ሻሽመኔ በአክራሪ ኦህዴዶች እስከተዳደረች ድረስ የሚለወጥ ነገር አይኖርም #ግርማ_ካሳ

እንደገና በሻሸመኔ የሆነውን አንገት የሚያስደፋ አሳፋሪ ድርጊትን የሚያሳይን ፎቶ ብቻ እንጂ ቪዲዮ ማሳየቱን አልፈለኩም። በጣም ማየቱ ስለሚከብድ።

ሻሸመኔ የፍቅር ከተማ ናት። አማራው ጉራጌው፣ ሲዳማው፣ ከንባታው፣ ኦሮሞው ….ሁሉም በሰላምና በፍቅር የኖሩባት ከተማ። የከተማዋ ሕዝብ ሕብረ ብሄራዊ ነው። አብዛኛውም ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው። ሆኖም ከተማዋ የኦሮሞ ናት በሚል በኦሮሞ ክልል ስር እንድትሆን ተደርጋለች። ከተማዋን ከላይ እስከ ታች የሚያስተዳድሯት፣ በከተማዋ ማይኖሪቲ የሆኑት ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው። ልክ እንደ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጂማ፣ አሰላ..እንዳሉ ከተሞች ማለት ነው።

አብዛኛው የሻሸመኔ ነዋሪን የሚወክል አስተዳደር ባለመኖሩ፣ በሌሎች ማህበረሰባት ላይ አድልዎ፣ በደል፣ ግፍ ሲፈጸም ፣ የዘር ልዩነት ሲደረግ፣ ለሌሎች ማህበረሰባት የሚቆም አካል የለም። ልክ በደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ዘመን ለጥቁሮች መብት የሚቆም በአፓርታይድ የመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ እንዳልነበረው ሁሉ። ያኔ ነጮች በጥቁሮች ላይ ግፍ ሲፈጸሙ የሚከለክላቸው፣ የሚቀጣቸው የበላይ አካል አልነበረምና።

በሌሎች የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች እንደሚታየው በሻሸመኔም ጥቂት የኦሮሞ አክራሪ ቄሮዎች የፈለጉትን ሲያደርጉ፣ የፈለጉትን ሲገድሉ፣ ሲያስሩ ለምን የሚላቸው አካል የለም። የከተማዋ የኦህዴድ/አዴፓ አመራሮች ሕዝቡን የማይወክሉ ከነዚህ ከጃዋር አክራሪዎች ጋር  የሚያብሩ ናችው። በመሆኑም በሻሸመኔ እነዚህ ጽንፈኞች ከሕግ በላይ ሆነዋል።

የከተማዉን ህዝብ የሚወክል የከተማ ፖሊስ ሃይል፣ የከተማዋን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ የከተማዋ አስተዳደር ቢኖር ኖሮ፣ ሻሸመኔ እንደዚህ አትሆንም ነበር። አሁን ግን የሻሸመኔን ሕዝብ የማይወክሉ ጥቂት የኦሮሞ ዘረኛ ግሩፖሽ ከተማዋን ስለያዙና በሃላፊነት ላይ ስልተቀመጡ  ከተማዋ የወንበዴ ከተማ ሆናለች።

ከዚህም የተነሳ የአክራሪ ቄሮ መሪን ጃዋርን ለመቀበል በሻሸመኔ ተሰባስበው በነበረበት ወቅት፣ አንድ ማንጎ የሚሸጥ የሻሸመኔን ድሃ ነዋሪን፣ ቦንብ ነው የያዘው ብለው ቄሮዎች ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ዘቅዝቀው መግደላቸውና ሌሎች ይሄንን ድርግቲ ከማስቆም፣ በሆታና በጭብጨባ ሲያዳምቁት እንደነበረ የሚታወስ ነው። የኦህዴዶች የአካባቢው አመራሮች፣ ወንጀለኞች አሰርን ብለው መግለጫ ሰጥተው ነበር።፣ ግን ይሄን ጊዜ በርግጥ ስለማሰራቸው ወይንም አስረው ከሆነ እነርሱ መልሰው ቅጣት ብዙ ሳይቀጡ ፈተዋቸው ሊሆን እንደሚችል የሚታወቅ ነገር የለም።

አሁን ደግሞ እነዚሁ አክራሪ ቄሮዎች ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ሽማግሌዎችን ሲደበደቡ እያየን ነው። ዜጎች ተዘቅዝቀው ሲሰቀሉ ፣ እንደ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ምልክት ተወስዶ እርምጃዎች ቢወሰዱ ኖሮ፣ በሻሸመኔ የሕግ የበላይነት ቢከበር ኖሮ ፣ በሻሸመኔና አካባቢዋ ያሉ የኦህዴድ/አመራሮች ከሃላፊነታቸው ቢነሱ ኖሮ፣ አሁን የታየው ባልታየ ነበር። ቄሮዎች ለሕግ ተጠያቂ እስካልሆኑ ድረስ፣ ከኛ በላይ ማንም የለም የሚል ስሜት እስካላቸው ድረስ፣ የአካባቢዎቻቸው የኦህዴድ/ኦዴፓ አመራሮችና ፖሊሶች ከነርሱ ጋር እስካሉ ድረስ ፣ ወይንም በጎናቸው ባይቆም እነርሱ ላይ እርምጃ ለመዉሰድ እስካልፈልጉ ድረስ የሚሻሻል ሆነ የሚስተካከል ነገር አይኖርም።

የሻሸመኔ ሕዝብ ከነዚህ ጉጅሌዎች ነጻ መውጣት አለበት። እየፈራ፣ እየተገደለ፣ እየተደበደበ የሚኖሩበት ምንም ምክንያት የለም። ሻሸመኔ በሻሸመኔ ነዋሪዎች መተዳደር አለባት። በከተማዋ ያሉ ኦሮሞዎች፣ ያዉም አካራሪ ኦሮሞዎች ብቻ ከተማዋን የሚያስተዳድሩበት ምንም ምክንያት የለም። ለለዚህ ፍትህ ለሻሸመኔ !!!!! ነጻነት ለሻሸመኔ !!! እላለሁ።

በአዋሳም ተመሳሳይ ችግር አለ። ኢጄቶ በሚሉ ተፈጥሮም ነበር። በኔ እይታ ሻሸመኔ፣ ወንዶገነትና አዋሳ ፣ የፌዴራል ልዩ ዞን መሆኑ ለአዋሳም፣ ለሻሸመኔ፣ ለወንዶገንትም እዚያ አካባቢ ለሚኖረው ሁሉም ማህበረሰብ የሚጠቅም ነው። ከሻሸመኔ፣ አዋሳ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ ነው። ጎን ለጎን ናቸው በአዋሳ የሚኖረው ሕብረብሄራዊ ማህበረሰብ። በሻሸመኔ የሚኖረው ሕብረ ብሄራዊ ማህበረሰብ።

የሕወሓት የፓርላማ አባላት የተቃወሙት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ አስፈጻሚው መንግሥት የቀረበለትን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን፣ ሐሙስ ታኅሳስ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በተለየ ሁኔታ የጋለ ክርክር አካሂዶ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።

በምክር ቤቱ መቀመጫ ያላቸው የሕወሓት አባላት ረቂቅ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ መፅደቅ የለበትም በማለት ከፍተኛ ክርክር አድርገዋል። የወሰንና የማንነት ጉዳይን የሚመለከት ሥልጣን በሕገ መንግሥቱ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠ በመሆኑ ተመሳሳይ ኃላፊነት ለኮሚሽኑ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ሞግተዋል።

