ማነህ ባለሳምንት እኔ ነኝ የምትል ተረኛ ገዥ ብሄርተኛ (አዲስ ጀምበር)

ለነጻነት የተከፈለ መሰዋት ቅኝ አገዛዝን በአካል ማሰወገድ ቢችልም ቅኝ አገዛዝ ትቶት የሄደውከፋፍለህ ግዛ ጦስ ሃገር እና ህዝብን መልሶ ወደ ውስብስብ የፖለቲካ ችግር ስላስገባ ዛሬም እኩልነት፤ ነጻነት እና ፍትህ እንደራቁ ናቸው፡፡ የነጻነት ትግሉ ቡድኖችን ለስልጣን አበቃ እንጅ ሀገር እና ህዝብን ከባርነት አላወጣም፡፡

የቅኝ አገዛዝን መወገድ ተከትሎ የፖለቲካ ተዋናይ የሆኑት ሊህቃን ናቸው፡፡ የሁሉም ሊህቃን መነሻ ሀገር እና ህዝብ ቢሆንም የአብዛኛወቹ ሊህቃን መድረሻ ግን የስልጣን ፍላጎትን ማሳካት ሆነ፡፡ ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም የተወሰኑ ሊህቀን ቃላቸውን አክብረው በኩል አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ገብተው የህዝብን ዳኝነት ሲቀበሉ ድብቅ የስልጣን ፍላጎት ያነገቡ ግን ሁልጊዜም ሃገር እና ህዝብን ያምሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ ገበሬዎች ግፍ እና ግብር በዛ ብለው በተለያዩ ጊዚያት በአገዛዝ ላይ ያደረጉት አመጽ ራሳቸው በራሳቸው ለራሳቸው ያደረጉት እንቅሳቃሴ ነበር፡፡ የ1950ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ በሃገር እና በህዝብ ስም የተደረገ የ”ሊህቃን” እንቅስቃሴ ነበር ማለት ይቻላል፡፡በዚህ እንቅስቃሴ ለብሄር እና ለዲሞክራሲ ጥያቄ ሀገራዊ ቅርጽ እና ይዘት ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ በዚህ ሂደት ነው ሊህቃን ወደ ብሄር እና ሀገራዊ ፖለቲካ የገቡት፡፡ ወያኔም የዚህ ሂደት ውጤት ነው፡፡

የወያኔ ትግል መነሻ የትግራይ ብሄር ተቀማ የሚለውን የዮሃንስ ዘውድ ማስመለስ የሚል ነው፡፡ ነገስታት ዘውድ የተቀማሙ ቢሆንም የተቀማውን የብሄሬን ዘውድ ላስመልስ ብሎ የተነሳ ብሄር በታሪክ የለም፡፡ ወያኔ ብሄር ሳይሆን ስግብግብ ፍላጎቱን ለማሳካት በትግራይ ብሄር ስም የተደራጀ ዘረኛ ቡድን ነው፡፡ይህን ዘረኛ ማንነት ከወያኔ ህልውና በፊት እነ ወልደ ስላሴ/ስብሃት /ነጋ ገና ተማሪ እያሉ የትግራይ ሴቶች ትግሬ ያልሆኑ ባሎች አገቡ በማለት ትግሬ ያልሆነ ሁሉ ከትግራይ ይውጣ በማለት ዘረኛ አቋማቸውን ያስተጋቡ ነበር፡፡ ይህ የነወልደስላሴ ነጋ ዘረኛ ማንነት ነበር ለ1968 የወያኔ ማኒፌስቶ እርሾ እና መሰረት የሆነው ፡፡

ወያኔ ለስልጣን የበቃው አልደገፋችሁኝም ፤አልተባበራችሁኝም ያላቸውን ትግራዊያን ከሃዲ በማለት ጨፍጭፎ፤ በትግራይ ባዶ 6 እስር ቤት አሰቃይቶ፤ በስሌት በአውሮፕላን አስደብድቦ/ሀውዜን/፤ ለእርዳታ የመጣውን እህል ቀምቶ እና ሽጦ ህዝብን በረሃብ ቀጥቶ፤ እንወያይ ብሎ የጋበዘውን ሌላውን የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት በቤቱ በእንግድነት በአስተኛበት አርዶ ፤ መላውን የትግራይን ህዝብ አንድ ለአምስት ጠርንፎ ነው፡፡ አንዳንድ የወያኔ ነባር ታጋዮች እንደሚገልጹት ወያኔ የገደለው የትግራይ ህዝብ ቁጥር ደርግ ከገደለው በአራት እጅ ይበልጣል፡፡ ወያኔም በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የሚፈጽመው ጭካኔ በትግራይ የተለማመደውን እንደሆነ በስፋት ይነገራል፡፡

