ከህወሓት ጋር ተናንቆ የተሰዋው የኢህዴን ታጋይ አስደማሚ ታሪክ! (ጓዶቹ እንደፃፉት)

(ጓዶቹ እንደፃፉት)

~”እኔ እኮ የምታገለው የኢትዮጵያን ህዝብ ከደርግ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት እንጅ ህወሓትን ለማገዝ አይደለም”

ይርጋ አበበ በትግል ስሙ ሀው ጃኖ/ ይባላል። ስለ ጀግንነቱ ደግሞ የራያው መብረቅ ይሰኛል

በ1975 ዓ/ም ትግሉን ከኢህዴን ጋር ተቀላቀለ፡፡ ጎበዝ ተዋጊ እና አዋጊ ጀግና ስለነበር የኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ለመሆን ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል መሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ የሚደረግ አድሎአዊ አሰራርን ለመቃወም አስችሎታል፡፡ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ወቅትም ሆነ በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሁም በኢህዴን ጦር መካከል በሚደረግ ስብስባ ህወሓት በኢህዴን ላይ የሚያደርገውን የቀጥታ ጣልቃ ገብነት በጽኑ ያወግዝ ነበር፡፡ ይህን በማድረጉም በአድር ባዩ ኢህዴን/ብአዴን አድር ባይ ዓመራሮች አልተወደደለትም ነበር።

ሓው ጀኖ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ የኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆኖ የተመረጠ ሲሆን ብዙ ጦርነቶችንም በአዛዥነት ተዋግቶ አዋግቷል። በተለይም በጉናና ደብረታቦር አካባቢዎች በተደረጉ ጦርነቶች የተሰጠውን ግዳጅ በጀግንነት ተወጥቷል።

ይህ ታጋይ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ከደርግ ሰራዊት ጋር በሚደረገው የጦርነት ወሎ ግምገማ ላይ በህወሃት አመራሮች የሚነሳውን “ኢህዴን ፈሪ ነው፣ በቀላል የውጊያ ስልት የተሰጠውን ግንባር አሸንፎ ብዙ ንብረት መማረክ እየቻለ መስዋትነት ስለምትፈሩ አውዳሚ የጦር ስልት ትከተላላችሁ፣ … ከደርግ የተማረኩ ወታደሮችንም በታጋይነት በኢህዴን ውስጥ እየገቡ እንዲታገሉ አድርጉ ሲባል ፍላጎቱ የላችሁም፣.. ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ብቻ የሚታገል ብሄርተኛ ድርጅት መሆኑን እያወቃችሁ ለምን ምርኮኛ ወታደሮች በህወሓት ስር ጭምር ተደራጅተው እንዲታገሉ አይደረግም የሚል ማዕከላዊነትን ያላከበረ ጥያቄ ታነሳላችሁ፣… በትግሉ ወቅት የሚማረኩ ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያዎችንም ህወሓት ብቻውን ለምን ይወስዳል የሚል ጥያቄ ታነሳለችሁ” የሚል ሂስ በሰፊው ይቀርብ ነበር።

ይህ ጀግና ደግሞ፣ “እኔ እኮ የምታገለው የኢትዮጵያን ህዝብ ከደርግ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት እንጅ ህወሓትን ለማገዝ አይደለም። ድርጅታዊ የትግል እኩልነት የለም።” የሚል ጠንካራ ትችት ያቀርብ እንደነበር በወቅቱ በትግሉ የነበሩ አሁንም በህይወት ያሉ ታጋዮች ህያው ምስክሮች ናቸው። በዚህ ሃገራዊ አቋሙ ምክንያት በህውሃት ከፍተኛ አመራሮች ጥርስ የተነከሰበት ሀወጀኖ መለስ ለታምራት “ከኢህዴን አመራርነት አሰናብቱ እና ገለል ይበል…” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ያስተላልፋል።

እነ ታምራት ላይኔም የመለስን ትዕዛዝ ተቀብለው ከአዋጊነቱ ተነስቶ የሎጅስቲክስ አመራር እንዲሆን ያደርጉታል። በዚህ ሃላፊነቱም ቢሆን የኢህዴን ሰራዊት አባላትና ክፍለ ህዝቦች ለስራ የሚያስፈልጋቸውን ከምግብ እስከ አልባሳት ድረስ እንዳያገኙ እና ትግሉን እንዲጠሉ ሲደረግ በተቃራኒው ከደርግ የተማረኩ ብርድልብሶችና ዮኒፎርሞች ግን ለህወሓት ሰልጣኞች ይሰጥ የነበረ መሆኑን አሁንም ለግምገማ ያቀርባል። በተለይም ህወሓት ሃገረ ሰላም ላይ በነፃ መሬት ወደ ትግሉ የተቀላቀሉ ወጣቶችን ትምህርት ቤት ከፍታ በራሷ ካሪኩለም ቀርፃ ስታስተምር ነባር የጎንደር እና የወሎ ራያ አማራ መሬቶችን በትግራይ ስር እንደሚተዳደሩ እና የትግራይ መሬቶች እንደሆኑ የምታስተምር መሆኑን የተረዳው ሀወጀኖ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” ሲል ለማዕከላዊ ኮሚቴ ጥያቄውን አቅርቦ ሲሟገት “…እኛ ኮሚኒስቶች ስለሆንን ሃገር የለንም። ደርግን ከጣልን በኋላ ህዝቡ እራሱ ይወስናል እናስተካክላለን…” እስከማለት ደርሰው እንደነበር የትግል ጓዱ አጫውቶኛል።

በዚህ ወቅት ታዲያ ህወሓት “ይች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም” የሚል ሴራ ተሴረበት። በኢህዴን አመራር በኩል ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቱ እንዲታገድና ከሎጅስቲክስ ሃላፊነቱም ተነስቶ በወቅቱ ኢህዴን ወታደር ያሰለጥንበት ወደነበረው አዲስ ዘመን አካባቢ እንዲዛወር አደረጉ። ይህን ጊዜ ሁኔታው አላምር ያለው ሀወጀኖ በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ የተያዘውን ይህንን ምስጢር ዘክዝኮ በመፃፍ ለተወሰኑ የድርጅት አባላት በድብቅ አሰራጨ። በውጤቱም እኛ ፈሪ ከሆንን ህወሓት እራሱ ይወጣው ሲል የኢህዴን ታጋይ ይመክር እና ጋሳይ አካባቢ በተደረገው ጦርነት የህወሓት አንዲት ሃይል ሰብራ ገብታ የኢህዴን ሃይሎች ደግሞ ግራና ቀኝ ከበባ እንዲያደርጉ የተሰጠውን ትዕዛዝ አልቀበልም በማለት ሰብራ የገባችው የህውሃት ሃይል በደርግ የቀለበት ውጊያ እንድትጠቃ በመደረጉ የህወሃት ሰራዊት ወደ ኋላ ለማፈግፈግ እንደተገደደ አጫውቶኛል።

ከዚህ ሽንፈት በኋላ ህወሓት የለመደችውን ስለላ እና አደናጋሪ ግምገማ መሰረት አድርጋ “ሀወጀኖ ከጀርባ ሁኖ ወግቶናል ስለዚህ ባለበት መታሰር አለበት” ስትል ኢህዴን ሀው ጃኖን እንዲያስር ትዕዛዝ ተሰጠው። ለዚህ ተልዕኮም ህላዊ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ እና ንጉሴ ጺሞ ወደ አዲስዘመን ተላኩ። ስብሰባም ጠሩ። ይህንን ስብሰባ በጥርጣሬ ያየው ሀወጀኖ ወደስብሰባው ከመግባቱ በፊት ሙሉ ትጥቅ ታጥቆ ሲገባ የተመለከተው ፀሃየ የተባለ ታጋይ “የት ልትሄድ ነው…?” ብሎ ሲጠይቀው “ወደ ሰማይ ቤት” ብሎ እንደመለሰለት ታሪኩን ያጫወተኝ ታጋይ ፀሃየ ነገረኝ ሲል አጫውቶኛል።

