‹‹የአማራ ህዝብ ጀግና እና ኩሩ ህዝብ ነው፡፡በተባበረ ክንድ ሳንበታተን መሄድ አለብን፡፡የጨለመ መስሎ የሚታየን እየነጋ ስለሆነ ነው፡፡››አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

‹‹የአማራ ህዝብ ጀግና እና ኩሩ ህዝብ ነው፡፡በተባበረ ክንድ ሳንበታተን መሄድ አለብን፡፡የጨለመ መስሎ የሚታየን እየነጋ ስለሆነ ነው፡፡››አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ አበባ፣ ከየት ወደየት? – (ዶ/ር ሺመልስ ቦንሣ)

ስለ ጥንቷ አዲስ አበባ ከዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህሬ እንካችሁ! ዝምታ አለማወቅ አይደለም። የመጡበትን ሳያውቁ የሚሄዱበትን ማወቅ አይቻልም!
ሙሉነህ ዮሃንስ
*********
አዲስ አበባ፣ ከየት ወደየት? – (ዶ/ር ሺመልስ ቦንሣ)

“የድሮዋ በረራ (የአሁኗ አዲስ አበባ) የአምሃራ፤ ጉራጌ እና ጋፋት ክርስትና ተከታዮች ይኖሩባት የነበረች ከተማ ነች”

በመጀመሪያ

የዛሬ አንድ መቶ ሠላሳ አንድ አመት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1878 ንጉሰነገስት ምንሊክ ወደ አርሲ ሰራዊታቸውን ይዘው ይዘምታሉ።

ባልተቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ደግሞ እንጦጦ የነበረውን የመንግስት መቀመጫ ወደ አሁኗ አዲስ አበባ ያዛውራሉ።

ለጤና ተመራጭ የሆነው ፍልውሃ ፊንፊን ይልበት የነበረው ቦታ ለከተማው መቀየር አንዱ ግብዐት ቢሆንም የአድዋ ድል፣

የመንግስቱ መረጋጋት፣ የእንጦጦ ቀዝቃዛነትና ባካባቢው የነበረው የማገዶ እንጨት እጥረት የአገሪቷን ዋና ከተማ ወደ አዲስ አበባ ለመቀየር ተጨማሪ ምክንያቶች ሆነው አገልግለዋል።

ንግስቲቷ የአገሪቷን መናገሻ አዲስ አበባ ብለው ሲሰይሟት ሌላ ፡ ማለትም ስድስተኛ፡ ምክንያት እንድንፈልግ እንድንመረምርም ያደርገናል፣ ታሪክ ።

በስም ወይም ስያሜ ውስጥ ምን አለ? አዲስና አበባ አዲስ አበባ የሁለት ቃላት ጥምር ውጤት ነው፣ አዲስ እና አበባ።

የቦታውን ልምላሜና ውበት ከሚወክለው አበባ ከሚለው ስያሜ ይልቅ እንደገና መጀመርን፣ መታደስን፣ መነሳትን የሚያሳየው አዲስ የሚለው ቃል የተለቀ ትርጉም የተሸከመ ስም ይመስላል።

ባንድ በኩል ስያሜው የውጭ ወራሪ ጠላትን በማሸነፍ ከመጣው መረጋጋትና እርግጠኝነት በተጨማሪ ስለወደፊቱ የነበረውን ብሩህ ተስፋን፣

ወደፊት ማደግን መመንደግን፣ በአለም ማህበረሰብ ውስጥ ተገቢውን ቦታ አግኝቶ መከበርን ሲያመለክት በሌላ በኩል ደግሞ ወደሁዋላ ተመልሶ ማስታወስን፣ የጠፋን መመለስን ፣ የፈረሰ መገንባትን፣ እንደገና መታደስን ያሳያል።

እስቲ በሁለተኛው ትርጉም ላይ በማተኮር ወደሁዋላ ተመልሰን የከተማዋን ታሪክ መረጃዎቹ በሚሉት መሰረት እንመርምር።

ከተማና ታሪክ፣ ከበራራ እስከ አዲስ አበባ

የከተሜነት ታሪክ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊነቱን ለመረዳት በትንሹም ቢሆን የአገሪቷን ታሪክ ማንበብ ከተቻለም የከተሜነት ስልጣኔዋን የሚመሰክሩ የከተሞች ፍርስራሾችን {ለምሳሌም የሃን፣ አዱሊስን ፣ ቆሃይቶን}፣ ወይንም እስካሁን ያልጠፉትን ፣ ህይወት ያለባቸውን እነአክሱምን፣ ሃረርን፣ ጎንደርን መመልከት ይበቃል።

በስነህንጻ፣ በስነጽሁፍ፣ በስነመንግስትና በኪነጥበብ አክሱም የደረሰችበትን የስልጣኔ ከፍታ የተረዳው ማኒ የተባለው ፐርሻዊ ጸሓፊ

አክሱማዊት ኢትዮጵያን ከክርስቶስ ልደት በሁዋላ በአራተኛው ክፍለዘመን ከነበሩት አራት ታላላቅ ስልጣኔዎች አንዷ ናት ብሎ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

ሃረርና ጎንደርም የከተማነት ዝናቸው በብዙ ቦታ የናኘ መሆኑ ሰፊው ታሪካቸው ቆመው የሚታዩትም የስነሕንጻ ቅሪቶችም ማረጋገጫዎች ናቸው።

ይህንን ስንመለከት የአሁኗ አዲስ አበባ የዚህ ጥንታዊና ጥልቅ የከተማ ስልጣኔ ወራሽ እንጂ
ጀማሪ እንዳይደለች እንረዳለን ማለት ነው። እስቲ ስለአዲስ አበባ ትንሽም ቢሆን ታሪክን ወደሁዋላ እንበል።

የኢትዮጵያ የታሪክ ድርሳናትም፣ ሆነ የውጭ ሀገር ጸሐፍት የሚያረጋግጡት አሁን ሸዋ ተብሎ የሚጠራውና የአገሪቱ መናገሻ አዲስ አበባ የሚገኝበት አካባቢ ከዛሬ 700 አመት በፊት ማለትም የሰለሞናዊው መንግስት ከተመሰረተበት ከ13ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ የአገሪቱ ቁልፍ የፖለቲካ፣ የወታደራዊ፣ የኢኮኖሚና፣ የባህል ማዕከል ሆኖ ያገለግል እንደነበረ ነው።

በጊዜው የነበረው ማዕከላዊው መንግስት ከቦታ ቦታ ተዘዋዋሪ ቢሆንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ከተሞችን የመሰረተ ሲሆን ትልቁና በተደጋጋሚ የሚጠቀሰው ግን በራራ የተሰኘው ከተማ ነበር።

ወረብ በራራ የምትገኝበት ቦታ ሲሆን በመሐከለኛው ዘመን ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት እና የነገስታቱ ቤተመንግስት የተሰራበት የነበረ በ16ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ብዙ የውጭ ሀገሮችን የጎበኙት ፣ አባ ዳንኤል የተባሉ ኢትዮጵያዊ መነኩሴም ከኢየሩሳሌም ጋር ሁሉ ያመሳሰሉት ሀብታም አካባቢ ነበር።

ሺሃብ አድ ዲን {በቅጽል ስሙ አረብ ፋቂህ} የተባለው የመናዊ የፍቱህ አል ሃበሻ {የሃበሻመወረር} መጽሃፍ ጸሐፊ የግራኝ አህመድን ጦር በማጀብ ወረብንና በራራን ያየ ሲሆን ወረብን የሀበሾች ገነት ብሎ ጽፎላታል።

የበራራ ከተማ በአሁኗ አዲስ አበባ አካባቢ በተለይም እንጦጦ ላይ የተመሠረተ ሲሆን የኢትዮጵያ መዲናነት ታሪኩ የሚጀምረው በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት {እኤአ1380-1413} ሲሆን

የሚያበቃውም በአህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ጋአዚ {በቅጽል ስሙ ግራኝ አህመድ} ጦር በሚቃጠልበት የአጼ ልብነ ድንግል {እኤአ 1508-1540} ዘመን ነው።

እኤአ በ1450 ለመጀመሪያ ጊዜ ከተማው ፍራ ማዉሮ የተባለ ቬኒሲያዊ {ጣልያናዊ} ባዘጋጀው የዘመኑ ፈር ቀዳጅ በሆነው የአለም ካርታ ላይም ለመስፈር በቅቷል።

ካርታው መሬት ላይ ባሉ መረጃዎች ተመስርቶ የተሰራ ሲሆን እነሱም አዉሮፓ ከነበሩ ኢትዮጵያዉያንና በተለያየ ወቅት በተለይም በአጼ ይስሀቅ {እኤአ 1414-1430} እና

አጼ ዘርዓ ያዕቆብ {እኤአ 1434-1468} ዘመን ኢትዮጵያን ከጎበኙ አዉሮፓዉያን የተገኙ ነበሩ። ሰዓሊ ማዉሮም ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፣

“…{በካርታው ላይ የተመለከቱትን ስለአፍሪካ} ደቡባዊ ክፍሎች ማዉራቴ ለአንዳንዶች አዲስ ነገር ሊሆን ስለሚችል በጥንቶችም {በባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ስለማይታወቁ ከሰይቶ ጀምሮ ወደላይ ያለውን ጠቅላላ ስዕል ያገኘሁት ከቦታው ተወላጆች ነው ብዬ እመልሳለሁ።

እነርሱም ቄሶች ሲሆኑ {በካርታው ላይ ያሉትን} ክፍለ ግዛቶች ፣ ከተሞች፣ ወንዞችና ተራሮችን ከነስማቸው በእጃቸው ለእኔ የሳሉልኝ እነርሱ ናቸው።

ካርታው አሁን ድረስ ያሉ፣ እንዲሁም ስማቸው የማይታወቅ ቦታዎችን የጠቀሰ ሲሆን አቀማመጣቸውንም በመረጃ አስደግፎ ለማሳየት ሞክሯል።

ለምሳሌም ከዘረዘራቸው ውስጥ የየረር፣ የዝቋላ፣ የመናገሻና የወጨጫ ተራሮች፣ የዱከምና አዋሽ ወንዞች፣ በወጨጫ ተራራ አካባቢ የሚገኙ የቤተመንግስት ፍርስራሾች፣ ይገኙባቸዋል።”

ከማዉሮ ካርታ በተጨማሪም በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንና የውጭ ሰዎች ስለበራራና አካባቢው ብዙ መረጃዎችን ትተውልን አልፈዋል።

አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ያህል አሌሳንድሮ ዞርዚ የተባለ የቬኒስ ጣልያናዊ {15ተኛዉና 16ተኛው ክፍለዘመን} ፣ የመናዊው ሺሃብ አድ ዲን {16ተኛው ክፍለዘመን} ፣ እና አዉሮፓ የነበሩ የኢትዮጵያ መነኮሳት ፡ አባ ዞርጊ፣ አባ ሩፋኤል፣ አባ ቶማስና አባ እንጦንዮስ {15ተኛዉና 16ተኛዉ ክፍለዘመን} ይገኙበታል።

እኤአ በ1529 ሽምብራ ኩሬ {በደብረዘይት ወይም ቢሾፍቱና ሞጆ መሃል ያለ ቦታ} በተደረገ ጦርነት ንጉስ ልብነ ድንግል መሸነፉና ወደሰሜን ማፈግፈጉ ወረብንና የአገሪቱ መዲናን በራራን ለጥቃት ያጋለጠ ሲሆን እኤአ በ1530 ቦታዎቹ በግራኝ አህመድ ጦር ለመያዝ ከተማዋም ለመቃጠል በቅተዋል።

