገባቸው፣ አሸናፊነት ብቻ እጣ ፋንታቸው የሆነ ብቸኛ ሃያላን አድርገው እንዲያስቡ ሳያደርግ አልቀረም፡፡ ይህ ስህተት ስህተትን እየወለደ ሄዶ ከስልጣን መውረድ፣ከአድራጊ ፈጣሪነት መጉደል ሊመጣ እንደሚችል እንዳያስቡ እና አሁን ላሉበት ሁኔታ የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዳያደርጉ ከልክሏል፡፡ ጠመንጃ ወደ ስልጣን መምጣት ያስችል ይሆናል እንጅ ስልጣን ላይ እንደማያኖር መረዳት አልሆን ያላቸው ህወሃቶች ባላሰቡት ብቻ ሳይሆን ባላሰብነው መንገድ ብቻቸውን ሃገር ከመዘወሩ ገለል ብለዋል፡፡እውነቱን የተቀበሉት ግን አይመስልም፡፡

እንደ ህወሃት ያለ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ፣ስልጣን ላይ ተወዝቶ ስር የሰደደ ፓርቲ እንዲህ በቀላሉ እንደጉም ብን ብሎ ከመንበር ይታጣል ብሎ መገመቱ ራሱ ከባድ ነበርና ህወሃትም ይህን መቀበል ቢያስቸግረው አይፈረድበትም፡፡ በዚህ ላይ የኢህአዴግን ስጋ ለብሶ ሁሉን የሚያደርገው ህወሃት አጥብቆ ይመካ የነበረው አለቅነቱን በግድ በጫነበት ኢህአዴግ ውስጠ- ፓርቲ አንድነት ነበር፡፡

በህወሃት የበላይነት ሳይነጋገር ተስማምቶ ለጥ ሰጥ ብሎ በሚገዛው የአጋር እና አባል ፓርቲ ካድሬ አስተማማኝ ባርነት አጥብቆ የሚመካው ህወሃት ነግ በእኔ ሳይል በተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደ አክርማ መሰንጠቅ ይስቅ ነበር፡፡በጌታ-ሎሌ ግንኙነቱ የቆመውን ‘ውስጡን ለቄስ’ የነበረውን የፓርቲውን አንድነት የፓርቲ ዲስፕሊን በማጎልበት ይተረጉመው ነበር፡፡ ህወሃት ያለ አባል ፓርቲዎች  እኩልነት አንድነት አመጣለሁ ብሎ ማመኑ ድንገት ሞቶ መገኘትን አመጣበት፡፡ ይህን ማመን ህወሃትን ሆነው ሲያስቡት ከባድ ነው፡፡

ህወሃትን የመሰለ ሁሉን በጉልበት ማድረግ የሚቀናው፣ፈርጣማ ፓርቲ ገፍትሮ ለመጣል ከህዝብ የተፋፋመ ትግል ጋር የወገኑት አዲሶቹ የኢህዴድ አመራሮች ድፍረታቸው የሚደነቅ ነው፡፡ በህወሃት ቤት ማደጋቸው የፓርቲውን የቤታቤት ደባ፣ሼር እና ተንኮል በደንብ መረዳት ስላስቻላቸው የህዝብ ትግል ወዝውዞ ወዝውዞ ባደከመው ህወሃት ላይ የመጨረሻውን ሃይለኛ ምት ሰንዝረዋል፡፡ ውድቀቱ ከወደ ብረት አንጋች ተገዳዳሪዎቹ መንደር(በተለይ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት) ብቻ እንደሚመጣ ይጠብቅ የነበረው ህወሃት ይህን ድንገቴ የማንጅራት ምት መቋቋም አቅቶት ተሽመድምዷል፡፡

ህወሃት የመጨረሻ የውድቀት ደወሉን የደወለው አቶ ኃ/ማርያምን ተለማምጦ ስልጣን ላይ ለማቆየት ኩራቱ በጄ ያላለው ጊዜ ነው፡፡በህወሃት ነቃፊዎች ዘንድ የዓለምን ውርጅብኝ እያስተናገዱም ቢሆን ‘አቤት ወዴት’ ሲሉ የኖሩትን አቶ ኃ/ማርያምን ክፉኛ ያስከፋው ህወሃት ሰውየው በእጁ እያሉ ለሚፈልገው በሰው ክንድ የአዞ ጉድጓድ የመለካት ፖለቲካ የሰጡት ጥቅም አልታየውም ነበር፡፡

ባልጠበቀው ሁኔታ፣ኦህዴድ ክፉኛ ባንጓጠጠበት ወቅት፣በሃገር ዳርቻ በተነሳ ተቃውሞ ወንበሩ እንደወተት እየተናጠ ባለበት ወቅት በአደገኛ መገጣጠም ስልጣን በቃኝ ያሉትን አቶ ኃ/ማርያምን በግማሽ ቀን ሲያሰናብት የሚመጣውን አላመዛዘነም፣ያንዣበበት አደጋ አቶ ኃ/ማርያምን ከመለመን የበለጠ መዘዝ እንደሚያመጣበት አላሰበም ነበር፡፡ የአቶ ኃ/ማርያምን መነሳት ተከትሎ በመጣው ውስጠ-ፓርቲ ጉሽሚያ ባለጠመንጃው ህወሃት በባለ ብዙ ህዝቡ ኦህዴድ መሸነፉ ለሽንፈት ተዘጋጅቶ ለማያውቀው ህወሃት ሊዋጥ የማይችል እንደ ህልም ያለ ነገር ነው፡፡

ህወሃት ባላሰበው አቅጣጫ የመጣበት ምት ስልጣኑን እንዳሳጣው ለመረዳት ብቻ ሳይሆን ሽንፈቱን ለመቀበልም ያስቸገረው ይመስላል፡፡ በፍጥነት እየተቀያየረ ያለውን የሃገራችን ፖለቲካ ጭራ ለመያዝም ግር እንዳለው ያስታውቃል፡፡ ፈጣኑ የፖለቲካ ሁነት በመንገዱ ሁሉ የህወሃትን ስር እየነቀለ የሚሄድ መሆኑ ግርታውን አብሶታል፣የሚይዝ የሚጨብጠውን አሳጥቶታል፡፡ለወትሮው ሲያሾረው የነበረው ኦህዴድ የማይጋፉት ባለጋራ ሆኖበታል፡፡ ብአዴንም የድሮው አይደለም፡፡     ቀን ከዞረበት ጋር ጉዳይ የሌለው የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡም ከአሸናፊው ጋር ሽው እልም እያለ ነው፡፡

ልክ ባልሆነ ከመጠን ያለፈ የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ሰክሮ የኖረው ህወሃት ሽንፈትን መቀበል በራሱ ችግር እንደሚሆንበት ባያጠራጥርም እንደ ባዶ እቃ እየሞላ የፈለገውን ሲያደርጋቸው ከነበሩት ገባር ፓርቲዎች የመጣበትን ሽንፈት እንዲህ በቀላል ተቀብሎ እኛ እንደምናስበው ሟሽሾ እንደማይቀር መገመት ደግ ነው፡፡ገሃድ የሆነውን የፖለቲካ ስልጣን ቢያጣም በስልጣን ላይ ስር ሰዶ እንደ መኖሩ የልቡን ባያደርስለትም፣የንዴቱን ያህል ባይሆንም አንዳንድ ከፀጥታ እና ደህንነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍጠር የሚያስችል ጉልበት አያጣም፡፡

