ከጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ አምስት ሰዎች ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ

ከጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ የአምባሰል ንግድ ስራዎች ስራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ምትኩ በየነን ጨምሮ አምስት ሰዎች ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ ሲል የአብመድ ዘግባ ያመለክታል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ የአምባሰል ንግድ ስራዎች ስራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ምትኩ በየነን ጨምሮ አምስት ሰዎችን ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ በህግ ቁጥጥር ስር አውሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ ባሕርዳር ከተማና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል 

ኢፕድ)

የማንነት ብሔርተኝነት የተጠላው አማራ ይጠቅመኛል ብሎ ስለያዘው ነው (ባየ ተሻገር)

* ማሳሰቢያ፤ ጽሑፉ ረጅም ነው። ከመጀርያው እስከ መጨረሻው *
* ብታነቡት ቁም-ነገር አታጡበትም። ዋና መጽሐፍቶቹን*
* እና አርቲክሎቹን እንትታነቡ ትበረታታላችሁ። *

መግቢያ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አማራን በሚመለከት በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይቶች የተከፈቱ ቢሆንም የበርካታ ፖለቲከኞች ትኩረት ግን የዜግነት ብሔርተኝነትን መሠረት አድርገው የሚንቀስቅቀሱ ድርጅቶች የአማራን ማንነት መሰረት አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ይሻላሉ ወይንም የአማራን ብሔር የሚወክሉ ድርጅት/ድርጅቶች አያስፈልጉም፣ ለአማራ ህዝብ አይመጥኑም አገር አፍራሾች ናቸው የሚል እና ይህንን አስተያየት ለመመከት የሚሰጥ ግብረ-መልስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአገራዊ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ሳይቀር እጅግ የተዛባ ፅንሰ-ሃሳብ ያላቸው አንዳንዴም ትርጉም የለሽ ቃላት መጠቀም የተለመደ ሆኗል። ለምሳሌ “የአንድነት ጎራ” የሚለው ቃል ትርጉም የለሽ ነው። የማንነት ብሔርተኞችን (ethnic nationalists) “ብሔርተኞች” ብቻ ብሎ መግለጽ ከመደበኛ የሚዲያ አካል የሚጠበቅ አይደለም። በአጠቃላይ የብሔርተኝነት ጽንሰ-ሃሳብ እጅግ ተዛብቶ እየቀረበ ይገኛል። በእርግጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አማራ የሚያራምደው የፖለቲካ አጀንዳ ዘወትር እንደተገፋና እንደተጠላ ነው፤ የማንነት ብሔርተኝነት የተጠላው አማራ ይጠቅመኛል ብሎ ስለያዘው ነው።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ትኩረት የማደርገው ብሔርተኝነት ምንድን ነው? የብሔርተኝነት መንሥኤዎች ምንድን ናቸው? በዓለም አቀፍ ደረጃ የማንነት ብሔርተኝነት እንዴት ይታያል? ማንነትን መሠረት አድርጎ የሚካሄድ ብሔርተኝነት መጥፎ ጎን ብቻ ያለው እንቅስቃሴ ነውን? እና በዜግነት ላይ ያተኮረ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች የማንነት ብሔርተኝነትን ለምን ይጠሉታል? የሚሉትን መዳሰስ ይሆናል።

በመሠረቱ ብሔርተኛ (nationalist) ያልሆነ ድርጅት የለም። የሚለያየው ድርጅቱ ለሚያራምደው ብሔርተኝነት በመንስኤነት የያዘው ሃሳብ እና የመታገያ አጀንዳው ነው። አንድ ድርጅት የመታገያ አጀንዳውን ቋንቋ፣ ባህል፣ ምጣኔ ሐብት፣ ዜግነት ወይንም እንደየአካባቢው ሁናቴና እንደ ሕዝብ ፍላጎት ሌላ ሊያደርግ ይችላል። ድርጅቱ የመታገያ አጀንዳውን ከፖለቲካ ርዕዮት ጋር አዛምዶ የትግል ፍኖት ይቀርጻል ። በብሔርተኛው ድርጅት መታገያ ሆኖ የቀረበለትን አጀንዳ እና የምርጫ ቅስቀሳ መዝኖ ህዝብ ይበጀኛል፣ ጥያቄዎቸን ይመልሳል፣ ኑሮዬን ያሻሽላል ያለውን ይመርጣል። ኢትዮጵያ ውስጥ በብሔር ማንነታቸው ተደራጅተው ከሚታገሉት በስተቀር በዜግነት ብሔርተኝንት የሚንቀስቅቀሱ ድርጅቶች የጠራ የመታገያ አጀንዳ የላቸውም፤ የዜግነት ብሔርተኝነትን የሚያምዱ ድርጅቶች አሉ ለማለት በራሱ አያስደፍርም። በእርግጥ የሌሉት የዜግነት ብሔርተኝነት እንዳይኖር የሚያደርግ ምክኒያት ስለለ ነው። ይኸውም ኢትዮጵያ የመድብለ-ብሔር አገር ከመሆኗ ባሻገር እያንዳንዱ ብሔር አንገብጋቢ ችግሬ ነው ብሎ እንዲመለስለት የሚፈልገው ጥያቄ ያለው መሆኑ ነው፤ ጥያቄ መኖሩ ብቻ ሳይሆን የአንዱ ብሔር ጥያቄ ከሌላው ብሔር ጥያቄ የተለየ አልፎ አልፎም የሚቃረን በመሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በዜግነት ብሔርተኝነት ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች የመታገያ አጀንዳ እንዳይኖራቸው አድርጓል።

በዘመናዊ የፖለቲካ አሰራር የመታገያ አጀንዳ የሚወሰነው በህዝቡ ፍላጎት ነው። ለምሳሌ የአማራ ህዝብ በአስቸኳይ እንዲመለሱለት ከሚፈልጋቸው መካከል ቀዳሚው ወሰንን ማስከበር የተመለከት ነው። የወልቃይት፣ የራያ፣ የመተከልና የሸዋ መሬቶች ጉዳይ የሁሉም አማራ አፍ መፍቻ ሆኗል። በመሆኑም የአማራን ህዝብ ይሁንታ ማግኘት የፈለገ ድርጅት እነዚህን ጉዳዮች የግድ የመታገያ አጀንዳ ማድረግ አለበት። ይሁን እንጅ የዜግነት ብሔርተኝነት አራማጅ ድርጅቶች ቀደም ብዬ በገለጽኩት ምክኒያት የወሰን ማስከበርን ጉዳይ አጀንዳቸው ሊያደርጉትም አይችሉም። ከዚህ ቀደም የወልቃይትና መሰል አካባቢዎች የወሰን ማስከበር ጥያቄ አስመልክቶ ጥያቆአ የተቀረበላቸው እንደ ግንቦት 7 ያሉ የዜግነት ብሔርተኝነት እናራምዳለን የሚሉ ድርጅቶች እንኳን ጥያቄዎቹን በአጀንዳቸው ሊያካትቱ በእንዲህ ዓይነት ዘዴ እንፈታለን ለማለት ያስቸገራቸው ሲሆን በደፈናው የህወሓት (ትህነግ) ወያኔን መንግሥት እንደ ምክኒያት አድርገው ለበርካታ ጊዜያት ዋና ጠላታችን ካሸነፍን በኋላ እንመለስበታለን የሚል ማምለጫ መንገድ በማመቻቸት ሲሸሹት ቆይተዋል። ይህ በር ግን ዛሬ ላይ ማምለጫ አይሆንም ምክኒያቱም የህወሓት ወያኔ መንግሥት ባይወገድ እንኳን ተንኮታኩቶ የበላይነቱን ተነጥቋልና። በመሆኑም ምላሽ የላቸውም።

ቀጥሎ የብሔርተኝነትን ትርጉም እና ዓይነቶች እንመልከት።

ሀ) የብሔርተኝነት ትርጉም

እንደ ክርስቶፈር ሙስካቶ አገላለፅ “ብሔርተኝነት ማለት በአንዲት አገር የጋራ ሃሳብ ዙሪያ አንድነት ያለው ማንነት ከፍ ማለት ማለት ነው (Nationalism is the elevation of a unified identity around the shared concept of the nation: Christopher Muscato, University of Northern Colorado)።”ብሔርተኝነት የተቃውሞ ዝንባሌ ያለው ጽንሰ-ሃሳብ ነው። ብሔርተኝነት ከአገር ባለቤትነት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን የአገር ኅልውና መሠረትም ነው። ብሔርተኝነት አርበኝነት(patriotism) አይደለም። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች አንጻራዊ የበላይነት ለማግኘ እና የሕዝቡን ወኔ በመቀስቀስ ከጎናቸው ለማሰለፍ ሲሉ ብሔርተኝነትንና አርበኝነትን በተለዋዋጭነት ይጠቀሙባቸዋል፤ ነገር ግን ሁለቱ አንድ ዓይነት ትርጉም የላቸውም። በዚሁ ዘርፍ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሙስካቶ አርበኝነት አንድ ግለሰብ ስለአገሩ የሚሰማው ኩራት ወይንም ክብር እና ለአገሩ ያለበትን ግዴታ እንደሆነ ያመለክታሉ። ብሔርተኝነት ደግሞ በአንዲት አገር የጋራ ሀሳብ ዙዙሪያ አንድነት ያለው ማንነት ከፍ በማድረግ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት ሥርዓት የመፍጠር ጉዳይ ነው ሲሉ ያስቀምጡታል። አርበኞች አገራቸውን ይወዳሉ (Patriots love their country) ፤ ብሔርተኞች ደግሞ አገራቸውን ናቸው (nationalists are thier country!)። በሌላ አገላለጽ አርበኞች ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣን ድንበር እና አገራዊ እሴቶችን ለማስጠበቅ ዘብ በመቆም አገሪቱን ከውስጣዊና ውጫዊ ኃይሎች ወይንም አገራዊ እሴቶችን ሊጎዱ ከሚችሉ አስተሳሰቦች የመከላከል እንቅስቃሴ ሲሆን ብሔርተኝነት የሚያተኮረው ፖለቲካን እንደ መሣሪያ በመጠቀም በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሃብት ክፍፍል፣ ብልጥግና፣ እና ማህበረሰባዊ ለውጥ መቀመር ላይ ነው።በመሆኑም ብሔርተኝነት የአንድ ማኅበረሰብ አካል ብለን ከምንጠራው የኅብረተሰብ አካል ከመሆን ጽንሰ-ሀሳብ ጋር የተያያዘነው። በእርግጥ አርበኝነትን የተላበሰ ብሔርተኝነት አብቦ የጎመራባቸዋና ውጤታማ የሆነባቸው አካሄዶችም አሉ።

በአጠቃላይ በምሁራን መካከል ብሔርተኝነት ከሁለት የተለያዩ ቅርጾች አንዱን ሊወስድ እንደሚችል የሚታመን ቢሆንም በርካታ የኅብረተሰብ ሳይንስ ተማራማሪዎች ከሁለት በላይ ብሔርተኝነቶች እንዳሉ ይጠቅሳሉ። እንደ ሚካኤል ኢግናቴፍ (Micheal Ignatieff) አገላለጽ ብሔርተኝነት ሁለት መልክ ሊኖረው ይችላል። የመጀመሪያው ማንነትን መሠረት ያደረገብ ሔርተኝነት (ethnic nationalism) ሲሆን ይኸውም የጋራ ቋንቋ፣ ሀይማኖት፣ ሥነ-ልቦና ያለው እና በተመሣሣይ መልክዓ-ምድር አካባቢ የሚገኝ ሕዝብ ወይንም ብሔር በጋራ ማንነቱ ከፍ ማለት ባለው ጥብቅ ሀሳብ ተመስርቶ የሚያንቀሳቅሰው የፖለቲካ አጀንዳ ነው። በአማራ አውድ ለ”ethnic nationalism” በጣም ተቀራራቢው ፍች የማንነት ብሔርተኝነት ነው። ሁለተኛው ዜግነታዊ ብሔርተኝነት (civic nationalism) ነው። ይህ የጋራ የሲቪክና የፖለቲካ እሴቶችን መሠረት ያደረገ ብሔተኝነት ሲሆን እነኛን የጋራ እሴቶች መሠረት በማድረግ ዜጎች ሁለንተናዊ ጥቅማቸው እንዲጠበቅ ለማድረግ የሚከተሉት የፖለቲካ ሥልት ነው።

ምሁራን ብሔርተኝነትን በአራት የተለያዩ መነጽሮች ተመልክተው ይተነትኑታል። ብሔርተኝነትን እንደ ፖለቲካ ርዕዮት (ideology)፣ ቡድናዊ አስተሳሰብ (group sentiment)፣ የአገር ምሥረታ ሂደት(process of nation building) ወይንም ማኅበረሰባዊ ንቅናቄ (social/collective movement) በመውሰድ ጥናቶች ይካሄዱበታል (Ethnic Nationalism and State Power – Mark Suzman (1999))። በኢትዮጵያ ውስጥ ከንጉሣዊ ሥርዓት መውደቅ በኋላ የታዩት ብሔርተኝነቶች አራቱንም ዓይነት ይዘት ያላቸው ሲሆኑ የሻዕቢያ፣ ትህነግ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ እና የመሣሰሉት ብሔርተኝነቶች በአገር ምሥርታ ላይ ያተኮሩ ናቸው። በአንጻሩ ደርግ እና በደርግ አገዛዝ ወቅት የነበሩ እንደ መኢሶን፣ ኢሀፓ፣ ኢዲዩ ወ.ዘ.ተ. እና በዘመነ ኢህአዴግ የታዩት እነ መድረክ፣ ቅንጅት፣ ሰማያዊ ፓርቲ ወዘተ በደረቅ ፓለቲካዊ ፍልስፍና እና እሽቅድድም ላይ ያተኮሩ ብሔርተኝነቶች ናቸው። በትህነግ ፊታውራሪነት ተቀምረው ለተቀረው ኢትዮጵያዊ በአገዛዝ መሳሪያነት (ዲክታትነት) የተከፋፈሉት እነ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴን ወዘተ በቡድናዊ አስተሳሰብ የተቃኙ ናቸው። በመጨረሻም በቅርቡ ህዝባዊ ተቀባይነትን ያገኙት የአማራ ብሔርተኝነት እና “ቄሮ” በሚል ቅፅል ስም የሚቀነቀነው የኦሮሞ ብሔርተኝነት በማኅረሰባዊ ንቅናቄ ደረጃ ያሉ ብሔርተኝነቶች ናቸው።

