“ዝም አልልም፤ ለምን ዝም እላለሁ”፡ አና ጎሜዝ

አና ጎሜዝImage copyrightANA GOMES FACEBOOK

ጥያቄ፡- ሰሞኑን አቶ በረከትን ቃለ መጠይቅ አድርገንላቸው ነበር። ‘ወ/ሮ አና፣ ‘እባክዎ አርፈው ይቀመጡ’ ብለዎታል፡፡ እንዲያውም እኚህ ሴት ‹‹የፖርቹጋል ቅኝ ግዛት አስተሳስብ አልለቀቃቸውም››፤ ሲሉ ነው አስተያየት የሰጡት።

ወይዘሮ አና ጎሜዝ፡- ለእንዲህ ዓይነት የወረደ ሐሳብ መልስ መስጠት አልሻም ነበር። አገሬን መስደባቸው ግን ትክክል አይደለም። እኔን እና አገሬን ከቅኝ ግዛት ጋር ማያያዛቸውም አሳፋሪ ነው። በፖርቹጋል እኔ የምታወቀው በጸረ ቅኝ አገዛዝ ተጋድሎዬ ነው። ያውም ቅኝ ግዛትን መጻረር ፈታኝ በሆነበት ዘመን ነው የምልህ። ሕይወቴንም አደጋ ላይ ጥዬ ነው ይሄን ያደረገኩት። ተማሪ እያለሁ ጀምሮ ነው ይሄን ተጋድሎ የፈጸምኩት። ታሪኬ የሚያስረዳውም ይህንን ነው።

«ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ»

አቶ ታደሰ ካሳ፡ “…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው”

ያለመከሰስ መብት ለማን? እስከምን ድረስ?

ጥያቄ፡- ሁለታችሁን እንዲህ የቃላት ጦርነት ውስጥ የሚከታችሁ እኛ የማናውቀው ነገር አለ?

አና ጎሜዝ፡- ነገሩ በ2005 እኔ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ቡድንን መምራት በጀመርኩበት ጊዜ የሆነ ነው። እሱ ያኔ የመንግሥት ተወካይ ነበር። ከእኔና እኔ ከምመራው የምርጫ ታዛቢ ቡድን ጋር እሱ ነበር በየጊዜው የሚገናኘው። የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትርም ነበር። በዚያ የታዛቢ ቡድን አማካኝነት እኔና የቡድኔ አባላት የተደረገውን ማጭበርበር ስላጋለጥን ነው በእኔ ላይ ቂም ይዞ የቆየው።

ከበረከት ስምኦን ጋር በጁን 8፣ 2005 የነበረንን ንግግር መቼም አልረሳውም። በመሐል አዲስ አበባ የተደረገውን ግድያ ሰምቼና ሆስፒታሎችን ጎብኝቼ ወዲያውኑ አገኘሁት። የጎበኘኋቸው ሐኪሞችና ነርሶች እያለቀሱ ነበር [በጥይት የተመቱትን] የሚያክሙት፡፡ ሁኔታው አስቆጥቷቸው ነበር። ባየሁት ጉዳይ ላይ መግለጫ እንደምሰጥ በረከትን ነገርኩት። እርሱ በዚህ ውሳኔዬ ተበሳጨ፡፡ ይባስ ብሎ ለተፈጠረው ግድያ ተጠያቂው የአውሮፓ ኅብረት ነው አለኝ። ይህ ብሽቅ የኾነ ሐሳብ ነው።

ጥያቄ፡- በቀደም ለታ የትዊተር ገጽዎ አቶ በረከትን ‹‹ርህራሔ የሌለው፣ ዋሾና፣ ጨካኝ›› ብለውታል። አልበዛም? የተጠቀሟቸው ቃላቶች የዲፕሎማት ቋንቋ አይመስልም።

አና ጎሜዝ፦ እውነት ስለሆነ ነዋ፣ እውነት ስለሆነ ነው፥ እርሱ ጨካኝና ውሸታም ነው። በ2005 በደንብ አውቀዋለሁ ሰውዬውን። ባህሪው እንደዚያ ነው። እኔ ከአገሪቱ ጋር ምንም ችግር የለብኝም። የኔ ችግር ሁልጊዜም ከአምባገነኖች ጋር ነው።

ጥያቄ፡- አሁን ነገሩ ረዥም ጊዜ ሆነው እኮ፤ ለምን አይረሱትም ግን እርስዎ?

አና ጎሜዝ፡– ለምን እረሳለሁ?! በ2005ቱ ምርጫ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሞተዋል። የነርሱ ቤተሰቦች ይህን የሚረሱ ይመስልኻል? ስለዚህ እኔም አልረሳም። የሰው ሕይወት ነው የጠፋው፤ ለግድያው ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው ሰዎች አሉ፤ አንዱ አቶ በረከት ነው።

ይህን ጉዳይ የግለሰቦች ጉዳይ ለምን ታደርገዋለህ። እኔ በግል ከሰውየው ጋር ምንም ችግር የለብኝም እኮ። ፖለቲካዊ ነው ጉዳዩ። በርካታ ሰዎችን የጨፈጨፈውን ሥርዓት ሲያገለግል የነበረ ሰው ነው። እኔ ለማወቀውና ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ይሁን ነው እያልኩ ያለሁት። ብቸኛው ተጠያቂ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ሆኖም አንዱና ዋንኛው ነው።

ጥያቄ፡- ለማለት የፈለኩት ከእርስዎ ጋር ምርጫውን የታዘቡ፣ የኾነውን የተመለከቱ ብዙ ዲፕሎማቶች ነበሩ፤ አንዳቸውም በእርስዎ መጠን መንግሥት ላይ ትችት ሲሰነዝሩ አልሰማንም። እርስዎ ለምንድነው አንዲህ ነገሩን ለዓመታት የሙጥኝ ያሉት?

አና ጎሜዝ፡– ዲፕሎማቶች የተፈጠሩት እንዲዋሹ አይመስለኝም። ዝም አልልም፤ ለምን ዝም እላለሁ፤ በመለስና በአቶ በረከት ትእዛዝ የተገደሉ ሰዎችን አይቻለሁ፤ ስለምን ዝም እላለሁ? አሁንም ላረጋግጥልህ የምፈልገው፤ አሁንም ወደፊትም ዝም አልልም።

ሌሎች ዝም ብለዋል ላልከው እኔ ያኔም ያስተጋባሁት የ200 የቡድኔን አባላት በመላው ኢትዮጵያ ተዘዋውረው ያዩትን ነው። ያወጣነው ሪፖርት ደግሞ ከካርተር ሴንተር ካወጣው ሪፖርት ጋር የሚመሳሰል ነው። ነገር ግን ሁሉም ሰው ለአንድ ጉዳይ የሚሰጠው ምላሽ ተመሳሳይ ላይሆን ይችላል። እኔ ባየሁት ነገር እጅግ ተቆጥቻለሁ። የመለስና የበረከት መንግሥት የሕዝብን ድምጽ ያጭበረበረበት መንገድ አናዶኛል። የአውሮፓ አገራት ይህንን መንግሥት እሹሩሩ ያሉበት መንገድ አበሳጭቶኛል።

አሁንም ዝም አልልም፤ ወደፊትም ዝም አልልም፤ በእጃቸው የሰው ደም ያለባቸውን እንደ አቶ በረከት ያሉ ሰዎችን በዝምታ አላልፋቸውም።

አና ጎሜዝImage copyrightANA GOMES FACEBOOK

ጥያቄ፡- አቶ በረከት ወንጀለኛ ናቸው ለፍርድ ይቅረቡ እያሉ ነው?

አና ጎሜዝ፡- ይሄ ምን ጥያቄ አለው፤ አቶ በረከት ለፍርድ ነው መቅረብ ያለበት። እርግጥ ነው ብቻውን አይደለም፤ ግን ዋናው ሰው ነው፤ ለፍርድ የማይቀርበው ለምንድነው? አሁን ለውጥ ላይ ያለው መንግሥት ወደዚህ ድምዳሜ ላይ ይመጣል የሚል ተስፋ አለኝ።

ጥያቄ፡- የአቶ በረከት ስምኦንን ጉዳይ ለጊዜው ገሸሽ እናድርገውና፤ ሌላ ጥያቄ ላንሳ፤ በ2012 አቶ መለስ ዜናዊ በብራስልስ መሞታቸውን ለኢሳት መረጃ ያቀበሉት እርስዎ ኖት እንዴ?

አና ጎሜዝ፡- ሊሆን ይችላል። መረጃው ነበረኝ። ያኔ ማንም መለስ ዜናዊ መታመሙን ቀርቶ አገር ውስጥ አለመኖሩንም የሚያውቅ ብዙ ሰው አልነበረም። መሞቱንም ብዙ ሰው አያውቅም ነበር። የነበረኝ መረጃ እጅግ አስተማማኝ የሚባል ነበር። ያን መረጃ ኢሳት የተጠቀመበት ይመስለኛል። ቀደም ብሎ መሞቱን የነገረኝ ምንጭ እጅግ የምተማመንበትና አስተማማኝ ነበር።

ጥያቄ፡- ስለዚህ አቶ መለስ የሞቱት በመንግሥት ከገለጸው ቀን ቀደም ብሎ ነው ብለው በእርግጠኝነት መናገር ይችላሉ?