ወያኔ ባልጠበቀው እና ባላሰበው ሁኔታ ኢትዮጵያን የመግዛት እድል ሲገጥመው ስሜቱ እና ስሌቱ የትግራይን ኢኮኖሚ አጎልብቶ እና መከላከያውን አጠናክሮ ኢትዮጵያን እስከቻለ መግዛት፤ ካልሆነ የትግራይ ሪፖብሊክን አውጆ የዮሃንስን ዘውድ መድፋት ሆነ፡፡ ሃሳቡን ለማሳከት ለም መሬቶችን ከየቦታው ነጠቀ፤ የኔ አይደሉም የሚላቸውን እየነቀለ የእኔ የሚላቸውን እየተከለ በየቦታው ወደ ልማት አስገባ፡ የኮንትሮባንድ ንግድን ሙሉ በሙለ ተቆጣጠረ፤ የፋይናንስ ተቋማት ብቸኛ ተጠቃሚ ሆነ፡፡ ፌደራል ኢንቨስትመንትን ወደ ትግራይ አፈሰሰ፡ በአጭሩ የኢትዮጵያን ሀብት እና ንብረት በድርጅቶቹ እና በሰዎቹ እጅ ውስጥ አስገባ፡፡መከላከያ ሃሉን ፤ፌደራል ፖሊሱን እና ደህንነቱን በቁጥጥሩ ስር አዋለ፡፡

ወያኔ ስልጣኑን የበለጠ ለማጠናከር ህዝቡን በእምነት እና በብሄር ከፋፍሎ መጨፍጨፍ እና ማጨፋጨፍ ቀጠለ፡፡ ዛሬ በትግራይ እና በወልቃይት ፤በትግራ እና በራያ ፤በትግራይ እና በአፋር፤በአፋር እና በአማራ

፤በአፋር እና በኢሳ፤በአፋር እና በኦሮም፤በኦሮሞ እና በሶማሌ፤በኦሮሞ እና በጌዲዮ፤በኦሮሞ እና በአማራ፤ በኦሮሞ እና በጋምቤላ፤ በኦሮሞ እና በቤንሻንጉል፤በቤንሻንጉል እና በአማራ፤ በአማራ እና በቅማንት ፤በጉራጌ እና በቀቤና፤በሲዳማ እና በወላይታ…ወዘተ የሚፈሰው ደም ፤የሚወድመው ሃብት እና ንብረት ፤የህዝብ

መፈናቀል፤ ፤መሰደድ፤በረሃብ እና በችጋር መጠበስ የወያኔ ዘረኛ ብሄርተኛ ሰሜት እናስሌት መዘዝ ውጤት ነው፡፡

 

የወያኔ ስሜት እና ስሌት በከፋ ጭካኔ ቢታጀብም ያተረፈለት የተመኘውን ሳይሆን ከህዝብ የዘረፈውን ስልጣን ሃብት እና ንብረት ይዞ በስልጣን እንዳይቀጥል ያደረገውን ፤የኢትዮጵያን ህዝብ ተንበርክኮ ይቅርታ በመጠየቅ አገዛዙን ለማስቀጠል ያሰበውን ጥረት ያከሸፈበትን ፤በየክልሉ የዘር ግጨት እየጫረ ቀውስ የመፍጠር ሙከራውን ያዳከመበትን እንቢ አልገዛም ህዝባዊ አመጽን ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን አገዛዝ ለማሰወገድ በሚታገልበት ወቅት ፤እኩልነት፤ ነጻነት እና ፍትህ ለሁሉም በሚባልበት ወቅት ፤የብሄር መብት እና ነጻነት ይከበር በሚባልበት ወቅት ህዝብ እንደ ድሮ አብሮ አንድነት፤እኩልነት፤ነጻነት እና ዲሞክራሲ በሚልበት ወቅት ከወያኔ በኋላ ተረኛ ገTh ብሄርተኛ ነን ብለው ስልጣን የሚጠባበቁ ዘውገኞች እንደ ወያኔ የዘር ግጪት ይጭራሉ፤የዶክተር አብይ አህመድን ኢትዮጵያዊነት፤ዲሞክራሲያዊነት እና ተደማሪነት ጉዞን ያሰናክላሉ፤የየክልላቸውን ወጣቶች ወደራሳቸው መስመር ለማስገባት ከፋፋይ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ይህ ሂደት ወያኔን የት እንዳደረሰው በግልጽ እያዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ፤ሰቆቃ፤መፈናቀል፤መሰደድ፤መራብ…ወዘተ አነሰን ያለ ይመስል ወያኔን ተክቶ ወያኔነትን በከፋ ሁኔታ ለማራመድ የተዘጋጁ ይመስላሉ፡፡