ለ) የብሔርተኝነት መንስኤዎች

የብሔርተኝነቶች መንስኤዎች የተለያዩ ትርክቶች ናቸው። በፖለቲካዊ ርዕዮት መነጽር ሲለኩ የዜግነት ብሔርተኝነቶች መንስኤ የብሔርተኝነቱ አራማጆች ስለዓለም አጠቃላይ ሁኔታ ያላቸውን ግንዛቤ (conscious strategic understanding) ለማስመስከርና ማኅበረሰቡ በተጽዕኖ ፈጣሪነትና ተሰሚነት እንዲኖራቸው በማሰብ የምሁርነታቸውመገለጫ እንዲሆን በፋሽንነት የሚያመጧቸው ሃሳቦች ነው። መሰረታቸው ፖለቲካዊ ፍልስፍናን ብቻ ትኩረት ያደረገ በመሆኑ ከብዙሃን ፍላጎት የሚመነጭ አይደለም። በአንዲት አገር ካለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ወይንም ፖለቲካዊ እውነታ ይልቅ ዓለ’ማቀፋዊ ይዘት ባላቸው ፅንሰ-ሃሳቦች ላይ የሚያተኩር እንቅስቃሴ በመሆኑ የተለያዬ ማንነት እና የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ብሔሮች በሚገኙበት አገር ለአካባቢያዊ ሁናቴዎች መፍትሔ የማምጣት ጉልበት የሚያንሰው እንቅስቃሴ ነው። በዚህም ምክኒያት ውጤታማ ሲሆኑ አይታይም። በተለይ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ፖለቲካዊ ፍልስፍን ብቻ መሠረት ያደረገና ውጤታማ የሆነ አንድም የዜግነት ብሔርተኝነት የሚያራምድ ድርጅት አልነበረም፤ የለምም።

በማንነት ላይ ያተኮሩ ብሔርተኝነቶ መንሥኤዎች ከሃብት ክፍፍል፣ፖለቲካዊ ውክልና እና ማኅበረሰባዊ ፍትህ ጋር የተያያዙ ትርክቶች ናቸው። መንሥኤዎቹ ከማኅበረሰቡ የቀን ተቀን ኑሮ ጋር የተቆራኙ በመሆናቸው ህዝቡን ለማነሳሳትና ተቀባይነት ለማግኘት ጊዜ አይወስድባቸውም።

የብሔርተኝነቶችን ስኬት የሚወሰነው ለመነሻነት መንስኤ ባደረጉት ሃሳብ ነው። ለምሳሌ በአገር ግንባታ ላይ ያተኮረው የሻዕቢያ ብሔርተኝነት መንስኤ የገዥና ተገዥ (ቅኝ ገዥና ቅኝ ተገዥ) ትርክት ሲሆን ምንም እንኳን ትርክቱ እውነትነት ያለው ባይሆንም ይኸው ይዞት የተነሳው ትርክት ግብ መትቶ ውጤታማ እንዲሆን አስችሎታል።ይህም ማለት የሻዕቢያ ብሔርተኝነት ውጤታማ ተደርጎ የሚታየው በአሁኑ ሰዓት ኤርትራ የተባለች ሉዓላዊት አገር መመሥረት ማስቻሉ ነው፤ ሉዓላዊት አገር ከተመሠረተች በኋላ ያለው አገዛዝ አምባገነን መሆን እና የአገሪቱ አለመበልፀግ ከፊተኛው መንስኤ (ገዥና ተገዥትርክት) ጋር ሊደባለቅ አይገባም ምክኒያቱም ኤርትራ ነጻ ሃገርከ ሆነች በኋላ ዴሞክራሲያዊና የበለፀገች መሆን ወይም አለመሆን ከራሳቸው የኤርትራዊያን የውስጥ ጉዳይ እንጅ እንደ ምክኒያት ይዘውት ከተነሱት የገዥ ተገዥ ትርክት አኳያ የሚመዘን አይሆንም።

ሐ) የማንነት ብሔርተኝነት ዓለም-አቀፋዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች

የማንነት ብሔርተኝንት የቆዬ ነው በኢትዮጵያ አልተጀመረም። የማንነት ብሔርተኝነትን መሠረት ያደረገ ሌላ አገር የለም የሚለው ውሸት ነው። ማንነትን መሠረት ያደረገ ብሔርተኝነት አገር አፍራሽ፣ አደገኛ፣ የበላይነት ርዕዮት (supermacist ideology) ወዘተ የሚሉ አሉታዊ አስተያየቶች የሚሰነዘሩበት ብሔርተኝነት ቢሆንም ከ18ኛው እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን በአውሮጳ ተስፋፍቶ የነበረ ብሔርተኝነት ነው። በቅርብ ጊዜ ደግሞ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ በርካታ የምስራቅ አውሮጳ አገራትን ለነጻነት ያበቃ እንቅስቃሴ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለይ በምዕራቡ ዓለም ተቀባይነት እያገኘ የመጣ አስተሳሰብ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከአሥራ ሦስት በላይ በሚሆኑ የአውሮጳ አገራት ውስጥ የማንነት ብሔርተኝነት በአዲስ መልክ አንሰራርቷል። በኦስትሪያ፣ በኔዘርላንድ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመንና በጣልያን “far-right” በመባል የሚታወቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ ተቀባይነት በህዝብ ውስጥ እያገኙ መጥተዋል። እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም በኦስትሪያ ውስጥ በተደረገው አገራዊ ምርጫ የብሔርተኛው ድርጅት “Freedom Party” አመራር ኖበርት ሆፈር በምርጫው ተሸናፊ ይሁኑ እንጅ ከአጠቃላይ ድምፅ ውስጥ አርባ ስድስት ነጥብ ሰባት (46.7) በመቶ ድርሻው በማግኘት ብሔርተኝነቱ በህዝቡ ተቀባይነት ያለው መሆኑን አሳይተዋል። በፈረንሳይ የፕሬዚደንት ኢማኑአል ማክሮን ተገዳዳሪ ሰላሳ ሶስት ነጥብ ዘጠኝ (33.9) በመቶ ድምፅ ለማግኘት ችለዋል። በግልፅ “I am nationalist” የሚለው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካን እያስተዳደረ ነው (ትራምፕ አሜሪካ ለአማሪካዊያን የሚል አስተሳሰብ ያለው ሲሆን ለዓለም-አቀፍ ተቋማት የሚደረጉ እርዳታዎች በመቀነስ ወይም በማስቀረት እንዲሁም አሜሪካን ለታላላቅ ዓለም-አቀፋዊ ድርጅቶች እንድትወጣ በማድረግ የሚታወቅ መሪ ነው)፤ ብራዚል አዲስ ብሔርተኛ ፕሬዚደንት መርጣለች። በኔዘርላንድ ፓርላማ ከ150 መቀመጫዎች ውስጥ 20ዎቹ በቅርብ በተመሠረተ ብሔርተኛ ድርጅት (the Dutch Party for Freedom(PVV)) የተያዙናቸው። የጀርመኑ “Alternative for Germanay (AfG)” የምርጫ ቅስቀሳው ትኩረት አገራዊ ደህንነት እና ስደተኞችን መቆጣጠር (national security and immigration) የሚል ሲሆን ከፓርላማው መቀመጫ 3ኛውን ትልቅ ቦታ ይዟል። The New York Times እ.ኤ.አ ዴሴምበር 28፣ 2018 ይዞት በወጣው እትሙ የጀርመን ብሔተኞች የተመለከተ ዘገባ ወጣቶች ሲሆኑ የተሻለ የሚለብሱ፣ የተሻለ የተማሩ ነገር ግን ቁጡ-ያልሆኑ (less angry) ሲል ይገልጻቸዋል፤ አላማቸው ጀርመንን የጀርመናዊያን ብቻ ማድረግ ነው በተለይም አገራቸውን ከአክራሪዎችንና ከስደተኞች ቀዳሚ አጀንዳቸው መሆኑን ዘግቧል ።

ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱት ብሔርተኛ ፓርቲዎች ጥቃቅን ልዩነቶች ይኑሯቸው እንጅ የእንቅስቃሴያቸው አስኳል ህዝባቸውን ከመድብለ-ባህላዊና ግሎባላይዜሽን (ዓለም አቀፋዊነት) ተፅዕኖ በመከላከል ተመሳሳይ ማንነት ያለው ማኅበረሰብ (ethnically homogeneous society) በመፍጠር አገራቸውን ማዳን ነው።

መ) ሉታኒያ – የማንነት ብሔርተኝነት መልካም ምሳሌ

ከ30 ዓመት በፊት ገደማ ነጻነቷን ያገኘችውና ከማንነት ብሔርተኝነት ጋር ስሟ ተያይዞ የሚነሳው የማንነት ብሔርተኝነት አቀንቃኞች እንደ መልካም ማሳያ የሚወስዷት አገር ሉታኒያ ነች። ሉታንያ በምሥራቅ አውሮጳ የምትገኝ ትንሽ አገር ስትሆን እ.ኤ.አ.ከ 1940 ዓ.ም ጀምሮ በሶብዬት ህብረት ውስጥ የተጠቃለለች አገር ነበረች። ይሁን እንጅ ሉታንያዊያን በሶብዬት ህብረት ውስጥ መብታችን ሊከበር አልቻለም፣ ሉታኒያዊያን ሊተዳደሩ የሚገባቸው በሉታንያዊያን ነው፣ ሉታንያ ጥንትም የነበረች በመሆኑ ወደቀደመ ማንነቷ ልትመለስ ይገባል ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት እንቅስቃሴ አድርገው መጨረሻ ላይ ትግላቸው ውጤታማ ሆኖ ሉታንያ ነጻ አገር መሆኗን እ.ኤ.አ. ከማርች 11 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ አውጃለች። ሉታንያ ነጻ አገር መሆኗን ካወጀች ጀምሮ ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና የዜጎች መብቶች የሚከበሩባት አገር በመሆን ትታወቃለች። በሉታንያ ውስጥ የግለሰብ መብት ዘር፣ የቆዳ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለይ እስከ ጥግ ድረስ ይከበራል፣ ሉታንያ ለጎረቤቶቿም ሆነ ለቀሪው ዓለም ሠላማዊና ተባባሪ ነች፤ በተለይ ሉታንያ ነጻነቷን በአወጀችበት በጥቂት ጊዜያት ውስጥ የአውሮጳ ህብረት አባል አገር ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ በእርግጥም የሉታንያዊያን እንቅስቃሴ ራስን በራስ የማስተዳደር (Lithuania for Lithuanians) እንጅ ከሉታንያ ውጭ ያለው ጠላት ነው ወይንም ሉታንያዊያን የበላይ ናቸው (Lithuania above everything else) የሚል አንድምታ ያለው አለመሆኑን አሳይታለች። የችካጎ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ስኮማታስ ፖሲስ “In defence of Ethnic nationalism” በሚል ርዕስ The American Conservative ላይ ባስነበቡት ጽሑፋቸው “በማንነት ብሔርተኝነት ላይ ቁልፉ ነጥብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳይ እንጅ ከራስ ወገን ያልሆነን ኅብረተሰብ ወይንም ህዝብ በማጥቃት ላይ ያነጣጠረ አይደለም” ይላሉ። ይህ ከአማራ የማንነት ብሔርተኝነት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። የአማራ ብሔርተኝነት መንሥኤ የአማራ ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ መውደቅ ሲሆን ይህን ችግር የፈጠረው ቀዳሚው ምክኒያት የአማራ አማራ ባለፉት 27 ዓመታት ባልሆኑ ግለሰቦች መመራቱ ነው የሚል እምነት ያለው ነው፤ የአማራን ህዝብ እንደ በረከት ስምዖን ያሉ አማራ ያልሆኑ ሰዎች ሲመሩት መቆየቱ ይታወሳል።

ሠ) ጆርጅያ – የማንነት ብሔርተኝነት ውድቀት ማሳያ

የማንነት ብሔርተኝነት እንቅስቃሴ እንደ ማንኛውም እንቅስቃሴ ህፀፆች የሚኖሩበት ሲሆን በተለይ በማንነት ብሔርተኝነት ስም የበላይነትን ለማስፈን የሚደረግ ሸፍጥ ለከፋ ጉዳት ሊዳርግ ይችላል። የማንነት ብሔርተኝነት የበላይነት ስሜት ባላቸው ቡድኖች ሲጠለፍ አደገኛና አጥፊ እንደሚሆን ምሳሌዎችን ጠቅሶ ማሳየት ይቻላል። የመጀመሪያዋ ምሳሌ ሌላዋ
የምስራቅ አውሮጳ አገር ጆርጅያ ስትሆን ሁለተኛዋ ኢትዮጵያ ነች። ጆርጅያ የማንነት ብሔርተኝነትን ተጠቅማ ከሶቪዬት ኅብረት አገዛዝ ራሷን ነጻ ያወጣች ቢሆንም የበላይነት የሚሰማቸው ቡድኖች(ብሔሮች) የሩሲያን መንግሥት እንደ ከለላ በመጠቅም አገራዊ አመለግባባትና ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ ይገኛሉ። በጆርጅያ ግዛት ውስጥ ሦስት ብሔሮች ይገኛሉ፤ አብኻዚያ (Abkhazians)፣ ኦስሺያ (Ossetians) እና ቲቢሊሲ (Tbilisi) ናቸው። የብላድሚር ፑቲን መንግሥት አብኻዚያኖችንና ኦስሺያኖችን በጥቅም በመደለል ቲቢሊሲዎች ከእናንተ ጋር እኩል አይደሉም የሚል ትርክት በመፍጠር የጆርጅያን አንድ አምስተኛ ግዛት ለመያዝ የበቃ ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ በብሔሮች መካከል ግጭትን በመፍጠር ጆርጅያ የተረጋጋ ማዕከላዊ መንግሥት እንዳይኖራት አድርጓል። በተለይ”ምርጫው ተጭበርብሯል” የሚሉ ቡድኖችን በማሰማራት አለመረጋጋቱ እንዲቀጥል ሆኖል። በሩሲያ ጣልቃ ገብነት ምክኒያት ጆርጅያ የሚያባራ ጦርነት ውስጥ ለመግባት የተቃረበች አገር ሆናለች (ይህ ጉዳይ ህወሓት በቅማንት ስም የአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ሰላም ለመንሳት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጋር ተመሳሳይ አካሄድ ያለው ነው)። ። በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 27ዓመታት በማንነት ብሔርተኝነት ስም ተጀቡኖ የትግራይን የበላይነት ለማረጋገጥ በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ህወሓት) ሲካሄድ የቆየው እንቅስቃሴ ከዚህ ዘርፍ የሚመደብ ነው፤ አማራን በጨቋኝነት በመፈረጅ በመላ አገሪቱ የእርስበርስ ግጭትን የሚያስፋፉ ቡድናዊ አመለካከቶችን (group sentiments) በማስረፀና በማቧደን (ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴን ወዘተ) ተቋማዊ አሰራር በመፍጠር ከፍተኛ ሰቆቃና የሰብዓዊ መብትጥሰት ሊያስከትል ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ በየቦታው አስተዳደራዊ በደል ከማድረሱም ባሻገር የዘር ማፀዳት፣ የዘርማጥፋት፣ የማንነት ቀውስ፣ እና አገራዊ ሃብትና ንብረት ብክነትን አስከትሏል።

