የአስፈፃሚ አካላት ተፅዕኖ ጉዳያችንን ያዛባብናል ብለው ጠበቆች እንዳይሰጉ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ አሳሰቡ

የአስፈፃሚ አካል ተፅዕኖ ጉዳያችንን ያዛባብናል ብለው ጠበቆች እንዳይሰጉ የተናገሩት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ናቸው፡፡

በፍርድ ቤት አካባቢ እንደገና ማዋቀር አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ፍርድ ቤቶች የአስፈፃሚውና የሕግ አውጭው ተፅዕኖ የማይደፍቃቸው ሆነው እንዲደራጅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ለአዲስ ዘመን እለታዊ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሀላፊነቱን ሲቀበሉ ለመሪዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ “የፍርድ ቤት ነፃነትን ለማስከበር ሙሉ ነፃነት ይኖራል ወይ ?” የሚለውን እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

“የሃገሪቱ መሪዎች” ይላሉ ወይዘሮ መዓዛ “የሃገሪቱ መሪዎች በዚህ ረገድ ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው ተረድቻለሁ” ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትነቱን ስራ ከጀመሩ ወዲህ ዳኞችን ሲያነጋግሩ፣ “ስራችንን በነፃነት መስራት አልቻልንም” የሚል አስተያየት እንደሰሙ ጠቅሰዋል፡፡

ዳኞቹ ከፖሊስ፣ ከዐቃቤ ሕግ እና ከተለያዩ ቦታ ጫና እንደነበረባቸው መናገራቸውን፤ ወ/ሮ መዓዛ ግን ከዚህ በኋላ የዳኝነትን ነፃነት ለማረጋገጥ ዳኞችም ራሳቸው ለራሳቸው መቆም አለባቸው ይላሉ፡፡

“ሲታዘዙ አቤት ከማለት ወጥተው የዳኝነት ነፃነትን ለማስከበር እያንዳንዱ ዳኛም መቆም መቻል አለበት” ብለዋል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ፡፡

ሰበር ዜና.. ዳኛ ብርቱዋ ብርቱካን ሚዴቅሳ እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ ዳንኤል በቀለ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ ከሕወሓት አገዛዝ ነፃ ወጥቷል

የቀድሞው የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አማካሪ፣ የሂውማን ራይስት ዋች የአፍሪካ ዳይሬክተርና ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ የህሊና እስረኛ የነበረው አቶ ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹሟል።

በዚህ ጉዳይ ዶ/ር አብይ መመስገን አለባቸው፨ በመጀመሪያ “Inhuman” የሆነውን የሰብዐዊ መብት ኮሚሽነር ከማይገባው ቦታ በማንሳታቸው ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ በቦታው ላይ በጣም ተገቢውን ሰው መሾማቸው በጣም አስደሳች ነው፨

ዛሬ ሃገሬ በጣም ቀንቷታል! የሰብዐዊ መብት የመብቶች ሁሉ ቁንጮ የሚመስለኝ እኔ ይህን ዜና ስሰማ በጣም ነው ደስስስ ያለኝ በእውነት ! ደህና ቀን የመምጣት ፣ጎህ የመቅደድ ምልክቶች እያየን ነው፨ የሰው ልጅ ክቡርነትን ማወቅ የእድገት መጀመሪያ ፣የሰውነት ዋና መለኪያ ነው፨ መጨረሻችንን ያሳምርልን

መስከረም አበራ

ከብሔራዊ ዕርቀና ሰላም ኮሚሽን ምን እንጠብቅ? (ያሬድ ሃይለማሪያም)

በዚህ ሳምንት የሚንስትሮች ምክር ቤት እውነት እና ፍትሕ አፈላላጊ የብሔራዊ ዕርቀና ሰላም ኮሚሽን ለማቋቋም ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ሰምተናል። ይህ እጅግ የሚደገፍ ትልቅ እርምጃ ነው።

እጅግ የከፋ የመብት ጥሰት በተፈጸመበት፣ ብዙ ዜጎች በአገር እና በመንግስት ላይ እምነት ባጡበት፣ ጥቂት ግፈኞች የአገርና የሕዝብ ሃብት በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ብዙ ሚሊዮኖችን የመኖር ዋስትና ባሳጡበት፣ በፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት እና በዘር ፍረጃ ዜጎች ቁርሾ በተቃቡበት አገር እርቅ እና ሰላምን ለያመጣ የሚችል ብሔራዊ ኮሚሽን እንደሚያስፈልግ ብዙዎች ሲወተውቱ ከርመዋል። ጥያቄው ምላሽ ሊያገኝ መሆኑን መስማት ያስደስታል።

ይህ ኮሚሽን ምን አይነት ቅርጽ ነው መያዝ ያለበት፣ ምን ምን ተግባራትን ነው ሊያከናውን የሚችለው ወይም የሚጠበቅበት፣ በምን መልኩ ነው የሚዋቀረው እና ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ ይችላል የሚሉትን ጥያቄዎች ኮሚሽኑን የሚያቋቁመው ዝርዝር አዋጅ ሲወጣ የሚታይ ይሆናል። ሕዝብ ከኮሚሽኑ ምን ይጠብቅ የሚለውን ሃሳብ ግን ሌሎች ተመሳሳይ ችግር ውስጥ የነበሩ አገሮች ከብሔራዊ ዕርቀና ሰላም ኮሚሽን ያገኙትን ትርፍ እና ጥቅም በማስላት ከዚህ በታች ያሉትን ጉዳዩች የሚሸፍን ኮሚሽን ከሆነ አትራፊዎች ነን ብዮ አስባለሁ።

– ባለፉት አርባ አመታት በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠሩትን የፖለቲካ መቋሰሎች፣ የእርስ በርስ እልቂቶች፣ የብሔር ግጭቶችን ያስከተሉ ጉዳዮችን በዝርዝር በማጥናት፣ የደረሰውን የጉዳት መጠን በዝርዝር እና በማስረጃ አስደግፎ በጥራዝ መልክ በማዘጋጀት ይህን የግጭት ታሪካ ምዕራፍ ሊዘጋ የሚቻልበትን መንገድ ማመላከት፤

– ከዚህ ጥናት እና የምርምር ውጤት በመነሳት ተመሳሳይ ግጭቶች እና እልቂቶች እንዳይከሰቱ ሊከላከል የሚችል እና ሁሉም አካል ሊስማማበት የሚችል አንድ የሰላም እና የእርቅ ስምምነት ሰነድ ማውጣት፣

– ባለፉት አሥርት አመታት የተፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተመሳሳይ ሁኔታ በማስረጃ አስደግፎ እና ጠርዞ ለታሪክ እና ለትምህርት በሚውል መልኩ ማስቀመጥ። የመብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትን በድርጅት፣ በስም እና በሥራ ኃላፊነት ደረጃ ጠቅሱ በዝርዝር በሰንዱ ውስጥ ማስቀመጥ፣

– የመብት ጥሰት የፈጸሙ ወይም በማናቸውም ደረጃ በድርጊት ይሁን በሃሳብ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች በስም ተዘርዝረው ተጠቅሰው ኮሚሽኑ በሚያዘጋጀው አንድ ገጽ የይቅርታ መጠየቂያ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርሙ፤ ሕዝብን እና የበደሉትን ሰው በጥቅሉ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ፤

– የመብት ጥሰት ሰለባ የሆኑ ሰዎች፤ በተለይም በእስር የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመባቸው ሰዎች በሥነ አዕምሮም ሆነ በአካል ሊያገግሙ የሚችሉበት የስቃይ ሰለባዎች ማገገሚያ ተቋም እንዲቋቋም በማድረግ ተበዳዮቹ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፤

– የመብት ጥሰት ከተፈጸመባቸው ግለሰቦች መካከል የተወሰኑትን በማበረታታት ለአስተማሪነት ይረዳ ዘንድ የደረሰባቸውን የደል አይነት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ እንዲያካፍሉ ማድረግ እና የተበዳዮቹን የጉዳት መጠን የሚያሳዩ አጫጭር ታሪኮችን በሰነዱ ውስጥ ማካተት፣

– በሕዝብ መካከል የተፈጠሩ መቃቃሮች እና በፖለቲካ ኃይሎች ፍትጊያ ምክንያት የተፈጠሩ ቁስሎች እንዲያገግሙና ሙሉ በሙሉ እንዲሽሩ ሊረዳ የሚችሉ የውይይት፣ የሥልጠና እና የምክክር መድረኮችን እና የተለያዩ አውዶችን መፍጠር ወይም ማነቻቸት፤

– የፖለቲካ ፓርቲዎች በታሪክ ሂደት በመካከላቸው የተፈጠሩ መቃቃሮችን አክመው ወደ ሰለጠነ የፖለቲካ ፉክክር እንዲገቡ ለማድረግ የሚያስችል የውይይት እና የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት፤ እንዲሁም በጋራ የሚፈርሙት አንድ የእርቅ እና የሰላም ቃል-ኪዳን ሰነድ አዘጋጅቶ እንዲፈርሙ ማድረግ፤

– በቀጣል በሕዝም መካከልም ሆነ በፖለቲካ ኃይሎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች እና ቅራኔዎች ሊፈቱ የሚችሉበት፤ የአገሪቱን ባህላዊ እና ሌሎች እሴቶች ታሳቢ ያደረገ የግጭት አፈታት ስልት መንደፍ፤

– ሕዝብን ለግጭት ሲዳርጉ የቆዩ የመንግስት ፖሊሲዎችን፣ ሕጎችን (ሕገ-መንግስቱን ጨምሮ)፣ የአፈጻጸም ስልቶችን፣ የመንግስትን አወቃቀር እና የሚከተለውን የፖለቲካ አስተሳሰብ መስመር፣ በፌደራል እና በክልል መንግስታት እንዲሁም በክልሎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚፈትሽ፤ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት እና እርቅን ለማውረድ የሚረዱ አማራጭ ሃሳብችን የሚያቀርብ፤

– ዕርቅ እና ሰላም መሰረታቸው እውነት እና ፍትሕ መሆኑን አጽነኦት በመስጠት በአገሪቱ ውስጥ በሕዝብ ላይ የተፈጸሙ በደሎችን፣ ዚርፊያቆችን እና የመብት ጥሰት ወንጀሎች ዘርዝሮ እውነቱን የሚያሳውቅ እና ፍትሕ የሚገኝበትን መንገድ የሚጠቁም ኮሚሽን መሆን ይጠበቅበታል።

– ከላይ የተጠቀሱትን ሥራዎቻቸውን ለማከናወን የሚያስችል በቂ ነጻነት እና የሕግ ጥበቃ የሚደረግላቸው፤ እንዲሁም ሥራቸውን ለማከናውን የሚያስችል ተመጣጣኝ የሆነ በሕግ ተዘርዝሮ የተደነገገ ሥልጣን ያለው እና ተጠሪነቱም በአገሪቱ ከፍተኛ ሥልጣን ላለው ለፓርላማው ብቻ የሆነ ጠንካራ ተቋም መሆን አለበት።

እንዲህ ያለውን ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ኮሚሽኑ፤

– ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ሊወክሉ የሚችሉ፣

– በትለያዩ የሙያ ዘርፎች፤ በተለይም በሕግ ሙያ በቂ እውቀት እና ልምድ ያላቸው፣

– በማህበረሰቡ ውስጥ በበጎ ምግባራቸው የሚታወቁ እና ሕዝብ አመኔታ የሚጥልባቸው፤
– በመብት ጥሰትም ሆነ በመህበረሰቡ ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች ውስጥ ቀጥተኛም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ያልነበራቸው እና በየትኛውም አግላይ የሆነ አስተሳሰብ በሚያራምድ ቡድን ውስጥ ተሳታፊ ያልነበሩ፤

ቢሆኑ ሥራቸው የተቃና ይሆናል። በቂ የሕዝብ ድጋፍ እና አመኔታም ያገኛሉ። ሥራቸውም የታለመለትን ፍሬ ያፈራል። የብዙ አገሮች ልምድ ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ከሞላ ጎደል ያሟላ ሲሆን ጥሩ ውጤትም አስገኝቷል።

መንግስት የጀመረው ቀና እና በጎ መንገድ የሰመረ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጸኦ ሊያደጉ ይገባል።

በቸር እንሰንብት!

