ኦነግ ቀውስ መፍጠሩን ቀጥሏል፣ አቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ ትጥቅ አይፈታም ብለዋል

Dawd Ibsa, Oromo Liberation Front (OLF) leader.

(ECADF) — የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ:-

“ኦነግ ወደ ሀገር ቤት የገባው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ትጥቁን ፈትቶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረት ቢስ ወሬ ነው ። እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት ስምምነት የለም ። የታጠቀው አካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክንያት አይኖርም።”
ትጥቅ ፈቺም አስፈችም የለም ሲሉ አክለዋል።

ሁኔታው በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ የመነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኗል።

ኦነግ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮና ካዛም ቀደም ብሎ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የታጠቁና “በኦነግ ስም” ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ቡድንኖች እየፈጸሙ ባሉት ጥቃቶች ሀገሪቱን ከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ ከተዋት ይገኛሉ።

  • በሱማሌ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የታጠቁ የኦነግ ወታደሮች ከሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በየጊዜው በሚፈጥሯቸው ግጭቶች ከ1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
  • በደቡብ ክልል (በጌዲዮ ዞን) የኦነግ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚወስዷቸው ጥቃቶች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
  • የኦነግ ታጣቂዎች ሰሞኑን አራት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ባለስልጣናት ከኦሮሚያ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገው ሲመለሱ ተኩስ ከፍተው ገድለዋቸዋል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ዜጎች ሲገደሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።
  • በመስቀል አደባባይ ጠ/ሚ አብይ አህመድን ለመግደል የተደረገውን ሙከራም “በኦነግ ስም” የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንዳደራጁት የመንግስት አቃቢ-ህግ ገልጿል።
  • ኦነግና ከኦነግ ጋር የተባበሩ ሌሎች በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አንድ ላይ በመሆን በነጻ ሚድያነት የሚንቀሳቀሰውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮን (ኢሳት) በኦሮሞ ህዝብ ጠላትነት ፈርጀዋል። የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ለዘመናት በኢትዮጵያዊነት ተፋቅረው እና ተዋደው የሚኖሩባትን የሀገሪቱን መዲና አዲስ አባባ “የኦሮሞ” ነች ሲሉ መግለጫ አውጥተዋል።
  • የኦነግ መሪዎች የኢትዮጵያን ህዝብ ላለፉት 27 አመታት አፍነው ሲገዙ ከነብሩት ህወሃች ጋር የመሰረቱት ግንኙነት በስልጣን ላይ ላሉት ጠ/ሚ አብህይ አህመድ እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያሰጋ ሆኗል።

የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ኦነግን በሃይል ትጥቅ ለማስፈታት፣ የሚደፍሩ አልሆኑም ይልቁንም ኦነግ ሰራዊቱን ትጥቅ እንዲያስፈታና ወታደሮቹንም ወደ ካምፕ እንዲያስገባ በመማጸን ላይ ናቸው።

ኦነግ በሀገሪቱ ኹከት መፍጠሩን ቀጥሏል። አዲሱ የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደርም ኦነግ የሚፈጥራቸውን ቀውሶች በቁጥጥር ስር ማዋል ባለመቻሉ ደካማ ሆኖ እንዲታይ ሆኗል።

የዶ/ር አብይን አስተዳደር በግልጽ የሚቃወሙት የህወሃት ሰዎች በጎን ኦነግን እያበረታቱ እና እየደገፉ መልሰው ደግሞ የዶ/ር አብይን አስተዳደር “ሁኔታዎችን መቆጣጠር አልቻሉም” በማለት ይከሳሉ። አልፈው ተርፈውም በድህረገጾቻቸው አማካኝነት ዶ/ር አብይ አህመድ በሀገሪቱ ሰላም ማስፈን ባለመቻላቸው ከስልጣን እንዲለቁ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ።

ዶ/ር አብይ አህመድ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ አላቸው። ይሁንና የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ ካልቻሉ ህዝብ የሰጣቸው ድጋፍ ቀስበቀስ ሊቀንስ እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s