ይህ ከህወሃት የአልሸነፍ ባይ እልኽኝነት፣ስር ለስር ሄዶ የጨለማ ስራ የመስራት ልምድ እና በአመዛኙ ወታደራዊ ማንነት ውቅር ጋር ሲዳመር የሃገራችን መከራ በምናስበው ፍጥነት እንደማያበቃ ያመላክታል፡፡በሌላ በኩል ቁጣው በነደደው ህወሃት ተቃራኒ የቆመው የጠ/ሚ/ር አብይ አስተዳደር ህወሃት በማያውቀው የሲቪል እና ይቅር የመባባል ቋንቋ ብቻ አነጋግሬ ህወሃትን ገራም አደርጋለሁ ባይ ነው፡፡

ይህ ነገር ሁለት ቋንቋቸው የማይመሳሰል ሰዎች በየቋንቋቸው ሲያወሩ የሚፈጠረውን ነገር ይመስላል፡፡ ለህወሃት አይሆኑ ሆኖ ያኖረውን ወንበሩን የቀማው ሰው በምንም ቋንቋ ቢያናግረው ለበጎ መስሎ አይሰማውም፡፡ ለህወሃት መልካም የሆነችው አብሮነት እሱ ወንበሩ ላይ ሆኖ ሌሎች ወረድ ብለው ቆመው የምትደረገዋ ነች፡፡ያለ እንደዚህ ያለች አብሮነት ሃገርም ብትሆን በህወሃት ልቦና ትርጉም የላትም፡፡ አብይ ደግሞ “ሊያስሩኝ ይፈልጉ ነበር” ያሏቸውን ህወሃቶችን ዝም ብሎ በመተው ብቻ ፍቅርን ለህወሃት ማስተማር ይቃጣቸዋል፤ህወሃትን ህወሃት ያደረገውን የውድድር፣የበቀል እና ሁሌ የማሸነፍ ማንነት እንዲህ ባለ መንገድ የሚቀይሩ ይመስላቸዋል፡፡የትግራይን ህዝብ ደህንነት ማንም እንዳይጋፋ በማሳሰብ ብቻ በግድም በውድም ህወሃት በትግራይ ምድር የገነባውን ተቀባይነት ሊገዳደሩ ይሞክራሉ፡፡

በህወሃት ባህል ይህ ሁሉ ዋጋ ያለው አይመስለኝም፡፡ ህወሃት የሚያውቀው ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ነው-ማሸነፍ ወይ መሸነፍ፡፡ ማሸነፍ የእሱ ነው መሸነፍ ደግሞ የሌላ! ስለዚህ ጠ/ሚ አብይ ዛሬ ያሸነፉት ለህወሃት ብቻ የተሰጠውን ማሸነፍ ሰርቀው ነው፡፡ በተሰረቀ የማሸነፍ ሜዳ ላይ ቆመው የሚያናግሯቸው ዶ/ር አብይ የመደመር ሆነ የፍቅር፤ ሃገር ማዳን ሆነ የፍትሃዊነት ቋንቋ ለህወሃቶች እንደ ሚንሿሿ ፀናፅል ትርጉም አልቦ ነው፡፡ ማሸነፋቸውን ከሰረቃቸው ሰው ጋር መደማመጥ ለዘመናት ሲገነቡት የመጡትን፣ደርግን በማሸነፍ ደግሞ “ያረጋገጡትን” መሰረታዊ የአሸናፊነት ስነ-ልቦናቸውን የሚገዳደር አካሄድ ነው፡፡በህወሃቶች እሳቤ አሸናፊ ማለት እነሱ በአሸናፊነታቸው ዘመን እንደሚያደርጉት ባለጋራውን ለቃቅሞ የሚያስር፣የሚገድል፣የሚገርፍ፣የሚሳደብ፣የሚያሰድድ ነው፡፡

ይህን ያላደረጉት አብይ በህወሃቶች ዘንድ  አሸናፊ ናቸው ተብለው ይቆጠሩ ዘንድ የሚሆን አይመስለኝም፡፡ አሸናፊ፣ጉልበታም ማሰር እየቻለ ነገር ግን መንግስትነቱን በሚመጥን ማስተዋል አስተውሎ፣ የቂም በቀልን፣ የጥርስ መናከስ ፖለቲካዊ ባህላችንን የሆነቦታ ለመስበር ሲል ብቻ ማሰር የሚገባውን ላያስር እንደሚችል በህወሃቶች ዘንድ ግንዛቤው ያለ አይመስለኝም፡፡ አዲስ ባህል ሊያመጡ የሚቸገሩት ጠ/ሚ/ር አብይ የገጠማቸው ትልቅ ፈተና ቋጠሮው ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ አብይም የህወሃትን ነገራ ነገር አይተው የመደመር ፍልስፍናቸው በተደማሪው ሁሉ ዘንድ እሳቸው የሚሰጡትን (ከነተበው ፖለቲካችን የመውጣት መንገድ አይነት) ትርጉም ብቻ ሊይዝ እንደማይችል የተረዱ አልመሰለኝም፡፡በሁለት አካላት ዘንድ የሚደረግ የመስተጋብር ዘይቤ አንደኛው አካል የተረዳበት አረዳድ መልካም ስለሆነ ብቻ መልካም ፍፃሜ ላይኖረው ይችላል፡፡

የጠ/ሚር አብይ የመደመር ፍልስፍና የ “ኑ ተደመሩ ግብዣ” ለቀረበለት ህወሃት የሚሰጠው ትርጉም ፍፃሜውንም ሆነ ሂደቱን በመወሰን ረገድ ከፍ ያለ ሚና አለው፡፡ ህወሃት የፖለቲካ ስልጣን ላይ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይም ተንሰራፍቶ የኖረ ሥረ-ብዙ ፓርቲ እንደመሆኑ ስልጣንን አጥቶ ለመደመር ያለው ዝንባሌ ለወደፊቱ የፖለቲካችን ጉዞ የማይናቅ ሚና አለው፡፡ በተመሳሳይ ጠ/ሚር አብይ ህወሃትን ጨምሮ የመደመር ፍልስፍናቸው ለማይዋጥላቸው አካላት ተለዋጭ መላ መዘየዱን መርሳት የለባቸውም፡፡ እንጂ እሳቸው ያመጡት (ብዙዎችም የወደዱላቸው) የመደመር ፍልስፍና እንደ አየር ሁሉም ደስ እያለው ይስበዋል ብለው ማሰብ የለባቸውም፡፡ በጎ ነገርን ለመቀበል በጎ ማንነት ያስፈልጋል፡፡ በጎነት ሁሉ ስልጣን ላይ መውጣት ብቻ የሚመስለው ህወሃት ደግሞ ስልጣኑን ጥሎ የሚያነሳው ምንም ምድራዊ ስጦታ የለም፡፡ስለዚህ የከዳውን የስልጣን ገድ ለመፈለግ የሚማሰውን ሁሉ ይምሳል፤የሚጎነጎነውን ሁሉ ይጎነጉናል፤ ሚሴረውን ሁሉ ያሴራል፤ ለዚሁ ይረዳኛል ያለውን የክፉ ቀን ወዳጅ ሁሉ ይጠራል፡፡