‹‹ ከአገር በቀል ወደ አገር ነቀል የሪል ስቴት ዲቭሎፕርነት!!! የመሬት ቅርምት ሚሊየነሮች!!!›› ‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር›› ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

በህወሓት/ ኢህአዴግ ምላሳዊው መንግሥት፣ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማትና የመሬት ቅርምት ሚሊየነሮች አፍርታለች፡፡ በኢትዮጵያ የፍርድ ሥርዓት የሚዘወረውና የሚሽከረከረው በከፍተኛ ደረጃ ባሉ የፖለቲካ ባለሥልጣኖች ነው፡፡ የሃገሪቱ ህገ መንግሥት ነፃ የፍርድ ሥርዓት መኖሩን ለይስሙላ ቢያረጋግጥም ሙስናና ሌብነት የተንሰራፋበት መንግስታዊ አገዛዝ እንደሆነ ህዝቡና የንግዱ ህብረተሰብ የአገዛዙ ሥርዓት አወቃቀር በሙስና ሠንሰለት የተሳሰረ በጉቦና  ኪራይ ሠብሳቢነት ሥርዓቱ ግንኙነት ድርና ማግ ግንኙነት ድርና ማግ ናቸው፡፡ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሙስናና ሌብነት የሚገለጽባቸው በሃገሪቱ ባለው {1} የፍርድ ሥርዓት፣{2} ፖሊስ፣ {3} የህዝብ አገልግሎቶች፣ {4} የመሬት አስተዳደር፣ {5} የታክስ አስተዳደር፣ {6} የካስተም/የጉምሩክ አስተዳደር፣ {7} የፐብሊክ ፕሮክሪመንት፣ግልፅ ጨረታ {8} የተፈጥሮ ኃብቶች፣ {9} የህግ አውጪ፣ እንዲሁም {10} ሲቪል ሶሳይቲ/ማህበራዊ ድርጁቶች ውስጥ ነው፡፡ የወያኔ የመሬት አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ስም የተደረገውን የመሬት ቅርምት የሙስናና ሌብነት ሥራን እንቃኛለን፡፡

የመሬት አስተዳደር (Land Administration) በኢትዮጵያ  የመሬት አስተዳደር ስራ በከፍተኛ የሙስና ይፈፀምበታል፡፡ የንግዱ ህብረተሰብ የግል ንብረትና ኃብት መብት በህግ የተጠበቀ አይደለም፡፡ ግማሽ የሚሆኑት የንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች የግንባታ ፍቃድ በሚጠይቁበት ጊዜ ገፀ በረከት ስጦታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡  አንድ ሶስተኛ የንግዱ ህብረተሰብ ለመሬት አስተዳደር ጠራተኞች ጉቦ  ይሰጣሉ፡፡ በመሬት አስተዳደር የሥራ ዘረፍ ሙስናና የመሬት ቅርምት የተለመደ ነው፡፡ በመሬት አስተዳደር ዘርፍ በጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ላይ የተገነባ ስላይደለ ግልፅነት ፣ ትክክለኛ ፖሊሲዎች፣ እና የማስፈፀም አቅምና ኃብት የላቸውም፡፡ የመሬት አስተዳደር ሠራተኞች በሃሰተኛ መረጃ/ ፎርጀሪ ህገወጥ የመሬት ባለቤትነት ፍቃድ  ለ15000 ሰዎች ሰጥተዋል፡፡  በዚህ ድርጊት ጥቂት ሠራተኞች ብቻ ተጠያቂ ሆነዋል፡፡   የግሉ ዘርፍ የመሬት ባለቤትነት መብት የላቸውም፣ ሁሉም መሬት የመንግስት ኃብት ነው፣ መንግስት መሬት በሊዝ ለ99 አመታት ይከራያል፡፡ መንግሥት የ3000 ኢንቨስተሮችን መሬት አላለማችሁምና አልሰራችሁበትም በማለት ነጥቆል፡፡ There is a high risk of corruption  in Ethiopia’s land administration. Businesses report that property rights are insufficiently protected in Ethiopia (GCR 2016-2017). Half of all companies expect to give gifts when applying for a construction permit (ES 2015). A third of Ethiopians report having paid a bribe to a land administration official (GCB 2013). Petty corruption and land-grabbing is common in the land administration sector (TI 2014). This is caused by the absence of strong institutions, transparency, clear policies, and a lack of resources (TI 2014). Officials have also engaged in forgery practices, thereby assigning themselves an estimated 15,000 titles illegally; only a few have been held accountable (TI 2014). There is no right to private ownership of land; all land is owned by the state and leased out for up to 99 years (ICS 2017). Expropriation may only happen when required by the public interest and with payment of adequate compensation (ICS 2017). The government revoked the leases of 3000 investors for “failing to develop the land” because they had not started production within the agreed-upon time frames (BTI 2016). Conflicts between international investors and local communities over land rights have occurred in the past; the government has been accused of performing land-grabs in favor of international investors (BTI 2016). Investors are advised to perform thorough due diligence on the attitude of local communities before making an investment (ICS 2017). Registering property in Ethiopia is slightly faster than the regional average, while the number of steps required is in line with regional averages (DB 2017).

የፐብሊክ ፕሮክሪመንት/ጨረታ፣ (Public Procurement) በኢትዮጵያ የፐብሊክ ፕሮክሪመንት፣በመንግሥታዊ ዘርፍ አሰራር ግልፅና ነፃ ጨረታ እንደሌለ ይህም አሰራር ለሙስናና ሌብነት ሥርዓቱን እንደዘፈቀው ይታወቃል፡፡ ከአምስት አንድ የንግድ ካንፓኒዎች የመንግስት የኮንትራት ሥራ ያለጨረታ ለማግኘት ጉቦ ይሰጣሉ፡፡ የንግድ ፍቃድና የኮንትራት ስራ ለማግኘት ጉቦ መስጠት የተለመደ ነው፡፡ መንግሥታዊ የጨረታ አስተዳደር ስለሌለ በሙስናና ሌብነት ጨረታ በማጭበርበር ይከናወናል፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፍ ይቆጣጠራል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ከባንክ ብድር የማግኘት ዕድል፣ ለኢፈርት፣ ሜቴክ፣ሜድሮክ የመሳሰሉ ድርጅቶች የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ የሚያበድረው ብድር አድሎ የተሞላበት ነው፡፡ ፋጣንና ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት የማግኘት እድል፣  የውጭ ምንዛሪ በቅድሚያ የማግኘት እድል፣ የመንግስት ጨረታን ያለውድድር የማግኘት እድል፣ የሃገር ውስጥና የውጭ ገበያ የማግኘት እድል፣ የመሬት ጥያቄ ለመንግስትና ለግሉ ዘርፍ ለተሰማሩ አድሎ መኖር፣ የመንግስት ግብር አለመክፈል፣ በብሔራዊ ባጀት ‹የመንግስት የልማት ድርጁቶች› አጠቃላይ ባጀት ይገለፃል እንጂ የተናጥል ባጀታቸው ለህዝብ ይፋ አለመደረግ፣ እንዲሁም የኦዲት ሪፖርት አለማድረግ ወዘተ  እነዚህ ድርጅቶችን በቦርድ የሚያስተዳድሩት የህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ሹማምንቶች፣ የፖለቲካ ካድሬዎችና የጦር ጀነራል መኮንኖች ሲሆኑ በትምህርትና በእውቀት ነፃ ውድድር የተያዘ ሥራ ባለመሆኑ ብዙዎቹ ለኪሳራ ይዳረጋሉ፡፡ ከግሉ ዘርፍ የበለጠ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ግልፅ የጨረታ ሥርዓት አለመኖሩ ምክንያት ሜቴክ የተዘፈቀበትን ወንጀል ልብ ይበሉ፡፡ ‹‹ሜቴክ ያለ ህጋዊ የጨረታ ሂደት የ37 ቢሊየን ብር የውጭ ሃገር ግዥ ፈፅሞል፡፡ አዲስ አበባ፣ ህዳር 3 ቀን 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)  ያለ ህጋዊ የጨረታ ሂደት  የ37 ቢሊየን ብር የውጭ ሃገር ግዥ መፈፀሙን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለጸ፡፡….የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከ2004 እስከ 2010 ዓ/ም ድረስ ባከናወናቸው ግዥዎችና ተዛማጅ ጉዳዬች ላይ ምርመራ በማድረግ … በንብረት ግዥና ፋይናንስ ጋር በተያያዙ የግዥ ሂደቶች ላይ ከፍ ያለ የህግ ጥሰት መፈፀሙን አስረድተዋል፡፡…. ከሃላፊዎች ጋር የስጋ ዝምድና ያላቸው ግለሰቦችም እንደ ደላላ በመሆንና ተቆሙን ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች ጋር በማገናኘት ግዝው እንዲፈፀም ማድረጋቸውን ጠቅስው በዚህም በቢሊየን የሚቆጠር የሃገር ሃብትና ንብረት መመዝበሩን አንስተዋል፡፡ የንብረት ግዥው ከአንድ ኩባንያ በድግግሞሽ እንደሚፈፀም … በዚህ ሂደት ግዥው ላይ እስከ 400 ፕርስንት የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ግዥው ይፈፀም ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈም ተቆሙ የሃገር ውስጥ ግዥን ሙሉ በሙሉ  ያለምንም ጨረታ ሂደት መፈፀሙንም አስረድተዋል፡፡››  Public Procurement/ There is a high risk of corruption in Ethiopia’s public procurement sector. One in five companies indicate expecting to give gifts in order to obtain government contracts (ES 2015). Likewise, irregular payments and bribes are common in the process of awarding public contracts and licenses (GCR 2015-2016). Companies complain of unlawful contract termination and non-transparent tender award processes, and report  favoritism towards vendors who provide concessional financing (ICS 2017). State-owned enterprises (SOEs) and companies owned by Ethiopia’s ruling party dominate major sectors of the economy (ICS 2017). SOEs have advantages over private companies, including easier access to credit and easier customs clearance (ICS 2017). Foreign investors complain of the lack of level playing field; there are indications that SOEs receive preference in government tenders (ICS 2017). While many tenders are publicly advertised, there are major instances of contracts being awarded without a tender (GI 2017). Metal & Engineering Corp, the biggest employer in the country, has frequently received contracts without a bidding process (GI 2017). Documents relating to procurement processes are difficult to obtain due to a burdensome bureaucracy and a lack of transparency (GI 2017). The FDRE Public Procurement & Property Administration Agency publishes a list of companies barred from future bidding due to past violations on its website (GI 2017).

የተፈጥሮ ኃብቶች Natural Resources፣  የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ያለዓለም አቀፍ ጫረታ ሳይወጣ ለጣሊያኑ ሳሊኒ የተሰጠ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡There is a high risk of corruption in Ethiopia’s natural resources sector. Financial records relating to natural resource exploitation are not publicly available (GI 2017). There have been concerns that the Grand Ethiopian Renaissance Dam was developed without competitive bidding and the quality of the environmental assessment was lacking (TI 2015). Ethiopia’s extractive industries, especially the mining sector, are a hotbed for corruption ; state-owned drilling companies benefit from political favoritism, whereas private companies face high market-entry barriers (World Bank, 2012). Following its application in 2014, Ethiopia is currently working towards implementing the EITI standard to improve accountability and transparency in the mining sector (EITI 2017). Ethiopia’s compliance with the standard will be measured starting in 2018 (EITI 2017).