ረ) በዜግነት ላይ ያተኮረ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች የአማራ ብሔርተኞችን የሚጠሉባቸው ምክኒያቶች

ኢትዮጵያ ውስጥ በማንነት ብሔርተኝነት ላይ በተለይም በአማራ ብሔርተኝነት ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችና አሉታዊ አስተያየቶች በተለያዩ ምንክኒያቶች የሚመነጩ ናቸው። የመጀመሪያው ምክኒያት በማንነት ብሔርተኝነት ላይ ጥልቅ ግንዛቤ የሌለውን የኅብረተሰብ ክፍል በዲስኩር (propaganda) በማምታታት እና የማንነት ብሔርተኝነትን በማንነት ካባ የተሸፈነ የበላይነት ብሔርተኝነት (superiority nationalism) አስመስሎ በማቅረብ ህብረተሰቡ ጠልቶ እንዲሸሽው የማድረግ ሂደት ነው። ለምሣሌ በአማራ ብሔርተኝነት ላይ ትችት የሚሰነዝሩት የኦሮሞ ኦንላይን ጋዜጦች (ayaantuu የተባለውን እና Addis Standardን መጥቀስ ይቻላል) የአማራ ብሔርተኝነት ጥርስ-አልባ (toothless) ነው በማለት የሚያናንቁት ሲሆን በምትኩ ግንቦት 7 ለአማራ ህዝብ የሚመጥን አድርገው ቅስቀሰ ይሰራሉ። እውነታው ግን ለአማራ ህዝብ ከአብራኩ ከወጡት ከአማራ ብሔርተኞች የበለጠ ግንቦት 7ም ሆነ የኦሮሞ ብሔርተኛ ጋዜጦች ሊቆረቆሩለት የማይችሉ መሆኑ ነው።

ሁለተኛው ምክኒያት የዜግነት ብሔርተኝነት አራማጆች የማንነት ብሔርተኝነትን ከአገር ምሥረታ ጋር ብቻ አቆራኝቶ የማየት አባዜ ነው። ይኸውም ብሔርተኝነት ከግዛት ክፍፍል ጋር ተያይዞ ጠብ ቀስቃሽ ነው የሚል ስጋት ማስተጋባታቸው ነው። ይህን ስጋት ፉርሽ የሚያደርገው እንደ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኔዘርላንድ፣ ኦስትሪያ፣ ብራዚል ወዘተ ባሉ አገሮች ውስጥ ብሔርተኛ ድርጅቶች መፈጠራቸውና ጉልበት ማግኘታቸው ነው። በምዕራቡ አገራት ተቀባይነት እያገኙ የመጡት ብሔርተኛ ድርጅቶች አዲስ አገር የመመሥረት ዓላማ ያላቸው እንዳይደሉት ሁሉ ማንኛውንም ብሔርተኛ ድርጅት እንደ ተገንጣይ እና አገር መሥራች አድርጎ መመልከት ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ነው። በመሠረቱ የማንነት ብሔርተኝነት የአገር ምሥረታን የሚመለከትበት አግባብ በቅጡ ከተጤነ እንዲህ ዓይነት የጅምላ ተቃውሞ ትክክል አለመሆኑን መረዳት ይቻላል።

ምሳሌ፤

ተመሣሣይ ቋንቋ የሚናገር አንድ ማህበረሰብ አለ እንበል። ይህን ቋንቋ አማርኛ እንበለው። ይህ አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ ተመሳሳይ ባህላዊ እሴቶችን፣ ባሕልን እና እምነቶችን ይካፈላል እና በአጠቃላይ አንድ ሃይማኖት አለው እንበል። በጊዜ ሂደት እነዚህ የማህበረሰብ አባላት (አማሮች) የራሳቸውን ማንነት ያዳብሩ እና የተለያዩ ቋንቋዎችን ከሚናገሩ ወይንም የተለየ እምነት ካላቸው ከሌሎች ቡድኖች የተለዩ ይሆናሉ። ብሔር ይሆናሉ ማለት ነው። ከጊዜ በኋላ ደግሞ እነዚህ የአማርኛ ተናጋሪ ብሔር አባላት ማንነታቸውን የሚስብ የጂኦግራፊያዊ አካባቢን (መልክዓ ምድርን) ይወስናሉ። ይህን አደረጉ ማለት ግን አዲስ አገር ፈጠሩ ማለት አይደለም። በዚህ ደረጃ ያለ ሁናቴ በእንግሊዝኛው አጠራር “nation” ይባላል፤ ወያኔ “nation” የሚለውን ቃል” ብሔር ብሔረሰቦች” ብሎ ይጠራዋል፤ ወያኔ የተጠቀመበት ቃል ትክክለኛ ፅንሰ-ሃሳቡን ካለመግለፁም በላይ ብሔር የሚለውን የማንነት መግለጫ ቃል ከ”nation” ጋር በድርብ መጠቀሙ ውዥምብርን ፈጥሯል። ለ”nation” በጣም የሚቀርበው ቃል ክፍለ-ሃገር የሚለው ነው። ክፍለ-ሃገር ሉዓላዊ ግዛት የለውም። ስለዚህ የማንነት ብሔርተኝነት ከግዛት (realm) ጋር የተያያዘ አይደለም፤ ብቻውን የቆመ ነው፤ የሚወክለው ማህበረሰቡን ነው፤ ግዛቱን አይደለም። የብሔሩ ያሉበት አካባቢ በሙሉ የብሔሩ ክፍል ነው። ለዚህም ይመስለኛል አብዛኞቹ የአማራ ብሔርተኛ ድርጅቶች የአማራ አገሩ መላው ኢትዮጵያ ነች የሚሉት።

ኔሽን (ክፍለ-ሃገር) ሉዓላዊነት የለውም። ኔሽን ሉዓላዊ ሆኖ ወደ አገርነት ለመቀየር ሀገረ-መንግሥት (state-nation) መመስረት ይኖርበታል። ይህ ደግሞ እውን የሚሆነው ኔሽኑ ፖለቲካዊ አንድነት ለመፍጠር የሚያስችሉ የመንግስት መዋቅሮችን ማቋቋም ሲጀምርና ጂኦግራፊያዊ ወሰኑን መጠበቅ ሲጀምር ነው።

በመሆኑም የአማራ ብሔርተኝነት አሁን ባለበት ደረጃ የሀገረ-መንግሥትነት ጥያቄ የለውም። አለው እንኳን ቢባል ሊኖረው የሚችለው የነጻ-መንግሥትነት ጥያቄ እንጅ የሉዓላዊነት አይደለም።

ሶስተኛው ምክኒያት የአማራ ህዝብ በተለይም የአማራ ምሁራን የፕሮፓጋንዳ ሰለባ መሆናቸው ነው። ባለፉት አርባ አመታት አማራው “የኢትዮጵያ ጠባቂ” ተደርጎ እንዲሳልና የማንነት ብሔርተኝነት ኢትዮጵያን የማፍረስ እንቅስቃሴ ነው ብሎ እንዲያምን እና ዘወትር ተቃዋሚ ሆኖ እንዲሰለፍ በጥናት ላይ የተመሰረተ ፕሮጋንዳ ተሰርቶበታል። ይህ ፕሮፓጋንዳ አማራው ያለበትን ሁኔታ እንዳያስተውል ከመገደቡም በላይ የአማራው ህዝብ የማንነት ብሔርተኝነትን በሩቁ እንዲፀየፈው አድርጎታል። በፀረ-አማራ ቡድኖች የተዘጋጀለት አደገኛ ወጥመድ አማራው በኢትዮጵያ ስም ገንዘቡን፣ ሃብቱና ንብረቱን ለሌቦች እንዲገብር አድርጎታል። ከምንም በላይ ይህ የፕሮፓጋንዳ ወጥመድ አማራው በሁለት ጎራ ተከፍሎ እርስበርስ እንዳይስማማ አድርጎታል። አሁንም ቢሆን በህብረ-ብሔራዊነት ወይንም በዜግነት ብሔርተኝነትና በማንነት ብሔርተኝነት ጎራ ለይቶ እርስበርሱ እየታገለ የሚገኘው አማራው ነው።

አራተኛው ምክኒያት ህወሓት ያራምደው የነበረው የበላይነት ብሔርተኝነት (superiority nationalism) በዜግነት ብሔርተኝነት አራማጆች ላይ የፈጠረው የተጠቂነት ስሜት (victim mentality) ነው። ይህ የተጠቂነት ስሜት የማንነት ብሔርተኝነት ሁሉ እንደ ህወሓት ጨፍጫፊ፣ አሳሪ፣ ዘራፊ እና አፋኝ መስሎ እንዲታያቸው አድርጓል።

ማጠቃለያ
——-

ሲጠቃለል የማንነት ብሔርተኝነት እንደ ማንኛውም የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ መልካምም መጥፎም ጎኖች ይኖሩታል። መጥፎ ነገሩን ብቻ እየነቀሱ አማራው ተደራጅቶ እንደ ብሔር የሚደርስበትን ጥቃት እንዳይከላከል ማድረግ በምንም መመዘኛ ትክክል ሊሆን አይችልም። ባለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚታገል ድርጅት ወይንም ቡድን የቀድሞ ሥርዓት
ናፋቂ፣ ጨቋኝ፣ በዝባዥ እና ትምክህተኛ አድርጎ በመፈረጅ ከፖለቲካው ምህዳር እንዲገለል ሲደረግ ቆይቷል። አማራው ራሱን ያደረጀው ኢትዮጵያዊ በሚለው ብሔርተኝነት ሥር ብቻ ስለነበር ተጎጅ ሆኗል። በእቅድ የተፈፀመው አማራን የማግለል እኩይ ተግባር አማራው ከአገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ እንዲሆን አድርጎታል። አሁን ደግሞ ሁኔታውን በአንክሮ ያጠኑ በአብዛኛው ወጣት አማሮች የአማራን ብሔርተኝነት በማራመድ ከፖለቲካ ውይይት ውጭ የተደረገውን ህዝብ ወደ ውይይት መመለስ ሲጀምር በማንነት ላይ የተመሰረተ ብሔርተኝነትን “አደገኛ” አድርጎ ማስቀመጥ አማራው ይዞት የሚነሳውን አጀንዳ በሙሉ ጥቅም የለሽ ወይንም ጎጅ በማድረግ አማራው በተቀውሞ ጎራ ብቻ እንዲሰለፍና የሥልጣን ተጋሪ እንዳይሆን የማድረግ የተለመደ አካሄድ ነው። የማንነት ብሔርተኝነት የተጠላው አማራ ሲያራምደው ነው። የማንነት
ብሔርተኝነት ዱሮም የነበረ ወደፊትም የሚኖር ነው። የማንነት ብሔርተኝነትን በማራመድ የአማራ ህዝብ የመጀመሪያም የመጨረሻም አይደለም።

በአቶ በረከት ስምኦን ጉዳይ .. አና ጎሜሽ የአውሮፓ ፓርላማ አባል

አና ጎሜሽ የአውሮፓ ፓርላማ አባል

“እፎይታ ተሰምቶኛል። እኝህ ሰው በኢትዮጵያ በተፈጸመው የመብት ረገጣ እጅግ የከፋ የመብት ጥሰትና የተዛባ መረጃ በማሠራጨት ሚና ነበራቸው ብዬ ስለማምን በኃላፊነት በመጠየቃቸው ትልቅ እፎይታ ነው የተሰማኝ።” አና ጎሜሽ የአውሮፓ ፓርላማ አባል።ዋሺንግተን ዲሲ — 

በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት ቀድሞው የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ሚንስትር የአቶ በረከት ስምኦን እስር ዜና አሁንም እያነገገረ ነው።

አቶ በረከት በገዥው ፓርቲ ውስጥ የነበራቸውንና ለረዥም ዓመታት የዘለቀ ከፍተኛ የፖለቲካ ሚናና የመንግሥት ሥልጣን ተንተርሶ የተለየ ትኩረት የሳበው እስራቸው፤ ከተለያዩ አካባቢዎች በርካታ አስተያየትችን ጋብዟል።

ከዚህ ቀደም በትዊተር አማካኝነት ባስተላለፏቸው መልዕክቶች “አቶ በረከት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የሚል አስተያየት የሰነዘሩት የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ ሚስ አና ጎሜሽ የቀድሞው የኢሕአዴግ ባለ ሥልጣን እስር ዜና እንደተሰማ እርምጃውን በማወደስ ፈጥነው አስተያየታቸውን ካሰፈሩት ውስጥ ናቸው።

አቶ በረከት ስሞኦን
አቶ በረከት ስሞኦን

ሚስ አና ጎሜሽ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲያ ጉዳዮች ዙሪያ ጠንከር ያሉ ትችቶችን በማቅረብም ይታወቃሉ። ይህንኑ አስተያየታቸውን መነሻ በማድረግ ከሚስ ጎሜሽ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ዝርዝሩን ይዟል።

“የተከሰሱበትን ጭብጥ ሙሉ በሙሉ ባላውቅም .. በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በደረሰው በደል፣ በበኩላቸው በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ይሆናሉ፤ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።” የሚሉት ሚስ ጎሜሽ – የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚያ ቀደም ታይቶ በማያውቅ ደረጃ ወጥቶ ድምጹን በሰጠበት፣ የአውሮፓ ሕብረትን በመወከል በታዛቢነት በተሳተፉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ወቅት ያዩትን ዋቢ አድርገው፤ ከአቶ በረከት ጋር በቀጥታ የተገናኙባቸውን ጊዜያት ያነሳሉ።

በኢትዮጵያ በመጣው “እጅግ አሰደናቂ” ባሉት ለውጥ .. ከሀገራቸው ውጭ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ተቃዋሚዎች ወደ ሃገር እንዲገቡ መደረጋቸው፣ የሚያምኑትን በግልጽ መናገር መቻላቸው “አሳድሮብኛል” ያሉትን ትልቅ ተሥፋም ሚስ ጎሜሽ ገልጠዋል።

16x9 Image

አሉላ ከበደ

ጥቂት “ስለ አቶ በረከት ልጆች” (ገዛኸኝ ሰርቤሳ)