ከዚህ ጋር አያይዞ በተለይ የኦሮሞ ብሄርተኞችን ከተወሰኑ ጉዳዮች አንጻር በሁለት  መድቦ አቋማቸውን ማየት ይቻላል፡፡አንዱ ከወያኔ በኋላ ተረኛ ገTh ብሄር ኦሮሞ ነው ሲል ሌላው ሃገራዊ እና ብሄራዊ ፍላጎቶችን አጣጥሞ በእኩልነት፤በነጻነት እና በፍትህ አብሮ መኖር ይቻላል ይላል፤ አንዱ ኦሮሞ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በማለት ሲከፋፍል ሌላው ሰርገኛ ጤፍ ናቸው ይላል፤ አንዱ መጀመሪያ ኦሮሞ ነን ኢትዮጵያዊነታችን በድርድር ስለሚወሰን ዛሬ ነጻ ኦሮሚያ ሲል ሌላው ኦሮሞ በደሙ እና በላቡ የገነባት ኢትዮጵያ ይላል፤አንዱ ዲባባ ሁሉ ኦሮሞ አይደለም ሲል ሌላው ኦሮሞነት በመወለድ አጋጣሚ የሚኮን እንጅ በሊህቃን በጎ ፈቃድ የሚቸር ወይም የሚነፈግ ማንነት አይደለም ይላል፤ አንዱ ኦሮሞ እንደወርዱ እና ስፋቱ ተጠቃሚ አልሆነም ሲል ሌላው እኩልነት፤ነጻነት እና ፍትህ የዜጎች መሰረታዊ እኩል ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንጅ ወርድ እና ስፋት እየተለካ የሚታደሉ መብቶች አይደሉም ይላል፤ አንዱ ፈጣሪ ለኦሮሞ በሰጠው መሬት ተጠቃሚው ሌላ ሆነ ሲል ሌላው ከብሄረሰቦች ሁሉ ኦሮሞን የበለጠ ወዶ የኢትዮጵያን መሬት ለኦሮሞ በብቸኝነት የሰጠ “ብሄርተኛ ፈጣሪ” የለም፤የሃገር ውሰጥ ፍልሰት ለኦሮሞ ብቻ የተፈቀደ ስለሆነ ኦሮሞ በደረሰበት የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉ ነባር ፤ፍልሰት ለሌላው የተከለከለ ስለሆነ በሄደበት ሁሉ መጤ ነው ብሎ ውጡ ማለት ከስግብግብነት እና ከራስ ወዳድነት የመነጨ አላስፈላጊ ተረክ ነው ይላል፡፡