ሚያዚያ 20 ቀን 1983 ዓ.ም ረፋድ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አይቀሬው ስብሰባ ተጀምሮ ሀው ጀኖ “ከድርጅቱ መርህ ውጭ የማዕከላዊ ኮሚቴ ምስጢር ለታጋዮ አውጥተሃል” የሚል ግምገማ ከላይ በጠቀስኳቸው ሰዎች ሲቀርብ ደሙ የፈላው ሀው ጀኖ የያዘውን ክላሽንኮብ አቀባብሎ ወደ ታደሰ ካሳ ሲተኩስ ታደሰ ጥንቅሹ እና ህላዊ ዮሴፍ በመስኮት ዘለው እንዳመለጡና ንጉሴ ፂሞ ተቀምጦ እንደቀረ እና ሀወጀኖም በብስጭት ውስጥ ሆኖ ተኩሶ እንደገደለው አጫውቶኛል። ከዘ በኋላ ከነ ህላዊ ዮሴፍና ታደሰ ጥንቅሹ ጠባቂዎች ጋር ተታኩሶ እንደተገደለ እና በአዲስ ዘመን ቅድስተ ሃና በተክርስቲያን እንደተቀበረ በእልክና በቁጭት እየተናጠ ይህ የአይን ምስክር ታጋይ አጫወተኝ።

(የዚህ ጀግና ታጋይ አፅም ከአዲስ ዘመን ተወስዶ ነገ ራያ አላማጣ ላይ ያርፋል)

ዴሞክራሲ ወይስ የተረኛነት ጥያቄ? የኦሮሞ ፖለቲካ ወዴት? (ብርሃኑ አበጋዝ (ዶ/ር) )

ዴሞክራሲ ወይስ የተረኛነት ጥያቄ?
የኦሮሞ ፖለቲካ ወዴት?
***
ብርሃኑ አበጋዝ (ዶ/ር)
***
ለዚህች አነስተኛ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ የሰሞኑ አክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች አካሄድ ነው፡፡ እነዚህ አካላት ቡራዩና አሸዋ ሜዳ ላይ በንጹሐን ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ፍፁም ኢሰብአዊ የሆነ የጥፋት እርምጃ ከማውገዝ ይልቅ፣ ድርጊቱን የፈፀሙት የኦሮሞ ወጣቶች አይደሉም ብለው ለመካድና ነገሩን ለማድበስበስ የሄዱበት ርቀት፣ እንዲሁም በኦሮሞ ሕዝብ ስም የተደራጁ ፓርቲዎች አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች መስከረም 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ ቡራዩና አሸዋ ሜዳ ላይ የተፈፀመውን ድርጊትና አዲስ አበባ ከተማን በሚመለከት ያራመዱት አቋም አክራሪው የኦሮሞ ጎራ ለዴሞክራሲ ያለውን ዝግጁነት አጠያያቂ መሆኑን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡

ዝቅ ብየ እንደምገልጸው፣ በእኔ አስተያየት ኢትዮጵያችን ከዚህ በኋላ የአንድ ቡድንም ይሁን የአንድ ሕዝብ የበላይነት የነገሠበት የአፈና አገዛዝ የመሸከም አቅሙ የላትም፡፡ መድኀናችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ ከዴሞክራሲም ሁሉንም ሕዝቦች አካታችና አሳታፊ የሆነው (consociational democracy) ዓይነት ዴሞክራሲ ነው፡፡ በዘውጋዊ ማንነታቸው የተደራጁትም ይሁን በዜግነት ላይ የተመሠረተ ኢትዮጵያዊነትን እንከተላለን የሚሉት የፖለቲካ ኀይሎች ሁሉ በነጻነት የሚሳተፉበትና ሁሉም እንደየአቅማቸው የሚሳተፉበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሲገነባ ብቻ ነው በአገራችን ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት ሊረጋገጥ የሚችለው፡፡ አንዳንድ በኦሮሞ ሕዝብ የተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች ከሰሞኑ የሚያራምዱት “የእኛ ተራ ነው” የሚል ከዴሞክራሲ ጋር የሚጋጭ አዝማሚያ ለአገርና ሕዝብ በምንም ዓይነት መንገድ አይበጅም፡፡

ታሪክ፡- የጦርነት አውድማ
***
ታሪክ የዘውጌ ብሔርተኞች ዋና የጦርነት አውድማ ነው፡፡ የትኛውም ዘውጌ ብሔርተኛ ታሪክን እሱን በሚያገለግል መልኩ መጻፍ ዓይነተኛ መለያ ባሕርይው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ በተለይ የውጭ አገራት የሥነ-ሰብዕ፣ ታሪክና ቋንቋ ምሁራን እንዲሁም ሚሲዮናዊያን አስተዋጽዖ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ዊሊያም ሀስቲንግስ የተባለው ብሪታኒያዊና ‹ኢስት ኢንዲያ ካምፓኒ› ውስጥ በኀላፊነት ቦታ ላይ ይሠሩ የነበሩ ባልደረቦቹ የቤንጋል ቋንቋን በማሳደግ ለሕንድ ብሔርተኝነት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡ የኦሮሞ ዘውጌ ብሔርተኝነትም በአውሮፓ ወንጌላዊ ሚሲዮናዊያን እና እንደ ባርቴልስ (Bartels, L.)፣ ሃበርላንድ (Haberlaned Von, E.)፣ ባክስተር (Baxter, P.T.W.)፣ ሆሎኮምብ፣ (Holocomb,B.K.)፣ አስምሮም ለገሠ ወዘተ. ባሉ የሥነ-ሰብዕና የቋንቋ ምሁራን አማካይነት የተፈጠረ ነው፡፡

በዚህ የታሪክ አውድ ውስጥ ተወለደው የኦሮሞ ዘውጌ ብሔርተኛ የኢትዮጵያ ታሪክ የሁሉንም ሕዝቦች ታሪክ ያካተተ ብሔራዊ ታሪክ አይደለም ብሎ ሲያበቃ እዚያው በዚያው ራሱን በሚጠቅም መልኩ ልዩ ልዩ ድርሳናትን እያዘጋጀ ታሪክን የፖለቲካ መሣሪያነት ሲገለገልባት ከርሟል፡፡ የትናንቱን ኹነት በዛሬ መነጽር በማየት ተመልሶ ከ1983 ዓ.ም. በፊት በታሪክ ውስጥ ስላልነበረችው “ኦሮሚያ” የተባለች አገር የፈጠራ ታሪክ ያስነብበናል፤ የኦሮሞን የገዳ ሥርዓት የገደሉት አባ ጅፋርን ጨምሮ ከራሱ ከኦሮሞ ሕዝብ የወጡት ባህላዊ መሪዎች (አባ ሞቲዎች) መሆናቸው በግልጽ እየታወቀ፣ አክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች የሐበሻ ወረራ የፍትሕ ሥርዓታችንን አወደመ ብለው ሳያፍሩ መጻሕፍት ያሳትማሉ፤ የኦሮሞ ሕዝብ በብዛት በሚኖርባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙት አብያተ-ክርስቲያናት የተሠሩት በአባ ገዳዎች መሰብሰቢያ ላይ ስለመሆኑ ይተርኩልናል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮምኛ ስያሜ ያላቸው አካባቢዎች የኦሮሞ እንደነበሩ ይገልጹልናል፡፡ አዲስ አበባ ብቻ ሳትሆን ሰፈሮቿም የኦሮምኛ ስያሜ የነበራቸው ስለመሆኑ የሚያብራራ መጽሐፍ ከመጻፍም አልፎ የግል ባንኮችና ዩኒቨርሲቲዎች በእነኝህ ስያሜዎች ቅርንጫዎቻቸውን እንዲሰይሙ በመደረግ ላይ ነው፡፡