አና ጎሜዝ፡- ያለምንም ጥርጥር። መጀመርያ ብራዚል ለሕክምና ተወስዶ ነበር። ከሐኪሞቹ ጋር በብራዚል ተገናኝቷል። የሕመሙ ሁኔታ የተገመገመው ብራዚል በሚገኙ ስፔሻሊስቶች ነበር። ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ተነገረው። ከዚያ በኋላ ነው ብራስልስ እንዲመጣ የተደረገው። እኔ መረጃውን ባገኘሁበት ቅጽበት ራሱ ከቀናት በፊት መሞቱ ነው የተነገረኝ። ሆኖም በምሥጢር ተይዞ ነበር።

ጥያቄ፡- ትክክለኛ ቀኑን ያስታውሱታል?

አና ጎሜዝ፡- አላስታውስም

ጥያቄ፡- የትኛው በሽታ ለሞት እንደዳረጋቸውስ ያስታውሳሉ?

አና ጎሜዝ፡- እ…አንዳች የካንሰር ዓይነት ሕመም ሳይሆን አይቀርም፤ በትክክል ምን እንደነበር እርግጠኛ አይደለሁም።

ጥያቄ፡- መንግሥት ለምን መሞታቸውን ዘለግ ላለ ጊዜ መደበቅ የፈለገ ይመስልዎታል?

አና ጎሜዝ፡- እነርሱን ነው መጠየቅ ያለብህ። ነገር ግን በአምባገነን መንግሥታት ውስጥ የጠንካራ መሪ ሞት መደበቅ የተለመደ ነው፤ የመለስን ሞት ቀደም ብዬ አውቅ ነበር እያልኩህ አይደለም። እንደሰማሁት መረጃውን ሰጠሁ። ብዙም ሳይቆይ መንግሥትም መሞታቸውን አረጋገጠ። ከዚያ በፊት ግን ስለመታመማቸው እንኳን ለኢትዯጵያ ሕዝብ አልተነገረም ነበር።

ጥያቄ፡- እርስዎ መች ነው ግን ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም የሰሙት?

አና ጎሜዝ፡- በልጅነቴ ነው። በቅኝ ግዛትና ከቅኝ ግዛትም በፊት በነበረው የአገሬ ታሪክ ወስጥ የኢትዮጵያ ስም ገናና ነው። ፖርቹጋሎች ለረዥም ዓመት ኢትዮጵያ በእግር ተጉዘው ለመድረስ ይሞክሩ ነበር። የፕሪስት ጆን አገር ተብላ ትታወቅ ነበር። የፖርቹጋል አሳሾች ትልቅ ጉጉት ነበራቸው፤ ይቺን አገር ለማየት።

እኔ አገሪቱን የረገጥኩት በ97 ምርጫ ጊዜ ነው። የያኔዋ ኮሚሽነር እኔን ወደዚያ እንድሄድ የመረጡኝ ከዚያ በፊት ምንም ዓይነት ግንኙነት ከአገሪቱ ጋር ስላልነበረኝና ገለልተኛ ስለነበርኩ ነበር፤ በቆይታዬ አገሪቱን ተዘዋውሬ ሕዝቡንና ታሪኩን ስረዳ ይህ ሕዝብ ዲሞክራሲ ይገባዋል የሚል እምነት አድሮብኛል።

እኔ በአገሬ በጭቆና መኖሬ በጭቆና የሚኖር ሕዝብን እንድረዳ ረድቶኛል። ጨቋኞች ቋንቋቸው ይገባኛል። ዲሞክራሲ የሚል ቃል ያበዛሉ፤ ሽግግር ላይ ነን ይላሉ። በዚህ ጉዳይ ከመለስ ጋር ረዥም ውይይትን አድርገናል።

ጥያቄ፡- ዘለግ ያለ ቆይታ ከአቶ መለስ ጋር ከነበርዎ አቶ መለስን ያውቋቸዋል ማለት ነው፤ አቶ መለስን እንዴት ይገልጿቸዋል?

አና ጎሜዝ፡- ብልህ አጭበርባሪ (Deviously smart) ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዳልዎ ይታማሉ፡፡

አና ጎሜዝ፡- (ዘለግ ካለ ሳቅ በኋላ) ይሄ ፌዝ መሆን አለበት። ብርሃኑን አውቀዋለሁ። ባለቤቱን ዶክተር ናርዶስም አውቃታለሁ። ኢትዮጵያ እያለሁ ነው የማውቃት። እሷም ታውቃለች። አሁን የምነግርህን ታሪክ እሷ ራሱ ልትነግርህ ትችላለች። በ2005፣ ጁን 7 ሌሊት ጁን 8 ሊነጋ የኾነ ታሪክ ነው፡፡

የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር የነበሩት ቲም ክላርክና ባለቤቱ ቤት ነው ያደርኩት። ያኔ የኔን የሸራተን መኝታ ለብርሃኑ ነጋ ለቅቄ ነው የሄድኩት። ለርሱ ብቻ አይደለም። ባለቤቱም ጭምር። ምክንያቱም ይህን ያደረኩት አደጋ ላይ ስለነበሩ ነው። ሌላ ቦታ ተደብቀው ነበር። የት እንደነበር አሁን አልነግርህም። የተሸሸጉበት ቦታ በመለስ ወታደሮች ሊታሰስ እንደሆነ መረጃ ለአምባሳደር ቲም ደርሶት ነበር። በአምባሳደር ቲም ክላርክና ባለቤቱ ጥያቄ መሠረት የሸራተን ክፍሌን ለብርሃኑና ባለቤቱ ለቅቄላቸዋለሁ።

ጥያቄ፡- ይህ ደርጊትዎ በራሱ በወቅቱ እርስዎ ገለልተኛ እንዳልነበሩ የሚያሳይ አይመስልዎትም?

በፍጹም! በፍጹም! ሕይወቱ በአምባገነኖች አደጋ ላይ ላለ ለማንኛወም ሰው ላደርገው የምችለውን ነገር ነው ያደረኩት። የዶ/ር ብርሃኑና ባለቤቱ ሕይወት እኮ አደጋ ላይ ነበር። ለዚያም ነው አምባሳደር ቲም ክላርክ እኔ ክፍል እንዲቆዩ የፈለገው።

ጥያቄ፡- ብርሃኑን ካነሳን ዘንዳ ወደ ኤርትራ በረሃ መውረዱን ያደንቁለታል?

አና ጎሜዝ፡- ለኔ ሊታገል አይደለም እኮ እዚያ የሄደው፤ ሰዎች ሲገፉ የት ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ እረዳለሁ። አንዳንድ ጊዜ አምባገነኖች ላይ ነፍጥ ማንሳት ሊያስፈልግ ይችላል። ማንዴላም አሸባሪ ሲባሉ ነበር። በሰላማዊ ትግል ነው የማምነው፤ ኾኖም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች፥ ምንም አማራጭ በሌለበት ሁኔታ ይህ ሊሆን እንደሚችልም እረዳለሁ።

ጥያቄ፡- ኢትዮጵያዊ ስም እንዳልዎ ያውቁ ይኾን?

አና ጎሜዝ፡- አዎ ብዙ ሰዎች ብዙ ስም እንዳወጡልኝ አውቃለሁ። በዋናነት «ጎቤዜ» የሚባለውን ሰምቻለሁ (ሳቅ)

ጥያቄ፡- ምን ይሰማዎታል ?

አና ጎሜዝ፡- የሚያኮራ ነው። ሆኖም እኔ ከኢትዮጵያ ጋር የምጋራው ህልምና የሚያኮራኝ ነገር ካለ አንድ ነገር ነው፤ እሱም አገሪቱ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲ ተሸጋግራ ማየት።

ጥያቄ፡- አንዳንድ ቦታ ሰዎች የተቃውሞና የድጋፍ ሰልፍ ሲወጡ የርስዎን ምሥል መያዝ ጀምረዋል

አና ጎሜዝ፡- ምን ልበልህ …አመሰግናለሁ ስለ እውቅናው፤ ግን በሆነ መልኩ ደግሞ ኃላፊነትም ጭምር ይሰጣል። ስለ ዲሞራሲ ከሚታገሉ ሰዎች ጋር የኔን ምሥል ማየቴ ኢትዮጵያዊያንን በማገዝ እንድገፋበት ነው የሚያደርገኝ፤ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥሩ ጅምር ላይ ያለ ይመስላል፤ ነገር ግን አስተማማኝ መሠረት ላይ ገና አልተቀመጠም።

ጥያቄ፡- ኢትዮጵያዊ ዜግነት የመጠየቅ እቅድ ይኖርዎ ይሆን? ወይም ደግሞ የጡረታ ዘመንዎ በኢትዮጵያ የማድረግ ሐሳብ…

ሳቅ- የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ። ኾኖም የምትለው ዕቅድ የለኝም፤ ራሴን የማየው እንደዚያ ነው። እኔ ራሴን አንድ የዓለም ዜጋ አድርጌ ነው የምቆጥረው

ጥያቄ፡- በግልዎ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ጀግና እንደሆኑ ይሰማዎት ይሆን?