በኢትዮጵያ የሪል ስቴት የቤቶች ልማት ልማት ፖሊሲ ሳይወጣ፣ የሪል ስቴት አልሚዎች እውቀትና ክህሎት ሳይጠና፣ የቤቶቹ ገንቢዎች ገንዘብ በዝግ አካውንት ባንክ ውስጥ ሳይቀመጥ በቀጥታ በሪል ስቴት ዲቨሎፐርስ አካውንት ውስጥ የቤት ፈላጊዎች ገንዘብ በመቀመጡ ብዙ ዜጎች ለዘረፋ ተዳርገዋል፡፡ በዚህም የህወሓት/ኢህአዴግ ሙስኛና ሌባ መንግሥት የዜጎቹን የወደፊት እድልና ተስፋ ቀጭቶል፡፡ የዜጎቹን ገንዘብ ቆጥቦ ቤት የመገንባት የወደፊት ተስፋ አጨልሞል፡፡ የቤቶችና የገንዘብ ቁጠባ ባንክን (ሞርጌጅ ባንክን) አፍርሰዋል፡፡ በሪል ስቴት የቤቶች ልማት ስም የብዙ ዜጎች መሬት ተነጥቆል፣ ተዘርፎል፣ ከፍተኛ የመሬት ቅርምት ተደርጎል፡፡ ዛሬ በከተማችን የምናያቸው ቢሊየነሮችና ሚሊየነሮች የሃብታቸው ምንች ከመሬት ቅርምት የተገኘ ለመሆኑ ጠንቆይ መቀለብ፣ ኮኮብ ቆጣሪ ማጠየቅ፣ መፀሃፍ ገላጪ ማስነበብ አይጠይቅም፡፡  በ2002ዓ/ም ድረስ የሪል እስቴት አልሚዎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የወሰዱት ቦታን በማየት የተፈጸመውን ወንጀል፣ መሬቱን የተዘረፈውን ዜጋ በማስረጃ ለማየት ይጠቅማል እንላለን፡፡ ወያኔ ግብረ አበሮቻቸው በተመቻቸላቸው የዘረፋ ሥርዓት የህዝብ ንብረትና ሃብት በጉልበት ነጥቀው ዜጎችን አደህይተዋል፣ ዛሬ አንድ ሜትር ካሬ መሬት እስከ 350 ሽህ ብር በጨረታ ይቸበቸባል፣ ዛሬ አንድ ቪላ ቤት ከ5 እስከ 10 ሚሊየን ብር ይሸጣል፡፡ የከተማው ነዋሪ በመሬቱ ላይ እንዳይኖር አራትና አምስት ፎቅ ካልሰራህ ልቀቅ እየተባለ ከመሬቱ ተገፋ፣ ተነጠቀ፣ ተዘረፈ፡፡ የእነዚህ ሪል ስቴት አልሚዎች የደም ገንዘብ ከዜጎች ላይ የተመዘበረ በመሆኑ በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ስም የተላለፈላቸው የ160 ግለሰቦችና ድርጅቶች ስም ዝርዝር (2002 የተደረገ ጥናት)

{1} የመሬት ቅርምት እስከ 57,679  ሽህ ካሬ ሜትር እስከ 1,336,296 ሚሊዩን የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት በሪል ስቴት ልማት ስም የተዘረፈውን ዜጋ ይታደጋል፡፡

 • አያት ኃ/የተ/የግ/ማ የቦታው ስፋት 1,336,296 ካ.ሜ ልዩ ልዩ ክፍለ ከተማዎች
 • ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ የቦታው ስፋት 262,868 ካ.ሜ ልዩ ልዩ ክፍለ ከተማዎች
 • ካራ ቆሬ ኃ/የተ/የግ/ማ ድምር የቦታው ስፋት 255,046 ካ.ሜ ልዩ ልዩ ክፍለ ከተማዎች
 • ጊፍት ትሬዲንግ ሪ/ኃ/የተ/የግ/ማ የቦታው ስፋት 162,997 ካ.ሜ የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • ሳትኮን ኮንስትራክሽን የቦታው ስፋት 104,100 ካ.ሜ የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • ተ/ብርሃን አምባዬ ሪል እስቴት የቦታው ስፋት 100,000 ካ.ሜ የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • ዮሴፍ ተገኝ ድምር የቦታው ስፋት 71,996 ካ.ሜ የካ 20/21 የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • Getty / ኖርዝ ጌት /LTD/ የቦታው ስፋት 68,700 ካ.ሜ ቦሌ 16 ክፍለ ከተማ
 • ቫርኔሮ የቦታው ስፋት 67,500 በካ.ሜ ን/ስ/ላ 1 ክፍለ ከተማ
 • ሙሉነሽ ፍጥረት የቦታው ስፋት 66,763 ካ.ሜ ን/ስ/ላ 1ክፍለ ከተማ
 • ጌታቸው ወልዴ ሪል እስቴት የቦታው ስፋት 57,679 ካ.ሜ በን/ስ/ላ 1 ክፍለ ከተማ
{2} የመሬት ቅርምት ከ40,000  ሽህ እስከ 50,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ የመሬት ቅርምት 50,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ሴንቸሪ 21 ኮንስትራክሽን፣ ኤስ ኤን  ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ጋድ ኮንስትራክሽን፣ ጂ.ኤች ሲሚክስ፣ ከአጆ ኢንተርናሽናል፣ ኖብል ሪል እስቴት፣ አደይ አበባ ሪል እስቴት፣ ገ/ሚካኤል ማርቆስ፣ ፔትራም ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዮቴክ ኮንስትራክሽን፣ ቢኒያም ጥላሁን /ማርብስ/፣ ካንትሪ ክለብ ደቤሎኘመንት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ያንኮማንድ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ፈሪስት ሪል እስቴት፣ እንይ ጀነራል ቢዝነስ፣ አክስስ ሪልእስቴት፣ አድሮም ጀኔራል ትሬዲንግ፣ ሉና /የተ/የግ/ማ፣ ማጅኮን ጠ//ተቋራጭ፣ ደግነት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ፖስራክሲንክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ የመሬት ቅርምት 49,610 ሽህ እስከ 40,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ጋራድ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ በርታ ኮንስትራክሽን፣ ጌት አስ ኢንተርናሽናል፣ኃይሌና አለም ሪል እስቴት፣አምባሳደር ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዶ/ ቻርልስ ሪል እስቴት ናቸው፡፡      

{3} የመሬት ቅርምት 30,000 ሽህ እስከ 39,216 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አሚዎች፣ብርሃን ጐህ//የተ/የግ/ማ፣ ኤን ኤም ቢ፣ አምድይሁን ጠቅላላ ንግድ፣ ጋን ችንግ ሪል እስቴት፣ አሴ ትሬዲንግ፣ ስርደንጂ ሃውሲንግፓንአፍሪካ ሪል እስቴት፣አሴ ትሬዲንግ፣ አሴር ሪል እስቴትተፈሪ ይርጋ፣ ሮማናት ሪል እስቴት፣ ብስራት ፀጋ ሪል እስቴት፣ መሐመድ ሰብደን፣ ኢኬር ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ደ.ኤምሴ፣ ኮሜቶ ትሬዲንግ፣ይርጋ ሀይሌና ቤተሰብ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ካስትል ሪል እስቴትካንጋሮ ኘላስት ሪል እስቴት ናቸው፡፡

{4} የመሬት ቅርምት 20,000 ሽህ እስከ 25,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ኒው ሆኘሪል እስቴት፣ ሰሙ ተክሌ፣ ሆም ስዊት ሆም፣ ሾላ አክስዮን ማህበር፣ ናሰው ሪል እስቴት፣ ፊባ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ሆስኢ ትሬዲንግ፣ ሚካኤል ቤቶች አካባቢ ፣ ካስማ ኢንጂነሪግ፣ ማረፊያ ሪል እስቴት፣ ክንድያ ሀጐስ ሪል አስቴት፣ ዜደ.ኤም፣ ሮማናት ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ ሪል እስቴት ናቸው፡፡

{5} የመሬት ቅርምት 19,800 ሽህ እስከ 10,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ሁሴንሲራጅ ሪለ እስቴት፣ቶኘ ላንድ ሪል እስቴት፣ ሲሳይ ደስታ፣ አል አድ አሳ ሪል አስቴት፣ ሀውስ ዊዝደም ሪል ስቴት፣  ኃ/የተ/የግ/ማ፣ አቤንኮ ሪል እስቴት፣ ማይተባይ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዮሐንስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ፊሊክስ ኃ/የተ/የግ/፣ ጉላጉል ትሬዲንግ ኃ/የት/የግ/ማ፣ ላዋራ ንግድና ኢንዱስትሪ፣ ወ/ ይርጋለም አሰፋው፣ ስብሃቱና ልጆቹ፣ አዜብ ሃይሉ፣ ፍቃዱና ጓደኞቹ ሪለ እስቴት /የተ/የግ/፣ ራጉኤል የቤቶች ግንባታ /ማ፣ ሰንሴት ሆምስ ሪል እስቴት፣ ቶፊቅ ሻሽ፣ አበው ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዋይድ ኢንጂነሪንግ፣ ፍሬው ብርሃኔ ሪል እስቴት፣ መሠረት በትዛዙ ሪል እስቴት፣ መሃመድ አሊ ሪል ስቴት፣ ሉሲ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ወ/ሮ አልጋነሽ ሃይሉ ሪል እስቴት ናቸው፡፡

{6} የመሬት ቅርምት 1,072 ሽህ እስከ 6,940  ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ኤልያስአባሚልኪኤልያስ መሃመድና ኢብራሂም መሃመድ፣ እስክንድር ካሳ፣ አምሳለ ጌታቸው ፣ጀኖሪል አስቴት፣ ማይክሮ /ሥራ ተቋራጭ፣ ማደክ ካርጌት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ሜይ ሪል እስቴት፣ አዱኛ እጅጉ፣ ሳሙኤል አለማየሁ፣ አቶ ሰለሞን ወርቁ፣ ማቲያስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ማቲያስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣አንቶኒዩ ካርናቪያክኢምፓየር ሪል እስቴት፣ ፋሪይም ኃየተ/የግ/ማ፣ አቶ አስራት መኮንን አለም፣ ረዘነ ተፈራ፣ መልካም ራዕይ ሪል እስቴት፣ አበራ ቶላ፣ መክሊት ሪል እስቴት ናቸው፡፡ በወያኔ አገዛዝ ባለፈው 27 አመታት ውስጥ በህዝቡ ውስጥ የተፈጠረ የኃብት ክፍፍል መረን ያጣው ዜጎች በቤቶች ልማት ስም የተነጠቁት አንጡራ የመሬት ኃብት የተነሳ ነው፣መሬታቸውን የተነጠቁ ከግማሽ ሚሊን የሚበልጡ ሰዎች ቱጃሮች ሊካሱ ይገባል፣ተመጣጣኝ ቤት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የህዝብ መሬት የተቀራመቱት ሌቦችም ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ምንጭ {1} Last updated: August 2017 GAN Integrity

{2https://www.business-anti-corruption.com/country-profiles/ethiopia/.

{3https://tradingeconomics.com/ethiopia/corruption-rank.

‹‹ ከአገር በቀል ወደ አገር ነቀል የሪል ስቴት ዲቭሎፕርነት!!! የመሬት ቅርምት ሚሊየነሮች!!!››

‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር›› ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

በወፍጮ ላይ መጁ

‹‹ስሚኝ እማምዬ፣ለምን ታለቅሻለሽ

በወፍጮ ላይ መጁ፣ሲጨፍር እያየሽ!!!››

ማምዬ ስሚኝ፣ለምን ታነቢያለሽ

በመሬት ቅርምት፣አገር ተሸጠልሽ

መብራት ወሃ የለ፣በደሳሳው ጎጆሽ፣

በመሬት ቀማኛ፣ ቀላድ መተሩብሸ

አጃና ባቄላ፣ አንቺ ነሽ የከካሽ

አሻሮና ብቅል፣ በተራ የፈጨሽ

ዓለም ተሸዓተ፣ ወያኔ እያለሽ

የትም፣ የትም ፍጪው

ዱቄት፣ ድቄቱን አምጭው

ሰው ስው ባልሸተተ ልማት

ልጆችሽ አለቁ፣ በርሃብና ስደት

ከጥንት ከጠዋቱ፣ በተካንሽው ዘዴ

ከወፍጮ ስር እህል፣ ከመጁ ስር ስንዴ

አልመሽ አድቅቀሽ፣ከሆነብሽ ሁዳዴ

ሰጪው ዱቄትሽን፣ ለንፋስ ዘመዴ፣

እንኮን የመሶቡን የጄን ተውኩላችሁ

እነ ዘር ቆጣሪ፣ እነ አጥር አጣሪ

ቀረ ዓለም ከእንግዴ፣ ከሰው ከፈጣሪ!!!

