የቀን ጅቦች ያሠማሯቸውና በወያኔ እንክርዳድ ያበዱ እንክርዳዶች! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

እነዚህ ወያኔ ዘራሽ እንክርዳዶች ‘የገዳዮቻችንን አርማ አንግበውና እነሱን ወክለው’ አዲስ ፀረ-ዲሞክራሲና ነፃነት ‘የFB ዘመቻ ከፍተዋል::

ይህ ቡድን “በልሣነ አማራ” እየተመራና ወያኔያዊ መርዙን የሚተፋው ጋጠወጥ ምንደኛ መንጋ እርቃኑን እየወጣ ነው:: የወያኔን የጎሣ ፓለቲካ የተጋቱና የጠመቀውን የጎሣ ፌደራሊዝም እያነበነቡ በዚህ ወያኔያዊ እንክርዳድ ያበዱ እንክርዳዶችን እያየሁ ነው:: የወያኔን ቀበሮ ለሽርፍራፊ ጥቅም ሲሉ ያመለኩ ወደል አህያዎች (the jackasses who worshipped weyane jackals) ‘ሂትለራዊ የአርያን ዘር መርዝ’ እየረጩ ታላቁን ኢትዮጵያዊ የአማራ ህዝብ ከሣር ቅጠሉ ጋር እያጋጩ ወያኔያዊ ተልዕኮአቸውን እየተወጡ ነው:: “ልሣነ አማራ” እ.አ.አ. በነሃሴ 1 ቀን 2018 በፌስቡክ ገፁ ፁህፍ “አብይ፣ ኦህዴድ፣ ኦነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ሆዳም አማራ፣ ህወሃት፣ ደደቡ ዳያስፖራ በአንድነት አማራን አፍዝዞ ለዳግም ባርነት ለማዘጋጀት አንድ ላይ ናቸው:: …የአማራን ብሔርተኝነት በማንኮላሸት የአንድነት ፖለቲካን በአማራ ላይ ለመተግበር በፕ/ር መስፍን፣ በግምቦት 7፣ በሰማያዊ ፓርቲ እና በዶ/ር አብይ ስምምነት መደረሱን ዉስጥ አዋቂዎች ጠቁመዋል” ይለናል::

በነባራዊው የኢትዮጵያ ፓለቲካ የአንድነት ፓለቲካን የሚጠላው “የጎሣ ፌደራሊዝምና የጎሣ ፓለቲካን” አራማጅ ወያኔና ፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎች ብቻ ናቸው:: የአንድነት ፓለቲካን ማጥላላት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከሚጠሉና ለመጥፋቱ ከሚሰሩ ሃይሎች ጋር ማበር ነው:: ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማራና ከአማራ ክልል ውጭ ለሚኖሩ አማሮች ዜግነት ብቻ ሣይሆን የህልውናና የማንነት መታወቂያ ነው:: የአማራ ብሔረተኝነት ፓለቲካዊ ርዕዮተ-ዓለም አይደለም:: የአማራን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል የዘር መፈናቀልና ጭፍጨፋን (extensional threat) ለመመከትና በአማራ ላይ የሚቃጣን ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አማራዊ አንድነት መፈጠር አለበት በሚል እሣቤ ይሁንታን ያገኘ ማህበራዊ ስብስብ ነው:: የአማራ ህዝብ ያለውን የእምነት፣ የፓለቲካና የፆታ ልዩነት ታሳቢ አድርጎ ለውህደት (uniformity) ሣይሆን በጋራ የህልውና ጥያቄ ላይ የሚፈጠር የጋራ የሃሣብ መግባቢያ ሠነድ (conceptual memorandum of understanding) እንጂ በርዕዮተ-ዓለምና በመርህ የተዋቀረ ፓለቲካዊ ድርጅት አይደለም:: “ከኔ ሌላ ውጪ” የሚልን አምባገነናዊ የመንደር እቁብና እድር የመፍጠር እቅድም አይደለም (unity doesn’t mean uniformity):: ይህ አደገኛ የእቃ ጨዋታና የጨቅላ ተረት ውጤቱ አስከፊና እንኳን የአማራን ህልውና አደጋ ላይ ከሚጥል የዘር መፈናቀልና ጭፍጨፋን (extensional threat) መመከት ቀርቶ የአማራን ህዝብ በማህበራዊና ፓለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ለመጣል የተነደፈ የአማራና የኢትዮጵያ ጠላቶች ንድፍ ነው:: ኢትዮጵያውያንን በጎሣና በእምነት ስም በጅምላ እየተጣቆሰ በማስተባበር አማራን ከወገኖቹ በመነጠል ከወገኖቹ በማጋጨት ህልውናውን ከበፊቱ በባሰ መልኩ ለማምከን የሚሠራ ደባም ነው:: ‘አያድን ጋሻ ቂጥ አስወጊ’ እንደሚባለው::