የአቶ በረከት ስምኦን በሌብነት ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ እሳቸው በሌብነት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጉዳዮችም ሊጠየቁ እንደሚገባ በቀደም እለት የኢሳት ቴሌቭዥን ባቀረበው እና አቶ ኤርሚያስም የተሳተፉበትን ውይይት አጣጠሜዋለሁ፡፡ እናም የውይይቱ ጭብጥ ባጭሩ አቶ በረከት ስምኦን ሊጠየቁ የሚችሉባቸው ጉዳዮች

 • በሰብአዊ መብት ጥሰት (ያሳሰሯቸው፣ ደብዛቸው እንዲጠፋ ያሰወሯቸው፣ ምናልባትም በድብቅ ያስገደሏቸው በርካታ ዜጎች እንዳሉ በስፋት ይነገራል)፣
 • በ97 ምርጫ ወቅት እና ከዚያ በኋላ በርካታ በአገርና በዜጎች ላይ ያደረሷቸው እና እንዲደርስ ያስደረጓቸው ወንጀሎች፣
 • ስልጣንን ያለአገባብ በመጠቀም ለግልና ለፖለቲካ ትርፍ ማዋል፣
 • ሀሰተኛ እና አሳሳች ወሬ በመንዛት እና እንዲሰራጭ በማድረግ፣
 • በፍርድ ቤት አሰራር ጣልቃ በመገባትና ፍትህን በማዛባት (ዳኞችን በቀጥታ በማዘዝ፣ በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ ጥፋተኞችን ከህግ ውጭ ከእስር በማስፈታት፣ ያለጥፋታቸው እና ያለበቂ ማስረጃ ሰዎች እንዲታሰሩ እና እንዲንገላቱ በማድረግና በማስደረግ)
 • በአገሪቱ የገንዘብ ስርዓት ውስጥ ባንኮች ያላአገባብ የማይሰበሰብ ብድር እንዲሰጡ  በማድረግ፣
 • የፖለቲካ ሴራ በማካሄድ አገሪቱን ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንደትጓዝ የማድረግ ሙከራዎች እና

በተመሳሳይ ተጨማሪ ወንጀሎች ሊጠየቁ እንደሚገባ ሌሎች የሚጋሩኝ የሚመስለኝ የግሌም እምነት ነው፡፡

በአጭሩ ይህን ጉዳይ ላንሳ እንጂ አሁን ማውጋት የፈለግኩት የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ፣ የመንግስት ሰራተኞችን የሚሰልል እና የሚያስፈራራ አሰራር እና ይህን ለማስፈፀም በየመንግስት መሰሪያ ቤቶች አሰማርቷቸው ስለነበር እና አሁንም በስራቸው ላይ ባለዑት እና አተ በረከት ስምኦን ስለአሰማራቸው ቅጥረኞች ወይም “የአቶ በረከት ልጆች” ጉዳይ ነው፡፡

“የአቶ በረከት ልጆች” ያልኳቸው በየመንግስት መስሪያ ቤቶች “በከፍተኛ ደመወዝ” እንዲመደቡ የተደረጉ እና ከመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ደንብና ስርዓት ውጭ በርካታ ስርዓት አልባ የሆነ ጉዳይ ሲፈፅሙና እና የስለላ ስራ ሲያከናውኑ የነበሩ የስርዓቱ ቅጥረኛችን ጉዳይ ለመጠቆም ነው፡፡

ከምርጫ 97 በኋላ ኢህአዴግ መንግስት የሚሰራውን ስራ የማሳወቅ ስራዬን ለመወጣት በሚል የመንግስት ኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ካቋቋመ በኋላ በአቶ በረከት የወያኔያዊ ስልት እና አካሄድ ከክልሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ምናልባትም ከመንገድ ሊሆን ይችላል የእነሱን አላማ በጭፍን ይሁን የግል ጥቅም ለማግኘት የሚደግፉ ሰዎችን በማሰባሰብና በማእከል በማሰባሰብ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ “የኮሚኒኬሽን ኦፊሰር” በሚል የስራ መደብ ያለምንም መዋቅር ደመወዝ ተቆርጦላቸው እንዲመደቡ ተደርገዋል፡፡ ለእነዚህ “ስርዓት አልባ ተቀጣሪዎች” ደመወዝ ደግሞ ለቀድሞ የተፈቀደ መዋቅር የሚጠይቀው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ያለምንም የመዋቅር ጥያቄ የተጠየውን ሁሉ ይፈቅድ ነበር፡፡ እነዚህ ባለልዩ ባለመብቶች እና የፓለቲካ ተመዳቢዎችን ነው “የአቶ በረከት ልጆች” የምንላቸው፡፡

“የአቶ በረከት ልጆች” ተፈጥሯዊ ገፅታ

 1. “የአቶ በረከት ልጆች” በየመንግስት መስሪያ ቤቱ ሲመደቡ ከመስሪያ ቤቶች መዋቅር ውጭ እንዲሆን መደረጉ በወያኔያዊ ስልት የተለየ ትኩረት የተቸራቸው ናቸው – በአቋሯጭ አዳጊዎች ናቸው፡፡
 2. “የአቶ በረከት ልጆች” የመንግስት ኮሚኒኬሽን ኦፊሰርነት ስራን ያገኙት ለሁሉም ዜጎች አኩል የመወዳደርን እድል በመንፈግ ሲሆን የስራ እድሉን እንዲያገኙ የተደረጉት በፖለቲካ መስፈርት ብቻ መሆኑ ልዩ ባህርያቸው ነው፡፡
 3. “የአቶ በረከት ልጆች” ለኮሚኒኬሽን ኦፊሰርነት የስራ ደረጃ የሚያስፈልገውን የትምህርትና የሙያ ተፈላጊ መስፈርት አሟልተው ሳይሆን በፖለቲካ አመለካከታቸው እና ለፖለቲካ አቃጣሪነት እና ለስለላ ስራ ፈቃደኝነትን ብቻ የሚጠይቅ እና ከየትኛው አይነት ሙያ (እኔ በቅርበት የማውቃቸው እንኳ የስታቲስቲክስ፣ የኬሚስትሪ፣ የሂሳብ፣ የጂኦግራፊ … አንዳዳንዶች ደግሞ ምናልባትም “የምንም” ሙያ ያላቸው ነበሩ፣ የሚገርመው አሁንም አሉ – ሰሚና የሚፈራቸው ግን ያላቸው አይመስልም፡)፡፡
 4. “የአቶ በረከት ልጆች” በፈቃደኝነት ከየቦታው ተሰባስበው መጥተው በአዲስ አበባ የቤት ችግር እንዳይገጥማቸው ከመንግስት ቤቶች አስተዳደር ድርጅት (የመንግስት ኪራይ ቤቶች አስተዳደር) በቅድሚያ ቤት እየተፈለገ የተሰጣቸው ናቸው -የወያኔ እንቆጳዚዮን ናቸዋ፡፡
 5. “የአቶ በረከትን ልጆች” ከሌላው የኢህአዴግ የነበረችው የኢፌድሪ የሚሏት አገራቸው ስር ካሉ እና በህግና ስርዓት ተቀጥረው ከሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች የሚለያቸው መስፈርት “የአቶ በረከት ልጆች” መሆናቸው ሲሆን የአቶ በረከት የግልና ለስርዓቱ በታማኝነት ለማቀጣር ብቁና ዝግጁ መሆናቸው ብቻ በቂ ነበር፡፡
 6. “የአቶ በረከት ልጆች” ዋና ፍጥረት የኢህአዴግ መንግስት የመረጃ እጥረት እንዳይኖርበት እና በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ያለው የሰራተኛ ሃይልን የመቆጣጠሪያ መሳሪነታቸው ነበር፡፡ በየመስሪያ ቤቱ የስራ ሁኔታ እንዲሁም ሰራተኞች በተፈላጊ ትኩረት በሚያስፈልግ ጉዳይ ላይ ያላቸው እንቅስቃሴ የመሰለልና ለጌቶቻቸው ሪፖርት ማቅረብ ዋነኛ የተፈጠሩበት ስራ ሲሆን በአንዳንድ ተቋማት ሃላፊዎችም ጭምር ይሰለሉ ነበር፡፡ የሚፈሩ ሃላፊዎችም እንደበሩ የሚታወቅ ነው፡፡
 7. ሌላው “የአቶ በረከት ልጆች” የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ የወያኔን መራዥ የፖለቲካ ርእዮት በተለያየ ስብሰባዎች፣ የመልእክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች በመጠቀም ሰራተኞችን በግድም በውድ የመጋት እና እንዲቀበሉት የማድረግ ተግባር የተፈጠሩበት በፍላጎታቸው የተጎናፀፉት የስራ ባህርያቸው ነበር፡፡

“የአቶ በረከት ልጆች” የስራ ላይ ባህርይና አፈፃፀም

“የአቶ በረከት ልጆች” እንደየግለ ባህርያቸው ቅርፀት የተለያዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ሳያስፈልገው የሰው ልጅ የባህርይ ብዙህነት ብቻ መመልከት በቂ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለወያኔ ስርዓት ታማኝነትና የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዊነት በምርጫቸው ጥቅም ላይ የዋሉ እንደሆነ በስፋ የሚታይ ባህርያቸው ነው፡፡ የስርዓቱ መገለጫ የእነሱም መገለጫ በመሆኑ የግል ጥቅም እና ባቋራጭ ማደግ ተመሳሳይነት ይታይባቸዋል፡፡ ፀሃፊው “የአቶ በረከት ልጆች” በመየመስሪያ ቤቱ የመመደብ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ቁጥጥር የማካሄድ ስርዓት ከተዘረጋ ጀምሮ በሁለት መስሪያ ቤቶች ሰርተዋል፡፡ እናም ከፀሃፊው የእውን ልምድ እና ከሌሎች ተሰላይ የመንግስት ሰራተኞች የቃረሟቸውን “የአቶ በረከት ልጆች” አፈፃፀም ለምልከታ ያህል እንደሚከተለው በአጠሪራ (አጠሪራ በአጭር በአጭሩ በአጭሩ የቀረበ አንኳር ሃሳብ እንደማለት ተደርጎ ይወሰድ)ቀርቧል፡፡

 • የግንቦት 20 በዓል በየመስሪያ ቤቱ ሲከበር በዝግጅት ላይ የሚቀር ሰራተኛን መመዘገብ፣ ማስጠንቀቂያ የመስጠትና የማሰጠት፣
 • “የባንዲራ ቀን” ሲከበር ማን ተሳተፈ ማን አልተሳተፈ ይመዘገባል፣ ሲያስፈልግም ተፈላጊውን እርምጃ የማስወሰድ፣
 • መንግስት መረጋጋት ሲሳነው በሚያደርግው የመንግስት ሰራተኞችን የመገምገም አካሄድ ዋነኛ ተዋናይ በመሆኑ የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው በሚሏቸው እና ምንም አይነት ምልክት በማያሳዩ ተጠርጣሪዎች ላይ የግምገማ ናዳ የማውረድ ስራ በማከናወን ለፈሪ ዎች የፍርሃትና የኢህአዴግ አስፈሪ ገፅታን ማያሳየት ሚና ይጫወታሉ፣
 • በተለያዩ የስራ፣ የግለሰብ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ለአቶ በረከት ወይም ለመንግስት ኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ሪፖርት የሚያደርጉ በመሆኑ በአንዳንድ ቦታ የመስሪያ ቤት ሃላፊዎችን ጭምር የማስፈራራት ሁኔታ ታይቷል፣
 • የስራ ግምገማ አቅጣጫን በሚፈልጉት አቅጣጫ እንዲሄድ የማስደረግ፣
 • ለበላይ ሃላፊዎች መረጃ በመስጠት ሰራተኞች እንዲባረሩ የማስደረግ ስራ ይሰሩ ነበር፡፡ በተግባር በነበርኩበት መስሪያ ቤት የገጠመኝን ለማንሳት ያህል በወቅቱ የህዝብ ግንኙነቱን ጃላፊ እና አንድ የቡድን መሪ ለመባረራቸው ምክንያት እራሱ የኮሚኒኬሽን ኦፊሰሩ መሆኑን ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ሲባረሩ የበላይ ሃላፊው ጠርቶ ልቀቁ ወይም ማህደራችሁን አበላሸዋለሁ በማለታቸው ከማይጋፉት ጋር መጋፋት ስለሆነባቸው መልቀቂያ እንዲያስገቡ ተደርግው ተባረዋል፡፡ የተባረሩት በመሰሪያ ቤቱ ሃላፊ በተሰጣቸው ውሳኔ ቢሆንም በማህደራቸው የተያያዘው ሰነድ ግን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተደርጎ ነው በሀሰት የተቀመጠው፡፡
 • አንዳንዶቹ በእርግጥ በእውን የገጠመኝ ነገር ደመዎዝ ያንሰኛል በማለት አዲስ መደብ እንዲከፈት በማስደረግ ያለምንም ውድድር፣ በማይገባ መንገድ የደመወዝ ጭማሪ እንዲያገኝ የሚያስደርጉ ነበሩ፡፡ ይህ ልምድ ደግሞ የአብዛኞቹ “የአቶ በረከት ስምኦን ልጆች” ባህርይ ነው፡፡
 • ከሌላው በተለየ ሁኔታ እና ያለምንም ውድድር በድርጅታቸውና በመንግስት በኩል ልዩ ልዩ የትምህርት እድል እንዲያገኙ የሚደረግ ሲሆን ዋናውን የመሰሪያ ቤት ስራ እየሰሩ የሚኖሩ የተመልካችነትና ምን ዋጋ አለው ወደሚል ዝንባሌ የመግፋትና ሞራል የመጣል ሚና እንዲጫወቱ ከፍትኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
 • “የአቶ በረከት ልጆች” በትክክልኛ አገላለፅ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው ለማለት የሚያስችል መስፈርት የማያማሉ ቢሆንም በመስሪያ ቤቶች ዋና ዋና እና ወሳኝ ኮሚቴዎች ውስጥ የመመደብ እና የሚፈልጉትን ውሳኔ ማስወሰን ስራ ያከናውኑ ነበር፡፡

በበኩሌ “ስለ አቶ በረከት ልጆች” በጥቂቱ በተወሰነ መስሪያ ቤት እንዲያውም በሁለት መስሪያ ቤት፣ በሌላ እንዲያውም በአብዛኛው ከአንድ መስሪያ ቤት ብቻ ያየሁትንና የገጠመኝን ልምዴን ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡ በየመስሪያ ቤቱ በእነዚህ “የፓለቲካ አቃጣሪነት ሰራተኞች” አፈፃፀም እና ያስከተሉት በደልና ግፍ ቢዘረዘር በርካታ መሆኑን አልጠራጠርም፡፡ ይህን “የአቶ በረከት ልጆች” የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ እጃቸው ከዘረጉት ዋናዎች መካከል አቶ ኤርምያስ ለገሰም እንደነበሩበት በስፋት  የሚነገር በመሆኑ እሳቸውም ስርዓቱን ከድተው አሁን ውጭ አገር የሚኖሩ በመሆኑ ይህን ፅሁፍ ካነበቡት እራሳቸው ቢናገሩበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡

አመሰግናለሁ – ስላነበባችሁኝ፡፡

ድሬዳዋ የነዋሪዎቿ ብቻ ናት!