አዋጁን በማፅደቅ ኮሚሽኑ እንዲቋቋም ማድረግ ሕገ መንግሥቱን በሁለት መንገድ እንደሚጣረስ አውስተው፣ አንድም የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን በመንጠቅ በሌላ በኩል ደግሞ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ያልተከተለ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ማድረግ መሆኑን በመጥቀስ ተከራክረዋል።

የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት የምክር ቤቱ አባል አቶ አጽብሃ አረጋዊ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረስ መሆኑን በመግለጽ ከተከራከሩ በኋላ፣ ‹‹በቀላሉ እንደሚፀድቅ እርግጠኛ ነኝ፣ ነገር ግን የሚያመጣውን ጣጣ ቆም ብለን ብናይ?›› ሲሉ ጠይቀዋል።

አቶ አጽብሃ ይህንን መናገራቸው በአንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ላይ ቁጣን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል የአዴፓ አባል የሆኑት የምክር ቤቱ አባል አቶ አጥናፍ ጌጡ ይገኙበታል።

አቶ አጥናፍ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹ጣጣ ያመጣል፣ አደጋ አለው የሚሉ ኃይለ ቃሎችና ማስፈራሪያዎችን መናገር ለዚህ ምክር ቤት አይመጥንም፣›› ሲሉ የግሳፄ ይዘት ያለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ይህ አዋጅ ለውጡ ያመጣው ዕድልና ለአገሪቱ ሕዝቦች ሰላም የሚሰጥ መሆኑንም አክለዋል።

ኮሚሽኑን እንዳይቋቋም የሚፈልጉ ወገኖች ኮሚሽኑ ሕገ መንግሥቱ የማይሸፍናቸውን የማንነትና የወሰን ጉዳዮች ጭምር ወደኋላ ሄዶ ያያል ከሚል ሥጋት እንደሚቃወሙት ጠቅሰው፣ ኮሚሽኑ ወደ ኋላ ሄዶ ሕገ መንግሥቱ የማይሸፍናቸውን ጉዳዮች ጭምር ሊመረምር እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በረቂቁ ላይ ዝርዝር ምርመራ በማድረግ የውሳኔ ሐሳብ ያቀረቡት የፓርላማው የውጭ ግንኙነትና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ የኮሚሽኑ መቋቋም ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንደማይጣረስ፣ እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ሥልጣን እንደማይጋፋ ተናግረዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቋሚ ኮሚቴው በኩል በረቂቅ አዋጁ ላይ አስተያየቱን እንዲሰጥ መደረጉን የተናገሩት አቶ ተስፋዬ ኮሚሽኑ መረጃ የመሰብሰብ፣ የመተንተንና ለሚመለከታቸው አካላት ምክረ ሐሳብ የማቅረብ ኃላፊነት ብቻ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነበት ምክረ ሐሳቡን ሊቀበል እንደሚችል፣ በራሱ መንገድም ተመሳሳይ ኃላፊነት ያለው ኮሚሽን ወይም ተቋም እንዳያቋቁም የሚከለክለው ነገር ባለመኖሩ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንደማይጣረስ አስረድተዋል።

ሌሎች የምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት ደግሞ የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱና ሲኮላሹ የሕገ መንግሥት ጥሰት ጥያቄ ሳይነሳ፣ ለሰላም ፋይዳ ያለው ኮሚሽን እንዳይቋቋም የሕገ መንግሥት መጣረስን እንደ ምክንያት ማቅረብ እንደማይገባ በመግለጽ ተከራክረዋል።

አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በቂ ክርክር እንደተደረገ ገልጸው ፓርላማው ወደ ድምፅ መስጠት የተሸጋገረ ሲሆን፣ በስብሰባው የታደሙት 33 የሕወሓት አባላት የተቃውሞ ድምፅ ሰጥተዋል።

አራት የደኢሕዴን አባላት ደግሞ የተዓቅቦ ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሠረት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

ሪፖርተር

በዝምታ ሊታለፍ የማይገባው የአቶ ዳውድ ኢብሳ መግለጫ (አሰፋ በድሉ)

በ12/04/2011 ዓ.ም በሁለት ሰዓቱ ዜና የሰማሁት መግለጫ ነው፡፡ለህወሃት ከበሮየን አቀብሉኝ የሚያስብል መግለጫ ነው፡፡ከሞት ይታደገዋልና፡፡በዝምታ የሚታለፍ አደለም ያልሁት በቀጥታ ሁላችንንም ኢትዮጵያውያንን የሚመለከትና የሚያሳስብ ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አልፎ አልፎ ጽሁፎችን የማትመውን ነገር ተወት አድርጌ ዝም ብየ ስለነበር ነው፡፡ይህም የተሻሉ ሰወች መኖራቸውን በማስተዋል አንባቢ ላለመሻማት፤ብጥብጡም በዛ በማለቱ የዕብድ ገላጋይ ላለመሆንና የለውጡን መሪወችም ስራ ላለማብዛት ነበር፡፡አሳሳቢ ጉዳይ ስለመሰለኝ ነው የተመለስሁ ለማለት ነው፡፡በዕርግጥ አልፎ አልፎ ጽሁፌ የአታሚወችን ኬላ ሳያልፍ ቀርቷል፡፡በዚህ ቅር አይለኝም፡፡ከእኔ እነሱ የተሻለ የማየት፤የማወዳደር እና የመገምገም ዕድልም፤መብትም አላቸው፡፡

ወደ መግለጫው ልመለስ-ከመግለጫው የተረዳሁት

1ኛ. ኦነግ ሰራዊቱ ወደ መከላከያ እንደሚቀላቀል ከመንግስት ጋር ስምምነት እንደነበረውና ይህም በመንግስት በኩል ተግባራዊ ባለመደረጉ ችግሮች እንደተከሰቱ፤2ኛ.ኦነግ የታጠቀ ሀይል እንዳለውና አቶ ዳውድ ኢብሳባይናገሩም እኔም የገባኝ ይህ ሃይል ከመንግስት ጋር ግጭት ውስጥ እንደገባ ነው 3ኛ. ጥያቄ እያቀረበ ያለ ህዝቡ  ነው የሚል ጥሪ አዘል መልክቶች ናቸው፡፡

ለውጡን በሚመለከት የአብሮነትን ጠቀሜታ፤የእኛን ልዩ ባህሪ፤አኗኗር ወዘተ…ሁሉም ልዩ፤ልዩ ተሰጥኦ ባላቸው ኢትዮጵያውያን መልካም የሚባሉ ቃሎች ተነግረው ስላለቁ እኔም እነሱን በመድገም አንባቢን አላሰለችም፤አቶ ዳውድም ጆሮ የሚሰጡኝ አይመስለኝም፡፡ነገር ግን ጠቅላያችን ወይም ሰብሳቢያችን የገለጹበትና አንዲሁም ዶ/ር አምባቸው በቅርቡ በአሜሪካ አዴፓ ልዑክ ጋር ባደረጉት ጉብኝት ያሰሙት ንግግር ለውጡ ለምን የሚያሳሳ፤አንደ እንቁላል እንክብካቤ እንደሚሻ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ለዚህም ነው በዚህስ እኔም ዝም አልልም ያልሁት፡፡ ጠቅላያችን ባላቸው የሚገርም ድልብ ስነ ቃል ና ውብ አገላለጽ በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር “እንቁላል ከውስጥ ሲሰበር ህይወት፤ከውጭ ሲሰበር ደግሞ ሞት ነው” በሚል ለውጡ ለሁሉም ወገን ጠቃሚ እንደሆነ ገልጸው ነበር፡፡የሚገባው ካለ ከዚህ በላይ ገላጭ አባባል አይገኝም፡፡ዶ/ር አምባቸው በድርጅቱ ውስጥ የነበረውን ሂደት ሲገልጹ “እኛም ማሸነፋችንን ሳናውቀው እነሱም መሸነፋቸውን ሳያውቁት ዶ/ር አብይን በመምረጥ” እንደተጠናቀቀ ነበር ያወሱት፡፡መቀሌ የእናቶቻቸው ቀሚስ ውስጥ በእርጅና የተደበቁት ጀግና ነን እያሉ ስንት የሸለሉት ተስፋ የቆረጥንባቸው ወንዶሞቻችን አልገባቸው አለ እንጂ ይህን እድል የቀደሙት የአገሪቱ መሪችና ድርጅቶች አላገኙትም፡፡አገር ሲጠብቅ ከጠላት ጋር ሲፋለም የኖረው መከላከያ እንኳን አላገኘውም፡፡በምን እንደተቋጨ ሁሉም የሚያውቀው ዘግናኝ ታሪካችን ነው፡፡ይህን ሽክርክሪት ለመስበር ነው በሚል ይመስለኛል የሁሉም ኢትዮጵያዊ የእንቁላል አሰባበርን ትርጉም የወደደው፡፡ከፍ ብዩ የገለጽሁትን ገለጻ አቶ ዳውድ እንደማይወዱልኝ እገምታለሁ፤ስለሆነም ከዕሳቸው ጋር በደረቁ እናውጋ፡፡አቶ ዳውድ ኢብሳን ያህል በፖለቲካ የኖረ ሰው ኦነግም የፖለቲካ ድርጅት መሆኑን፤ኢትዮጵያ ውስጥም ሌሎች ህዝቦች መኖራቸውን ዘንግቶ አሁን ያለው መከላከያ የኢህአዴግ ስለሆነ የኦነግ ሰራዊት ሊቀላቀልበት ይገባል የሚል ክርክር አሰምተው የምር ያደርጉታል ብሎ ማመን በጣም ይቸግራል፡፡ከእነ ድክመቱም ቢሆን በየቦታው እሳት እያጠፋ ያለ ሰራዊት ነው፡፡እናም እሱኑ መጠገን ይበጀናል፡፡ሰራዊቱ ሪፎርም ያስፈልገዋል ማለት አንድ ነገር ነው፡፡አንዱና ዋናውም የህዝብ ጥያቄ የነበረው ይህ አብይ ጉዳይ ነው፡፡ይህን በመገንዘብ ይመስለኛል ጠቅላያችን ለውጡ በዋናነት የተደረገው መከላከያ ውስጥ ነው በማለት ደጋግመው የሚገልጹት፡፡ይህንን ስስ ነገር በጣምም ከአወክነው ውጤቱም ይታወቃል፡፡ለውጥ እንደተደረገ ግልጽና የሚታይ ነው፡፡ምን ያህል ይቀራል ፈልፍሎ አውጥቶ ማቅረብ ነው፡፡ግን ለውጡ ቀስ ብሎ ለምሳሌ ጄኔራል ሳሞራን በጡረታና በሜዳሊያ አክብሮ መሸኝትን ጭምር ያካተተና ተሸናፊና አሸናፊነትን ያላነገሰ ሰብዓዊም ጭምር ስለሆነ ለውጥ የሌለ ሊመስል ይችላል፡፡ቀረ የተባለውን ደግሞ ከህብ ጋር ሆኖ የፖለቲካ ትግል ማድረግ ነው፡፡የትጥቅ ትግል አላልሁም፡፡የኦነግ ሰራዊት የኢትዮጵያ ሰራዊት ይሁን ማለት ደግሞ ፍጹም የተለየ ነገር ነው፡፡እንዲያው ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ ሆነ እንጂ ዛሬም መከላከያ የቅጥር ማስታወቂያ ሲያወጣ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ የምትለዋን አይረሳትም፡፡በዚህ አካሄድ እንዴት ገለልተኛ ጦር ሰራዊት፤ፍ/ቤት፤ደህንነት…ወዘተ እንደሚገነባ እርሳቸው ነው የሚያውቁት፡፡ኦሮሚያም ውስጥ እንኳን ያሉትን የፓርቲውች ቁጥር አያውቁትም እንዴ? የሽግግር መንግስት እንኳ እያቋቋምን ቢሆን አሁን የእሳቸው አቀራረብ በፖለቲካም፤በህግም ሲታይ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው፡፡ለመሆኑ ምንድን ነው ጥያቄአቸው? የቀድሞ የኦነግ ሰራዊትን መልሶ ስለማቋቋም ነው? ወይንስ የፖለቲካ ጥያቄ ነው? ምንድን ነው? የቀድሞው ሰራዊት ያልሁት አንድ በምርጫ የሚወዳደር ፓርቲ መቼም ሰራዊት ያለው እኔ አላውቅም፡፡ሁለቱ ምርኩዞች የሚላቸው ዶ/ር መራራ፡፡ሰራዊት ካለው ፓርቲ መሆኑ ቀርቶ አማጺ ወይንም መንግስት ይሆናል ማለት ነው፡፡መንግስት ደግሞ አለ፡፡የዴሞክራሲ ግንባታውን መሠረት ለመጣል እስከ አሁን ባየነው እየሰራ ነው፡፡ይኽው የዕርሶን መግለጫ እየሰማን አይደል በይፋ፤እርሶም እየተናገሩ እኮ ነው፤ እኔም ይመስገን እየጻፍሁ ነው፡፡ይቺን እናቆያት ባከወት! በዴሞክራሲ ከሳሪ የለም፡፡ስልጣንን ከምርጫ ውጪ ማሰብ ውጤቱ መቀሌ መደበቅና ህዝብንም ችግር ውስጥ መክተት ነው ትርፋ፡፡ፈረሱም ያው ሜዳውም ያው ተብሎ የለ እንዴ፡፡በዕርግጥ እኛ ቸር አሰማን እያልን እንጂ እርሶ የታጠቀ ሃይል እንዳለ ለዋልታ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የሚያስፈታውስ ማን ነው ፈቺስ ማን ነው በማለት እኔ ነኝ ያለ ይሞክረኛ አይነት አነጋጋሪ ቃለ መጠይቅ ሰጥተው ነበር፤በአሁኑም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡መልሶ ማቋቋም ከሆነ ደግሞ መከላካያ ማቋቋማያ የስራ እድል ቦታ እንዳልሆነ፤አሳምረው ያውቁታል፡፡አዲስ መከላከያ ቢያስፈልግ እንኳን በኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች እንጂ እንዴት የአንድ ግንባር ታጋይ በነበሩ ሊሆን እንደሚችል የሚያውቁት እሳቸው ብቻ ናቸው፡፡በፓርቲም ከሆነ ምርጫ ቦርድ የሚያውቀውም የማያውቀውም ወደ ብሄረሰቦች ቁጥር ጋር የሚጠጋ ፓርቲወች አሉ፡፡እናም እነዚህ ሁሉ ፖርቲወች በፖለቲካም ይሁን በሞራል ኦነግ ያለው መብት አላቸው፡፡ቀድሞ ሰራዊት ያላቸው ከተባለ ደግሞ መንግስት የግንቦት ሰባትን ሰራዊት ትጥቅ አስፈትቶና ወደ ሲቭል ህይወት መልሶ የኦነግን ወደ መከላከያ የሚቀላቅልበት ልዩ ህግ ከአለው የሚታይ ይሆናል፡፡በተረፈ የኢትዮጵያ ህዝብ አገሪቱንና ራሱን የሚከላከል ሃይል መገንባት ቢያስፈልገው እንኳን ማንም የማይገሰው ልዑአላዊ ባለመብት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡እናም የተነሳው ጉዳይ ከፖለቲካም በላይ ስለሆነ እንደገና ቢጤን መልካም ነው፡፡በነገራችን ላይ ይህ ጉዳይ በክልል ደረጃ የሚታይ አይደለም፡፡ለመሆኑ የቀድሞ የኦነግ ሰራዊት ቁጥር ስንት ነው? ጠ/ሚ/ሩ ካምፕ ይገኛል ያሉት ሶስት ሺህ የማይሞላ ነው ወይንስ ህዝብ ውስጥ አለን የሚባለው ድብብቆሽ? ስሌቱ የደደቢት አስተምህሮ ከአለበት ፍጻሜውም የደደቢት ነው የሚሆነው፡፡ምናልባት ይህን ያከልሁት የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና በምርጫ ኦሮሚያን ልንይዝ እንችላለን ነገር ግን ይህ ብቻውን አገር ለመምራት አያበቃንም፡፡ስለሆነም መከላከያን መያዝ አለብን፡፡ለዚህም አቋራጩ መንገድ የኦነግን ሰራዊት integrate ማድረግ ነው፡፡ስንት ስንባል ቀደም ብለንም ሰራዊቱ ውጪ ብቻ ሳይሆን አገር ውስጥም በህቡ ውስጥ ሲንቀሳቀስ ስለነበረ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ዛሬም ጭምር መልምለን መቀላቀል ያስችለናል፡፡ከዚያም ኦሮሞ በወርዱና በቁመቱ ልክ የሚለውን በማንሳት ቁልፍ ቦታወችን እንይዝና ሌሎች ቴክኒኮችን ጨምረን አገሪቱን እንቆጣጠራለን መምራትም ያስችለናል ነው ነገሩ፡፡ምናቤን አይደለም እየጻፍሁ ያለሁት፡፡ኦነግ መከላከያን ከያዘ ቀጥሎ ያለው ግልጽ ነው፡፡ይሄን ደግሞ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ከህወሃት በቂ ትምህርት ወስደናልና አንፈቅድም፤በቻልነው ሁሉ እንታገላለን፡፡የኦነግን ሰራዊት integrate ማድረግ እሺ ይባል ቢባል እንኳን በተመሳሳይ ግንቦት ሰባት በስፋት ደቡብና አማራ ክልል ሲንቀሳሰቀስ ስለነበረ ከኦነግ በላይ እርሾ ባይኖረው እንኳን የእነሱም ከፍተኛው ቁጥር አገር ውስጥ በህቡ ሲንቀሳቀስ ስለነበር ከኦነግ የበለጠ ቁጥር ማቅረብ ስለሚችል ሰፊ ህዝብ ስለሆነ የእነሱም መልስ ሲያገኝ አብሮ መልስ ያገኛል፡፡በተረፈ መንግስት ሁለቱም ድርጅቶች ከኤርትራ እግራቸውን ከመንቀላቸው በፊት መስራት የነበረበትን የቤት ስራ ቢዘገይም አሁኑኑ መስራት አለበት ባይ ነኝ፡፡ይኽውም ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ሳይውል ሳያድር ውሳኔ ማሳለፍ አለበት፡፡ይኽውም ሁለቱም ድርጅቶች ግንቦት ሰባትና ኦነግ አሁን ውጪ ያለ ፤ አገር ውስጥ ያለ የሚለው ድብብቆሽ ስላበቃ ነበረን የሚሉትን ሃይል ቀነ ገደብ ተሠጥቷቸው በትክክል ያላቸውን ቁጥርና ዝርዝር አሳውቀው ድራማው አብቅቶ ይህ ሰራዊት ስልጠና ወስዶ ራሱን ማቋቋሚያ ፕሮጄክትና ቢሮ በፌደራል ደረጃ ተቋቁመሞ ወደ ሲቭል ህይወት መመለስ አለበት፡፡በተረፈ ይህን ቀዳዳ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል ተቀባይነት የለውም፡፡ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም፡፡ኦነግ መምረጥ አለበት፡፡ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቭል ተቋማት መግለጫ ቢሰጡበት መልካም ነው እላለሁ፡፡

ከደደቢት አስተምህሮ እንጠበቅ!!!

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ‹‹ማንንም የፀጥታ አካል አልገደልኩም፣ ራሴን ነው የተከላከልኩት›› አሉ

ሀምሌ 5 ቀን 2008 እቤታቸው ድረስ ከመጡ የህወሃት ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ያደረጉትና በዚህም ታስረው የተፈቱት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ አስረዱ፡፡ 

በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው አማካኝነት በአዲስ አበባ መታተም የጀመረው በረራ ጋዜጣ ቃለምልልሳቸውን ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ቃለምልልስ ስለ ሀምሌ አምስቱ ጥቃት ኮሎኔሉ ሲያስረዱ ማንንም የፀጥታ ሀይል እንዳልገደሉና ራሳቸውን እንደተከላከሉ ገልፀዋል፡፡ በእለቱ ከለሊቱ 10 ሰአት ላይ የቤታቸው ግቢ መንኳኳቱን የገለፁት ኮ/ል ደመቀ ሲናገሩ ‹‹የግቢያችን በር ሲንኳኳ እኔ ያሰብኩት መርዶ ይሆናል ብዬ ነበር፡፡ እንደገና ያለማቋረጥ ሲንኳኳ ያበደ ሰው ይሆናል ብዬ እንጂ የህወሀት ታጣቂ ይሆናል ብዬ በጭራሽ አላሰብኩም ነበር›› ብለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ባለቤታቸው ተነስታ እነማን ናችሁ እንዳለቻቸውና እነሱም ዝም ብለሽ ክፈች ብለው በሩን በሀይል መደብደብ መቀጠላቸውን አስታውሰዋል፡፡ በሩ ሲደበደብ ጮክ ብለው ‹‹ቤቱ ህጋዊ ነው፣ የምንኖርበትም ህጋዊና ሰላማዊ ነን፣ ህጋዊ ከሆናችሁ እስኪነጋ ጠብቁ›› ማለታቸውን የተናገሩት ኮ/ል ደመቀ ጨምረውም እነሱ ግን ሳያዳምጧቸው በሩን ለሁለት ገንጥለው በመግባት ጥይት መተኮስ መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡ ከ

ዚህ ጋር በተያያዘ የህወሀት ሰዎች በየስብሰባው የፀጥታ ሀይሎችን የገደለ ሰው ለምን ይፈታል እያሉ ጥያቄ እያነሱ ይታወቃል፡፡ ይህን በተመለከተ ከበረራ ጋዜጣ የተጠየቁት ኮ/ል ደመቀ ሲመልሱ ‹‹እኔ ራሴን ነው የተከላከልኩት፡፡ አሁንም ቢሆን ማንኛውም አማራ በእንደዚህ ያሉ ተኩላዎች እንዲያዝ አልመክርም፡፡ ራሱን የመከላከል መብት አለው፡፡ ይህን መብቴን ነው የተጠቀምኩት፡፡ ከምሽቱ 12 ሰአት እስከ ጠዋቱ 12 ሰአት የሚመጣ ህጉም ይፈቅዳል፣ ማንኛውም ግለሰብ ራሱን የመከላከል መብት አለው፡፡ ይህን መብቴን ነው የተጠቀምኩት፡፡ ማንንም የፀጥታ ሀይል አልገደልኩም፡፡ ራሴን ነው የተከላከልኩት›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹እንዲያውም መንግስት ካለ ህፃናትና ሴቶች ባሉበት በመትረየስ፣ በቦምብ የደበደበን ነው መጠየቅ ያለበት፡፡ በወቅቱ በእኔ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያዘዙት ሰዎች አሁንም ድረስ ስልጣን ላይ ናቸው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ህወሀት በተፈጥሮው አጥፍቻለሁ ብሎ አምኖ እንደማያውቅ ያስረዱት ኮ/ል ደመቀ መርከብን ያህል ዘርፈውና ያንን ሁሉ ሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመው ስለታሰሩ እንዲፈቱ ሰልፍ የሚወጡ በመሆናቸው በእሳቸው ላይም ለምን ተፈቱ የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው እንደማይገርማቸው ጠቅሰዋል፡፡ አሁንም ቢሆን ከህግ ውጭ ሊያጠቃቸው የሚመጣን የመከላከል መብት እንዳላቸው የሚናገሩት ኮ/ል ደመቀ ሌላውም ዜጋ ራሱን የመከላከል መብት እንዳለው አስረድተዋል፡፡ 

‹‹ህወሀት በውሸት ያደገና በውሸት የጎለበተ ድርጅት ስለሆነ ደመቀ ለምን ተፈታ ብሎ ቢጠይቅ አይደንቀኝም፡፡ ነውረኛ ድርጅት ነው እኮ›› ያሉት ኮ/ል ደመቀ ጨምረውም ‹‹ለህፃናት ልጆቼ ሳይጨነቁ ቤቴን የጦር ቀጠና ያደረጉ፣ እኔና ጓደኞቼ መብታችንን በጠየቅን ያለአግባብ እንድንታሰርና ብዙ ግፍ እንድንቀበል ያደረጉ ሰዎች ናቸው ተጠያቂ መሆን ያለባቸው›› ሲሉ ለበረራ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ ይህ ኮ/ል ደመቀ ጀብድ የፈፀሙበት መኖሪያ ቤት ተከራይተው ይኖሩበት የነበረ ሲሆን ህዝቡ ገንዘብ አሰባስቦ ከገዛው በኋላ አሁን የአማራ ጀግንነት ማሳያ ሙዚየም መሆኑ ይታወቃል፡፡

መቼም የትም እንዳይደገም! NEVER EVER AGAIN!!!! ፀት ፂዮን ዘማርያም

ለትግራይ ህዝብ

የህወሃት  የጦር አበጋዞች ከኢዲዩ፣ኢህአፓ፣ ከደርግ፣ጦርነት ገጥሞ ኢትዩጵያን ተቆጣጠሩ፡፡ ህወሃት  የጦር አበጋዞች  ህዝቡን በዘር በመደራጀት (ትግሬ፣ኦሮሞ፣ አማራ፣ሱማሌ ወዘተ) ለሃያ ሰባት አመታት በአንድ ፓርቲ ገዛ፡፡

    ፀጋዬ ገብረመድህን(ደብተራው)፣አበራሽ በርታ፣ ለማ ኃይሉ፣ ከበደ ተስፋ (ፎቶ ከአህአፓ ዌብ ሳይት)

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን በትግራይ ወህኒ ቤቶች ውስጥ አስረው በድብደባ በማሰቃየት፣ ከወላጆቻቸው እንዳይጠየቁ በመሰወርና በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል እንዳይጎበኙ በማድረግ ያለፍርድ እንደረሸኞቸው እንደገደሎቸው በአቶ ገብሩ አስራት መፅሃፍ ይፋ ወጥቶል፡፡ ከነዚህም ውስጥ {1}ጸጋዬ ገብረ መድህን(ደብተራው)፣{2} ይሳቅ ደብረፂዎን፣{3} ስጦታው ሁሴን፣{4} በለጠ አምኃ የኢህአፓ ከፍተኛ አመራሮች የነበሩና ሌሎች አንጋፋ አባሎች ውስጥም {5} ደሳለኝ አምሳሉ፣ {6} ሃጎስ በዛብህ፣{7} ተክላይ ኃይለ ሥላሴና ከሱዳን ተላልፊ የተሠጠው {8} አዛነው ደምል፣ይገኙበታል፡፡ ከ1993 እኤአ ከአዲስ አበባ፣ባህር ዳር፣ ጎሞ ጎፋ በህወሓት የተሰወሩና የት እንዳደረሶቸው የማይታወቁት ውስጥ {9} አበራሽ በርታ፣ {10} ለማ መኮንን፣ {11}ተስፋዬ ከበደ፣ {12} ወንዱሲራክ ደስታ፣ {13} እዬብ ተካበ፣ {14}ሞት ባይኖር፣{15} አይነኩሉ፣ {16} ዬሴፍ፣ {17} ጋይም ገብረእግዚአብሄርና ጎደኞቹ በቅሎ ቤት አካባቢና {18} ጃታኒ አሊ በናይሮቢ  በህወሓት የጦር አበጋዞች ሲገደሉ ሌሎች የደረሱበት አይታወቅም፡፡ ከኬንያ ታፍነው መጥተው የተገደሉ {19} ኢንጅነር ተስፍሁን {20}ኢንጁነር መስፍን  ከየመን ታፍኖ ወደ ኢትዩጵያ የመጣው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ፣ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተቃዋሚ የህዝብ ልጆችን እያደኑ በመግደል ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔዊ ተግባር ፈፅመዋል፡፡  የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት መሪ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ተወልደ ወልደ ብርሃን፣ በረከት ስምኦን፣ አባይ ፀሃይዬ፣ አለምሰገድና ኃያሎም አርዓያ ለግድያው ተጠያቂ ሲሆኑ ሌሎቹም ግልገል ፋሽስቶች አንድ ቀን ለፍርድ እንደሚቀርቡ ከደርግ መንግስት መማር ይገባቸዋል፡፡ በትግራይ ክልል በወያኔ ድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የቶርቸር/ ግርፋት የስፈጸሙና የፈጸሙ ለህግ እንዲቀርቡ፣ መቐለ የመሸጉ ወንጀለኞችን የትግራይ ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ ሥልጣናቸውን በሰላማዊ መንግድ ያሸጋግራሉ ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ እንደመተበቅ ይቆጠራል፡፡ ህወኃት በ43 ዓመታት የፈጸማቸው ወንጀሎች ተቆጥረውና ተዘርዝረው አይዘለቁም፡-

{1} በትግራይ ክልል ብዙ የትግራይ ተወላጆችን፣ የኢዲና የኢህአፓ/አህአሠ ሰራዊትን ገድለው ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ ወያኔ የኢዲዩ አባላቶችን አስሮ ካሰቃያቸው በኃላ በነፍሰ ገዳይ ስኮዶቹ በነ ደብረጺዮንና ብስራት አማረ አማካኝነት ረሽነዋቸዋል፡፡ {2} የኢህአፓ አመራር አባሎችን እነ ፀጋዬ ገብረመድህን (ደብተራው)ና ሎሎችን ከመቀሌ እስር ቤት አስረው ካስቃቸው በኃላ ረሽነዋቸዋል፡፡ ለዚህ ግድያ ተጠያቂዎቹ የህወኃት አመራሮች ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ አባይ ፀኃዬ ወዘተርፈዎች  በደም የተጨማለቁ ነፍሰ ገዳዬች መሆናቸውን አንርሳ፡፡ ህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ በትረ ሥልጣን ከያዙ በኃላ በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የጅምላ ግዳያዎች በመፈፀም እጃቸውን በደም የታጠቡ ብድኖች ናቸው፡-{3} በኦሮሚያ በወለጋ፣ በበደኖ፣ በባሌ ከያዶት ወጣ ብሎ ብዙ ሰዎች ገብለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡{4} በሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት፣ ወያኔ ብዙ ሰዋች በኦብነግ ሥም ገድሎ በግሬደር ቆፍሮ የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች በሚዲያ ዘጋቢ ፊልም ተዘጋጅቶ፣ ለሰፊው ህዝብ እንዲቀርብ በሠማዕታቱ ሥም እንተይቃለን፡፡ {5} በአማራ ክልል ብዙ የወልቃት ተወላጆችን ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡{6} በጋምቤላ ክልል ብዙ የአኝዋክ ተወላጆችን እነ አባይ ፀሃዬና ገብርአብ በርናባስ ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ስላሉ ፍለጋው ቅድሚያ ይሠጠው እንላለን፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው!!! ለመጭው ትውልድ ወንጀለኞችን አናውርሰው እንላለን!!!

የወህኒ ቤቶች ሁኔታPrison and Detention Center Conditions

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የወህኒ ቤቶች ሁኔታ በተመለከተ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ ሦስት የፊዴራል እስር ቤቶችና 120 የክልል መንግስቶች እስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ብዙ ይፋ ያልሆኑ እስር ቤቶች በሃገሪቱ ውስጥ ሲገኙ ከነዚህ መኃከልም በዴዴሳ፣ በብር ሸለቆ፣ በጦላይ፣ ሆርማት፣ ብላቴ፣ ታጠቅ፣ ጅጅጋ፣ ሆለታና ሰንቀሌ የጦር ካንፖች ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የወህኒ ቤቶች ሁኔታ ለእስረኛዎች ህይወት በጣም አስጊና ብዙ ሰዎች ተፋፍገው የታሰሩበትና ለመተኛት አመች ያልሆኑ ቦታዎች እንደነበሩና ብዙ ሰዎች በግፍ ተታስረ፣ተገርፈው ያለህግ ተገድለው በጅምላ መቃብር ሥፍራ ተቀብረዋል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ለእስረኞች በቀን ስምንት ብር ወይም ግማሽ ዶላር ለምግብ፣ ለውሃና ለጤና ጥበቃ ወጪ ያወጣል ነበር፡፡ ብዙዎቹ እስረኞች ተጨማሪ ምግብ ቤተሰቦቻቸው እየገዙ ያቀርቡላቸዋል ነበር፡፡ የእስረኞች ጤና ጥበቃ በተመለከተ በፊዴራል እስር ቤቶች ውስጥ አስተማማኝ ህክምና አያገኙም ነበር፡፡ በክልል እስር ቤቶች ውስጥም የህክምና አገልግሎት አልነበረም፡፡ በሃገሪቱ በሚገኙ ወህኒ ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመኖሩ የተነሳ እስረኞች ንፅህናቸውን ለመጠበቅ ባለመቻላቸው ብዙዎቹ በጤና ችግር ይሰቃያሉ ነበር፡፡ እስረኞች አነስተኛ የህክምና አገልግሎት ብቻ ያገኙ ነበር፡፡ በወርሃ የካቲት በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ አንድ የጣልያን ዜጋ በህክምና እጦት የተነሳ ህይወቱ አልፎል ነበር፡፡ በአመቱ መገባደጃ ላይ በአጠቃላይ በግምት 86,000 ሽህ እስረኞች ሲገኙ ከዚህ ውስጥ 2,474 ሴት እስረኞች ሲሆኑ፣ 546 ህፃናቶች ከእናታቸው ጋር ታስረው ይገኙ ነበር፡፡ የወጣት ጥፋተኞች አንዳንድ ግዜ ሞት ከተፈረደባቸው ጎልማሶች ጋር በአንድ ላይ ይታሰሩ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ወንድና ሴት እስረኞች በተለያዩ ቦታዎች ታስረው ይገኛሉ፣ ቤተሰቦቻቸውም ይጠይቆቸው ነበር፡፡ በሌላ በኩል  ቤተሰቦቻቸው የማይጠይቆቸው የተከለከሉ እስረኞች ነበሩ፡፡ The country has three federal and 120 regional prisons. There also are many unofficial detention centers throughout the country, including in Dedessa, Bir Sheleko, Tolay, Hormat, Blate, Tatek, Jijiga, Holeta, and Senkele. Most are located at military camps. Prison and pretrial detention center conditions remained harsh and in some cases life threatening. Severe overcrowding was common, especially in sleeping quarters.  The government provided approximately eight birr ($0.50) per prisoner per day for food, water, and health care. Many prisoners supplemented this with daily food deliveries from family members or by purchasing food from local vendors. Medical care was unreliable in federal prisons and almost nonexistent in regional prisons. Water shortages caused unhygienic conditions, and most prisons lacked appropriate sanitary facilities. Many prisoners had serious health problems in detention but received little treatment.  In April an Italian citizen died after receiving allegedly substandard medical treatment in Kality prison. At year’s end there were an estimated 86,000 persons in prison, of whom 2,474 were women and 546 were children incarcerated with their mothers. Juveniles were sometimes incarcerated with adults who were awaiting execution. Male and female prisoners generally were separated. Authorities generally permitted visitors. In some cases family visits to prisoners were restricted to a few per year.

በሁሉም ክልሎች ውስጥ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል፣ በሱማሌ፣ በሃረሪ፣  ደቡብ ክልሎችና በአዲስአበባና ድሬዳዋ አስተዳደር ድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የቶርቸር/ ግርፋት የስፈጸሙና የፈጸሙ ህወሓት/ ኢህአዴግ ሹማምንቶች ለህግ እንዲቀርቡ፣ በየክልሎቹ ያሉ ያደፈጡ ስብኣዊ መብት የጣሱ ወንጀለኞችን ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጣቸውና ለፍርድ እንዲቀርቡ በማድረግ ሁሉም ክልሎች በትጋት እንዲሰሩ እንጠይቃለን፡፡ በሃገራችን መቼም የትም እንዳይደገም! NEVER EVER AGAIN!!!! ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል የሚሆነው ጥፋተኞቹን ለህግ በማቅረብ ነው፡፡ ኢሠመጉ አስፈላጊውን መረጃ ማቅረብ በአፋጣኝ ይጠበቅበታል፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው!!! ለመጭው ትውልድ ወንጀለኞችን አናውርሰው እንላለን!!!

ምንጭ በአቶ ገብሩ አስራት

ግንቦት ሃያና መለስ ዜናዊ የሚሉ መጠሪያዎች በባህር ዳር እየተቀየሩ ነው

በባህር ዳር ከተማ ቀደም ሲል ግንቦት  20 ክፍለ ከተማ ይባል የነበረው የከተማው ክፍለ ከተማ ስም፣ ዳግማዊ ሚኒሊክ በሚል  ክፍለ ከተማ ስም እንዲጠራ በከተማዋ አስተዳደር እንዲተወሰነ ከባህር ዳር የደረሰነ መረጃ ይጠቁማል። በክፍለ ከተማዋ ያለው የጤና ጣቢያውም መጠሪያ በአዲሱ የክፍለ ከተማ መጠሪያ እንዲሆን መወሰኑንም የከተማዋ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ መለስ ዜናዊ ፓርክ ተብሎ ይጠራ የነበረው ደግሞ “አሸት ፓርክ” ተብሎ እንዲጠራ መወሰኑንም ለማወቅ ችለናል።

በከተማ፣ በክልሉና በአገሪቷ ባሉ በርካታ ዜጎች በተደጋጋሚ ባህር ዳር ያለው ግንቦት ሃያ ተብሎ የተሰየመው የባህር ዳር አለምአቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ስሙ ተቀይሮ በ=ደጃች በላይ ዘልቀ ተብሎ እንዲጠራ ቢጠየቅም እስከአሁን አለመቀየሩ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። የአዴፓ የከተማዋ ሃላፊዎች፣ አይሮፕላን ማረፊያው በፌዴራል መንግስት ይዞታ ስር ስለሆነ ዉሳኔው መተላለፍ ያለበት በፌዴራል ደረጃ ስለሆነ ነው ያልተቀየረው የሚል ምክንያት ይሰጣሉ። ቢሆምም፣ ምንም እንኳን በከተማ አስተዳደር ደረጃ የአዴፓ አመራሮች በጉዳዩ ላይ ከሕዝብ ፍላጎት ጋር እየተራመዱ ቢሆንም፣ በፌዴራል ደረጃ ያሉ የአዴፓ አመራሮች እንደዚህ አየነቱን፣ ሕዝብ የሚፈለገውን ቀላል ዉሳኔዎች ማስወሰን አለመቻላቸው አዴፓ/ብ አዴንን በፌዴራል ደረጃ ወክለው የተቀመጡ አመራሮችን ትልቅ ድክመት የሚያመላክት እንደሆነ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስቃይ

ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ፣ በተለይም ከአማራ ክልል የመጡም ላለፉት በርካታ ቀናት በትልቅ ችግር ላይ የነበሩ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ ከአማራ ክልል የፀጥታ ቢሮ ከመጡ፣ ባለስልጣን፣ ኮሎኔል ማርዬ ፣ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና ከዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባላት ጋር ስብሰባ እንዳደረጉ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ስብሰባው በተባለበት ሰዐት ባለመጀመሩ ተማሪዎች ቅር ቢሰኙም ስብሰባውን ዘግይቶም ቢሆን ሊቀጥል ችሏል፡፡ፕሬዝደንቱ ፣ በጊዜ ያልተገኙበት ምክንያት፣ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ ስለነበራቸው እንደሆነ ገልጸው በይቅርታ በመጠየቅ ስብሰባውን ሲጀመሩ ከተማሪዎች ከፈተኛ ተቃዉሞ ቀርቦባቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ በቁጣ “ይቅርታ አናደርግለትም፣ ሲጀመር ስብሰባ አልነበረውም፡፡ቢኖረውም እንኳ ስብሰባውን አቋርጦ መጥቶ ችግሩን በቀላሉ መፍታት ይችል ነበር” ሲሉ በፕሮዘዳንቱ ላይ የተጠራቀመ ብሶታቸውን አሰምተዋል።

በስብሰባው የተነሱ በርካታ ሃሳቦች የነበሩ ከተነሱ ሐሳቦች የሚከተሉትን እንደሚገኝበት ከስፍራው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡

  • ሁለት ሴት ተማሪዎች ከጊቢ ተጠልፈው ጠፍተዋል፡፡
  • አንድ ተማሪ ከፎቅ ተወርውረዋል፡፡- ሁለት ተማሪዎች በጩቤ ተወግተዋል፡፡
  • የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መገለጫ የሆነው ነጠላ ተቃጥሏል
  • በጣም በርካታ ተማሪዎች ላይ ድብደባ ደርሶብናል- laptop computer ፤ mobile ፣ ልብስ ፣ጫማ የመሳሰሉት ዘረፋ ተፈፅሞብናል፡፡
  • ይህ ሁሉ ነገር ሲፈፀም ፕሮዘዳንቱ ዝም ማለታቸው ሳያንስ ተማሪዎች ሜዳ ላይ ከወጡ ስምንት ቀን ቢሞላቸውም አንድ ቀን እንኳን ፕሬዝደንቱ መጥቶ አለመነጋገራቸው፡፡
  • በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አገልግሎት የሚሰጠው በኦሮሞኛ ቋንቋ ብቻ ነው፡፡
  • አማራ ቡዳ ፣ አማራ አዝማሪ፣ የሚኒሊክ ዘር ይውጣልን የሚሉ መፎክሮች ሰምተን ሪፖርት ብናደርግም ጊቢው ችላ ብሎናል፡

ጭቱ ከመነሳቱ በፊት ለፕሬዚዳንቱ ያስገቡትን ማመልከቻ በማሳየት እና ፕሬዝዳንቱ እንዳልሰማ ማለፋቸውን በመረጃ ላይ አስደግፈው አሳይተዋል።
ተማሪዎቹ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ ለማገገም ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸው፣ ላልተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ፣ ወደቤተሰቦⶨው ሄደው፣ ሁኔታዎች ሲመቻቹ፣ ደህንነታቸው ማረጋገጥ ሲቻል፣ ተመልሰው እንዲመጡ ጠይቀዋል። ጥያቄዎቻቸው የማይመለሱ ከሆነ ይህ ካልሆነ የበላይ አካል ችግራቸውን እስከሚፈታ ወደ ዶርም እንደማይገቡም ገልጸዋል።170

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽንን ማቋቋሚያ አዋጅ ፀደቀ


የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በሕግ ይፅደቅ ወይንስ አይፅደቅ የሚለው የህዝብ እንደራሴዎች አባላትን በእጅጉ ካከራከረ በኋላ ፀድቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ከዚህ ቀደም ለምክር ቤቱ ቀርቦ ለዝርዝር እይታ ለውጪና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ይታወሳል፡፡
ረቂቅ አዋጁ እንዲፀድቅ ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ግን ይፅደቅ አይፅደቅ በሚለው በሁለት ጎራ ተከፍለው ሰፊ ክርክር አድርገዋል፡፡
አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት የማንነትንና የአስተዳደር ወሰንን በተመለከተ ስልጣን የተሰጠው ለክልሎችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኮሚሽኑ መቋቋም የህገ መንግስቱን አንቀፆች የሚንድ ነው፣ አዋጁ ለመፅደቅ ለምክር ቤቱ ከመቅረቡ በፊት ክልሎች ተወያይተውበት መስማማት ላይ መድረስ ነበረበት ሲሉ ረቂቅ አዋጁ እንዳይፀድቅ ተከራክረዋል፡፡
ሌሎች ደግሞ፣ ኮሚሽኑ ለዘመናት በአስተዳደር ወሰንና በማንነት ጥያቄ ምክንያት ሲቆራቆሱ የቆዩ ሕዝቦችን ሰላም ይመልሳል ሲሉ አዋጁ መፅደቅ አለበት ብለው ሞግተዋል፡፡
ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ለግጭት ምክንያት የሆኑ የወሰንና የማንነት ጉዳዮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት ምክረ ሀሳቦችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤትና ለሚመለከተው የመንግስት አካል የማቅረብ ሀላፊነት ይኖረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በራሱ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ስልጣን አልተሰጠውም፡፡
በመሆኑም፣ የየትኛውንም ተቋም ስልጣን አይጋፋም፣ የህገ መንግስቱን አንቀፆች አይሸረሽርም ሲሉ ከፊሎቹ አባላት አዋጁ እንዲፀድቅ ተከራክረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ዜጎች ሲኮላሹ፣ ሲገደሉና ሲሰቃዩ ይህ ምክር ቤት ህገ መንግስት ተጣሰ፣ የሚል ቃል ወጥቶት አያውቅም ያሉት አባላቱ ዞር ብለን አይተነው የማናውቀውን ህገ መንግስት ሲመቸን ብቻ እንደፈለግን እየተረጎምን ልናወራበት አይገባም ሲሉም አዋጁ

ሀገር አቀፍ የወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው


የወጣቶች ኮንፍረንሱ “ወጣቶች ለሀገራዊ ለውጥና ሠላም” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።

የወጣቶች ኮንፍረንሱ “ወጣቶች ለሀገራዊ ለውጥና ሠላም” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።

በኮንፈረንሱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፥ ኢትዮጵያ የሰላም ባለቤት እንድትሆን ወጣቶች ባለእዳም ባለአደራም መሆናቸውን ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ እና ለመገንባት ወጣቶች ያለባቸውን ድርብ ሀላፊነት ሊወጡ  ይገባልም ብለዋል።

ነገን ዛሬ በአግባቡ ስንሰራው ሰላምን በውክልና ሳይሆን በባለቤትነት እናረጋግጣለን ነው ያሉት የሰላም ሚኒስትሯ።

በሀገሪቱ በርካታ ቁጥር የያዘው ወጣቱ በመሆኑ የሀገሪቱ መፃኢ እድል በወጣቶች ላይ መሆኑን ሚኒስትሯ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት የለውጥ ጉዞ አጓጊ ቢሆንም ይህን የለውጥ ጉዞ እንዳታስቀጥል ለማድረግ የሰላም መደፍረስ እያገጠመ መሆኑን ያነሱ ሲሆን፥ ይህንን ለመከላከልም የወጣቶች ሚና ከፍተኛ  እንደሆነ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ የወጣቶች ሚና ለውጥ እንጂ ነውጥ አለመሆኑን በስራቸው ማረጋገጥ ይገባቸዋል ብለዋል በንግግራቸው።

የሴቶችና ህጻናት ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋየ በበኩላቸው፥ ያለሰላም ስለለውጥ ማሰብ፣ ማቀድና ስኬትን መጎናፀፍ  በፍፁም የማይቻል አይደለም ያሉ ሲሆን፥ለዚህም ወጣቶች ለሰላም እጦት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች እራሳቸውን ማራቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ የሰላም መልዕክተኛ እናቶች በመገኘት ለወጣቶች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ ወጣቱ ለሀገር ሰላም ግንባታ ትልቅ ሀይል በመሆኑ ሁሉም ወጣት የሰላም አምባሳደር በመሆን እንዲሰሩ ቃል አስገብተዋቸዋል፡፡

የሰላም እናቶቹ ወጣቶች በየሚኬዱበት አካባቢ  ስለሰላም እንዲያስተምሩ ለወጣቶቹ አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ በባህል ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ኮንፈረንሱ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኮንፈረንሱ አላማ ወጣቶች ለግጭትና ተያያዥ ችግሮች ያላቸውን ተጋላጭነት በመቀነስ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ መሪ ተዋናይ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው ተብሏል።

በዙፋን ካሳሁን

FBC

ክብር ለአቶ ለማ መገርሳ !!


የሃሳብ ከፍታ እንዲህ ነው፤ ከዘረኝነት አዙሪት መውጣት የተሳናችሁ ጊዜው የኛ ነው ባይ የፖለቲካ ድኩማኖች ሆይ ከህመማችሁ መፈወስ ትፈልጉ እንደሁ ይህው መድሃኒት…

“ዛሬ ኦሮሞ ቤተመንግስት የገባው ቤተመንግስቱን የኦሮሞ አድርጎ ሊጨፍርበት ሳይሆን ቤቱን የሁሉም የኢትዩጵያ ህዝቦች የፍትህ የእኩልነትና የሀቅ ቤት ለማድረግ ነው።

እኛ ይህን ቤተመንግስት የኛ ቤት አደረግን ብለን የምንዘፍን ከሆነ ከሌሎች በምን ተሻልን ታድያ? እኛ ግን እንደዝህ አይደለንም። የታገልነው ለስልጣን ሳይሆን ለፍትህ እና እኩልነት ለህዝቦች ነጻነት ነው።”

• ከሰማይ በታች እጅግ ይፈሩ የነበሩትን አስረን የህግ የበላይነትን አሳይተናል
• ወንበር ይዘን አልተቀመጥንም ።
• እንደ ግለሰብ ድርጅት ነበር ስርዓቱ የተገነባዉ።
• ስርዓት አፍርሶ አዲስ ለሁሉም የሚያገለግል ስርዓት መገንባት ጊዜ ይፈጃል።
• ከሰማይ በታች እጅግ ይፈሩ የነበሩ፤ እንኳን ለማናገር ቀና ብሎ ለማየት ይፈሩ •የነበሩ ሰዎችን አስረን ህግ ከማናችንም በላይ እንደሆነ አሳይተናል፡፡

“የታለ ለዉጡ? ይሉናል?/?? እኛ የታገልነዉ ለማን ፕሬዝዳንት ለማድረግ አብይን ጠ/ሚኒስትር ለማድረግ ነዉ ወይ? ይሉናል፡፡ ምን አረጋችሁ መቀመጫችሁን ይዛችሁ ቁጭ አላችሁ እንጂ ይሉናል?? መቀመጫ አልያዝንም!!!
አልተቀመጥንም፡፡ ችግሩ የስርዓት ችግር ነዉ!!! ስርዓቱን እንትና የሚባል ሰዉ ለራሱ እንዳመቸው እንደ የግል ድርጅቱ ነዉ ። የገነባዉ፡፡ 
ገንብቶ እየተጠቀመበት የነበረ ስርዓት ነበር፡፡ ያንን ስርዓት ማፍረስን ይጠይቃል!!!

ይሄን ህዝብ፣ ብሄርና ብሄረሰቦችን በሚያገለግል መልኩ ለማቆም አፍርሶ መገንባትን ይጠይቃል፡፡ 
ለማፍረስ ጊዜ ይጠይቃል፤ ለመገንባትም ጊዜ ይጠይቃል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ ፡፡

ደም መላሽ ተገኘ


የኦነግ ሰራዊት ምእራብ ሸዋ፣ ጀልዱን ከኦሮሞ ክልል መንግስት ተቆጣጥረዋል። በኦሮሞ ክልል በይፋ የርስ በርስ ጦርነት ተጀምሯል።

ግርማ ካሳ

በሰላሌና ሰሜን ሸዋም ሕዝቡ በጣም ተደናግጧል።