እንደሺሃብ አድ ዲን ትረካ ከሆነ የግራኝ ሰራዊት በአስር ቀናት ውስጥ ከአዋሽ ወንዝ መነሻ {የአሁኗ ግንጪ} ተነስቶ በራራ በመድረስ አጭር ቆይታ አድርጓል፣

ከበራራም ሆኖ ግራኝ የተወሰኑ ወታደሮቹን የስድስት ቀን የእግር መንገድ ወደሚፈጀው ደብረ ሊባኖስ ልኮ እንዳቃጠለ ይዘረዝራል።

የተቃጠለው የኢትዮጵያ መዲና የነበረው በራራ ከተማ የሚገኝበትን የወረብ ግዛት እንዲያስተዳድር ሙጃሂድ የተባለውን ታማኙን መሾሙንም ይጽፋል።

ከዚህ ጊዜ አንስቶ እስከ 19ተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ስለበራራ የሚዘግብ ምንም የጽሁፍ መረጃ አልተገኘም።

በ19ተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ግን የጥንቱን በራራ ታሪክ የሚያስታዉሱ ግኝቶች መታየት ይጀምራሉ።

እኤአ በ1881 በንጉስ ምኒልክ የሚመራው የሸዋ ፣ እኤአ ከ1889 በሁዋላም የኢትዮጵያ መንግስት መዲናውን እንጦጦ ላይ ያደርጋል።

እንደዘመኑ ትርክት ከሆነ {ድርሳነ ራጉኤል ላይ እንደተጻፈው} የንጉስ ምንሊክ እንጦጦ ላይ መከተም ከስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ታሪካዊ ትርጉም ነበረዉ፣ እሱም ታሪክ የዘከረዉን የጥንቱን የአጼ ዳዊት ከተማን እንደገና መገንባት፣ ወደአገሪቱ መዲናነትም መመለስ ነበር።

ንግርቱም ታሪካዊ መሰረት እንደነበረው የሚያመላክቱ መረጃዎች በእንጦጦ {የጥንቱ በራራ ክፍል} የተገኙ ሲሆን ይህንንም በጊዜው ሀገሪቷን የጎበኙ የውጭ ሀገር ሰዎች {ዲፕሎማቶች፣ ተጓዦችና ወታደራዊ ባለሙያዎች} ዘግበዉታል።

ቻርለስ ማይክል፣ ሲልቬይን ቪኘራስ፣ ሻለቃ ፓወል ኮተን፣ አልበርት ግሌይቸን፣ እና ቸዛሬ ኔራዚኒ፣ ጥቂቶቹ ሲሆኑ ሁሉም በቦታው የነበረዉን ጥንታዊ የመከላከያ ቅጽሩን ተመልክተው ስለጥንካሬዉና ግዙፍነቱ አድናቆታቸውን በጽሁፍ አፍረዋል።

እንጦጦ ላይ የፔንታገን ቅርጽ {አምስት ጫፎች ያሉት} ያለው በዙርያውም 12 መመልከቻ ማማዎች የያዘ እንደመከላከ የሚያገለግል ቤተመንግስትና ግንብ የተገኘ ሲሆን ርዝመቱም 520 ሜትር ከፍታውም እስከ 5 ሜትር እንደሚደርስ ታውቋል።

የስነህንጻና አርኪዎሎጂ ባለሙያዎች {ለምሳሌም ዴቪድ ፊሊፕሰን፣ ማይክል ዎከርና ማርክ ቪጋኖ እንደተነተኑት ግንቡ

እኤአ ከ1550 በፊት የነበረዉን የፖርቱጋልና ስፔን የመከላከያ ግንብ አሰራር ዘዴ የተከተል ሲመስል ቢያንስ የ400 አመት ወይም በላይ ዕድሜ ያለዉና በ16ተኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አጋማሽ ምናልባትም በአጼ ልብነ ድንግል የተገነባ እንደሚሆን ነው።

የአዲስ አበባ ምንነት

እንግዲህ በጥንቷ በራራና በአሁኗ አዲስ አበባ መሐከል ታሪካዊ ግኑኝነት እንዳለ ካየን አሁን ደግሞ የሁለቱን ከተሞች በተለይም የአዲስ አበባን መልክ ወይንም ዋና መገለጫ ባህርይ ምን እንደሚመስል እንመልከት።

የኢትዮጵያ ከተሞችና መዲናዎች {ለምሳሌም አክሱም፣ ጎንደር} ልክ እንደአገሪቷ ህብረብሄራዊ ገጽታ የነበራቸው ሲሆን በውስጣቸው የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ፣

የተለያየ እምነትና ባህል ተከታይ የሆኑና፣ በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁም የዉጭ ሀገር ተወላጆች የሚኖሩባቸው ቦታዎች ነበሩ።

ጥንታዊቷ አክሱም በሶስት ቋንቋ {ግዕዝ፣ግሪክ፣ ሳባ} የምትጽፍ፣ ከሶስት ቋንቋ በላይ የምትናገር፣ ከኢትዮጵያዉያን በተጨማሪ ግብጻዉያን፣ የመረዌ {ሱዳን} ሰዎች፣ የመናዉያን፣ የምስራቅ ሜድትራንያን {ፊንቄያዉያን፣ ግሪኮች፣ የጥንት ሶሪያዉያን} ተወላጆች እንዲሁም ህንዶችና ቻይናዉያን የኖሩባት ወይም ደግሞ የሰሩባት ታላቅ ከተማ ነበረች።

ጎንደርም ብትሆን የክርስትና፣ የእስልምናና የአይሁድ እምነት ተከታዮች አብረው ኖረው {ተለያይተው የሰፈሩ ቢሆንም} ፣ በስራና በህይወት ተስተጋብረው መልኳንና ታሪኳን ውብና ዥንጉርጉር አድርገው የቀረጿት ከተማ እንደነበረች ታሪኳ ይመሰክራል።

ሀረርም ከአራቱ የእስልምና ቅዱሳን ቦታዎች አንዷ ስትሆን በብዝሀነቷ እና በእምነት ማዕከልነቷ የምትታወቅ፣ በመቻቻል ታሪኳ የተመሰገነች በዚህም እንደ ታዋቂዉ የፈረንሳይ ገጣሚ አርተር ራምቦ እና እንግሊዛዊዉ ሪቻርድ በርተን ያሉ የውጭ ሰዎችን ለመማረክ የቻለች ምስራቃዊ እንቁ ነበረች፣ ነች።

የበራራም ታሪክ ቢሆን በብዝሃነት ያሸበረቀ እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። በከተማዉም ሆነ በዙሪያው ባሉ እንደ ወረብ ባሉ ግዛቶች ይኖር የነበረው ማህበረሰብ በብዛት ከአምሃራ፣

ከጉራጌ እና ከጋፋት {ሶስቱም ተቀራራቢ ቋንቋዎችን ይናገራሉ } የተዉጣጣ እና የክርስትና እምነት ተከታይ የነበረ ሲሆን በተጨማሪም የሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎችና እምነት ተከታዮች ይገኙ እንደነበረ ይታሰባል።

ለዚህም ምክንያቱ ከተማው ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በተለይም ከምስራቅ ኢትዮጵያ በዛም በኩል አድርጎ ከአረቡና የህንዱ ስልጣኔ ጋር በንግድ እና በባህል የተገናኘ ስለነበረ ነው።

በበራራ የታሪክና የስነህንጻ አሻራ ላይ የተገነቡት ሁለቱ ወራሽ ከተሞችም {እንጦጦና አዲስ አበባ} የነዋሪዎቻቸው ያሰፋፈር ታሪክ ከዚህ በተለየ መንገድ የተቃኘ አልነበረም፣ ይልቁንም የበፊቱን ታሪክ መሰረት አድርጎ ፣ ብዝሃነትን አቅፎና ደግፎ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሆኖና ተላብሶ የተፈጠረ ቅኝት፣ ያደገ ማንነት ነው ያላቸው፣ በፊትም አሁንም።

አዲስ አበባ ስትመሰረት የነበራትን ጥልፍልፍና ድርብርብ ታሪክ በ19ኛውና በ20ኛ ክፍለዘመን መባቻ ላይ በሃገርኛና በጎብኝዎች የተጻፉ ስራዎች ዘግበውታል።

ነገስታቱ በተለይም አጼ ሀይለ ስላሴ ከተማዋ ዘመናዊ ብቻ ሳይሆን ብሄራዊ ሆና እንድትፈጠር ወይንም እንድታድግ ያቀዱና የሰሩ ስለነበር አዲስ አበባ ከተማም፣ የሀገርም ምልክት ሆና በእሷ ውስጥ ኢትዮጵያን በኢትዮጵያ ውስጥም እሷን እንዲታይ፣ እኛም እንድናይ ሆና ነበር የተቀረጸችው።

በእርግጥ በአገሪቱ መሪዎች እና በከተማ ቀራጮች አእምሮ ውስጥ የታለመችው አዲስ አበባ እንደታሰበችው ሁሉ መሬት ላይ ባትሰራም

{ለምሳሌ የመሰረታዊ አገልግሎቶች እጥረት፣ የስራ አጥነት፣ የሀብት ልዩነት ቢስፋፋባትም } ከተማዋ የኢትዮጵያውያን ሆና ኢትዮጵያን ከነዥንጉርጉር ውበቷና ከነውስብስብ ችግሯ መስላና፣ ተመስላ እስካሁን አለች፣ ትኖራለች።

አዲስ አበባ፣ አዱገነት ሸገራችን ከብዙ የአፍሪካዉያን ከተሞች በተለየ ድሃና ሀብታም ተሰባጥረው የሚኖሩባት፣ ነዋሪዎቿን ከነብዝሃነታቸው ሳትለይ አቅፋ የኖረች፣ ያኖረች፣

የምታኖር የኢትዮጵያ የልብ ትርታ፣ ነርቭ ማዕከል የሆነች ኦ አዲስ አበባ “ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ“ የምንልላት ከተማችን፣ ችግሯም ችግራችን፣ ፍቅራችን እንደገናም ተስፋችን፣ የሆነች ማረፊያችን ሆናለች።

የአዲስ አበባ ማንነት

ይህችን ስብጥር የሆነች ከተማ፣ ንብርብር ታሪክ የተሸከመች ምድር፣ ከመሪዎቿ በላይ የብዙሃን ነዋሪዎቿ ድምር ውጤት፣ የእጅ ስራ ነጸብራቅ ሆና የኖረች ግማደ-ኢትዮጵያ የማን ናት?

በብዝሃነት ጥልፍልፍ ተጸንሳ ለተወለደች፣ አድጋም ለጎለመሰች አዲስ አበባ ምንነቷና የማንነቷ ምስጢር በአንድነት ተጋምዶ፣ በልዩነት ውበት አሸብርቆ ደምቆ የተፈጠረ የሃገርነት ቋጠሮ ነው።

አዲስ አበባ ልክ እንደኢትዮጵያ የነዋሪዎቿ ስብስብ ውጤት ብቻ ሳትሆን፣ ከድምርነትም በላይ እጅግ የጠበቀ፣ የጠለቀ ጥልፍ ስብጥር ናት። ለመሆኑ እዲስ አበባን ለመፍጠር ያልተጋ ኢትዮጵያዊ እጅ የት አለ

ኦሮሞው ከአማራው፣ ጉራጌ ከትግሬው፣ ዶርዜ ከሀረሪው፣ ሶማሌ ከወላይታው፣ ምስራቁ ከደቡብ፣ ሰሜኑ ከምዕራብ፣ ወንዱ ሴቱ፣ ልጅ አዋቂዉ፣ አማኙ የማያምነው፣

ነጋዴው ከምሁሩ፣ ሀገሬዉ ከሌላው ተዋዶ፣ ተዋልዶ፣ ተናግዶ፣ ተቀናጅቶ የፈጠራት፣ ከተማ ከሚባል ነገር በላይ የሆነች ምስጢር አይደለችምን?