በየትኛውም አገር ውስጥ በብሔራዊ ታሪክ ላይ አለመግባባቶችና ክርክሮች አሉ፡፡ በየትኛውም አገር ከዋናው ብሔራዊ/አገራዊ የታሪክ አተያይ (interpretation) የሚለዩ የታሪክ ድርሳናትና አተያዮች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም አንድ ሁሉም ሕዝቦች የእኛ ታሪክ ነው ብለው የሚቀበሉት ብሔራዊ ታሪክ ከሌለ ጠንካራ አገረ-መንግሥት ሊኖር አይችልም፡፡ ታሪክ የዘውጌ ብሔርተኞች የፖለቲካ መሣሪያ ሲሆን ደግሞ መዘዙ ከሁሉም የከፋ ነው፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሞ ርስት ናት የሚለው የአክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች ትርክት የሚያሳየው ዘውግ-ተኮር ታሪክ ምን ያህል አገር እንደሚያጠፋ ነው፡፡ የሕወሓት የበላይነት የሰፈነበትን አገዛዝ ያንኮታኮተው ቄሮ ነው እያሉ ለ27 ዓመታት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የከፈሉትን መስዋዕትነትና ያስገኙትን ፍሬ ለአንድ ቡድን አሳልፎ መስጠት ዘውግ-ተኮር እይታ ምን ያህል አእምሮን እንደሚሸብብ ምስክር ነው፡፡

ማነው ኢትዮጵያዊ?
****
የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኀይለማርያም A History Of Nationalism in Ethiopia፡ 1941-2012 በሚል ርዕስ በጻፈው የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ሥራው እንደገለጸው በማርክሳዊ አስተሳሰብ የተቃኘው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ የሚመራበት ርዕዮተዓለም በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አመለካከት ውስጥ በመደባዊና አውራጃዊ ወይም በአውራጃዊና ብሔራዊ ጭቆናዎች፤ በጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔረሰቦች፣ በደቡብና በሰሜን ንፍቀ አገራት፣ በባህላዊ ራስ-ገዝነትና በፖለቲካዊ መገንጠል ወዘተ. የተፈረጁ ተቃርኖዎችን ያለቅጥ በማጋነን ትልቅ ጥፋት አድርሷል፡፡ ማነው ኢትዮጵያዊው? የሚለው ውስጠ ወይራ ጥያቄ የአፍለኛው ምሁር የትግል አጀንዳ ሆኖ ብቅ ያለውም በዚህ ግርግር ውስጥ ነበር፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዳብራራው ይህንን ብዥታና ወላዋይነት ተጣብተው የተፈለፈሉት ጥገኛ አስተሳሰቦች ቀስ በቀስ የብሔረሰቦችን ጥያቄ በማጉላት ገዥ መርህ ሆኖ እንዲወጣ ለማድረግ ቻሉ፡፡ ገና የኢትዮጵያ አብዮት ከመፈንዳቱ ቀደም ብሎ በየአውራጃው በሕዝብ ስም የተቋቋሙ ልዩ ልዩ የባህልና የመረዳጃ ማኅበሮችን በመጠለል ሲንቀሳቀሱ የቆዩት የብሔረሰብ ፖለቲካ አቀንቃኝ ኀይሎች የአብዮቱን ሒደት መቆጣጠር እንዳልቻሉ በተገነዘቡ ጊዜ ወዲያውኑ እውነተኛ ማንነታቸውን በማጋለጥና እነኘህን ማኅበራት በብሔረሰብ ስም ወደተደራጁ አማጺ ቡድኖች በመቀየር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መዋጋት ቀጠሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እንደ አብነት የሚጠቀሰው “ሜጫና ቱለማ” (1955 ዓ.ም.) በኋላ ለተመሠረተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መቀፍቀፊያ በመሆን አገልግሏል፡፡

የኦነግና ሌሎች ዘውጌ ብሔርተኛ ታሪከኞች የዓለም ሁሉ ክፋትና ጥፋት ምንጭ ምኒልክ ነው የሚሉ ትርክቶችን በማድራት፤ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቋንቋና የባህል ማኅበረሰቦች መካከል ያሉ የአብሮነት ታሪኮችን፣ የጋራ ዕሴቶችንና ባህሎችን በመካድ፤ ከብዙ ዐሥርት ዓመታት በፊት የተደረጉ ጦርነቶችን እየተቀሱ በአዲስ መልክ የጭቆናና የሰቆቃ ገድሎችን በመፍጠርና በማጉላት፣ ኢትዮጵያውያንን የሚያገናኙ ድልድዮችን ሁሉ ለማፍረስ ያልተጓዙበት ርቀት የለም፡፡

ኢትዮጵያ የሁላችንም እንድትሆን የጋራ ዕሴቶችን ከመፍጠርና ከማጉላት ይልቅ በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ግጭትን በሚፈጥሩ አጀንዳዎች ላይ ብዙ ሀብት ፈሰሰ፤ ብዙ ጉልበት ባከነ፡፡

“የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግል”
****
በኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን አካባቢ ስለ “ሐበሻ ወረራ” እና ከዚህ ወረራ ነጻ ስለመውጣት ብዙ ተጽፏል፤ ለረዥም ዘመናት ብዙ ተብሏል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና በገዳ አባ ጃራ ይመራ የነበረው የኦሮሞ እስላማዊ ግንባር ዋና ዓላማ “ፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግል” ማካሄድና ነጻ የኦሮሚያ ሪፐብሊክን መመሥረት እንደነበርም የሚታወቅ ነው፡፡

እንደነ አሰፋ ጃለተና ሲሳይ ኢብሳ ያሉ የኦሮሞ ምሁራን ኢትዮጵያን “ብቸኛዋ የጥቁር ቅኝ ገዥ” ይሏታል፡፡ መፍትሔው ከኢትዮጵያ የቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነጻ መውጣት ነው የሚል ትርክት ለበርካታ ዓመታት ሲራመድ ቆይቷል፡፡ በብዙ አንጃዎች የተከፋፈለው ኦነግ ይህን ነባር ትርክቱን ይቀይር አይቀይር በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡

ኦነግ ምንም ይበል ምን የነዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን መያዝ ለረዥም ዘመናት ሲያራምደው የነበረው አጀንዳ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ይበልጥ ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ጥርጥር የለውም፡፡ እንደ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ያሉ የኦሮሞ ልጆች በበላይነት የሚመሯት ኢትዮጵያ የኦሮሞ ቅኝ ገዥ ናት ቢሉ የሚሰማቸው የለም፡፡ ስለሆነም አክራሪው ጎራ ኦሮሚያን እገነጥላለሁ (በእነሱ አነጋገር ነጻ እናወጣለን) ነባሩን አቋሙን ቀይሮ ተራው የእኛ ነውና አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል አጀንዳ ማራመድ የጀመረ ይመስላል፡፡