‹‹ስሚኝ እማምዬ፣ለምን ታለቅሻለሽ

በወፍጮ ላይ መጁ፣ሲጨፍር እያየሺ!!!

ጦቢያ ወፍጮ ሆና፣ መጁ ወየነልሽ

አንዱ ጡት ሲጠባ፣አንዱ ተጠማልሽ

የእንጀራ እናት ጡጦ፣ አጉርሽው እባክሽ!!!

ዱቄትሽ ተነጥቀው፣ ተራቡ ልጆችሽ

መሬት ላራሹ! ይሉ እንዳልነበር

አራሹም መሬቱም የተመነጠር!!!

የደም ግብር ለአግአዚ ጦር

እስከ መቼ እንገብር!!

ተሰደድ ከቀያቸው

ተነቀሉ ከቤታቸው

የተከሉ ከወንዛቸው

ኮበለሉ ድንበር ዘለው

የዓባይ ልጅ ውሃ ጠማው

ከውቅያኖስ ጠጡ ሰምጠው

አፈር ገፍተን፣ድቄት ፈጭተን

ታሰርን ሞተን፣የተገፋን

አብረን ተርበን የተጠማን

ዛሬም ነገም እየገበርን

ያልሰማህ ስማ ለአዋጁ አዋጅ

‹የማን ቤት ፈርሶ፣ የማ ሊበጅ

የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ!!!››

የአበው ቃል ስማ፣ እንደ እሣት የሚፋጅ

ሃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው

ወፍጮ ላይ ታዝሎ፣ አይጨፍርም መጅ!!!››

የእናት ጡት ነካሽ፣ ያዘው እጅ በእጅ

የአበው ቃል ስማ፣ ለሃገር የሚበጅ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 300 ሚሊየን ዶለር ጉድ እና ሜቴክ (ሚክይ አምሃራ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስፋፊያ አይታቸዉሁት ከሆነ በኢንተርናሽናል ተረሚናል በኩል የተሰራዉ ትንሽየ ማስፋፊያ 300 ሚሊየን ዶላር ነዉ የፈጀዉ ወየም ወደ 10 ቢሊየን ብር፡፡ ይህ ዋጋ አሁን ባለዉ የአለም ገቢያ መሰረት ትንሽየ ማስፋፋት ሳይሆን አንድ ራሱን የቻለ ደረጃዉን የጠበቀ ኤርፖርት ይገነባል::

ጉዳዩ እንዲህ ነዉ፡፡ኪሮስ አብርሃ የሚባል የህወሃት ሰዉ ነበር አሁን ሜቴክ የያዛቸዉን የመከላከያ ኢንደስትሪዎችን ይመራ ነበር፡፡ ከዛም ሰራርቆ ከወጣ በኋላ የራሱን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ አቋቋመ፡፡ ወደ ቻይና ሄደ እና እዛ ለይምሰል አንድ አነስ ያለ ድርጅት ጆይንት ቬንቸር ፈጠርኩ አለ፡፡ ይሄን ያረገበት ዋና አላማዉ የአየር መንገዱን ማስፋፊያ ከኋላ ሁኖ ለመስራት ነዉ፡፡ የጨረታዉን ኮንትራትም ከአቶ ተወልደ ጋር በመሆን እንዲያሸንፍ ሆነ፡፡ ኪሮስ አብርሃ ከጀርባ ሁኖ ትንሽየ ማስፋፊያ በ300 ሚሊየን ዶላር ከቻይና ኩባንያ ጀርባ ሁኖ ዘረፈ ማለት ነዉ፡፡

የኪሮስ አብርሃ ልጅ አብርሃ ኪሮስ ይባላል፡፡ ኖርዌ ይኖራል በኖርወይ አገር ዉስጥ ከ1 እስከ 10 ካሉት ባለሃብቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ ይባላል፡፡ ዉሎ እና ኣዳሩ የካረቢያን አገሮች ላይ ነዉ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ በየቀኑ ይመላለሳል፡፡ ዋና ስራዉ የህወሃቶችን ዶላር እየተቀበለ የካረቢያን አገሮች ባንክ ዉስጥ ማስቀመጥ ነዉ፡፡ ኖርዌ ዉስጥ ማስቀመጥ እይችልም፡፡ ገንዘቡን የሚያወጣዉ ከአየር መንገዱ በመመሳጠር ነዉ፡፡ እንዲሁም አየር መንገዱ በአዉሮፓ ባሉት የትኬት መሸጫ ጣቢያወች የሚገኘዉን ገንዘብ እዛዉ ያስቀርና አዲስ ላይ በኢትዮጵያ ብር ይከፈላል፡፡

ሌላኛዉ መረጃ ሰሞኑን ግር ግሩን ተጠቅሞ የፍራንክ ፈርት የአየር መንገዱ ጣቢያ ሰራተኛ 1 ሚሊየን ይሮ ይዞ ተሰዉሯል፡፡ ማኔጅመንቱ ተሰብስቦ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ይልቁን ወሬዉ እንዳይወጣ ተስማምተዋል፡፡

ሌላዉን ጉድ ልንገራችሁ ባለፈዉ ተወልደ ፕሌን አለዉ ብያችሁ ነበር፡፡ እሱ ብቻ አይደለም የሜቴክ ሰወች እራሱ አላቸዉ፡፡ አባይ ሊዝንግ ሌላም አንድ ድርጅት አለ በእነዚህ ድርጅቶች ምክንያት የኢትዮጵያን አየር መንገድ ሎጎ አድርገዉ ስራ ሚሰሩ ብዙ አዉሮፕላኖች አሉ፡፡ ገንዘቡ ግን ገቢ ሚሆነዉ ለሜቴክ ሰወች ነዉ፡፡

የብርጋዴር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ዝርፊያ ሲጋለጥ

አማኑአል አብነት

ጋሽ ፖሊሱ ይህን መረጃ ለማግኘት በእርግጠኝነት 8 ወር ይጨርስብህ ነበር። እኔ ግን እንካ በነፃ ብየሀለሀ። አቶ ኢሳያስ ዳኘው፤ የሜይቴኩ አቶ ክንፈ ዳኘው ወንድም ነው፤ አማርኛም እንግሊዘኛም በቅጡ አይፈልጥም፣ በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ ትልቅ ስም ያለው በዝባዥ ነው። ይህ ሰው ከ2000ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ በቀጣይ ጄነሬሽን ኔትወርክ(NGN)ፕሮጀክቶች ላይ አራጊ ፈጣሪ የነበረ ኤክስኪውቲቪ ነው። ከ1.5 billion USD telecom project ውስጥ የመንግስትን ካዘናን በvendor Finance ስም ያስበዘበዘ ጉማሬ ነው።

ከ2001-2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን የኔክስት ጀነሬሽን ኔትወርክ(NGN) እና የኔክስት ጀነሬሽን ፕሮግራም ኦፊስ(NGPO) ቢሮዎች ሲቋቋም ቀጥታ በእነ አቶ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የኢንፎርሜሽን እና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ትእዛዝ ከኢንተርፕራይዝ(የድርጅት)ስራ አስኪያጅነት ወደ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅነት ተቀይሮ የ1.5billion Dollar project እመየራ ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን እያሰራ የነበረውን የ4.5 ቢሊዮን ዶላር ቬንደር(Vendor) ፕሮጀክት ከቻይናው ZTE ጋር የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን እና የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈርሙ ከእነ ደብረፅዮን ጋር ካደረጉ ስዎች መካከል አንዱ ነው። ጨረታ ላይ ከETC ጋር የቀረቡት የቴሌኮም ካምፖኒዎች Nokia(ቀድሞ የኢትዮጵያን ቴሌኮም ኢንፍራስትራክቸር የሰራ)፣ Ericsson-የቴሌኮም እቃ አቅራቢ እና በጥራቱ የታወቀ ቬንደር እና service provider እና ZTE-ርካሽ እና ጥራታቸው በጣም ዝቅተኛ የሆነ እነዚህ ነበሩ። ያሸነፍ የነበረው እና ሁሉንም standard requisition ያሟላው ኤሪክሰን እና ኖክያ ነበር። ተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦ ያሸንፍ የነበረው ኤሪክሰን ነበር። ያው ከቻይናዎች ጋር በድርድር (lobby) ተደርጎ በጥቅም እና በወደቀ ኳሊቲ ከእነ ደብረፅዮን ትዕዛዝ እንዲገባ ተደረገ።

ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ጥቅምት 2005 ዓ.ም ላይ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲቀየር ይህ ሰው የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር(COO) ሆነ ብዙ ፋዎሎችን ፈውሏል። ወይ አባ ግዶ ማንን ሊሰማ
1.ለድርጅት ደንበኞች የሚሰጥን የማስታወቂያ እና branding እቃዎችን ከፍላሽ እስከ ሞደም፣ከመደበኛ ስልክ እስከ ድብቅ ካሜራ ሀላል የሚዘርፍ ወንበዴ
2. ያለ ጨረታ ከሜይቴክ ለቴሌ ኬብል(ፋይበር እና ኮፕር)፣pvc ቱቦዎችን እና የመብራት ትራንስፎርመሮችን ፣የሰራተኛ እና መኪኖችን ተዋውሎ የሸጠ፣የሽያጭ ውሉን በውጭ ዶላር በዩክሬን ኩንባያ ስም ያስደለለ ጋንታ ዱርየ ነው። ደሞ ደሞዜ 8000 ብር ነው ይለናል፣የቴሌ ሹፌር እንኳን ከዛ በላይ ይበላል፤ይህን ሹፈት እና ሽሙጥ ክቡሩ ፍርድ ቤት ልደታ ከቴሌ ፋይናንስ ክፍል ያጣራ ወይም ከETA ኤግዚቢት ይያዝ
3.የወጭ ስልጠና በተለይ ህዋዊ እሱን የሚድምመው የለም የበረራ ገዞውን ማገላበጥ ይቻላል
4. ኢትዮ ቴሌኮም ያላገኘውን የሰው ሀይል እና የድርጅት አቅም በተገዙ የቻይና እና የእንግሊዝ ድርጅት የጥራት ለኪዎች አይሶ የማያሟላባቸውን እንደ ሽልማት በማስመሰል ድርጅቱን እንስዳስቀለደበት
5. በቴሌኮም ፍራውድ የወንድሙን ሜይቴክን እና ጓደኛውን የብሄራዊ ደህንትነን ተክለብርሀን እና ቢንምያን በመተማመን ከ12 ሚሊየን ዶላር በላይ ድርጅቱ ሲመዘበር ዝም ብሎ ያለፈ እና በድርጅቱ ሰራተኞች እና ደንበኞች ዋይታው ሰበዛ የሞደም አስተላላፊ አክተር ሆኖ መገኘቱ እና የጥቅም ተካፋይ መሆኑ
6. በአዳዲስ የV8 ክሩዘር ለአመራሮች መኪና ግዢ ላይ የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ ያጭበረበረ እና በግዴታ ግዢው ሲፈፀም ኢትዮጵያ ውየጭ ምንዛሬ ችግር ውስጥ በገባችበት ሰአት ይገዛ ብሎ የፈቀደ የሀገር ክህደት የፈፀመ ዘራፊ ማፍያ ነው።
7. በዘሩ የሚመካ እና ለሌሎች ወንድም ዘሮች እና ኢትዮጵያውያን ደንታ የሌለው እንደውም በንቀት የተሞላ እብሪተኛ ነው።

ስላልተነገረ እንጅ ጉዱ እልፍ ነው። ደሞ ደሞዜ 8000 ብር ነው ይላል።
በሉ አስገቡልን አቦ ቤቱ ባልሳስሳት ኢምፔሪያ አካባቢ ነው። ለነገሩ አንድ 3 ቪላ ይኖረው ይሆናል ማን ያውቃል።

ሜቴክ የእንግዴ ልጅ ሚሊየነሮች! በስመ ‹‹ፕራይቬታይዜሽን!›› ‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር›› ክፍል አንድ ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

(METEC MILLIONERS IN THE NAME OF BRIBE-VITAIZATION)  /ለሜቴክ የሙስና አጣሪ ኮሚቴ የተላከ

አባት ጅብ ከሁለት ልጆቹ ጋር ሆኖ አንድ ወደል አህያ አግኝተው አባትየው ብቻውን አህውን በለና በአካባቢው ሰዎች ተከበቡ ይባላል፡፡ አባት ጅብ ዱላው ሲበዛበት ልጆቹ እንዲያግዙት እተጣራ ተመፀነ፡፡