ከቦታነት በላይ የዘለቀች ሁሉም እምነቷን ካመኑ፣ ሕይወቷን ኖረው ትርጉሟን ካወቁ አባል የምታደርግ፣ እጆቿን ዘርግታ የምትቀበል፣ የራሷ የምታደርግ ትልቅ ሃሳብ {Addis Ababa as an Idea} አልሆነችም?

አዲስ አበባ አግላይ ከሆነ የኔነት፣ የኔ ናት ከሚል ህሳቤ ወጥታ፣ ርቃ አልፋ ሄዳ፣ የኛነት፣ የእኛ ናት ወደሚል ሰብሳቢ ሃሳብነት ያደገች ከተማ ሆናለች።

ይህ ማለት ግን ሁሉም እኩል ነበር? እኩል ታይቶስ ነበር? ብዙው አዲስ አበቤ አልተገለለም? እስቲ በምሳሌ እናስረዳ።

በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን በ1960ዎቹ አመታት በቁጥር 1768 የሆኑ ግለሰቦች 58% የሚሆነውን የከተማውን ቦታ ተቆጣጥረው ነበር።

24000 የሚሆኑት የከተማው ነዋሪዎች 7.4% {በግለሰብ 150 ካሬ ሜትር ማለት ነው} የከተማውን ቦታ ሲይዙ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የከተማው ህዝብ መሬትም ሆነ መኖርያም አልነበረውም።

በንጉሳዊው ዘመን፣ ከስርዓቱም መውደቅ በሁዋላ ባሉት መንግስታት በተለይ አሁን ጥቂቶችን በጠቀመ ልማትና ዘመናዊነት ስም ከተሜው ከኖረበት ቀዬው እየተነሳ ይፈናቀላል፣ ከኑሮውም ከማህበራዊ ህይወቱም ይቆራረጣል።

በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ዙሪያ የሚኖሩት አርሶአደሮችም {ኦሮሞም አማራም ትግሬም ሲዳማም እና ሌሎች ኢትዮያውያን} በአነስተኛ ካሳ መሬታቸውን ይቀማሉ፣ ሰርቶ የመኖር መብታቸውን ይነጠቃሉ።

እንግዲህ የአዲስ አበባንና የሌሎች ከተሞቻችንን ታሪክ ስንተርክ እነኝህንና ሌሎች ታሪካዊ በደሎችን፣ ዘመናዊ ነጠቃዎችን የተሸከመ ከተሜነትና ዘመናዊነት ይዘን መሆኑን ሳንዘነጋ ነው።

አዲስ አበባና የዘመኑ ትርክት በአሁኑ ሰዓት፣ እንደ በፊቱ ሁሉ፣ የአገሪቱ መዲና አዲስ አበባ ቅራኔዎች የሚፈጠሩባት፣ እንዲሁም የሚንጸባረቁባት ቦታ ሆናለች።

ውጥረቶቹ በመሠረታዊነት መደባዊ ሆነው በብሄር ማንነት መነጽር ይተነተናሉ፣ በዛም ላይ ተንተርሶ ህዝብን ለትግል ማደራጃ ሆነው ያገለግላሉ።

በአሁኑ ጊዜ ሁለት ትርክቶች የከተማውንም ሆነ የአገሪቱን ትኩረት ስበው ይገኛሉ ።

ሁለቱም ታሪክን በተለያየ መንገድ ይመለከታሉ የራሳቸውንም በደሎች ያጣቅሳሉ።

አንደኛው ህብርብሄራዊ ሆኖ ረጅም የታሪክ ምልከታ ይዞ አዲስ አበባን፣ ከፍ ሲልም ኢትዮጵያን በህብረብሄራዊ መነጽር እያየ በከተማውም ሆነ በአገሪቱ ያሉ የተንከባለሉ ብሶቶችን በመደብ መነጽር ይተነትናል።

ሁለተኛው ብሄርን ማዕከል አድርጎ በቅርቡ የታሪክ እይታ ተመስርቶ ከተማውን፣ በከተማዉና በአገሪቱ ያሉ የተከማቹ በደሎችን በብሄር መነጽር ይሞግታል፣ አማራጮችንም ይጠቁማል።

ሁለቱም እይታዎች እነሱም ላይ የቆሙ ትንተናዎች የየራሳቸው እዉነቶች አሏቸዉ።

የከተማዉን ብሎም የአገሪቷን ታሪክ እና ነባራዊ ሁኔታ በራሳቸው መንገድ ይተርካሉ ፣ ይሞግታሉ።

ነገር ግን አዲስ አበባን በሁለቱ መነጽሮች ብቻ መመልከት የከተማዋን በዛውም የአገሪቷን ንብርብር እና ቁልፍልፍ ታሪክና እውነት አበጥሮ ፣ አብጠርጥሮ ለመረዳት የሚያስችል መንገድ አይሆንም።

የጎደለ እይታን ይፈጥራልና። በተለይ ደግሞ መጤ እና ነባር የሚለው ትርክት በአንድ አገር ዜጎች መሐከል ደረጃ በማውጣት አንደኛና ሁለተኛ ዜግነትን በመፍጠር የማግለል አንዳንዴም የመንቀል ፖለቲካን ያመጣል።

በሰዎች ህይወትም ላይ የሚወስን ነውና አደገኛም ነው።

በቅርቡም በመንግስት የቀረበው “የልዩ ጥቅም መብት“ ከፍ ሲልም በአንዳንድ የዘውጌ ልሂቃን የተነሳው “የባለቤትነት“ ጥያቄ በከተማውም ሆነ በአገሪቱ ያለውን ውጥረት ያሳያል።

የአዲስ አበባ የልዩ መብትና የባለቤትነት ፖለቲካ በኢትዮጵያ እየጦዘ ፣ እንዲጦዝ እየተደረገ ያለው የዜግነት፣ የአገርነትና ፣ የአገር ባለቤትነት ትልቅ ጥያቄ መገለጫ ነው። ታዲያ ምን ይሻላል።

የአዲስ አበባ ምሳሌነት አዲስ አበባ በብዙ መንገድ የኢትዮጵያ ተምሳሌት መሆኗ በየቀኑ የሚታይ እውነታ ነው ከተማዋን ማወቅ ማለት አገሪቷን መረዳት ማለት ነው።

የአዲስ አበባን ችግሮች ተረድተን መፍታት ከጀመርን የኢትዮጵያን ጥያቄዎች የመሞገት ፣ ፈተናዎቿንም የመጋፈጥ ታላቅ ስራ ጀመርን ማለት ይሆናል።

ከተማዋን የምንመለከትበት መነጽር ፣ ከፍታዎቿን፣ ዝቅታዎቿንና ተስፋዎቿን የምንተነትንበት መንገድ ለአገሪቷም ይሰራልና ለጊዜው እንደዚህ ብንጀምርስ፣

አንደኛ፣ እይታዎቻችን በብሄር ወይንም በመደብ ምልከታ ከማጥበብ፣ እኛም ከመጥበብ ሰፋ አድርገን ፣

ሁለቱንም ተቀብለን ሌሎችም አማራጮች እንዳሉ ግን አጥብቀን ተረድተን ፣ እንሱንም ፈልገን ፣ ሁሉን አቀፍ አገራዊ እይታ ብንፈጥርስ (avoiding the danger of a single story)

ሁለተኛ፣ ከተማችን እንዲሁም አገራችን የብዙዎች እኛነቶች ጥምር ውጤት መሆኗን አምነን ያንዳችን ችግር ወይም ብሶት እንደራሳችን ወስደን እይታቸውንም ዋጋ ሰጥተን ያጋመዱንን ገመዶች ብናጠብቅስ (having radical empathy for fellow countrymen)

ሶስተኛ፣ በእኔነት እና በልዩነት ብቻ የገነገነውን ፖለቲካና ትርክታችንን በእኛነት ላይ፣ ድልድይ በመስራት ፣ ከእኛ ባሻገር ካሉ የኛዎች ጋር ባለን አንድነት ላይ አትኩረን። ብንሰራስ (Bridge building, crossing borders)

ሺመልስ ቦንሣ
ህዳር 16, 2010 ዓ.ም.

Image may contain: 1 person, text

“ሀገርን ማን ይምራ?”

ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ
የኢኮኖሚክስ መምህርና ጸሓፊ

(ሸክም የበዛበት ትውልድ፡ 2009 እና
የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ
)

በአንድ ወቅት በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሶስት ሰዎች ስለሀገራቸው ነባራዊ ኹኔታ እጅጉን ቢጨነቁና ቢጠባቸው እርስ በራስ ሲወያዩ የውይይታቸው ሂደት ሄዶ ሄዶ ጥያቄዎችን እንዲያነሡ ግድ አላቸው፡፡ “ሀገርን ማን ይምራ?”፤ “ሀገር በማን ብትመራ ውጤታማ ትኾናለች?”፤ “እንዴትስ ብትመራ ዘላቂና አስተማማኝነት ያለው ኹለንተናዊ ስኬትን ታመጣለች?” የሚሉ ዋነኛ ጥያቄዎችን አነሡ፡፡

እነዚህ ሶስት ሰዎች በዕድሜ – ወጣት፣ ጎልማሳና አረጋዊ ሲኾኑ የከተማ ነዋሪዎችና ስለወቅታዊ ነባራዊ የሀገራቸው ነባራዊ ኹኔታ በቂ ግንዛቤ ያላቸው ናቸው፡፡

በውይይታቸው ወጣቱ “እኔ ሀገር መመራት ያለባት በወጣት ነው፡፡ ምክንያቱም የሀገራችንን አብዛኛውን ቁጥር የሚይዝው ወጣቱ ነው፡፡ – -” ገና ሳይጨርስ ጎልማሳው አቋርጦት “መሪ እንጂ አማሪ እኮ አላልንም፡፡ ደሞ – – -” ወጣቱ እየተናደደ አቋርጦት “ኸረ ባክህ ዲሞክራሲ ማለት እኮ የአብዝሃ አመራር ነው፡፡ እኛ ደሞ ብዙ ነን፡፡”

ጎልማሳው “ኸረ ውሸት!! የፈጣሪ ያለህ! ዲሞክራሲ የአብዝሃ ፍላጎት ይመራል – የጥቂቶች መብት ይከበራል፤ የአብዝሃ ሃሳብ ገዥ ይኾናል – የጥቂቶች ሃሳብ ይከበራል፤ የአብዝሃ ድጋፍ ያገኘ ይመራል – የጥቂቶች ነጻነት ይከበራል፤ እንጂ በፍጹም ብዛት ያለው ይመራል አይልም፡፡ ደሞ እኮ – እኛም ወጣት ነበርን፡፡ መቼ መራን? እናንተም በጊዜ ሂደት ከወጣትነት ትርቃላችሁና ከዚህ ፍሩሽ ሀሳብ ብትወጣ ይሻላል፡፡”