እኔም ድሬዳዋ ነኝ:: ከድሬዳዋ ሕዝብ ጎን እቆማለሁ:: የሕዝብን ነፃነትና መብት በኮታ መሸንሸን አይቻልም::

በድሬዳዋ የሚሞከመረው ሕዝብን የማፈናቀልና የነዋሪው ሕዝብን መብት ለመግፈፍና ሊተገበር የሚፈለገው ስነህዝባዊ ምህንድስና Demographic Engineering) እሉታዊ ነው:: መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ በመግባት ሁኔታውን መታደግና ተጠርጣሪዎችን ለሕግ ማቅረብ አለበት።

ደግመን ደጋግመን ብለናል:: አሁንም እንላለን:: ማንኛውም የኢትዮጵያ ግዛት አካል ወይም መሬት የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ወይም የወል ንብረት ነው:: ማንኛውም የሐገሪቱ ሕዝብ የግል እንጂ የወል ንብረት ይዞ አንዱ ለሌላው አላከራየም:: ማንም ይሁን ማንም ለሚኖርበት ቦታ ሠፋሪ ነው:: ከመሬቱ ጋር የተፈጠረ ባለቤት የለም:: ከዚህ በፊት እንዳልነው የአሜሪካ ቀይ ሕንዶች ከአውሮፓውያን በፊት ይስፈሩ እንጂ እነርሱ እራሳቸው ከ12000 እስከ 14000 ዓመታት በፊት ከኤሺያ የመጡ ናቸው::

ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት መብትና ነፃነት እንጂ የመሬት መቀራመትና የመሬት ባለቤትነት ደብተር አይደለም::

“አንዱን ጣትህን ወደ ሌላ ሠው ስትቀስር ቀሪው አራት ጣት ወደ አንተ እንደሚያመለክቱ እወቅ” የሚባለውን እናስተውል!!

ሞት “ለጎሣ ፌደራሊዝም”!
፭፭፭፭፭፮፮

ድሬ ሆይ!

‘ሃዘንሽም ሃዘኔ ነው፣
ችግርሽም ችግሬ ነው፣
ጭንቀትሽም ጭንቀቴ ነው፣
ብሶትሽም ብሶቴ ነው፣
ሃዘንሽም ሲወራ ነብሴም ይጨነቃል፣
ችግርሽን ስሰማ ነብሴ ይጨነቃል።’
(ከመስፍን አበበ ዘፈን የተወሰደ!)

Hailu AT

ማንነትና የማንነት ፖለቲካ

ዛሬ በዚህ ርዕስ ለመጻፍ የተነሳሳሁት በጉዳዩ ባለሙያ ሁኜ ወይንም ልዩ ጥናት አካህጄ ሳይሆን የጉዳዩ ወቅታዊነትና አሳሳቢነት እንደ ዜጋ እረፍት ስለሚነሳኝ ትንሽ ልተንፍስ ብዬ ነው፡፡ አገራችን አሁን ያለችበትን ሁኔታ በተስፋና በስጋት አይን እመለከታለሁ፡፡ ተስፋዬ እድሜ ልኩን እውር ሆእኖ የኖረ ሰው ነገ ዐይንህ ይበራልሀል ሲሉት ሌሊቱን እንዴት አድሬ እንዳለው ግለሰብ ካልሆነ በቀር የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እስካሁን ያልታዬና አበረታች መሆኑ የተስፋየ ምንጭ ነው ፡፡ ስጋቴ ደግሞ ለውጡ መጣብን ብለው የተሸበሩ ቡድኖች ያለ የሌለ ሀይላቸውን ተጠቅመው መቀልበስ እንደማይችሉ እርግጠኛ ብሆንም እያስከተሉት ያለው ወድመት ተባብሶ ብዙ ዋጋ እንዳያስከፍለን ከማሰብ ነው ፡፡

ማንኛውም ለሀገሩ ሉአላዊነት ፣ ለሕዝቡ አንድነት ፣ ለእድገት ፣ ለብልጽግና ፣ ለፍትህና ለእኩልነት የሚያስብና የሚጨንቀው ኢትዮጵያዊ ለውጡን ለማስቀጠል መረባረብና መንግሥትን ማገዝ የጊድ ይላል ፡፡ ያ ካልሆነ ግን እንደ ልማዳችን ሰደን ስናሳድድ እንኖራታለን እንጂ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባታ አንችልም ፡፡

ኢትዮጵያውያን ሁላችንም መቀበል ያለብን አንድ ሀቅ አለ ይሄውም ኢትዮጵያ የሚትባል እኛ ያልፈጠርናት እኛ ግን የተፈጠርንባት እንደየ ወቅቱ ሁኔታ በአዎንታዊም ይሁን አሉታዊ ምክንያቶች በመላዉ ዓለም የምትታወቅ ጥንታዊት አገር እንዳለችን ነው ፡፡ ይህቺን ተፈጥሮ ያደላትን ውብ ሀገር ለኛ በሚስማማን መንገድ አሳድገንና አበልጽገን በጋራ መጠቀም ሲገባን ራሳችን በፈጠርናቸው ችግሮች ምድርቱን ተጠያቂ በማድረግ ለእኔ ያልሆነች አገር ትፍረስ ማለት ድንቁርና ይመስለኛል ፡፡ ትናንትና ፊደል ሳይቆጥር ያስተማረን ወገናችን ብቻውን መወጣት የማይችላቸውን ችግሮች ለመቅረፍ እድር ፣ እቁብ ፣ ደቦ ፣ ጂጊ ፣ የወንፈልና የቃንጃ ወዘተ እያለ ሲደራጅና ሲተባበር ነበር የምናውቀው ፡፡ ዛሬ ግን የምንደራጀው አገር ለማፍረስ ፣ እርስ በርስ ለመገዳደልና ችግር በያይነቱ ለመፈልፈል መሆኑን ስናይ መሃይሙ ባለ ድግሩ ገበሬ የነበረውን ብቃትና ችሎታ የዘመኑ ባለድግሪ ምሁር ነኝ ባይ አጥቶ ለጥፋት ሲጋብዘን ማየትና መስማቱ አሳዛኝና አሳፋሪም ነው የሚሆነው ፡፡

ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ እንዲሉ ለአንድ ዓላማ መተባበሩ ቀርቶ የየራሳችችንን ይዘን መደማመጥም ጥፍቶ እንደ እብድ መጯጯህ ስፍኗል ፤ እናቱ እንደ ሞተችበትና ወንዝ እንደ ሄደችበት ህጻን ሁላችንም እኩል እያለቀስ ነው ፤ ማን ቀልደኛ ማንስ ቁምነገረኛ መሆኑን መረዳት ተስኖናል ።

የሰው ልጅ ከሌሎች እንሰሳት የሚለየው በሁለት ምክንያቶች ይመስለኛል ፡፡ አንደኛው ተፈጥሮን እንዳለ ተጠቃሚ ሳይሆን ለራሱ በሚስማማው መልኩ ቀይሮ መጠቀሙ ሲሆን ሁለተኛው እንደ እንሰሳት ዘወትር ጉልበት ባለው እንደተጠቃ ለመኖር አለመፍቀዱ ነው ፡፡ በሌላ አገላለጽ የሰው ልጅ በህገ አራዊት ዝንተ ዓለም በጉልበትና በጉልበተኛ አይገዛም ማለት ነው ፡፡ ሕዝባችን በታሪኩ ድሞክራሲ የሚባል ነገር በተግባር ሊያገኝ ቀርቶ በትዎሪ ደረጃ በአግባቡ የሚያውቀው ጽንሰ ሀሳብ አይደለም። ይሁን እንጂ በህገ አራዊት በጉልበተኞች ይደርስበት የነበረውን ሁሉ አቀፍ ጭቆና አሜን ብሎ የተቀበለበት ወቅት አልነበረም ፡፡ ሆኖም ግን የሥርአት ለውጥ ለማምጣትና ዲሞክራሲያዊ መስተዳድር ያለው የሕዝብ መንግሥት ለመመስረት አልቻለም ፡፡

ለምን ?

ጥያቄው መሰረታዊና አግባብ ያለው ምላሽ የሚሻ ነው ፡፡ በመሆኑም ብዙም ሳንርቅ የቅርብ ታሪካችንን ብንዳስስ ከመሳፊንቱ ወደ ንጉሣዊ ከንጉሣዊው ወደ ሶሻሊስት መር ስርአት ከዚያም ወደ አብዮታ ድሞክራሲና ዘር ተኮር ፖሌቲካ የገባነው በሕዝቡ ፍላጎትና ነባራዊ ሁኔታ ስለፈቀድ ሳይሆን ጥቂት እኛ እናውቅልሃለን ባይ ግለሰቦችና ቡድኖች ለሥልጣን ሲሉ በጉልበት ስለምጭኑብን ነው ፡፡ ሩሲያውያን አንድ ቆንጆ አባባል አላቸው ይሄውም ብልህ ከሰው ስሕተት ይማራል ጅል ግን ከራሱም ስህተት አይማርም ይላሉ ፡፡ እኛም ከሌላው ይቅርና ከራሳችን ስህተቶች ለመማር አለመቻል ይሁን ካለመፈለግ አሁንም በጎጥ ፖሌቲካ አረንቋ ውስጥ ተረፍቀን መንቀሳቀስ ተስኖን እንወዛወዛለን ፡፡

ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያዊነትን አስረስቶ በትውልድ ቀዬና በጎጥ ተከልለን እርስ በርስ እንድንጠፋፋ ሕወኃት የቀየሰው የጎሣ ፖሌቲካ ሀገሪቷ እንደ ሀገር ሕዝቡም እንደ አንድ ሕዝብ እንዳይኖር አድርጎት እዚያም እዝይህም ብጥብጥ እየተካሄደ የሰው ህይወት እያለፈ ፣ ንብረት እየወደመና ሰው እየተፈናቀለ ይገኛል ፡፡ ትናንትና እኔ አውቅልሃለሁ ባይ ዘረኛ ቡድኖች በጎጥ አደራጅተው መቀመቅ የከተቱን ትምህርት ሊሆነን ሲገባ በአሁኑ መልካም የለጥ ጅማሮ ወቅት አዲስ አይንአውጣ ጎጠኞች አዎን ትምክህተኞች ነን ትምክህተኛ በመሆናችን አናፍርም የሚሉ የተገኙበትን ጎሣ ታሪክና ኢትዮጵያዊ ማንነት ሲያኮሰምኑት ማየትና መስማት ያሳፍራል

፡፡

የጎሣ ፖሌቲካ በአገራችን ዲሞክራሲያዊ ያልሆነው ጎሰኞቹ እንደሚሉት የአፈጻጸም ችግር ኖሮት ወይንም ሕወኃት ስለመራው ሳይሆነ በተፈጥሮው ሰውን በሰውነቱና በግለሰብንቱ የሚገባውን ሁለንተናዊ መብቱን የሚያጎናጽፍ ሳይሆን በትውልድ የዘር ሀረጉ ከሌላው ለይቶ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያደርግና አግላይ በመሆኑ ነው ፡፡ ሕወኃት በፖሌቲካው ፣ በኢኮኖሚውና በማህበራዊ ዘርፉ ጠቅላይና የበላይ እንዲሆን አመቺ ሁኔታን የፈጠረለት የሄው የጎሳ ፖሌቲካ ነው። በመሆኑም ነው አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን

እየመሩ ለትግራ አዲስ የኢድገትና የብልጽግና ፕላን ነድፈው ሳይተገብሩት ሞቱ ብላ ባለቤታቸው አዜብ መስፍን ሙሾ ስታወርድ የሰማናት።

ሕዝባችን ለሃያ ሰባት ዓመት ጎራ ለይቶ ሲገዳደልና ከቄዬው እንዲፈናቀል የተደረገው በየደረጃው ሥልጣን ላይ የነበሩ በሙሉ ክፋተኞች በመሆናቸው ሳይሆን የዘር ፖሌቲካው እትዮጵያን ለማፈራረስና ሕዝቧንም ለመበታተን ላቀደው ህወኃትና ግብረአበሮቹ አዋጭ የመጫወቻ ካርታ በመሆኑ ነው ፡፡ እነኚህ ግለሰቦችና ቡድኖች የመዘዙት ካርድ የተወሰነ መንገድ አስክዷቸዋል ፡፡ ውጤቱም አሁን መሬት ላይ ያለው የስጋታችን ምንጭ የሆነው ትርምስ ነው ፡፡ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የዘር ፖሌቲካው ከድጡ ወደ ማጡ የከተተን የአፈጻጸም ችግር ኖሮት ወይንም ካሁን በፊት ተዋናይ የነበሩ የጎሣ መሪዎች የመተግበር ብቃት አጥተው ሳይሆን በዘር ላይ የተመሰረተ ፖሌቲካ የደም ትስስር ላላቸው የጎሣው አባላት ፖሌቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ የቆመ በመሆኑ ይህንን ተልእኮ ከማስፈጸም ሌላ አማራጭ ስላልነበረው ነው ፡፡

አሮጌዎቹ ጎጠኞች ዳክረው ዳክረው አላዋጣ ያላቸውን የዘር ፖሌቲካ አሁን ደግሞ አዲስ ጎሰኞች በአዲስ አቁሟዳ አሮጌውን የጎጥ ፖሌቲካ ይዘውብን ብቅ አሉ ፡፡ ቁምነገሩ ከአቁሟዳው ሳይሆን በውስጡ ከያዘው ጎሰኝነት ነው ፡፡ ጎሰኝነት የዘር ሀረግ መዞ የሚያቀርብና የሚያገል ዘረኝነት ነው ፡፡ ዘረኝነት ደግሞ ሰወን በስብዕናው ፣ በችሎታው ፣ በስነምግባሩና በአስተዋጽዖው የሚመዝን ሳይሆን የእኔ ወገን ነው በሚል የደም ትስስር የሚለካ ነው ። በመሆኑ አግላይና ጸረ ዲሞክራሲያዊ ነው ፡፡ በመሆኑም በሃያ ሰባት ዓመት የጎጥ ፖሌቲካ በየክልሉ የተካሄደውን የዘር ማጽዳት ዘመቻ ያስከተለውን አሰቃቂ እልቂት ማስታወሱ ብቻ በቂ መረጃ ነው።

ማንነት ምንድን ነው ?