ልሣነ ወያኔዎቹ “አብይ፣ ኦህዴድ፣ ኦነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ሆዳም አማራ፣ ህወሃት፣ ደደቡ ዳያስፖራ በአንድነት አማራን አፍዝዞ ለዳግም ባርነት ለማዘጋጀት አንድ ላይ ናቸው” ብለውናል::

እኔ የማንኛውም ድርጅት አባልና ነገረፈጅ አይደለሁም:: ጥብቅናዬ ለእውነትና ስለእውነት ብቻ ነው:: “ልሣነ አማራ” እና መንጋዎቹ ባለብዙ ግንባር ጦርነት ከፍተዋል:: “ግንቦት 7 የአማራ ወጣቶችን ሲያስገድል፣ ሲያሳስር የነበረዉ ይህ ድርጅት፣ በንፁሀን ደም የታጠበ፣ እነ ገብርየን ገድሎ በደማቸዉ የለመነ፣ ነፈዝ የአማራ ዲያስፖራዎችን ኪስ እያለበ…” ነውም አሉን:: ይህን ለማረጋገጥ አሉባልታን ሣይሆን መረጃንና ማስረጃን በማያሻማ መንገድ (burden of proof beyond reasonable doubt) ማቅረብ የሚገባው “ልሣነ አማራን” እንጂ ግንቦት 7 አይደለም:: ከድርጅቱ ጋር በፓለቲካ አመለካከት አለመስማማት መብት ሲሆን መረጃን ሳያቀርቡ “ግንቦት 7 የአማራ ወጣቶችን ሲያስገድል፣ ሲያሳስር የነበረዉ ይህ ድርጅት…” ብሎ መፈረጅ የስም ማጥፋትና ወንጀል ነው:: ለማንኛውም ምክንያታዊ ህሊና ይህ ፍረጃ የአማራና የሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በአርባ ጉጉ፣ በደኖ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ኢሊባቡር፣ ጉራፈርዳ፣ ጌዲኦ፣ ጉራጌ፣ በኦሮሚያ ወ.ዘ.ተ. በወያኔ እጅና በወያኔ አቀናባሪነት የተፈፀሙ የዘር መፈናቀልና ጭፍጨፋዎችን ለጨፍጫፊውና ህዝብን በሃይል ለአገተው (captor) ወያኔን እንደእራስ በማየትና ስሜቱን በመካፈል (by showing empathy & sympathy to captors or ‘Stockholm syndrome) በታጋቹና በተጠቂው (victims) በህዝብ ስም አጥቂው ወያኔን በማወደስ ወንጀሉን ወደሌሎች ማዞር ነው:: በአማራ ብሔረተኝነት ስም ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነትን መዋጋትና ወያኔያዊ ተልዕኮን ማሣካት ነው:: “ግንቦት 7…ደደቡ ዳያስፖራ በአንድነት አማራን አፍዝዞ…በአማራ ወጣቶች በደማቸዉ እየየለመነ፣ ነፈዝ የአማራ ዲያስፖራዎችን ኪስ እያለበ…” የሚለው ክስ ገራሚ ነው:: ለእነዚህ የይትኖራ ገ/ማህበር ተራኪዎች ወይም እነ ቆምጬ አምባው እንደነሱ “የአንስታይን ማሰቢያ ህሊና” ያልተገጠመላቸውን “ነፈዝ፣ ደደብ ዲያስፓራ፣ ዲቃላና ግንቦት 7 ላስገደላቸው አማሮች ገንዘብ እያዋጡ” በማለት ለአማራ ወጣቶች ግድያ ግንቦት 7ን ብቻ ሣይሆን አማራውን ተጠያቂ የሚያደርጉ ዋልጌዎች አማራ ወገኖቹን “ግንቦት 7 እንዲገድል ገንዘብ የሚያዋጣ” የአማራን ዲያስፓራ የሚወነጅሉ ድፍኖች መወከል ያለባቸው አማራን ሳይሆን አማራና ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ለ27 ዓመታት ሲገድል የነበረውን ወያኔን ነው:: “Clean your finger before pointing it at others” (Benjamin Franklin)