ወጣቱ ለጥቂት ደቂቃ ዝም ካለ በኃላ “እሺ – ባልከው ሀሳብ ተስማማሁ!!! ነገር ግን ወጣቱ ጉልበት፣ ዕውቀት እንዲሁም የመስራት ትልቅ ፍላጎት ስላለውና የአብዝሃን ፍላጎት ስለሚረዳ ሀገር መመራት ያለበት በወጣት ነው፡፡”
ጎልማሳው እየሳቀ “ወጣቱ ልምድ የለውም፡፡ አብዛኛው ወጣት ገና በትምህርት ዓለም ላይ ያለ ነው፡፡ የተመረቁትም ቢኾኑ ገና ሥራ መጀመራቸው ነው፡፡ ደሞ አብዛኛዎቹ ከመዝናናት፣ ስለጾታዊ ፍቅር ከማሰብ፣ ገና ራሳቸውን እንኳ ያልቻሉ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ጥገኛ የጥገኛ ናቸው፡፡”

ወጣቱ “እና ማን ይምራ?”
ጎልማሳው “ጎልማሳው ነዋ!!!”
ወጣቱ “ኸረ ባክህ! ጎልማሳው አስመሳይና ዳተኛ ነው!!!”
ጎልማሳው “እንዴት?”
ወጣቱ “ይኸው አብዛኛዎቻችሁ ስለራሳችሁ፣ ስለቤተሰቦቻችሁ እንጂ ስለሀገር ለማሰብ ጊዜ የላችሁም፡፡ አንተ ራስህ ለስሙ የተማርከው ትምህርት ስለሕዝብ ኾኖ የምትሰራው የግል ድርጅት ውስጥ ነው፡፡ ደሞ ትዳርና ልጆች ስለሚይዛችሁ መስዋዕትነት አትከፍሉም፡፡”

ጎልማሳው አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ፡፡ እውነታውን በራሱ ሕይወት የተመለከተው በመኾኑ ለመመለስ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ዝምታን መረጠ፡፡፡

ዘወትር እንደለመዱት እጅግ በጭቅጭቅ፣ በእልህና በአልሸነፍ ባይነት ሲከራከሩ ቢቆዩም ከላይ የተነሡትን ጥያቄዎች ካነሡ ወዲህ መቀዛቀዝ አለ፡፡ እስካሁን አንዳች ያልተነፈሱትን አረጋዊ ወጣቱና ጎልማሳው ሲመለከቱ እሳቸውን እንደሚጠብቁ የገባቸው አረጋዊ ጉሮሯቸውን አጽድተው “ጥያቄው ከባድ ነው፡፡ ለኔ ለራስህ አደላህ እንዳትሉኝ እንጂ ሀገር በአረጋዊ ብትመራ መልካም ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ህጻንነትንም፣ ታዳጊነትን፣ ወጣትነትንም ኾነ ጎልማሳነትን በደንብ ስለሚያውቁትና ስለሚረዱት አረጋውያን ቢመሩ መልካም ይመስለኛል፡፡”

ጎልማሳው “እኔ ግን አረጋውያን ለለውጥ ብዙም አይተጉም፡፡ ራሳቸውን ከነገ ይልቅ ከትላንት ጋር ስለሚያነጻጽሩ፣ ዘመኑን ለመዋጀት ዳተኞች ስለኾኑ ለውጥ ያመጣሉ ብዪ አላስብም፡፡”
ወጣቱ “እኔም እንደዛ ነው የማስበው፡፡ ብዙ ጊዜ ከአረጋዊ ጋር ቁጭ ስል የሚያወሩት ወሬ ኹሉ ታሪክ – ታሪክ – ታሪክ ነው፡፡ ብዙም አዲስ ነገር ለማምጣት፣ ለመፍጠርና ከጊዜው ጋር በፍጥነት መሮጥ አይችሉም፡፡”
ጎልማሳው “እውነት ነው፡፡ አረጋውያን ብዙም ለነገሮች ስለማይጓጉ መሪነት ከሚጠይቀው ትዕግስት፣ ዕውቀት፣ ልምድና ጥበብ ያላቸው ቢኾንም ከዛ በተጨማሪነት ወሳኝ ወቅታዊነት፣ ከታሪክ አውጊነት ይልቅ ታሪክ የመስራት ቁጭትና ትጋት፣ ኹነትን የማንበብና ራስን በእጅጉ ከማድመጥ ባሻገር ሌላውን የማድመጥ ችግር አለባቸው፡፡ እኔ ብቻ ልክ ነኝ! እኛ ያልነው ካልኾነ! የማለትና ሌላውንም ይንቃሉ፡፡ ደሞ ለራሳቸው የተጋነነ ምስል አላቸው፡፡”
ወጣቱ “በጣም! ብዙ ጊዜ እነሱ በሚሉትና መሬት ላይ ባለው ጥሬ ሃቅ መሐከል እጅግ የሰፋ ልዩነት አለ፡፡”

አዛውንቱ “ታድያ ሀገራችንን ማን ይምራ? ወጣቱ ስሜታዊና ልምድ አልባ ነው፡፡ ጎልማሳው ደሞ በኑሮ ተወጥሮና የኑሮ እስረኛ ነው፡፡ አረጋዊ ግን በብዙ መለኪያዎች የተሻለ ነው፡፡ ዕውቀት፣ ልምድና ትዕግስት አለው፡፡ ደሞ ከኹሉ በላይ ኔትወርክ አለው፡፡” ሲሉ መልስ የሚሰጥ ጠፋ፡፡ ዝም ዝም ኾነ፡፡

እንደሌላው ጊዜ ውይይታቸው ሊረዝም አልቻለም፡፡ ልዩነታቸው ጎራ ለይቶ የግድ ይሄ መኾን አለበት ለማለት ሳያስችላቸው ቀረ፡፡ ረዥም ሰዓት ወስደው ተራ በተራ ሀሳባቸውን ቢገልጹም ዞሮ ዞሮ ቀድመው ካነሡት የተለየ አልኾን ሲላቸው ወጣቱ “እኛ መስማማት አልቻልንም፡፡ ለምን ታላቁ መምህር ጋር ሄደን አንጠይቃቸውም?” ሲል በሀሳቡ ተስማምተው – ተነሡ፡፡

በመንገድ ሲሄዱ በየራሳቸው ሀሳብ ነጉደው አረጋዊው ከመሐከል ጎልማሳው በቀኝ – ወጣቱ ደግሞ በግራ ኾነው በፍጥነት ሲራመዱ ለተመለከታቸው እጅግ ለአስቸኳይ ጉዳይ የሚፈጥኑ ይመስላሉ፡፡ አረማመዳቸው የኾነ የቸኮሉበት ጉዳይ እንዳለ በግልጽ ያሳብቃል፡፡

እጅግ የታወቁትና የሚፈሩት መምህር ብዙ ጊዜያቸውን በማንበብና በማስተማር የሚያሳልፉ ታላቅ በሕብረተሰቡ ዘንድ የሚከበሩ በገዥዎች ደግሞ በቀጥተኛና በደፋር አንደበታቸው የተነሣ የሚጠሉና የሚፈሩ ኹለገብ አዋቂ ቢኾኑም በዋናነት የሃይማኖትና የፍልስፍና ሊቅ ናቸው፡፡ የዕውቀትና ጥበብ ጉዳይ ከተነሣ እሳቸው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡ ይጠራሉ፡፡ ይገኛሉ፡፡ እሳቸው ያሉት “እንዲህ እኮ አሉ” ተብሎ በብዙዎች ዘንድ ይጠቀሳል፡፡

ታላቁ ምሁር ዘንድ ሲደርሱ መምህር ከተማሪዎቻቸው ጋር ቁጭ ብለው ስለሰው ልጅ ሕይወት ምንነትና ግንኙነት እየተነተኑ “- – – ሰው ከራሱ፣ ከፈጣሪው፣ ከመሰሉ፣ ከአካባቢውና ከተፈጥሮው ጋር የማይቋረጥ ግንኙነት አለው፡፡ ይህ ጤናማ፣ ሰላማዊ፣ ፍቅር፣ ትዕግስትና ትጋት የተሞላበት እንደኾነ የስኬት ኑሮ ይኖራል፡፡ ካልኾነ የመከራና የስቃይ ኑሮና አኗኗር ይኖራል፡፡ ያኗኑራል፡፡ – – ” ያስረዳሉ፡፡ ትምህርታቸውንም ሲጨርሱ በጸሎት ዘግተው ተማሪዎቻቸው ጉልበት እየሳሙ ሲሄዱ ሶስቱ ሰዎች ቀርበው በመሳለም የአክብሮት ሰላምታ ሰጥተው አጠገባቸው ቁጭ አሉ፡፡

ሰላምታ ተለዋውጠው ዝም ዝም ሲባባሉ ወጣቱ “መምህር የመጣነው ጥያቄ ለመጠየቅ ነው፡፡”

መምህር ”መልካም – ስለምን” አሉ ፊታቸው እንደኹል ጊዜው በፈገግታና በፍቅር ተሞልቶ፡፡ ወጣቱ “ስለሀገር ጉዳይ ስናነሣ ሶስት ዋነኛ ጥያቄ አነሣን፡፡ 1ኛ. ሀገርን ማን ይምራ? 2ኛ. ሀገር በማን ብትመራ ውጤታማ ትኾናለች? 3ኛ. እንዴትስ ብትመራ በኹለንተናዊ መንገድ ውጤታማ ትኾናለች? የሚሉ ናቸው፡፡ እኛ መስማማት ስላልቻልን እርሶን ለመጠየቅ መጣን፡፡”

መምህር “መልካም – ጎበዞች! ሰው በዚህ ዘመን ስለራሱና ስለራሱ ብቻ በሚያስብበት ጊዜ ቦታ ሰጥታችሁ፣ ጉልበታችሁንና ስሜታችሁን ስለሀገር ጉዳይ ሰጥታችሁ መወያየታችሁና ረዥም ርቀት ተጉዛችሁ መምጣታችሁ – ዕውነት የታላቅነታችሁ መገለጫ ነው፡፡ ለመኾኑ እናንተ ምን መለሳችሁ?”

ሶስቱም እርስ በራስ ተያይተው፡፡ አንተ – አንተ ሲባባሉ ቆይተው፡፡ አረጋዊው ጀምረው – ጎልማሳው በመቀጠል በስተመጨረሻ ወጣቱ በዝርዝር የተነጋገሩበትን በየራሳቸው አንደበት በስፋት ሀሳባቸውን ገለጹ፡፡
በጥሞና ሲያደምጡና በአዎንታ ራሳቸውን እየነቀነቁ የቆዩት መምህር “ሀገር በምንድነው

የምትመራው? በሀሳብ ወይስ በዕድሜ?”

ሶስቱም ደንግጠው በአንድነት “በሀሳብ! በሀሳብ! በሀሳብ!” አሉ፡፡

መምህር “ስለኾነም የተደራጀ፣ የጠራና ዘመኑን የዋጀ ሀሳብ ያለው ሀገርን ቢመራ መልካምና ውጤታማ ያደርጋታል፡፡ ይህም ወጣቱ፣ ጎልማሳው አልያም አረጋዊው ጋር ሊኖር ይችላል፡፡ ይህንንም የያዘና በባለቤትነት መያዝ የሚችል የመሪነቱን ቦታ ሊያገኝ ይገባል፡፡” ብለው ዝም ሲሉ ሶስቱም በመልሳቸው ተደንቀው፡፡ በነሱ አለማስተዋል አፍረው – ዝም አሉ፡፡

መምህር ከከፍታው ቤታቸው ሩቅ ያለ አድማስ ላይ አተኩረው እየተመለከቱ “ወዳጆቼ ሀገራችን ዛሬ መሪ ብቻ ሳይኾን ጥሩ ተመሪም አጥታለች፡፡ የሰው ልጅ ታሪክን ስንመለከት – መሪም ተመሪም የሌለበት፣ ገዢነት በተመሪነት ላይ ለመሠልጠን የተጋበት፣ ገዥነት የሠለጠነበት፣ ገዥነት ወደ መሪነት በተመሪዎች ትግል ያደገበት፣ ተመሪነት በዝቅጠት የተሞላበትና ተመሪና መሪ ድንበር አልባ የኾነበት፣ ተመሪ መሪን መምራት የቻለበት – መሪ በራሱና በሚያስፈልገው ሳይኾን በተመሪዎች ፍላጎት የተመራበት፣ ጭራሽ ዛሬ መሪነትም ኾነ ተመሪነት ዝቅጠት ውስጥ ያለበት ዘመን ነው፡፡” አሉ፡፡

ከረዥም ጸጥታ በኃላ ወጣቱ “መምህር መፍትሔው ምንድነው?”