በድንገት የቆመበት መሬት እየተናደበት ያለው ህወሃት እንደፈለገ ሲያደርጋት የኖረውን ሸገርን ለባለ ጊዜ ሰጥቶ መቀሌ መሽጓል፡፡ በመቀሌው የድንጋጤ ቁዘማ የተሰየመው ግን ህወሃት ብቻውን አይደለም፡፡ ለወትሮው ህወሃትን በሰብዓዊ መብት ረጋጭነቱ፣በአምባገነንነቱ፣ በሙስናው ህዝብን በማስመረር ሲከሱት የነበሩት የቀድሞ አባሎቹ አይተ ግደይ ዘርዓፅዮን እና ዶ/ር አረጋይ በርሄ፣ተቃዋሚ ነን ብለው አረና ትግራይን የመሰረቱ አመራሮች፣አቶ መለስ አፈር ሳይጫናቸው ከህወሃት ተሰነጠርን ያሉ ግለሰቦች እና ሌሎች ትግራዊያን ሁሉ ከህወሃት ጋር ለስብሰባ ተሰይመዋል፡፡

እነዚህ በህወሃት ጭንቅ ጊዜ ከበውት ስብሰባ የተቀመጡ ሰዎች ከትግሬነታቸው በቀር ከህወሃት ጋር የሚያዛምዳቸው ነገር ግልፅ አይደለም፡፡ ሁሉም በሚባል ሁኔታ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ህወሃትን በዘረፋ እና ኢ-ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በማስፈን የሚከሱት ነበሩ፡፡አብሮ ስብሰባ ለመቀመጥ የሚያስችል የቀደመ ይፋዊ ውይይት አድርገው እንደሁ ግልፅ ያደረጉት ነገር የለም፡፡አሁን የሚያደርጉትም ህወሃት የቀድሞ ስህተቱን አምኖ ወደፊት አብሮ ለመስራት የሚያስችል ድርድር ለማድረግ እንደሆነ የተነገረ ነገር የለም፡፡ከዚህ ይልቅ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ የህወሃት የወንጀለኝነት ምልክት ተደርጎ በሚወሰደው ኢፈርት እጣ ፋንታ ላይ መምከር አንዱ የስብሰባቸው አላማ እንደሆነ ነው ከገለልተኛ ምንጮች እየተዘገበ ያለው፡፡

በግል ትዝብቴ ከአቶ ገብረመድህን አርአያ በቀር የኢፈርትን ወንጀል-ወለድ ድርጅትነት እና የህወሃት የአድሎ ምልክትነት አንስቶ ሲያወግዝ የሰማሁት የትግሬ ፖለቲካኛ፣አክቲቪስትም ሆነ ልሂቅ አላጋጠመኝም፡፡በተቃራኒው በሌላ ጉዳይ ህወሃትን የሚያብጠለጥሉ የትግሬ ፖለቲከኞችም ሆኑ አክቲቪስቶች በኢፈርት ጉዳይ ላይ ወይ የትግራይ ህዝብ አንጡራ ሃብት እንደሆነ ፈርጠም ብለው ይናገራሉ አለያም፤ ለትግራይ ህዝብ ሳይሆን ለህወሃት በመጥቀሙ ይቆጫሉ፤ ካልሆነም ኢፈርትን መንካት የትግራይን ህዝብ የሚያስቆጣ መዳፈር እንደሆነ ያስጠነቅቃሉ፡፡የአሁኑ ከምድር ዳርቻ መቀሌ ላይ  ከትሞ የኢፈርትን እጣ ፋንታ ለመወሰን መሟሟቱ የኢፈርትን አፈጣጠር ጤናማነት በወል የመቀበሉ ቅጥያ ነው፡፡

ኢፈርት የተፈጠረው በዘረፋ፣ ቆሞ የሚሄደውም የኢትዮጵያ ህዝብ ለፍቶ ወይ በስሙ ተለምኖ በሚመጣ ዶላር  በሚንቀሳቀሱ ባንኮች ላይ በሚደረግ ደባ እንደሆነ ህወሃት ላልሆኑት ዛሬ ህወሃትን ከበው መቀሌ ለከተሙት ምሁራን፣ታላላቅ ሰዎችም ሆነ ወጣት ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች የሚጠፋቸው ጉዳይ አይደለም፡፡ትክክል መስሎ የተሰማቸው በወንዛቸው ልጆች በእነሱ ቀየ የተደረገ ነገር ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ ተመሳሳዩ በሌላ ቦታ ቢደረግ ኖሮ ለእሪታው የሚቀድማቸው እንደማይኖር የመንደራቸው ጥቅም የተነካ ሲመስላቸው በሚያሰሙት ሮሮ አንፃር መገመት አይቸግርም፡፡

በሃገራዊ ደረጃ ተደመሩ በሚለው የዶ/ር አብይ ብሄራዊ ጥሪ ሰበብ መጥተው ከህወሃት ጋር ለመደመር መቀሌ ያቀኑት የትግራይ ተወላጅ ጉምቱ ፖለቲከኞች ስብሰባ የተቀመጡት እንደፓርቲ  ወንጀለኝነትን ከጠገበው ህወሃት ጋር ነው፡፡በግል ደግሞ ማዕከላዊው መንግስት በወንጄል ሲፈልጋቸው አሻፈረኝ ብለው ወደ ትውልድ ቀያቸው ከኮበለሉት እስከ ህወሃት ከወረደ ስልጣን ላይ አልቀመጥም ብለው ስልጣን ካስረከቡት የህወሃት አባላት ጋር ነው፡፡ ግፋ ሲልም በትግራይ ቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው ጥፋቱ ምን እንደሆነ ግልፅ ባልሆነው ጠ/ሚ አብይ ላይ ውግዝ የሚያወርድም አለ፡፡ አብይ ቢያጠፉ ቢያጠፉ ከህወሃት የበለጠ ያጠፉት ነገር አይኖርም፡፡ለዲሞክራሲ፣ለህግ የበላይነት እና ነፃነት እንታገላለን ይሉ የነበሩት ስደተኛ ፖለቲከኞች የህግን ጥሪ አሻፈረኝ ካለ ሰው ጋር ምን እንጋራን ብለው እንደተቀመጡ ብቻ ሳይሆን ቀድሞስ ከህወሃት ጋር ተጣላን የሚሉት ለምን እንደሆነ ግር ያሰኛል፡፡

በመደመር ስም ወደሃገር ቤት የመጡ ስደተኛ ፖለቲከኞች ምን እየሰሩ እንደሆነ ነገሬ ብሎ የማይከታተለው የዶ/ር አብይ መንግስትም እኩል ግር ያሰኛል፡፡ኢትዮጵያን ሁሉ የሚያስተዳድረው የዶ/ር አብይ መንግስት መቀሌ ወርዶ በወንጄል የሚፈለጉ ግለሰቦችን ማምጣት ካልቻለ እንዴት በብዙ ሊታመን ይችላል? በዚህ ሁኔታ ህወሃት ከስጣን ገለል በማለቱ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ የተፈጠረው ተስፋስ እንዴት ሊፀና ይችላል?