ዴሞክራሲ ብቻ!
***
በመግቢያዬ እንደገለጽኩት ለኢትዮጵያዊያን መድኅናችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህች አገር የአንድ የፖለቲካ ቡድንም ይሁን የአንድ ሕዝብ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት የሚኖርበት የፖለቲካ ሁኔታ የለም፡፡ ሁሉም አገራችን የፖለቲካ ኀይሎች ይህን መሠረታዊ ሐቅ በሚገባ ተገንዝበው ሁላችንም በእኩልነት የምታስተናገድ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በሚያሳዝን መልኩ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚታየው አካሄድ ከዴሞክራሲ በተጻራሪ ቆመ ነው፡፡ የክልሉ መንግሥት ሁኔታዎችን ለማስተካከል ጥረት እያደረገ ቢሆንም በክልሉ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ ፈርተውና ተሸማቅቀው እንዲኖሩ ሆኗል፡፡ አክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች በሚረጩት የጥላቻ አዋጅ ምክንያት ዜጎች ትልቅ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የአገሬና የሕዝቤ ጉዳይ ይመለከተኛል የምንል ኢትዮጵያዊያን ጠንከር ብለን ለሁላችንም የሚበጀውን ስንናገርና በአክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች ላይ ሂስ ስናቀርብ “የኦሮሞ ጥላቻ” (Oromo phobia) አለብህ/ሽ እያሉ ዜጎችን ለማሸማቀቅና ዝም ለማሰኘት ከመሞከር ተቆጥበን፣ ለሁላችንም የምትሆን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመገንባቱ ላይ እናተኩር፡፡ ብቸኛው መዳኛችን ዴሞክራሲ ብቻ ነው!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!

Advertisements

Report this ad

በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ሁለት አሳሳቢ ነገሮችን ነዋሪው ማወቅ አለበት።

በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ሁለት አሳሳቢ ነገሮችን ነዋሪው ማወቅ አለበት።

በገፍ መታወቂያ ለክልል ልጆች በመስጠት የነዋሪውን ድምፅ የመስረቅ ሂደት መኖሩንና መንግስት ታጥረው የነበሩ መሬቶችን ወደ መንግሰት መልሶ ለነዋሪ የሚያሸጋግርበትን አሰራር ግልፅነቱን ማወቅ።

መፍትሄዎቹ :-

1 – አዲስ አበባ ባሉ ቀበሌዎች የሚሰራ ማንኛውም የከተማ ነዋሪ በህገ ወጥ መንገድ መታወቂያ ሲታደል ካየ ከሰማ ወይም ከጠረጠረ መረጃውን በማቀበል ይፋ እንዲወጣ በማድረግ የነዋሪነት ግዴታውን ይወጣ።

2 – መንግስት 400 ሄክታር ታጥረው የነበሩ መሬቶችን መውረሱን ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ነግረውናል። ራሱን የቻለ ትንሽ ከተማ መሆን ይችላል ሲሉም የመሬቱን ትልቅነት አጉልተው ገልፀዋል።

ዛሬ ታከለ ኡማ አዲስ አበባ የሚገኙ የኦሮሞ ወጣቶችን ሰብስቦ ሲያነጋግር ባዶ መሬቶች ለወጣቶች ተላልፈው ይሰጣሉ ብለዋል። የአዲስ አበባ መሬት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እንጂ ለአንድ ብሔር ብቻ ተላልፎ የሚሰጥ አይደለም። ቅድሚያ መሬት ለሌላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መሆን አለበት። ከሌላ ቦታ አምጥተህ የምታሰፍረው የሰፈራ ፕሮግራም አይደለም።

መሬቶቹ ለማን እንደሚሰጡ በግልፅ ለነዋሪው መነገር አለበት። መሬቱን ለተወሰኑ የማህበረሰብ አካላት አሳልፎ የመስጠት እቅድ ይዞ ከተንቀሳቀሰ ትልቅ ችግር እንደሚገጥመው ማወቅ አለበት።

Sara MoAwol እንዳስቀመጠችው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጀርመን ፍራንክፈርት እና በፓሪስ ከተሞች ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እንደሚያካሂዱ ተገለጸ።

DW – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጀርመን ፍራንክፈርት እና በፓሪስ ከተሞች ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እንደሚያካሂዱ ተገለጸ። በፍራንክፈርት ከተማ የፊታችን ጥቅምት 21 (ኦክቶበር 31) ስለሚካሄደው ውይይት እና የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ ዛሬ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፍራንክፈርት ቆንስላ ጽሕፈት ቤት መግለጫ ተሰጥቷል።

ባለፈው ሃምሌ ወር ማገባደጃ ላይ በአሜሪካ ሦስት ግዛቶች ከኢትዮጵያውያን ጋር ተገናኝተው ጥልቅ ውይይት ያካሄዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በቀጣዩ ወር መጨረሻ ላይ በፈረንሳይ ፓሪስ እና በጀርመን ፍራንክፈርት ከተሞች ተመሳሳይ ውይይት ከኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚያደርጉ በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በአውሮፓ የተለያዩ አገራት የሚያደርጉት ጉብኝትም ” በፍቅር እንደመር፤ በይቅርታ እንሻገር “፣ ” ግንቡን እናፍርስ፤ ድልድዩን እንገንባ ” በሚል በአሜሪካ ያደረጉት ጉዞ ቀጣይ አካል እንደሆነ በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ጄኔራል አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የጉብኝት ጉዞ መርሃ ግብር ለመረዳት እንደቻልነው በቅድሚያ ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ ም በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ያካሄዳሉ። በማግስቱ ጥቅምት 20 ወደ ጀርመን ርዕሰ መዲና በርሊን በማቅናት ከአገሪቱ ከመራሔተ መንግስት አንጌላ ሜርክል እና ከተለያዩ የአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ያደርጋሉ።

Deutschland Diskussion im äthiopischen Konsulat in Frankfurt mit Abiy Ahmed

ሜርክል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር የሚያካሂደውን የለውጥ እንቅስቃሴ በመደገፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጀርመን ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ በስልክ ጥሪ እንደጋበዟቸው ይታወሳል።  በጥቅምት 20 ” ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ” የተባለ ወደ 11 የሚጠጉ የአፍሪቃ አገራት መሪዎች የሚሳተፉበት ጉባኤ በርሊን ላይ ይካሄዳል። የአፍሪቃ መሪዎች ከጀርመን ጋር ባላቸው የልማት ትብብር ላይ በሚመክረው በዚህ ልዩ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም እንደሚታደሙ ታውቋል።

በመጨረሻም በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት እና የአውሮፓ ዋና ማዕከል ተብላ በምትጠራው የፍራንክፈርት ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከመላው አውሮፓ የሚሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በሚገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ በጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ. ም. ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ይህን ዝግጅት ለማስተባበር ዛሬ ከፍራንክፈርት እና የተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተውጣጡ ከ 80 በላይ የማህበራት እና የተቋማት አደረጃጀት ተወካዮች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተዘጋጅቶ ነበር። ከውይይቱ በኋላ የተዋቀረው የጠቅላይ ሚኒስትሩን አቀባበል የሚያስተባብረው ንዑስ ኮሚቴ የማህበራዊ ጉዳዮች የስፖንሰር አፈላላጊ የሚዲያ እና ቅስቀሳ የመስተንግዶ እና ሎጂስቲክ እንዲሁም ልዩ ልዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ አባላትን በፈቃደኝነት ሰይሟል።