መምህር “አይ ልጄ – መፍትሔ እንዲሁ በቀላሉ የሚነገር ቢኾን ገና ድሮ መፍትሔ ይኖር ነበር፡፡ ትልቁ ስህተታችን እጅግ ሰፊ፣ ውስብስብና ተለዋዋጭ ኹለንተናዊ ለኾነው የሀገራችን ችግር እንደቀላል መፍትሔው ይሄ ነው! ብለን መግለጻችን ነው፡፡ የሀገር ችግር እንደምናወራው፣ እንደምንጽፈው፣ እንደቃል ምንገባው፣ እንደሚነገረውና እንደሚባለው ቀላል አይደለምና የሀገር መሪነት ከቀላል ሰዎች እጅ መውጣት፤ እንዲሁም በተመረጡ አካላት በኩል ሰፊ ኹለንተናዊ ጥናት ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡” አሉ፡፡

በታላቅ ተመስጦ ሲያደምጡ የቆዩት ሶስቱም የተመካከሩ ይመስል በደስታ፣ ፊታቸው ፈክቶ፣ ውስጣቸው ሰላም አግኝቶ በአክብሮት ተነሥተው ሲቆሙ፡፡ መምህር በእርጋታ ከወንበራቸው ተነሥተው እያሳለሙ – በእቅፋቸው ውስጥ አስገብተው በፍቅር ሳሟቸው፡፡ ሶስቱም በአንድነት አመስግነው ሲራመዱ መምህር ”ወዳጆቼ ሀገር የህጻናት፣ የታዳጊም፣ የወጣትም፣ የጎልማሳና የአረጋዊ ነች፡፡ አንዱን ያጎደለች እንደኾነ ጎዶሎ ትኾናለች፡፡ ደሞ እንዳትረሱ ሀገራችን የኹላችንም ናት!!! እንዳትረሱ ሀገራችን የኹላችንም ናት!!! በዕድሜ ብቻ ሳይኾን በግብርና በምግባርም ወጣት ሳሉ እንደአረጋዊና ጎልማሳ የሚያስተውሉ፤ ወጣት ሳሉ የህጻን፣ ጎልማሳ ሳሉ እንደህጻን፣ አረጋዊ ሳሉ የህጻንነትን ጠባይ የያዘውም ጭምር፤ የደጎቹ ብቻ ሳይኾን የክፉዎቹም፤ የእውነተኞቹ ብቻ ሳይኾን የሀሰተኞቹም፤ የሀብታሞቹ ብቻ ሳይኾን የድሃዎቹም፤ የየዋህና ቅኖቹ ብቻ ሳይኾን የመሰሪዎቹና የአስመሳዪቹም፤ የባለራዕዮች ብቻ ሳይኾን የዓላማ ቢሶችም፤ የጌቶች ብቻ ሳይኾን የአሽከርና ባሪያዎችም ጭምር ናት!!! በግብር የሚመሳሰሉ በአንድነት ያለ-ሌላው ተመሳሳይ ብቻ የሚኖርበት ሀገር ከሕይወት ህልፈት በኃላ ነው፡፡” ሲሉ ሶስቱም በአዎንታ ራሳቸውን እየነቀነቁ በታላቅ አክብሮት ዝቅ ብለው የስንብት ሰላምታ ሰጥተው ወደ መውጫው አመሩ፡፡

ፈጣሪ ሀገራችን ነጻ ፍቃድን የኹሉ ነገር ማዕከል ወደ ሚያደርግ የዕሳቤ ሂደት ትገባ ዘንድ ይርዳን!
ቸር እንሰንብት!

ኦሮማራው ‹‹እኔ›› | ከዮሐንስ መኮንን

(ክፍል አንድ)
“”””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””

ስለ ኦሮሞ ሞጋሳ (Moggaasa) የጻፍኩት አጭር ማስታወሻ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ግለታክ አካል ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቼ መልእክቱን ተጋርተውታል:: ስለ አባቴ በመተረክ የጀመርኩት ጽሑፍ የእናቴን ደግሞ እንድተርክ ገፋፍቶኛል፡፡ አሁን ደግሞ የራሴን ግለታሪክ ላካፍል ነው::
በፌስቡክ ገጽ የሚጋራ ጽሑፍ በጠባዩ አብዛኛው አንባቢ በሞባይሉ ገጽ (Screen) ስለሚያነበው ከሚገባው በላይ አጭር በመሆኑ ብዙ ጠቃሚ ታሪኮችን ቆርጦ ለመጣል ያስገድዳል፡፡ ይህንን ግለታሪክ ግን ያለቅጥ ክማሳጠር ይልቅ ባይሆን በሦስት ክፍል ላቀርበው ወስኛለሁ:: ክፍል አንድ እነሆ!
“”””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””

ቀደም ብዬ እንዳጫወትኩህ አናት እና አባቴ ከአዲስ አበባ በስተምእራብ (ጅማ መሥመር) 83 ኪሜ አካባቢ ምዕራብ ሸዋ በቶሌ ወረዳ ባንቱ የተባለች ትንሽዬ የገጠር ከተማ (ጥጊያ መንገድ እንኳን ባልነበራት) በኦሮሞ ምድር ወልደው ከብደዋል፡፡ እኔ ለቤተሰቤ 12ተኛ ልጅ መሆኔ ነው፡፡ (አራት ታናናሾች እንዳሉኝ ሳትረሳ)

ንፋስ በነበርኩበት የልጅነቴ ወራት ከአባገዳ ልጆች ጋር ከብት እንጠብቅ ነበር፡፡ ኦሮማራ የሆንን እረኞች (እኔ እና ጓደኞቼ) ከብት ስንጠብቅ ውለን ፀሐይዋ መግረር ስትጀምር ከብቶቻችንን ከመስኩ ላይ አሳርፈን እኛ ደግሞ በአባገዳ ዋርካ ጥላ ሥር ምሳችንን እየተሸማን በጋራ እንበላ ነበር፡፡ የእሸት ወራት ሲሆን ደግሞ አቤት ደስታችን ! ከማሳዎቻችን የስንዴ ነዶ አጨድ አጨድ አድርገን እንቁጦ (በእሳት የተለበለበ እሸት) ቃም ቃም እያደረግን እነርሱ አያቶቻቸው ያቆዩላቸውን ሂቦ (Hibboo የኦሮሞ ሥነቃል) ሲያጫውቱኝ እኔ ደግሞ የመንዞቹን አያቶቼን ‹‹እንቆቅልሽ›› እየነገርኳቸው አስፈነድቃቸው ነበር፡፡ (የአባ ገዳ ልጆች በልጅነቴ ነግረውኝ እስከዛሬም ልረሳው ያልቻልኩት ሂቦ በተጠየቅ አንዲህ ይላል (Ejarsaa waaritu – Sinbirti hin qaaritu – ትርጓሜው የምሽቱን ወይራ ወፍ ብትበርር አትዘለውም) መልሱ ‹‹እግዚአብሔር›› ማለት ነው)

አባቴ ጥብቅ ክርስቲያን ስለነበር ልጆቹን በሙሉ ክርስትና ሲያስነሳን ለታቦት ነው የሰጠን፡፡ ስለዚህ የክርስትና አባት እና እናት ማናችንም የለንም፡፡ ባይሆን የዓይን እናት እና አባት ሆነው የተዛመዱን የአባገዳ ልጆች ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ የእኔ የዓይን አባቴ ቦንሳ ረጋሳ ሲሆኑ ለዓመት በዓል ለልጆቻቸው ልብስ ሲገዙ ለእኔም ይገዙልኝ ነበር፡፡

በዚህች ጭው ባለች ትንሽ የገጠር ቀበሌ ውስጥ በልጅነት ልቤ እንደነፍሴ ስምወዳቸው ጓደኞቼ ላጫውትህማ፡፡ አንደኛው ሶሎሞን ሚርከና ጫሊ ነው፡፡ ሚርከና በደርግ ዘመን ወታደር ሆኖ ኤርትራ የዘመተ ኦሮሞ ሲሆን ከዘመቻ ሲመለስ ኤርትራዊት ሚስቱን እና አራት (?) ልጆቹን ይዞ ቀበሌያችን ይመጣል:: ከኦሮሞ አባት እና ከኤርትራዊት እናት ከተወለዱት ልጆች ትንሹ ሶሎሞን ሲሆን ጥፍጥ ያለ ኮልታፋ አማርኛውን ለመስማት ስል ጏደኛዬ አደረኩት:: እኔ “ኦሮማራ” ሶሎሞን “ኦሮግሬ”! (ኦሮሞ +ትግሬ) አቤት ስንዋደድ:: የሚያሳዝነው ኦሮግሬው ሶሎሞን አሁን የት እንዳለ እንኳን አላውቅም:: እህቶቹ ስለ ኤርትራ ባህር ይነግሩን ስለነበር ባላየነው ቀይባህር ወደባችን በዓይነ ህሊናችን እየሳልን በደስታ እንፍነከነክ ነበር::

ሁለተኛው የልጅነት ጏደኛዬ ደግሞ ሠይፉ ይባላል:: ሠይፉ የትምህርትቤታችን እውቅ የሒሳብ መምህር የባጫ ጭሪ ሠፋቶ (Baacaa Cirri Safaato) ልጅ ነው:: ሠይፉን በሁለት ምክንያት ልቤ እስኪጠፋ እወደው ነበር:: አንደኛ ጸጉሩ ሉጫ ስለነበር ሲሆን (ይሄኔ እኮ አሁን ተመልጦ ይሆናል!) ሁለተኛው በትምህርቱ ጎበዝ ስለነበር ነው:: (በነገራችን ላይ አብረን ይተማርነው 1ኛ ክፍልን ብቻ ነው) እንደ እርሱ በትምህርት ጎበዝ ለመሆን የጀመርኩት መንገድ ሰምሮልኝ ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል ስማር አንድ ጊዜም ሁለተኛ ወጥቼ አላውቅም:: ሁሉንም አንደኛ ደረጃ ተማሪ ነበርኩ! እድሜ ለሠይፉ:: ዛሬ ሠይፉ ባጫ ጎበዝ ሐኪም (specialist) እንደሆነ እና ባሌ ጎባ ሆስፒታል ይሠራ እንደነበር ሰምቻለሁ:: (ይህን ጽሑፍ ያነበው ይሆን?)