ከፅንሰት ውልደቱ ጀምሮ ትግራይን እስከመገንጠል በደረሰ አክራሪ የትግራይ ብሄርተኝነት የሚታወቀው ህወሃት በስልጣን ዘመኑ ሁሉ የትግራይ ህዝብ እና ህወሃት አንድ ነው ሲል ኖሯል፡፡ የትግራይ ህዝብ ደግሞ ለዚህ ያለውን መልስ በገሃድ ወጥቶ ተናግሮ አያውቀምና ‘አንድ ነው አይደለም?’ የሚለው ክርክር የሚደራው በትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች እና አክትቪስቶች እንዲሁም ትግሬ ባልሆኑ የሃገራችን ፖለቲከኞች እና በህወሃት መሃል ነው፡፡ ህወሃት ‘የትግራይ ህዝብ እና እኔ አንድ ነን’ ሲል ቀደም ብለው የተጠቀሱት ፖለቲከኞች ደግሞ የለም የትግራይ ህዝብ እና ህወሃት አይገናኙም ይላሉ፡፡ ከባለቤት የወጣ ነገር በሌለበት የትኛው ክርክር እውነታውን ወካይ እንደሆነ ለማወቅ አዳጋች ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ህወሃት የስልጣኑ መሰረት ሲያረገርግ ወደ ትግራይ መንጎዱ ቀድሞም ‘እኔ ህዝብ ነኝ ህዝቤም እኔ ነው’ ሲል ከኖረው ነገር ጋር በደንብ ይገጥማል፡፡

ይህ ነገር የማይረታውን የህዝብ ትግል ለማሸነፍ ሲንተፋተፍ ኖሮ በስተመጨረሻው ተስፋውን ወደ ትውልድ መንደሩ ወደ ሲርት ያደረገውን አምባገነኑን የሙአምር ጋዳፊን መጨረሻ ያስታውሳል፡፡ ጋዳፈ ተስፋ ያደረጉበት የሲርት ህዝብም ባለው አቅም የለውጥ ሃይሉን በመፋለም ለሰውየው የስልጣን እድሜ መራዘም አጋርነቱን አሳቷል፡፡ዝምታው የበዛው እና ከስንት ዘመን በሀኋላ አደናጋሪ ሰልፍ እያደረገ ያለው የትግራይ ህዝብ መቼ ምን እንደሚያደርግ ማወቅ ባይቻልም ህወሃት ግን ጨራረሱን እንደ አጀማመሩ ወደ ትውልድ መንደሩ በማድረግ እስትንፋሱን ለማቆየት ያሰበ ይመስላል፤በትውልድ ቀየው ከወንዙ ልጆች ጋር መክሮ ሞቱን በህይወት ለመቀየር፣ዳግም ለማንሰራራት ማሰቡም የማይጠበቅ አይደለም፡፡ህወሃት ሲዳከም ህወሃትን ተክቶ የትግራይን ህዝብ ከመጣው አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ጋር ማላመድ፣የትግራይ ህዝብንም (እንደሚባለው ከህወሃት የሚለይ ከሆነ) ከኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ጋር ማሰለፍ ይገባው የነበረው አረና ትግራይ የተባለው ፓርቲም ፀሃይ ከጠለቀችበት ህወሃት ጋር በር ዘግቶ መቆዘሙን መርጧል፡፡

የዶ/ር አብይ መንግስትም ለህግ እምቢኝ ባይ የህወሃት ባለስልጣናትን  ትግራይ ዘልቆ ከህግ በላይ አለመሆናቸውን ለማሳየት አቅም ይጠረው፣ ፍላጎት አይኑረው፣ በይደር ያቆየው በውል የታወቀ ነገር የለም፡፡ ሆኖም ዶ/ር አብይ እነዚህን አሻፈረኝ ባይ ባለስለጣናት ከመቀሌ አምጥቶ በሚፈልጋቸው ህግ ፊት ለማቆም የትግራይን ህዝብ ቅዋሜ እንደፈራ ከሰሞኑ ከዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር ባደረጉት ንግግር ላይ ጠቆም አድርገዋል፡፡ይህ ነገር ዶ/ር አብይ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵዊ  የትግራይ ህዝብ የህወሃቶችን ክፉ እንደማይወድ እንሚያስቡ ያመላክታል፡፡

ከሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለየ ህወሃት ጥፋተኝነቱ እየታወቀ ሳይቀር ቆምኩለት ባለው ህዝብ ዘንድ ግዙፍ  ተቀባይነት ያለው ፓርቲ ከመሆኑ አንፃር የዶ/ር አብይ ንግግር ስህተት የለውም፡፡ይህ ንግግራቸው ዶ/ር አብይ ለአብሮነት ሲባል የሚያደርጉትን እላፊ መጠንቀቅ ቢያሳይም ስህተት ግን አለው፡፡የትግራይ ህዝብ በህግ የሚፈለግ ሰው እንደማናቸውም ሰዎች ዝም ብሎ ካልተንጎራደደ ብሎ የመቀየም መብት የለውም፡፡ የትግራይ ህዝብ እውን በዚህ ጉዳይ ይቀየማል ወይ በሚለው ጉዳይ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም የሚቀየም ከሆነ ቅያሜው ህጋዊነትም አግባብነትም ያለው ነገር አይደለም፡፡

በአሁኑ ወቅት መቀሌ የሰፈሩ ከስልጣን ተነሽ የህወሃት የቀድሞ ባለስልጣናት አንዳንዶቹ ቢሮ ለማስረከብም አሻፈረኝ እንዳሉ ነው የሚነገረው፡፡ይህን የልብ ልብ የሰጣቸው ምንድን ነው? ብሎ መመርመሩ አይከፋም፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት ህወሃት ወንበር ላይ ተወዝቶ ብዙ በመኖሩ በቀላሉ እፍ ብለው የማያጠፉት  ቅሪት ተፅዕኖ ሃያልነት ነው፡፡ህወሃቶች የተካኑበት በድለው እንኳን የተበደሉ ያህል ገርፎ የመጮህ ልማድ እውነትን የያዘን ሰው ሳይቀር የተሳሳተ መስሎት  ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፡፡ጠ/ሚር አብይ በዚህ ነገር ሳይቸገሩ አይቀሩም፡፡

አብይ እንደ መንግስት በሚያደርጓቸው የህወሃትን ጥግ የነካ የጥቅመኝነት ዝንባሌ የሚነኩ ውሳኔዎች ሳቢያ በህወሃት እና ጋሻ ጃግሬ እህት ድርጅቶቹ ካድሬዎች የድርጅት ግምገማ እና ስብሰባ ወቅት መብጠልጠላቸው አይቀርም፤አልፎ ተርፎ የድርጅት ኪዳን በመብላት ሊከሰሱ ይችላሉ፡፡መንግስትን ይመራል የሚባለው የፓርቲያቸው ዘይቤ ደግሞ ለዚህ ይረዳል፡፡ ይህ ደግሞ አብይ ከድርጅት መንፈስ ውጭ እንደ መንግስት በሚያደርጓቸው ውሳኔዎች ላይ እንደልባቸው እንዳይሆኑ ማድረጉ አይቀርም፡፡በዚህ ምክንያት ህዝብ እንደሚጠብቀውም ዶ/ር አብይ ራሳቸው እንደሚመኙትም ለመራመድ ፈተና ይሆንባቸዋል፡፡