ልጄ ማንሾለላ፣
ምን ሰጠህኝ ከአንድ ጆሮ ሌላ!
ልጄ መዝሩጥ፣
እንደበላህ እሩጥ! አሉት ይባላል፡፡ ‹‹ማነሺ ባለሣምንት!!!››

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (Metals and Engineering Corporation (METEC)፣ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት፣ በመከላከያ ሚኒስትር ስር የተዋቀረው የእንግዴው ልጅ ብኢኮ/ሜቴክ፣  ከደርግ ወታደራዊው መንግስት፣ መከላከያ ሠራዊት የተወረሱ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመረ የእንግዴ ድርጅት ነው፡፡ ሜቴክ በ2010 እኤአ በአስር ቢሊዩን (10,000,000,000) ብር መነሻ ካፒታል ተመሠረቶ ሥራ ሲጀምር ከደርግ መከላከያ ሠራዊት የተወረሱ አስራሁለት ሜካናይዝድ ፋብሪካዎች ሥም በመቀየርና በወታደራዊ ሣይንስ የተካኑ የሠራዊቱ አባላቶች ዕውቀትና ልምድ ማርኮ የተዋቀረ እንግዴ የወያኔ ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት  ዘመን እንግዴው ሜቴክ ተንሰራፍቶ፣  ከስባ አምስት እስከ መቶ ፋብሪካዎች በላይ ያሰባሰበ  ድርጅት ለመሆን ችሎል፡፡ የህወሃት ሜቴክ ጀነራል ማኔጀር ብርጌደር ጀነራል ክንፉ ዳኘው ሲሆኑ እንዲሁም ምክትል ጀነራል ማኔጀር ኮለኔል ጠና ኩርንዲ ይባላሉ፡፡ ሜቴክ ኮርፖሬሽን ከ13000 ሠራተኞች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ 1000 ዎቹ ማሃንዲሶች ናቸው ይሉናል፡፡

በኢትዮጵያ ‹‹ወታደራዊ የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› ነቀላና ተከላ የተኮላሸው ለዚህ ነው፤ ከደርግ ወታደራዊ መንግሥት ወደ ዘረኛ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ተሸጋገረ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሠራዊት ተቆማቶች በወያኔ ጠባብ ዘውጌ ሠራዊት ከተተካ 26 ዓመታት ተቆጠረ፡፡ ከነዚህ ‹‹ወታደራዊ የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› ውስጥ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት የመከላከያ ሚኒስትር ስር የተkkመው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም ከወታደራዊ መንግስት ንብረትነት ወደ ሕወሃት መንግስት ንብረትነት ሽግግር በስመ-ፕራይቨታይዜሽን ስም የተሸጋገሩ ዋና ዋናዎቹ የህዝብ ኃብቶች ቀጥሎ በዝርዝር ይቀርባሉ፡፡

(1) የደጀን አቨየሽን ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ (Dejen Aviation Engineering Complex (DAVEC) በወታደራዊው መንግስት በ1984 እኤአ በኢትዩጵያ አየር ኃይል የተመሠረተው  የአውሮፕላን ማደሻና መመርመሪያ ማዕከል በመሆን ከፍተኛ የአየር ኃይል አውሮፕላን ጥገናና እድሳት ሥራ በማድረግ ይታወቃል፡፡ ከአዲስአበባ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት በደብረዘይት ከተማ የሚገኘው ኢንደስትሪ በስሩ፣ ስምንት የነበሩ ፋብሪካዎች በማደራጀት የማይንቀሳቀስና ተንቀሳቃሽ የአውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ኤሮስፓስና ሜካኒካል ፋብሪካ፣ አቪዩኒክስ ሲስተም ኢንቲግሬሽን ፋብሪካ፣ ፓወር ፕላንት  ፋብሪካ፣ የአውሮፕላን አካልና መቃን አቆም/ስትራክቸር ፋብሪካ፣ ዩኤቪ ምርቶች ፋብሪካና የአውሮፕላን ጥራትና ችሎታ መፈተሻ ማዕከል ፋብሪካዎች በህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ተገንብቶ ነበር፡፡ የቀ.ኃ.ሥና የደርግ ዘመን ‹‹ወታደራዊ የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› ዛሬ በወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ ተካሄደበት፡፡ በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት  ዘመን ድርጅቱ ዳቦ ሳይቆረስ ደጀን አቨየሽን ኢንድስትሪ ተብሎ በ(ብኢኮ) ንብረት ሆኖ ተወረሰ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሌተናል ኮነሬል ኪዱ ፀጋዬ እና ሜጀር ሃይለ ገብረ ጊዮርጊስ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

(2) የጋፋት ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ (Gafat Engineering Factory) በወታደራዊው መንግስት በ1989እኤአ ኤኬ-47  እና አርፒጂ ቀላል  መትረየስ ጠመንጃ በማምረት ይታወቃል፡፡ ፋብሪካው ከአዲስአበባ ደቡብ ምስራቅ 65 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲገኝ፣ ፋብሪካው በ4,412 ስኮየር ኪሎሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነበር፡፡ፋብሪካው በተጨማሪ ኤኬ 103፣ 40 ሚሊሜትር የቦንብ አውዘግዛጊና ሌሎች አቶማቲክ መሣሪያ በጦር መኪናዎችና በሂሊኮፕተር ላይ የሚገጠሙ ላውንቸር፣ ማኑፋክቸሪንግ የጦር መሳሪያ መለዋወጫና ብረት በማቅለጥና ምስል መቅረፅና በመጫን ምርቶችን አምርቶ ለገበያ የማቅረብ አላማ አካቶ ፋብሪካዉ ያመርት ነበር፡፡ የጋፋት  የመሳሪያ ኢንደስትሪ ስድስት ፋብሪካዎችን ያካትታል እነሱም፣ አነስተኛ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ማምረቻ፣መካከለኛ ካሊበር ማምረቻ ፋብሪካ፣ሮኬት ላውንቸር እንዲሁም ሞርታርስ ፋብሪካ ማምረቻ  እና ከባድ መሳሪያ የመድፍ ማምረቻና ቅርብ ርቀት የሚተኩስ ጠመንጃ ፋብሪካ ማምረቻ ፣እንዲሁም የመሣሪያ መለዋወጫ ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎችና በህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በ2002እኤአ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት  ዘመን ካንፓኒው ስሙን በመቀየር ጋፋት የመሳሪያ ኢንደስትሪ (Gafat Armament Industry) በመባል  የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ግሩም ገብረኪዳንና ሜጀር አፅብሃ ገብሬ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

(3) የናዝሬት የትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ (Nazareth Tractor Assembly Plant (NTAP)በወታደራዊው መንግስት በ1984እኤአ  ከአዲስ አበባ ከተማ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት በናዝሬት ከተማ ውስጥ በ114,388 ስኩየር ሜትር ባታ ላይ የተገነባ ነው፡፡ ፋብሪካው  ትራክተር በመገጣጠም፣የውሃ መርጫ ማጠጫ/ፓምፕ እንዲሁም የተለያዩ የግብርና መሣሪያዎች መገጣጠሚያና መለዋወጫ ምርቶች በመስራት ይታወቅ የነበረ ነው፡፡ በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት  ዘመን ስሙ ተቀይሮ  የአዳማ የግብርና ማሽነሪ ኢንደስትሪ (Adama Agricultural Machinery Industry (AAMI) ተብሎ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡ የናዝሬት የትራክተር መገጣጠሚያ አራት ፋብሪካዎች ስብስብ ነበር፣ ወታደራዊው ፋብሪካና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሻንበል ሚኪያስ ሜጋ ይባላሉ፡፡

(4) የናዝሬት የልብስና ጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ በወታደራዊው መንግስት በ1987እኤአ፣የልብስና ጨርቃ ጨርቅ  ፋብሪካ፣የልብስ መስፍያ ፋብሪካ፣ፓራሹትና የዕቃ ማንሸራተቻ ፋብሪካ፣የጫማና የእጅ ጎንት ፋብሪካና የቤት ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ የመሳሰሉትን በማምረት ይታወቃል፡፡ ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 105 ኪሎ ሜትር ርቀት በናዝሬት ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት  ዘመን የአዳማ የልብስ ኢንደስትሪ (Adama Garment Industry (AGI) ተብሎ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡ ወታደራዊው ፋብሪካና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ከተማ አብዲ ይባላሉ፡፡

(5) የአቃቂ መሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ (Akaki Basic Metals Industry (ABMI) በወታደራዊው መንግስት በ1989እኤአ በመባል ልዩ ልዩ ከፍተኛና ዝቅተኛ መገጣጠሚያና ማኑፋክቸር መለዋወጫዎች እንዲሁም የካፒታል ጉድስ ማለትም የስካር ማምረቻ ወፍጮ ፍብሪካ፣የስካር ማቀነባበሪ ማፍያና መቀቀያ መለዋወጫዎች፣የብረት ካሶችና የብረት ሠፌዶች፣የጉድጎድ የብረት ክዳኖችና መቃኖች እና ተንቀሳቃሽ የብረት ዘንጎች በማምረት ይታወቃል፡፡ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት በአቃቂ ከተማ ወጣ ብሎ ይገኛል፡፡በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት  ዘመን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ( Privatization and Public Enterprises Supervising Agency ) አማካኝነት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡

ፋብሪካዎችና በህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ጀማል አብዲልከድር እና ሻንበል ሙሳ ይማም  ይባላሉ፡፡

(6) የብሸፍቱ አውቶሞቲቨ ኢንደስትሪ (Bishoftu Automotive Industry (BAI) በኢህአዴግ መንግስት በ1999 እኤአ በብሄራዊ መከላከያ ሚኒስትር አስተዳደር የተመሰረተ ፋብሪካ ነበር፡፡ ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት በደብረዘይት ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ፋብሪካው ወታደራዊና የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብሶች፣ የከተማ ውስጥ አውቶብሶች፣ የጭነት መኪናዎች፣ ፒክ አፕ መኪናዎችና ሲዩቪ መኪኖች ይገጣጥማል፡፡ በ2010 እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተዘዋወረ፡፡ ፋብሪካውና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሌተናል ኮነሬል ገብረ መድህን ገብረ ሥላሴና ሻንበል አብዱልፈታ ናስር ይባላሉ፡፡

(7) የኢትዩጵያ ፕላስቲክ ኢንደስትሪ ( Ethiopia Plastics industry) በቀ.ኃ.ስ ዘመን በ1960እኤአ የተገነባው ፋብሪካ ነበር፡፡ በ1973 እኤአ በወታደራዊው መንግስት 55 በመቶ የመንግስት ኃብትነትና ቀሪውን 45 በመቶ ለባለቤቱ ድርሻ ንብረትነት በመስጠት ፋብሪካው ቀጠለ፡፡በ1978 እኤአ ፋብሪካውን የደርግ መንግስት ሙሉ በሙሉ ወረሰው፡፡ የፋብሪካው ምርቶችም፣ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶች፣ የሽቦና የኬብል ምርቶች፣ ተጣጣፊና ደረቅ ኮንዲዩቶች፣ ፒፒር እና ኤችዲፒኢ ቱቦዎች/ፓይፖች፣ ፖሊቲሊን ምርቶች ማለትም የፊልም ፓኮዎች፣ ተጣጣፊ መጠቅለያ ሽፋን፣ የገበያ ቦርሳዎች፣ ፖሊቲሊን ቱቦዎች፣ ረዥም የላስቲክ ቱቦ፣ የኢንደስትሪ ቦት ጫማዎች፣ እና መገናኛ ሣጥኖች በማምረት ይታወቃል፡፡ በ2011እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ዳግም ተወረሰ፡፡ ፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት በአዲስአበባ በሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ሲሆን የፋብሪካው ማምረቻ ቦታ በገርጂ ይገኛል፡፡ ፋብሪካውና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ አቶ ጋሻው ይመር ይባላሉ፡፡

(8) ህብረት ማኑፋክቸሪንግና የማሸን ግንባታ ኢንደስትሪ Hibret Manufacturing and Machine Building Industry (HMMBI) በቀ.ኃ.ስ ዘመን በ1945 እኤአ የተገነባው ፋብሪካ ነበር፡፡ HMMBI has five factories:  machine building factory, material treatment and engineering factory, mechanical subsystem factory, precision machinery factory and conventional manufacturing factory. The manufactured products primarily serve as input into a wide variety of industrial machinery used by agencies in the public and private sectors. በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡ ፋብሪካው በአዲስአበባ በሜቴክ ዋና መስሪያ ቤት አጠገብ ይገኛል፡፡ ፋብሪካውና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ተሰማ ግደይ ይባላሉ፡፡

(9) ሃይ-ቴክ ኢንደስትሪ (Hi-Tech Industry (HTI) ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት በለገዳዲ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡Production and assembly of communication radios (both for military and commercial purposes), various types of radar systems, electronic devices such as TV sets, electromechanical devices such as energy meters, harmonic analyzers, optical devices such as night vision devices, thermal imagers, and security cameras, other electronic technology products.

