አፓርታይዳዊ ከተማ ዳሬዳዋ – #ግርማ _ካሳ

አርባ ፣ አርባ ሃያ የሚባል አሰራር አለ፣ ድሬዳዋ። ድሬዳዋ ከተማ የኦሮሞና የሶማሌ ክልል የይገባኛል ጥያቄ ስላቀረቡ የፌዴራል ቻርተር ከተማ ናት።፡ሆኖም ግን በከተማዋ ከፍተኛ የዘር መድልዎ የሚታይባት ከተማ ናት። በተለይም ኦሮሞና አማር ያልሆኑ ዜጎች እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ዜጋ ነው የሚቆጠሩት። ይሄ ግፍ ነው. ይሄ ዘርኝነት ነው። ይሄ ጭቆና ነው።ይሄ አፓርታይድ ነው።

ግሩም ተበጀ ከጥቂት ወራት በፊት የጻፈውን እንደሚከተለው አቅርቤላቹሃለሁ

————————————–

Dire Dawa! “Stop 40 – 40 – 20” !!

(በግሩም ተበጄ)

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ የድሬን ጉድ ተመልከት…
ድሬን ለሚወድ ሁሉ፣ 
ድሬዳዋ ላይ የተጫነው “40 – 40 – 20” የተሰኘ አስቀያሚ ኢኮኖሚያዊ አፓርታይድ ይቁም !!!

… 
ለመሆኑ ድሬዳዋ ላይ “40 – 40 – 20” የተሰኘ የአፓርታይድ አይነት ሕግ እንዳለ ታወቁ ይሆን…
ማንም ድሬን በዝና እንኳ የሚያውቅ ሰው ይህን ሲሰማ መደንገጡ አይቀርም፡፡ ይህ የግፍ ሐሳብ በተለይ በዚህ ዘመን በአፋጣኝ እንዲነሳ እጠይቃለሁ፡፡ የዚህ “40 – 40 – 20” የሚሉት ክፋትን ትርጉም ልንገራችሁ፡፡
በመላው ኢትዮጵያ የተጫነው የከረፋ የዘር ፖለቲካ ድሬም ደርሶ ከድሬዳዋ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት…
40 ፐርሰንቱ የኦሮሞ፣
40 ፐርሰንቱ የሶማሊ ይልህና
20 ፐርሰንቱ የሌላ ብሄር ይላል፡፡

እስቲ አሁን ይሄን ግፍ ምን ትሉታላችሁ !!!
ይህ የግፍ አሰራር በአፋጣኝ እንዲቆም እጠይቃለሁ፡፡ የተለያዩ ብሄሮች ህብረቀለም ውበት በሆነችው ድሬ ላይ የተጫነው ይህ አስቀያሚ ስርዓት እንዲነሳ ድሬን የሚወድ ሁሉ ድምፁን ያሰማ!”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s