Deutschland Diskussion im äthiopischen Konsulat in Frankfurt mit Abiy Ahmed

በፍራንክፈርቱ ትልቁ የኮሜርስ ባንክ አሬና ስታዲየም በሚከናወነው በዚህ ልዩ ሥነ ሥርዓት ላይ ከ 15 ሺህ እስከ 25 ሺህ የሚገመቱ የለውጡ ደጋፊ ኢትዮጵያውያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቆንስላ ጄኔራል አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ ገልጸዋል። አቶ ምህረተአብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመቀበል ከተቋቋመው ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ መላው ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ ላይ በመታደም በአገራችን ለተጀመረው ለውጥ ያላቸውን ድጋፍ እና አጋርነት እንዲገልጹ ጠይቀዋል። የፊታችን ጥቅምት 21 በፍራንክፈርት ከተማ በሚከናወነው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአቀባበል ሥነ-ሥርአት ከመላው አውሮፓ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴም ተጀምሯል።

ዛሬ በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ያነጋገርናቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች በአገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማጠናከር እና ለማገዝ በልዩ ልዩ የልማት እና የኢንቨስትመንት መስኮች ተሰማርተው አገራቸውን ለመርዳት እና በውጭ ያካበቱትንም ዕውቀት እና ልምድ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው በማካፈል ከፍተኛ የዕውቀት ሽግግር በማካሄድ የዜግነት ድርሻቸው የመወጣት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል ።

DW Amharic

የብሄር ፖለቲካ አይንህ ለአፈር እየተባለ ነው (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን

Urban people don't have tribe in Ethiopia.

የብሄር ፖለቲካ እያቃሰተ ይመስላል። ከአዲስ አበባ እየተመለሱ ያሉ ሰዎች እንደሚነግሩኝ መሬት ላይ ያለው ዕውነት በዚህ መንደር ከሚናፈሰው የተለየ ነው። የብሄር ቡድኖች ጉልበታቸውን የሚያሳዩት በአብዛኛው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለመሆኑ የተለያዩ አስረጂ ምሳሌዎችን እየጠቀሱ አጫውተውኛል። መሬት ላይ ያለው ሀቅ በእጅጉን ይለያል። መሬት ላይ የብሄር ቡድኖች ሜዳ እየጠበበና እየኮሰመነ በአንጻሩ የዜግነት ፖለቲካ ስጋ ለብሶ በአሸናፊ ግርማ ሞገስ ብድግ ብሎ እየተነሳ ነው። የሰሞኑ የመግለጫ ጋጋታ፡ የጽንፈኛ አክቲቪስቶች እርግጫ የበረከተው ያለምክንያት አልነበረም። የብሄር ፖለቲካ አይንህ ለአፈር እየተባለ በመሆኑ ነው።

በእርግጥም የብሄር ፖለቲካ እንደዳይኖሰር ከምድር ገጽ ላይ መጥፋት የሚገባው ነው። እንደ ጋና ያሉ ሀገራት በህገመንግስታቸው ገደብ እስኪጥሉ የደረሱት መዘዙን ጠንቅቀው ስለተረዱት ነው። የብሄር ፖለቲካ ዩጎዝላቪያን ወደ ትንንሽ ሀገራት ለውጧታል። የብሄር ፖለቲካ አፍሪካን የሰው ልጅ የስቃይ ምድር ትሆን ዘንድ ፈርዶባታል። ምንም እንኳን አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት የብሄር ፖለቲካን እያጠፉ ቢሆንም የቅኝ ግዛት ዘመን ማክተምን ተከትሎ የአፍሪካ ነቀርሳ ሆኖ ከአንድ ክፍለዘመን በላይ ቆይቷል። በአፍሪካ የብሄር ፖለቲካ እየገነገነ ሊወጣት የደረሰው ኢትዮጵያን ብቻ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ። በኢትዮጵያም ይሀው ኋላ ቀር የፖለቲካ መስመር የቁልቁለት ጉዞውን መጀመሩን ምልክቶችን ማየት ጀምረናል። እሰየው ነው።

የኦሮሞ ውድ ልጆች የሆኑት ለማ መገርሳና አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ የተሻገረ፡ ፓን አፍሪካኒዝምን ያለመ ራዕይ ይዘው መነሳታቸው ለብሄር ፖለቲካ አቀንቃኞች ምቾት የሚሰጥ አልሆነም። እነዚህ ኢትዮጵያን በምጸአቷ ቀን ደርሰው ከገደል አፋፍ የመለሷትና ተስፋን የሰጧት መሪዎች የብሄር ፖለቲካን አስታመው ወደ መቃብሩ እየሸኙት ናቸው። በዜግነት ፖለቲካ ውስጥ የተየለያዩ ቡድኖችን መብት ማስጠበቅ እንደሚቻል የተረዱት የቲም ለማ አመራሮች ለኢትዮጵያ በትክክለኛው ዘመን ፈዋሽ የሆነውን መድሃኒት ቀምመው በፍቅርና ይቅርታ መርፌ መውጋት መጀመራቸውን ቀጥለዋል።

ቀድሞውኑ የተፈወሱ ከእነዚህ መሪዎች ጎን ሆነው እያገዟቸው ነው። በሽታውና ልክፍቱ በደማቸው የሚዘዋወርባቸው በረድፍ ተሰልፈው መርፌውን ይወጉ ዘንድ እድሉ ተሰጥቷቸዋል። የሚፈራገጥ አይጠፋም። መርፌው መርዝ የሚሆንበትም የትየለሌ ሊሆን ይችላል። ግን ምርጫ የለውም። ከነልክፍቱና በሽታው አብረው ተያይዘው ይጠፏታል እንጂ ከዚያ ያለፈ የሚያመጣው አንዳች ነገር የለም።

ዓለም ወደ አንድ መንደር እየገባች፡ በየሀገራት መሀል ያለው ድንበር እየደበዘዘ፡ አንድ የጋራ የመገበያያ ገንዘብ በየክፍለ አህጉሩ እየተፈጠረ፡ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጸሀይ መጥለቂያ፡ ከሰሜን ዋልታ፡ እስከ ደቡብ የመሬት ንጣፍ ድረስ የዓለም ህዝብ ቤተሰብ እየሆነ በመጣበት 21ኛው ክፍለዘመን በብሄር ፖለቲካ የሰከሩ፡ ከመንደራቸው ጋጥ የዘለቀ ራዕይ ማየት የተሳናቸው፡ ሰፊዋን ዓለም በጠባቡ የጎጣቸው መሬት ልክ መመልከትን የመረጡ የፖለቲካ ነጋዴዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በርክተው ይታያሉ።

ጥላቻን መፈክራቸው፡ ጽንፈኝነትን መስመራቸው፡ መበታተንን ግባቸው ያደረጉት እነዚህ የብሄር ፖለቲካ አቀንቃኞች የሚጋልቡትን ያህል ከኋላ አሰልፈው የሚችሉትን እየሞከሩ ለመሆናቸው ከሰሞኑ እየታዘብ ነው። የማህበራዊ ሚዲያዎች ደግሞ እንደፈለጋቸው የሚፈነጩበት ሰፊ ሜዳ በመሆኑ ጉልበት አቅማቸውን በማሳየት የመሬት ላይ ኪሳራቸውን ለመሸፈን በትጋት እየሰሩበት ነው። ከዚህ መደረክ ወርዶ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ለመረመረ ሰው እነዚህ በብዙ የሚጮሁት የብሄር አቀንቃኞች፡ ደካማ፡ አቅመ ቢስ፡ ትንንሽ ፍጡሮች ሆነው ይታዩታል። አይ ፌስቡክ?! ስንቱን ኮሳሳ አገዘፈብን ባካችሁ?!