ማንነት አንድ ግለሰብ በህብረተሰቡ ወይንም ማህበረሰቡ ውስጥ ራሱን የዚያ አካል አድርጎ የተቀበለበትና ራሱን ያገኘበት ስፍራ ነው ማለት ይቻላል ፡፡ ራሱን ያገኘበት ስፍራ ደግሞ የሱነቱ መገለጫ የሆኑ የተለያዩ ኤለሜንቶች ወይንም ናኡሳን ክፍሎች ይኖራሉ ። እነዚህን የማንነቱ ናኡሳን ክፍሎች እንዲያድጉ ፣ እንዲበለጽጉ በማህበረሰቡ እኩል ተቀባይነት እንዲኖራቸው ይፈልጋል ። ይህ ተፈጥሮአዊና ተቀባይነት ያለው ነገር ነው። ይህንን ተጻሮ መቆም ግን አግባብነት የለለውና ጸረ መብትና ጸረ ነጻነት ነው ። የሰው ልጅ በህይወት ዘመኑ የተሟላ ደስታ የሚያገኘው በማንነቶቹ ውስጥ ( የሰው ልጅ የተለያዩ ማንነቶች ስላሉት ማለት ነው) መጣጣም (harmony) ሲኖር ነው ፡፡ መጣጣሙ እንዲኖር ደግሞ ሀላፊነቱ የግለሰቡ ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡም ጭምር ነው ።

ግለሰቦች ከተለያዩ የማንነቱ መገለጫዎች አንዱን ወይንም የተወሰኑትን የራሱ አድርጎ ሊቀበል ይችላል መብቱም ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ጎሳዎች አገር እንደመሆኗ መጠን ኢትዮጵያዊነት የዜጎቿ የሁሉም የማንነት መገለጫ ሲሆን ጎሣ ደግሞ የእያንዳንዱ የጎሳው አባላት ማንነቱ ነው ። የማንነት መገለጫ የሆኑ ሌሎች ንኡሳን ክፍሎች ቢኖሩም ለአንድነትም ሆነ ለልዩነት የጎላ ተጽእኖ አሳዳሪ ናቸው የሚል ግምት ስለሌለኝ ለመዘርዘር አልፈለኩም ። የሕዝባችንን ታሪክ መለስ ብለን ከመረመርነው አብሮ ተዋልዶና ተዋህዶ የኖረ ሕዝብ በመሆኑ የማንነት መዛነቅ ስላለ የእኔ ማንነት ይህና ይህ ብቻ ነው ብሎ ለመናገር ድርቅና ካልሆነ በቀር በዲኤንኤ አስመርምሮ የሚያረጋግጥ ኢትዮጵያዊ አይኖርም። ስለሆነም የጋራ ማንነታችንን (ኢትዮጵያዊነትን) እየተንከባከብን ሌሎቹን የማንነት መገለጫዎቻችንን በጋራ በማሳደግና በማበልጸግ አማራጮቻችንን ማስፋት ይኖርብናል ። ከዚህ በተቃራኒው ሄደን ኢትዮጵያን እናፍርሳት ማለት የቆጡን እናወርዳለን ብለን የብብታችንን መጣል ነው የሚሆንብን ።

እንድ ኢትዮጵያ ባሉ ባለ ብዙ ጎሣ አገሮች የመብት ጥያቄዎች የማንነትን ጨምሮ ሊፈቱ የሚችሉት ዲሞክራሲያዊ ሥርአትን በማስፈን ብቻ ነው ። የዲሞክራሲያዊ ሥርአት መፍትሄ የሚሆነው ደግሞ የግለሰብን መት ያለምንም ልዩነት ስለሚያረጋግጥና በዘር ቆጠራ፣ በቁጥር መብዛትና ማነስን መስፈርቱ አድርጎ በቁመቱ ልክ ለአንዱ ቀሚስ ለሌላው ጥብቆ የሚያሰፋ ባለመሆኑ ነው ።

ፖሌቲካችን መሬት የረገጠ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበና ካለፉት ስህተቶቻችን ትምህርት የቀሰምንበት መሆን አለበት እንጂ እያንዳንዱ አዋቂ ነኝ ባይ በሚያቀርበው ፋንታዚ ሊሆን አይገባም ። ሕዝባችንም ዘወትር የአዲስ ርእዮተአለምና የዘር ፖሌቲካ መሞከሪያ አይጥ መሆኑ ማብቃት አለበት ። የዘር ፖሌቲካውን ሁለተኛ ዙር እንሞክር ያለፈው የአተገባበር ችግር እንጂ በራሱ ችግር አይደለም የሚለው ትርክት ሙሉ በሙሉ ስህተት ነው ። ያንን የሚሉት ደግሞ አተገባበሩ ምን መሆን ሲገባው ሳይሆን እንደቀረ በንድፈሃሳብ ደረጃ የሚያቀርቡት አማራጭ እንኳን የላቸውም ። ከሃያ ሰባት አመቱ ተሞክሮ በመነሳት ለሚቀርበው ትችት ምሁራዊ ምላሽ ሳይሆን የድሮን ናፋቂ፣ አሀዳዊ መንግሥት ፈላጊ ፣ በጎሣ የተከለለ ፌደራሊዝም አያዋጣንም ሲባል ጸረ ፌደራሊዝም እያሉ ስድብ ይደረድራሉ ። የጎሣ ፖሌቲካን መቃወም በምንም መስፈርት የሌላውን ጎሣ ቋንቋ ፣ ባህል ፣ወይንም ራስን በራስ የማስተዳደር መብት መቃወም ሊሆን አይችልም ። በጎሣ ፌደራሊዝም የሁሉም መብት የተከበረባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት አይቻልም ብሎ መተቸት የፌደራል ሥርአትን አልቀበልም የሚል ትርጉም ሊሰጥ አይችልም ። መፍትሔው የግለሰብ መብት የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ብቻ ነው ። ለዚህም የሚያስፈልገው የጎጥ ድርጅትና ፖሌቲካ ሳይሆን ሕብረ ብሔራዊ አደረጃጀትና የዜጊነት ፖሌቲካ ነው ።

ስም አልባው ጸሐፊ (Anonymous)

ተማሪዎች ቤታቸው ነው- አንተና ብ አዴን ባህር ዳር መልቀቅ ትችላላችሁ – አያሌው መንበር

አቶ ሙለቀን ሆይ ተማሪዎች ከባህር ዳር መውጣታቸው በፊት አንተ ከንቲባ ቢሮን ለቀህ ውጣ!!

ዝም ስላልን እንጅ እኛም አንተን ውጣ ለማለት የሚያስችል በርካታ ሰነድ አለን።አስፈላጊ ከሆነ ከደቂቃዎች በኃላ እለጥፍልሃለው።

ለጊዜው ግን አንተ የባህር ዳር ከተማ ትምህርት መመሪያ ሀላፊ ሁነህ የክልሉ መዲና ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ጠይማ ት/ቤት ተማሪዎች መሬት ላይ ተቀምጠው ሲማሩ ወንበር እንኳን ማሟላት ያልቻልክና በዚህ ደካማ አፈፃፀምህ ከቦታው የተነሳህ መሆኑን ልንገርህ።

ከንቲባ ስትሆን ዝም ያልነው በብዙ ምክንያቶች እንጅ አንተ ለከንቲባው ቦታ የማትማጥን እንደነበርክ እኮ ይታወቃል።አንድ ጽ/ቤትን መምራት ያልቻለ ከ10 በላይ ጽ/ቤትንና ከተማን የመምራት አቅም ከየት አምጥቶ ነው?

ቢገባህ እኮ ዛሬ ውጡ ያልካቸው አንተ ቁሳቁስ ማሟላት ባልቻልክበት ት/ቤት ሁሉ ችግርን ተቋቁመው ለዚህ የደረሱ እንቁዎች ናቸው።

አንተና ብአዴን ፀባይ ከሌላችሁ ባህር ዳርን መልቀቅ ትችላላችሁ።ተማሪዎች ግን ቤታቸው ነው።

አርበኝነት ምንድን ነው? (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ
ኮተቤ ሜትሮፖሊን ዩኒቨርስቲ

Professor Berhanu Nega with Patriotic Ginbot7 fighters

ቅዳሜ ጥር 04/2011 በዋልታ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ አቶ መንግስቱ ወ/ስላሴን(የአርበኞች ግንቦት ሰባት የቀድሞ የፖለቲካ ጉዳዬች ቃል አቀባይ ወይም የአርበኞች ግንባር መስራች አባል) ቃለ-መጠይቅ አድርጋላቸው ነበር፡፡ በነበረው ውይይት አቶ መንግስቱ ከግንቦት ሰባት ጋር በነበራቸው ውህደት የእነርሱ ፈቃድ እንደሌለበት፣እንደ ድርጅት አብረው እንዳልኖሩ፣በመካከላቸው መለያየት እንደነበር፣ ኢሳት የህዝብ አይንና ጀሮ የሚባልለት ጣቢያ የግንቦት ሰባት እንደነበር፣ ከግንቦት ሰባት አባላት መካከል አንድም ወታደራዊ ዕውቀት ያለው አባል እንዳልነበር፣ ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጋር እንደማይስማሙ ሰማሁ፤ ቀጠል አደረጉና አሁን የሚፈልጉት አርበኝነታቸውን እንደሆነ እና የአርበኝነት ታሪካዊ ዳራ እንዲጠበቅላቸው እንደሚፈልጉ እና ሌሎች ዘርዘር ያሉ ጉዳዬችን ሲናገሩ አዳመጥሁና የዝርዝር ጉዳዩ ጭብጥና አስፈላጊነት ልቃቂቱ ጠፋብኝና ግርምትን ጫረብኝ፡፡

ዘረኛ፤ አድሎዓዊ እና ከፋፋይን ስርዓት ተቃውመው በረሃ የወረዱ ጀግኞች የህብረት-ድምቀትን ፈጥረው ህዝቡን ሊታደጉት ሲገባ እንዴት አርበኞች ግንባር እና ግንቦት ሰባት የነበራቸውን መለያየት በአሁኑ ስዓት ይተርኩልናል? ማውራቱስ ውርደት እንጅ ምን ፖለቲካዊ ጠቀሜታ አለውበዘመነ ህወሃት የተወሰነው የማህበረሰብ ክፍል ከህወሃት አገዛዝ ለመላቀቅ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን የጦር ሃይል ተስፋ ጥሎበት ነበር፡፡ ያ ተስፋ ከንቱ እንደ ነበር አሁን ለህዝቡ መተረኩ ፋይዳው ምንድን ነው? በወያኔ የድቅድቅ ጨለማ ዘመን በመረጃ እጦት ስር የነበረውን ህዝብ ቀን ከሌት ሳይታክት መረጃ ሲያቀርብ የነበረውን ትክክለኛ የመረጃ ቋት(ኢሳትን) ጥላ-ሸት መቀባት ለምን አስፈለገ? በዘመነ-ህወሃት በኢትዮጲያ ፖለቲካ ላይ ልዩ አሻራ ያለውን አንጋፋው ፖለቲከኛን  ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን የስልጣን-ጥም እንዳለበት አድርጎ ማቅረብ ለምን ተፈለገ?

በየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ የሀሳብ ልዩነቶች ሊታዩ ይችላሉ፤ እነዚህን የሀሳብ  ልዩነቶችን በክርክር እና በሀሳብ ብልጫ ማሸነፍ ሲገባን ከስም ማጥፋት አዙሪት ውስጥ መውጣት ኢትዮጲያውያን ለምን ተሳነንበዘመናዊ የኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ከ1960ዎች የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ ትልቁ ችግራችን የመጠላለፍ እና የሴራ ፖለቲካ ነው፡፡ ይህ መጠላለፍ እስካሁን እየተበተበን አንድ ስንዝር የፖለቲካ ለውጥ እንዳናሳይ ምክንያት ሁኖዓል፡፡ ፖለቲካን መሰረት አድርገው ህብረትን በፈጠሩ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚታየው ሽኩቻ፤ ጥላቻ እና ስም ማጥፋት እጅግ አሳዛኝ ከመሆኑም ባሻገር አብዛኛው የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚዎች የቆሙለትን ዓላማ በርካሽ የፖለቲካ ዝና ለመቀየር ሲታትሩ ይታያሉ፡፡ በዶ/ር አብይ ዘመን እንዲህ አይነት የፖለቲካ ሽኩቻ እጅጉን ያስፍራል፡፡

አቶ መንግስቱ ወ/ስላሴ የሚፈልጉት አርበኝነታቸውን እንደሆነ እና የአርበኝነት ታሪካዊ ዳራ እንዲጠበቅላቸው እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡ በርግጥ አቶ መንግስቱ ህወሃትን ለመዋጋት ኤርትራ በረሀ ሂደው ከነበር አርበኛ ናቸው፡፡ ግን አርበኝነት ትርጉሙ ምንድን ነውአርበኝነት ከፅንሰ-ሀሳባዊ ትርጉሙ (Conceptual definition) ይልቅ አውዳዊ ትርጉሙን (operational definition) ስንመረምረው በዘመነ ፋሽስት አርበኛ ማለት ፋሽስትን የተዋጋ፤ የፋሽስትን ስርዓት ተቃውሞ ለፋሽስት ስርዓት እና አገዛዝ ያልተንበረከከና፤ያላጎበደደ ዜጋ ማለት ሲሆን የዚህን ቃል አውዳዊ ትርጉም ካለንበት ዘመን አንፃር ስንቃኘው አርበኛ ማለት በረሃ የወረደ ጀግና  ብቻ ማለት ሳይሆን ሰው በጠፋበት ጊዜ በሰዎች መካከል ሁኖ ስለ-ህዝብ እና ስለ-ሀገር ጥቅም ስርዓቱን በድፍረት የተዋጋ፤ በስርዓቱ ውስጥ ሁኖ ስልታዊ በሆነ የፖለቲካ ጥበብ ስርዓቱን ያዳከመ፤ ለህወሃት አገዛዝ እጅ ያልሰጠ፤ ስርዓቱን የነቀፈ፤የተዋጋ፤የተቸ እና ስርዓቱን ለመቀየር በየትኛውም መንገድ የተገዳደረ በሙሉ አርበኛ ሊባል ይችላል፡፡

ስለሆነም መላ/ዘዴ  በጠፋበት፣ ነገሮች  እስርስር ባሉበት፣ እና ብርሀን በማይትይበት በህወሃት ዘመን በጠፍ ጨረቃ ላይ  እንደ አጥቢያ ኮከብ ጎልተው ብቅ ያሉት እነ ለማ መገርሳ፤ዶ/ር አብይ አህመድ፤እነ ገዱ እንዳርጋቸው፤ ኮ/ር ደመቀ ዘውዱ፤ፖሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፤አንዳርጋቸው ፅጌ እና በርካታ ፀሀፊያን፤ጋዜጠኞች፤ እውነተኛ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በህወሃት ዘመን በፖለቲካ ጉዳይ ህይወታቸውን የገበሩ፤ አካላቸውን ያጡ፤ እስር-ቤት የነበሩ ጀግኖቻችን፤ህወሃትን ለማንበርከክ በየትኛውም መንገድ እውነተኛ ትግል  ያደረጉ በሙሉ አርበኞቻችን ናቸው፤ ልናወድሳቸው እና ልንዘምርላቸው ይገባል፡፡ አርበኝነት ማለት ለትግል በረሀ መውረድ ብቻ ነው ብለን የምንተረጉመው ከሆነ፤ የቃሉ ትርጉም ብቻ ሳይሆን የዘመናዊ የፖለቲካ ትግል ስልትም አልገባንም ማለት ነው፡፡

ከፖለቲካ ዳራው ባሻገርም መለያየት በሰፈነበት ጊዜ አንድነትን፤ ጥላቻ ባንዣበበበት ስርዓት ፍቅርን፤ ቂምና ኩርፊያ በተንሰራፋበት ወቅት  ይቅር-ባይነትን፤ርኩሰት በበዛበት ማህበረሰብ ቅድስናን መስበክና ማስተማርም አርበኝነት ነው፡፡ አርበኝነት ትርጉሙ ሰፊ ነው፡፡

የህወሃት መኳንንት ነገር… (በመስከረም አበራ)

በመስከረም አበራ

Tigray People's Liberation Front (TPLF) in crisis.

በሃያ ሰባት አመታት የህወሃት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ ስርዓት የኖረው የሃገራችን ህዝብ በትግሉ የህወሃትን የበላይነት ከኢትዮጵያም ከኢህአዴግም ትከሻ ማሽቀንጠርን ችሏል፡፡ ስልጣን ሲጥመው የቀረበት ህወሃት ታዲያ እሱ የማይዘውራት ኢትዮጵያ በሰላም ውላ ማደሯን የሚወድ አይመስልም፡፡ በስልጣን ዘመኑ “እኔ ከሌለሁ ሃገር ይፈርሳል” እያለ ሲያስፈራራ ስለኖረ እሱ በሌለበት ሃገር ሰላም ውላ ማደር እንደማትችል ማስመስከር ይፈልጋል፡፡ህዝብ ለውጡን ለመደገፍ ነቅሎ በወጣበት የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦምብ በመወርወር፣በሃገሪቱ አራቱም አቅጣጫ የሚከሰቱ ብጥብጦችን በመቆስቆስ፣እንደ ኦነግ ያለውን ወዳጅ ጠላት የማይለይን የፖለቲካ ቡድን አይዞህ እያለ በማበጣበጥ ይጠረጠራል -ስልጣን ወዳዱ ህወሃት፡፡

ሳይፈልግ ብቻ ሳይሆን ሳያስብ የለውጥ ማዕበል ያጣለመው ህወሃት ለውጡ ይዞት የመጣውን አመራር ለመቀበል እንደተቸገረ ያስታውቅበታል፡፡አሁን የለውጥ ሃይል ሆኖ ስልጣን የተቆናጡት  አካላት(በዋናነት ኦዴፓ እና አዴፓ) ቀድሞ የህወሃት ታማኝ ታዛዥ አገልጋዮቹ የነበሩ መሆናቸው ህወሃት ለራሱ ከሚሰጠው የተጋነነ እና የተሳሳተ ግምት ጋር ሲደመር ያፈጠጠውን እውነት ለመቀበል እንዲቸገር ሳያደርገው አልቀረም፡፡

ህወሃት ሊወድቅ ዘመም ዘመም ሲል ወደ ጀርመን ተጉዘው የህወሃት ደጋፊዎችን ያነጋገሩት አቶ ጌታቸው ረዳ “ህወሃት በሌላ ይታዘዝ ማለት ነውር ነው” ሲሉ የተናገሩት ንግግር ህወሃቶች ንዑስነታቸውን በማይመጠን ሁኔታ ለራሳቸው የሰጡትን ትልቅ ግምት አመላካች ነው፡፡እንዲህ ባለ አለቅጥ በተጋነነ የትልቅነት ስነ-ልቦና ውስጥ የቆየው ህወሃት በራሱ አገልጋዮች ተባርሮ መቀሌ መግባቱ ሊቀበለው የማይፈልገው ሃቅ ነው፡፡ሃቅን መቀበል ባለመቻሉ ሳቢያ በስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ ያለው ህወሃት የራሱን ቀውስ ሃገራዊ ቀውስ ለማስመሰል ታጥቆ እየሰራ ነው፡፡በዚህ ምክንያት በሃገራችን የታየውን የለውጥ ጭላንጭል በማጨለሙ በኩል ህወሃት ቀዳሚው ስጋት ሳይሆን አይቀርም፡፡

ህወሃት የለውጡ ስጋት መሆኑን የሚያስመሰክርበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡የመጀመሪያው እና ዋነኛው በወንበሩ ላይ የተቀመጠውን የለውጥ አመራር እንደመንግስት ለመቀበል መቸገር ነው፡፡ይህ ዝንባሌ ከሚገለፅባቸው ሃቆች አንዱ የዶ/ር አብይ አስተዳደር በወንጀል የሚፈልጋቸውን ግለሰቦች ትግራይ ሰብስቦ ማስቀመጡ ነው፡፡ጌታቸው አሰፋን የመሰለ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ በጉያው የያዘው ህወሃት “ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ይዤ ለማእከላዊው መንግስት የሰጠሁት እኔ ነኝ” ሲልም ይደመጣል፡፡ ጀነራል ክንፈ ዳኘው በተያዙ ሰሞን ወንጀለኞችን ለመያዝ የትግራይ ክልላዊ መንግሰስት ከማዕከላዊው መንግስት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ የክልሉ መሪ ዶ/ር ደብረፅዮን ተናግርው ነበር፡፡ ይህን ብለው አፍታም ሳይቆዩ ደግሞ “ወንጀለኞችን ተጠያቂ የሚያደርገው የመንግት አካሄድ የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ያለመ ነው” ሲሉ ነገሩን ሁሉ እግር በራስ አድርገውት ቁጭ አሉ፡፡ይህ አደገኛ አስተሳሰብ የሚመሩት ክልል ህዝብም የሚጋራው እንደሆነ በተግባር ለማሳየት ሰላማዊ ሰልፍ በማታውቀው ትግራይ ክልል ሰው በቤቱ የቀረ የማይመስልበት ሰልፍ አሰለፉ፡፡

ህግ የሚፈልጋቸውን ተጠርጣሪ ወንጀለኞች የደበቀ ክልል ህገ-መንግስት ይከበር ሲል የዋለበት ሰልፍ የትግራይ ክልል መንግስት ለዶ/ር አብይ አስተዳደር ለመታዘዝ ዝግጁ አለመሆኑን ያስመሰከረበት ነው፡፡ ይህን በመሰለው ለተጠረጠረ ወንጀለኛ ጥብቅና የመቆም ሰልፍ ያሁሉ የትግራይ ህዝብ መገኘቱ ህወሃት እና የትግራይ ህዝብ በጣም የተራራቁ ናቸው ብሎ የሚያስበውን ከትግራይ ውጭ ያለ ሌላው ኢትዮጵያዊ በከፍተኛ ግርምት ውስጥ የከተተ ነበር፡፡

በሰልፉ ሰዓት ከተደረገው የዶ/ር ደብረፅዮን ንግግር በተጨማሪ እንደ አቶ አስመላሽ ገ/ስላሴ፣አቶ ስብሃት ነጋ ያሉ የህወሃት አባላትም በትግራይ ቲቪ ብቅ  እያሉ የሚናገሩት ንግግር ኢትዮጵያ ከህወሃት ውጭ በሌላ መተዳደሯ እንደማይዋጥላቸው የሚያሳብቅ ነው፡፡አልዋጥ ያላቸው ሃቅ ደግሞ ህዝብን አግተልትሎ ሰልፍ ከማስወጣት አልፎ በመላ ሃገሪቱ የሚደረጉ ብጥብጦችን እስከ ማጋፈር የደረሰ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ከመንግስት በኩል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየተገለፀ ነው፡፡

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለፌደራሉ መንግስት አልታዘዝም ከማለት አልፎ ራሱን እንደ ሉዓላዊ ግዛት በማሰብ በህገመንግስቱ ያልተፈቀደለትን አካሄድ እንደ መብት በመቁጠር ለኤርትራ መንግስት ደብዳቤዎችን በመፃፍ ግንኙነት ለማድረግ ሲሞክር ታይቷል፡፡ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በፌደራል መንግስቱ ታዞ ከዛላምበሳ በሚነሳበት ወቅት ያካባቢው ነዋሪ ያለመብቱ ገብቶ ለማዘዝ ሞክሯል፡፡ የክልሉ መንግስት በማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዝ ለስራ ጉዳይ ወደ ትግራይ የሚገቡ ወታደራዊ መኮንኖችን እና ተሸከርካሪዎቻቸውን አግቶ ለወራት በትግራይ አስቀምጧል፡፡ዶ/ር ደብረፅዮንን፣አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴን፣አቶ ጌታቸው ረዳን፣አቶ አባይ ፀሃይየን ጨምሮ አብዛኞቹ የህወሃት አባል የፓርላማ ተመራጮች ሌላው ቀርቶ ዶ/ር አብይ ፓርላማ በሚገኙባቸው ቀናት እንኳን የፓርላማ ወንበራቸው ላይ አይታዩም፡፡

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ፓርላማው ከፍተኛው የስልጣን ባለቤት ነው፡፡የፓርላማ አባላት የተባሉ ሰዎች በመርህ ደረጃ ይህን ከፍተኛ ስልጣን የተሸከሙ ግለሰቦች ናቸው፡፡ስልጣን ደግሞ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት ያለው ነገር ነው፡፡ የፓርላማ አባልነትን የመሰለ ክብር ያለው ሃላፊነት የተሸከሙ ሰዎች ከኔ ቢጤው ተራ ህዝብ ላቅ ያለ ህግ የማክበር ስብዕና ሊኖራቸው ግድ ነው፡፡በእኛ ሃገር በተለይ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የፓርላማ አባላት ላይ  እየታየ ያለው ፈለግ ግን ህግ አክባሪነትን የሚያንፀባርቅ አይደለም፡፡ የህዝብ ድምፅ ይሆናሉ ተብለው በክቡሩ የፓርላማ ወንበር የተሰየሙ አባላት አዘውትረው በፓርላማ ስፍራቸው ሲገኙ አይታይም፡፡

ይህ ነገር በህወሃት ባለስልጣናት በተለይ ባስ ይላል፡፡ ከላይ በስም የተጠቀሱት የህወሃት ባለስልጣናት የዶ/ር አብይን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በፓርላማ አዘውተረው ሲገኙ አይታይም፡፡ በተመሳሳይ የቀድሞው ጠ/ሚ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ ባላቸው አቶ መለስ ካረፉ ጀምሮ ወደ ፓርላማ ትውር ብለው አያውቁም፡፡ይብስ የሚገርመው ደግሞ ህግ-ይከበር ብለው ሰልፍ የሚወጡት/የሚያስወጡት እነሱው መሆናቸው ነው፡፡ከዚህ የምንረዳው ለነዚህ የህወሃት ባለስልጣናት ፓርላ የሚያስቀምጣቸው፣ሃላፊነቱ የሚጥማቸው፣ህግ አክባሪ ከእኔ በላይ ላሳር የሚያስብላቸው ሁሉ የተቆራኛቸው የስልጣን ጥም እንጅ ሌላ እንዳልሆነ ነው፡፡ባይሆን ኖሮ የአዲስ አበባውን ስልጣን ተነጥቀው ወደ መቀሌ በኮበለሉ ማግስት ስለ ህግ አክባሪነታቸው ሃያ ሰባት አመት ሙሉ ሲመፃደቁ መኖራቸውን ረስተው የፓርላማ ወንበራቸው ላይ እንኳን ያለመገኘት ተራ አመፀኛነት ውስጥ አይገቡም ነበር፡፡

እነዚህ ባለስልጣናት ፓርላማ አለመገኘታቸውን አስመልክቶ ሃይ የሚላቸው አካል የሌለ መሆኑ ደግሞ ኢህአዴግ መሪ በሆነበት መንግስት ህግ ምን ያህል መቀለጃ እንደሆነ ያሳያል፡፡መቼም የፓርላማ አባላት ስነ-ምግባር ከፓርላማ ስንት ቀን መቅረት እንደሚያስቀጣ ሳያስቀምጥ አይቀርም፡፡ፓርላማ ቀርቶ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ተማሪ ምን ያህሉን የትምህርት ቀን በክፍል ውስጥ መገኘት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ራሳቸውን እንደ ህግ አክባሪ በመቁጠር አትዝረፉ ያላቸውን ሁሉ በህገ-ወጥነት እየከሰሱ የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የነበሩ ግብዝ የህወሃት ባለስልጣናትም ከፓርላማ መቅረት ህጋዊ እንዳልሆነ አያጡትም፡፡ከፓርላማው የሚያስቀራቸው ጉዳይ ሌላ ነው-የአዲስ አበባውን ወንበራቸውን የማጣት እብድ የሚያደርግ ቁጭት፡፡

ሕወሃት ተበድሏል?

ሳያስቡት ከአዲስ አበባ ተባረው መቀሌ የከተሙት አዛውንት የህወሃት ባለስልጣናት ቁጭታቸውን ተንፈስ ሚያደርግላቸው እጃቸው ላይ የቀረ ነገር ቢኖር ስልጣናቸውን ለቀማቸው አካል ባለመታዘዝ ንቀታቸውን ማሳየት፣የወንበር ነጣቂያቸውን ሰላም ከሚያደፈርስ ጋር ሁሉ ማህበር መጠጣት ነው፡፡ከኦነግ ጋር ማዕድ ያስቆረሳቸው ይሄው ነው፡፡ ኦነግ በበኩሉ በኦዴፓ በሚመራው አዲሱ የለውጥ አመራር ላይ ቅሬታ አለበት፡፡

የዳኦድ ኢብሳ ኦነግ ዛሬ በኦዴፓ የኦሮሚያ ፀጥታ እና ደህንነት ሃላፊ ተደርገው የሾሙትን ጀነራል ከማል ገልቹን በኤርትራ በረሃ ደማቸውን ሊያፈስ አጥብቆ ይፈልጋቸው የነበረ ደመኛው ናቸው፡፡በዚህ ላይ ለውጡን የሚመራው ኦዴፓ “በታሪክ አማራ ኦሮሞን ሲበድል ኖሯል” የሚለውን የዳኦድን ኦነግ ፓርቲ ፕሮግራም የማዕዘን ድንጋይ አናግቶበት የሚያላዝንበት ሙሾ አሳጥቶታል፡፡በኦዴፓ አዲስ እይታ ሳቢያ የአማራ እና ኦሮሞ የጠላትነት ታሪክ ግርግዳ መፍረስ ምናልባትም ከኦነግ በላይ ህወሃትን እብድ በሚያደርግ የፖለቲካ ኪሳራ ላይ የጣለው ነው፡፡የአብይ/ለማ/ደመቀ/ገዱ ቡድን በህወሃት ላይ ያስመዘገበው አብረቅራቂ ስኬት ጅማሬም ፍፃሜም ይሄው ስልት ነው፡፡ይህ የለውጡ አመራር ስኬት ደግሞ የዳኦድን ኦነግ እና ህወሃትን እኩል ያከሰረ ስልት ስለሆነ ነው ሁለቱ ከሳሪዎች ግንባር መፍጠራቸው፡፡ በተመሳሳይ የጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ፀጥታ እና ደህንነት ሃላፊ መደረግ የዳኦድን ኦነግ እንዳናደደ ሁሉ የጀነራል አሳምነው ፅጌ የአማራ ክልል የፀጥታ እና ደህንነት ሃላፊ መሆን ደግሞ ህወሃትን ብግን የሚያደርግ የእግር እሳቷ ነው፡፡

ሌላው ህወሃት ተከፋሁበት የሚለው ነገር ሃገር ቆማ እንዳትሄድ አድርጎ ሲዘርፍ የኖረውን ሜቴክን ሲያጋፍሩ የኖሩት ጀነራል ክንፈ ዳኜው ሲያዙ በሃገሪቱ ቴሌቭዥን ቀጥታ መተላፉ፣እጃቸው ላይ ካቴና ገብቶ መታየቱ፣ሰውየው ይመሩት የነበረውን ሜቴክን ሁለንተናዊ ሌብነት የሚያሳይ ዲክመንተሪ ፊልም መሰራቱ ነው፡፡ክንፈ ዳኘው ሊያመልጡ ሲሉ የተያዙበት ሁኔታ ከቦታው በቀጥታ መተለላለፉም ሆነ ሰውየው ሲያዙ እጃቸው ውስጥ ካቴና መግባቱ ምንም ነውር ያለበት ነገር አይደለም፡፡ ይልቅስ ማንም ሰው ከህግ ስለማያመልጥ የፍርድቤት ጥሪ ሲደርሰው አክብሮ ህግን መጋፈጥ እንዳለበት፣ መሸሽ እንደማያዋጣ ትምህርት ይሰጣል፡፡የጀነራል ክንፈ ጉዳይ በፍርድ ቤት ተይዞ ሳለ ጉዳዩን አስመልክቶ ዶክመንተሪ ፊልም መስራቱ ይልቅ ጥፋት ነው፡፡ ኢህአዴግ ይህን አባዜውን ሊያቆም ይገባዋል፡፡

በተረፈ ተጠርጣሪ ወንጀለኛው እጅ ላይ ለምን ካቴና ገባ የሚለው ነገር ከህወሃት ሲመጣ የሚያስመሰክረው የህወሃትን ድልብ ዘረኝነት ነው፡፡ምክንያቱም ይህን ወንጀል አድርጎ የሚያወራው ህወሃት ራሱ ክስ ፈብርኮ በከሰሳቸው መናኝ መነኮሳት ሰላላ እጅ ውስጥ ካቴና አስገብቶ፣ እንደ በግ አቆራኝቶ አስሮ ሲያንገላታ የኖረ፣እነ ኡስታዝ አቡበክርን፣እነ አንዱአለም አራጌን፣እነ ዶ/ር መረራ ጉዲናን በካቴና ጠፍንጎ አስሮ በቴሌቭዥን ሲያሳይ የነበረ ግፈኛ መሆኑ ነው፡፡ አሁን የክንፈ ዳኘው ልዩ ሆኖ የታየው ክንፈ ዳኘው “ወርቅ ነው” እያለ ከሚያወራለት ዘር የተገኙ የወንዙ ሰው ስለሆኑ ብቻ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ህወሃት ይሄ እበልጣለሁ ባይነቱ ከዙፋኑ ባፍጢሙ እንደደፋው እስከ ዛሬ እንኳን አለመገንዘቡ ነው፡፡

ሌላው የህወሃት ትልቅ በደል እንደደረሰበት አድርጎ የሚያቀርበው ነገር ፓርቲው  ሲያጋፍረው በኖረው የደህንነት መስሪያቤት አዛዥነት በሰው ልጆች ላይ ሲደረግ የኖረው አረመኔያዊ የሰብዐዊ መብት ጥሰት በሃገሪቱ ቴሌቭዥን መጋለጡ፣ ሲጋለጥ ደግሞ ተጎጅዎቹ “የገረፉን ትግርኛ የሚናገሩ ሰዎች ናቸው” ማለታቸውን ነው፡፡ይህን የሚለው ህወሃት ሃገሪቱን በሚዘውርበት ዘመን የህወሃቱ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ተገኝተው የካቢኔ ሹመት ሲያፀድቁ ከእጩዎቹ ስም ቀጥለው የሚጠሩት ዘራቸውን እንደነበር ማንም አያጣውም፡፡ህወሃት ባዋቀራት ኢትዮጵያ ለመሾም ለመሻር፣ለመግረፍ ለመገረፍ፣ነግዶ ለማትረፍ ለመክሰር፣ለመውጣት ለመግባት ሁሉ ዘር ሳይጠራ አይሆንም፡፡ ስዚህ  የገራፊ ዘር ሲጠራ ሰማይ እና ምድር ቦታ የተቀያየሩ ማስመሰሉ ቅን ነገር አይደለም፡፡ የገራፊ እና የተገራፊ ድልድል ለማድረግ ዘር መስፈርት መሆኑም የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ገራፊ ለመሆን ወንበር ላይ የተቀመጠውን ባለጊዜ የልብ የሚያደርስ ዘር ባይፈለግ ኖሮ ገራፊው እና አሳሪው ሁሉ ከአንድ ዘር በልሆነ ነበር፡፡በአጠቃላይ ዘር ሳይጠራ ምንም የማይደረግበት ሃገር በራስ እጅ ካበጃጁ በኋላ ለምን የገራፊ ዘር ተጠረራ ብሎ ተበደልኩ ማለት ትርጉም የለውም፡፡

የአማራ ክልል እና የራያ ወጣቶች ወደ ትግራይ የሚሄደውን መንገድ ሲዘጉብን የዶ/ር አብይ መንግስት ዝም ማለቱም አስከፍቶናል ባዮች ናቸው ህወሃታዊያኑ፡፡መንገድ መዘጋቱን ብቻ ሳይሆን ለምን ተዘጋ ብሎ መጠየቅም ያስፈልጋል፡፡የራያ ህዝብ መንገድ የዘጋው ማንነቴ ትግሬ አይደለም በማለቱ ሳቢያ የትግራይ ልዩ ሃይል በጥይት ስለቆላው ነው፡፡በአማራ ክልል በኩል ያለውን መንገድም እንዲሁ የአማራ ህዝብ በህወሃት ተዘቅዝቆ ሲገረፍ የኖረ በመሆኑ በመሰለው መንገድ ቅሬታውን ማሳየቱ ነው፡፡

በፌሮ ሲገረፍ የኖረ፣በማንነት ጥያቄው ላይ ሲሾፍበት የኖረ ህዝብ ለተወሰነ ቀን መንገድ መዝጋቱ እሪ ሊያስብል አይገባም፡፡ የሚያዋጣው ስህተትን አምኖ ለበደል ይቅርታ መጠየቅ እንጅ ስገርፍ የኖርኩት ህዝብ ዘንባባ ያንጥፍልኝ የሚል ትዕቢት አይደለም፡፡ በዚህ ላይ የቆየውን ያህል ቆይቶም መንገዱን ያስከፈተው የዶ/ር አብይ መንግስት መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ የዶ/ር አብይ መንግስትም ቢሆን ህዝብ ቅሬታውን ማቅረብ ያለበት መንገድ በመዝጋት እንዳልሆነ ህዝብን ቀርቦ እስኪያስረዳ ቀናት እንደሚያልፉ መገንዘብ ከባድ ነገር አይደለም፡፡አብይ መንገዱ የተዘጋ የዕለቱ ዕለት ከዙፋኑ ወርዶ ሲገሰግስ አድሮ ለምን በማግስቱ አላስከፈተልንም የሚለውም እበልጣለሁ ባይነትን የተሸከመ ትዕቢት ያለበት ክርክር ስሆነ የሚያስኬድ ነገር አይደለም፡፡

ከሁሉም በላይ ህወሃት መንገድ ተዘጋብኝ ብሎ በሚጮህበት ወቅት ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ እሪ የማይሉ ግን ለወራት መንገድ ተዘግቶባቸው ያሉ ወገኖች ነበሩ፤ወለጋ ላይ በጥይት የሚቆሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ወቅቱ የሽግግር እንደመሆኑ፣ህወሃት ደግሞ ደህና በመስራት የማይታወቅ ፓርቲ እንደመሆኑ ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ ባልጠየቀበት ሁኔታም ሁልቀን ፋሲካ መጠበቅ የለበትም፡፡ህወሃት ራሱ በሰጣት የቤት ስራ ምክንያት እየታመሰች ባለች ሃገር ለምን የኔሰፈር ብቻውን በቸር ውሎ አላደረም ማለት፣ይህንንም አምርሮ ማራገብ ክፉ ራስ ወዳድነት ነው፡፡

በሙስና እና በሰብዐዊ መብት ጥሰት የተጠየቁ አመራሮች ሁሉ ህወሃቶች ብቻ ናቸው፤ይህ የሆነው ደግሞ የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ነው የሚለው ሌላው ህወሃቶች ተለይተን ተጠቃን የሚሉበት ነገር ነው፡፡ ለዚህ ነገር የመጀመሪያው ክርክር በወንጀል መጥሪያ የተቆረጠባቸው ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ህወሃቶች ብቻ አይደሉም፡፡ህወሃቶች ብቻ የሆኑት የፍርድቤት መጥሪያ ተቆርጦባቸው ሳለ ለህግ አንታዘዝም ብለው በትውልድ ቦታቸው የከተሙት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ናቸው፡፡ ለተጠርጣሪ ወንጀለኛ የወንዙ ልጆች ዘር ቆጥሮ መጠለያ እየሰጠ ያለውም የትግራይ ክልላዊ መንግት ብቻ ነው፡፡ እነ ያሬድ ዘሪሁን፣ተስፋየ ኡርጊ፣ጠና ቁርንዲ ወዘተ ትግሬዎች ያልሆኑ፣የክልላቸው መንግስትም ዘር ቆጥሮ ያልደበቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በተረፈ ወደፊትም በተጠያቂነቱ ዝርዝር  የህወሃት ሰዎች በርከት ብለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ይህ ህወሃት ከመባረሩ በፊት መስርቶት የነበረው ስርዓት የወንዝ ልጆች ተጠራርተው፣ፍትሃዊ ባልሆነ ሁኔታ የሃገሪቱን ሁለመና የመዘወራቸው ነፀብራቅ እንጅ እንደሚያወሩት ትግራይን የማጥቃት ሃራራ ያለበት መንግስት ስለመጣ አይደለም፡፡ የሃገራችን መንግስት ህወሃትን የማንበርከክ ጥማት አለው ቢባል እንኳን ልዕለ ሃያሏ አሜሪካ ጌታቸው አሰፋን የምትፈልገው ትግራይ ተንበርክካ ለማየት ካላት ክፉ ምኞት ሊሆን አይችልም፡፡ ማገናዘብ ደግ ነው!

ህወሃት እንዴት አደብ ይግዛ?

ወንጀለኛ ሰብስቦ የያዘው፣የፌደራሉን መንግስቱን በግልፅ ሃገር ማስተዳደር የማይችል ነው የሚለው የትግራይ ክልልን የሚመራው የህወሃት አዛውንቶች ስብስብ በሃገር ላይ ሌላ ሃገር መስርቶ የመኖሩ ነገር ሊያበቃ ይገባል፤በክልሉ የከተሙ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችም ከህግ በላይ አለመሆናቸው ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡ካልሆነ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ ለውጥ ውስጥ ነኝ ብላ መናገር አትችልም፡፡ትዕግስት የህግ የበላይነትን ተፈታትኖ፣አለቃ እና ምንዝር የማይታወቅበት ስድ ፖለቲካ እስኪያመጣ ድረስ ልቅ መሆን የለበትም፡፡

የትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት ስር እንደመሆኑ መጠን በክልሉ ያሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን እንዲሰጥ መለመን ሳይሆን መታዘዝ ነው ያለበት፡፡ለወራት ወንጀለኛን ደብቆ ያስቀመጠው የትግራይ ክልል መንግስት ውንጀል ሰርቷልና ከደበቃቸው ወንጀለኞች እኩል መጠየቅ አለበት፡፡ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙት የክልሉ ፕሬዚደንት ዶ/ር ደብረፅዮን በተለይ በግምባር ቀደምነት መጠየቅ አለባቸው፡፡ይህን ለማድረግ እንደ መንግስትም እንደፓርቲም እርምጃዎችን መውሰድ ይቻላል፡፡

እንደ መንግስት የትግራይ ክልል መንግስት ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹን ለፌደራሉ መንግስት የሚያስረክቡበት የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ የመጀመሪያው እርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡ በጊዜ ገደቡ የማያቀርቡ ከሆነ በሚኒስትሮች ምክርቤት አስወስኖ የዶ/ር ደብረፀዮንን ያለመከሰስ መብት ለማንሳት በፓርላማ ማስወሰን፡፡ወንጀለኛ የደበቀ ወንጀለኛ ነውና ደብረፅዮንም ከተፈላጊ ወንጀለኖች ዝርዝር  ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡ክልሉ ደግሞ በታዳኝ ወንጀለኛ መመራት ስለሌለበት የፌደራል መንግስቱ በደብረፅዮን ለሚመራው የክልሉ መንግስት እውቅና መንፈግ አለበት፡፡እንደ መንግስት ይህን ካደረጉ በኋላ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ተሰብስቦ  ህገ-ደንቡን በተከተለ ሁኔታ በህወሃት ላይ ቅጣት መጣል አለበት፡፡ይህ ሁሉ ሆኖ ካልሆነ መንግስት ለክልሉ የሚሰጠውን የበጀት ድጎማ እስከ ማቆም የሚሄድ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