በገጠር ቀበሌ ሁሉም ልጅ ክረምት ላይ እረኛ ይሆናል:: ትምህርት ቤት ሲከፈት ግን ክብት ጠባቂዎች በሁለት ብር ወርሃዊ ክፍያ ከብቶቻችንን ስለሚጠብቁልን እኛን ያሳርፉን ነበር:: ታዲያ በጠዋት ማልደን ተነስተን ከብቶቻችንን ለጠባቂዎች እስረክበን በእሸት ማሳዎች መሀል በሩጫ አቆራርጠን ደወል ሳይደወል ወደ ትምህርት ቤት መድረስ ይጠበቅብን ነበር:: የትምህርት ቤታችንን ደወልን በልጅነቴ በአድናቆት እመለከተው ነበር:: ሳድግና ሳውቀው የመኪና ጎማ ቸርኬ ኖሯል ዛፍ ላይ ሰቅለውልን በማረሻ ብረት “የሚደውሉልን:: የእኛ ከብት ጠባቂዎች የእነ አዲቾ ጉርሜሳ ቤተሰቦች ነበሩ:: (አዲቾ በኦሮሚፋ ፀአዳ ወይንም ነጭ ማለት ነው) ታዲያ አንዳንዴ ከብቶቼን ላደርስ በሄድኩበት የአዲቾ እናት የጥቁር ጤፍ ቂጣ በወተት ስለሚሰጡኝ ትምህርት ቤት መሄዱን እየርሳሁ እዚያው እየዋልኩ ፈተና ሁሉ እምልጦኝ ያውቃል::

አባቴ ቆፍጣና ገበሬ ስለነበር ከእርሻ በተጨማሪ የገጠር ሆቴል ነበረን:: የገጠር ሆቴል ምን እንደሚመስል ታውቃለህ? አራት የሽቦ አልጋ የተዘረጋባቸው ሁለት ክፍል አልቤርጎዎች እና ስድስት አግዳሚ መቀመጫ ያለው ማለት ነው:: ስለዚህ እንግዶች እኛ “ሆቴል” ያርፉ ነበር:: ከማልረሳቸው የሆቴላችን ደምበኞች ወዳጆቼን ትግራዋዮቹን እነ ተጫነ ዓለሙን እና እነ በየነን አስታውሳቸዋለሁ:: የስፖርት አስተማሪያችን ትግሬው መኮንንስ እንዴት ይረሳል? ተጫነ ሥራው ፖሊስ ሲሆን እነበየነ የግብርና ሠራተኞች ነበሩ:: አንዳንዴ ለትግሬው ተጫነ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ የኦሮሚፋ አስተርጏሚ እሆናለሁ:: (ያው ከገበሬዎቹ በኦሮሚፋ አናግሬ ሁለት ብር ጉቦ እቀበልለት ነበር ልልህ ብዬ ምሥጢር ማውጣት እንዳይሆንብኝ ተውኩት) እርሱ ደግሞ ቤት ሲመጣ ትግርኛ ያስተምረን ነበር:: “ንሽተይ ንሽተይ” ለመስማት ታህል የምትሆን ትግርኛ ያወቅሁት ያኔ ነው:: ያኔ የጀመረችው አንደኛዋ እህቴ ግን አሁንም ትግርኛን በደምብ አቀላጥፋ ስለምታንበለብለው ለማያውቋት “ተጋሩ” ነው የምትመስላቸው::

አንድ ብር የመክፈል አቅም ያለውን የመንደራችንን ሰው መሀመድ የተባለ ጉራጌ (ሙስሊም) ፎቶግራፈር ባልሳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ ወደገጠር ከተማችን መጥቶ በጥቁር እና ነጭ (black and white) ፎቶ ያነሳን ነበር:: መሀመድ ሲመጣ ከተማ ውስጥ ካልነበርክ ፎቶ አመለጠህ ማሉት ነው:: ፎቶ መነሳት ካማረህ በቃ መበሳጨት አያስፈልግህም:: በቶሎ ይመለሳል … ስድስት ወር ብቻ ታግሰህ ትጠብቃለህ!

ይህን ሁሉ የተረኩልህ እስከ ስምንት ዓመቴ የነበረውን ታሪኬን ነው:: በስምንተኛው ዓመቴ አዲስ አበባ ገባሁና እሳት የላስኩ አጭቤ የአብነት ሠፈር ልጅ ሆንኩ::

የትም ተወለድ ሸገር ላይ እደግ !!!
“””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””
(ይቀጥላል

አብይ ይህችን ሰዓት ! (መስከረም አበራ)

 

መሪ ማለት የእዝብ አገልጋይ መሆኑን ከ27 ዓመት በኋላ አሁን አስታወስኩኝ

ዶ/ር አብይ ከባዷን ኢትዮጵያ በቀላል ልብ ሊመሩ የተረከቡ አሳዛኝ ሰው ናቸው፨ ሊሄዱበት ያሰቡት መንገድ ለሁሉም እኩል አይገባውም – የሚኒሶታ መድረክ ላይ ቆይታቸው ምስክር ነው !

አብይን እኛም የጎሳ ተጋሪዎቻቸውም እንደግፋቸዋለን፤ተስፋ እናደርግባቸዋለን፨ እነሱ ዝም ብለው የሚወዷቸውን ያህል ችግርም ይፈጥሩባቸዋል ፤ግራ ያጋቧቸዋል፨ ጃ warንም አብይንም እኩል ከመውደድ በላይ ምን ግራ አጋቢ ነገር አለ?

እኛ ደግሞ ይህኛውን የአብይን ችግር ለመረዳት ይቸግረናልና፨ አላስርም ያለ ሰው የሚመራው መንግስት ያውም በገፍ እያፈሰ ሲያስር ግር ይለናል፤አጥብቀን እንጠይቃለን ፨ በዚህ ላይ የምናምነው አብይ ድምፃቸው ሲጠፋ “ዋሹን እንዴ? “ብለን እንጠረጥራለን፨በመሪዎቹ ሲከዳ ፣ሲዋሽ የኖረ ህዝብ ይህን ቢል ፍርድ የለም ! ሁሉም እንደገባው መላ ይመታል ፣ ይጠረጥራ ፣ አንስቶ ይጥላል፨ እኔም ከእዚህ ወገን ነኝ!

የጅምላ እስሩ እጅግ አስከፍቶኛል! ሆኖም መንስኤው የአብይ ቃላቸውን ከመጠበቅ መንሸራተት አይመስለኝም፨ ፖለቲካ ያልፈለጉትን ጭምር ሊያሰራ የሚችል አጣብቂኝ እንዳለው ይገባኛል፨ ይህ አጣብቂኝ ነው አብይን ዝም ያደረጋቸው፨

የዛሬዋ ሃገራችን ከገሃነም መልስ ጉዞ ላይ ነች! የመልስ ጉዞዋ በርባንን ፈታችሁ ንፁሁን ስቀሉ የሚሉትን ማስከፋት መልሶ ወደ ገሃነም የሚጨምርበት ነገር ይኖራል፨ የጲላጦስ ንግስናም ሆነ ይሰቀል ስለተባለው ኢየሱስ የሚያውቀው ሃቅ ኢየሱስን ከመሰቀል አላዳነውም፤ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ጲላጦስ ቢቸግረው እጁን ታጠበ፨ አንዳንዴ ቅዝምዝም እስኪያልፍ እንዲህ ነው ! ንግስና ሁሉ ውሳኔን ላያስችል ይችላል፨ ቀስ እያለ የሚፀና ወንበር አለ !

በአብይ ወንበር እና ህልም መሃል አላዋቂዎች የሚዘውሩት ስሜት የሚነዳው ዘረኝነት የተባለ ብርቱ ፈተና መጥቷል፨ በዚህ መሃል መዘወሪያው ምክንያታዊነት የሆነው ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ችግር ውስጥ ገብቷል፨ እዚህ ላይ አብይም ኢትዮጵያን ከሚሉት ወገን ናቸውና ችግር ውስጥ ናቸው ማለት ነው፨ ግራ የገባው ሃገር ውስጥ ነን!

ወገኖቻችን እንዲፈቱ እንጩህ፤ ግን በእሾህ በተከበቡት አብይ ላይ ለመፍረድም አንቸኩል ! በልቡ ከወያኔ እስከ ኦነግ መንፈስ በተሞላ መዋቅር ውስጥ ናቸውና ሁሉ እንደልባቸው ላይሆን ይችላል፨ ምስጋናችን ቶሎ አይራቀን፨ በበኩሌ ፖርላማ ቀርበው አሸባሪ እኛ ነን ጥፍር የምንነቅል ፣ጨለማቤት የምናስር ለማለት ያልተቸገሩ ሰውዬ በእስር ሃገር ለመግዛት ያስባሉ ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፨

ፓለቲካችን በዛቻ እና ማስፈራሪያዎች እየተወጠረ ነው (ያሬድ ሃይለማሪያም)

ተራው የኛ ነው እያሉ ያሉት አክራሪ ልሂቃን እና የብሄር ድርጅቶች ሕዝብን፣ ሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶችን፣ መገናኛ ብዙሃንን፣ ጋዜጠኞችን እና መንግስትን ጭምር ከወዲሁ ማስፈራራት ጀምረዋል። የዛሬው የአምስቱ ድርጅቶች መግለጫ፣ ቀደም ብሎ አክራሪ ግለሰቦች ይሰጧቸው ከነበሩት ማስጠንቀቂያና ዛቻዎች የተለየ አይደለም። በዚህ አካሄድ የት ይደረስ ይሆን?

እኔን የሚያሳስበኝ በመግለጫው ላይ የተነሱት የመብት ይሁን የጥቅም ጥያቄዎች አይደሉም። እጅግ አሳሳቢው ነገር የዘረዘሩዋቸውን የጥቅም እና የመብት ጥያቄዎች ለማስጠበቅ እየሄዱበት ያለው መንገድ ነው። ያነሱት የአዲስ አበባ ባለቤትነት፣ የፌደራሊዝም እና ሌሎች የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የፖለቲካ ጥቅሞችን ለማስፈጸም እንደ አንድ ተወዳዳሪ ፓርቲ በምርጫ ሂደት ውስጥ ተወዳድረን ስናሸንፍ እናስፈጽማልቸዋለን አይደለም እያሉ ያሉት። እንዲያ ቢሆንማ ምን ገዶን ቅር ይለናል። እዳው ለመራጩ ሕዝብ እና በምርጫው ለሚወዳደሩት ሌሎች ተፎካካሪ ድርጅቶች ይሆን ነበር።

እየተባለ ያለው ግን ወደድክም፤ ጠላህ፣ ወደፊት በሚካሄደው ምርጫ ተመረጥንም፣ አልተመረጥንም እነዚህ ጥቅሞቻችን እና መብቶቻችንን የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍንጫውን ይዘንም ቢሆን እናስከብራለን ነው። ይህ አካሄድ ኢዲሞክራሲያዊ ከመሆኑም ባሻገር የወደፊቱን ምርጫ አስፈላጊነት ከወዲሁ ጥያቄ ውስጥ የከተተ እና እነሱ የፈለጉት ካልሆነም ወደ ኃይል እርምጃ እንደሚገቡ ያመላከተ ነው።

በአዲስ አበባ ውስጥ በኦሮሞ ትምህርት ቤቶች፣ ተቋማት እና ከክልሉ በመጡ ሰዎች ላይ የተደረገውን ሕገ ወጥ ነገር ማውገዝ ይገባል። እሱን እኛም እናወግዛለን። አጥፊዎቹም በሕግ አግባቢ ሊጠየቁ ይገባል። እደግመዋለሁ በሕግ አግባብ። ወታደራዊ ካምፕ ሰዎችን ማጎርን አይጨምርም። ነገር ግን ያንን ክስተት ሽፋን አድርጎ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ እየተሰነዘረ ያለው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ግን ለከት እያጣ እየመጣ ነው። አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነች። በከተማው ውስጥ የመኖር እጣ ፈንታህ በእኛ እጅ ነው የሚመስል ማስጠንቀቂያ ሌላ የፖለቲካም ሆነ የጸጥት መዘዝ እንዳለው ልትረዱት ይገባል።

ለማንኛውም እያየን እና እየታዘብን ያለነው ነገር ይች አገር ወዴት እየሄደች ነው የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ግድ ይለናል። እነ ዶ/ር አብይ እና ቲም ለማም የገቡበት ፈተና ቀላል አይመስልም። ሕዝብ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። እነሱም ተስፋ ለሰጡት እና ቃል ለገቡለት ሕዝብ በጽናት ከፊቱ እንዲቆሙ እግዚያብሔር ብርታቱን ይስጣቸው።

ጉባኤው ብአዴንን የት ያደርሰዋል?

የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን እና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
አጭር የምስል መግለጫየብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን እና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

በገዢው ግንባር ኢህአዴግ ጥምረት ውስጥ በተካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና አላቸው ተብለው ከሚጠቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤውን ያካሂዳል።

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ ሆኖ በቆየባቸው ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ በውስጡ አንዳንድ ለውጦችን እያደረገ በገዢው ግንባር አባልነት ዘልቋል።

• የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር

• አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

የብአዴን መስራች አባላት ዋነኛ መሠረታቸው ከሆነው ኢህአፓ በመለየት መንቀሳቀስ በጀመሩበት ጊዜ መጠሪያቸውን ኢህዴን (የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) የሚል አድርገው ነበር።

ነገር ግን በገዢው ግንባር ውስጥ ያሉት ሦስት ድርጅቶች የተወሰነ ሕዝብና አካባቢን የሚወክል መጠሪያ በመያዛቸው ኢህዴን በተለይ የአማራ ህዝብን ወካይ የኢህአዴግ አባል መሆኑን ለማጉላት ስያሜውን ወደ ብአዴን ቀይረ።

ከዚህ ውጪ ግን እንደቀሪዎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በግንባሩ ስር በመሆን ተመሳሳይ ለውጦችንና ውሳኔዎችን በክልሉ ውስጥ ሲወስንና ሲያስፈፅም ቆይቷል።

በዚህም በርካቶች ብአዴን የራሱ የሆነ ፖለቲካዊ አቋም የሌለው እንዲሁም መጠሪያው ያደረገውን ህዝብ ጥቅምና መብት ማስከበር የማይችል ድርጅት ነው በማለት ሲተቹት ቆይቷል።

• አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ

በተለይ ከአማራ ክልል ውጪ የሚኖሩ አማሮች የተለያዩ ችግሮች ሲገጥሟቸው ብአዴን አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን የሚጠበቅበትን አልተወጣም የሚሉ በርካቶች ናቸው።

ለረዥም ጊዜ የተለያዩ አካላት በድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች ከአማራ ህዝብ አብራክ የወጡ ባለመሆናቸው በአግባቡ ሊወክሉት አይችሉም በማለት ከንቅናቄው እንዲወጡ በተለያየ መንገድ ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል።

ግለሰቦቹ የወከሉትን ህዝብ በአግባቡ አላገለገሉም ከመባላቸው ባሻገር የድርጅቱንና የህዝብን ንብረት አባክነዋል፤ እንዲሁም እንደቤተሰብ ንብረት ተገልግለውባቸዋል የሚሉ ወቀሳዎችም ሲቀርቡባቸው ነበር።

የብአዴን አርማImage copyrightANDM FB

በዚህም ሳቢያ በተለያዩ ስፍራዎች ወቀሳና ተቃውሞዎች ሲቀርቡበት የቆየው ብአዴን ንቁ ሆኖ በኢህአዴግ ውስጥ በመንቀሳቀስ የህዝቡንና የክልሉን ጥቅም የሚያስከብሩ ሥራዎችን እንዲሰራ ከውስጥም ከውጪም ግፊቶች ሲደረጉበት ቆይቷል።

በተለይ ከ2008 ወዲህ በተለያዩ የሃገሪቱና የክልሉ አካባቢዎች እየተጠናከረ የመጣው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ንቅናቄውን ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግን ጭምር ስጋት ውስጥ በማስገባቱ በግንባሩ ውስጥ ለውጦችን ለማድረግ ሰፊና ተከታታይ ስብሰባዎች ተካሂደው ነበር።

• ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት?

በግንባሩና በመንግሥት አመራር ላይ ለውጦችን ይዞ የመጣው ተከታታይ ስብሰባና ግምገማ በኢህአዴግና አባል ድርጅቶቹ ውስጥም ከፍተኛ የሚባል፣ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥና መነቃቃትን በመፍጠሩ በርካቶች ብአዴንም ይህንን ለውጥ በማጠናከር በኩል አስተዋጽኦ እንደነበረው ይናገራሉ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በነሐሴ ወር አጋማሽ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን በጥረት ኮርፖሬት ላይ በፈጠሩት ችግር ምክንያት እስከ ድርጅቱ ጉባኤ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ አሳልፏል።

ከዚህ ውሳኔ በኋላ የታገዱት አባላት ከንቅናቄው አመራሮች ጋር በመገናኛ ብዙሃን እሰጥ አገባ ገጥመው ነበር።

• አቶ ታደሰ ካሳ፡ “…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው”

የአሁኑ ጠቅላላ ጉባኤም በአቶ በረከትና በአቶ ታደሰ ላይ የመጨረሻ ውሳኔውን ከማሳለፍ ባሻገር ሌሎች መስራችና ነባር አባላቱን እንደሚያሰናብት እየተነገረ ነው።

ግልጽ ያልሆነው ነገር እነዚህ የሚሰናበቱት አመራሮች ኦዴፓ (ኦህዴድ) እንዳደረገው በክብር ይሰናበቱ ይሆን የሚለው ነው።

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ለረጅም ጊዜ ሲተቹበት የቆየው አዳዲስና ወጣት አመራሮችን አለማብቃታቸው ዋነኛው ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ያልተጠበቁ ለውጦችን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ እንዳመጡ የሚነገርላቸው ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ወጣቶችን ወደ አመራር የማምጣቱ ጥያቄ በየአባል ድርጅቶቹ ውስጥ ዋነኛ አጀንዳ ሆኗል።

በዚህም ኦዴፓ እንዳደረገው ብአዴንም በርካታ ቀደምት የድርጅቱን አመራሮች በማሰናበት አዳዲስ ወጣቶችን ወደፊት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም የበርካታ የክልሉን ወጣቶች ቀልብ እየሳበ ያለውን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ተግዳሮት ለመቋቋም ሊጠቀምበት ይችላል።

• «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ»

ብአዴን “የለውጡ ቀጣይነት ለአማራ ህዝቦች ተጠቃሚነትና ዲሞክራሲያዊ አንድነት ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚያካሂደው 12ኛ ደርጅታዊ ጉባኤ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም በተለያዩ መስኮች የለውጥ እርምጃዎችን በመውሰድ በክልሉ ህዝብ ዘንድ ተመራጭ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ መገኘት የሚያስችሉትን ውሳኔዎች እንደሚሰጥበት ንቅናቄው በተለያዩ አጋጣሚዎች አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም የብአዴን አቻ ኦህዴድ እንዳደረገውና የንቅናቄው አባላት ጥያቄ እንደሆነ የተነገረው የድርጅቱን ስያሜ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይም ማሻሻያ እንደሚያደረግ ይጠበቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ባለፉት ዓመታት የአማራ ክልልን ጨምሮ በመላ ኢትዮጵያ ለህዝቦች መፈናቀልና መሰደድ፣ ለህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት የሆኑ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ለመፍታት የሚረዱ መንገዶች ላይ ውይይት እንደሚያደርግም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም በድርጅቱ ስር ያሉ የልማት ድርጅቶች፣ ማለትም ጥረት ኮርፖሬት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ የተባሉት ድርጅቶች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግሥት እንዲሆን ተወስኗል።

ጉግል ስለእርስዎ ብዙ ያውቃል፤ እርስዎስ ስለ ጉግል ምን ያውቃሉ? እነሆ 10 ነጥቦች

ጉግል ለሁለት ተማሪዎች የተሰጠ 'የቤት ሥራ' ነበር ቢባል ማን ያምናል?Image copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫጉግል ለሁለት ተማሪዎች የተሰጠ ‘የቤት ሥራ’ ነበር ቢባል ማን ያምናል?

ጉግል 20ኛ ዓመት የልደቱን በዓሉን ሊያከብር ሽር ጉድ እያለ ነው። ይህን ተንነተርሰን ስለ ጉግል ምናልባት የማያውቋቸው 10 ነጥቦች ይዘን ብቅ ብለናል።

ከጉግል በፊት ሕይወት ምን ትመስል ነበር? አንድ መረጃ በፍጥነት ሲፈልጉ ምን ያደርጉ እንደነበር ያስታውሱታል?

ምንም ይፈልጉ ምን፤ የአንድን ቃል ትርጓሜ እና አፃፃፍም ይሁን የቦታ ጥቆማ፤ ብቻ የሆነ ነገር ሲፈልጉ ወደ ጉግል መሮጥ የተለመደ ሆኗል። ‘ዕድሜ ይስጠውና’ ጉግል ፊት ነስቶን አያውቅም፤ ‘ጎግለው’ እንዲል የሃገሬ ሰው።

 

በየሰከንዱ ይላል ፎርብስ የተሰኘው መፅሄት መረጃ. . .በየሰከንዱ 40 ሺህ ሰዎች ‘ይጎግላሉ’፤ በቀን 3.5 ቢሊዮን እንደማለት ነው።

ጉግል ሁሉ ነገር ሆኗል፤ ማስታወቂያ በሉት፣ የቢዝነስ ዕቅድ እንዲሁም ግላዊ መረጃ መሰብሰቢያ ነው።

እንግዲህ እውነታውን ልናፈራርጠውም አይደል፤ እናማ ስለጉግል አንድ ሚስጢር እንንገርዎት። መረጃ ፍለጋ ወደ ጉግል በሮጡ ቁጥር ጉግል ስለእርስዎ የተወሰነ መረጃ ይሰበስባል።

«ግን ምን ያህል መረጃ?» አሉን?፤ መልካም! እነሆ የጠየቁንን ጨምሮ ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች።

፩. ስያሜው

ጉግልImage copyrightGETTY IMAGES

ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።

በእንግሊዝኛው ‘googol’ ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።

እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።

• አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ

፪. የጀርባ ማሻ

የጀርባ ማሻImage copyrightGETTY IMAGES

የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው ‘Backrub’ ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።

ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ።

ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።

. የተንጋደደ

ሰኪው በጉግል ላይ
አጭር የምስል መግለጫአያስቦ፤ እይታዎ ሳይሆን ምስሉ ነው የተንጋደደው

ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።

እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን “askew” የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።

ውጤቱ አዩት?

፬. ፍየሎች

ፍየሎችImage copyrightGETTY IMAGES

ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው።

አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ።

ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።

፭. እየተመነደገ የሚገኝ ‘ቢዝነስ’

ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም ወይ ቴሌግራም መለያ ምልክቶችImage copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም ወይ ቴሌግራም ይጠቀማሉ? የማን ንበረት እንደሆኑስ ያውቃሉ?

ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።

ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።

፮. ዱድል

ጉግልImage copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫየጉግል የተማሪዎች ውድድር

ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።

ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።

አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።

• ከደሴ – አሰብ የሞላ?