ለማንኛውም የብሄር ፖለቲካ በገበያው ፈላጊ እያጣ ነው። አቀንቃኞቹ ከዚህም በላይ አብዝተው ቢጮሁ አትፍረዱባቸው። ውድቀትን በጩሀት ማስቀረት አይቻልም። ኢትዮጵያ ለሁሉም ትሆን ዘንድ ቤተመንግስት የገቡት መሪዎች ስራቸውን እየሰሩ ነው። በኢሳትም ሆነ በሌሎች የዜግነትን ፖለቲካ በሚያቀነቅኑ ሃይሎች ላይ ሰሞኑን የበረከተው እርግማንና የሰይፍ መዓት ያነጣጠረው አራት ኪሎ ቤተመንግስት በተቀመጡትና አፍሪካ ድረስ ራዕይ አንግበው በተነሱት ቁርጠኛ የህዝብ መሪዎች ላይ ነው።

የሰኔ 16ቱ ጥቃት የዚሁ የቀበጺ ተስፋ እርምጃቸው አንዱ አካል ነው። ከእንግዲህም ሊሞክሩ ይችላሉ። ግን አያሸንፉም። ሀሳብ ታጥቆ የተነሳን ለማሸነፍ ሀሳብ እንጂ ሰይፍ መወርወር አያዋጣም። ጊዜያዊ መንገጫገጭ ቢኖር እንኳን በዘላቂነት የአሸናፊነት አክሊሉን የሚደፋው የዜግነት ፖለቲካ መሆኑን ለመናገር ነቢይ መሆን አይጠይቅም።

አርበኞች ግንቦት 7 – እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የተጀመረዉ የለዉጥ ሂደት ግቡን እንዲመታ የራሱን አስተዋጽኦ የማድረግ ሀላፈነት አለበት!

አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ

Patriotic Ginbot 7 logoአገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዉስጥ ለረጂም ዘመን ነጻነታቸዉን ጠብቀው ከኖሩና ጥንታዊ ሥልጣኔ ካላቸዉ አገሮች ዉስጥ አንዷና ቀዳሚዋ ናት። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ብሄር ብሄረሰቦች ከሚኖሩባቸዉና ህብረ ባህል ካላቸዉ አገሮች ዉስጥ አንዷ ናት። ይህ የተፈጥሮ ስጦታ አገራችን ኢትዮጵያን የተለያዩ እምነቶች የሚመለኩባት፥ ብዙ ባህሎችና ወጎች የሚገኙባትና አያሌ ቋንቋዎች የሚነገሩባት አገር እንድትሆን አድርጓታል። ለምሳሌ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ኢትዮጵያ ዉስጥ አዲስ አመትና የመስቀል በአላት ተከብረዋል፥ በነገዉ ዕለት ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ በየአመቱ በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ የሚያከብረዉ የኢሬቻ (የምስጋና በዐል) በከፍተኛ ድምቀት ይከበራል። በዚህ አጋጣሚ አርበኞች ግንቦት ሰባት በነገዉ ዕለት የኢሬቻን በዐል ለሚያከብሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን እና ባለፈዉ ሐሙስ የመስቀል በዐል ያከበሩትን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን በሠላም አደረሳችሁ በማለት ደስታዉንና መልካም ምኞቱን ይገልጻል። አዲሱን አመትና የመስቀል በዐልን በአንድነትና በወንድማማችነት መንፈስ በሠላም እንዳከበርን ሁሉ በነገዉ ዕለት ቢሾፍቱ ዉስጥ የሚከበረዉን የኢሬቻ በዐልም ሁላችንም ከኦሮሞ ወንድሞቻችን እና እህቶቻቸን ጋር በሠላም በማክበር የሚመሳሰሉና የሚወራረሱ አያሌ ባህሎችና የጋራ እሴቶች ያለን ህዝብ መሆናችንን ለአለም ህዝብ እናሳይ!

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አስርተ አመታት ሁለት የከሸፉ አብዮቶችን አስተናግዳ ዛሬ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንክሮ ወደሚከታተለዉና ምናልባትም በታሪካችን የመጨረሻ ወደሆነዉ ስር ነቀል የለዉጥ ሂደት ዉስጥ ገብታለች። ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ ለአመታት በከፈለዉ ከፍተኛ መስዋዕትነት የተጀመረዉ የለዉጥ ሂደት አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የፍትህ፥ የነጻነት፥ የዲሞክራሲና የእኩልነት መሰረት መጣሉን ለማረጋገጥ ቆርጦ የተነሳ መሆኑን እና ይህንን ለማድረግ ደግሞ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በለዉጡ ሂደት ዉስጥ ለማሳትፍ ፈቃደኛ መሆኑን ባለፉት ሦስትና አራት ወራት የተጓዘበት መንገድ በግልጽ አሳይቶናል። ይህንን ተከትሎ በጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ የሚመራዉ መንግስት ያደረገዉን የሰላምና የአብረን አገራችንን እንገንባ ጥሪ ተቀብለዉ በዉጭ አገሮች የሚኖሩ አያሌ የፖለቲካ ድርጅቶችና ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አገራቸዉ ዉስጥ የተጀመረዉን የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደት ለማገዝ ወደ አገር ዉስጥ ገብተዋል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት እኛ ኢትዮጵያዊያን ለአመታት የታገልንለትን ዲሞክራሲያዊ ስርአት ገንብተን የሰላምና የብልፅግና ኑሮ መኖር የምንችለዉ በመጀመሪያ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መረጋጋት የሰፈነባት አገር ስትኖረን ብቻ ነዉ የሚል ጽኑ እምነት አለዉ። ዛሬ ሁላችንም በግልጽ እንደምንመለከተዉ በመፍረስ ላይ ካለዉ ስርአት የተወረሱ አንዳንድ ተቋማዊ ችግሮች በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ለረጂም ዘመን አብሮ የኖረን ህዝብ እርስ በርሱ ሲያጋጩና ደም ሲያፋስሱ እየተመለከትን ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባት እነዚህ ችግሮች የሁላችንም ችግሮች ናቸዉና የኢትዮጵያ ህዝብ፥ መንግስት፥የፖለቲካ ድርጅቶች፥ የሀይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች አንድ ላይ በመምከርና የችግሮቹን መፍትሄ በመፈለግ ፍትህ፥ ነጻነት፥ ዲሞክራሲ፥ እኩልነት፥ ሠላም እንዲሁም ዕድገትና ብልፅግና የተረረጋገጠባትን ኢትዮጵያ ለሚቀጥለዉ ትዉልድ ለማስተላለፍ ጠንክረን አንድ ላይ እንስራ የሚል አገራዊና ወገናዊ ጥሪ እያስተላለፈ አዲሱ አመት በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ድል የምናስመዘግብበት የሠላምና የድል አመት እንዲሆንልን ምኞቱን ይገልጻል።

አንድነት ሀይል ነዉ!!! 
አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ
መስከረም 19 2011 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አለም አቀፍ የመንገደኞች አየር ማረፊያና ሆቴል ሊገነባ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አለም አቀፍ የመንገደኞች አየር ማረፊያና ሆቴል ሊገነባ ነው።

በዓመት ሰማንያ ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግድ የመንገደኞች አየር ማረፊያ ከአዲስ አበባ አርባ ስምንት ኪሎሜትር ላይ ከምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ ሊገነባ ማቀዱን ይፋ አደረገ።

የፋና ብሮድካስት ድርጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅን ተወልደ ገብረማሪያም ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አየር መንገዱ ለሚገነባው አየር ማረፊያና ከጎኑ ለሚገነባው ሆቴል ከኦሮሚያ ክልል ጋር እየመከረ መሆኑ ታውቋል።

ኢትዮጵያዊነት በአንጻረ ጎሰኝነት (ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ ጂግሳ)

ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ የሚያገናኘን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ጎሰኝነት ወይም በቋንቋ መቧደን ሁላችንንም አያገናኘንም። ጎሰኝነት ወይም የቋንቋ አንድነት የሚያቀራርበው አድ ቋንቋየሚናገሩትን ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊነትን የተቀበሉት ግን ኢትዮጵያዊነት ያስተሳስራቸዋል።

የኦሮሞ ልሂቃንን እንደምሳሌ ብንወስድ ከባለፉት 45 ዐመታት ወዲህ የተወለዱት እንደ እነ ዶር ዐብይ እና አቶ ለማ መገርሳ ዐይነቶቹ ምንም ኢትዮጵያዊነትን በሚጠላ ስርዐት ውስጥ ቢያድጉም ከዘር ማንዘራቸውበደማቸው ውስጥ በተንቆረቆረው የኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተነሳ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፤ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ነን፤ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ፤ እስከማለት ደርሰዋል። ኦሮሞ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሚያው የሚልድመት ሳይሆን የሚያገሳ አንበሳ እንደሆነ አውቀው ይኮራሉ እንጂ አያፍሩም። የዝቅተኝነት ወይም የተጠቂነት ስሜት የላቸውም። እነሱ ከኢትዮጵያም ዳር ድንበር አልፈው አፍሪካን በመውደድ ተነድፈዋል።የአፍሪካዊነት ስሜትም አላቸው። ዶክተር ዐብይ አፍሪካንም ጭምር ለማሳደግ እቅድ እንዳለው ገልጾልናል። ይህን ለማሳካት ኢትዮጵያን፥ ጅቡቲን፥ ሶማሊያን፥ ሱዳንን እና ኤርትራን አንድ ለማድረግ ጀምሯል።ጅማሮው ድንቅ ነው። ይህ እቅዱም ትልቅ ባለራዕይ ያሰኘዋል። ያስከብረዋልም።

ዐብይ እና ለማ ሳይወለዱ ወይም ህጻን ሳሉ የዛሬ 45 ዐመት ትግል ውስጥ የገቡት የኦሮሞ ልሂቃን ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ይጠላሉ። ቃሉንም አይወዱም። ሰንደቅአላማውን ማየት አይፈልጉም። የኢትዮጵያ ታሪክሲባል በዳግማዊ ምንይልክ ዘመን የነበረው ብቻ ይመስላቸዋል። ከዛ በፊት የኦሮሞ ዝርያዎች ንጉሠነገሥታት እና ንግሥተ ነገሥታት ሆነው ለ 600 ዐመታት ኢትዮጵያን እንደገዙ አያውቁም፤ ወይም ሊያውቁአይፈልጉም። ዐያት ቅድመ ዐያቶቻቸው በገዳ ሥርዐት ታዘው ድንበር እየዘለሉ፥ ወሰን እያሰፉ ከኢትዮጵያ ቱስተው እስከ ሩዋንዳ እና ማሊ እንደደረሱ አያውቁም። እንደ እነሱ አስፍተው ማየት ባለመቻላቸው እጅግጠበው እንኳን የኢትዮጵያን ድንበር ዘልለው ሊሄዱ ቀርቶ ኢትዮጵያን በሞላ መያዝ ተስኖአቸው ወይም ተጃጅለው ከሰፊዋ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ቁራጭ መሬት ቀፍፈው ኦሮምያ ብለው ሰይመው፥ በውስጧምፊንፊኔ የምትባል ምድር ጨምረው እሷ ላይ ሙጭጭ ይላሉ። አባቶቻቸው ጠላቶቻቸውን የሚያጠቁ ኩሩ ጀግኖች እንደነበሩ ዘንግተው እነሱ ተጠቂ ነን እያሉ ያለማባራት ያለቃቅሳሉ።

ሰሞኑን በሽማግሎቹ የኦሮሞ ፓለቲከኞች ላይ የታየው ሁኔታ ይህን የሚያንጸባርቅ ነው። እነሱ የእነ ዐብይ እና ለማ ተቃራኒ ናቸው። ከየ21ኛውን ክፍለዘመን አዲስ መዝሙር ለመዘመር አዳግቷቸው ያንኑ የ 20ኛውንክፍለ ዘመን ዘፈን ያለማቋረጥ ይዘፍናሉ። ፈረንጅ ሲተርት “You can’t teach an old dog a new trick. ይላል።  “ያረጀ  ውሻን  አዲስ  ፈሊጥ  አታስተምረውም”ማለት ነው።የእነሱም ሁኔታ እንደዛ ስለሆነ እነ ዐብይእና ለማ ዐይነቶቹ የአዲስ ዘመን ኦሮሞዎች እንደ ቀስት ወደፊት ይስፈነጠራሉ። ሽማግሎቹ እንደ ቀስቱ ደጋን አንድ ቦታ ተገትረው ይቀራሉ።

የ2012ቱ ምርጫ እና የየፖለቲካ ቡድኑ ፍላጎት (በፈቃዱ ኃይሉ)

በመጪው የኢትዮጵያ ዓመት – በ2012 ኢትዮጵያ መደበኛ አገር ዐቀፍ የሕዝብ እንደራሴዎች ምርጫ ታካሒዳለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምርጫውን አጓጊ የሚያደርገው ላለፉት አራት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲንጣት ከቆየው ሕዝባዊ አመፅ ቀጥሎ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣

ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ተለውጫለሁ ባለበት – ነገር ግን ውስጥ ውስጡን በተከፋፈለበት፣ በሽብርተኝነት ሳይቀር ተፈርጀው የነበሩ ድርጅቶች ወደ ፉክክሩ የገቡበት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ ምርጫው ምናልባትም ከምርጫ 1997 ወዲህ ከፍተኛ ፉክክር የሚኖርበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዚህ ምርጫ ጉዳይ የተለያዩ የፖለቲካ ተዋናዮች ገና ካሁኑ የተከፋፈለ አቋም ወስደዋል፡፡ ዋና ዋናዎቹን በሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን፡፡ የመጀመሪያው ነጻ፣ ገለልተኛ እና ተአማኒነት ያለው ምርጫ ይደረግ እና «ይዋጣልን» የሚሉት ቡድኖች/ግለሰቦች ስብስብ ሲሆን፣ «የለም! አሁን ባለው ሁኔታ የምርጫ ፉክክር ማድረግ አንችልም፤ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳው ይራዘም» የሚሉት ቡድኖች/ግለሰቦች ስብስብ ሌላኛው ነው፡፡ በርግጥ፣ «መደበኛ ምርጫ ለማካሔድ ቅቡልነት ያለው አካል የለም፤ አሁን የሚያስፈልገን ሁሉን አሳታፊ የሽግግር መንግሥት መመሥረት ነው» የሚሉም አሉ፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሊያናግሩ በሔዱበት ወቅት «እኔ አሸጋግራችኋለሁ» የሚል ቁርጥ ያለ መልስ በመስጠታቸው የዚህ ጥያቄ አቅራቢዎች ቁጥር ቀንሷል፡፡