አና ጎሜዝ፡- እንደዚያ እንደማላስብ ነግሬሀለሁ፤ አሁን የታየውን ተስፋ እንዲለመልም በጣም ተስፋ በማድረግ ላይ ነው ያለሁት።

ጥያቄ፡- ሳስበው ቤትዎ በኢትዮጵያዊ ቁሳቁሶች የተሞላ ይመስለኛል።

እውነትህን ነው፤ አሁን የማወራህ በብራስልስ ቢሮዬ ሆኜ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባንዲራ አለ። በአንድ አርቲስት የተሳለ ቆንጆ የአዲስ አበባ ሥዕልም ይታየኛል፡፡ ቤቴም ቢሆን ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቼ የሰጡኝ ማስታወሻዎች ይገኛሉ። በ97 ምርጫ የለበስኩት የምርጫ ታዛቢነት የደንብ ልብስም በማስታወሻነት አለ። በርካታ መስቀሎችም አሉኝ፡፡ ከመርካቶ የገዛኋቸው።

ጥያቄ፡- ወደ አቶ በረከት ጉዳይ አንድ አፍታ ልመስልዎ። ሰሞኑን በአማርኛ መጽሐፍ ጽፈዋል። የሚተርጉምልዎ በጎ ፈቃደኛ ቢያገኙ የማንበብ ፍላጎት አለዎ?

አና ጎሜዝ፡- ብዙ የምሰራቸው ቁምነገሮች አሉ። ብዙ ማንበብ ያለብኝ መጽሐፍት አሉኝ። ለምን ብዬ ነው ዋሾ ነው ብዬ የማምነው ሰው የጻፈውን መጽሐፍ የማነበው። የፕሮፓጋንዳ ፋብሪካ ነው እኮ እሱ። ምናልባት ወደፊት ሥራ ፈት ብሆን ላነበው እችል ይሆናል።

ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በሚያደርጉት የበዛ ተሳትፎ…

አና ጎሜዝ፡- የበዛ አትበል። የበዛ ነው ብዬ አላምንም።

ጥያቄ፡- …… በዚህ ተሳትፎዎ የሚበሳጩ ሰዎች የሉም?

አና ጎሜዝ፡- ኦ! ብዙ ስድቦችንና ማንቋሸሾች በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል ይደርሱኛል። ከመንግስት ሰዎች ግን እንዲያ ያለ ነገር ዐይቼ አላውቅም። እዚህ ብራሰልስ የማገኛቸው ዲፕሎማቶች በመከባበር ነው የሚያወሩኝ። በ2013 አዲስ አበባ ሄጄ ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለምሳ ጋብዘውኛል። ሌሎችንም አግኝቻለሁ። የተለየ ነገር አላየሁም። ግለሰቦች ግን ይሳደባሉ። መለስ ዜናዊም ‹‹በኢትዮጵያን ሄራልድ›› ጋዜጣ ያን ሁሉ ገጽ ከተቃዋሚ ብር ትቀበላለች ብሎ ሰድቦኛል፡፡

ጥያቄ፡- ወደ አዲስ አበባ የመምጣት ፍላጎት አለዎት?

ብዙ ወዳጆቼ ለውጡን ተከትሎ እንድመጣ ይጠይቁኛል። ለመሔድ ብዬ አልሄድም። የማግዘው ነገር ሲኖር ያን አደርጋለሁ፤ ሰሞኑን ለምሳሌ ስቶክሆልም ባሉ ኢትዮጵያዊያን ለውይይት ተጋብዣለሁ። እሄዳለሁ።

ጥያቄ፡- ዐብይ አህመድን አግኝተዋቸዋል?

አና ጎሜዝ፡- አላገኘሁትም። እስክንድር ነጋን ግን አግኝቼዋለሁ። በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡

ጥያቄ፦ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይገመግሙታል?

አና ጎሜዝ፡- መገምገም የምችለው በማገኛቸው ሰዎች ዐይን ነው። ለምሳሌ አንዳርጋቸው ጽጌ እዚህ አውሮፓ ኅብረት ምስክርነት ለመስጠት መጥቶ አግኝቼዋለሁ። ከዐብይ አሕመድ ጋር ቆይታ እንዳደረገ ነግሮኛል። አሱ በዐብይ ላይ ባሳደረው ተስፋ ተደንቂያለሁ። ለዲሞክራሲ ሕይወታቸውን የሰጡ ሰዎች ዐብይ ላይ ተስፋ ካሳደሩ እኔ ተስፋ የማላደርግበት ምክንያት የለም።

ጥያቄ፡- ተቃዋሚዎች ሥልጣን ቢይዙም ድምጾትን ማሰማቱን ይቀጥሉበታል?

አና ጎሜዝ፦ አዳምጠኝ፤ እኔ በኢትዮጵያ ጉዳይ ኤክስፐርት አይደለሁም። ባየሁት በደል ነው የተነሳሳሁት፥ የዓለማቀፉ ማኀበረሰብ ለኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ጉጉት ያሳየውን ንቀት ነው እዚህ ውሰጥ የከተተኝ። ያ ነው አጋርነቴን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳደርግ የሚያደርገኝ፡፡እኔ ማንም ይሁን ማን ለኢትዮጵያ ደሞክራሲን የሚያመጣ ልቤን ያሸንፈዋል፡፡ በ97 ያየሁትን የማውቀው እኔ ነኝ።

ጥያቄ፦ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እጅግ የሚያደንቁትን አንድ ሰው ይጥቀሱ ቢባሉ ያ ሰው ማን ነው?

ብዙ አሉ እኮ! ለምሳሌ የኦሮሞ ወጣቶች ይሄን አመጽ የጀመሩት ጀግኖች ናቸው። ብዙ ድንቅ ኢትዮጵያዊያን አጋጥመውኛል፤ እነ መረራ፣ እነ እስክንድር…

ጥያቄ፡- አንድ ነበር ያልኩዎት?

አና ጎሜዝ፦ አንድ ጀግና የለም። ዲሞክራሲ በአንድ ሰው አይገነባም። ብዙ ሰዎች ናቸው የሚገነቡት። እነ አንዳርጋቸው፣ ደግሞ ብርቱካን ሚደቅሳ ድንቅ ሴት ናት። የማይታወቁ ስንት ወጣቶች አሉ። ዐብይ የሚባለውን ሰው መቼ አውቀው ነበር? ሥልጣን ከያዘ በኋላ ነው ስለርሱ የሰማሁት፡፡

ጥያቄ፦ከፖርቱጋል ውጭ በዓለም ላይ ካሉ አገሮች በአንዱ የመኖር ዕድል ቢሰጥዎ የት ይመርጣሉ?

አና ጎሜዝ፦ ተመልከት! አሜሪካ እንደ ዲፕሎማት ስኖር ይህ ዓይነቱ ነገር (ግሪንካርድ) ይቀርብልኝ ነበር። እኔ እንዲህ ዓይነት ነገር ደስ አይለኝም። ፖርቹጋላዊት ሆኜ ኖሬ መሞት ነው የምፈልገው። ያ ግን ለሌሎችን አገሮች ከመቆርቆር አይከለክለኝም።

የጠ/ሚኒስትሩ የመፍትሔ እንክብሎች ይቀጥላሉ ወይስ አልቀዋል?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አገሪቱ በፈተና ምጥ ተይዛ ባለችበት ወቅት ነበር ወደ ሥልጣን የመጡት። መንበረ ሥልጣኑን በተቆጣጠሩ የመጀመሪያ ቀናቶች ውስጥ ከችግሮቿ የሚገላግላት ሁነኛ መድኃኒት ማቅረብ ባይችሉም የሕመም ማስታገሻ እንክብሎችን እያዋጧት ነበር ማለት ይቻላል።