፯. ለሌሎች ያመለጠ ዕድል

በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።

ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።

አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።

፰. መሪ ቃላት

የመልካምና የመጠፎ ምልክቶችImage copyrightGETTY IMAGES

‘ከይሲ አይሁኑ’ ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።

‘ምን አገባው’ የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።

፱. ምግብማ ግድ ነው

ከጉግል ዋና መሥሪያ ቤት የማይጠፋ ነገር ቢኖር ምግብ ነውImage copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫከጉግል ዋና መሥሪያ ቤት የማይጠፋ ነገር ቢኖር ምግብ ነው

ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።

የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።

፲. የጉል ባልንጀራ

ውሻImage copyrightGETTY IMAGES

የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።

ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።

አጀብ ነው!

ዶ/ር ዓብይ አህመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት አስተላለፉ

ዶ/ር ዓብይ አህመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት አስተላለፉ

ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው እና በነገው ዕለት የሚከበረውን የመስቀል በዓል በማስመልከት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ አስተላለፉ::  

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች- እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

ለዘመናት ተቀብሮ የኖረው የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከተጫነው ተራራ- ከተደበቀበት ስውር ስፍራ እና በክፋት ከተተወበት ምሽግ ጎራ ይወጣ ዘንድ በአማናዊ ደመራ- ሰማያዊ ምልክት የታየበትን ቀን ለምናከብርበት ለዚህ በዓል ለመላ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለማስተላለፍ በመቻሌ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ስገልጽ ከተለየ አክብሮት እና ፍቅር ጋር ነው፡፡

ይህ ታላቅ እና ግሩም በአል በአልነቱ የክርስትያን ወገኖቻችን ቢሆንም ቅሉ ክብሩ እና ሀብትነቱ ግን የመላ ኢትዮጵያውያን ጸጋ ነው፡፡ በአለ መስቀል ከሀይማኖታዊ አስተምህሮቱ እና ከመንፈሳዊ እውነትነቱም ባሻገር የሚያስተምረን እና በውል እንድናስተውል የሚያስገድደን ሌላም ቁም ነገር ነገር አለው፡፡

እውነት የቱንም ያህል ዘመን፣ በምንም ያህል ውሸትና ቅጥፈት- ተንኮልና ሤራ፣ በየትኛውም ስልጣን እና ክፋት ብትሸፈንም በዘላቂነት ልትቀበር እንደማትችል አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ለጥቂት ጊዜ ፀሐይን እንደሚሸፍን ደመና እውነትን ለተወሰነ ጊዜ መከለል፣ ውሸትንም እውነት ማስመሰል ይቻል ይሆናል፡፡ በመጨረሻ ግን እውነት እንደምታሸንፍና ከተቀበረችበትም ወጥታ ቀባሪዎቿን እንደምታሳፍር ለማስረዳት የክርስቶስ መስቀል ታሪክ ግሩም ማስረገጫ ነው፡፡
ይህንን የከበራ ሥርዓት የሠሩልን ቀደምት አበውና እመውም እምር በሆነው የበአል ስርአታችን የመስቀሉን አስተርእዮ ሁለንተናዊ መልክ በቀጥታ የተረኩልን እና በጥበብም ያቆዩልን ቢሆንም በተራዛሚው ግን የማይታወቅ የተሰወረ፤ የማይገለጥ የተከደነ ነገር ለዘለአለም ሊኖር ያለመቻሉን መንፈሳዊ እና ሰዋዊ እውነት በድንቅ የበአል ክዋኔ ሂደት አቆይተውልናል፡፡

በዚህ ፍጹም አስገራሚ የከበራ ስርአት ውስጥም ለእውነት ብቻ እንድንቆም፡፡ ለጊዜያዊ ጥቅም ስንል እውነትን እንዳንቀብር፤ ሥልጣን አለን- ብንናገር እንሰማለን- ጊዜው የኛ ነው- ወዘተ በሚል ቀባሪ እና አደናጋሪ አተያይ እውነትን ብንቀብራት እንኳን እውነት ግን ያው እውነት ናትና ጊዜዋን ጠብቃ እንደምትወጣ ብቻ ሳይሆን በተለየ ክብር እና በድንቅ የመገለጥ ሚስጥር እንደምትነሳ እንድናስብ የሚያደርገንን ይሄንን ታሪክ በመሳጭ የከበራ ጥበብ አደረጅተው እዚህ አድርሰውልናል፡፡
ዛሬ ከምንም ነገር በላይ ለእውነት የምንቆምበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ በዙሪያችን ብዙ የተሳሳቱ መረጃዎች፣ ስም ማጥፋቶች፣ የሐሰት ወሬዎች፣ አሳሳች አሉባልታዎች እና በስሜት የሚነዱ ማስመሰሎች በገፍ አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ጊዜያዊ ግርግሮች ለጊዜያዊ መሸንገል እንጂ ለዘላቂ ድል መሰረት ሊሆኑ እንደማይችሉ የመስቀሉ ታሪክ ሁነኛ ምሳሌ ነው፡፡

ምንም ያህል ቢያብረቀርቁ በፍጹም ወርቅ እንዳልሆኑ መገንዘብ እና እውነተኛው ወርቅ ግን ጊዜውን ጠብቆ እንደሚወጣ ከመስቀሉ ታሪክ እንማር ዘንድ ይገባናል፡፡ እኛ ከጸናን፣ ካልተከፋፈልን፣ መድረሻችንን ካወቅን፣ ከበደል ሳይሆን ከፍትህ ካበርን እና ለሐሰተኞች ጆሮ ልቦናችንን ከነፈግን እውነት ብትቀበር እንኳን እንደ ታላቁ መስቀል ሁሉ ቢዘገይም ነጻ እናወጣታለን፤ነጻ ማውጣትም ብቻ ሳይሆን ሰማየ ሰማያት ደርሶ የመገኛ አቅጣጫ ብስራት ይዞ የተመለሰ ጭስ እንዳስገኘው ደመራ በአለም ፊት እናበራታለን- እናደምቃታለን፡፡

ይህ በዓል የደመራ በዓል ነው፡፡ የመደመር በዓል ነው ልንለውም እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ እንጨት ተደምሮ ችቦ ይሠራል፡፡ እያንዳንዱ እንጨት ባንድ ሆኖ በታላቁ ደመራ ህልው መሆን ውስጥ የራሱን ድርሻ ይወጣል፡፡
እየተጨፈለቀ ሳይሆን ህብር በራሱ ብርሀን እየደመቀ፡፡ እየተዋጠ ሳይሆን የራሱን ብርሀን እየሰጠ፤ እየተጠፋፋ ሳይሆን አንዱ በአንዱ ውስጥ እየሰፋ፡፡ እየተደመረ- እየተጨመረ ታላቁን ደመራ በክብር ይደምራል፡፡
ደመራ ደመራ እንዲሆን አያንዳንዱ እንጨት- እያንዳንዱ ችቦ አንድ ላይ ሆኖ ለአንድ ዓላማ በጥበብ፣ በውበት እና በአንድነት መቆም አለበት፡፡ አንድ ሆኖ ተደምሮ እንዲቆምም አንዱ ከሌላው መያያዙ ግዴታ እንጂ ሲሻ ብቻ የሚሆን ውዴታ አይደለም፤ መያያዝ፣ ህብር መፍጠር አብሮ መቆም እና አብሮ ማብራት ለደመራ ባህሪው ሳይሆን ተፈጥሮው ነው፤ እኛም እንዲያ ነን- ደመራነት ነው የሚያምርብን- መደመራችን ነው የሚያበረታ የሚያቆመን፤ የሚያበራን፣ የሚያደምቀን እና የሚያሞቀን፡፡

የሺ ፍልጥ ማሠሪያው ልጥ እንደሚባለው እንጨቶቹ በልጥ እየተያያዙ አንድ ችቦ ሆነው ጸንተው ይቆማሉ፡፡ ይህ ማያያዣ ልጥ ሕጋችን፣ ሥርዓታችን፣ እሴቶቻችን፣ ለውጥ ፈላጊነታችን፣ መፈቃቀዳችንና መተባበራችን ናቸው፡፡
‹ለየብቻ እንወድቃለን፣ በጋራ እንቆማለን› ብለን ተደምረን አብረን መቆም አለብን፡፡ ችቦዎቹ ብቻቸውን ደመራን አይመሠርቱም፡፡ አንድ ላይ ሆነው በአንድ ዋልታ ዙሪያ መቆም አለባቸው፡፡ ይህ ዋልታ ኢትዮጵያዊነታችን ነው፡፡ ሁላችንም የምንቆምበትና የምንቆምለት ሀገራዊ እሴትና ማንነት፣ ሀገራዊ አንድነትና ሀገራዊ መንግሥት አለን፡፡ ያንን ለመፍጠር ነው ሁላችንም አንድ ላይ ተደምረን የምንቆመው፡፡

ሀገራችን ደመራ ናት፡፡ ሁላችንም አንድ ላይ ተደምረን የምንቆምላትና የምንቆምባት፡፡ ለአንድ ሀገራዊ ዓላማ የምንሰለፍባት፡፡ በየሠፈራችሁና በየአካባቢያችሁ ደመራውን ስትመለከቱ ሀገራችሁን አስቡ፡፡ ራሳችሁንም ከችቦዎች ውስጥ ፈልጉ፡፡ ችቦው እንዲቆም፣ ደመራውም እንዲጸና እኔ ምን አድርጌያለሁ ብላችሁም አስቡ፡፡ለአፍታም ራሳችሁን ጠይቁ፡፡

በባሕላችን ከመስቀል ወዲያ ክረምት፣ ረሐብና ችጋር የለም ይባላል፡፡ ክረምት የሚያመጣው ፈተና ከደመራ በኋላ ያልፋል ተብሎ ይታመናል፡፡ እኛ መከራን፣ ችጋርን፣ ጦርነትንና ግጭትን በበቂ ሁኔታ ቀምሰናቸዋል፡፡
አይናፍቁንም፤ አንመኛቸውም፡፡ አሁን እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ደመራው ሁሉ አንድ ሆነን ተደምረናልና ከዚህ በኋላ እነዚያ የእንባ ሰበቦቻችን አይቀጥሉም፡፡ እንዲቀጥሉም አንፈቅድም፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆነው ሊፍጨረጨሩ ይችላሉ፡፡ ይህም ከመስቀል በኋላ እንደሚመጣ ዝናብ ነው፡፡ ዝናቡም እያለቀ፤ ችግሩም እየነጠፈ ይሄዳል እንጂ እድሜ አይኖራቸውም፡፡ ይህ እውን እንዲሆን ግን ደመራውን በምንለኩሰበት ቅጽበት እንደ ሀገር እንደመር ዘንድ ሁላችንም የበኩላችንን ለማድረግ ቃልኪዳናችን እናጸና ዘንድ በፍጹም ትህትና እና አክብሮት ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

መስቀል የአዲሱ እህል እሸት የሚበላበት ጊዜ ነው፡፡ ይህም ለአርሶ አደሩ ተሥፋ ነው፡፡ እናም አርሶ አደሩ ይህንን ተሥፋውን ማማ ሠርቶ ከአውሬ ይጠብቀዋል፡፡ እኛም የዴሞክራሲን፣ የፍቅርን፣ ይቅርታን፣ የመደመርንና የለውጥን ተሥፋ እየቀመስን ነውና ይህንን ተሥፋችንን የአንድነት ማማ ሠርተን ከአውሬዎች- ከአጥፊዎች ልንጠብቅ ይገባናል፡፡

እንደ ደመራው ተደምረን እንድናበራና ጨለማውን እንድንገፈው ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ፡፡ መልካም በአል!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!
አመሰግናለሁ፡፡