አሁን በአገራችን የሚካሄደውን ተለዋዋጭ ህዝባዊ ግር ግር በማስተናገድ ብቻ ወደ እውነተኛ ፣ ዘላቂ ፍታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት በእውን ማሸጋገር ይቻላልን? (አበባየሁ አሉላ)

ከአበባየሁ አሉላ
ዋሽንግተን ዲሲ

እውነተኛ ለውጥ በስሜትና በምኞት ብቻ ከቶውንም እውን ሊሆን አይችልም፤ በአገራችን ትላንትም በስልጣን ላይ የነበረው ኢህአደግ ነው ዛሬም በስልጣን ላይ በመሆን እኔ አሸጋግራችኃለው እያለ ያለው አሁንም ኢህአደግ ነው።

እውነተኛ ለውጥ የሽግግር ሂደት ይኖረዋል ይህም ሲባል የግለሰቦች ሽግግር ሳይሆን የመንግስታዊ ተቋም ሽግግር መሆን እንዳለበት ይታመናል፤ ለዕውነተኛ መንግስታዊ ሽግግር የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን በነፃነት  መገንባት እጅግ ወሳኝ ነው፤ ለውጥ ግን ሙሉ በሙሉ በግለሰብ ትከሻ ላይ የተመረኮዘ ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲያዊ ተቋማት መገንባት ትከሻ ላይ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ዘላቂ ዋስትናን ያገኛል ።

በአገራችን ቀደምት መንግስታት የመንግስት አወቃቀር አሃዳዊ መንግስታዊ ቅርፅን መሰረት ያደረገ የተማከለ አመራር ሲሆን በህወኃት/ኢህአድግ መንግስት ግን ቋንቋንና ብሔርን መሰረት ያደረገ ፌዴራላዊና ክልላዊ መንግስታዊ መዋቅር ሲሆን ይህም የፌዴራሉን መንግስት አወቃቀር መሰረት በማድረግ የተዋቀረ ነው፤ ስለሆነም ዲሞክራሲያዊ ተቋማት በነፃ መገንባት ሰባል በተዋረድ ከማዕከላዊ ፌዴራላዊ መንግስት እስከ ክልል መንግስታት ጭምር መሆን ግድ ነው፤ በነፃ ስለተቋማት መገንባት ሲናነሳ አራቱን ኢህአደግን ከፈጠሩ ክልል መንግስታትና ፓርቲዎችም ውጭ በነፃነት በየደረጃው ማወቀርን የግድ ይላል!

ዘላቂ እውነተኛ ለውጥ እውን ለማድረግ ኢህአደግ በራሱ ያለገለልተኛ አካል ባለቤትነት ተቋማትን በነፃ መገንባት ከቶውንም የሚቻል አይሆንም!! ኢህአደግ ከአንበሳው ድርሻ ውጪ ባልሆነበት ነፃ የድሞክራሲያዊ ተቋማትን መጠበቅ ከእባብ የእርግብ እንቁላልን እንደመጠበቅ ነው፤

ለዚህም ነፃ ምርጫ በቅድሚያ የነፃ ተቋማት መገንባትን የሚሻው።

ይህንን እውን ለማድረግ ሁሉንም ያገባናል የሚሉ ባለድርሻ አካላትን ( Steack holders) ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ወይም የጥምር አሊያም በባላደራ መንግስት በጋራ በመመስረት ተቋማትን ያለምንም ተፅእኖና ጣልቃ ገብነት ከሚመሰረተውም የሽግግርም ይሁን ባላደራ መንግሥትም መዳፍ ውጭ መገንባት ይቻላል፤

ኢህአደግ ስልጣን ላይ እስካለና አንበሳዊ ድርሻውን በያዘበት የሚደረግ ምርጫ ውጤቱ እራሱ ኢህአደግን ለአምስትና አስርት ዓመታት በኢትዬጵያ መንበር ለማስቀጠል የሚደረግ በተፅዕኖ ስር የወደቀ ህዝበ ውሳኔ ነው ።