ምንደኞቹ አንዱዓለም አራጌ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ እና ታማኝ በየነ ግልፅ ደብዳቤና ማስጠንቀቂያ ሰተዋል:: የግለሰብና የድርጅትን ነፃነት በነፃነት ስም ይነድፋሉ:: ነፃነትን የሚፈልጉት በተራቸው አምባገነናዊ ወያኔን ሆነውለመጨቆን ይመስላል:: ሲያሻቸው በእነዚህ ባለተልዕኮዎች የተመረዙ ሃገር በቀል መናጆዎችም ጭራሹን “ኢትዮጵያን የፈጠረ አማራ ነው” እያሉ በአማራ ስም አማራውን ያስነክሳሉ:: አማራንም ይሁን ኢትዮጵያን የፈጠረ ፈጣሪ ነው:: ከእነርሱ ውጪ ማንም “የድርጅት ጽ/ቤት እንዳይከፍት” ይላሉ:: በክልላችን “ከኛ ወዲያ ላሣር ነው”: ማንኛውም “የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አይገባብንም” ካሉ እነርሱን ጨምሮ ሁሉን አይነት ድርጅት እንዲቋውም የፈቀደውን ህግ ሲጥሱ እነርሱም እንደሚከስሙ አይረዱም? ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነትን ከኢትዮጵያዊው አማራ ውስጥ አውጥተው “ወያኔያዊውን ብሔረተኝነት” መዝራትስ ያምራቸዋል? አማራን ገንጥለው” የአማራን ሪፑብሊክ” መስርተው ለመኖር ያልማሉ? ለመሆኑ አማራን የመቀበልና የማግለል ልዩ አማራዊ መብት የሰጣቸው ማነው? በአማራ ውስጥ በአማራ ስም የሂትለር ደቀመዝሙሮች ሆነው ሌላውን አማራ “ዲቃላ፣ ነፈዝና ደደብ” የሚል ስያሜ ያወጣሉ:: ‘ያሳደከው ውሻ ሲነክስህ፤ ያስተማርከው ዳኛ ሲፈርድብህ’ ይሉሃል ይህ ነው::

“…የፖለቲካ ማህበር(ፖርቲ) እምነት አራማጅ ወይም ጀሌ ካልሆንኩ ገነት መግባት አትችልም ብባል እንኳ ወደ ገነት አለመሄድን እመርጣለሁ” (ቶማስ ጀፈርሠን) “…If I could not go to heaven but with a party, I would not go there at all. (Thomas Jefferson)

የግለሰብና የድርጅትን ነፃነት በነፃነት ስም ይነድፋሉ:: ዴሞክራሲና ነፃነትን ልክ እንደፈጣሪያቸው ወያኔ ለማፈን ገና ለስልጣን ሳይበቁ ያልማሉ:: ወዴት ነው የሚወስዱን? ለምን? ይህ ነው ተግባራቸውን ልዩ የወያኔ ዘመቻና ተልዕኮ የሚያደርገው ይህ ነው::