በ2011እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተቆቆመ፡፡ ፋብሪካውና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር በሪሁ ግደይና ሻንበል ጋሻው ይባላሉ፡፡

(10) ሆሚቾ የጦር መሣሪያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ (Homicho Ammunition Engineering Industry (HAEI)በ1987 እኤአ በወታደራዊው መንግስት ዘመን፣ ፕሮጀክት 130 በመባል የተገነባው ማኑፋክቸሪንግና የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ሲሆን ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 140 ኪሎ ሜትር ርቀት በምስራቅ ሸዋ ዞን(አንቦ/ ጉደር) በ980,000 ስኩየር ሜትር (በ224 ሄክታር) ላይ የተገነባ ፋብሪካ ነበር፡፡ ፋብሪካውን የገነቡት የሰሜን ኮሪያና የራሽያ መንግስታቶች በህብረት ነበር፡፡ ከዛም የሰባት ፋብሪካዎች ስብስብ ሲሆን እነሱም የአነስተኛና መካከለኛ የጦር መሣሪያ ማምረቻ፣ከፍተኛ የጦር መሣሪያ ማምረቻ  ግምጃ ቤት ፋብሪካ፣ የሣጥንና የመርከብ ጥገና፣የፈንጂና የሚሽከረከር/ውልብልቢት ማምረቻ ፣የሮኬት ማምረቻ፣ባልቦላ ወይም የመብራት ቆጣሪና የፈንጂ ማምረቻ ፋብሪካዎች ያጠቃልላል፡፡ በ2010 እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተዘዋወረ፡፡ ፋብሪካውና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ኮሎኔል ሃድጉ ገርብጊርጊስና ሜጀር ዘውዱ አለፈ ይባላሉ፡፡

(11) የብረት ፋብሪኬሽን ኢንደስትሪ (Metal Fabrication Industry) ብረታ ብረት የፈጠራ ሥራ ኢንደስትሪ፣  ፋብሪካው በአዲስአበባ ከተማ በልደታ ክፍለ-ከተማ ውስጥ ከሜቴክ ዋና መስሪያ ቤት አጠገብ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው በብረት ፈጠራ ሥራ ዋናዎቹ የግንባታ ማሽነሪዎች፣የአውቶቡስ አካልና መቃን መሥራት፣ ጀልባ ሥራ፣ ከባድ እቃ ማንሻ መሣሪያ ለፎቅ፣ የግንባታ አሳንሱር፣ የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ማማ፣ ተገጣጣሚ ቤቶች ማምረቻ፣ እንዲሁም የቅጂና መጫን ምርቶች ያካትታል፡፡ ፋብሪካውና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሻንበል ቢቂላ በቃና እና ጌታሁን ገብረ ትንሣይ ይባላሉ፡

(12) የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ (Ethiopia Power Engineering Industry (EPEI) የፋብሪካው አጠቃላይ ጥናትና እቅድ ከውጭ የመጡ በግሉ ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆን ፍቃድ ተከልክለው ከቆዩ በኃላ በ2010እኤአ  በሜቴክ ጥናቱ ተሰርቆ ፋብሪካው ተመሠረተ ፡፡ ፋብሪካው ከአዲስአበባ ከተማ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ካንፓኒው በስሩ ሰባት ፋብሪካዎችን ያካትታል፣ እነሱም የትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ፣ የኤሌትሪክ ሽቦና ቱቦ ማምረቻ፣ አውቶማቲክ የኤሌትሪክ ኃይል ማስተካከያ፣ የኤሌትሪክ ኃይል የሚተላለፍበት/ ስብስቴሽን ጥገናና መለዋወጫ ማምረቻ፣ የፀሃይ ብርሃን ማጠራቀሚያ ባርድ ማምረቻ፣ የሞተርና የጀነሬተር ማምረቻና፣ የሞተር፣ እንዲሁም በፈሳሽ ወይም በዓየር የሚሽከረከር/ተርባይን ሞተር ማምረቻ ፋብሪካዎች ናቸው፡፡ ፋብሪካውና የግሉን ዘርፍ ሥራ የነጠቀ ህብረ-ብሄራዊው የእውቀት ክህሎትን ያጨለመ በወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ የተከወነ ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር አስፋ ዩሃንስና ሻንበል ዘመድኩን ይባላሉ፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ የኤሌትሪክ ሽቦና ቱቦ ማምረቻ ፋብሪካ እንዲሁም ከ400KV እና 500 KV ከፍተኛ ቮልቴጅ የኤሌትሪክ መስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚዎች( high-voltage electricity- transmission cables,) በሁለት መቶ ሚሊዩን ብር ወጭ  ለታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብና ለግልገል ጊቤ ሦስት ፕሮጀክቶች ሥራ ተሠጥቶታል ፋብሪካውም ከአዲስአበባ ከተማ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሞጆ ከተማ ውስጥ ተገንብቶል፡፡ “The Ethiopian Power Engineering Industry inaugurated a wire and cable factory which is one of its eight factories built in the Modjo town at a cost of 200 million Birr to produce electric cables that can carry 400 and 500 KV, especially for the power transmission of the Grand Renaissance and Gibe III dams.”

በአሁኑ ግዜ  በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በመከላከያ ሚኒስትር ሥር የሚገኘው፣የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ከስባ አምስት እስከ መቶ ፋብሪካዎች በላይ በስሩ ያሰባሰበ  ድርጅት ሲሆን የፋብሪካዋቹ፣ የሥራ ዘርፎች፣የካፒታላቸው መጠን፣የግብር አከፋፈላቸው፣የስም ዝርዝራቸውን፣የሚገኙበት ቦታ፣ጀነራል ማናጀራቸው፣የኦዲት ሪፖርታቸው ለህዝብ ይፋ አይደሉም፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች በኢትዮጵያ ‹‹ወታደራዊ የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› ነቀላና ተከላ የተኮላሸው፤በወያኔ የዘር ሞኖፖሊ በማዋቀር ለህገ-መንግስቱና ለህግ ተገዥ ያለመሆን ስርዓት ለአለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሜቴክ በኢትዩጵያ  ኢኮኖሚ ዘርፎች በሲቪልና በወታደራዊ መስኮች፣ ያለ ሕግ የሚንቀሳቀስ የህወሃት የንግድ ካንፓኒ ሲሆን፣የግሉን ዘርፍ ያገለለና የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ዕዝ ኢኮኖሚ የመለሰ ስርዓት መሆኑንና ከደርግ ስርአት ውድቀት መማር ያልቻለ፣ለማንም ህሊና ላለው ዜጋ ሁሉ ግልጽ ነው፡፡ የሃገራችንን ኢንደስትሪ/መኑፋክቸሪንግ/ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ቀስ በቀስ ድጋፍ ከተደረገላቸው ማደግ ይችላሉ፡፡ በልማታዊ መንግስታት በቻይና፣ደቡብ ኮሪያና፣ታይዋን በመሳሰሉት ሀገራቶች በኢንደስትሪ/መኑፋክቸሪንግ/ዘርፍ በተሰማሩ  በሲቨሉ ህብረተሰብ እውቀትና ስልጠናና በመንግስት ድጋፍ የኢንደስትሪ ዘርፍ አድጎል፡፡  የህወሃት ልማታዊ መንግስት  በመከላከያ ሚኒስትር ስር በተገነባው፣የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሃገሪቶ የኢንደስትሪ ዘርፍ እድገት በምንም ተዓምር አይመጣም፡፡ የግሉን ዘርፍ ደፍጥጦ በመከላከያ ሠራዊት የኢንደስትሪ አይገነባም፡፡ በሌሎች ሃገራትም በዚህ መንገድ የተገኘ የኢኮኖሚ እድገትና ግኝት የለም፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞች፣ ጀነራል መኮንኖቹ በአዲስአበባና በየክልሎቹ ከተሞች ፎቆች የሚገነቡት ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ በመሆን የምትታለበዋ ላም ሜቴክ መሆኖ ያደባባይ ሚስጢር ነው፡፡በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ፣ ከደርግ መንግስት ለህወሃት  መንግስት ‹የማፍያ መንግስታዊ ሞኖፖሊ› የህዝብ ኃብትን የወረሰና ያሸጋገረ፣ የእዝ መንግስታዊ ኢኮኖሚ የዘረጋ መሆኑን፣ የዓለም ባንክና  አይኤም ኤፍ እውቅና የሰጠው፣የአውሮፓና አሜሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ ጠበብት የሚያውቁት ሃቅ ነው፡፡1986እኤአ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተቆቁሞ በወታደራዊው መንግስት ከግለስብ ኢንቨስተሮች የወረሰውን 365 መንግስታዊ ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፍ አዘዋውራለሁ ቢልም አሰራሩ መልሶ፣ ከደርግ ወደ ህወሃት መንግስታዊ ኃብትነት የተዘዋወረ የወያኔ መንግስታዊ ሞኖፖሊ ሆነ፡፡ የመንግሥታዊ ዘርፍ፤ነቀላና ተከላ!!! ዝውውር ከደርግ ወደ ህወኃት የፖለቲካ ድርጅት ተሸጋገረ፡፡

የደርግና የህወሃት መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ የካፒታሊስቱን ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ በመተው፣ መንግስታዊ ሞኖፖሊ በመፍጠር አገሪቶን ወደ እዝ ኢካኖሚ ከተዋታል፡፡ የህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶችን የገዥው ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች የአገሪቱን ኢኮኖሚ ዘርፎች ተቆጣጠሩ፡፡ መንግስታዊ ሞኖፖሊ በቴሌካምኒኬሽን፣ በኤሌትሪክ ኃይል፣ በባንክ፣ በኢንሹራንስ፣ በአየር ትራንስፖርት፣ በመርከብ መጎጎዣ፣ የስካር ፋብሪካዎች፣ እርሻዎችና የመሬት ኃብት በወያኔ መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ የሃገሪቱ የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የትራንስፖርትና የጭነት መጎጎዣዎች፣ የማዳበሪያ ፋብሪካና የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች በአመዛኙ በህወኃት መንግስት፣ በኢፈርት፣ሜቴክና ሜድሮክ  ኃብቶች ናቸው፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር መሪ ዶክተር ደብረፂዋን ገብረሚካኤል ሜቴክ በሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ሃገራት የቢዝነስ አጋሮቹ ጋር በመሆን ወደሃገር ውስጥ የሚገቡ ምርትና ሸቀጦችን በመተካት የውጭ ምንዛሪ ለማዳን ሜቴክ ይንቀሳቀሳል ቢሉም ሜቴክ የሰራው ምርትና ያዳነው የውጭ ምንዛሪ ደፍረው አልገለፁም፡፡ ሜቴክ መንግስታዊ ሞኖፖሊ እንደሆነ የግሉን ዘርፍ ስራ እየነጠቀ እንደሆነ ዶክተሩ የሚመሩት ቴሌኮም ከዓለማችን ካሉ ሃገራት የመጨረሻ ተርታ ውስጥ መሆኑን መረዳት ተስኖቸዋል፡፡