    
180621 Kolumne BefeQadu Z Hailu

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማንኛውም ዜጋ ሳይቀር በማይከብድ ቋንቋ ፍቅር፣ ይቅርታ እና ሠላምን ሰብከዋል። ይህም ጊዜያዊ እፎይታ አስከትሎ ነበር። ነገር ግን እያደር የሕመም ማስታገሻው እየደከመ፤ ሕመሙ እየበረታ መምጣቱ አይቀጥርም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ተዘጋጅተዋል?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከሚያደርጓቸው ንግግሮች ጀምሮ እስከሚወስዷቸው እርምጃዎች ድረስ አስደናቂ ነበሩ። ፍጥነታቸው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ያልተለመደ ከመሆኑም በላይ ለመተንተንና ቀጣዩ ይህ ይሆናል የሚለውን ለመተንበይ ይቸግር ነበር። አሁን ግን ፍጥነቱ ጋብ ያለ ይመስላል። ጠንካራ ትችቶችም እየተሰነዘሩ ነው። ፍጥነቱ በምን ምክንያት ተቀዛቀዘ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገራሚ የመፍትሔ እንክብሎቻቸውን ጨርሰው ይሆን?
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የድንገቴ እርምጃዎች ሕዝቡም መደነቅ እየቀነሰ፣ በጣም ተቀባይነት ያገኙ ሐሳቦቻቸው ሳይቀር ለትችት እየቀረቡ ይመስላል። ሌላው ቀርቶ “መደመር” የሚለውና የከተሜው አንደበት ውስጥ ዘሎ የገባው  መርሓቸው ሳይቀር ተጠያቂ ሆኗል። “ከእነእከሌ ጋር አልደመርም” ከሚሉት ቅሬታዎች ጀምረው “መደመር ማለት ምንድነው? የራስን አመለካከት ይዞ ግዜያዊ ችግርን ለመፍታት መተባበር ወይስ ማንነትን ጥሎ በዘላቂነት መዋሐድ?” እስከሚለው ጥያቄ እየተነሳ በተቺዎች ተብጠልጥሏል።
በዚህ ሳምንት ደግሞ ሪኔ ሌፎርት እና አሌክስ ደዋል የተባሉ ሁለት የኢትዮጵያ ጉዳይ ታዋቂ ተንታኞች ስለኢትዮጵያ መፃኢ ግዜ የሚታያቸውን ጽፈዋል። ሁለቱም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አካሔድ አደጋ ያዘለ እንደሆነ አልሸሸጉም። ትልልቆቹን የፖለቲካ ተቃርኖዎች እየፈቱ ነው ተብሎ በሚታሰብበት ወቅት የፖለቲካ ተንታኞች አደጋው ብቻ የሚታያቸው በምን ምክንያት ነው?
ሰዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ እርምጃዎች መደነቅ የቀነሱት በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው፣ ዋና የሚባሉት ፖለቲካዊ የለውጥ እርምጃዎች በሙሉ ተበስረው አልቀዋል። ከፖለቲካ እስረኞች ፍቺ የተሰደዱትን እስከ መመለስ፣ ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ሠላም ከማውረድ ጀምሮ የመንግሥት ንግድ ተቋማትን ለከፊል የግል ይዞታ ማዘዋወር ጉዳይ፣ ከአፋኝ ዐዋጆች መሻሻል እስከ ተቋማዊ መልሶ ማዋቀር – ሁሉም ተነግረው አልቀዋል። እናም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነዚህ የበለጡ አስደናቂ ቃል ኪዳኖችን መግባት ከዚህ በኋላ ይቸግራቸዋል።
ሌላኛው ምክንያት የዜጎች እምነት መቀየሩ የወለደው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጡ ሰሞን የነበረው ግንዛቤ እርሳቸው የወሰዷቸውን እርምጃዎች ያደርጉታል ብሎ ለመገመት የማያስችል ነበር። ምክንያቱም ጠቅላይ ሚነስትሩ ከኢሕአዴግ የወጡ እንደመሆናቸው “የኢሕአዴግን ጥቅም” ብቻ (ማለትም “ሰጥ ለጥ አድርጎ መግዛት”) ያስጠብቃሉ ብሎ ይገመት የነበረ መሆኑ ነው። አሁን ግን ባለፉት አራት ወራት በተወሰዱት እርምጃዎች ስርዓቱ መለወጡን፣ አሮጌው ኢሕአዴግ ሞቶ አዲሱ መወለዱን ብዙ ሰው አምኗል። ሕዝቡ ፍላጎቱ እና ስርዓቱን የሚመለከትበት ዓይን ስለተቀየረ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አዳዲስ ቃል ኪዳኖች እንደ መጀመሪያው ሰሞን አይደነቅም።
ቀጥሎ ምን እንጠብቅ?
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክሮች፣ ንግግሮች እና አዳዲስ የማሻሻያ ሐሳቦች ዜጎችን ማስደነቅ ማቆማቸው ወይም መቀነሳቸው የማስታገሻ እንክብሎቹ መሥራት ማቆማቸውን ያሳያል። ቀጥሎ ፍቱን መድኃኒት የሚጠየቅበት ወቅት መምጣቱ አይቀሬ ነው።
አምና ፖለቲካችን ጤነኛ አልነበረም። ፖለቲከኞች በየእስር ቤቱ፣ በስደት እና በጦር ሜዳዎች ተበትነው ነበር። ሲቪል ማኅበራት ተመናምነው ሞት አፋፍ ላይ ነበሩ፤ ብዙኃን መገናኛዎችም እንደዛው። ዘንድሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕመም ማስታገሻ እንክብሎች አማካይነት የተበተኑት ተቃዋሚዎች ተሰባስበው ዳግም እየተደራጁ ነው። ዐዋጆች እየተከለሱ እንደመሆኑ ሲቪል ማኅበራት እና ብዙኃን መገናኛዎችም ቀስ በቀስ ማበባቸው አይቀርም። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማስታገሻ ሕክምና የፖለቲካ ምኅዳሩን ሊያሰፋው ይችላል፤ ለዘርፈ ብዙ ሕዝባዊ ጥያቄዎች ግን መድኃኒት ሊሆኑ አይችሉም። የተቃዋሚዎች መልሶ መደራጀት አዳዲስ ጥያቄዎች እና አዳዲስ አማራጮችን ለሕዝብ ያስተዋውቃል። የሲቪል ማኅበራት እና ብዙኃን መገናኛዎች ማንሰራራትም ዜጎች መብቶቻቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን የሚያቀርቡባቸው አማራጮችን ያበረክታል። ያኔ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ፈተና በይፋ ይጀምራል።
መፍትሔው ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ብዝኃነትን እንድትቀበል መፍቀድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከቀዳሚዎቻቸው በርግጥም የተለዩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ኢሕአዴግ በምርጫ ሊሸነፍ እንደሚችል ቢሰጉም እንኳ የፖለቲካ ምኅዳሩን ክፍት አድርጎ መጫወት ይጠበቅባቸዋል። ይህን ማድረግ የቻሉ እንደሆን ከማስታገሻ እንክብሎች ወደ ፍቱን መድኃኒት መስጠቱ ይሸጋገራሉ። አለበለዚያ ግን ወደ ቀደመው የቀውስ አዙሪት ተመልሶ ለመግባት ረዥም ግዜ አይወስድም።

በፈቃዱ ኃይሉ
በዚህ አምድ የቀረበው አስተያየት የጸሀፊው እንጂ የዶይቸ ቬለን አቋም አያንጸባርቅም።

አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበረከት ስምኦን ላይ ያወረደበት ናዳ

አቶ ንጉሱ ጥላሁን

ሰሞኑን የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በርከትን እና አቶ ታደሰን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ማገዱን ተከትሎ አቶ በረከት ለተለያዩ ሚዲያዎች ውሳኔው:-

=> በስብሰባው ለመታደም ዋስትና ስላልተሰጠኝ መገኘት አልቻልኩም፣

=> ውሳኔው መሰረተ ቢስ ነው፣

=> የኤርትራ መንግስት እጅ እና ፍላጎት ስለላበት በኤርትራ መንግስት ትዕዛዝ የተፈፀመ ነው፤ እኔ እርምጃ የተወሰደብኝ ኤርትራዊ ዘር ስላለኝ ነው፣

=> አቶ ደመቀ ጠቅላይ ሚንስትር እንዳይሆን ስለታገልኩት በቂም ነው፣

=> እኔ ከኦሮሞ አንድ አመራር ወደ ሀላፊነት(ጠቅላይ ሚንስትርነት)እንዲመጣ ፍላጎት ነበረኝ ታግያለሁም፣

=> የአማራ አመራር አቅም የሌለው በመሆኑ የወጣቱን ጥያቄ ስላልመለሰ አቅጣጫ ለማሳት ከሱዳን፣ ከትግራይ እና ከአፋር እያጋጨ ነው፣ ሲሉ ብአዴንን በመክሰስ እና ማንንም ሊያሳምንልኝ ይችላል ያሉትን ሁሉ ጠጠር በመወርወር ላይ ናቸው ፡ ፡
===
ይህንን ሰምተን እና እዳምጠን አቶ በረከትን በዕድሜያቸው አክብረን እውነትን ሲያዛቡ እና በተንኮል መንገዳቸው ሲነጉዱ ለግንዛቤ ይሆን ዘንድ ጥቂት ነገር ማለት ፈለግን ::
===
አቶ በረከት የጠየቁት ዋስትና የአማራ ወጣቶች እንዳያጠቋቸው በመፍራት እንደሆነ ገልፀዋል :: እሳቸውን የመሰለ አድራጊ ፈጣሪ፣ የፈለጉትን አንጋሽ እና አውራጅ ሰው ወደ ዋስትና ጠያቂነት ሲለወጥ ዋስትናውን ከመጠየቅ ለምን ወጣቱ ይህንን አለ፤ ምንስ አጠፋሁ ? ብሎ ራስን መመርመር የሚበጅ ስለመሆኑ እሳቸውን መምከር “ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች ” ስለሚሆን እንተወው:: ግን ግን በየወረዳው መድረክ ፈጥረን ባወያየንባቸው መድረኮች ሁሉ ወጣቱ ” በረከት የአማራን መብት አስረግጧል፣ ህዝቡን አስቀጥቅጧል፣ አማራን አንገቱን እንዲደፋ አድርጏል … ወዘተ “ብሎ ሲሞግተን እኛም ወጣቱን ስንመክር የሚወርድብንን ትችት ቢያዩት አቶ በረከት አመራሩን ባልኮነኑ እንላለን::
===
ውሳኔውን በተመለከተ አቶ በረከት መሰረተ ቢስ ነው አሉት እንጂ እኛ ደግሞ ብአዴንም ሆነ አመራሩ መወቀስ ካለበት ውሳኔውን በማዘግየቱ ን እና ከልክ ያለፈ ትዕግስት ማሳየቱ ነው:: አቶ በረከት ማዕከላዊ ኮሚቴው ስለ ክልሉ ህዝብ ተጠቃሚነት እንዳይወያይ በማድረግ የንትርክ እና የጭቅጭቅ ኮሚቴ ካደረጉት እኮ ከአምስት አመታት በላይ ሆኗቸዋል:: በብአዴን ውስጥ ብቃት ያለው አመራር እንዳይወጣ እና የአማራ ህዝብ ጥያቄ በአግባቡ እንዳይነስ ትንሽ ሀሳብ ብልጭ ያደረገን ሰው ከሌሎች ጋር ሆነው “ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ” በማለት አጎብዳጅ እና ተላላኪ ሆነን እንድንኖር ታግለዋል:: እሳቸውውን የታገሉትን ህይወታቸው እንዲመሰቃቀልም ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል:: ጥረትንም የተጨመላለቀ የቤተሰብ እና የጏደኛ ጎጆ መውጫ አድርገውታል ተብሎ መገምገሙን በሶስትና አራት ወራት አይረሱትም:: ስለሆነም ውሳኔው የዘገየ ከበቂ በላይ ፖለቲካዊ መሠረት ያለው ነው እንላለን:: በህግ የመጠይቅን ጉዳይ በተመለከተ ህግ ይየውም እንላለን::
===
” ውሳኔው የኤርትራ መንግስት እጅ አለበት፤ እኔም ኤርትራዊ ስለሆንኩ ነው ” ያሉት ነገር እርስ በእርሱ የሚጣፋ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አቶ በረከት ብአዴን በሌላ ውጫዊ አካል የሚታዘዝ ድርጅት ነው እያሉንም ስለሆነ “እሱ አክትሟል፤ እንኳን ከሌላ አገር በብእእዴንም ውስጥ ባዕድ ሀሳብ ሊጭን ይእሚችል ሀይል የሚሸከም ትከሻ የለም ” ልንላቸው እንወዳለን:: እኛም ወደ ኤርትራ የሄድንበትን ምክንያት ህዝብ ስለሚያውቀው ውሀ እንደማይቋጥር እሳቸውም አይጠፋቸውም :: በነገራችን ላይ የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ልዑክ መስከረም 3 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ ኤርትራ ይጏዛል::
===
አቶ ደመቀን በተመለከተ “ጠቅላይ ሚንስትር እንዳይሆን ስለታገልኩት ነው ” ላሉት ደግሞ ምክንያታቸው ደካማው ነው:: ምክንያቱም አቶ ደመቀ በእጩነትም እንዳይያዙ ለምክር ቤት አቅርበው እንደነበረ እና ምክንያታቸውም አዲስ አመራር እንዲመጣ ፍላጎት ስላላቸው መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ከመሆኑም በላይ የአቶ ደመቀን ትልቅነትና አስተዋይነት ያሳየ የወራት ትውስታ ስለሆነ ይህም ውሀ አይቋጥርም:: ለነገሩ አቶ በረከት በብአዴን መድረክ የአመራር ሽግሽግ አጀንዳ በማቀንቀን እሳቸው የሚያዙት አሻንጉሊት ሊቀመንበር ለማስቀመጥ አምርረው ታግለዋል፣ ጉዳዩንም እስክ ደምፀ ውሴኔ አድርሰዋል:: ሀሳባቸውም ውድቅ ተደርጏል:: አቶ በረከት ኦሮሞ ወደ ስልጣን ይምጣ ብለው እንደሞገቱ እና እንደታገሉ ገልፀዋል :: ነገር ግን ዶክተር አብይ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመረጡ ብአዴን ሲታገል ” አብይ ኢትዮጵያንም ኢህአዴግንም አይመጥንም ” ብለው የታገሉት አብይ የየትኛው ብሄር እና ድርጅት መሪ መስለዋቸው ይሆን? ምን አልባት በአልባት በሁለቱ ህዝቦችና ድርጅቶች መካከል ቅራኔ እንዲፈጠር ታስቦ ከሆነ ይሄ አልፎበታል:: ለነገሩ ባለፈው አመት በባህር ዳር የኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የጋራ መድረክ ስንፈጥር አቶ በረከት እና መሰሎቻቸው ” መርህ አልባ ግንኙነት ነው” ብለው መድረኩ እንዳይካሄድ እስከ ዋዜማው ጥረት ማድረጋቸው እና ትምክህትና ጥበት ያልተቀደሰ ጋብቻ መሰረቱ ብለው እንደወረዱብን ለምናስታውስ ጉዳዩ የቆየ እና ባህሪያዊ ስለሆነ እንደተለመደው እናልፈዋለን::
===
በመጨረሻም የአሁኑ የአማራ ክልል አመራር ደካማ ነው ሲሉ አመራሩን አጣጥለዋል :: ለመሆኑ ይሄ አመራር ደካማ ቢሆን ኖሮ እንዴት እሳቸውን ያህል ጉምቱ ፖለቲከኛ እና የተቀናቀኑትን መቀመቅ የሚያወርዱ ሰው ተቋቋመ? እንዴትስ ለእርሶ አላጎበድድም አለ? እንዴትስ ያልተደፈሩትን የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ደፍሮ ተሟገተባቸው? ባለፉ ጥቂት ወራት በነበሩን ስብሰባዎችስ ብአዴን ላይ ተስፋ አለኝ አላሉምን ? አሁን ያለው አመራር የወጣቱን የስራ ዕድል ይፈጠርልኝ ጥያቄ አይመልስም ሲሉ ለመሆኑ ይህ አመራር ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ምን እየሰራ እንደሆነስ ያውቁ የለም ? የአማራ ወጣት ጥያቄ ስራ እና ዳቦ ብቻ ነው እንዴ ? ጥያቄው እኮ ከዳቦ በላይ ነው:: ጥያቄው ነፃነት፣ እኩልነት፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት፣ ማንነት ነው:: ለነገሩ እነዚህ ጥያቄዎች አማራ ሲያነሳቸው ለእርስዎ ትምክህት ናቸው:: እነዚህን ያነሱ የብአዴን አመራሮችን አሳደው መምታትዎትን መናገር እርስዎን መድፈር ስላልሆነ እንናገረዋለን:: አመራሩስ ደካማ ቢሆን ማን መራው፣ ማን አሰለጠነው፣ ማን ገመገመው ቢባል ቀዳሚው ሰው አቶ በረከት መሆንዎ አይቀርምና የአመራር አያያዜ ምን ይመስል ነበር ብሎ ራስን መፈትሽ ከእውነት ያስታርቃል::

ታዲያ ይህንን ስል የትንታኔ ብቃቶትን፣ የትግል ድፍረቶትን እና እድሜዎትን በመድፈር አይደለም :: ቢያድልዎት ኖሮ ልክ እንደ አንዳንዶቹ የድርጅታችን መስራቾች “ቦታውን የያዘው አመራር በራሱ መንገድ ይምራ፣ እኛ ገብተን አንፍትፍት ” ብለው መድረኩን ለባለመድረክ ቢልቁ መልካም ነበር እንላለን:: እርሶን ያህል የኢትዮጵያን ሚዲያዎች ያሾር የነበረ ሰው አንድ ድብቅ አላማ ያነገብ እውደድ ባይ ግለሰብ የሚዘውራት እዚህ ግባ ማትባል ቦታ መገኘትዎትም እርስዎን አይመጥንም እና ይቅርብዎት እንልዎታለን::

ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል

የ VOA ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ ከ20 ዓመታት ገደማ በፊት ለአቶ በረከት ስምዖንን ለቃለመጠይቅ ሲጋብዛቸው በ “በአማርኛ ቋንቋ መናገር አልፈልግም” ብለውት ወደ አዳነች ፍስሃዬ refer ብሏቸው ከዚያ ጊዜ በኋላ ቃለመጠይቃቸው ከትግርኛ ትርጉም ይቀርብልን ነበር።

ዛሬ “አማራ ነኝ”.. “ከእኔ ወዲያ ለብአዴን ማን ሊመጣ”.. እያሉ ነው። ምን እንበላቸው .?

Negesse Teferedegn

በዓመቱ ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት ለኢንስቨትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበር ተባለ

ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
አጭር የምስል መግለጫበ2010 የበጀት ዓመት በኢንቨስትመንት ፍሰት 4.6 ቢሊዮን ለማምጣት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ማሳካት የተቻለው መጠን ግን 3.75 ቢሊዮን ዶላር ነው

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በላቸው መኩሪያ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በፅሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ከአንድ ወር በፊት የተጠናቀቀው የ2010 የበጀት ዓመት ለኮሚሽኑ በብዙ ረገድ “በጣም ፈታኝ ግን ደግሞ ውጤታማ ነበር” ብለዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተስተዋሉ ያለመረጋጋቶች በኢንቨስትመንት ላይ “ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል።” የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ዕቃን ወደ አገር ውስጥ ከማስገባት እና ማስወጣት ጋር በተያያዘ ያለው የማጓጓዣ ፍጥነት (ሎጅስቲክስ) ችግር ሌሎች ፈተናዎች ነበሩም ተብለው በኮሚሽነሩ ተጠቅሰዋል።

• በሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ጥቅም ላይ ከዋለው ቦምብ ጋር የሚመሳሰል ቦምብ በተጠርጣሪ ቤት ተገኘተፅዕኖው በኢንቨስትመንት ፍሰት ረገድ በቀዳሚው የ2009 የበጀት ዓመት ከነበረው በታየው መጠነኛ መቀነስ ይገለፃል የሚሉት ኮሚሽነሩ በተጠቀሰው ዓመት የነበረው የኢንቨስትመንት ፍሰት መጠን 4.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደነበረ ያስታውሳሉ። በ2010 የበጀት ዓመት በኢንቨስትመንት ፍሰት 4.6 ቢሊዮን ለማምጣት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ማሳካት የተቻለው መጠን ግን 3.75 ቢሊዮን ዶላር ነው።እንደዚያም ቢሆን እንደኮሚሽነር በላቸው በዓመቱ ውስጥ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፤ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ሥራ እንዲቀጥሉ በማገዝ እና መተማመንን በመፍጠር ረገድ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል።

በበጀት ዓመቱ ከ270 በላይ የውጭ ባለሃብቶች ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን ባለሃብቶቹ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ኢንቨስት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዓመቱ ኮምቦልቻ እና መቀሌ ፓርኮች ሥራ መጀመራቸው ከኮሚሽኑ ስኬቶች መካከል እንደሚጠቀሱ ያወሱት ኮሚሽነር በላቸው አሁን በአገሪቱ ውስጥ ስራ በጀመሩ ስድስት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሃምሳ ሃምስት ሺህ ለሚጠጉ ሠራተኞች ስራ ተፈጥሯል ብለዋል።

• እነ አንዷለም አራጌ ህይወት እንደገና

ኮሚሽኑ የማምረቻ ዘርፍ እ.ኤ.አ በ2025 ከአገሪቱ ዓመታዊ ጠቅላላ ምርት ሃያ በመቶ ድርሻ እንዲኖረው ዕቅድ ያለው ሲሆን የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ይሄንን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ያግዘኛል ብሎ ያስባል።

የፖለቲካ አለመረጋጋት ለኢንስትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበርImage copyrightAFP

በአሁኑ ወቅት ዘርፉ በዓመታዊ አጠቃላይ ምርት ውስጥ ያለው ድርሻ አምስት በመቶ አይሞላም። ከኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ምርቶችን ወደ ውጭ አገር በመላክ ወደ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል።በአዲሱ የ2011 የበጀት ዓመት የኢንቨስትመንት አዋጁን የማሻሻል ዕቅድ እንዳለ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ማሻሻያዎቹ በአንድ በኩል ኢትዮጵያ መንግስታዊ የልማት ተቋማትን ወደ ግል ለማዛወር ከያዘችው ውጥን ጋር የሚያያዙ ሲሆኑ በሌላ በኩል ለባለሃብቶች የሚሰጡ ማትጊያዎች አፈፃፀምን መሠረት ያደረጉ ናቸው።

እየተሻሻለ ባለው የአሰሪና ሠራተኛ ህግ የዝቅተኛ ደሞዝ ወለል ጉዳይ እንደሚካተት የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ ይህ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ክፍያ ዝቅተኛነት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ቅሬታዎች መፍትሄ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ አክለው ተናግረዋል።

• የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ?

አብዲ ዒሌ እስር ቤት ገብቷል፣ በረከት ስምዖን የውርደትን እፍታ ቀምሷል (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Former Ethiopia's Somali region president Abdi Iley

አብዲ ዒሌ እስር ቤት ገብቷል። በረከት ስምዖን የውርደትን እፍታ ቀምሷል። ጌታቸው አሰፋ የሚደበቅበት ጉድጓድ ፍለጋ ላይ ተጠምዷል። አባይ ጸሀዬ ድምጹን አጥፍቷል። ስብሃት ነጋ በመቀሌ አክሱም ሆቴል ውስኪውን እየላፈ ቆዝሟል። በእብሪትና ትዕቢት ያበጠው የጌታቸው ረዳ ልብም ተንፍሷል። ሳሞራ የኑስ የጡረታ ዘመኑን በስጋት ይገፋል። አስመላሽ ወ/ስላሴ ግን አሁንም ይፎክራል። ሞንጆሪኖም ”የትላንቱ ይበጀናል” ዜማ እያቀነቀነች በትካዜ ተውጣለች። ደብረጺዮን መሀል ላይ ይዋልላል። አዲስ አበባ ሲደርስ ይደመርና ወደ መቀሌ ሲመለስ ይቀነሳል።

ወደ ለውጡ ቅጥር ግቢ ለመግባት አጥር ላይ የተንጠለጠሉ አንዳንድ የህወሀት አመራሮች እንዳሉ ይሰማል። የህዝብ ማዕበል ወደ ለውጡ ይጎትታቸውና የነባሮቹ ህወሀቶች ቁንጥጫ ይመልሳቸዋል። አጥሩ ላይ እንደተንጠለጠሉ አራት ወራት አለፋቸው። ህወሀቶች ዘይቱን ሳያዘጋጁ ሙሽራው መጥቶባቸዋል። ዘይቱ ንሰሀ ነበር። ሙሽራው ደግሞ ለውጥ። እናም ዘይቱን ያላዘጋጀ ሙሽራውን እንዴት ይቀበለው?

ባለፈው ሳምንት አንድ የናዚ የጦር ወንጀለኛ ለ70 ዓመታት ከተደበቀባት አሜሪካ ለጀርመን ተላልፎ ተሰጥቷል። በ95 ዓመቱ በእጆቹ ላይ ሰንሰለት ጠልቆ ከርቸሌ ገብቷል። በእኛም ታሪክ ተመሳሳይ ክስተት ተመዝግቧል። በቀይ ሽብር ዘመን መሪ ተዋናይ የሆኑ ነፍሰ ገዳዮች ለዘመናት ከተደበቁባቸው ሀገራት ማንቁርታቸው እየታነቀ ለፍርድ ቀርበው አይተናል። የቀልቤሳ ነገዎን እዚህ ላይ መጥቀስ ይቻላል። ከፍትህ ለጊዜው ማምለጥ ይቻል ይሆናል። ቢዘገይም ግን አይቀርም። ሞት ቢቀድም እንኳን ነፍስ ዘላለሟን እረፍት ታጣለች። መለስ ዜናዊ ለፍርድ ሳይቀርብ ቢሄድም ስሙ በምድር እየተረገመ፡ ነፍሱ በሰማይ እየተሰቃየ ነው። ከመቃብር በላይ ትቷት ያለፈው በዘር ልትበጣጠቅ ጫፍ የደረሰች ሀገር ነበረችና መለስ ከምድራዊ ፍርድ ቢያመልጥም ዘላለማዊ ስሙ የተወገዘ፡ የረከሰ ሆኗል።

ጌታቸው አሰፋ ለጊዜው ከፍትህ ተደብቋል። እንደሰማሁት በኢንተርፖል ራዳር ስር እንዲሆን እንቅስቃሴው ተጀምሯል። ወደ አሜሪካ ያሸሻቸው ቤተሰቦቹ ዘንድ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል። ከፎቶና ከቪዲዮ ተደብቆ ስለኖረ በቀላሉ ላይታወቅ ይችላል። ግን አያመልጥም። እየተሽሎከለከ እድሜውን ሊያቆይ እየሞከረ ነው። ከመደበኛው ፍርድ ለጊዜው ሊሸሸግ ይችላል። ከምንም በላይ ከህሊና ፍርድ አያመልጥም። በሄደበት የሚከተለው ትንሹ እግዚያብሄር የሆነው ህሊናው እረፍት ሲነሳው ይኖራል። የኢትዮጵያ እናቶች እምባስ መች በከንቱ ፈሶ ያውቅና?

ህወሀቶች ጸሀይ እየጠለቀችባቸውም የተሰጣቸውን እድል መጠቀም አልቻሉም። ሰሞኑን ከመቀሌ ተሰብስበው ያወጡት መግለጫ ጥርሱ አልቆበት በድዱ ለመናከስ የሚንገታገት ያረጀ አውሬ አስመስሏቸዋል። በምስራቁ በር አንዱ የጥፋት እጃቸው ተቆርጦባቸውም ለተስፋ መቁረጥ እጅ መስጠት አልፈለጉም። አብዲ ዒሌ የተሰኘ የጥፋት ፈረሳቸው አይናቸው እያየ ከፍትህ እጅ ላይ ወድቋል። አያስመልጡት ነገር አቅም የለም። የእነሱንም እድል እጣ ፈንታ እርግጠኛ አይደሉም። ለጊዜው እድል ሰጥቶ የተዋቸውን ህዝብ ትዕግስት ግን እያስጨረሱት ነው።

ብአዴን

ብአዴን መጨረሻውን እያሳመረ ይመስላል። ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በህወሀት ልክ የተሰፋለትን ጥብቆ አድርጎ የኖረው ብአዴን ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ ከህወሀት ጋር የሚደረገው ፍቺ ቅርብ መሆኑን አመላካች ነው። ብአዴን ቆርጧል። የህወሀትን ቀሚስ አውልቋል። አርማና ስያሜ መቀየሩ ትርጉሙ ቀላል አይደለም። ህወሀትን ብአዴንን ጠፍጥፎ ሲሰሰራ የልደት ቀኑን ከህወሀት የአፈጣጠር ታሪክ ጋር እንዲመሳሰል ስለመደረጉ መገመት ይቻላል። 11 ቁጥር ላይ የቆረበው ህወሀት የብአዴንን የልደት ቀን ህዳር 11 ላይ ያደረገው ያለምክንያት አልነበረም። አርማውን ከህወህት አርማ የተቀዳ አድርጎታል። ብአዴን አርማውን ብቻ ሳይሆን በህወሀት የተተከለትን የልደት ቀኑንም መቀየር ይኖርበታል።