መብትና ነፃነትን የማያውቁ፤ ዴሞክራሲያዊ ተግዳሮትን ያልተላበሱ ቶሎ ፈላ ግንፍሎች ህዝብን ወደ ገደል ለመምራት ከጅለዋል:: ነፃ ያልወጡ ነፃ አውጪዎች በአማራ ህዝብ ስም እንዳይነግዱ በቃችሁ ልንላቸው ይገባል:: ድሮም ‘ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም’::

ይህ መብትን መጋፋት ብቻ ሣይሆን እብሪት ነው። ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ምልከታ ነው። “በኛ መንገድ ካልሄዳችሁ ፅድቅ የለም” ከሚሉን ወያኔዎች በግል የማሰብ፣ የመወሰንና የማመን መብትን ወደሚገፉ ጋጠወጦች መሸጋገራችን ይሆን? ‘ሞቷን የከጀለች አይጥ የድመት አፍንጫ ታሸታለች’ እንዲሉ። እነ አንዱኣለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ታማኝም ይሁን አንዳርጋቸው ለህዝብ ነፃነት ዋጋ የከፈሉት እነዚህ ድፍኖች በአንቀልባ ላይ እያሉ ነው።

ይህ የጥፋት መንገድ ነው። ጠጪውን “እኔ ባቀናሁት ስካር አትንገዳገዱ” የሚል እራሱ ሰካራም ነው። አምባገነንነት የሚጀመረው ባልወከለው ግለሰብና ህዝብ ስም መናገር ሲጀመርና ሃሣብን ማፈን ሲጀመር ነው።

ይህን ብዬ ላብቃ::

በሲቪክ ብሔረተኝነት አድጌ የጎሣ ብሔረተኝነትን ጭቃ አላቦካም። በጎሠኞችና በጎሣ ፓለቲከኞች ዓይነ-ምድር አልጫወትም።

ከዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት እንዲሁም የሲቪክ (ዜግነት) ብሔረተኝነት ውጪ ዴሞክራሲያዊ ሐገርም ይሁን ሕዝብ አይኖረንም። “በጎሣ ፌደራሊዝም”የተረጨ ወያኔያዊ መርዝ የሚመክነው በዴሞክራሲ ብቻ ነው። ዴሞክራሲና ነፃነት የሚመጣው ከዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ብቻ ነው። እራሱን በሃሣብ፣ በአመለካከትና በጠራ መርህ ነፃ ያላወጣ ግለሰብም ይሁን ቡድን በሌሎች ላይ ሊጭን የሚችለው ዴሞክራሲን ሣይሆን አምባገነንነትን ነው። ከስልጣን በፊት የሚደረግ ሐሳብን የማፈን ተግባር አምባገነንነት መለማመድና በሁዋላ መተግበር ነው።
የኔ ምንነቴም ሆነ ማንነቴ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ብቸኛ ሠፈሬ፣ መንደሬና ሐገሬ ኢትዮጵያ ናት። ያለ ጎሣ ፓለቲካና ድርጅት ነፃነት የለም ቢሉኝ እንኩዋን በገዛ ፈቃዴ በባርነት መኖርን እመርጣለሁ። ወደ እንሠሦች እርከን ደረጃ ከመውረድ ከሠውነት ጋር ማለፍ እመርጣለሁ።

ማንኛውም ዓይነት ፅንፈኝነት ልክ አለመሆን ብቻ ሣይሆን አደጋም ነው:: ማንኛውም ዓይነት የጎሣ አክራሪነት ከየትም ይሁን ከየት ይምጣ የአስተሳሰብ መላሸቅ፣ መጥበብና መውረድ ምልክት ነው። ከልጅ ጋር መጫወት ልጅን ለመምሰልና ልጅን ማስደሰት እንጂ ልጅ መሆን አይደለም። አንሣችሁ አታሣንሱን። ዘቅጣችሁ አታዝቅጡን።

የምንድን ከሆነ የምንድነው በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ባለቤት ያቀለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም። የመረጣችሁት መንገድና አቋራጭ ሁሉ ገደል ነው።

‘ድሮም ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም!። ‘አላዋቂ ሣሚ ንፍጥ ይለቀልቃል!’።
‘በሬ ሆይ ሣሩን ብለህ ገደሉን ሣታይ!’

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s