መንግስታዊ ሞኖፖሊ የግሉን ዘርፍ ኢኮኖሚ በማቀጨጭና በማቆርቆዝ ላይ ይገኛሉ፣ ነፃ ገበያ ባለመኖሩና የተመቻቸ የገበያ ውድድር ህግ ባለመኖሩ፣ የመንግስት ቢሮክራሲ የህግ ደንብና አፈፃፀም በግሉ ዘርፍ ላይ ከሚፈፀሙ አድሎዎች መኃል ለመጥቀስ (1) ከባንክ ብድር የማግኘት ዕድል፣ ለኢፈርት፣ ሜቴክ፣ሜድሮክ የመሳሰሉ ድርጅቶች የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ የሚያበድረው ብድር አድሎ የተሞላበት ነው፡፡ ለጀነራል ፃድቃን ገብረ ትንሳይ ለተቆቆመው ራያ ቢራ ፋብሪካ ባንኩ 910 ሚሊዩን ብር እንዲያበድር ቀጭን ትእዛዝ ተሰጥቶ ተበድረዋል፡፡  (2) ፋጣንና ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት የማግኘት እድል (3) የውጭ ምንዛሪ በቅድሚያ የማግኘት እድል (4) የመንግስት ጨረታን ያለውድድር የማግኘት እድል (5)የሃገር ውስጥና የውጭ ገበያ የማግኘት እድል (6)የመሬት ጥያቄ ለመንግስትና ለግሉ ዘርፍ ለተሰማሩ አድሎ መኖር (7) የመንግስት ግብር በመንግስታዊና በግሉ ዘርፎች ያለ ልዩነት (8) በብሔራዊ ባጀት ‹የመንግስት የልማት ድርጁቶች› አጠቃላይ ባጀት ይገለፃል እንጂ የተናጥል ባጀታቸው ለህዝብ ይፋ አለመደረግ፣ እንዲሁም የኦዲት ሪፖርት ከኢትዩጵያ ዓየር መንገድ በስተቀር የሌሎቹ ‹መንግስታዊ ልማት ድርጅቶች› ተደርጎ አይታወቅም፡፡ እነዚህ ድርጅቶችን በቦርድ የሚያስተዳድሩት የህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ሹማምንቶች፣ የፖለቲካ ካድሬዎችና የጦር ጀነራል መኮንኖች ሲሆኑ በትምህርትና በእውቀት ነፃ ውድድር የተያዘ ሥራ ባለመሆኑ ብዙዎቹ ለኪሳራ ይዳረጋሉ፡፡

በኢትዩጵያና ሌሎች ታዳጊ አገሮች ውስጥ የመንግስት ልማት ኢንተርፕራይዝና ኮርፖሬሽኖችን  ንብረቶች ወደ ግሉ ዘርፍ መተላለፍና መሸጥ ዋነኛ ምክንያቶች መኃል፣ የገንዘብ አያያዝ ብክነትና ሙስና  በየግዜው እየጨመረ መሄድ፣ንብረቶቹን የማስተዳደር ብቃት ደካማነት በዚህም ምክንያት በየአመቱ የመንግስት ድጎማ  እየተደረገላቸው በኪሳራ መስራታቸው ነው፡፡ የመንግስታዊ ፋብሪካዎች አስተዳደራዊ ስርዓት በዘመዳ ዘመድ ሥራዎች መጠመድ፣ በሙስና መጨማለቅና ነፃ የገበያ ስርዓት በመክላት ሃገሪቱን ወደ እዝ ኢኮኖሚ በመዝፈቅ፣ ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍና አልባ የማፍያ ስርዓት ዛሬም ተክለዋል፡፡

ከወታደራዊ መንግስት ንብረትነት ወደ ሕወሃት መንግስት ንብረትነት ሽግግር  ከፕራይቨታይዜሽን ስም የተሸጋገሩ በተለይ፣የመከላከያ ሠራዊቱና የደህንነት ከፍተኛ ሹማምንቶች በተለይ ጀነራል መኮንኖቹና ሹማምንቱ በመለስ ዜናዊ ፍልስፍና  ሠራዊቱ ለህወሃት መንግስት ታማኝ ሆኖ እንዲቀጥል በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በመግዛት፣መኖሪያ ቤት፣ሁለት ሦስት መሬትቶች እንዲሸጡና ቤት እንዲሰሩ በማመቻቸት፤ ከአንድም ሁለት ሦስት መኪኖች ለቤተሰባቸው መጠቀሚያ ጭምር በመስጠት፣ሲታመሙ ውጭ ሃገር ልኮ በማሳከም፣ለበታች ሹማምንቶችም ኮንዶሚኒም ቤቶች ገንብቶ በመስጠትና የቤት መስሪያ ቦታ በመስጠት ይደልላሉ፡፡ በወታደራዊ መንግስት ከግለሰብ ኢንቨስተሮች የተወረሱትን ንብረቶች ወደ ሕወሃት መንግስት ንብረትነት በማሸጋገር የሜቴክ ዓይነት ድርጅቶች በማቆቆም  የህወሃት ጀነራል መኮንኖችና ሹማምንቶችን በንግዱ ዓለም በማስመጥ፣ በሙስና በማጥመቅ፣ በዘመዳ ዘመድ በመጠቃቀም፣ ህዝቡን አፍኖ በመግዛት የስልጣን መንበራቸውን ማስጠበቅ ዋነኛ ዓለማቸው ነው፡፡

በዚህም ምክንያት በብዙ ታዳጊ አገሮች የፕራይቤታይዜሽን ሽግግር በብቃት፣ በእኩልነትና በግልፅነት ለማካሄድ አስፈላጊው ግዜና ጥናት ባለመካሄዱ የተኮላሸ ለመሆን በቅተዋል፡፡ በታዳጊ አገሮች ውስጥ የገበያ ውድድር ያለመኖር፣የመዋለ-ንዋይ ፍሰት ደካማነት፣ የፋይናንሻል ሃብት እጥረትና የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወተው ሚና ደካማነት ወዘተ ተደማምሮበት የፕራይቬታይዜሽን ሽግግር የተጨናገፈ ለመሆን በቅቶል፡፡ በኢትዬጵያ የፕራይቬታይዜሽን ሽግግርና ሂደት በቂ በሆነ የአገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ባለመሳተፋቸው ምክንያት አብዛኛዎቹ የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና  ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ኢፈርት፣ሜቴክና ሜድሮክ የመሳሰሉ ካንፓኒዎችና ንብረትነት ማዘዋወራቸው የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ያገለለና ያለ ገበያ ውድድር ለጥቂቶች ያለዋጋቸው የተቸበቸቡ የህዝብ ንብረቶች መሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በኢትዬጵያ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ዓላማዎች፣እንደ አዋጅ ቁጥር 146/1998 አንቀፅ 3 መሠረት ዋና ዓላማዎች ውስጥ፣ መንግስት ለሚያከናውነው የምጣኔ ሃብት እድገት የገቢ ምንጭ በመሆን የገንዘብ ፍሰቱን በቀጣይነትና በዘላቂነት ማጠናከር፣የመንግስት በሃገሪቱ ኢካኖሚ እድገት ሚናና ተሳታፊነት እንዲጎለብት በማድረግ ትልቅ አስተዋፅዖ ማድረግ፣እንዲሁም መንግስት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን የግል ዘርፉን ኢኮኖሚ ለማበረታታትና ለማስፋፋት የሚል ቢሆንም ከደርግ ወደ ህወሃት መንግስትዊ ሞኖፖሊነት የተሸጋገረ ኃብት ለመሆን በቅቶል፡፡

በኢትጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ከ1996 እስከ ዲሴንበር 2000 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 166 የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና ንብረቶች ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነት ተዘዋውረዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 130ዎቹ በሜድሮክና ግለሰቦች ተገዝተዋል ከነዚህ ውስጥም 45ቱ ለኢህአዲግ አዲስ ፋና ድርጅት ሠራተኞች ተሸጠዋል፣10 በቢዝነስ ድርጅቶች፣36 ኢንተርፕራይዝ በመንግስትና መንግስታዊ በሆኑ ድርጅቶች በመከላከያ ሚኒስትር ስር ለተkkመው ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተሰጥተዋል፡፡

በኢትጵያ በግሉ ዘርፍ፣ በብረታ ብረትና ፋብሪካዎች ግንባታ ኢንቨስትመንት ላይ የተሳተፉ ከሃያ አራት በላይ ባለሃብቶችን በውጭ ምንዛሪ ችግር ይሰቃያሉ፣በኤሌትሪክ ኃይል እጥረት(63 በመቶ)፣ከውጭ በሚገባ ተመሳሳይ ምርቶች ውድድር(61 በመቶ)፣ ዝቅተኛ የሰው ሃብት ልማት/የእውቀት ደረጃ መኖር(70 በመቶ)፣የምርምርና የልማት ጥናቶች ያለመኖር(80 በመቶ)፣ከሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ትብብርና ድጋፍ ማጣት እዲሁም የምርት አቅርቦታቸውን ለሃገር ውስጥ የግንባታ ዘርፍ ለማቅረብ ያለ ራዕይና የቴክኖሎጂ ሽግግር/ ልውውጥ አለመኖር በብረታ ብረት ኢንደስትሪ የግል ዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን  ለኪሳራ የዳረጋቸው አንካüር አንካüሮቹ ችግሮች እንደሆኑ ጥናቱ አመላክቶል፡፡ለዚህ ይመስላል የግል ባለሃብቶቹ ‹‹ትልቁ ዓሣ ጥንንሾቹን ዓሣዎች ዋጦቸው›› በማለት ምሬታቸውን የሚገልፁት፡፡የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰው አልባ ድሮውን(ሰው የሌለው የጦር አውሮፕላን ሰራን ብለው)በኢትዩጵያ ቴሌቪዝን የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ይታወቃሉ፡፡ሜቴክ አውቶብስ፣ መኪናና ትራክተር ከመገጣጠም ያለፈ  ይሄ ነው የተባለ ሥራ አልሰራም!!! የድሮውን ሥራ ቀርቶብን የገበሬውን የእርሻ መሣሪያዎች ብታሻሸሉ ምን ያህል በተመሰገናችሁ ነበር!!!

“Ethiopia produces first military drone aircraft:-February 14, 2013 (ADDIS ABABA) – An Ethiopian military source has told Sudan Tribune that the country has built the first unmanned aerial vehicle (UAV) or drone which could be used for multiple purposes. After undergoing testing, the locally made drones, have demonstrated their capability of performing a number of militarily and civilian applications, according to the source.”

ምንጭ ድረ-ገፆች (Reference Websites)

 1. Ethiopia celebrates its first solar panel | PV-Tech, pv-tech.org/…/ethiopia_celebrates_its_first_solar_panel

‎ Cached

29 Jan 2013 … Project developer SKY Energy International and Metals Engineering … are
celebrating the fabrication of the first solar panel in Ethiopia.

 1. The Grand Renaissance Hydroelectric Project – Power Technology, power-technology.com/…/the-grand-renaissance-hydroelectric-project/

‎ Cached

The project is located around 750km northwest of the Ethiopian capital Addis …
increasing the current electricity generation capacity of Ethiopia by four times. …
Metals & Engineering Corporation (METEC) of Ethiopia is responsible for the …

 1. The Grand Renaissance Dam – Ethiopia’s greatest risk – Power …, power-technology.com/…/featuregrand-renaissance-dam-ethiopia- greatest-risk/

‎ Cached

25 Feb 2013 … Ethiopian dams could dry up the lakeIn April 2011 Ethiopia unveiled its … Power
Technology Market & Customer Insight Log In · Request Demo · About … will
boost Ethiopia’s economy by enabling it to export energy all throughout Africa. …
Power Corporation contracted the military-run Metals & Engineering …

 1. [PDF]Basic Metal and Engineering Industries (BMEIs): International …, grips.ac.jp/forum/af-growth/support_ethiopia/…/BMEIs.pdf

‎ Cached

Ethiopia’s BMEI policy framework: (1) PASDEP II – trade and … from ore, scrap
and conversion of billet, slab etc.into primary metal products Strategy:sector
and technology.▫Mid-termHigher Education,Energy,Mineral Resources…

 1. [PDF]Critical Metals in Strategic Energy Technologies – Oakdene Hollins, oakdenehollins.co.uk/media/242/CriticalMetalsinSET.pdf

Similar

Critical Metals in Strategic Energy Technologies. 5. bottleneck to the
deployment of low-carbon energy technologies.African producing countries
are Democratic Republic of Congo, Ethiopia, Mozambique, Nigeria, Rwanda and
Uganda.