የብአዴን መግለጫ የህወህት የበላይነት ፍጻሜ ላይ ትልቅ ሚስማር የቸነከረ ነው። ኦህዴድ ታህሳስ ላይ የብሄር ጭቆና የለም የሚል አዲስ ትርክት ይዞ ሲመጣ ህወሀት የሚይዝ የሚጨብጠው አጥቶ ነበር። የመጽአት ቀኑን ያየበት አስደንጓጩ ምልክት የታህሳሱ የኦህዴድ መግለጫ ነው ማለት ይቻላል። በብሄር ጭቆና ላይ ታሪክ ፈጥሮ ስጋ ደምና አጥንት አልብሶ፡ እስትንፋስ ዘርቶበት ኢህ አዴግ በሚባል ፈረስ ኢትዮጵያን ለብዙ ዘመናት ሊጋልብ የተፈናጠጠው ህወሀት በኦህዴድ መግለጫ ህልሙ በአጭሩ ተቀጨ። ሲጠበቅ የነበረው የብአዴን አቋም ነበር። ሰሞኑን አፈረጠው። የብአዴን መግለጫ በህወሀት አንገት ላይ የጠለቀ ገመድ ማለት ነው። የሚቀረው ገመዱን ሸምቀቅ ማድረግና ህወሀት የረገጠውን መንጠልጠያ ማንሳት ነው። አዲዮስ ህወሀት!

መግለጫው በህወሀት ህልውና ላይ ሪፈረንደም ያደረገ ነው። የአማራ ክልል ወሰን ከእንደገና ይሰመር ዓይነት አቋም ከብ አዴን ሲሰማ መቼም ተአምር ነው። ይህ ማለት የወልቃይት፡ ራያና ሌሎች አከባቢዎችን በተመለከተ ብአዴን ጥያቄ ለማንሳት ወስኗል ማለት ነው። በቅርቡ በአንድ መድረክ ላይ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የወልቃይትን ጉዳይ ከእንግዲህ ችላ የምንለው አይደለም ሲሉ ጠርጥሬአቸዋለሁ። ይሀው የድርጅታቸው አቋም ሆኖ ይፋ ተደርጓል። የሱዳን ወታደሮች ከያዙት የኢትዮጵያ መሬት እንዲለቁ በብ አዴን መጠየቁ ለህወሀት ትልቅ መርዶ ነው። ህወሀት ለሱዳን የኢትዮጵያን መሬት የሰጠበት ድብቅ ስምምነት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው። ሱዳን ለህወሀት ምሽግ ናት። የክፉ ጊዜ መደበቂያ ናት። ለውለታዋ የጎንደር መሬት በስጦታ ተብርክቶላታል። ሱዳን ያን መሬት ከተነጠቀች ከህወሀት ጋር ያላትን ድብቅ ፍቅር መቀነሷ አይቀርም። ያ ደግሞ የትግራይ ህዝብ የተፋው ዕለት የሚደበቅበትን ዋሻ ያጣል ማለት ነው።

ብ አዴን በግል መብት ላይ የወሰደው አቋም በራሱ ለህወሀት አስደንጋጭ ነው። በቡድን መብት ስም ዘረኝነትን በማስፋፋት የበላይነቱን አስጠብቆ ለመኖር ፕሮግራም(ህገመንግስት) የቀረጸው ህወሀት ከብአዴን በቃህ ተብሏል። የቡድን መብት እንዳለ ሆኖ የግለሰብ መብት ላይ ማተኮር ለዴሞክራሲ ወሳኝ ነው የሚል አቋም ላይ የደረሰው ብአዴን በብሄራቸው እየተደበቁ ቁማር የሚጫወቱ የዘር ፖለቲካ አቀንቃኞችንም ቅስማቸውን የሰበረ አቋም ላይ መድረሱ አስደናቂ ነው። ህወሀት በቁሙ ተዝካሩን በላና አረፈው። በዚህ አልቆመም። የህወሀትን ጥቅም በአማራው ህዝብ ኪሳራ ለማስጠበቅ በብ አዴን ውስጥ የተሰገሰጉ አፍቃሪ ህወሀት የሆኑ ቀንደኛ አመራሮችን ጠራርጎ ማባረር የጀመረው ብአዴን ለህወሀት አንድ መልዕክት እንዲደርሰው የፈለገ ይመስላል። ”በቃ”

በረከተ መርገምት

አቶ በረከት ስምዖን አየሩን ተቆጣጥሮታል። የመንደር የኮሚኒቴ ሬዲዮ ሳይቀር ደጅ እየጠና እንዳለም ሰምቼአለሁ። ብዙ ሰዎች በረከት ሰሞኑን የሰጠው ቃለመጥይቅና አብሮት ከተባረረው ታደሰ ጥንቅሹ ጋር የጻፉት ደብዳቤ ላይ በማተኮር የበረከት ቅጥፈቶች ላይ ጊዜ ሰጥቶ ሲወያዩ ታዝቤአለሁ። ለእኔ በረከት እንዲህ ተዝረክርኮ፡ በስጋት ተንጦ፡ ቅስሙ ተሰብሮ፡ የሚደገፍበት አጥቶ፡ ሲንከራርተት እንደማየት የሚያስደስት ነገር አላየሁም። ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፡ በምዕራብና ምስራቁ እየተወነጨፈ ያሻውን ሲያደርግ፡ ሲያስገድልና ሲያሳስር የከረመ፡ ምድር አልበቃ ብላው በሰማይ መንሳፈፍ እስኪቀረው የደረሰ፡ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ረጅሙን ርቀት የተጓዘ ሰው ዘመን ተገልብጦ፡ በሰፈረው ቁና የሚሰፈርበት ጊዜ መጥቶ ”እንዳልንቀሳቀስ ገደብ ተጥሎብኛል” ዓይነት እዬዬውን ሲያስነካው እንደመስማት ያለ ምን ድል ይገኝ ይሆን? እንደዚያ በትዕቢት ተወጥሮ የሚታወቀው በረከት ኩምሽሽ ብሎ፡ በፍርሃት ርዶ የምቆም የምቀመጥበት አጣሁ ሲል መስማት ለእኔም ሆነ የፍትህን መረጋገጥ ሲናፍቁ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ነው።

በረከትን ሳስበው ሁል ጌዜ ከአእምሮዬ ጓዳ ብቅ የሚለው አንድ ወቅት ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ስለበረከት የተናገሩት ነው። ”መለስ ክፉ ነው። መለስን የበለጠ ክፉ ያደረገው ደግሞ በረከት ስምዖን ነው” እንግዲህ የክፋት አለቃ፡ የጭካኔ ደቀመዝሙር፡ የተንኮል ሀዋሪያ፡ የቅጥፈት አምባሳደር የሆነው በረከት ስምዖን ጊዜ ጥሎት፡ ዘመኑ አብቅቶ ዋጋውን ሊያገኝ ነው። በየሚዲያው ቀርቦ ”ቅዱስ ነበርኩ፡ ክንፍ የሌለው መልዕክ ከእኔ በላይ የት ይገኛል?” ዓይነት የሌባ አይነደረቅ ዲስኩሩን እየለቀቀው ነው። በረከት ብአዴኖች ላይ የጀመረው ውግዘት አፈጣጠሩንና ስነልቦናውን እንድንመራመርበት የቤት ስራ የሚሰጠን ሆኗል። ምድር የተጠየፈችው፡ በእኩይ ምግባሩ ሀገርና ህዝብ በአንድ ሰልፍ ፊት የነሳው ሰው፡ ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚል መፈክር ይዞ መልሶ ለእኛው ልንገራችሁ ማለት የጤና አይመስለኝም። የሚቀርቡት ወዳጆች ካሉት በጊዜ ዶክተሩን እንዲጎበኝ ቢመክሩት ጥሩ ነው። ጤናም እንዳልሆነ በብዙ ይነገርለታል።

በዘመኑ በሀሳብ የተለዩትን ላይ በጭካኔ አስሯል። የፖለቲካ ተቀናቃኝ ያላቸውን የሀሰት ዶሴ እየከፈተ ከእድሜአቸው ላይ ተቀንሶ በማጎሪያ እስር ቤት እንዲሰነብቱ አድርጓል። መለስ ሲሞት ለቅሶን በሀገር ደረጃ አደራጅቶ፡ ማቅ አስለብሶ፡ ህዝቡን በማህበር እንዲያዝን በማድረግ ታላቅ ግፍ የፈጸመ ወንጀለኛ ነው። በረከት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጥቁር ስም ያለው ነው። ዛሬ ”በነጻነት፡ በፖሊሲ” እንከራከር ሲል አለማፈሩ ይገርማል። ዛሬ እሱ የሚጠይቀውን መብት ትላንት የጠየቁትን ሲያዋርድ፡ የቴሌቪዥን ድራማ እያሰራ ስም ሲያጨቀይና ገፍቶም ሲያሳስርና ሲያስገድል ዓለም የሚያውቀው ሰው ዛሬ ተነስቶ ”በፖሊሲ እንከራከር” ብሎ አይኑን በጨው አጥቦ መጥቷል። እንግዲህ ‘ፍትህ’ ለዚህ ሰውዬም ያስፈልጋል።