በሁለቱ መካከል ያለው አቋም ግልጽ ነው፡፡ተረኛ ገTh ልሁን የሚለው ወያኔነትን በመድገም ኢትዮጵያን የመግዛት ተራ የኦሮሞ ነው፤ይህ ካልሆነ ከወያኔ የተረፈችውን ኢትዮጵያን ላፈራርስ ህዝብን ልግደል፤ላፈናቅል፤ላሰድድ፤ልበታትን፤ሃብት እና ንብረት ላውድም፤እያለ ነው፡፡ ይህን እብደት ለወያኔ ያልፈቀደው የኢትዮጵያ ህዝብ ተረኛ ገTh ልሁን ለሚለውም አይፈቅድም፤ፋኖ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው፤በቀለገርባ መሪዬ ነው ቄሮ የአማራ ደም ደሜ ነው ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ የእኔም መሪዬ ነው ያሉት ኢሬቻ የእኛ፤ጣና ኬኛ ተባብለው የፈጠሩት የትግል ቃል ኪዳን እና ትብብር ፤የከፈሉት የህይወት መሰዋዕት ፤ዘረኛ ወያኔን አስወግዶ በሌላ ዘረኛ ብሄር ለመተካት አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን የልብ ትርታ አዳምጦ የፈሰሰው እንባህን ላብስልህ፤ የፈሰሰው ደምን በአኩልነት፤ በነጻነት እና ፍትሃዊ የፖለቲካ ስርዓት ልዘክርልህ በሚል አቋምን የሚቀበለው ልግደልህ፤ልዝረፍህ፤ላፈራርስህ፤ ልበታትንህ…ወዘተ ብሎ ለመጣው ወያኔ እንዳደረገው በእንቢ አልገዛም አመጽ ሳይሆን እንደማዕበል ተደምሮ ወጥቶ ልባዊ ፍቅር በተሞላበት የምስጋና እና ድጋፍ ሰለፍ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን እና አፃነቱን ዳግም ላለማስነጠቅ  በተደመረበት፡ ወያኔ ምሽጌ እና መደራደሪያዬ የሚለውን የትግራይ ሕዝብ እያጣ ባለበት፡ የለውጥ ማዕበት አይሎ ሕዝብ የዶ/ር ዐቢይ አህመድን የለውጥ ጅምር ተቀብሎ በየክልሉ በነቂስ እየወጣ በርታ ወደሕጋዊና ተቋማዊ ለውጥ ግባ ግፋ በሚልበት ፡ ኦሮሞ ተረኛ ገዢ ነው ባይ ዘውገኞች ለውጡን በይፋ ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም አቅም አጥተው አድፍጠዋል፡፡ ላንተ ነው የቆምነው የሚሉት ብሔርና ክልል ዞሪያውን በተቀጣጠለ እሳት በተከበበት ወቅት ኦህዴድ (የነለማ መገርሳ ቡድን) ኦሮሞን ነፃ አያወጣም በማለት ቄሮውን ለማከፋፈል ኦሮሞን በማተራመስ ላይ ናቸው፡፡ ቄሮ ፋኖ ዘርማ … ወዘተ ኢትዮጵያን ነፃ አውጥተዋል፡፡ ወደባርነት ሊመልሱዋቸው እየጣሩ ያሉ ሥልጣን ናፋቂ ዘውገኞች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘረኞች ፤ ለስግብግቦች፤ ለራስ ወዳዶች ለገዳዮች እና ለዘራፊወች ቦታ እንደሌለው በእንቢ አልገዛም ጸረ ወያኔ አመጹ ፤መብቱን ፤ማንነቱን እና ነጻነቱን ላክብርልህ ለሚለውም ፍቅር እንደሚያዘንብለት በምስጋና እና ድጋፍ ሰልፉ በግልጽ አሳይቷል፤ የበደሉትን ይቅር እንደሚል ደጋግሞ ገልጿል፤በጋራ ቤቱ ኢትዮጵያ በእኩልነት፤በነጻነት እና በአንድነት ላይ በተመሰረተ ፍተሃዊ የፖለቲከ ስርዓት በጋራ አብሮ ለመኖር ወስነዋል፤የአንድ ብሄር የበላይነት አገዛዝ በወያኔ ይብቃ ዘወገኞች እና ባዶ አንድነቶች ህዝብን የስልጣን መወጣጫ ማድረጋቸውን ያቁሙ፤የኢትዮጵያ ህዝብ ተጨማሪ ሞት፤መፈናቀል፤አና መሰደድ አይፈልግም፤ሀገር ሲፈራርስ እና ህዝብ ሲበታተን ማየት አይሻም፤የሚፈልገው ሰላም እና መረጋጋት ፤ልማት እና እድገት እኩልነት እና ነጻነት፤የስልጣን ምንጭ እና ባለቤት ሆኖ ለተወዳዳሪዎች ዳኝነት መስጠት ስለሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ እንጅ ህዝብ የማተራመሻ አጀንዳ ለህዝብ አታቅርቡ ይህ ካልሆነ ግን የህዝብ እንቢ አልገዛም አመጽ እና ትግል ይቀጥላል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s