ሁለተኛው ምክንያት ህወሃት በትግራይ ክልል ሰፊ ተቀባይነት ያለው ፓርቲ መሆኑ ነው፡፡በዚህ ምክንያት የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች የፌደራል መንግስት ተፈላጊ የህወሃት ባለስልጣናትን ለመያዝ የሚያደርገውን ጥረት ከልባቸው ላያግዙ ይችላሉ፡፡ አልፈው ተርፈውም ለመከላከል ሊሞክሩ ይችላሉ፡፡ኤፍ.ቢ.አይ ባጣራው መረጃ መሰረት ደግሞ አዲስ አበባ ያሉ ባለስልጣናትም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡እነዚህን ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ህጋዊ በሆነ መንገድ በፍትህ ፊት እንዲቆሙ ለማድረግ የአብይ የፀጥታ ሃይሉን የማዘዝ ጉልበት ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ቀስ በቀስ ጉልበቱን እያበረታ እንደሆነ ከሚደረጉ ሹም ሽሮች መረዳት ቻላል፡፡

ሆኖም ህወሃት ለረዥም ዘመን የፀጥታ ሃይሉን ቀፍድዶ የመቆየቱ ነገር ከገሃዱ ስልጣን ወርዶ እንኳን ለረብሻ የሚሆን ጉልበት እንዳያጣ ሊረዳው ይችላል፡፡ በዚህ ላይ የሰሜን ዕዝ እና የማዕከላዊ እዝ ሰራዊት ትግራይ መከተማቸው፣የእዝ አዛዦቹም ከህወሃት ሊወግኑ የሚችሉ ሰዎች መሆናቸው፣የደብረዘይቱ የአየር ሃይልም በከፊል ወደ መቀሌ እንደተጓዘ ከሚነገረው ጋር ተደምሮ አብዝተው በወታደራዊ ጉልበት ለሚያምኑት ህወሃቶች የልብ ልብ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡

ሶስተኛው ምክንያት ህወሃት በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ኦሮሚያ ክልል በአልገዛም ባይነት ሲያስቸግረው እንደነበረ፤ኦህዴድም በሌሎቹ እህት ድርጅቶች መጠን ገራም ሎሌ እንዳልነበረ  (መለስ ሳይሞቱ ጭምር አንዳዴ ሲያስቸግር እንደነበረ ይታወቃል) እና ይሄው እርሾ አድጎ እነ ለማ/አብይን እንደወለደ ስልጣን ለማይጠግቡት ህወሃቶች በቁጭት እና በቂም የሚታሰብ ሃቅ ነው፡፡ስለዚህ ዛሬ ቀን ተቀይሮ ኦህዴድ ባለ ወንበር ሲሆን ህወሃቶች ደግሞ ወደ ትውልድ ቀያቸው አቅንተው ትግራይ ክልል ደግሞ በተራው ለኦህዴድ ዙፋን የማይመች ሁከተኛ ቀጠና(Restive political zone) ሊያደርጉት ሊመኙ ይችላሉ፡፡

ኦህዴድ ወደስልጣን ሳይወጣ  በኦሮሚያ ካለው ተቀባይነት ይልቅ ህወሃት ከስልጣን ወርዶም ሆነ ስልጣን ላይ እያለ ትግራይ ውስጥ ያለው ተቀባይነት ላቅ የሚል መሆኑ ለዚህ እሳቤው ማገር ሊሆን ይችላል፡፡ ከኤርትራ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ እንደሚደረግ የሚታሰበው የድንበር መካለል በኢሮብ ህዝቦች ላይ ሊያመጣ የሚችው ተፅዕኖ ደግሞ ህወሃት ስልጣኑን በማጣቱ የሚያደርገውን የማጯጯህ አካሄድ ለህዝብ የማሰብ መጋረጃ ሊሰጥለት ይችላል፡፡ህወሃት ብቻ ሳይሆን የህወሃትን ስልጣን ላይ መቆየት ለማይጠላው ዘረኝነት ሽው ያለበት ሁሉ የድንበር ማካለሉ ነገር ሰም ሆኖ ለወርቁ (የህወሃት ከስልጣን መታጣት ሃዘን) ጮክ ብሎ  እንዲያለቅስ ያግዘዋል፡፡

ከዚሀ በተጨማሪ ዋነኛ መነጋገሪ ነጥብ የሚሆነው የዶ/ር አብይ የመደመር እና የይቅርታ ፍልስፍና የህግ የበላይነትን ከማስከበር እና ወንጀለኞችን በህግ ፊት ከማቅረብ ጋር ያለው ፍቅር እና ጠብ እንዴትነት አለመታወቁ ነው፡፡ወንጀል የሰራ ሰው በህግ ፊት ቀርቦ ህጋዊ የእርምት እርምጃ ሊወሰድበት ግድ ነው፡፡ይህ ካልሆነ ወንጀለኞች ቀድመው በሰሩት ወንጀል አለመጠየቃቸው አንድ ጥፋት ሆኖ በህግ ጥላ ስር አለመሆናቸው ተጨማሪ ጥፋት እንዲስከተሉ ያግዛቸዋል፡፡በጉጉት የምናየውን የለውጥ ሂደት እስከማደናቀፍም ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ‘እኔ ከሌለሁ ትፈራርሳላችሁ’ እያለ ሲያስፈራራ የኖረው ህወሃት እሱ ሳይኖር ሃገር በተቀበለችው መሪ ተሰትራ ስትመራ ማየት ደስ ላይለው ይችላል፡፡

አብሮነት በመዝራቱ፣ከዘረኝነት ጋር በመፋለሙ፣ህዝብን በማክበሩ፣ስልጡን ፖለቲካ ለማምጣት በመድከሙ ጠ/ሚ አብይ አጠገብ ለመድረስ የሚያስችል ማንነት እንደሌለው ህወሃት አሳምሮ ቢያውቅም በተካነበት የመተኮስ ጥበብ ፀጥታ በማስጠበቁ ረገድ አብይን እንደሚበልጣቸው ማሳየት ሳይፈልግ አይቀርም፡፡ ስለዚህ የህወሃትን ከስልጣን መውረድ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ብጥብጥ አይጠላውም፤ሊያነሳሳው፣እየቆሰቆሰ ሊያባብሰውምይችላል፡፡

ይህን ለማስታገስ አብይ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር የቀደመ የፖለቲካ ባህላችንን የገመገሙበትን እና አስቀያሚውን የመበላላት ፖለቲካዊ ዘያችንን ሊያስቀሩ ያሰቡበት መንገድ እንደገና ማጤን ነው፡፡ ሁላችንም እንደምንስማማው እና ዶ/ር አብይም አጥብቀው እንደሚያምኑት የቀደመ የመግደል መጋደል፣የማገት መታገት፣የማመቅ መታመቅ ፖለቲካዊ ባላህችን መቀየር አለበት፡፡ ይህን ማድረጊያው ጥሩ ሰዓትም አሁን ነው፡፡

ለምን ቢባል የከረመው የፖለቲካ ባህላችን እግር ከወርች ቀፍድዶ አላራምድ ያለ የችግራችን ሁሉ ራስ መሆኑን ለመረዳት የቻሉ ጠ/ሚ ወንበር ላይ በመሆናቸው ነው፡፡ለዚሁ መልካም ነገር ልባቸውን ማስነሳታቸው ዶ/ር አብይን በእጅጉ የሚያስመሰግናቸው ሆኖ የከረመውን ልማድ በአንዴ ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን እላፊ ሄደው “ማሰር ያለፈበት ነው አናስርም” በሚል እሳቤ ወንጀለኞችን ሳይቀር ህግ እንደሚያዘው በህግ ጥላ ስር ለማድረግ ዳተኛ መሆናቸው የሚያስኬድ አልመሰለኝም፡፡አልፎ ተርፎ ለራሳቸው ህይወት እስከማስጋት፣ የተጀመረውንም የለውጥ ጭላንጭል እስከማዳፈንም ሊደርስ ይችላል፡፡ ከሁሉ በላይ የህግ የበላይነትን የሚጋፋ ይመስለኛል፡፡