 1. Ethiopia’s Metals and Engineering Corporation to Receive Solar …, com/…/ethiopia-s-metals-and-engineering-corporation-to-receive-solar -as

‎ Cached

12 Apr 2012 … Ethiopia’s Metals and Engineering Corporation to Receive Solar Assembly Line
… Spire Corporation is a diversified company serving the solar energy, …
products and services based upon a common technology platform.

 1. 600 m contract awarded for Ethiopian steel plant development,engineeringnews.co.za/article/ethiopia-2012-12-07

‎ Cached

7 Dec 2012 … $600m contract awarded for Ethiopian steel plant development … that offered us
high-quality European technology with a Chinese price,” says Al-Amoudi. …
including manufacturing, agriculture, energy, mining, tourism  nd …

 1. African Review , africanreview.com/ ‎ Cached

The South African parliament’s portfolio energy committee has requested the
legislature to ratify a … Standard Bank to use Watson technology for South Africa

 1. Macroeconomic Handbook in 2011/2012፡ Access Capital’s
 2. The author is graduate student at John Hopkins University. Email: ethiopia.capitalmarkets@gmail.com

11.http:://www.ppesa.gov.et/

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በአውሮፓ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተሰገሰጉትን አሻጥረኞች የዲሞክራሲ ጠላቶች ይመንጥሩልን

Ethiopian Embassy in Berlin.

Ethiopian Embassy in Berlin.

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ

እኛ በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገራችን በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ እየደገፍን እና እያበረታታን በመቀጠልም በአገራችን በሚካሄደው የዲሞክራሲ ግንባታ የሰባአዊ መብት መከበር እንዲሁም የሃገር ግንባታ ለመሳተፍ በከፍተኛ መነሳሳት ላይ ብንሆንም
በተንኮል የታነጹት በአየር ባየር ንግድ የተጠመዱት ኢትዮጵያውያንን ሲሰድቡ ሲያሰድቡ ሲሰልሉ ሲያሰልሉ ሲጠቁሙ እና ሲያስጠቁሙ የነበሩ የኢትዮጵያ ህዝብ እየተራበ አገራችን ኢትዮጵያ በሌላት የውጭ ምንዛሪ እየተከፈላቸው ምንም ሳይሰሩ ኢትዮጵያውያንን ሲከፋፍሉ የኖሩ ያሮጌው ዘመን ቁማርተኞች ተላላኪዎች እና አሻጥረኞች በአውሮፓ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተሰገሰጉ አሻጥረኞች የዲሞክራሲ ጠላቶችን ሙሉ በሙሉ ይመንጥሩልን።

ስራቸው እየዞሩ ኢትዮጵያውያንን መከፋፈል እንዲሁም ያየር ባየር ንግድ እና የሌብነት ስርዐት እንዲጧጧፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ሲከፋፍሉ ሲያመናጭቁ እና ሲያሸማቅቁ የነበሩ ተግባራቸው እየዞሩ ካደራጁዋቸው ግብረዓበሮቻቸው ጋር እድር እና ሰንበቴ ሲበሉ የከረሙ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኤንባሲዎች የተሰገሰጉ አሻጥረኞች አምባሳደር ካውንስለር እና የዲያስፖራ ክፍል ተብዬዎችን ይመንጥሩልን።

እነዚህ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኤንባሲዎች ኢትዮጵያውያንን ሲያንገላቱ የነበሩ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በሰሩት ሻጥር ግብረዓበሮቻቸውን በመሰብሰብ ብዙሃኑን ለሃገራቸው ቅን አሳቢ ኢትዮጵያውያንን ለስሙ በመጥራት በዋናነት ግን በማግለል በቅርቡ እ.አ.አ October 31 2018 በፍራንክፈርት ጀርመን እርስዎን ለመቀበል ከእርስዎ ጋር ለመወያየት በጉጉት ይጠብቁ የነበሩትን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ወደ ዘግጅቱ ቦታ እንዳይገኙ አድርጓል የተገኙትንም አጉላልቱዋል አሳዝኖዋል አበሳጭቶዋል። ይህ ባይሆን ኖሮ የዝግጅቱ ቦታ ጠቦ ኢትዮጵያውያን ውጭም ቆመው በደስታ በተቀበልዎት ነበር።

በቀጣይነት እኛ በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገራችን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ እና ቀጥታ ተሳትፎ ማድረግ እንድንችል ኢትዮጵያውያን በማሳደድ በመሰለል እና በመከፋፈል የሃገር ዘራፊዎችን ሲያስተናግዱ ሲያገለግሉ እና ሲገለገሉ የኖሩ በድህነት ከሚሰቃየው ህዝባችን ጉሮሮ ተነጥቆ በሚከፈላቸው የውጭ ምንዛሪ ሃገራቸውን እና ህዝባቸውን የበደሉ የሃገር ጠቃሚ ሳይሆን ጫና የሆኑትን ችሎታ ቢሶች አሻጥረኞች የዲያስፖራ ጉዳይ ሃላፊ እና ካውንስለር ተብዬዎች ጠራርገው ያጽዱልን።

አሁንም በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገራችን ጉዳይ ላይ አዎንታዊ ሚና እንዳይኖረን በማግለል በመጠራጠር በግፍ ዘመን ከኤምባሲው ጋር ሲሞዳሞዱ ከነበሩ ያሮጌው ዘመን ቁማርተኞች እጅ ነሺዎች ጋር ተቆራኝቶ የሚሰራውን የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአውሮፓ ያጽዱልን።

አሳዳጅ እና ተሳዳጅ ተጠርጣሪ እና ተገላይ በሆነ ስነ ልቦና ላይ በተመሰረተ ግንኙነት ባገራችን ጉዳይ መሳተፍ ስለማንችል በመተማመን የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዲሳካ ሲጀመር ስነልቦናቸው በመተማመን ሳይሆን በመጠራጠር እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በማሰባሰብ ሳይሆን በመከፋፈል ሴራ ላይ የተካኑትን እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሲያጉላሉ እና ሲያሰቃዩ የነበሩትን አሻጥረኞች የኢትዮጵያ ኤምባሲ አባሎች በአውሮፓ ካሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአፋጣኝ ያጽዱልን።

ከአክብሮት ጋር
የለውጡ ደጋፊዎች
በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን

የአቶ አደም ሀሚድ ሱሌማን እና ሜቴከ የዘረፋ ሽርክና (ሚክይ ዓምሃራ)

አደም ሀሚድ ሱሌማን ኦሪጅናሊ ኤርትራዊ ሲሆን የካናዳ ዜግነት አለው ዱባይ የሚኖር ሲሆን ኤርትራ ስትገነጠል አሰብና ምጽዋ የነበሩ መርከቦችን ከኤርትራ መንግስት ጋር በመመሳጠር እጁ አስገብቶ የመርከብ ባለቤት የሆነ ግለሰብ ነው። በህግ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ብቸኛ import export አጓጓዥ ከመሆኑ በፊት ዝቅተኛ የጭነት ዋጋ በመጠቀም ንግድ መርከብን ከጭዋታ ውጭ አድርጎት ነበር በአንድ ወቅት የኢንሹራንስ ብር ለማግኘት ሲል አንዷ መርከብ መኪና ጭና ወደ ምጽዋ ወደብ ስታመራ በእቅድ እንድትሰጥም ካደረገ በኃላ ብዙ የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሀብት አክስሯል ከኢትዮጵያም ከኤርትራም መንግስት ጋር ተጣልቶ ዱባይ ይኖር ጀመር ከጊዜ በኃላ ኢንቨስተር ተብሎ የቀድሞው ያኮና ኢንጅነሪንግን ከንግድ ባንክ ላይ ያለ ጫረታ በ 1 ሚሊየን ዶላር ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ መጣ እስከ አሁን ድረስ የቀድሞው ያኮና ኢንጅነሪንግ የአሁኑ ኢንተር ኤመሬት ኢንደስትሪ ተብሎ ከሜቴክ ያለ ጨረታ ስራ እየተሰጠው የትራንስፎርመር ቦዲ እና ብዙ ስራውችን ከሜቴክ ሰዎች ጋር በሽርክና ይሰራል።

አደም 50 ሺ ዶላር የሚገዛን እቃ 250 ሺ ብሎ ፕሮፎርማ በማሰራት ዱባይ ወደ ሚገኘው ናሮ ትሬዲንግ ወደሚባለው ወደ ራሱ ድርጅት ዶላር ያሸሻል ከሜቴክ የሚያገኘውን ብር በዚህ መልኩ ወደ ዱባይ ያሸሻል ከሜቴክ ሰዎች ጋር የጥቅም ተጋሪ ሆነው ይሰራሉ ። ድርጅቱ ግቢ ውስጥ የአቶ አደም መኖሪያ ቤት አለ እና እዚህ ቤት ውስጥ ትልልቅ እቅዶች ይነደፋሉ አደም ይመክራል እነሱ ተግባራዊ ያደርጋሉ ። አደም ከየትኛውም አለም ምንም አይነት ነገር መስራት የሚችል ኮንታክትም አለው ብርም አለው። ከመድሀኒት እስከ ጦር መሳሪያ እና አውሮፕላን ድለላ ይሰራል።

አደምን ብሄራዊ ባንክ በዶላር ማዘዋወር ምክንያት ብላክ ሊስት ዉስጥ አስገብቶታል፡፡ ይህች አዉሮፕላን የሳውድ አረቢያው የቀድሞው ልኡል የግል አውሮፕላን ናት መጀመሪያ ለፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ሊሸጥለት በ ጻድቃን በኩል ብዙ ተሞከረ ግን ስላረጀች ጻድቃን ዋጋዋ ተወደደ ብሎ ከፈረንሳይ አዲስ እንድትገዛ ምክር በመስጠቱ የሱዳኑ ሳልቫኪል ሳይገዛት ቀረ ከዛ ክንፈን ግዛት ብሎ አደም ማግባባት ጀመረ ከዛ ክንፈ ወደዚህ ስራ ገባበት፡፡ ከአዉሮፕላኗ ስር ፎቶ ሚነሳዉ አደም ሲሆን ፎቶ አንሽዉ ትናንት ከሁመራ ያመጣነዉ ሰዉየ ነዉ፡፡

በነገራችን ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ጉዳይ ZTE እና አንድ ሌላ ድርጅት ማስፋፊያ ተብሎ የመጣዉ 5.5 ቢሊየን ዶላር ጉዳይ እየመረመርኩት ነዉ ፡፡ ጉዱ ብዙ ነዉ፡

አሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኤምባሲውን “ኤምባሲያችን” እያሉ ሲጠሩ መስማት የብርቅ ያህል እየሆነ ነው

ጊዜ ተለውጧል። አሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኤምባሲውን “ኤምባሲያችን” እያሉ ሲጠሩ መስማት የብርቅ ያህል እየሆነ ነው።

ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያን ምግብና ባሕል ለማስተዋወቅ ያሰበበትን ዝግጅት እዚያው በኤምባሲው ውስጥ አካሂዷል።በዝግጅቱ ላይ ኤምባሲው ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች ባለቤቶችና በማኅበረሰቡ ሕይወት ውስጥ በንቃት ሲሣተፉ ቆይተዋል ላላቸው ግለሰቦችና ተቋማት የዕውቅና የምሥክር ወረቀት ሰጥቷል።አሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኤምባሲውን “ኤምባሲያችን” እያሉ ሲጠሩ መስማት የብርቅ ያህል እየሆነ ነው።በቀደመ ጊዜ ስፋት ያለው ኢትዮጵያዊና ትውልደ-ኢትዮጵያ የመጋበዝና ያንን ያማረ፣ በኢትዮጵያ ኃብትና ቁሳቁስ የተገነባ ሕንፃ እንደራሱ ንብረት አድርጎ ማየት ዘበት ነበር።አሁን ግን ጊዜ ተለውጧል።