በዚህም አሁን በግለሰቦች ብርቱነት የተጀመረውን የለውጥ ጅማሮ ዘላቂና ስር የሰደደ ዲሞክራሲያዊት ኢትዬጵያን እውን ማድረግ ካሻን ዲሞክራሲያዊ ተቋማት መገንባትና ፍርደ ገምድላዊውን የፍትህ ተቋም ፣ ህገመንግስትን ሳይሆን አምባገነን መንግስትን ዕድሜ ለማዝለቅ የሚያገለግል ህግ አስከባሪው ፣ አድሎዋዊ በተፅዕኖ የሚተነፍሱ የሚዲያ ተቋማት ፣ በገዥው ፓርቲ አባላትና ጽ/ቤት ኃላፊዎች የተዋቀረ ወይም ቁልፉን ገዥው ኢህአደግ የተቀፈደደው ምርጫ ቦርድ ወዘተ…ሙሉ በሙሉ በማፍረስ በአዲስ ሁሉም ተቋም ከማንም ተፅዕኖ በነፃ ከላይ እስከታች በመገንባት ኢትዬጵያን ወደ ህዝብ መንግስትነት ማሸጋገር ይቻላል! እንደተባለው በየአካባቢው በጨበራ ተስካርነት ክቡር ጊዜንና ገንዘብን ከማባከን በዘለለ ኢህአደግ ዛሬም በነገሰበት በሽግግር ሂደት ውስጥ እንዳለን ተደርጎ የሚነዛውን አደገኛ ህዝብን ማዘናጊያ ቃላት ወደ ጎን በመተው በተረጋጋና በሰከነ አዕምሮ ፓለቲካዊ ጥበብና ዕውቀትን መሰረት በማድረግ አጠቃላይ ሂደታችንን በመገምገም ፣ በማጤንና በመፈተሽ ብዙ መልካም አጋጣሚዎችን ትላንት እንዳጣነው እንዳይሆን አሁንም በአንድ በኩል የህወኃት አልሞት ባይ ተጋዳይነት፣ ከ50 በላይ በመገንጠል አባዜ የቆዬ ኃይሎች ፣ ማንነትን ከአገራዊ አንድነት አጉልተው ህዝብን የሚመሩ ሰብስቦችና ግለሰቦች ፣ የኤርትሪያና የአረብ አገሮች ፍላጎት በጥቅሉ አገሪቱ ከወትሮው የሰፉ ተፃራሪ ፍላጎቶችና ኃይሎች የጦዙበትና በነገሱበት ወቅት የአንድነት ኃይሉ የአገር አንድነትንና ሰላም ታሳቢ በማድረግ በሌሎች መዘውር ስር እንዳትወድቅ በጅምላ ብቻ ሳይሆን በጠበበ ተደራጅቶ በመናበብ መታገሉ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ከዚህም አልፎ በአራቱ ክልሎችና በጥቅሉም ” ኢህአደግ” በረቂቅም ህወኃትን ከአንበሳው ድርሻ ማውጣት ግድ ነው! ይህ ባልሆነበትና ሰንሰለቱ ከታች እስከላይ በተሸረበበትና ተቋማትን አንበሳውን ድርሻ የያዘው በራሱ እይታ ያቋቁም ተብሎ ቢተው ቢያንስ ቁልፋ ቦታዎች ላይ መሾም የሚችሉት ከኢህአደግ አጋር ድርጅት አባሎች ውስጥ ነው! ይህ አሁንም እየሆነ ነው! ሰሞኑን ምርጫ ቦርድን በመወከል የወይዘሮ አዜብ መስፍን ጎላ ወንድም አቶ ወንድሙ ጎላ ከዚህ በፊት ድርጅት መሰንጠቁ ሳይንሰው ዛሬም ምርጫ ቦርድን በመወከል ከውጭ የገቡ ተቃዋሚዎች ስለ ምርጫ ቦርድ መመዝገብ የመሩትን ስብሰባ አስመልክቶ በአሜሪካ ድምፅ ራድዬ ሰፊ ትንተና ሰጥተው ሰምተናል ፤  ይህ ደግሞ አሁንም የተንሻፈፉ ተቋማትን እስከተገነቡ ዲሞክራሲና ምርጫም የተንሻፈፈ እንጂ ዘላቂ እውነተኛ ፍታዊ ድሞክራሲያዊና ስርዓትን እውን ለማድረግ እረዥም ዓመታትን ይጠይቃል ።

አስራ ስምንት ወራት ገደማ የሚደረገው አገራዊ ምርጫም 27 ዓመት መንግስትና ፓርቲ ባልተለየለት 7 ሚሊዬን በፔሮል የሚተዳደሩ የድርጅት አባላትና ደጋፊ ዘዋሪ አባላት ያሉት ፣ ቢሮና መዋቅር በመላ አገሪቱ ክልሎች  እንደሸረሪት ድር የተተበተበው ኢህአደግ አንበሳውን ድርሻ በአጋር ድርጅቶቹ አማካይነት ገበሬ ማህበር ድረስ በያዘበትና ነገር ግን የኢትዬጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ዛሬም ድረስ በእኩል ተፎካራሪ ድርጅት በማያደርጋቸው የኃይል አሰላለፍ በምርጫው ውጤት ተፅዕኖ ፈጣሪ ያልሆኑ ጥቂት ወንበሮች በማግኘት የኢህአደግ መሪነትን በይሁንታ ሙሉ በሙሉ ማስቀጠል ግባቸው መሆኑ አይቀሬ ነው።

ኢህአደግ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ብዙ ቅስቀሳ አይሻም በመላው አገሪቱ ቅቡልነትን ያተረፈውን የፓርቲውን ሊቀመንበር ዶ/ር አብይን የመቀስቀሻ ባቲሪው በማድረግ ይህንን ሁሉ የለውጥ ተዓምር እንዲቀጥል ትፈልጋለህ ወይስ በተቃዋሚው እንዲቀለበስ ትሻለህ ብሎ መፈክር ማሰማትና ፓስተሮች ማዘጋጀት ብቻ ነው!

ስለሆነም ጎበዝ ትግሉን የጨበራ ተዝካር ብቻ ከማድረግ ተቆጥበን አንድነት ኃይሎች እንደ ቅንጅትና ህብረት ዓይነት በጠበቡ ስብስቦች በማቀናጀትና በማናበብ አጠቃላይ ሂደቱ ከስካር ወጥቶ ፓለቲካዊ ጥበብ በተላበሰ መልኩ የሚገመግም በሁሉም አካባቢዎችና በአገር አቀፍ ደረጃ እውነተኛ የአንድነት ኃይሉንና ገዥውንም አገዛዝ ጭምር ያሳተፈ መጪውን የአገሪቱን ዕጣ ፋንታ ከኢህአደግ ድርጅት ብቻ ውሳኔ በዘለለ ሁሉም ከድርጅት ሳጥን በመውጣት አገርን የማዳና እውነተኛ ፍታዊና ዲሞክራሲያዊት ኢትዬጵያን እውን ለማድረግ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የአሳተፈ የነጠሩ መፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የምመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ማድረግ እጅግ ወሳኝና አጣዳፊ ነው፣ በዚህ አንድነት ጎራው አንድ ቋንቋ ለመናገር ሰብሰብ ቢል ሁለት መፍትሔዎችን ከገዥው ኢህአደግ ፊት ማስቀመጥ ይቻላል፤

1/ ኢህአደግ እራሱም ባለድርሻ የሚያደርገው ያገባኛል የሚሉ ኃይሎችን ምሁራንን ፣ እምነት ተቋማትን ወዘተ ጭምር የአሳተፈ ሁለት ዓመት ብቻ የሚቆይ ጥምር ወይም ባላደራ መንግስት መመስረት፤ ይህ ሂደት ህገ መንግስቱን በህዝበ ውሳኔ ማሻሻል፣ በዚህም ተመርኩዞ መንግስታዊ ቅርፁን መወሰን ፌዴራላዊ በቋንቋ፣ በመልካ ምድር፣ አሃዳዊ ወዘተ በሚል ለማጥራት ፍቱን መድኃኒት ነው፤

2/ የሽግግር መንግስት ሂደቱን ዶ/ር አቢይ እንደፈነጠቁት ያለመቀበል ጠንካራ አቋም ካለ በሁለተኝነት ወደ ምርጫ ከመገባቱ በፊት የተባሉትን የዲሞክራሲ ተቋማትን ህግ ተርጓሚውን ፣ ህግ አስከባሪውን፣ብዙንኃ መገናኛን(ሚዲያ) ፣ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅትና እንባ ጠባቂ ተቋም ወዘተ በነፃነት የሚያዋቅርና የሚገነባ አገዛዙንም ተወካዬች ያካተተ ፣ ሰብሰብ በማለት ከተደራጅ ተቃዋሚ ድርጅቶች ፣ የእምነት ተቋማት፣ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች ወዘተ የሚያካትት የሽግግር ኮሚሽን ወይም የሽግግር ምክር ቤት መመስረት ነው! ይህ በነፃነት ሲዋቀር ወደ ምርጫ ሂደት ውስጥ በመግባት ውዝግብ ከተነሳ ምርጫ ቦርድና ፍርድ ቤት የሚወስነውን  ውጤቱ በፀጋ መቀበልና ለሚቀጥለው ምርጫ ተግቶ መስራት ይሆናል።

የሁላችንም ፍላጎት ከድርጅት ሳጥን ወጥቶ ስልጣንን ታሳቢ ባላደረገ መንገድ ከልብ ይህችን ሃገር ከዲሞክራሲያዊ ሂደት ሸርተቴ ማውጣትና እናት አገራችንን ከወደፊት ትርምስ ወጥታ፣ ከአፈናና አምባገነንነት ደዌ ተፈውሳ እንደ ጋናና መሰል አገራት በስደት የሚባዝነውን ምሁርና ዜጎች ሁሉ በማሳተፍ በልማትና ዕድገትና ደህንነት ቅነሳ ላይ ባተኮረ ፓሊሲ ላይ ሙሉ ጊዜዋን ያተኮረች እናት አገር ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ መገንባት ይቻላል፤

ከነዚህ ሂደቶች ውጭ የሚመጣ ለውጥ ውጤቱን የምንጠብቀው ቢያንስ ከአምስት ወይም አስር በላይ ዓመታት መሆኑን ልብ ልንል ይገባል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s