ሻሽመኔ በአክራሪ ኦህዴዶች እስከተዳደረች ድረስ የሚለወጥ ነገር አይኖርም #ግርማ_ካሳ

እንደገና በሻሸመኔ የሆነውን አንገት የሚያስደፋ አሳፋሪ ድርጊትን የሚያሳይን ፎቶ ብቻ እንጂ ቪዲዮ ማሳየቱን አልፈለኩም። በጣም ማየቱ ስለሚከብድ።

ሻሸመኔ የፍቅር ከተማ ናት። አማራው ጉራጌው፣ ሲዳማው፣ ከንባታው፣ ኦሮሞው ….ሁሉም በሰላምና በፍቅር የኖሩባት ከተማ። የከተማዋ ሕዝብ ሕብረ ብሄራዊ ነው። አብዛኛውም ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው። ሆኖም ከተማዋ የኦሮሞ ናት በሚል በኦሮሞ ክልል ስር እንድትሆን ተደርጋለች። ከተማዋን ከላይ እስከ ታች የሚያስተዳድሯት፣ በከተማዋ ማይኖሪቲ የሆኑት ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው። ልክ እንደ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጂማ፣ አሰላ..እንዳሉ ከተሞች ማለት ነው።

አብዛኛው የሻሸመኔ ነዋሪን የሚወክል አስተዳደር ባለመኖሩ፣ በሌሎች ማህበረሰባት ላይ አድልዎ፣ በደል፣ ግፍ ሲፈጸም ፣ የዘር ልዩነት ሲደረግ፣ ለሌሎች ማህበረሰባት የሚቆም አካል የለም። ልክ በደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ዘመን ለጥቁሮች መብት የሚቆም በአፓርታይድ የመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ እንዳልነበረው ሁሉ። ያኔ ነጮች በጥቁሮች ላይ ግፍ ሲፈጸሙ የሚከለክላቸው፣ የሚቀጣቸው የበላይ አካል አልነበረምና።

በሌሎች የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች እንደሚታየው በሻሸመኔም ጥቂት የኦሮሞ አክራሪ ቄሮዎች የፈለጉትን ሲያደርጉ፣ የፈለጉትን ሲገድሉ፣ ሲያስሩ ለምን የሚላቸው አካል የለም። የከተማዋ የኦህዴድ/አዴፓ አመራሮች ሕዝቡን የማይወክሉ ከነዚህ ከጃዋር አክራሪዎች ጋር  የሚያብሩ ናችው። በመሆኑም በሻሸመኔ እነዚህ ጽንፈኞች ከሕግ በላይ ሆነዋል።

የከተማዉን ህዝብ የሚወክል የከተማ ፖሊስ ሃይል፣ የከተማዋን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ የከተማዋ አስተዳደር ቢኖር ኖሮ፣ ሻሸመኔ እንደዚህ አትሆንም ነበር። አሁን ግን የሻሸመኔን ሕዝብ የማይወክሉ ጥቂት የኦሮሞ ዘረኛ ግሩፖሽ ከተማዋን ስለያዙና በሃላፊነት ላይ ስልተቀመጡ  ከተማዋ የወንበዴ ከተማ ሆናለች።

ከዚህም የተነሳ የአክራሪ ቄሮ መሪን ጃዋርን ለመቀበል በሻሸመኔ ተሰባስበው በነበረበት ወቅት፣ አንድ ማንጎ የሚሸጥ የሻሸመኔን ድሃ ነዋሪን፣ ቦንብ ነው የያዘው ብለው ቄሮዎች ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ዘቅዝቀው መግደላቸውና ሌሎች ይሄንን ድርግቲ ከማስቆም፣ በሆታና በጭብጨባ ሲያዳምቁት እንደነበረ የሚታወስ ነው። የኦህዴዶች የአካባቢው አመራሮች፣ ወንጀለኞች አሰርን ብለው መግለጫ ሰጥተው ነበር።፣ ግን ይሄን ጊዜ በርግጥ ስለማሰራቸው ወይንም አስረው ከሆነ እነርሱ መልሰው ቅጣት ብዙ ሳይቀጡ ፈተዋቸው ሊሆን እንደሚችል የሚታወቅ ነገር የለም።

አሁን ደግሞ እነዚሁ አክራሪ ቄሮዎች ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ሽማግሌዎችን ሲደበደቡ እያየን ነው። ዜጎች ተዘቅዝቀው ሲሰቀሉ ፣ እንደ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ምልክት ተወስዶ እርምጃዎች ቢወሰዱ ኖሮ፣ በሻሸመኔ የሕግ የበላይነት ቢከበር ኖሮ ፣ በሻሸመኔና አካባቢዋ ያሉ የኦህዴድ/አመራሮች ከሃላፊነታቸው ቢነሱ ኖሮ፣ አሁን የታየው ባልታየ ነበር። ቄሮዎች ለሕግ ተጠያቂ እስካልሆኑ ድረስ፣ ከኛ በላይ ማንም የለም የሚል ስሜት እስካላቸው ድረስ፣ የአካባቢዎቻቸው የኦህዴድ/ኦዴፓ አመራሮችና ፖሊሶች ከነርሱ ጋር እስካሉ ድረስ ፣ ወይንም በጎናቸው ባይቆም እነርሱ ላይ እርምጃ ለመዉሰድ እስካልፈልጉ ድረስ የሚሻሻል ሆነ የሚስተካከል ነገር አይኖርም።

የሻሸመኔ ሕዝብ ከነዚህ ጉጅሌዎች ነጻ መውጣት አለበት። እየፈራ፣ እየተገደለ፣ እየተደበደበ የሚኖሩበት ምንም ምክንያት የለም። ሻሸመኔ በሻሸመኔ ነዋሪዎች መተዳደር አለባት። በከተማዋ ያሉ ኦሮሞዎች፣ ያዉም አካራሪ ኦሮሞዎች ብቻ ከተማዋን የሚያስተዳድሩበት ምንም ምክንያት የለም። ለለዚህ ፍትህ ለሻሸመኔ !!!!! ነጻነት ለሻሸመኔ !!! እላለሁ።

በአዋሳም ተመሳሳይ ችግር አለ። ኢጄቶ በሚሉ ተፈጥሮም ነበር። በኔ እይታ ሻሸመኔ፣ ወንዶገነትና አዋሳ ፣ የፌዴራል ልዩ ዞን መሆኑ ለአዋሳም፣ ለሻሸመኔ፣ ለወንዶገንትም እዚያ አካባቢ ለሚኖረው ሁሉም ማህበረሰብ የሚጠቅም ነው። ከሻሸመኔ፣ አዋሳ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ ነው። ጎን ለጎን ናቸው በአዋሳ የሚኖረው ሕብረብሄራዊ ማህበረሰብ። በሻሸመኔ የሚኖረው ሕብረ ብሄራዊ ማህበረሰብ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s