መሆን ያለበት “አላስርም” ሳይሆን “ቀዳሚዎቼ በደምፍላት ያደርጉት እንደነበረው ያለ በቂ ምክንያት አላስርም፣አስሬም አልደበድብም፣ደብድቤ ያልሰሩትን እንዲናገሩ አላደርግም፣ባላደረጉት ሃጢያት ስማቸውን ጭቃ አልቀባም” ነው፡፡ ‘አስበው አልመው ባጠፉት፣ማስረጃ በተገኘበት ጥፋትም ቢሆን ጭርሱኑ አላስርም’ ማለት ግን ወደተፈለገው ስልጡን ፖለቲካ የሚወስደንን መንገድ ለአሰናካይ አሳልፎ መስጠት እንዳይሆን ስጋት አለኝ፡፡ ነገሩ ለወንጀለኛ ተጨማሪ በደል እንዲያደርስ፤ስልጣኑ ሲያምረው ለቀረው ቢሆንለትም ባይሆንለትም ለማንሰራረት እንዲፋትር እጣ ፋንታ ዕድል ተርታ መስጠት ነው፡፡

ምንም ዓይነት ግድያ ምሥጢርን አይደብቅም – ምሕረት ዘገዬ

በዚህች አጭር መጣጥፍ ውስጥ ደግሜ ላለመመላለስ ስል ሁለት ርዕሶችን በመጠኑ እዳስሳለሁ፡፡ የመጀመሪያው ከፍ ሲል ያስቀመጥኩት የዕለቱን ሁኔታ የሚገልጽ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ስለትምህርታችን የጥራት ደረጃ የታዘብኩትና ከሥር የቀረበው ነው፡፡

ኢንጂኔር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናው ውስጥ ሞቶ መገኘቱን በአሁኑ ሰዓት በሰበር ዜናነት እየተነገረ ነው፡፡ ስለአሟሟቱ ሁኔታ ገና የተሰማ ነገር የለም፡፡ እርግጡ ሳይታወቅ ደግሞ እገሌ ገደለው ወይ አስገደለው ማለቱ በመሠረቱና እንደአካሄድ ህጋዊም ተገቢም ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እንደ አንድ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ተራ ዜጋ ግምቶችን ማስፈር ይቻላል፡፡

እናም በኔ ግምት ይህ ሰው ሊገደል የሚችለው በወያኔ መንደር ከሚሰነዘር የጥቃት ብትር እንጂ በሌላ ሊሆን እንደማይችል ከመቶ በመቶ በላይ እርግጠኛ መሆን እችላለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች አንዴ ቂም አይቋጥሩ እንጂ ከቋጠሩ እስከመቼውም ካለመርሳታቸውም በተጨማሪ አይገቡ ገብተው ያን ሰው ከመግደል አይመለሱም፡፡ ከመነሻቸው አካባቢ በሻለቃ ጃተኒ (መባፅየን) በኬንያ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የፈጸሙትን ግድያ ጨምሮ ከዚያም በፊትና ከዚያም በኋላ እስከዛሬይቷ ቀን ድረስ ወያኔዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሓን ዜጎችን ሕይወት ቀጥፈዋል፡፡ የመግደል ዕድሉን እስካገኙ ድረስ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብም ቢረፈርፉ የማይረኩ የሰው ደም ወልፍ የተጠናወታቸው የለዬላቸው ሰይጣኖች ናቸው፡፡ አሁን አሁን የሚገርመኝ ነገር ይልቁንስ እነዚህ አጋንንት እንደሰው ይሆናሉ ብለው በተስፋ የሚጠብቁ የለውጡ ጎራ ሰዎች ትግስት አይሉት ፍራቻ አለማለቁ ነው፡፡ ምን እስኪሆኑ ድረስ ይሆን የሚጠብቁት?

ኢንጂኔር ስመኝ ምናልባት ከግድቡ ጋር በተያያዘ ሊያወጣው ዳር ዳር የሚለው ምሥጢር ይኖርና በዚያ ምክንያት የገደሉት ይመስለኛል፡፡ ከጓደኞቼ እንደሰማሁት ለኢቲቪ ቃለ መጠይቅ ሊሰጥ በቀጠሮ ላይ ነበር አሉ፡፡ በዚያ ቃለ መጠይቅ ወቅት ምሥጢር ያወጣብናል ብለው ፈርተውም ሊሆን ይችላል በሳይቀድሙኝ ልቅደም ዛሬ ጧት ይህን አስከፊ እርምጃ የወሰዱበት –  ለወያኔዎች ለማንኛውም ችግር አቋራጭ የመፍትሔ ሥልታቸው ግድያ ነው – አነስ ካለም በህቡዕ ቦታ አሥሮ ዕድሜ ልክ እያሰቃዩ ማቆየት፡፡ ቀደም ሲልም ኢንጂኔር ስመኝን የቁም እሥረኛ አድርገውት እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በግድቡ ምክንያት ብዙ የከበሩ ናቸው፡፡ የማይረባ ዕቃ እያቀረቡ ብዙ ቢሊዮን ብር አግበስብሰዋል፡፡ ማን ያውቃል ባልገባ ብረትና ስሚንቶም እንደገባ ተቆጥሮ ብዙ መዝብረው ይሆናል፡፡ ከጥራት አኳያም በርካታ ልፍስፍስና ዘመን ቀርቶ አንድ ክረምት የማይሻገሩ ውሽልሽል ሥራዎች በግድቡና በዙሪያው ተከናውኖ ይሆናል፡፡ የሆኖ ሀኖ ሰውዬው ሊያወጣው የተዘጋጀው ብዙ ምሥጢር እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ በመግደላቸው ግን ምሥጢሩን እስከወዲያኛው አፍነው ሊያቆዩት አይችሉም፡፡ ይዘገያል እንጂ ተደብቆ ዘላለሙን የሚቆይ ምሥጢር አይኖርም፡፡ ጊዜ ራሱም ያወጣዋል፡፡

በሌላም በኩል የዚህን ሰው ግድያ ስናይ ይህ የተሣካ የግድያ ሙከራ ብዙ አንድምታዎችን እደያዘ እንረዳለን፡፡ በመጀመሪያ የግድያው ቦታ መስቀል አደባባይ እንዲሆን መመረጡ “የቦምቡ ፍንዳታና የጠ/ሚኒስትሩ ግድያ ቢከሽፍም በምትኩና በቦታው ሌላ በግ አርደናል” ለማለት የፈለጉ ይመስላል፡፡ ሲቀጥልም “ኃይላችን ገና አልበረደም፡፡ ከኛ የግድያ ራዳር ውጪ የሚሆን የለምና ሁልሽም በዚህ ሰው መቀጣጫነት ተማሪ” ለማለት ፈልገውም ሊሆን ይችላል፡፡ ሲሰልስም “የፈለግነውን ብናደርግ ገልማጭ ቆንጣጭ የለንም፤ አሁንም ያሻንን ከማድረግ የሚያግደን አካል የለም” ማለታቸውም ነው፡፡ ይህ አዲሱ የለውጥ መንግሥት እነዚህ ባለጌዎች ምን እስኪሆኑ እየጠበቀ እንደሆነ በበኩሌ ማወቅ አልቻልኩም፡፡ “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” ብለን አዲሱን መንግሥት በይፋ ከመተቸታችንና ተስፋ ከመቁረጣችን በፊት በጠራራ ፀሐይ በሀገራችን መዲና በአዲስ አበባ ይህን ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ ሰዎች በአስቸኳይ ወደ ፍርድ እንዲቀርቡ ቢደረግ ከተጨማሪ ጥፋትና ኪሣራ እንድናለን፡፡ ከሚገባው በላይ እሹሩሩ በመባላቸው ይሄውና ከመስከን ይልቅ የልብ ልብ እየተሰማቸው ድፍረታቸው ድንበር አጥቷል፡፡ “ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጭ” እንዲሉ ነውና የነዶ/ር ዐቢይ ቡድን አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰደ ይህ ግድያ ነገ በማን እንደሚደመደም ግልጽ ነው፡፡ ለውጡ ከሸፈ ማለት ደግሞ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እንጂ ኢትዮጵያ ከሩዋንዳና ሦርያ በሚበልጥ የእሳት እቶን ላይ ትጣዳለች፡፡ ያኔ ከእሳት ለመትረፍ የሚኖረን ዕድል ከንፍሮ ወይም ከአሹቅ ጥሬ የመውጣት ያህል ነው፡፡ ለማንኛውም የስመኝን ነፍስ በገነት ያኑራት፡፡

እንደአጠቃላይ እውነት ግን እንዲህ እላለሁ፡፡ አንድ ድርጅትም ይሁን ግለሰብ ምሥጢር እንዳይወጣበት ብሎ ንጹሓን ዜጎችን ቢገድል ወይ ቢያስገድል ምሥጢሩን ይበለጥ ዘረገፈው እንጂ አልደበቀውም፡፡ ብዙ ምሣሌዎችን መጥቀስ ቢቻልም የሰማሁትን የበዓሉ ግርማን አገዳደል በመጠኑ ላስታውስ፡፡

እንደሰማሁት የተወሰኑ የደርግ ባለሥልጣናት – ከሊ/መንበር መንግሥቱ ዕውቅና ውጪ ነው አሉ – በዓሉን ለመግደል  ይወስናሉ፡፡ ሁለት ወታሮች እንዲገድሉ ግዳጁ ይሰጣቸዋል፡፡ እነሱ በሥውር ቦታ በዓሉን ገድለው በአገር አማን ወደመጡበት ሲመለሱ ሌሎች ሁለት ወታሮች እነዚህን ገዳይ ወታደሮች እንዲገድሉ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሀል የበዓሉ ገዳዮችና አስገዳዮች ማንነት የውኃ ሽታ ሆኖ ይቀራል፡፡ ሁሉም ነገር ተድበስብሶ ቀረ፡፡ ግን እስከ መቼ? ተደብቆ የቀረ ነገር የለም፡፡ በጊዜ ሂደት ሁሉም ታወቀ፡፡

መረዳት ያለብን አንድ እውነት አለ፡፡ በዓሉ ተገድሏል፡፡ ትልቁ እውነት እርሱ ነው፡፡ በዓሉን የገደለው ሰው/ቡድን ማንነት ሁለተኛ ጥያቄ ነው፡፡ ያንንም ማወቅ ብዙ ከባድ አይደለም፡፡ በጥርጣሬ የተጠርጣሪ ገዳዮችን ብዛት መጨመር ይቻል እንደሆነ እንጂ ዋናውን ተጠርጣሪ ገዳይ ማወቅ ብዙም ከባድ አይደለም፡፡ በመሆኑም በዓሉ መሞቱ እርግጥ ከሆነ ዘንድ የሚገድለው በጽሑፎቹ የተናደደ  የሥርዓቱ አንድ ወይም ጥቂት ባለሥልጣናት እንደሚሆኑ የማንም ግምት ነው፡፡ ስለዚህ የአራት ሰው ሕይወት የጠፋው በከንቱ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ዓይነት ማኪያቬሊያዊ የጭካኔ አካሄድ ከሀገራችን እንዲወገድ ሁላችንም ጥረት ማድረግ አለብን፡፡

በመሠረቱ በመገዳደል የትም መድረስ አይቻልም፡፡ በመገዳደልም ምሥጢርን ይበልጥ መዘክዘክ እንጂ መደበቅ የሚቻል አይደለም፡፡ የሚያዋጣን ብቸኛ መፍትሔ ችግሮችን በጤናማ የውይይትና ክርክር ሂደት ተደማምጦና ተግባብቶ በሰከነ ሁኔታ በሰላም መፍታት ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ያለው የእልህና የግድያ ጉዞ ዞሮ ዞሮ ሁሉንም አረንቋ ውስጥ የሚከት የጨለማ ጉዞ ነው፡፡

ወያኔ በአካል እስካሁኒቷ ቅጽበት እየገደለን ነው፡፡ አንድ ወንድማችንን ለአብነት ዛሬ አጣነው፡፡ ገና ይቀጥላል፡፡ ነገ ማንኛችንን እንደሚጥል አናውቅም፡፡ ከዚሁ ግድያ ጋር በተያያዘ ትልቁን ግድያ ደግሞ ቀጥዬ በምመለከተው ርዕስ አቀርባለሁ፡፡ ከግድያዎች ሁሉ ትልቁ ግድያ የምለው የአንድን ሀገር የትምህርት ሥርዓት እንክትክቱ እንዲወጣ ማድረግና በውጤቱም ደናቁርት ዜጎችን በብዛት ማምረት ነው፡፡ በዚህን ዓይነቱ ብልሹ የትምህርት ሥርዓት የሞራል ዕሤቶች አብረው ይሞታሉ፤ ሃይማኖታዊ ተቋማት፣ የጤና ተቋማት፣ ማኅበረሰብኣዊ የሞራልና የባህል ወጋግራዎች ተያይዘው ወደ ገደል ይገባሉ፡፡ የትምህርት ሥርዓት ተበላሽቶ በዚያ በተበላሸ የትምህርት ቧምቧ(አሸንዳ) የሚያልፉ ዳኞች፣ ጠበቆች፣ መምህራን፣ ኢንጂኔሮች፣ የማኅበራዊና የተፈጥሮ ሣይንስ ዶክተሮች፣ ዝቅተኛና ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች፣ ሹፌሮች፣ ፓይለቶች፣ ወታደሮች፣ ፖለቲከኞች፣ ወዘተ. ከሚጠበቅባቸው የአሠራር ብቃትና ሙያዊ ዲሲፕሊን ይወጡና ሀገር ጃርት እንደበላው ዱባ አካማሌ ትሆናለች – የደም ሥራቸው የሚሠራው በሙስናና በንቅዘት ከመሆኑም በተጨማሪ የሥራ ጥራት እንዘጭ ብሎ ሁሉ ነገር የብላኔ ይሆናል፡፡ ያኔ ሰዎች በቅርጽ እንጂ በይዘት ሰው መሆናቸው ያቆማል፡፡ ያኔ ሰዎች በሥነ ፍጥረት አቻዎቻቸው ከሆኑ ሌሎች እንስሳት እጅግ የሚያንሱ ወራዳ ፍጡራን ይሆናሉ፡፡ ሆዳሞች፣ ሰካራሞች፣ ሴሰኞች፣ ሌቦች፣ ቀማኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ወንጀለኞች፣ ከሃዲዎች፣ …. ይሆናሉ፡፡ ከዚህ ዓይነቱ የአሥሽ ምቺው አባዜ ነፃ የሚሆኑ በጣም ጥቂት ናቸው – እነሱም መፈጣራቸውን እየተራገሙ በስቃይና በሰቀቀን የሚኖሩ ይሆናሉ፤ “ጌታየ ሆይ በዚህን ክፉ ዘመን ስለምን ፈጠርከኝ?” በሚል የዘወትር ምህላ ፈጣሪያቸውን የሚወቅሱ ይሆናሉ (አለደምቡና አለባህሉ የጀሶ እንጀራ፣ የሞራና የሙዝ ቅቤ፣ የሸክላ በርበሬ፣ የአህያና የበከተ እንስሳ ሥጋ እያበላ ለሞትና ለበሽታ የሚዳርግህን አጋሰስ ትውልድ ከመረቅህ በርግጥም አንተ ብፁዕ ነህ)፡፡ በሀገራችን እያየን ያለነው አሳዛኝ ትርዒት እንግዲህ ይህንን ነው፡፡

 

ሁለተኛው ርዕሴ – Nature Gaves for Ethiopia you!

 

በክፍል ውስጥ የማስተምራቸውን ተማሪዎቼን አነጋገር የኮረጀ አንድ ምሁር በመምህራንና በጠ/ሚኒስትሩ የሰሞኑ ስብሰባ ላይ ተመለከትኩና ትንሽ ፈገግ ስላደረገኝ ይህችን ማስታወሻ ልጽፍ ተነሳሁ፤ አነሳሴ የደረስንበትን የማነስ ደረጃ ለመጠቆም እንጂ በሰው ስህተት ለመዝናናት እንዳልሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ የማይሳሳት ደግሞ የለም፡፡ ሁላችንም በአንድ ወይ በሌላ አጋጣሚ እንሳሳታለን፡፡ ስህተታችንን ስናውቅ ወይም ሲነገረኝ ግን ለመታረም ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ መወገድ ያለበት ነገር ስህተት መሥራትን እንደባህል ቆጥረን በስህተት መንገድ ሆነ ብለን መንጎድን ነው፡፡ እንጂ ከ”ሰው ስህተት ከብረት ዝገት” አይጠፋም፡፡

በነገራችን ላይ በዚህ ዘመን የምንጽፍበት ነገር በዛና ተቸገርን፡፡ ግዴላችሁም እነዚህ ሰዎች የርገረም አድርገውናል፡፡ “የርገረም” ማለት በተወለድኩበት አካባቢ ዘዬኣዊ አገላለጽ “ብልሽትሽቱ የወጣ” ማለት ነው፡፡ ከኔ ሠፈር ራቅ ባሉ ሌሎች የማውቃቸው አካባቢዎች ደግሞ “አካማሌ” ይላሉ፡፡ ያው ነው ትርጉሙ፡፡ አንድ ሰው ወይም አንድ ሁኔታ ሲግማማና ውጥንቅጡ ሲወጣ እነዚህን መሰል ቃላት በመግለጫነት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ለማንኛውም ወያኔዎች አካማሌ አድርገውን ሊጠፉ የተዘጋጁ ይመስላሉ – የርገረም አድርገውን፡፡ አሁን ከመሸም ቢሆን ተባብረን ይህን የጥፋት ዕቅዳቸውን በጋራ ካላመከንነው ታያላችሁ ማንኛችንም አንተርፍም፡፡ መድኃኒታችን የኛው ትብብርና ፍቅር ነው፡፡ ምርጫችን በየተራ ማለቅ ወይም ተባብሮ ጠላት ወለድ ችግሮችን በመታገል ሁላችንም ነፃ የምንሆንበትን ነፋሻ አየር መፍጠር ነው፡፡ በብዙ ሺዎች የሚገመቱ ጠላት ያሰለጠናቸው ነፍሰ ገዳዮችና ቤትና አካባቢን በእሳት እያጋዩ የሚሰወሩ ወምበዴዎች ሀገር ምድሩን እያጥለቀለቁ መሆናቸውን መንግሥት እያወቀ መቶ የማይሞሉ ጥቂት ሽፍቶችን እንክ እንክ እያለ ማባበሉ ለለውጡ እርምጃ ውጤታማነት ደግ አይደለምና ይታሰብበት፡፡ በአካልም በመንፈስም እየገደሉን እንዲቀጥሉ አንፍቀድላቸው፡፡

የምሁራንን ስብሰባ በኢቲቪ እያየሁ ሳለ አንዱ ቆፍጣና ጎፈሬ መምህር – መምህር ይሆን ይሆናል መቼም –  መነጋገሪያውን ተቀበለ፡፡ ሳይቸግር ጤፍ ብድ እንዲሉ ላያዛልቀው ንግግሩን በእንግሊዝኛ ጀመረ፡፡ “አሃ! ይቺ ሰው አማርኛ የምትጠላ ወይ ደሞ ባማርኛ ከምትናገር በእንግሊዝኛ ብትናገር እንደሚቀላት የተረዳች ኃይለኛ ምሁር ናት!” አልኩና በጉጉት መከታተሌን ያዝኩ፡፡ ውሸት መናገር ምን ይሠራል? መደባበቅስ ምን ይፈይዳል? አፈርኩ፡፡ ምሁሪት እንዲህ እያለች ቀጠለች፡፡ (የተነገረውን እንደወረደ ስለጻፍኩት ‹ኤዲት› አይደረግ(ብኝ)፡፡)

… for giving me the chance, I would like to say this:- you know, nature gaves Arab countries oil, nature gaves Uganda Victoria Lake; nature gaves Eritrea Dahlak Massawa; nature gaves Kenya Mombasa; nature gaves for Ethiopia you.(የቀለጠ ጭብጨባ) …. ቀጠለች ምሁሯ… one of my friend….

ታዲያ ምን ይጠበስልህ? የሚለኝ ካለ ለጊዜው ምንም ነገር እንዲጠበስልኝ አልፈልግም – በቅርቡ ነው ምሣየንም የበላሁት፡፡ ግን ግን የደረስንበትን ደረጃ ታዘቡ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ብዙ ቦታ እንደታዘብኩት በስህተቱ የማይቆጭ፣ መሳሳቱን ስትነግሩት ደግሞ “ዋናው መግባባቱ እንጂ ምን ጣጣ አለው? ምን ችግር አለው? አቦ አታካብዳ!” የሚለው መብዛቱ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እንግሊዝኛ ሞታ የቀብር ሥነ ሥርዓቷም ሊፈጸም ጸሎተ ፍትሓቱን የሚመሩት አቡን ከታላቋ ብሪጣንያ እስኪመጡ  እየተጠበቀ ነው፡፡ ከምንም ያልሆነ ትውልድ እያፈራን የርገረም ሆነን መቅረታችነ ያሳዝናልኝ – በጎንደር አማርኛ፡፡ ኤዲያ ለምን ዓይነት ሀገር ውሽጥስ ተፈጠርኩ እንዴ? – የትግርኛችን ተፅዕኖስ ለምን ይቅርብኝ…!