«ይዋጣልን» ባዮች
ምርጫው በጊዜ ሰሌዳው ተካሒዶ አሸናፊው አካል መንግሥት እንዲመሠርት የሚጠይቁት የፖለቲካ ቡድኖች፣ ምርጫው ከተራዘመ ሥልጣን ላይ ላለው አካል የመበላሸት ዕድል ይሰጠዋል የሚል ስጋት ያለባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ዋናው ስጋታቸው ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የፖለቲካ ስርዓቱ፣ የመንግሥት መዋቅሩ እና ሁሉም ነገር እንዲቀየርም አይፈልጉም፡፡ «ወቅታዊ ምርጫን ያህል ነገር ከተራዘመ፣ ሕገ መንግሥቱ እንዲሁም ፌዴራላዊ መዋቅሩ ሊነካ የማይችልበት ዕድል የለም» የሚል ፍርሐትም አላቸው፡፡ ይህንን ለማስወገድ አሁን በሚስተዋለው፣ አንፃራዊ ነፃ የፖለቲካ ምኅዳር ምርጫውን ማካሔድን እንደ ብቸኛ አማራጭ አድርገው ያቀርቡታል፡፡ እነዚህኞቹ ቡድኖች «አማራጭ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያስፈልጋቸው ጤናማ የፖለቲካ ምኅዳር ብቻ ነው» ባይ ናቸው፡፡ «ምኅዳሩ ከተገኘ ቀድሞውኑ የተቋቋሙለትን የፖለቲካ ግብ ይዘው ተወዳድረው ማሸነፍ ይችላሉ» የሚል ጠንካራ እምነት አላቸው፡፡

«ይራዘም» ባዮች
ምርጫው መራዘም አለበት የሚሉት የፖለቲካ ቡድኖች እና ድርጅቶች እንደ ምክንያት የሚያስቀምጡት የአገሪቱን አለመረጋጋት እና የዴሞክራሲ ተቋማትን ነጻ እና ገለልተኛ አለመሆን ነው፡፡ እነዚህኞቹ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ስትዳክርበት ከነበረው የሕዝባዊ አመፅ «ሀንጎቨር» አሁንም መውጣት ስላልቻለች፣ በዚህ ስሜት ውስጥ አገር ዐቀፍ ምርጫ ማካሔድ ተጨማሪ አመፅ መጋበዝ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ተአማኒነት ያለው ምርጫ ለማካሔድ የሚያስፈልጉት ነጻ እና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት አለመኖራቸው በምርጫው ሒደት ወይም ውጤት ላይ አለመስማማት ብሎም ቀውስ እንዲመጣ ያደርጋል የሚል ስጋት አላቸው፡፡ «ምርጫው መራዘሙ የዴሞክራሲ ተቋማትን ነጻ እና ገለልተኛ አድርጎ መልሶ ለማዋቀር ጊዜ ይሰጣል» ብለው የሚከራከሩት እነዚህኞቹ ቡድኖች፣ «ሒደቱ ወይም ውጤቱ የሚያጨቃጭቅ እና ወደ ቀውስ የሚያመራ ምርጫ በጊዜው ሰሌዳ መሠረት ከማካሔድ አለማካሔዱ ይጠቅማል» ባይ ናቸው፤ ምክንያቱም በእነርሱ አባባል፣ «አሁን የአገሪቱ ኅልውና አደጋ ላይ ነው»፡፡
የነዚህ ሙግቶች ግንባር ቀደም አራማጆች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው፡፡ ሁለቱ ግለሰቦች ቡድናቸውን ወክለው እና አንዳንዴም የግል አስተያየታቸውን ጨምረው በተናገሩባቸው መድረኮች እነዚህን ተቃራኒ አማራጮቻቸውን አንፀባርቀዋል፡፡ የሆነ ሆኖ ዋናው ውሳኔ አሁንም በገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ እጅ ነው፡፡ ኢሕአዴግ በሚቀጥለው ሳምንት ለረዥም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን መደበኛ ጉባዔውን ያደርጋል፡፡ እንደፓርቲ በውስጥ ችግሮች እና መከፋፈል የገጠመው ኢሕአዴግ የድርጅት ችግሮቹን መፍታት ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ዓይነት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይም ድርጅታዊ አቋም ማሳለፍ አለበት ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይሁን እንጂ አገር ዐቀፍ ምርጫን የማራዘም ወይም ያለማራዘም ጉዳይ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት አቋም ብቻ የሚወሰን ጉዳይ አይደለም፡፡ ሌላው ቀርቶ በሕዝብ እንደራሴዎች ፍላጎትም ቢሆን ይህንን ማድረግ አይቻልም፤ ምክንያቱም የሕዝብ እንደራሴዎችም ቢሆኑ ከተመረጡለት የአገልግሎት ጊዜ በላይ ለመቆየት የመወሰን መብት የላቸውም፡፡ ስለሆነም፣ በጉዳዩ ላይ ድርጅቶቹ የተለያዩ አቋሞችን ቢያሳልፉም ቅሉ፣ ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት ሊደረግበት ይገባል።

በፈቃዱ ኃይሉ

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት በተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ (ፋና)

Addis Ababa, Meskel Square rally explosion.

(ፋና) — የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ላይ በሽብር ወንጀል ክስ መሰረተባቸው።

ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ በሽብር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ጌቱ ግርማ ‘ብርሃኑ ጃፋር ‘ጥላሁን ጌታቸው’ ባህሩ ቶላና ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው።

ዓቃቢ ህግ ሁሉንም ተከሳሾች ሰኔ 16 በነበረው የድጋፍ ሰልፍ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ላይ ጥቃት ለማድረስ ብሎም በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚመራ መንግስት መኖር የለበትም የሚል ዓለማ ይዘው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል።

እንደ ክሱ ገለፃ ከሆነ ይህ ዓለማ ቀድሞ በተደረጃ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱና የቦንብ ጥቃት ማድረስ በሚችሉ አበላት አማካኝነት መሆን እንዳለበትም የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተቀባይነት የሌላቸው በተለይም በኦሮሞ ብሔረ ዘንድ አንደማይፈለጉ አድርጎ ለማሳየት በሚረዳ መልኩ ጥቃቱን ለመፈፀም ዐቅደው መንቀሳቀሳቸውም በክሱ ተጠቁሟል።

ለዚህ ደግሞ በኬንያ የምትኖር ገነት ታምሩ ወይንም በቅፅል ስም ቶሎሺ ታምሩ በምትባል የቡድኑ አባል አማካሽነት ተልዕኮ እንደተሰጣቸው በክሱ ተገልጿል።

አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከዚች ሴት ጋር ሰኔ 2010 በስልክ በመገናኘት ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ መካሄድ የለበትም’መሰረታዊ ለውጥ አልመጣም ‘ ሰልፉን የጠራው ገለልተኛ ወገን ሳይሆን ኢህአዲግ ነው ‘HR128 የተባለውና በአሜሪካ ኮንግረንስ የተላለፈው ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል በሚል ሰልፉ እንዲበተን አድርጉ የሚል ተልኮ እንደተቀበለም ክሱ አመልክቷል።

አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከሁለተኛ ተከሳሽ ብረሃኑ ጃፋር ጋር በሰኔ ሱሉልታ ላይ ስለ ተልኮው በመነጋገር ቦንብ እዲያዘጋጅ ቦንቡን የሚወረውርም እንዲያፈላለግ ተነጋግረው ለሶስተኛ ተከሳሽ ጥላሁን ጌታቸው ደውሎ ቦንብ የሚወረውር ሰው እንዲፈልግ ተልኮ መስጠቱም ክሱ የሳያል።

ሁለተኛ ተከሳሽ ያዘጋጀውን ሁለት ኤፍ 1 ቦንብ እንዲሁም አንድ የጭስ ቦንብ በአንደኛ ተከሳሽ ቤት በማስቀመጥ ከሱሉልታ በመነሳት ሰልፉን በመቀላቀል በኛው ተከሳሽ አመካኝነት ቦንቡን በማፈንዳት ሙሳ ጋዲሰና ዬሴፍ አያለው የተበሉ ግለሰቦች ላይ የሞት 165 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድ ና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውም በክሱ ተጠቁሟል።

በዘህም መሰረት ዓቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል