ለካ የግፍ አገዛዝ ገበና ሸፋኝ ነው! በተበዳይ ስነልቦና ሁሉንም አንድ አድርጎ ያኖራል! Yared Hailemariam

 

 

የግፍ አገዛዝ በተንሰራፋበት ሥፍራ ሁሉ አለቃው አንድ እና አንድ ሰው ወይም አንድ ቡድን ብቻ ነው። ያሻውን ያስራልም፣ ይገላል፣ ያፍናል፣ ይቆርጣል፣ ይፈልጣል። በዚህ ክፉ ሥርዓት ውስጥ ሁሉም አልቃሽ፣ ብሶተኛ፣ የግፍ ሰለባ እና ተሰዳጅ ነው። በደርግም ሆነ በወያኔ ዘመን አንድ ጉልበተኛ ብቻ ስለነበር አገሪቱን የተቆጣጠረው ሁሉም ጸጥ ለጥ ብሎ ነበር የግፍ እንቆቆውን ይጋት የነበረው።

ነጻነት ሁሉንም እኩል ያደርጋል። መንግስትንም ከገዳይነት እና ገፈኛነት አውርዶ የሕዝብ አገልጋይ ያደርጋል። ነጻነት ቀለም የለውም፣ ነጻነት ኃይማኖት የለውም፣ ነጻነት ብሔር ወይም ጎሳ የለውም፣ ነጻነት ባንዲራ ወይም መለያ የለውም። ነጻነት በሰፈነበት አገር ሁሉም ሰው እኩል ዋጋ አለው። ሁሉም ባህሎች፣ ኃይማኖቶች፣ ጎሳዎች ወይም ሌሎች መለያዎች ሁሉ እኩል ነጻ ናቸው። በነጻነት ምድር አንድ ነገር ብቻ ነው ኃያል ወይም የበላይ፤ እሱም የሕግ ልዕልና ነው።

የአንድ ሕዝብ ሕግ አክባሪነቱ፣ ሥርዓት አዋቂነቱም ሆነ ስልጡንነቱ የሚፈተነው በነጻነት ዘመን ነው። እያንዳንዱ ሰው ነጻነት ሲሰማው የሚያደርገው ነገር እና ነጻ ባልሆነበት ሥፍራ የሚያደርገው ነገር ፍጹም የተለየ ነው።

በአፈና ውስጥ ያለን ሕዝብ ባሕሪ ለማጥናትም ሆነ ለማወቅ እጅግ ከባድ ነው። ባህሪውን ላጥናም ብትል ሁለት ነገር ነው የምታገኘው አንዱ ሁሉም የጥቃት ሰለባ ስለሆነ በተበዳይነት ስነልቦና ሁሉም በጋራ ሊቆም ይችላል፣ አንድ አይነት ብሶትም ይነግርሃል። ሁለተኛው በፍርሃት ውስጥ ስለሚኖር አብዛኛው ሰው የልቡን ሳይሆን ገራፊዎቹ እና አሳሪዎቹ መስማት የሚፈልጉትን ነው የሚነግርህ። ወይም ለዘመናት ጸጥ እረጭ ብሎ ስለሚቆይ ምን እንደሚያስብ አታውቅም።

ባህሪ መገለጫው ያሳቡትን በነጻነት ሲናገሩ ወይም በነጻነት በተግባር ሲከውኑት ብቻ ነው። ለዛ ደግሞ ነጻ እና መብት ፈቃጅ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓት መኖር አለበት። ይህን ገበናⶭንን ደርግ እና ወያኔ ጋርደውልን ኖረዋል። ዛሬ ያ መጋረጃ ተቀዳዶ ገበናችን አደባባይ ላይ ወጥቷል።

ለፍቅር፣ ለመቻቻል፣ ለውይይት፣ ለመደማመጥ እና በእውቀት ላይ ለተመሰረጠ የለውጥ ጉዞ ወይስ ለጸብ፣ ለአንባጓሮ፣ እርስ በርስ ለመጠላለፍ ነው ቅርብ የሆነው?

እውነተኛ ማንነታችን የሚታየው አሁን ነው። ለዛም ነው የአዲስ አመታ ዋዜማ ላይ ባስተላለፍኩት የምኞት መልዕክቴን “እንኳን ለፈተና ዘመን አደረሰን!!!” ያልኩ።

ከዚህ ጽሑፍ ጋር ያያዘኳቸው ሁለት ምስሎች ያለፍነውን እና የምንመኘውን ሥርዓቶች ጥሩ አድርገው ይገልጻሉ። ከነ ልዩነቶቻችን አንድ ኢትዮጵያ በምትባል እሥር ቤት ውስጥ አብረን ሁሉንም መከራዎች አሳልፈናል። ዛሬ ከነ ልዩነቶቻችን ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ ነጻነትን ማጣጣም ጀምረናል። እርስ በእርስ እና ከመንግስትም ጋር ተከባብሮ መኖር እና መሥራት ያለውንም ትርፍ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ታዝበናል። አሁንም የሚጥመንን እንምረጥ፤ ታፍኖ – ተከባብሮ መኖር ወይስ ነጻ ሆኖ – ተከባብሮ መኖር ወይስ ነጻ ሆኖ- መገዳደል።

No automatic alt text available.
No automatic alt text available.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s