በረከትን ‘ኢትዮጵያዊው’ ጎብልስ በሚል የሚጠቅሱትም አሉ። የናዚው የፕሮፖጋንዳ ማሽን ጆሴፍ ጎብልስ ”ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” የሚለውን አስቀያሚ ትርክት ለዓለም ያስተዋወቀ፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በዚሁ ትርክቱ የናዚን ወታደሮችና የጀርመንን ህዝብ ለጦርነት የማገደ እንደነበረ ይነገርለታል። በረከት ስምዖን የዘመኑ ጎብልስ ሆኖ ኢትዮጵያውያን ላይ ተሰይሟል። ሀገሪቱን የውሸት ፋብሪካ አድርጓት አንድ ትውልድ በውሸት ተወልዶ እንዲያድግ ፈርዶበታል። በእርግጥ በናዚው ጎብልስና በህወሀቱ ጎብልስ መሀል ልዩነት አለ። ጎብልስ የቆመለት የናዚ ስርዓት ሲገነደስና እንደአምላክ የሚያየው አዶልፍ ሂትለር ራሱን ሲያጠፋ ጎብልስም ስድስት ልጆቹን መርዝ አብልቶ እሱንና ሚስቱንም በሽጉጥ ገድሎ ይህቺን ምድር ተሰናብቷል። በረከት ስምዖን ግን ፈሪ ነው። አምላኩ መለስ ዜናዊ ሞቶም እሱ እስከአሁን አለ። ወንድሙን ገድሎበት እንኳን በታማኝነት የገበረለትና የተገዛለት የህወሀት ስርዓት በቁሙ ሲገነደስ እያየ በረከት ግን መኖር ይፈልጋል። ፈሪ። መርገምት።

የራያ ሕዝብ “መብታችን ይከበር” ጥያቄ – ወሎየ አማራ ነን፣ ነፃ ኢትዮጵያዊያን ነን!

የራያ ሕዝብ መብታችን-ይከበር ጥያቄ:-
ወሎየ አማራ ነን፣ነፃ ኢትዮጵያዊያን ነን!!
ነሓሴ 23፣ 2010 ዓ.ም.
(ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር)

Wollo Ethiopian Heritage Society

የራያ ሕዝብ በተዋረድ ከአማራ፣ኦሮሞ፣ አገው፣ ትግሬና አፋር የተዋለደ ዛሬ እንደ ሌላው ወሎየ ባህላዊ ማንነቱን አማራ ብሎ ያስመዘገበ ህዝብ ነው። በሰሜን እንደርታ፡በደቡብ የጁ፡በምስራቅ አፋር እንዲሁም በመዕራብ ላስታ ያዋሱኑታል። በታሪክም በትግሬ፣ በዋግሹምና በየጁ ባላባቶች መካካል የፉክቻ ማዕከል ሆኖ ቆይቷል፡፡

የራያ ሕዝብ የራሱ የሆነ ልዩ ባህል እና ወግ አለው፡፡ ከሚደነቅበትና ከሚያስደስት ባህሉ ሁሉም እምነት ተከታዮች በተለይም ሙስሊም-ክርስቲያን፡ደገኛ-ቆለኛ ሳይል ተከባበሮ የሚኖርበት እሴቶችን ማቀፉ ነው። ብዙሃን ቋንቋዎችን ያንጸባረቀ የራሱ አነጋገር፡ አለባበስ፡ አዘፋፈን፡ የሰርግና የለቅሶ ስነስርአት ያለው ኩሩ እና ጀግና ውሎየ ነው። «ወያኔ» ተብሎ የሚጠራውን የ «አንረሳ» አመጽ በጣሊያን ወረራ ዘመን ያነሳውም ይህ ሕዝብ ነው።

ራያ ከዚህ ወራሪ-መሰሉ ትሕነግ መስተዳደር በፊት መቼም ቢሆን ከወሎ ክፍለ ሀገር ዉጭ የተዳደረበት ወቅት የለም። ነገር ግን ለ27 አመታት ካለ ፈቃዱ የደቡብ ትግራይ ወረዳ ሆኖ እንደ ወልቃይት፡ ጠገዴና፡ ጠለምት ሕዝብ በትግሬ ወያኔዎች ጫማ እየተረገጠና እየተፈናቀለ የቆየ ሕዝብ ነው። የትግራይ ክልላዊ መንግስት የመገንጠል ማስፈራሪያውን እሙን ለማድረግ እጅግ ለም እና ሰፊ የእርሻና ሌሎች ጥሬ ሀብቶች መገኛ የሆነዉን የራያን መሬት በጉልበት በመጠቅለል የተቃወሙትን ሰዎች በገፍ በማሰር በመግደልና ከቀያቸው በማሳደድ ሀብቱን በተለያዩ ህገወጥ የፓርቲ ኩባንያዎቹ በመቆጣጠር የራያን ሕዝብ የበይ ተመልካች አድርጎታል። ከመሃል አገር በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቀውን የዝርፊያ ሃብት ወደ መቀሌ ለማሸሽ እንዲመቸውና ኮረምንና አለማጣን ለማቆርቆዝ መንገዶችንና ሀዲዶችን በባዶ በበረሃ እንዲያልፉ አድርጓል፤እያደረገም ነው።

ሰሞኑን በሀገራችን በተፈጠረዉ የለውጥ ጭላንጭል ምክንያት ልክ እንደሌሎቹ አካባቢዎች ራያም እጂግ ሰላማዊና ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ የመብታችን-ይከበር ጥያቄዉን ቢያቀርብም ከኮራጁ «ወያኔ» የገጠመዉ የተለመደዉ የጉልበት ምላሽ ነዉ። የአለማጣ ሕዝብ ጌታቸው አሰፋ የተባለውን የደህንነት ወንጀለኛ ከአሁን በኋላ
አንተ አትወከለንም ብሎ ከስብሰባ አዳራሽ አባሮታል። የአለማጣ የዋጃና የኮረም ነዋሪዎች የለውጥ ሃይሎችን ለመደገፍ በተደጋጋሚ በሞከሩት የአደባባይ ድምፅ ማሰማት ታላቅ ድብደባዎች፣ጅምላ አፈናዎች፣ እስሮች፣ ግድያዎችና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች በመቀሌው የገዥ ቡድን ተደማምረውባቸዋል። በትሕነግ ጀነራሎች
የተጠለፈው የአፋር ልዩ ፖሊስና የወያኔ አጋዚ ሚሊሽያ ወረዋቸው ይገኛሉ። ቀደም ብሎ በወልድያ፣ ቆቦና መርሳ እንዳደረጉት የኮረምንና የአለማጣን ወጣቶች ከየቤቱ እያደኑ ወደ ማረሚያ ካምፖችና ወደ በረሃ ጨው ማምረቻዎች እያጋዟቸው ይገኛሉ።

የራያ ሕዝብ የጠየቀዉ ራስን-በራስ የማስተዳደር መብቱን፣ የተረሳውን እድገቱንና፣ በተለይም በጉልበት የተቀማዉን የታሪክ ማንነቱን ነዉ!

ወሎ ውርስና ቅርስ ከጎናችሁ መቆሙን በአጽንዖት እየገለጸ፦

(1) ጥልቅ ተሃድሶ አካሂዳለሁ የሚለው የኢሐዴግ አዲስ አመራር በአማራው ሕዝብ በተለይም በራያና በወልቃይት ነዋሪዎች ላይ ለረጅም ጊዜ የተነጣጠረውን የግፍ ስርዓት በጆሮ ዳባነት ወይንም ችግሩን በማቃለል እይታ ማፌዙን አቁሞ የዜጎችን እኩልነትና መብቶችን እንዲታደግ በጥብቅ እንጠይቀዋልን፤

(2) መላው የወሎ ሕዝብ ልጆችህ በተናጠል ሲመቱ በቁጭት ማየቱን አቁመህ ባለንላችሁ መንፈስና አንድ ግንባርነት ለነጻነትህ ካልታገልክ የጭቆና አገዛዝ በጫንቃህ ላይ እንደሚፈራረቅብህ አይቀሬነቱን ልናስግነዝብ እንወዳለን፤እንዲሁም

(3) የታመቀው የራያ ጉዳይ እየገነፈለ ይበልጥ ወደተወሳሰበ ደረጃ ከማደጉና በደቡብ ክፍለ-ሃገሮቻችን 3 ሚሊዮን ተፈናቃዮችን ወዳፈራው ሕዝብ-ለሕዝብ ግጭት ከማምራቱ በፊት የፌደራል መንግስት ተጠያቂነቱን በመገንዘብ ክልለ-መንግስታዊ ጽንፈኝነትን ባፋጣኝ እንዲያስቆም በአንክሮ እናሳስባለን።

ዘረኝነት፡ አግላይነት፡ ዘራፊነትና አምባገነንነት ያክትሙ!

የራያ ሕዝብ ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው!

ሰላምና ፍትህ ለመላው የኢትዬጵያ ሕዝብ!