የአስፈፃሚ አካላት ተፅዕኖ ጉዳያችንን ያዛባብናል ብለው ጠበቆች እንዳይሰጉ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ አሳሰቡ

የአስፈፃሚ አካል ተፅዕኖ ጉዳያችንን ያዛባብናል ብለው ጠበቆች እንዳይሰጉ የተናገሩት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ናቸው፡፡

በፍርድ ቤት አካባቢ እንደገና ማዋቀር አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ፍርድ ቤቶች የአስፈፃሚውና የሕግ አውጭው ተፅዕኖ የማይደፍቃቸው ሆነው እንዲደራጅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ለአዲስ ዘመን እለታዊ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሀላፊነቱን ሲቀበሉ ለመሪዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ “የፍርድ ቤት ነፃነትን ለማስከበር ሙሉ ነፃነት ይኖራል ወይ ?” የሚለውን እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

“የሃገሪቱ መሪዎች” ይላሉ ወይዘሮ መዓዛ “የሃገሪቱ መሪዎች በዚህ ረገድ ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው ተረድቻለሁ” ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትነቱን ስራ ከጀመሩ ወዲህ ዳኞችን ሲያነጋግሩ፣ “ስራችንን በነፃነት መስራት አልቻልንም” የሚል አስተያየት እንደሰሙ ጠቅሰዋል፡፡

ዳኞቹ ከፖሊስ፣ ከዐቃቤ ሕግ እና ከተለያዩ ቦታ ጫና እንደነበረባቸው መናገራቸውን፤ ወ/ሮ መዓዛ ግን ከዚህ በኋላ የዳኝነትን ነፃነት ለማረጋገጥ ዳኞችም ራሳቸው ለራሳቸው መቆም አለባቸው ይላሉ፡፡

“ሲታዘዙ አቤት ከማለት ወጥተው የዳኝነት ነፃነትን ለማስከበር እያንዳንዱ ዳኛም መቆም መቻል አለበት” ብለዋል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s